fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Gondar City Education Department

Gondar City Education Department

رفتن به کانال در Telegram

ይህ የጎንደር ከተማ አስ/ትምህርት መምሪያ የቴሌ ግራም ቻናል ነው። የፌስቡክ ገጻችንንም ይከተሉ፦ https://www.facebook.com/GondarEdu ወቅታዊና ጠቃሚ ትምህርት ነክ መረጃዎችን ያገኙበታል።

نمایش بیشتر
3 836
مشترکین
+1624 ساعت
+467 روز
+17930 روز

در حال بارگذاری داده‌ها

ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
نوامبر '26
نوامبر '26
+52
در 0 کانال‌ها
اکتبر '26
+190
در 2 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '26
+94
در 1 کانال‌ها
Get PRO
اوت '26
+177
در 3 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '26
+410
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '26
+1 320
در 5 کانال‌ها
Get PRO
مه '26
+857
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '260
در 2 کانال‌ها
Get PRO
مارس '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '250
در 1 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '250
در 1 کانال‌ها
Get PRO
اوت '250
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '250
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '250
در 1 کانال‌ها
Get PRO
مه '250
در 3 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '250
در 1 کانال‌ها
Get PRO
مارس '250
در 1 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '250
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '250
در 1 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '24
+32
در 1 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '24
+61
در 1 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '24
+84
در 1 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '24
+39
در 2 کانال‌ها
Get PRO
اوت '240
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '240
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '240
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '240
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '240
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '240
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '240
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '240
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '230
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '230
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '230
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '23
+1
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '23
+9
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '23
+107
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '23
+284
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '23
+26
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '23
+69
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '23
+44
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '23
+15
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '23
+19
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '22
+18
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '22
+17
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '22
+21
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '22
+43
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '22
+128
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '22
+48
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '22
+349
در 0 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشارات
کانال‌ها
06 نوامبر+6
05 نوامبر+17
04 نوامبر+4
03 نوامبر+4
02 نوامبر+7
01 نوامبر+14
پست‌های کانال
CamScanner 05-11-2026 11.32
CamScanner 05-11-2026 11.32

