fa
Feedback
ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️

ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️

رفتن به کانال در Telegram

ምድር እጅግ ሰፊ ናት፤ እኔ ወንድማችሁ በርናባስ ደግሞ ያሉኝ ሁለት ዐይኖች ብቻ! አባካችሁን ኑ...ና አጋጭተን (ዐይኖች አዋጥተን) እንይ!✍️ አሳብ አስተያየት ቢኖራችሁ፦ @barnica የግላችሁ ነው።

نمایش بیشتر
1 408
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
-830 روز

در حال بارگیری داده...

ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
سپتامبر '26
سپتامبر '26
+14
در 0 کانال‌ها
اوت '26
+28
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '26
+13
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '26
+13
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '26
+20
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '26
+19
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '26
+22
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '26
+120
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '26
+10
در 1 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '25
+19
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '25
+15
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '25
+29
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '25
+7
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '25
+10
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '25
+22
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '25
+4
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '25
+6
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '25
+4
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '25
+3
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '25
+5
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '25
+6
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '24
+11
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '24
+21
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '24
+27
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '24
+16
در 1 کانال‌ها
Get PRO
اوت '24
+19
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '24
+11
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '24
+5
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '24
+24
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '24
+16
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '24
+22
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '24
+17
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '24
+24
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '23
+15
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '23
+12
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '23
+17
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '23
+27
