💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
رفتن به کانال در Telegram
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
نمایش بیشتر8 835
مشترکین
-924 ساعت
+297 روز
-1130 روز
آرشیو پست ها
አሰላሙአለይኩም
~
አድስ ከኢቶ የመጣሸ እህት ካለሸ ስራ የፈታሸ
በ1500ሪያል ነይ የሆነ ስራ አለ
@Umu_Abdella_t
Repost from ስለ ቀልባችን
▫️ውድ እህቴ ይህ የምትጠይቂው ጥያቄ የብዙ እህቶቻችን የልብ ትርታ፣ የብዙ ቤተሰቦች ጭንቀት ነው።
✔️እህቴ... ምክሬን የምጀምረው «የሴት ልጅ እድሜ እንደ ጤዛ ነው» በሚለው ሀቅ ነው። ጤዛ ተኝቶ ሲነቁ ይጠፋል፤ የሴት ልጅም ወጣትነትና ውበት እንደዚሁ ነው። እድሜ መቆሚያ የለውም፤ ጊዜው ደግሞ ፈታኝ ነው። እናትሽ የሚጨቀጭቁሽ ይህ «ጤዛነትሽ» እያሳሰባቸው፣ ነገ እድሜሽ ገፍቶ ብቻሽን እንዳትቀሪ ካላቸው የናትነት ፍቅርና ስስት የመነጨ ነው።
🎯ወደ ዋናው ነጥብ ስመጣ፤ «ሁለተኛ መሆንን መፍራትና እንደ ነውር መቁጠር»
ውድ እህቴ! ዛሬ ላይ ብዙ ሴቶች «ከሌሎች እህቶች ምን ይጎድለኛል?»፣ «እንዴት ተደራቢ እሆናለሁ?» በሚል ስሜትና በፊልም በተለከፈ አስተሳሰብ ምክንያት ወርቃማ እድሎችን እያበላሹ፣ በመጨረሻም ወይ ፈላጊ በማጣት ወይም የማይሆን ሰው አግብቶ በመጦር ይቆጫሉ።
💭ልንገርሽ ስሚኝ! በድናችን ሁለተኛ ሚስት ማለት ግማሽ ሚስት ወይም ትርፍ ሚስት ማለት አይደለም። ሁለተኛ ሚስት ማለት ልክ እንደ መጀመሪያዋ ሚስት ሙሉ መብት ያላት፣ ክብር ያላት፣ የቤት እመቤት ናት። ሁለተኛ፣ ሶስተኛ ወይም አራተኛ መሆን ነውርም፣ ውርደትም፣ መቀነስም አይደለም።
እስቲ ቆም ብለሽ አስቢ፤
እናቶቻችን (የነብዩ ﷺ ሚስቶች)፣ ምርጥ የሆኑት ሶሀብያቶች አብዛኞቹ እኮ ሁለተኛ፣ ሶስተኛና አራተኛ ሆነው ነው የኖሩት። ታዲያ ለእነሱ ያልሆነው ውርደት ለአንቺ እንዴት ውርደት ይሆናል?ይህ ዲን የሰጠሽ መብት እንጂ ባህሉ የሰጠሽ ስም አይደለም።
🎀እህቴ ሆይ! ላንቺ የሚጠቅምሽ ብቸኛ ሚስት ሆኖ ከማይረባና ዲን ከሌለው፣ አላህን ከማይፈራ ሰው ጋር መኖር ወይስ አላህን ከሚፈራ፣ ዲን ካለው፣ ከሚያከብርሽና ከሚንከባከብሽ ሰው ጋር ሁለተኛ ሆኖ በክብር መኖር? ምርጫው ግልፅ ነው። ስንትና ስንት ብቸኛ ነኝ ብለው ያገቡ እህቶች ዛሬ በትዳራቸው ሲሰቃዩ እናያለን። በአንጻሩ ደግሞ ስንትና ስንት በሁለተኛነት የገቡ እህቶች፣ ባሎቻቸው አላህን የሚፈሩ በመሆናቸው ምክንያት የልብ ሰላም አግኝተው፣ ዲናቸውን ጠብቀው ይኖራሉ።
አሁን ላይ እድሜሽ በሃያዎች መጨረሻ ላይ ነው። ነገ ወደ ሰላሳዎቹ ስትገቢ ምርጫዎችሽ እየጠበቡ መምጣታቸው አይቀርም። የመጣው ሰው አላህን የሚፈራ፣ ስነ-ምግባሩ ያማረ፣ ሊያስተዳድርሽ አቅም ያለው ከሆነ፤ መስፈርቱን ካሟላ 2ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛም ቢሆን እሺ ብለሽ ማግባት የብልህ ሴት ውሳኔ ነው።
🌟ስለዚህ መፍተሔ ብየ የምመክርሽ፦