2
بدون متن...
1 920
3
የተሻሻለው በቅድመ አንደኛ፣ በአንደኛ እና በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በማስተማር ላይ ላሉ መምህራን የክፍል ምደባ መመሪያ ቁጥር 61/2018 ዓ.ም
4 552
4
​🔥 ነፃ የክህሎት ስልጠና እና የዲጂታል ሥራ ዕድል ማስታወቂያ! 🔥 ​ራሳችሁን በዘመናዊ የክህሎት ዘርፎች በማበልፀግ የዓለም አቀፍ የዲጂታል ሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን ይፈልጋሉ? ​በጎንደር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ እና በአሜሪካ ሃገር ነዋሪ በሆኑት ተባባሪ መስራች አቶ ሀቢቡ ታከለ ጥረት የተመሰረተውና ህጋዊ እውቅና ያገኘው እርካብ የክህሎት ማሰልጠኛ የበጎ አድራጎት ድርጅት በ2019 ዓ.ም በአጫጭር የክህሎት ስልጠና ዘርፎች ሰልጣኞችን በየ3 ወሩ አሰልጥኖ የዲጂታል የስራ እድል ለመፍጠር ዝግጅቱን አጠናቋል! ​በመጀመሪያው ዙር የነፃ የትምህርት እድል ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት 10 የስልጠና ዘርፎች ውስጥ ለአንድ ሰልጣኝ ቢያንስ 2 የትምህርት ዘርፎችን በመምረጥ መመዝገብ ይችላሉ። ​🎯 የሚሰጡ የስልጠና ዘርፎች (Courses): 1️⃣ Website Fullstack Developer 2️⃣ Mobile App Fullstack Developer 3️⃣ AI & Machine Learning (AI & ML) 4️⃣ Data Science 5️⃣ Cybersecurity 6️⃣ Remote Work Fundamentals & Freelancing 7️⃣ Business English & Digital Entrepreneurship 8️⃣ Climate-Smart Urban Agriculture 9️⃣ Small Scale Manufacturing 🔟 Content Creation (TikTok, YouTube, Graphic Design, Video Editing) ​📅 የምዝገባ ጊዜ እና ቦታ፦ • ​የምዝገባ ቀን፦ ከጥቅምት 13 እስከ 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ብቻ! (ፈጥነው ይመዝገቡ!) • ​አድራሻ፦ ጎንደር ከተማ ​🔗 የምዝገባ ሊንክ (Google Form): 👉 እዚህ በመጫን ይመዝገቡ ​💡 ከክህሎት ወደ ሥራ ዕድል! እርካብ – ዓለም አቀፍ ግንኙነት ​#FreeTraining #DigitalSkills #Gondar #Education #SkillDev
3 547
5
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የስቴም (Science, Technology, Engineering and Mathematics) ማዕከል የፈጠራና የቴክኖሎጂ ውድድር ተካሄደ ─── ​የነገዎቹን ሳይንቲስቶችና ችግር ፈቺ ተመራማሪዎች ለማፍራት ያለመ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የፈጠራና የቴክኖሎጂ ውድድር (Local Science Fair) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የስቴም (STEM) ማዕከል የመሰብሰቢያ አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ። ​ጥቅምት 11 እና 12 ቀን 2019 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ የፈጠራ መድረክ ላይ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 12 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡና በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እንዲሁም ኢኖቬሽን ዘርፍ የተለየ ተሰጥኦ ያላቸው 39 ተማሪዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለውድድር አቅርበዋል። ከእነዚህ ከተሳተፉ 12 ት/ቤቶች መካከል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት፣ የዩኒቨርሲቲው አዳሪ ትምህርት ቤት፣ የፋሲለደስ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2፣ የደብረሰላም ፣ የኪንግስና የአንገረብ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ይገኙበታል። ​በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አይንሸት አዳነ፤ መሰል የሳይንስ ፌሮች ገና በትምህርት