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '23
+31
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '23
+15
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '23
+16
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '23
+21
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '23
+21
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '23
+15
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '23
+6
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '23
+59
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '22
+21
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '22
+14
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '22
+15
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '22
+20
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '22
+24
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '22
+15
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '22
+13
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '22
+24
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '22
+28
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '22
+28
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '22
+37
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '22
+18
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '21
+17
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '21
+12
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '21
+9
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '21
+19
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '21
+8
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '21
+28
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '21
+32
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '21
+37
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '21
+24
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '21
+62
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '21
+327
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '21
+53
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '20
+2 113
در 0 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشارات
کانال‌ها
30 سپتامبر+2
29 سپتامبر0
28 سپتامبر+1
27 سپتامبر+1
26 سپتامبر0
25 سپتامبر0
24 سپتامبر0
23 سپتامبر0
22 سپتامبر0
21 سپتامبر0
20 سپتامبر+1
19 سپتامبر0
18 سپتامبر0
17 سپتامبر+1
16 سپتامبر0
15 سپتامبر+1
14 سپتامبر+1
13 سپتامبر0
12 سپتامبر0
11 سپتامبر0
10 سپتامبر+1
09 سپتامبر+2
08 سپتامبر0
07 سپتامبر0
06 سپتامبر0
05 سپتامبر0
04 سپتامبر+1
03 سپتامبر+1
02 سپتامبر0
01 سپتامبر+1
پست‌های کانال
