ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️
前往频道在 Telegram
ምድር እጅግ ሰፊ ናት፤ እኔ ወንድማችሁ በርናባስ ደግሞ ያሉኝ ሁለት ዐይኖች ብቻ! አባካችሁን ኑ...ና አጋጭተን (ዐይኖች አዋጥተን) እንይ!✍️ አሳብ አስተያየት ቢኖራችሁ፦ @barnica የግላችሁ ነው።
显示更多1 417
订阅者
无数据24 小时
-47 天
-430 天
数据加载中...
吸引订阅者
七月 '26
七月 '26
+12
在1个频道中
六月 '26
+13
在0个频道中
Get PRO
五月 '26
+20
在0个频道中
Get PRO
四月 '26
+19
在0个频道中
Get PRO
三月 '26
+22
在0个频道中
Get PRO
二月 '26
+120
在1个频道中
Get PRO
一月 '26
+10
在1个频道中
Get PRO
十二月 '25
+19
在0个频道中
Get PRO
十一月 '25
+15
在0个频道中
Get PRO
十月 '25
+29
在0个频道中
Get PRO
九月 '25
+7
在0个频道中
Get PRO
八月 '25
+10
在0个频道中
Get PRO
七月 '25
+22
在0个频道中
Get PRO
六月 '25
+4
在0个频道中
Get PRO
五月 '25
+6
在0个频道中
Get PRO
四月 '25
+4
在0个频道中
Get PRO
三月 '25
+3
在0个频道中
Get PRO
二月 '25
+5
在0个频道中
Get PRO
一月 '25
+6
在0个频道中
Get PRO
十二月 '24
+11
在0个频道中
Get PRO
十一月 '24
+21
在0个频道中
Get PRO
十月 '24
+27
在0个频道中
Get PRO
九月 '24
+16
在1个频道中
Get PRO
八月 '24
+19
在0个频道中
Get PRO
七月 '24
+11
在0个频道中
Get PRO
六月 '24
+5
在0个频道中
Get PRO
五月 '24
+24
在0个频道中
Get PRO
四月 '24
+16
在0个频道中
Get PRO
三月 '24
+22
在0个频道中
Get PRO
二月 '24
+17
在0个频道中
Get PRO
一月 '24
+24
在0个频道中
Get PRO
十二月 '23
+15
在0个频道中
Get PRO
十一月 '23
+12
在0个频道中
Get PRO
十月 '23
+17
在0个频道中
Get PRO
九月 '23
+27
在0个频道中
Get PRO
八月 '23
+31
在0个频道中
Get PRO
七月 '23
+15
在0个频道中
Get PRO
六月 '23
+16
在0个频道中
Get PRO
五月 '23
+21
在0个频道中
Get PRO
四月 '23
+21
在0个频道中
Get PRO
三月 '23
+15
在0个频道中
Get PRO
二月 '23
+6
在0个频道中
Get PRO
一月 '23
+59
在0个频道中
Get PRO
十二月 '22
+21
在0个频道中
Get PRO
十一月 '22
+14
在0个频道中
Get PRO
十月 '22
+15
在0个频道中
Get PRO
九月 '22
+20
在0个频道中
Get PRO
八月 '22
+24
在0个频道中
Get PRO
七月 '22
+15
在0个频道中
Get PRO
六月 '22
+13
在0个频道中
Get PRO
五月 '22
+24
在0个频道中
Get PRO
四月 '22
+28
在0个频道中
Get PRO
三月 '22
+28
在0个频道中
Get PRO
二月 '22
+37
在0个频道中
Get PRO
一月 '22
+18
在0个频道中
Get PRO
十二月 '21
+17
在0个频道中
Get PRO
十一月 '21
+12
在0个频道中
Get PRO
十月 '21
+9
在0个频道中
Get PRO
九月 '21
+19
在0个频道中
Get PRO
八月 '21