ገበታ ላይ ያሉ ታዳጊዎች የፈጠራ እሳቤዎቻቸውን ለህዝብ የሚያቀርቡበት፣ ከባለሙያዎችና መምህራን ገንቢ ግብአቶችን የሚያገኙበት እንዲሁም ለበለጠ ስኬት የሚያንሰራሩበት ትልቅ ድልድይ መሆናቸውን ገልጸዋል። አያይዘውም ውድድሩ ማሸነፍን ብቻ አላማ ያደረገ ሳይሆን ተማሪዎች አዳዲስ እውቀቶችንና ክህሎቶችን የሚያካብቱበት መሆኑን ጠቁመው፤ ዩኒቨርሲቲው የወጣቶችን የፈጠራ እሳቤ ከጅምር እስከ ምርትና ንግድ (Commercialization) ለማድረስ የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶችንና የሰለጠነ የሰው ሃይል ለማሟላት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ​የውድድሩን አጠቃላይ ሂደት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የዳኞች አስተባባሪና የኢንኩቤሽን ማዕከሉ አስተባባሪ አቶ አንተነህ በላይ፤ ውድድሩ አፕላይድ ሳይንስ (Applied Science) እና ሲስተም ዲቨሎፕመንት (System Development) በሚሉ ሁለት ዋና ዋና ዘርፎች ተከፍሎ መካሄዱን ገልጸዋል። በዚህም መሰረት ከየዘርፉ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የወጡ የፈጠራ ባለቤቶች የገንዘብና የምስክር ወረቀት ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን፣ በቀጣይ አዲስ አበባ ላይ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ውድድር ላይ ማዕከሉን ወክለው የሚሳተፉ ተማሪዎች ተመርጠዋል። በአፕላይድ ሳይንስ ዘርፍ በረከት እዮብ 1ኛ በመውጣት ሲመረጥ፣ በሲስተም ዲቨሎፕመንት ዘርፍ አማኑኤል ተፈራና ቡድኑ እንዲሁም የመሳፍንት ውቤ ቡድን ማዕከሉን ወክለው እንዲወዳደሩ ተለይተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከአንገረብ ት/ቤት ተማሪ ዋሴ ደርሶ ልዩ ተሸላሚ በመሆን በተመሳሳይ የገንዘብና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶለታል። ​በመርሃ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የማዕከሉ ዋና አስተባባሪ አቶ ግርማ ወርቄ፤ ተማሪዎች አሁን ያሉበትንና የአለም አቀፍ ችግሮችን ጠልቀው በመረዳት የነገዋን አለም የሚቃኙ መፍትሄ አመንጪዎችና ሳይንቲስቶች እንደሚሆኑ ያላቸውን ትልቅ ተስፋ ገልጸዋል። የጎንደር ከተማ ትምህርት መምሪያ የስርዓተ ትምህርት ባለሙያ አቶ ጋሻው እሸቴ በበኩላቸው፤ የስቲም ማዕከሉ ተማሪዎች ተሰጧቸውና ክህሎታቸውን አውጥተው እንዲጠቀሙበት ያመቻቸውን እድል በማድነቅ፣ ተማሪዎች ከአካባቢያቸው ነባራዊ ችግሮች በመነሳት በቴክኖሎጂ የተደገፉ መፍትሄዎችን እንዲያመጡ ጥሪ አቅርበዋል። ​የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን ተገኘ በማጠቃለያ ንግግራቸው፤ ከዚህ ቀደም ከዚሁ ማዕከል የፈለቁ ተማሪዎች በሀገር አቀፍና እንደ NASA (ናሳ) ባሉ አለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ትልቅ ቦታ መድረሳቸውን አውስተው፣ ተወዳዳሪዎች ወቅቱ የሚጠይቀውን እውቀትና ክህሎት በመታጠቅ ከዚህ በላይ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ዶክተር ካሳሁን አያይዘውም ለመርሃ ግብሩ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል። ​በዕለቱ የተማሪዎች የፈጠራ ስራዎች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የማዕከሉ ተገልጋይ የነበረውና አሁን ላይ በግል ስራ ፈጠራ የተሰማራው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ወጣት ዮሃንስ ጥላሁን ለገበያ ያቀረበውን የፈጠራ ስራ በማቅረብ ለተማሪዎቹ ተሞክሮውን አካፍሏል። ​በመድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪ ትስስርና የማህበረሰብ አሳታፊነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ክብሮም አድኖ፣ የማዕከሉ አሰልጣኞች፣ የውድድሩ ዳኞች፣ የትምህርት መምሪያ ባለሙያዎች፣ ወላጆችና ተማሪዎች ታድመዋል። ─── ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ትስስር የተወሰደ
2 632
6
እንገናኝ
1
7
+2
بدون متن...
2 224
8