✅️የእናትሽን ምክር ስሚ።እናትሽ "አግቢ" የምትለው ካየችው የህይወት ተሞክሮ ነው። የምትሰሪው ስራ፣ የምታገኘው ደሞዝ፣ የለበስሽው ዘመናዊ ልብስ የባልን ቦታ አይተካም፣ የልጅን ጣም አይሰጥም።
✅️መስፈርትሽን ቀለል አድርጊ።እንዲህ ካልሆነ፣ ካልተማረ፣ ካልከበረ...የሚሉ መስፈርቶችሽን ወደ ጎን ትተሽ፤ ዲን አለው ወይ? አላህን ይፈራል ወይ? ጥሩ ስነ-ምግባር አለው ወይ? የሚለውን ብቻ አጥብቀሽ ያዢ።
✅️ሁለተኛ መሆንን አትጥይ። ሸይጣን የሚያስፈራራሽን ሀሳብ ትተሽ፤ አላህ የፈቀደውን ሀላል አትግፊ። ጥሩ ወንድ ከመጣ አግብቶ የፈታ ነው፣ ወይም ሚስት አለው ብለሽ አትመልሺ። ጨዋና ዲን ያለው ባል በዘመናችን ውድ ነው። ካገኘሽው አትልቀቂው።
✅️ዱዓ አድርጊ። ያ አላህ! ለአንተ ብዬ፣ ዲኔን ለመጠበቅ ብዬ የመጣውን ሀላል ተቀብያለሁና አንተ ደግሞ ህይወቴን አሳምርልኝ፣ ባሌን መልካም አድርግልኝ፣ትዳሬን የተባረከ አድርግልኝ ብለሽ ለምኚው።
💡ውድ እህቴ! ትዳር የኢማን ግማሽ ነው። ግማሽ ኢማንሽን ለመሙላት፣ እራስሽን ከፊትና ለመጠበቅ፣ እናትሽንም ለማስደሰት ስትይ፤ ከመጣው አማራጭ ውስጥ መርጠሽ፣ ቁጥር ሳትቆጥሪ በሀላል ተሳሰሪ። አላህ መልካም፣ ሩህሩህና አላህን ፈሪ የሆነ ባል ይስጥሽ። መጨረሻሽን ያሳምረው።
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
🔖ሁሌም እጃችሁን ወደጌታቹህ ከፍ ስታደርጉ በመልካም ዱአቹህ እህት ወንድሞቻችሁን አትርሱ!
ሙዕሚን ከራሡ አልፎ የሌሎች ጭንቀት የሌሎች ማጣት ያሣሥበዋል! አትርሱ እናንተ ለሌሎች ስትቆሙ አላህ ለእናንተ ይቆማል።
Repost from «🔵Abu_Aisha (Awel_kasaw)»
አሏህን ማውሳት!!
2ተኛው ፕሮግራም በኡስታዝ አቡ ሓቲም ተጀመሯል፡
https://t.me/+KgW1mviu_thiOGQ0
Repost from Abu_Oubeida~channel
ታላቅ የዳዕዋ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም
እነሆ የፊታችን ጁመአ ከምሽቱ 3:00 በመርከዝ ኢብኑ አባስ በታላላቅ የሱና መሻይኾችና ኡስታዞች በአይነቱ ልዩ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ እየጠበቃችሁ ነው።
በፕሮግራሙ ላይ የሚታደሙት ተጋባዥ እንግዶቻችን
1) ሸይኽ አወል አሕመድ (አቡ አማር) ሐፊዘሁሏህ
2) ኡስታዝ ኸድር አሕመድ (አቡ ሐቲም) ሐፊዘሁሏህ
3) ኡስታዝ አብዱል መሊክ ሐፊዘሁሏህ
4) ኡስታዝ አቡ ኢምራን ሐፊዘሁሏህ
5) ኡስታዝ ሙሐመድ አያሌው ሐፊዘሁሏህ
6) ኡስታዝ አቡ ሹራ ሐፊዘሁሏህ
7) አስታዝ ዓሊይ ዩሱፍ (አቡ ሐሳን) ሐፊዘሁሏህ
እና ሌሎችም ስማቸው ያልተጠቀሱ ብርቅዬ የሱና ኡስታዞች ወንድሞችም ፕሮግራሙን ባማረ እና በደመቀ መልኩ ያሳምሩታል
ፕሮግራሙ የሚመሩት
አቡ ዑበይዳ እና አቡ ማሒ
ማሳሰቢያ
እንዳትቀሩ (መቅረት አይደለም ማርፈድም አይቻልም)
አድስ ነገርም አለ የሚነገራችሁ (ተናገሪያለሁ ከወዲሁ)
➥በየት ነው የምትገኙት ለምትሉን
አድራሻችን ይሄው ➠https://t.me/+lmLw2jJXwF45Zjdk
ተቀላቀሉ ሼርም አድርጉ
ለእህቶቸ ማስታወሻ!!