ስለ ቤቱ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው? ሀ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክሩ ይጸና ዘንድ ሕዝብ ያሻዋል። ለ) እንደው ደከማችሁ እንጂ አሁን ያለንበትን ኑሮ ለመግፋት እኮ ምክሩም ቤቱም ብዙ አስፈላጊ አልነበረም። ሐ) ሲጀመር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምንድነው? የእኛ ሕዝብ ሁነኛ ተወካይ ኖሮት ያውቃል? መ) ቆይ ግን እርሱ ቤት በባለ ቤትነት የማነው? ምክሩ ለሕዝቡ ነው ተብሏል! የቤቱስ ኋላ ኋላ የማን ይኾን? ሠ) እኔ እንጃ! አታነካካኝ። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

2
"ሴትነት ታማኝነት!" ---👁--- ከበርናባስ በቀለ ከቀናት በፊት ወደ ክፍላገር ስጓዝ የአውቶቡስ ጉዞዬን ጨርሼ ዶልፊን በሚሉት ሚኒባስ ወደ ተልዕኮዬ መዳረሻ ከተማ እየከነፍን ነው። በሾፌሩና እኔ መካካከል አንዲት ወጣት ልጅ አለች። ከሾፌሩ ጋር የቀደመ ትውውቅ ያላቸው መስሎኛልና ጸጥ ብዬ እየተጓዝሁ በጥቂቱ እሰማቸዋለሁ። በመካከል ሾፌሩ "እኔ ሴቶችን አላምንም! በፍጹም። ስንት ጊዜ ጉድ ተደርጌአለሁ?" ብሎ መሪውን እየደበደበ ያስረዳታል። "ይህን ስል ታዲያ በዓለም ሁሉ የተረጋገጠ ስለሆነ ማንም እንዲያስረዳኝ አልፈልግም!" እያለ በአንድ ዐይኑ ይሾፈኛል። ነገር እንደፈለገኝ ገብቶኛል። በሴቶች ስብዕና እና ክብር ጉዳይ ደግሞ ማን ብሎኝ! በመካከል "ትክክል አይደል ወንድሜ?" አለኝ። እኔም፦ በፍጹም እንደርሱ አላስብም። የሚገርምህ ያንተና የእኔ ልዩነት የሰማይና የምድር ያህል ነው። እኔ ደግሞ ሴቶችን ሳምናቸው እኖራለሁ። ሲጀመር ከሴት ውጭ ለታማኝነት ሞዴል ሆኖ የሚቀርብ ፍጥረት አለ? የ"ሴትነት" ሌላኛው ትርጉሙ "ታማኝነት" መሆን አለበት ባይ ነኝ። እኔ ሚስቴን አምናታለሁ! ሴት ልጆቼን አምናቸዋለሁ። እናቴን እህቴንም አምናታለሁ። የሥራ (የተልዕኮ) አጋሮቼን ሳምናቸው ኖሬአለሁ። "አንተ ለምን ሴትነትን አምነኻቸው በከዱህ ሴቶች ትለካለህ?" የሚል ጥያቄ አስከተልሁ። "ውይይ! ወንድሜ! ተበልተሃል! አለቀልህ!" አለኝ። ቀጥሎም "ግን እንዴት ነው የሸወዱህ? የምር አመንካቸው? እግዚአብሔር ይድረስልህ!" እኔም ምናልባት ሰው ለማመን የሚቸገሩ ሰዎች ለራሳቸው የማይታመኑ ሰዎች ናቸው ሲባልስ ሰምተህ ይሆን? መካከላችን ያለች ልጅ "እኮ!" ትላለች። ልጁ ጸጥ ብሎ ይሰማኝ ጀመር። ኋላም "የሴቶች ቀን" የሚለው አዚሁ ያለው ልጥፌን አውጥቼ ስለ ሴት ልጅ ክብርና ስብዕና አነበብኩለት። ኋላም ረጅም አወራን። "እንኳን ለእኔ ለአገር የምትታመን ሚስት አለችኝ" ስለው "ታድላ እንዴት ይህ ሁሉ ሰው ተሸወደላት?" ሲለኝ እየሳቅሁ ደውዬላት የጨዋታው መስመር ላይ አስገባኋት። መጨረሻ ላይ ግን በአንድ ጉዳይ ተስማማን ሴትን ልጅና ስለ ሴት ልጅ በቅጡ እንደማያውቅ። የወንድነትን ጥሪ (mission) እና ሚና (role) በትክክል ሳይወጣ ሴትነትን ሲራገም የቆየ ሰው ስለመሆኑን። ታዲያ ልጅት አንጀቷ ቅቤ ጠጣ! በቃ እንደዚህ አይነት ሰዎች ናቸው የሚያስፈልጉን አለች። እኔም ምንም የተለየ አላደረኩኝም ስለ እህቶቼ ማሰብና መሆን የነበረብኝን ነው ያደረግሁት አልኩኝ። ሴትነት ጥልቅ ሚስጢር ነው! ክቡር ማንነትና ስብዕና ነው። የእውነት ላመኗቸው የሚታመኑና ለቃላቸው ሟች ጭምር ናቸው። በዚህም እንወቃቸው!!!! ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
177
3
ስለ ጥቂቶች የግል interest በሚደረግ ጦርነት ለሰይፍና እልቂት ስለተዳረጉ ንፁሃን ወንድም እህቶቼ በጣም አዝናለሁ። ስለ ኃያላን ርግጫ ዋጋ ስለሚከፍሉ ጥቂት ድኩማን ልቅሶዬ ይቀጥላል። ከወዲህም ከወዲያም ስለ ታጠቁ ኃይሎች ልፊያ ስለ እለት ጉርሱ የሚጋደል ነፍሱን ሲሰዋ እየሰማሁ እንዴት ያስችለኛል? የምር ሃዘኔ ጥልቅ ስብራቴም ብዙ ነው። 😥 ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
304
4
Please ይህን ቼክ አድርጉት ⚠️ ሰሞኑን ቴሌግራም ላይ ጽሑፎቼን ስለጥፍ ቴሌግራም ማስታወቂያዎችን ከፖስቶቼ ቀጥሎ እያኖረ እንደሆነ ጥቂት ወዳጆቼ መረጃ ሰጥተውኛል። እኔ በዚህ ቻናል ምንም አይነት ማስታወቂያ አልለጥፍም። ግን ቴሌግራም በራሱ እያደረገው ነው። ምናልባት የማስታወቂያዎቹ ይዘቶች እኔን የማይወክሉኝ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስባለሁ። ብዙዎቻችሁ ጋር ራሱ መርጦ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን እየላከ ስለሆነ እኔ አልቆጣጠረውምና understand አድርጉኝ። ከቻናሉ ተጨማሪ Admns ጋር በመሆን ማስታወቂያ ለማጥፋት ስንሞክር "ከማስታወቂያ ነጻ የምትሆኑት Telegram Premium ሲኖራችሁ ብቻ ነው!" ብሎናል። ስለዚህ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም። እስቲ በጉዳዩ የተሻለ መረዳት ያላችሁ አናግሩኝ። እናንተስ ጋር ከጽሑፌ ጋር ማስታወቂያ መጥቶ ያውቃል? እርሱንም ብታሳውቁኝ ምን አይነት ማስታወቂያዎች እየተሠሩ እንደሆነ እንዳውቅ ይረዳኛል። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