+8
在0个频道中
Get PRO
七月 '21
+28
在0个频道中
Get PRO
六月 '21
+32
在0个频道中
Get PRO
五月 '21
+37
在0个频道中
Get PRO
四月 '21
+24
在0个频道中
Get PRO
三月 '21
+62
在0个频道中
Get PRO
二月 '21
+327
在0个频道中
Get PRO
一月 '21
+53
在0个频道中
Get PRO
十二月 '20
+2 113
在0个频道中
| 日期 | 订阅者增长 | 提及 | 频道 | |
| 24 七月 | 0 | |||
| 23 七月 | 0 | |||
| 22 七月 | +1 | |||
| 21 七月 | 0 | |||
| 20 七月 | 0 | |||
| 19 七月 | 0 | |||
| 18 七月 | 0 | |||
| 17 七月 | +2 | |||
| 16 七月 | 0 | |||
| 15 七月 | +1 | |||
| 14 七月 | 0 | |||
| 13 七月 | +2 | |||
| 12 七月 | 0 | |||
| 11 七月 | 0 | |||
| 10 七月 | 0 | |||
| 09 七月 | +1 | |||
| 08 七月 | 0 | |||
| 07 七月 | 0 | |||
| 06 七月 | 0 | |||
| 05 七月 | +1 | |||
| 04 七月 | +2 | |||
| 03 七月 | +1 | |||
| 02 七月 | 0 | |||
| 01 七月 | +1 |
频道帖子
ሕያዊቷ ማኅበር-- ሕያውነት ከራቃት ዓለሙማ ተስፋ የለውም። እርሷ ለዓለም እውነተኛ ህሊና ናት። የርሷ ህሊና ከጎደፈ ዓለሙማ በጨለማ ይዋጣል።
| 2 | ክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር እቅፍ ወጥቶ ለቤዝዖቱ ሥራ መጣ፣ ከክርስቶስ ኢየሱስ ማንነትና ሥራ የድነት ወንጌል ወጣ፣ ከወንጌሉ ውስጥ መሲሓዊቷ ማኅበር (ቤተ ክርስቲያን) ወጣች፣ ከቤተ ክርስቲያን (በኩል) ሕያውነት ወደ ዓለሙ ይወጣል።
------------
Join Us! & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 145 |
| 3 | በሥራዬ ጉዳይ ወጥቼ ቦሌ Morning Star አካባቢ ያለ ካፌ ውስጥ ነኝ። አጠገቤ አንድ ቆፍጠን ያለ ወጣት አለና ይደወልለታል። ስልኩን አንስቶ ወዳጁን "እ.. እየጠበኩህ ነው አትመጣም?" ይለዋል።
"እየመጣሁ ነው ግን አንተ መኪና ይዘሃል አይደል? የእኔን መኪና ትቼው ልምጣ?" ብሎ ይጠይቀዋል። አጠገቤ ያለው ጎረምሳ "የእኔ መኪና ፓርኪንግ ውስጥ ናት" ያንተን ይዘህ ና እና ሮጥ ብለን እንመለሳለን ይለዋል።
ከዚያም ያኛው ወዳጁ "የእኔ መኪና ላንተ አትሆንም፣ እባክህን ያንተን አውጣ ይለዋል" ኋላም ይኸኛው (አጠገቤ ያለው) ሰው "አንተ ምን ሆነህ ነው? እኔ በሳይክልም መኼድ እችላለሁ እኮ፣ ደግሞ vits እኮ ትልቅ መኪና ነው!" ይለዋል ያኛው እንደተሳቀቀ "እሺ" አለውና ይኸው እየጠበቀው ነው። ቦሌ የሆነ ተፋልሶማ አለ!
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 237 |
| 4 | ካረጁ አይበጁ!
---🔘----
ከበርናባስ በቀለ
ዓለም ዋንጫዋን አስረክባለች። ሌጀንዶቹን እነ ክርስቲያኖንና ሊዮኔል ሜሲን ሸኝታ Yamalንና መሰሎቹን (አዲሱን ትውልድ) ማንቆለጳጰሱን ይዛዋለች። "እኔ የሚያስፈልገኝ አዲስ ትውልድና አሠራር ነው!" (ካረጁ ለእኔም አይበጁ!) የምትል ይመስላል። እርሷ መች ያልቅባትና!
