cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

ይህ የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት ቻናል ነው 👉👉ለጠቅላላ @weldwahid 👉👉ለአብነት እና ግእዝ ቋንቋ ትምህርት @weldwahidabinet 👉👉 ለቤተ መጻሕፍት አገልግሎት @Abaiyesuslib 👉👉ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @mels_asteyayet

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 012
مشترکین
+224 ساعت
+207 روز
+8130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
✨✨✨✨✨✨ዛሬ✨✨✨✨✨ 💍💍💍💍💍💍💍💍💍💍💍💍💍💍 “ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።” "መዝ 127፥3" 💍💍💍💍💍💍💍💍💍💍💍💍💍💍       🔔ሳምንታዊው የረቡዕ ጉባኤ🔔 ክፍል ፩ የወጣቶች ህይወት ከጋብቻ በፊት በመምህርና ጋዜጠኛ፦ ግሩም ንጉሤ             ⌚️ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ      ⛪️ በምዕራፈ ጻድቃን ሰንበቴ አዳራሽ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ከሚሰጡን አባቶች፣ ትምህርተ ወንጌል ከሚያካፍሉን መምህራነ ወንጌል ቀድሞ መገኘት የጉባኤ ስርዓት ነው፤ ደግሞም የእለቱን መርሐግብር በሰዓቱ ጀምሮ በሰዓቱ ለማጠናቀቅም ያግዘናል። 📋ማስታወሻ ደብተር (ወረቀት) እና ብዕር መያዛችሁ አትርሱ።     ❤  "ረቡዕ የትምህርት ቀን"
نمایش همه...
👍 2
“አንኳኩቼ አላገኘሁም” አትበል፡፡ ብቻ የለመንከው፣ ደጅ የጠናኸው አንተ የምትወደው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚወድልህ ይሁን፡፡ ወደ እግዚአብሔር የተዘረጋ እጅ ፈጽሞ ባዶውን አይመለስም፡፡ ስለዚህ ራስህን፣ ልመናህን ምን ዓይነት እንደሆነ ፈትሽ እንጂ አንኳኩቼ አላገኘሁም አትበል፡፡ እንኳንስ ንጹሐ ባሕርይ የሆነው እግዚአብሔር ክፋት የሚስማማው ምድራዊ አባትም ለልጁ ጀሮውን አይደፍንም፡፡ አስቀድሞ ሕያዊት ነፍስን “እፍ” ብሎ እንዲሁ የሰጠን ጌታ፣ ኋላም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጁን ሳይራራ ከሰጠን እንደምን በዚህ ይታማል? እንደምንስ አይሰጠንም እንላለን? /ሮሜ.8፥32/፡፡ ልጁን የሰጠው እኮ ጭራሽ “ስጠን” ብለው ላልለመኑ አሕዛብም ጭምር ነው፡፡ ታድያ እንዲህ የምንለምን እኛማ እንዴት አብልጦ አይሰጠንም? የሚበልጠውን ሰጥቶን ሳለስ እንደምን ትንሹን አይሰጠንም እንላለን? ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀውን ሳናደርግ “እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማም” የሚል የሰነፎች አባባል የምንናገር አንሁን፡፡ ጀሮን የፈጠረ ይሰማል!” #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ (ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ ገጽ 178)
نمایش همه...
"እንደ ጋኔን ቅናተኛ የለም፡፡ ቅናቱ ግን በሰው ልጆች ላይ እንጂ እርሱን በሚመስሉ አጋንንት ላይ አይደለም፡፡ ሰው ግን በገዛ ወንድሙ ላይ ይቀናል፤ በአጋንንት እንኳን በጭራሽ የማይደረግ በገዛ ቤተ ሰቡ ላይ ይቀናል፡፡ ታዲያ እንደዚህ ዓይነት ሰው እንዴት ይቅርታን ያገኛል? እንዴት ምሕረት ቸርነትን ያገኛል?" ~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ፩ኛ ቆሮ. ድርሳን ፴፩፥፯
نمایش همه...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
"ጋብቻ በአግባቡ ሊኖሩበት ለሚፈቅዱ ሰዎች የንጽሕና ደሴት ነው፤ የአንድ ሰው ተፈጥሮ አውሬያዊ እንዳይኾንም ይጠብቀዋል፡፡ አንድ ግድብ የሚፈስሰውን ውኃ ገድቦ እንደሚይዘው ኹሉ፥ ጋብቻም ሩካቤ ሕጋዊና ሥርዓት ያለው እንዲኾን ዕድል ይሰጣል፤ በዚህ መንገድ የሩካቤ ወንዝ መሻትን ይቆጣጠራል፡፡ ጸጥተኛ በኾነ ባሕር ውስጥ እንድንኾን ያደርገናል፡፡ ስርግርግ በሚል የዝሙት ማዕበል ውስጥ እንዳንሰጥም ይጠብቀናል፡፡ ይህን ትድግና (ረዳትነት) የማይፈለጉና በባሕሩ ላይ እስከ መጨረሻው ዋኝተው መሔድ የሚሹ አንዳንድ ሰዎች ግን አሉ፡፡ ከዚህ ከጋብቻ ደሴት ይልቅ በፆም፣ በትግሃ ሌሊት፣ መሬት ላይ በመተኛትና የትሕርምት ሕይወትን በመኖር ራሳቸውን መግዛት የሚፈልጉ አሉ፡፡ ለእነዚህ ሰዎች እንዳያገቡ እመክራቸዋለሁ እንጂ የግድ ከጋብቻ አልከለክላቸውም፡፡" ~ በእንተ ድንግልና፥ 9፥1 ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 🌹ሳምንታዊው የረቡዕ ጉባኤ🌹   " መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን "  ዕብ  13÷4         "ጋብቻ ወይስ  ጋር ብቻ? "                       ልዩ             ተከታታይ ትምህርት 📆 ከረቡዕ ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም  ጀምሮ ክፍል ፩ የወጣቶች ህይወት ከጋብቻ በፊት በመምህርና ጋዜጠኛ፦ ግሩም ንጉሤ             ⌚️ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ      ⛪️ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ 📋ማስታወሻ ደብተር (ወረቀት) እና ብዕር መያዛችሁ አትርሱ።                🔔🔔🔔🔔🔔              🔔  1 ቀን ቀረው🔔                 🔔🔔🔔🔔🔔
نمایش همه...