395
5
ሁለቱ አንዶች! --👁--- ከበርናባስ በቀለ ሚስቴ፦ "ባርኒ ከአንድና ከሁለት" እኔ፦ ሁለት። ሚስቴ፦ "በቃ እሺ፣ ጠብቀኝ።" እኔ፦ ምን አስበሽ ነው? እርሷ፦ "መክሰስ ምን እንብላ የሚለውን ለመወሰን ነው።" እኔ፦ "ቁጥሮቹ ምን ነበር የያዙት?" ሚስቴ፦ "➊ ፓንኬክ ➋ በሶ ጁስ' እኔ፦ እና አሁን መክሰስ በሶ ጁስ ሆኗል ማለት ነው? ሚስቴ፦ "አዎን።" እኔ፦ እማ... እኔ እኮ ሁለትን የመረጥኩት አንድ በውስጡ አለ ብዬ ነው። መቼስ በሂሳብ ቀመር ሁለት ብቻውን ያለ ቁጥር አይደለም። አንድን በውስጡ ሸክፎ ይዟል። ሲጀመር ሁለትን ሁለት ያሰኘው አንድ ነው። ምን እርሱ ብቻ፣ እንደውም ሁለት ማለት "ሁለት አንዶች አንድ ላይ ሲቆሙ ነው!" ሚስቴ፦ "እና ምን ልትል ነው?" እኔ፦ አይይ! ነገሩን እኮ ነው። ሚስቴ፦ "ባርኒ ቁጥር አታጭበርብር፣ አሁን አርፈህ ወደ በሶ ጁስህ።" ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
344
6
"በነገራችን ላይ አይጎድልም። ጎደለ የምትለው የምትመኘው ነገር ሲኖር ነው። ምኞትህን መግታት ከቻልክ የሚጎድልህ ነገር የለም። ምኞትን መግታት ነው።" (አለማየሁ ገላጋይ) ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
311
7
ኮፊያዬ ጉድ አደረገኝ! ---👁--- ከበርናባስ በቀለ ታከለ በጣም የምወደው ጓደኛዬ ነው። የአባቱን ስም እዚህ የማልጠቅሰው ነገሩን private ላድርገው ብዬ ነው። እርሱን የምታውቁ ጽሑፉን የበለጠ እንድትረዱት ፍንጭ ልስጣችሁ። ታኬ ዘማሪ ነው (የድሮ ዘማሪ)። ላለፉት አስራ አመታት የቆየ ጥሩ ተልዕኳዊ ቁርኝት አለን። በየመስካችን ተሰማርተን ረጅም ተጠፋፍተን ስንገናኝም ካቆምንበት የምንቀጥል አይነት ሰዎች ነን። ስልኬ እንደወትሮው ሁሉ ዝግ አይደል! አመሻሹን ስልኬን ቼክ ሳደርግ ወዳጄ ታከለ ሲሞክርልኝ እንደዋለ 824 አሳወቀኝ። እኔም ሙሉውን ቀን ይህ ሁሉ "የአሳውቁኝ ምልክት" እንዲሁ አይሆንም ብዬ ደወልኩለት። ታኬ ስልኩን አነሳ፦ "ባርኒ ነግሬሃለሁ! ቲክቶክ ላይ "ስልቻና ቀልቀሎ" በሚለው ቪዲዮህ ላይ ገርግደህ የቆምከውን ኮፊያ ከቤትህ አስወግድ! በጣም ነው የሚያስጠላው። ደግሞ ኮፊያ አይኼድብህም! ሲጀመር ኮፊያ አታድርግ። ያንን ኮፊያ ደግሞ ከቤትህ አስወጣ። አንተና እኔ በምናውቀው 'መብራት ኃይል' ግቢ የነበረ ዋርካ ታውቃለህ? እርሱን ነው የሚመስለው! ትልቁን ዋርካ። 'የጎፋ በራሪ' ታውቃለህ? በቃ እንደርሱ ነው የምትመስለው። በቃ ደስ አይልም። መልእክትህ እኮ አስደንጋጭና ልብ የሚገዛ ነው። ግን ኮፊያህ ራሱ ቀልቀሎ ነገር ነው! በቃ እርሱን ኮፊያ አሁን አስወግድ። ቤት ገብተሃል? በል አውጥተህ ጣለው። ሆሆሆ! እንደዚህ የሚያምር Content በዚህ ኮፊያ ይዘህ ትመጣለህ? ደግሞ ምንድነው አቋቋምህ? ስክሪኑን ሞልተሃል! ሸንቀጥ በል። ጸጉርህን ደግሞ ሙልጭ አድርገህ አታስነሳ። ከፊት የተወሰነ አስቀር! ምንድነው ይኼ ሜዳ!? አንተ በዚያ መንገድ ወደ ሚዲያ ለመምጣት ማመንህ ቀላል አይደለም! ግን በቃ እኛንም ስማን! ይህን ኮፊያ ከስወግድ።" ንግግሩን ጨረሰ። እኔ መንገድ ላይ በሳቅ ፈረስኩኝ። ከትራንስፖርት እንደወረድሁ ነበርና ከፊቴም ከኋላም ያለው ሰው "መጥኔ ይስጠው!" እያለ ያየኛል! ታኬ እኮ በስርዓት እንኳን ሰላም አላለኝም። ደግሞ ቁጣው! (ታላቄ ስለሆነ ቁጣውን እወደዋለሁ)። ግን በጣም አስቆኛል። በቃ ደንግጬ የምለው ጠፍቶኛልና "በቃ ታኬ ኮፊያውን አሁን አስወግደዋለሁ!" አልኩት። ሳቄን ቀጠልኩኝ! ከማን ጋር ልሳቅ? ታፍኜአለሁ። ቤት ደርሼ ለሚስቴ እስክነግራት ቸኩዬአለሁ፤ የታኬ ቁጣ ፊቴ ላይ አለ። እንደገባሁ ሚስቴንና ልጄን ሰላም ሳልል ጭምር ኮፊያውን ካለበት አንስቼ መጣል እንዳለብኝ ነግሮኛልና ላደርግ የምችለውን እያሰብኩ ነው። አንድ ታኬንና ነገረ ሥራውን የሚያውቅ ሰው ጋር መደወል እንዳለብኝ ተሰማኝ። ብሩኬ ጋር ደወልኩኝ። ብሩኬን እወደዋለሁ። የገባውን ሕይወት ለመኖር የሚጥር ሚስኪን ወጣት ነው። ላለፉት 17 አመታት ገደማ ታኬን Commonly እናውቀዋለን። ሲያወራ የፊቱን ገጽታ እንወደዋለን። ለብሩኬ የሆነውን ሁሉ ነገርኩት! ብሩኬም በሳቅ ነፈረ። እርሱንም (ብሩኬንም) አንተም ኮፊያ አለህና እንደ እኔ ሰው እንዳታሰናክል ተጠንቀቅ አልኩት። ሲጀመር ከብሩኬ ኮፊያዎች አንድ የማልወደው "የሚልሻ ኮፊያ" የሚመስል ኮፊያ አለና በተራዬ "ያንን ኮፊያ አስወግድ!" አልኩት። አሁን ሳስበው ለአቤኒ መለሰም መደወል ነበረብኝ። አቤኒም ቨዲዮውን አይቶታልና የታኬን reaction