ዓለምዬ (ዓለሚቱ) ጎበዝ ናት ማንን መቼ ተጠቅማ ውጥኗን ማሳካት እንደምትችል ታውቃለች። ለምን ሳር ምድሩ ያደነቀህ... ሰማይ ምድሩ ያጨበጨበልህ አትሆንም? ጊዜህ ሲያልፍ አለፈ ነው። "በእነ እንትና ዋጋ መክፈል የመጣ ለውጥ" እያለች ያለፈውን ዘመን legacy ስታዳንቅ አዳዲሶቿን አትቀርብርም። "አዳዲሶች አሉኝ እኮ" እያለች ቡቃያዎቿን ወደ ምድሩ ፊት ገጽ ታወጣለች።
"ካረጁ አይበጁ" መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ ባታገኙለትም ግን ሃሳቡ ጤናማ ነው። እርጅና የፍሬያማነት ዘመን ሳይሆን የእረፍትና አዳዲሶችን የማብቂያ ብሎም የጥሞና ዘመን ነው። ስለ ቀደሙት ሰዎች አሠራርና legacy ለማስቀጠል ሲል አዲሱን ትውልድ ለሚሰዋ ማኅበር ሁሉ አድርሱልኝ። አዲስ ነገር የሚጨንቃቸውና የጥንቱ አሠራር ታማኝ እስረኞች የሆኑት የአመራር መዋቅሮች ከዓለም እንዲማሩ ይህችን ነገር ስደዱልኝ።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 256 |
| 5 | አሁን በጨለማው ክምር ላይ ትንሽዬ የብርሃን ተስፋ እያቆጠቆጠች ነው። ቀጥሎ ያለውን ዐረፍተ ነገር ስጽፍ ደግሞ ጨለማው አድራሻውን ሊለቅ ነው። ይኸው ብርሃን! ይኸው ወገግታ። ታዱያ ጎህ ሲቀድ ሊነጋ ሲያቅላላ የብርሃኑ ጮራ ሲፈነጥቅ ጨለማው ደግሞ ሲፈረጥጥ ያዩ ዓይኖቼ የእግዚአብሔርን በጎነት የሚተርክ ዘጋቢ ፊልም እያዩ ይመስል ትዕንግርት ውስጥ ናቸው። እግዚአብሔር ቸሩ!
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 290 |
| 6 | ሰማዩ ዝም ያለ ሲመስለንና ነገረ ዓለሙ ግራ ገብቶን ስንዋትት እግዚአብሔር የነፍሳችን ማረፊያ ነው። እርሱ ልባችንን በሕያውነቱ የሚያሞቅ የደህንነታችን ምንጭ ነው። የሞት ሸለቆ በሚመስል ዝቅታ እያለፍን ያለን ሲመስለን እርሱ የዘላለሙ ከፍታችን ነው። ስለ ነገያችን አስበን እርግጠኝነት ሲጎድለን ዓለማትን በመግቦቱ የያዘው እርሱ መድን ዋስትናችን ነው።
-------
Join Us!
@metsihafuyinager
@metsihafuyinager
-------
በውስጥ፦ @adfontess | 402 |
| 7 | የኢሉሚናቲ መንፈስ!