“ልጆቼ ፦ እግዚአብሄርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሄር ልናቀርብ ይገባናል ፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን? የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን? እንዲህ ከሆነ መሓሪ እግዚአብሄርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሄርን ፈልጉት ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሄርን ፈልጉት፤ እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሄርን ፈልጉት እግዚአብሄርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡” (ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ)
نمایش همه...
👍 2 1
"ታጋሽ ሆነን በተጋድሎኣችን ከተጋን፤ የሥራችን ዋጋ የሆነውን ፍቅረ እግዚአብሔርን እናገኛለን። ቀላል (የዋዛ ፈዛዛ) ሕይወት ያሳለፉ ቅዱሳንና ጻድቃን የሉም። ዘለዓለማዊ ሕይወታቸውን ያስዋበላቸው፥ ጠንካራ ሥራና ታላቅ ገድል ነው። በትዕግሥት ስናገለግል፤ መልካም ፍሬ እናፈራለን። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን እናያለን። ጊዜኣችንንም ሆነ ልባችንን ለእርሱ እናስገዛለን። መረጋጋትና መጽናናትንም ስለምናገኝ፤ የደረሰብን ችግርም ሆነ መከራ ከምንም የማይቆጠርና የተረሳ፣ ተራ ነገር ይሆናል።" 🔥እማሆይ ማርታ🔥 💥በረከቷ በሁላችን ይደር!💥 *አሜን! ይሁን ይደረግልኝ!*
نمایش همه...
5👍 1
🌿ሰላምና ደኅንነት 🌿 ሰላም ደኀንነት መንፈሳዊ ሕይወትን ያደላድላል ፦"ስለዚህ ፤ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ ፦ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቁጣም የዘገየ ይሁን ፤ ..." ያዕ 1÷19። "ሳሙኤልም ፦ በውኑ የእግዚአብሔር ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ ፦ መታዘዝ ከመሥዋዕት ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል ።" 1ኛ ሳሙ 15÷22
نمایش همه...
4
Photo unavailableShow in Telegram
ኦርቶዶክሳዊ ትዳር፥ በክርስቶስ ወደ ክርስቶስ የሚያደርጉት ጉዞ ነው። ከኃጢአት እየነጹ በምግባርም እየጎለመሱ የሚሔዱት መዳረሻው ሱታፌ ክርስቶስ የኾነ ጉዞ ነው። ከኃጢአት ለመንጻትና በምግባር ለመጎልመስም ራሱን የቻለና የሚጠበቅ ተጋድሎ አለው። ብዙዎች ይህ የሚጠበቀውን ተጋድሎ "ለመፍታት" አስበው፥ ትዳራቸውን ከኦርቶዶክሳዊ ዐውዱ አስወጥተው ፈትተውታል። በዚህ ጉባኤ ላይ ከትዳር አጋርዎ፣ ከዕጮኛዎ፣ ለብቻዎም ቢኾን ቢገኙ፥ ስለዚህ የሕይወት ጉዞ መሬት የረገጡ ምሳሌዎችን እያነሣን እንዴት ጽናትን ተላብሰን መጓዝ እንደምንችል ለተከታታይ ሳምንታት እናወጋለን። አዘጋጅ፦ የወልድ ዋህድ ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል ቀን፦ ዘወትር ረቡዕ ሰዓት፦ ማታ 12:00-1:45 የሚጀምርበት ቀን፦ 14/09/2016 ዓ.ም                    ✨✨✨✨ ✨✨✨✨2 ቀን ቀረው✨✨✨✨                     ✨✨✨✨
نمایش همه...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ ። የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ ። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ። (መልክአ ሚካኤል) ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ጠላት ይጠብቀን፤ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።
نمایش همه...
2👍 1
🥰 4