ነግሬው ቢሆን ስስር አድሬ ሆዴ ይቆስል ነበርና እንኳን ቀረብኝ። ለማንኛውም አቤኒ (Ab) እዚህ መድረክ ላይ አለህና ይህን ጉድ ስማ። ጉዳዩ በቀጥታ የማይመለከታችሁ ሰዎች ረጅም ጽሑፍ በማንበብ ዛጋችሁ አይደል? ይቅርታ። ግን የታኬ reaction አይገርምም? ባለፈው ጽሑፌ ላይ እኮ ሚስቴ ስለ ኮፊያው ያለችኝን እዚሁ ጽፌአለሁ። "መልእክቱ ጥሩ ነው ግን ጢምህና ኮፊያህ (በቃ ነገረ ሥራህ) ደንበኛ ሀዘን ላይ ያለህ ይመስላል!" ብላኛለች። ይኸው የታኬ ተደገመ። ታኬ ደግሞ "ኮፊያው አናትህ ላይ ትልቅ ዋርካ ያስገጠምክ ነው የሚመስለው" ይለኛል። አንተ ደግሞ "የጎፋ በራሪ ነው የምትመስለው" ይለኛል። የጎፋ በራሪ ምንድነው እርሱ? ጠይቄው አልነገረኝም። 😁 ደግሞ ኮፊያ አስወግድ! አይኼድብህም ይለኛል እንዴ?😥 "የኮፊያ አገሩ አንተ ነህ!" ያሉኝ ጓደኞቼ መልካም ቃሎችስ? የምራቸውን አልነበረም ማለት ነው? "ቡና ካልጠጣህና ኮፊያ ካላደረግህ አንዳንዴ ወሰድ ያደርግሃል ብዬ ነው!" ብሎኝ ከባዕድ ምድር ውስጡ የወታደር ትጥቅ ያለው የሚመስል ኮፊያ ያመጣልኝ ፋኑኤልስ ይህን ለምን አልነገረኝም? ያንን ተጨማሪ ኮፊያ ሲሰጠኝ ሌላ መጥፊያ እየጨመረልኝ ነበር ማለት ነው? እንደ ተልዕኮ የቅርብ አጋሬ ኮፊያ እንደማያምርብኝ እርሱ አይነግረኝም ነበር!? ፋኑ አንተም ተይዘሃል። ወይም የጠቀስኋችሁን ሁላችሁንም አንድ ቀን እዚሁ Live ላስገባና አንዳችሁ ለሌላችሁ መልስ ትሰጣላችሁ። አንዳንዶቻችሁ ኮፊያ ስትገዙልኝ አንዳንዶቻችሁ "አያምርብህም!" ስትሉኝ እሺ እኔ ማናችሁን ልስማ? ለታኬስ ምን ልመልስለት? ዛሬ እኮ ደውልልኝ ብሎኛል። ቆይ አሁን ከምሳችን በፊት ለSolም እነግረዋለሁ። እርሱም ባለ ኮፊያ አይደል! ወይ አያምርብህም ይለኛል! አለዚያም አንድ ክፊያ ይገዛልኛል then 5 ኮፊያዎች ይኖሩኛል። እናንተስ? እውን ግን ቪዲዮው ላይ ኮፊያዬ እንዲህ የሚጨንቅ ነው? ሲጀመር የኮፊያ ሰው አይደለህም! ነው የምትሉኝ? ወይስ ኮፊያ ትገዙልኛላችሁ? ማሳሰቢያ፦ አሁን ያሉኝ አራቱም ኮፊያዎች ጥቁር ናቸው። ታኬ የሥራውን ይስጠው! ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
399
8
ዛሬ ደግሞ "የኔ ተራራ" የተሰኘው ከዚህ በፊት ብዙዎቻችሁ የወደዳችሁት ራስ ታዘብ ሙግቴ በቪዲዮ መልክ እዚያ (አዛጦን) መንደር ቀርቧል። ቪዲዮው ሁለተኛው በመሆኑ ከትላንትናው የተሻለ ነገር ያለው ይመስለኛል። ግን ምንም ብትሉኝ ፊት ለፊት ማውራትን የመሰለ ነገር የለም። ጥቁር ብረት ላይ አስፈጥጠውኝ ያስወሩኝ ጀመር እኮ። ለማንኛውም ግን ቪዲዮው ተጥዷል ለማለት ነው። https://vt.tiktok.com/ZSqpv93vy/ ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
319
9
በጥቂት ሰዎች ጉትጎታ "ትዝብተ-በርናባስ" ወደ ቲክቶኩ መንደርም ተዘርግቷል። የመጀመሪያው ቪዲዮ "ስልቻና ቀልቀሎ" በተሰኘ ከቀናት በፊት ባጋራኋችሁ ጥንቅር ጀምሯል። https://vt.tiktok.com/ZSqqTbnvo/ እኔ የቪዲዮ ሰው አይደለሁም። ካሜራ ፊት ማውራቱም የጸጋ ስጦታዬ አይደለም። መልእክቶቼን በድምፅ ባጋራ እመርጣለሁ። የማኅበራዊ ሚዲያ አማካሪዎቼ ደግሞ ፊትህም መቅረብ አለበት ብለውኛል። እንግዲህ እጥራለሁ ብዬአለሁ። ከእናንተም በቪዲዮ ሥራ ጥሩ የሆናችሁና ምቹ ጊዜ ብሎም skill ያላችሁ እዚህ የሚቀርቡትን ይዘቶች ወደዚያ ላሉትም ማድረስ እንችላለን። ዝርዝር ሃሳቦቹ ላይ እንመካከር ዘንድ ጻፉልኝ። የዛሬዋን ቪዲዮ ግን ኼዳችሁ ጎብኙ፣ ለሌሎችም አጋሩ። ንፁህ መውደዴ የገባችሁበት ገብቶ ያግኛችሁ። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
429
10
ቡና ወይስ አልኮል? ---👁---- ከበርናባስ በቀለ ...ከምሳ በኋላ ቡና እየተፈላ ነው። ሚስቴ፦ አልኮል እንደማትጠጣ አውቃለሁ። "ቡና ውስጥ አልኮል ተገኝቷልና ከእንግዲህ መጠጣት የለባችሁም!" ተብሎ ቢደነገግ ምን ትሆናለህ? ቡና ታቆማለህ? እኔ፦ አልኮል በይፋ መጠጣት እጀምራለሁ! ሚስቴ፦ "እንዴ ለምን!? (ረጅም ሳቋን አስከትላ)" እኔ፦ ታዲያ ላለፉት አስርት አመታት አልኮል (ቡና) ስጠጣ ከርሜ የለ። ቡና ጠጥቼ ከማንም ተጣልቼ (ሰክሬ የሰው ንብረት አይቼ) አላውቅም። ስለዚህ አልኮል መጠጥ በይፋ ጀምሬአለሁ ብዬ አውጃለሁ። የምጠጣው አልኮል ግን አንድ ብቻ ይሆናል፦ ይኸውም ቡና። ☕ ሚስቴ፦ "ሥራህ ይፍረስ (ረጅም ሳቅ) ሃሳብህን አልስተውም እኮ። እንዲህ ልትል እንደምትችል ገምቻለሁ" 😊 እኔ፦ ቡናው ይፍጠንና እየጠጣን እናፈርሳለን! ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
492
11
ውስንነቴ ትልቁ ድካሜ። ይህን ያወቀና በቅጡ የተረዳ ደግሞ እውነተኛው ወንድሜ!