---🔘-----
ከበርናባስ በቀለ
ከሰሞኑ ሚስቴና ልጄ ለጋራ ተልዕኳችን ኼዴዋልና ሳምንቱን ላጤ ነኝ። ምግብ ሠርቼ መብላት እችላለሁ፣ ኧረ ማብላትም እችላለሁ። ግን እነርሱ ኼደው ብቻዬን ስበላ የከዳኋቸው ይመስለኝና አይዋጥልኝም። ላስበውም አልፈልግም። እናም ሚስቲቱ "ትክክል አይደለህም፣ እንደውም ስመለስ ሽምግልና መቀመጥ አለብን!" ብላኛለች። እሺ፣ እኔ ምን ላድርግ? እርሷ በሌለችበት ቤት ምግብ መብላት በታማኝነት ጉድለት የሚያስከስስ የሚመስለኝን ነገር ምን ላድርግ? ደግሞ እኮ ላለፉት 7 አመታት እንደ ትንሽ ልጅ እንዲሁ ነው ሳስቸግራት የኖርሁት።
ትላንትም ወደ ነበረኝ መርሓ-ግብር ያቀናሁት ምሳዬን ሳልበላ ነበርና ጓደኛዬ ሰሎሞን አዝኖልኝ "መፍትሔ አግኝቼልሃለሁ" አለኝና ቀጥሎ "የኛ ቤቱን የምግብ policy ተከተሉ! እኛ ቤት ሁሉም ሰው በየራሱ ሳህን (Dish) ስለሚበላ በምግብ ጉዳይ ማንም ከማንም ጋር emotionally attached አይደለም! ስለዚህ Betty ስትመለስ ይህን ዘዴ ተከተሉ!" እኔም ከአፉ ቀበል አደረግሁና "ይህ የኢሊሙናቲ መንፈስ ነው!" ሥራህ ይፍረስ! አልኩት። በቃ Ema ስትመጣ በትክክል እበላለሁ። ዛሬም በምሽት ፕሮግራሜ አምሽቼ 4:35 ገብቼ ስለ ውሎዬ ምስጋናዬን ወደ ላይ ካሳረግሁ በኋላ "ስለ ምግብ" የሕሊና ጸሎት በማደርግበት ሰዓት ነው ይህችን የጻፍሁት። ነገ ወጥቼ ፏ ያለ ቁርስ እበላለሁ። እናንተ ምን አለባችሁ፣ ራታችሁን በልታችሁ የሰው ቤት ጉድ አንብቡ! የመጣ ይመጣል እንጂ ግን Solን አልሰማውም።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 444 |
| 8 | ሞትም ሰልጥኗል!
---🔘----
ከበርናባስ በቀለ
የቅርብ ወዳጄ ናት። እጅግ ትጉህና የአቋም ሴት በመሆኗ ዙሪያ ባሉ ዘንድ ተከብራ የምትኖር እንስት እንደሆነች ስነግራችሁ እኔም ከተጽዕኖዋ ያልተረፍሁ መሆኔን ሳልሸሽጋችሁ ነው። ከምትኖርበት ከተማ ወደ ሌላኛው የክፍ'ላገር ከተማ በጉዳይ ተጉዛ ነበር (እርሱንም ከሳምንታት በፊት አሳውቃኛለች)፣ የዚያ ከተማ ተልዕኮዋን ጨርሳ ወደ እናት ከተማዋ ልትመለስ ሁለት ቀን ሲቀራት "ወንድምሽ አርፏልና ቶሎ ድረሺ" የሚል የስልክ ጥሪ ደረሳት። 😥
"ባርኒ ወንድሜን አጣሁት እኮ" ብላ text አደረገችልኝ። መደወል ፈራሁ! ስልኬን አስሬ እያነሳሁ መለስሁ። እንደምንም ግን ደወልኩላት። መቼ? እንዴት ምን ሆኖ? ብቻ ብዙ ጥያቄዎችን አከታትዬ ጠየቅኋት። "ባርኒ እንዴት የሚለውን እኔም አላውቅም" ይኸው ቀብረነው ቁጭ ብለናል። እኔም ማለት? ምንም ሳይታመም? ያለ ምንም አደጋ? ብዬ እንደ ደነገጥሁ ግራ መጋባቴን ነገርኋት።
እሺ፣ ቆይ ምን ይባላል? ስለ ብዙዎች ኃላፊነት በመውሰድ የሚታወቅ ጀግና ወንድም ሲሠራ ውሎ ባለበት ወደቀ ሞተ፣ የሚለውን እንዴት እንመን? ህመም ቀርቷል ማለት ነው? ሞትም ሰልጥኖ በሌላ version እየመጣ መሆኑ ነው? ወይስ እኛ ያልገባን ሌላ ነገር አለ? ወንድማችን ሳይማቅቅ ሳይሰቃይ ወደተሻለችው ከተማ ኼዷል፣ ወዳጄ (ሀረግዬ) ከጥቂት ቀናት በኋላ ደህና ትሆናለች አውቃለሁ፣ እኛም አለንላት። ግን ለምን? እና እንዴት የሚለው ጥያቄ አዕምሮዬን ሰቅዞ ይዞታል።