ቫዝሊን ፦ሎሽን የተለያዩ ሠዉነትን ማለስለሻዎች እንደፈለጋችሁ ወታችሁ መግዛት የማትችሉ በተለይ ጠለብ ያላችሁ እህቶች ከአረብ ቤት የማይጠፋ ነገር ላመላክታችሁ።ይህም ዘይዘይቱን ነዉ ማታ ማታ ሰዉነታችሁን ተቀቡት።የሹዐይብ ጥሪ!
~
((وَيَا قَوْمِ أَوْفُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِينَ * بَقِيَّتُ اللَّهِ خَيْرٌ لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ ۚ وَمَا أَنَا عَلَيْكُمْ بِحَفِيظٍ)
«ሕዝቦቼም ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ፡፡ ሰዎችንም ምንም ነገራቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ፡፡ አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ ምእመናን እንደሆናችሁ (አላህ በሰጣችሁ ውደዱ)፡፡ እኔም (መካሪ እንጅ) በናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም፡፡» [ሁድ: 85–86]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
🔖 ከአኺራው ጀነት በፊት በዱንያው ጀነት ውስጥ እራስህን ማግኘት ከፈለግክ የጥዋት እና የማታ ዚክር ላይ ተጠናከር።
~
الأيام ثلاثة...قالَ ابنُ الجَوزِي -رَحِمَهُ الله تَعَالَى : - «يا هَذا، الأيَّامُ ثلاثةٌ: ~أمسٍ قَد مضَىٰ بِمَا فِيه، ~وغَدٍ لعلَّكَ لا تُدرِكُه، ~وإنَّما هُوَ يومُكَ هَذا، فاجتَهِدْ فِيه،
ولِلَّـهِ درُّ مَن تنبَّهَ لِنَفسِه، وتزوَّدَ لِرَسمِه، واستدرَكَ ما مضَىٰ مِن أمسِهِ قبلَ طولِ حَبسِه».📘 التبصِرَةُ: (١٥٨/١)
وأنّهُ لاَ مُستراح للرُّوحِ ولا لذّةٌ للقلبِ إلاّ بالعيشِ فِي رِحاب القُرآن!.
«ከሰው ሁሉ ጠንካራ መሆን ያሰኘው ሰው በአላህ ላይ ብቻ ይመካ»።
ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ)
ምንጭ፦📚 ዛዱል መዓድ (2/364)
=
✅ የተከበሩ ወራቶች!
ከአቢ በክራህ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إنَّ الزَّمانَ قَدِ اسْتَدارَ كَهَيْئَتِهِ يَومَ خَلَقَ اللَّهُ السَّمَواتِ والأرْضَ، السَّنَةُ اثْنا عَشَرَ شَهْرًا، مِنْها أرْبَعَةٌ حُرُمٌ، ثَلاثٌ مُتَوالِياتٌ: ذُو القَعْدَةِ، وذُو الحِجَّةِ، والمُحَرَّمُ، ورَجَبُ، مُضَرَ الذي بيْنَ جُمادى، وشَعْبانَ.﴾
“አላህ ሰማይና ምድርን በፈጠረ ግዜ አመትን አስራ ሁለት ወር አድርጎቸዋል።
ከነሱ ዉስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሶስቱ ተከታታይ ሲሆኑ፤ ዙልቂእዳ ዙልሂጃና ሙሀረም ናቸው። ሌላው ደግሞ በጁማዳና በሻዕባን መካከል ያለው የሙደር (ጎሳዎች የታወቁበት) የ”ረጀብ” ወር ነው።”
📚 ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበውታል
t.me/https_AsselfyaRepost from አቡ ሙዓዝ (Abu muaz)
እኛው ለእኛው የሙሓደራ ዝግጅት
====
እነሆ ነገ እሁድ ማታ 2:30 ላይ በገራዶ ቢላል መስጅድ የግንባታ ግሩፕ ላይ የደዕዋና የምክክር እንድሁም የቻሌንጅ ቅየራ ፕሮግራም ይኖረናል።
ተጋባዥ እንግዶቻችን
አቡ ሙአዝ
አቡ ዓኢሻ
ሌሎችም ይኖራሉ ኢንሻአሏህ
ስለሆነም ሼር ሼር እያደረጋቹህ ለወዳጅ አዝማድ እያደረሳቹህ ጠብቁን ባረከሏሁ ፊኩም።
https://t.me/geradobilalmesjid
ዶዒፍ!
~
اللَّهمَّ بارِكْ لَنا في رجبٍ وشعبانَ وبلِّغنا رمضانَ
"አላህ ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ባርክልን። ረመዷንን ደግሞ አድርሰን።"
-
ነወዊ፣ ኢብኑ ሐጀር፣ አልባኒ፣ . . . ዶዒፍ (ለመረጃ ብቁ ያልሆነ) እንደሆነ ገልፀዋል።
=