569
12
ስለ ወዳጅነት እግዚአብሔር ቸር ነው። ምህረቱም ለዘላለም! ሰው ግን ውስን ነው ለሕያውነቱ ከርሱ (ከእግዚአብሔር) በሚመጡ መግቦቶች የሚኖር። ሰው ድካሙ ውስንነቱ ነው። "ለምን ድካም ይታይበታል?" ስትሉ "ለምን ውስን ይሆናል?" እያላችሁ እንዳይሆን ፍሩ። ስለ ሰው ልጆች ድካም ረጅም አታውጠንጥኑ፤ በድኩማኑ ሰዎች ስለተገኙ ጥቂት መልካም ነገሮች ተደነቁ። በሁሉ ጥንቁቅ እንደሆነ ለሚነግራችሁ ወዳጃችሁ እርሱ በፍጥረቱ ውስን እንደሆነ ንገሩት። አንናንተም ከሰዎች ጋር ኅብረት ስትጀምሩ ውስንነታችሁ የሚጎላበትን አቅጣጫ (ድካማችሁን) በግልጽ አሳውቁ። ደካማውን ፍጥረት ቀርባችሁ (ወዳችሁት) "ለምን ደክምክ?" እንዳትሉት ተጠንቀቁ። ይልቅ በድካሙ በኩል ልትቆሙለት እንደመጣችሁ አስቡ። እርሱም ደግሞ በእናንተ ድካም በኩል ሊቆም ይገባል። በድካሞቻችሁ ካልተማመናችሁ እርሱ ከባድ ይሆናል፤ ድካም የለብኝም የሚልን ሰው ልታግዙት አትችሉምና። ------------ Join Us & Share! 🔥 @metsihafuyinager ------------ ወደ ውስጥ፦ @adfontess
551
13
"የሰላሜ ሰዎች!" ---●--- ከበርናባስ በቀለ የልቤን ሰላም ለመጠቅ ከሰዎች መራቅ ከጀመርሁና የዙሪዬን አጥሮች አርዝሜ በሮቼንም ከከረቸምሁ ቆይቻለሁ። ግኑኝነቶቼ ሁሉ ተልዕኳዊ ብቻ አንዲሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጣርሁ ነው። ግልጽ ተልዕኮና ዓላማ ሳይኖረን ለወዳጅነት ብዬ የማኖረው room እንደሌለኝ ዙሪያዬ ላሉ ምርጦቼም አሳውቄአለሁ። ግን እኮ የልቤን ሰላም ለመጠበቅ ስል ጉዳት ፈርቼ አይደለም፤ ልቤ በመንገዴ ላይ እንዲሆን ስለፈለግሁ እንጂ። ዛሬ ግን አንዱ ወዳጄ "ባርኒ ግኑኝነቶችህን ከሕይወት ዓላማህና ተልዕኮህ መስመር ጋር ብቻ ማሰብህን እወደዋለሁ! አደንቃለሁም፤ ግን ሰላምህን ለመጠበቅ ስትል "አንዳንድ የሰላምህን ሰዎች" (ከስንት አንድ ወደ አጥርህ የሚመጡትን) ጭምር እንዳታጣቸው እፈራለሁ!" ብሎኛል። ይኸው ቤት ገብቼ ቀኔን ኦዲት ሳደርግ "የምር እውነት አለው ይሆን?" ብዬ እያሰላሰልሁ ነው። መቼስ "የሰላሜ ሰዎች" ከመቶ መካከል ሁለቱ ናቸው አይደል የሚሆኑት? ታዲያ ሁለቱን እስካገኛቸው (ለነርሱ በሬን ክፍት ላደርግ ስል) 98ቱ አንድ የሚያደርገን ነገር ሳይኖረን "ወዳጅነት" በሚል የዳቦ ስም በልቤ ሰገነት ያሻቸውን ያድርጉ? ኧረ ተው! ባይሆን "የሰላሜ ሰዎች" ከወዲሁ ራሳቸውን ይግለጡ። ተልዕኮ መር ሕይወት፣ መርሕ ተኮር ምልልስና ሰማይ ወለድ ተስፋ ያላቸው ያ ማንነታቸው የሚጠይቀውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ የሆኑ ከወዲሁ "እነሆኝ" ይበሉኝ! ታዲያ ስለ እነርሱ (ስለ 2ቱ) ብዬ አጥሬን ክፍት አድርጌ 98ቱ ስለምን ልቤን ቅርጫ ይከፋፈሏታል!😥 ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
548
14
እኔም ብሎ ተደራሽ! ---🔘--- ከበርናባስ በቀለ "አገልግሎትህ ተደራሽ እንዲሆን ወደ ሚዲያዎች በስፋት መምጣት አለብህ" አትበሉኝ፣ እኔ ለተደራሽነት የምሠራ አይደለሁምና። እጄ ላይ ያለ Content ሰዎች ጋር እንዲደርስ ብዬ አልሠራም፣ ግን ለትውልዴ ካለኝ ሸክም የተነሳ ጥቂት ማድረግ ከቻልኩ ብዬ አንቧችራለሁ። የማርኬቲንግ ቋንቋ አይገባኝምና እንደርሱ አታውሩኝ። ራሴን መሸጥ (አደባባይ ማቅረብ) ስለምችልበት ዘዴም አትወትውቱኝ። ዘዴውን አውቀዋለሁ፤ ደግሞ ያመንሁትንም አውቀዋለሁ። እምነቴ የክንውኖቼ ስልተ-ምት (rhythm) መሠረት ነውና ከማምነው የሚጋጭ ነገር እንድኖር አትምከሩኝ። እኔ ለተደራሽነት አልሠራም (እኔም ብሎ ተደራሽ! ሲጀመር ምን እፍኝ የሚሞላ አለኝና!)። ለመድረስ ግን እሠራለሁ። ወንድሞቼ ጋር ለመድረስ። የሚጠቅም ነገር ከተገኘብኝ በዐውዳቸው አንዳች ለማቀበል። ስለዚህ ስትመክሩኝ "ያንተ ሥራዎች ወደ ሰዎች መድረስ አለባቸው!" ከምትሉኝ "ወገን ታሟል፣ ሰውነት ከስሟል፣ ብዙዎች በሰዎች ተከበው ሰው ርቧቸዋል፣ የእውነተኞች እጣ ፈንታ እንግልት ሆኗል፤ ስለዚህ እጅህ ባለው ነገር እንድረስላቸው!" በሉኝ። ያኔ ሁለንተናዬ ሰጥቼ አብሬአችሁ እጓዛለሁ። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