ቤተሰቦቼ ሞት ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ራሱን አዘምኖ ወደኛ ቀርቧልና አጠገባችሁ ያለውን ሰው ቼክ ማድረጋችሁን አትዘንጉ። በርግጥ ሞትን የምፈራ አይደለሁም፣ እርሱም ይህን ጠንቅቆ ያውቃል። ሞቼ አላየሁትም እንጂ የምወዳቸውን ስቀብራቸው ኖሬአለሁ። ተስፋዬም ከሞት ባሻገር ያለው ሕይወት ስለሆነ ወደዚያ ለመሻገር ከሚናፍቁ መካከል ነኝ። የኼደ አንዴ ኼዷልና እርሱ አይጨነቅም፣ ግን እዚህ ለቀረን ግዙፍና በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጥያቄ ትቶልን ይኼዳል።
ስለ ወዳጄ እጸልያለሁ፣ እናንተም በጸሎታችሁ ታግዟታላችሁ። ግን አጠገባችሁ ላለ ሰው መልካምነት ልታሳዩ አስባችሁ እንደሆነ ቀን አትቅጠሩ። አዝናችሁበት እንደሆነ ለነገ አትበሉ። ትወዱትም እንደሆነ ፍቅራችሁን ለመግለጥ ዘይግታችሁ ጠሃይቱ አትግባ። ነገ አታገኙትምና ዛሬ ድረሱለት። ቀጣይ አመት አብሯችሁ ላይሆን ይችላልና ልባችሁ ከብዶበትም ከሆነ ዛሬውኑ ጊዜ ሰጥታችሁ ንገሩት። በንፁህ ፈገግታችሁ ቀን የምትጨምሩላቸው በአጠገባችሁ አይጠፉምና ግራ ቀኛችሁን ቼክ ማድረጋችሁን አትዘንጉ።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 606 |
| 9 | "የዓለም ዋንጫ"
----▣------
ከበርናባስ በቀለ
ከሚከተሉት መካከል ስለ ዓለም ዋንጫ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው? በፍጥነትና በትክክል የመለሱ የመጀመሪያዎቹ 5 ሰዎች ይሸለሙ ዘንድ ወስነናል።
-----------
ሀ) ዓለም ዋንጫ አላት፣ በብርቱ ለሮጠላት ትሰጠዋለች።
ለ) ዓለም የዋንጫ ጨዋታ አዘጋጅታ ልጆቿን እያጫወተች ነው፤ ልጅ ጨዋታ ይወድ የለ?
ሐ) የእግር ኳስ ስፖርቱ ተወንጫፊ ከዋክብት በዓለሙ ገጽ ፊት የሚያበሩበት የትዕይንት መድረክ።
መ) አንተ ደግሞ፣ እስቲ አታወዛግበን።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 576 |
| 10 | ⚠️
------
ከበርናባስ በቀለ
ሩጫ በዝቶብኝ ጉልበቴ ዝሎ እና አዕምሮዬ ረጅም እረፍት የሚያስፈልገው አይነት አኳኻን ውስጥ ስሆን--- ከአካላዊ እረፍቱ በላይ ለምን በዚህ ልክ ተወጣጠርሁ? ጊዜዬን እየበሉት ያሉት ነገሮች ድንበር ዘለል፣ መርኾ ተኮርና እግዚአብሔር ለአጽናፈ ዓለሙ ካለው እቅድ ጋር የሚቆራኙ ናቸው? ለሚል ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ ማግኘቱ የበለጠ ያሳርፈኛል። ከዚያም ወደ physical & mental እረፍቴ አቀናለሁ።
ባለፉት ጊዜያት ብዙውን ጊዜዬን የበላብኝ አፍርሶ መገንባት እንደሆነ ስላስተዋልሁ፤ አሁን አዲስ ግንባታዎችን ሁሉ ማቆም አለብኝ። ባይሆን የተገነቡ ግኑኝነቶችንም ሆነ እንቅስቃሴዎቼን እየመረመርሁ በየቅድሚያቸው ማሰለፍ ይኖርብኛል። ትክክል የሆነ ነገር ሁሉ እውነተኛ ብሎም ዘላለማዊ አይደለምና እድሜዬን በtrial & error ⚠️ እንዳልጨርስ ከወዲሁ በተጠንቀቅ መቆም አለብኝ።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 699 |
| 11 | በምድሩ ላይ ርገጥ!
----▣---
ከበርናባስ በቀለ
ለተጨነቀች ነፍስ ማዳንህን ለምትሻ
ለ"አዳኝ ያለህ!" ባይዋ ከክፉው ንክሻ
በሰማያት ያለህ በምድሩ ላይ ርገጥ
ምህረትህን አውርድ ክንድህንም ግለጥ።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 711 |
| 12 | በቸርነትህ ብቻ የቆሙ ግን ማዳንህን የዘነጉ በየእለት ኑሯቸው ከእጅህ የሚበሉ ግን ስለ ፊትህ ግድ የሌላቸው ሰዎች መካከል ራሴን ሳገኝ አንተ እግዚአብሔር የመልካም ነገር ሁሉ መገኛ ምንጭ እንደሆንህ እመሰክር ዘንድ ክንድህ ይደግፈኝ። አለዚያ እኔም ተደርቤ ለጠላቶችህ ሳማህ ልውል ነውና በፊትህ ብርሃን ጨለማዬን ወግድ በልልኝ። ከበባውንም በትንልኝ።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 757 |
| 13 | የMercy መስመር!
----▣----
ከበርናባስ በቀለ
ጉዳይ ቢጤ ነበረኝና Mercy ጋር በጠዋት ስልክ መታሁ። ያቺ ሴትዮ "የደወሉላቸው ደንበኛ መስመር ስለተያዘ" ስትለኝ ብዙ ነገር አሰብሁ። ደግሞ "የደወሉላቸው ደንበኛ" ትላለች እንዴ? ደበኝነቷ እኮ ለእነርሱ ነው! ለእኔ እኮ ወዳጄ ናት። ለምን "የደወሉላቸው የቅርብ ወዳጅዎ አትለኝም?" ይህች ዓይን አውጣ ሴትዮ! እያልሁ አጉተመትማለሁ።
ብዙ ነገር ማሰቤን ቀጠልሁ። እሺ፣ መስመሯ የተያዘው ለምንድነው? መስመር ያዢዎቹ ጠላፊዎች ቢሆኑስ? የመስመር ላይ ሌቦች ቢሆኑስ? እንዲሁ በቀላሉ መስመርን የመሰለ ነገር ማስያዝ!? ሆሆሆ! እያልሁ መንገዱ ላይ ብቻዬን አወራለሁ። መስመሯ በትክክለኛ ያዥ (በሕጋዊ መስመረኞች) ተይዞ መሆን አለበት። የሆነ ሆኖ ግን ደጋግሜ ስሞክር ስልኳ ተነሳልኝ። እኔም Mercye ደህና ነሽ? ሴትየዋ "መስመርሽ ተይዟል" ስትለኝ እኮ ደንግጫለሁ አልኋት። እርሷ እየሳቀች "ለምን ባርኒ?" አለችኝ። በልቤ ሰው ተጨንቆ እርሷ ትስቃለች እንዴ? እያልሁ መስመርሽ በመያዙ ነዋ! አልኋት።
"ኦኦኦ ባርኒ፤ የስልኬ መስመር እኮ ነው።" አለችኝ። እኔም፦ ኡኡፍ! እንደርሱ በዪኛ ታዲያ አልኋት። እኔ የስልኳ መስመር ብቻ የተያዘ መሆኑን በምን አውቃለሁ። ሴትዮዋ እንደሆነች አታብራራ። "መስመር ስለተያዘ" ብቻ ነው የምትለው። ቀጥዬም ሌሎች መስመሮችሽ ደህና ናቸው? አልኋት። "አዎን! ሁሉም ጥሩ ነው!" አለችኝ። እሰይ! ብዬ ወደ ዋናው ጉዳዬ አመራሁ። እናተስ መስመራችሁ ደህና ነው? በመስመርማ ቀልድ የለም!!!