569
15
ዘመዶቼ ለሳምንት የጠፋሁባችሁ ከላይ ባኖርሁላችሁ ልጥፍ (post) መሠረት ክፍ'ላገር ስለነበርሁ ነው። እንደው ወደዚህ ግድም አላመጣሁም እንጂ በሳምንቱ በቆይታዬ ለዚህም ሆነ ለሌሎች ምስባኮቼ የሚሆኑ ጥንቅሮችን ከትቤአለሁ። ትዝብቶች፣ ቁጭቶች፣ የነፍስያዬን ጩኸቶች የሚያትቱ ጽሑፎችን ክታቤ ላይ አስፍሬአለሁ። ከቢሮዬ ተልዕኮ ጋር የሚገናኙ ሥራዎችን ከውኜአለሁ። የምወዳቸውን ጥቂት ሰዎችን አግኝቼ በሸነና ለማለት እድል አግኝቻለሁ። በንፁህ ፍቅራቸው ሁሌም እገረማለሁ። የቀጣዩ ዘመን ጉዞዬን አሰላለፍ በሚመለከት አዳዲስ ውጥኞችን ይዤ ተመልሻለሁ። እናንተስ እንዴት ናችሁ? ከእንግዲህ በሳምንት ስንት ቀናት ልጻፍ? ደግሞ ተናፍቃችኋል። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
615
16
ክፍ'ላገር ድሮ ቀረ! ---🔘---- ከበርናባስ በቀለ ክፍ'ላገርን ክፍ'ላገር የሚያሰኘው ምንድነው? እኔ ሲመስለኝ የማኅበረሰብ ስብጥሩ፣ የባላገሩ ባህልና ወጉ፣ መሃል አገር በቀላሉ የማይገኙ ነገሮች easily access መደረግ መቻሉ ጥቂቶቹ ናቸው። በዚህ ወቅት ግን ክፍ'ላገሩ ወጉን የተወው ይመስላል፤ ባለፉት ሁለት ወራት በቃኘኋቸው ሦስት ከተሞች ያስተዋልሁት ይህንን ነው። ከተሞች ተመሳሳይ ቅርጽና ዐውድ እየፈጠሩ ይገኛሉ። አንዱን ከተማ ከሌላኛው ለመለየት እስክትቸገሩ ምስስሎሹ ተቀራርቧል። ምናልባት የሉላቀፋዊነቱ (globalization) ተጽዕኖ /effect/ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፦ ዛሬ ያለሁባትን ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ የሚለየው እኔና ቤተሰቤ የምንኖረው አ/አ መሆኑ ብቻ ነው። ያመሸንበት ሰፈር ደግሞ CMC ከኮንቬንሽን ሴንተር ወደ ፍየል ቤት ስትኼዱ ያለው መንገድ ቅርጹ አለ አይደል? በቃ እንደርሱ። እዚህ የሚወስደን ታክሲ ወደ ሪዞርቱ እየወሰድኋችሁ ነው ይለናል፣ እኛ በልባችን ወደ ፍየል ቤት (ሳፋሪ) እየኼድን ነበር። አቤት! ከሰሞኑ አመሻሹ ላይ ፍየል ቤት አካባቢ ያስተዋልሁት ወከባ! መንገዱን ስሻገር ፊልም ላይ እየተወንሁ ያለሁ ነበር የመሰለኝ። በወከባ ከምትናጥ የጉድ ከተማ ስንመጣ በክፍላገሩ ነፋሻማ vibe ደግሞ ልባችን ለቀቅ ማለት አልነበረበትም? ልዩነት ሂንጅሩ። እዚያም ወከባ እዚህም ወከባ። የከተሞች ፎረምና ምክክር ላይ የምትቀመጡ ሰዎች የምትሰበሰቡት ከተሞቹን መንትያዎች (በሁሉ ነገር የሚመሳሰሉ) ስለማድረግ ነው እንዴ? ኧረ ከአንደኛው ጫፍ ወደ ሌላኛው ስንኼድ የቆየንበትን ጩኸትና ግርግር በመርሳት እንጽናና ዘንድ የድሮ እሴቶችን ተውልን። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
770
17
የጃር ውኃ ይቅርባችሁ!😥 ----------- ጓደኛዬና ቤተሰቡ (ባለቤቱና ልጆቹ) በጃር ውኃ ምክንያት ታመው ሆስፒታል ገብተዋል። በተለይ የመጀመሪያ ልጃቸው በከባድ የሐኪሞች ርብርብና እርዳታ ነው የተረፈው። ባለቤቱ ትላንትና ግሉኮስ ላይ እንደዋለች አሁን ደውሎ አሳወቀኝ። እኛም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የጃር ውኃ ተጠቃሚዎች ነበርንና ከወራት በፊት ከሰማናቸው መረጃዎች ተነስተን የጃር ውኃ አቁመን ነበር። ግን ከቀናት በፊት ውኃ በጣም ባስፈለገን ሰዓት አስመጥተን ተጠቅመናል፣ ሁለቱን ቀናት ዝም ብሎ የሆድ ቁርጠት ነገር ራሴ ላይ አስተውዬ ለባለቤቴ ነገርኋትና ውኃውን አቆምን። ግን የመጣውን ጃር ተጠቅመን ጨርሰናል። ከዚያም ውኃ ለሚያመጣልን ልጅ ኼጄ ይህን ጃር የሚሉትን ጉድ ግን ባታመጡት (ለሕዝቡ ብትናገሩ) አይሻልም? ብዬው እንደተመለስሁ አስታውሳለሁ። ስለ ወዳጄ ቤተሰብ የሰማሁት ግን አሁን ነው። እርዳታዬ አስፈልጎት በደወለልኝ ሰዓት ስልኬ ዝግ ስለመሆኑ አውርቶኝ ሳምንቱን ያለፉበትን ስቃይ አጫወተኝ። የኼዱበት ሆስፒታል ሐኪሞቹም "የጃር ውኃ አትጠቀሙ ብለን ለሕዝቡ እየነገርን ነው ግን ሕዝቡ እየሰማ አይደለም። መንግሥት ስላላስቆመ ነው እኛም ጸጥ ያልነው እንጂ ችግሩን በይፋ መናገር እንችል ነበር!" ብለውናል አለኝ። በጣም አዝኛለሁ። ጃር የምትጠቀሙ እባካችሁን አቁሙ። ሌላስ ምን እናድርግ? በዚህ አቅጣጫ የሕግ መንገድ የምታውቁ ማኅበረሰቡን ለመታደግ ምን እናድርግ? ቢያንስ ግን መልእክቱን በማጋራት የጃር ውኃ ተጠቃሚዎችን እንታደግ!!! ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
905
18
እሑድም አይደል! እኔ እየተጓዝሁ ነው። ሚስቴና ልጄ ደግሞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ኼደዋል። ሲመለሱ (ሳገኛቸው) የት ኼደው እንደነበር እጠይቃቸዋለሁ።
708
19
ቤተ ክርስቲያንን ስታስቡ ጥንቅቅ ያለ ፕሮግራም ተካፍሎ ስለመመለስ፣ ከዐውድ ያላፈነገጠ ትምህርትና ስብከት ተካፍሎ ስለመምጣት አስባችሁ ከሆነ የነገረ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረታችሁ ችግር ገጥሞታል። ቤተ ክርስቲያን ፕሮግራም ተካፍሎ ለመመለስ የሚኬድበት ቦታ ሳይሆን ሕይወት ለመካፈል (ለመቀበልና ለመስጠት) የሚኬድበት ሕያው የሆነ የወንድሞች ኅብረት ነው። ሕያውነቱ አንዱ ሰው በሌላው ውስጥ በመኖሩ የሚረጋገጥ ነው። ወደ ቅዱሳን ጉባኤ ኺዱ፤ በፍጹም አትቅሩ። ዛሬ ጠዋት በኼዳችሁበት ጉባኤ በስንት ወንድምና እህቶች ልብ ውስጥ በቋሚነት አላችሁ? ስንት ሰዎች actively በሕይወያችሁ ውስጥ መብትና ኃላፊነት አላቸው? እንደርሱ ካልሆነ የኼዳችሁት ወደ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ወደ አንድ ቆንጆ ማኅበራዊ ክለብ ነው። ------------ Join Us! & Share!!! @metsihafuyinager @metsihafuyinager ------------ ወደ ውስጥ፦ @adfontess
639
20
ነገረ ቀልቀሎ --🔘--- ከበርናባስ በቀለ "አንተ ለምን ነገሮችን ሌጣቸውን አትረዳቸውም" ይሉኛል። ሌጣውን ያለ ነገር አለ? ያለ ዐውድ፣ ጊዜና ቦታ የሚነገር ድስኩር ኖሮ ያውቃል? ሲያልፍም የሰጡትን ብቻ የሚቀበል ቀልቀሎ ወይም ስልቻ ነው። ይህም የሆነው ቀልቀሎ ስለ ሰጡት ነገር reflect ለማድረግም ሆነ በሰጡት ነገር እሴት (value) መጨመር የሚያስችለው ስብዕና ስለሌለው ነው። ለሕላዌው የሚያስብለት ሌላ ነው። የሚገለገልበትም ሌላ አካል ነው። አያስብም፣ ማሰብ ስላለመቻሉም አይጨነቅም። አሳቢው ሌላ ነውና የሰጡትን ብቻ ይቀበላል። በእህል ጠቅጥቀው ያኖሩትና የሰጡትን በታማኝነት ሸክፎ ይይዛል። ይመቸው! እኔ ግን ስብዕና አለኝ። በአምሳለ ስላሴ የተሠራሁ እንደመሆኔ አሳቢና ተመራማሪ አዕምሮ የተጎናጸፍሁ ፍጡር ነኝ። ስለዚህ የሰጡኝን ብቻ የምቀበል አይደለሁም። "ትውፊት፣ ታሪክ፣ ወግና ትርክት ይህን ይላልና ተቀበል" ሲሉኝ ቆዩኝ እስቲ እቀበለው ዘንድ በደንብ ልረዳው እላለሁ። ታዲያ ትርክትና ትውፊት ጠል አይደለሁም ግና ጠያቂ አዕምሮ ያለኝ አማኝ ነኝ። እጠይቃለሁ፣ አሰላስላለሁ፣ ደግሞም በደረስሁበት መረዳት መሠረት ኃላፊነት ወስጄ እወስናለሁ። ምክንያቱም ስልቻና ቀልቀሎ አይደለሁም! ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊
655