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 700 |
| 14 | ደብረብርሃን አየሯ ብርዳማ ነው። በመግቢያዋ ያለች "ጠባሲ" የተሰኘች ከተማ ስሟን ያገኘችው ብርዷ የሚጠበስ ስለመሆኑ እንደሆነ ነግረውናል። በርግጥ እኛ የመጣነው አየሩ ጥሩ በሆነበት ወቅት ስለመሆኑም አጫውተውናል።
ትራንስፖርት ውስጥ ያገኙን አዳዲስ ከሆናችሁ "አረቄ ግድ ነው!" ይሉናል። "እኛ ቅዝቃዜውን የቻልነው በአረቄው ነው!" እያሉ ምርጥ የደብረብርሃን አረቄ ያለበት ቤት ይጠቁሙናል። እኛ ደግሞ ቡናችንን በሰዓቱ እናግኝ እንጂ አያሳስባችሁ (የኛ ቤት አረቄ ቡና ነው!) እንላቸዋለን።
የሆነ ሆኖ ግን የልበ ቅኖች ከተማ ናት። ለመጣንበትም ተልዕኮ ቀና ምላሿን ሰጥታናለች። ከእንግዲህ ደብረብርሃን በሰሜን ሸዋ አንዷ የተልዕኳችን ማዕከል ሆና ልታገለግለን ቃል ገብታልናለች። አንኮበር፣ ደሴና ኮምቦልቻና መንዝ የቀጣይ ወር መዳረሻዎቻችን ናቸው። በእነዚህ አካባቢ ያላችሁ ወዳጆቼ ከዚህ ጉባዔ ወደ ኋላ ቀርታችሁ እንድታገኙኝ ይሁን!😊
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 653 |
| 15 | እንዳልቀባጥር! 🤲
---▣----
ከበርናባስ በቀለ
ለጣዕመ ቢስ ልሳኔዬ በድንቅ አደራረግህ ለዛ ሰጥተኸው ሌሎችን የሚያንጽ ነገር ማውራት ከቻልሁ ዘንዳ አንደበቴ የምህረትህ ባለ ዕዳ ነውና በጎነትህን ብቻ ያውራ። ክብርህን በሚሻማ መልኩ ለአፍታ እንዳልቀባጥር መንፈስህ ለከናፍርቴ ዘብ ይቁምልኝ።
እንዳስለመድከኝ ሁሉ በዛሬውም ጉዞዬ (ከፊቴ ባለች ከተማ) ነገያቸውን ማየት ላቃታቸው ከነገህ (from your future) እየጨለፍሁ የፍጻሜያቸውን ተስፋ አመለክት ዘንድ ደካማውን ስብዕናዬን እንድትጠቀም ልመናዬን አቀርባለሁ። ምስክርህ ሆኜ በምቆምበት ሁሉ "እኔ አይደለሁም፣ እርሱ ነው!" እያልሁ አድንሆትህን አስተጋባ ዘንድ ቅዱሱ መንፈስህ እኔነቴን በአንተነትህ ይክደንልኝ።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 651 |
| 16 | ሜሮን፦ "ሰላም! ላለፉት ሁለት ቀናት ለምን አልፖሰትህም? ፖስቶችህን የለመድን ቴሌግራማችንን ቼክ የምናደርግ አለን እኮ።"
እኔ፦ oww! በእውነቱ እንዲህ አስቤ አላውቅም። እኔ እንደው እንደ ጉዞ ማስታወሻዎች ከሆነኝና plus ደግሞ ዙሪያዬ ላሉ የአገልግሎቴ አጋሮች updates ልስጥ በሚል እንጂ በዚህ ልክ የሚጠቅም ነገር እንዳለው አላስብም።
የሆነ ሆኖ ግን ሜሪ (ዛሬ ያወቅሁሽ አንቺ ግን በጽሑፎቼ እንደምታቂኝ የነገርሽኝ) ወዳጄ ስለ አብሮነትሽ አመሰግናለሁ። ትላንት በI Care Family ስለነበረን የጋራ ጊዜ እየተዘገጃጀሁ ስለነበር ለሁለት ቀናት ከዚህ መንደር ጠፍቼ ነበር።
እርሷ፦ "እርሱ family እኛን አያካትምም?"
እኔ፦ በርግጥ! ቃለ እግዚአብሔርን መሠረት ያደረገ አስተምህሮና ተግባራዊ ሕይወት የናፈቃቸው፣ ሲያልፍም እውነተኛ ሰው የራባቸው የሚሰበሰቡበት ወርሃዊ መድረክ ነው።
እርሷ፦ እሺ ባርኒ፣ ለመቀላቀል መስፈርቱ ምንድነው?
እኔ፦ ጤናማውን አስተምህሮ መሠረት ያደረገ ኅብረት የሚናፍቅ ልብ፤ እውነተኛ ወዳጅነት (ቤተሰባዊነት) የሚፈልግ ጠንካራ መንፈስ።
ሜሪ፦ "በል እንግዲህ ለቀጣይ ወር ስብሰባችሁ አንደኛ ላይ ጻፈኝ።"
እኔ፦ ሜሪዬ አመሰግናለሁ። ለአስተባባሪዎቹ የግል መረጃሽን እሰጣቸዋለሁ። ደግሞ ከወዲሁ ቡና የምትጠጪ ስለመሆኑ እርግጠኛ ሁኚ። እኔ ቡና ከማይወድ ሰው ጋር ኅብረት የለኝምና። 😊
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 751 |
| 17 | የ'ኛ ልጅ በርቺ!😊
---▣----
ከበርናባስ በቀለ
በቤተሰቤ (I Care family) ካሉ እንስቶች በትጋትዋ ትታወቃለች። የያዘችውን ነገር አድምታና አድቅቃ ነው የምትሠራው። አዕምሮዋ ብሩህ ነው። መማርና መመራመር ውስጧ ነው። መጠየቅ ስለምትወድ ብዙ ታስወራችኋለች። ላለፉት ጥቂት አመታት ስታጠናው የቆየችውን የምርምር (ወረቀት ሥራዋን) ዛሬ በዘርፉ ጠበብት ፊት አቅርባለች። "Nationwide Phenotypic and Genotypic Assessment of Glucose-6-Phosphate Dehydrogenase Deficiency in Relation to Malaria in Ethiopia" የምርምር ሥራዋ ርዕሰ ጉዳይ ነበር።
ታዲያ ልጅት ምርምሩን አጃዕብ በሚያሰኝ ብቃት ያቀረበች ሲሆን የሙያው ጠበብትም ይህ ሥራ እጅግ የላቀ ውጤት (Excellent) ይገባዋል ብለው ቆመው አጨብጭበዋል። ታዲያ ይህች ልጅ የኛ (የቤታችን) እንደሆነች ማሰቡ ራሱ ደስ አይልም!? ሲያልፍም ልጅት በምርምር ኢንስቲትዩቱ ተመራማሪ ሆና ከተሰየመች ቆይታለች። ከእንግዲህ Malariaን ምን ይውጣት ይሆን!?
ስለርሷ ደስ ብሎኛል፣ ቀጥሎም ደስ ይለኛል። እንደው ከእለቱ ግድንግድ ደስታዎቼ አንዱን ላጋራችሁ ብዬ ነው። ልጅት ማን ናት!? የምትሉና በቅርበት ልታውቋት የምትሹ (አ/አ ያላችሁ ዘመዶቼ) ስለ ስኬቷ አብረናት ቡና ልንጠጣ ማቀድ እንችላለን። ወንድሞች ግን አረጋጉት። የ'ኛ ልጅ በርቺ በርቺ! 😊
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 626 |
| 18 | እኛም...
---▣---
ከበርናባስ በቀለ
አንተ በአምሳልህ ፈጠርኸን፣ ለክብርህም ሠራኸን፤ እኛም ክቡር ፍጥረትህን በአምሳላችን ፈጠርን፣ ለገዛ ክብራችንም ስንዋደቅ አደርን።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 922 |
| 19 | እየተጓዝን ነው፤ "ወሬ አልሰማም አልምኮ ትቼ" የሚለው የዴቭ ዝማሬ በቲክቶኩ ተቀናብሮ እየሰማ ነው። ቀጥሎ Scroll አያደርግም ማለት ነው!? እሰይ! እኛም አረፍን።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 629 |
| 20 | ለናታን ቢኾን!
---▣---
ከበርናባስ በቀለ
ዝናቡ ከሰማይ
ቡቃያው ከምድር
ለናታን ቢኾን ለከድር
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊ | 648 |