9
+3
بدون متن...
1
10
📢 በ2019 የትምህርት ዘመን በልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ቅበላ ውድድር ማስታወቂያ! ​በጎንደር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ስር በሚገኙ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች+1
📢 በ2019 የትምህርት ዘመን በልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ቅበላ ውድድር ማስታወቂያ! ​በጎንደር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ስር በሚገኙ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ለምትማሩ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል መፈርቱ የምታሟላ ተማሪዎች በልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ለመማር የውድድር ማስታወቂያ የወጣ መሆኑን እየገለጽን በተገለጸው ጊዜ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን። ​📅 የምዝገባ ጊዜ፡ ከጥቅምት 9 እስከ ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም (በመንግስት የሥራ ሰዓት) 📍 የምዝገባ ቦታ፡ ፋሲለደስ 2ኛ ደረጃ፣ አዘዞ 2ኛ ደረጃ እና ዋልያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 📑 የሚያስፈልጉ ሰነዶች፡ ከላት የተጠቀሱ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ፣ እንዲሁም መታወቂያ። ​📧 ለተጨማሪ መረጃ፡ gondareducation@gmail.com ጥያቄዎቻችሁ መላክ ትችላላችሁ።
4 797
11
📢 ለመምህራን የወጣ የውድድር ጥሪ ማስታወቂያ! ​በጎንደር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተቋቋመ የሚገኝ ሲሆን በተቋሙ የሚያስተምሩ መምህራንን በውድድር መድቦ
📢 ለመምህራን የወጣ የውድድር ጥሪ ማስታወቂያ! ​በጎንደር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተቋቋመ የሚገኝ ሲሆን በተቋሙ የሚያስተምሩ መምህራንን በውድድር መድቦ ማሰራት ይፈልጋል። ​📌 አጠቃላይ መስፈርቶችና መረጃዎች • ​የትምህርት ደረጃ፡ በትምህርት ዘርፍ ሁለተኛ ዲግሪ (Master's) እና ከዚያ በላይ (በአፕላይድ ሳይንስ ለተመረቁ PGDT ሰርተፊኬት ያለው/ላት) • ​የመምህርነት ማዕረግ፡ «መምህር» እና ከዚያ በላይ • ​የትምህርት ዓይነቶች፡ አማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ሂሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ሰማጎ፣ አግሪካልቸር፣ ጂኦግራፊ፣ ታሪክ፣ የዜግነት ትምህርት፣ አይሲቲ (ICT) እና ኢኮኖሚክስ • ​ጥቅማጥቅም፡ ደሞዝ በያዙት ደረጃ ሆኖ እንደ ልዩ ትምህርት ቤቱ ደንብ ቶፕ አፕ ክፍያ ይፈጸማል። ​🗓 የምዝገባ ሁኔታዎች • ​📅 የምዝገባ ጊዜ፡ ከጥቅምት 9 እስከ ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም (በመንግስት የሥራ ሰዓት) • ​📍 የምዝገባ ቦታ፡ ጎንደር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 • ​📑 የሚያስፈልጉ ሰነዶች፡ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ዋናውና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ ​📊 የምልመላና መረጣ መስፈርት • ​📝 የጽሁፍ ፈተና፦ 50% • ​👨‍🏫 የተግባር ማስተማር ምዘና፦ 30% • ​💼 የሥራ ልምድ፦ 15% • ​📈 የቅርብ ጊዜ የሥራ አፈፃፀም ምዘናና የማህደጥራት፦ 5
2 400
12
📢 የማስታወቂያ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤ ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ክፍት ቦታዎች ተ
📢 የማስታወቂያ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤ ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ክፍት ቦታዎች ተማሪዎችን ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ መወሰኑን እንገልጻለን። 📝 የፈተናው ዝርዝር መረጃ 📅 የፈተናው ቀን፦ መጪው ቅዳሜ፣ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም ⏰ የመግቢያ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት 📍 የፈተና ቦታ፦ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን (Online) በተሰጠባቸው የፈተና ማዕከላት ⚠️ ማሳሰቢያ፦ ተማሪዎች ፈተናውን አልፈው በሚመደቡባቸው የትምህርት ቤቶች ለመማር ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
2 968
13
መመሪያ ቁጥር 51-2018ዓ.ም (2).pdf
3 787
14
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የዕውቅናና ሽልማት መመሪያ
1
15
የመምህርነት ምልመላ+8
የመምህርነት ምልመላ
5 865
16
የቅጥር #ማስታወቂያ 📢 የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት 🏫+2
የቅጥር #ማስታወቂያ 📢 የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት 🏫
2 551
17
መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል። በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል። ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው። በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል። አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል። በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል። በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል። በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል። የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል። አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል።
4 144
18
1148_የአጠቃላይ_ትምህርት_መምህራን_የደረጃ_እድገት_አፈጻጸም_1.pdf
1
19
የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያን ይፋ አደረገ። የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ ተፈጻሚ የሚሆን "የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1148/2018" አውጥቷል። ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ያዘጋጀው ይህ መመሪያ፣ በማስተማር ሥራቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ መምህራንን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በመመሪያው ድንጋጌ መሠረት የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የእድገት መሰላል በሰባት ደረጃዎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ እነሱም ፦ - ጀማሪ መምህር፣ - መለስተኛ መምህር፣ - መምህር፣ - ከፍተኛ መምህር፣ - ተባባሪ መሪ መምህር፣ - መሪ መምህር እና ከፍተኛ መሪ መምህር ናቸው። በመመሪያው የተቀመጠው የቆይታ ጊዜም ከጀማሪ ወደ መለስተኛ መምህርነት ለመሸጋገር 2 ዓመት፣ በቀጣዮቹ ደረጃዎች ደግሞ በእያንዳንዱ እርከን የ3 ዓመታት ቆይታ የሚጠይቅ ነው። ይሁን እንጂ አንድ መምህር በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ በውድድር ሁለት ጊዜ እድገት ማግኘት ካልቻለ ለሦስተኛ ጊዜ የመወዳደር ዕድል እንደማይኖረው በመመሪያው ተደንግጓል። መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል። በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል። ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው። በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል። አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል። በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል። በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል። በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል። የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል። አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል።
3 700
20
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የፀደቁና በፍትህ ቢሮ የተመዘገቡ መመሪያዎች ለማግኘት ይፈልጋሉ። ንግዲያውስ ከታች 👇 በሃሳብ መስጫ ሳጥን ላይ የተጠቀሱትን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የፀደቁና በፍትህ ቢሮ የተመዘገቡ መመሪያዎች ለማግኘት ይፈልጋሉ። ንግዲያውስ ከታች 👇 በሃሳብ መስጫ ሳጥን ላይ የተጠቀሱትን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆች ይከተሉ/ይወዳጁ። ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ወቅታዊ እና ጠቃሚ የትምህርት መረጃዎችን ያግኙ! 📚✨ Facebook: https://www.facebook.com/share/1EozHfa3kB/ WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbBFbyrGZNCxP1X9ZI3w X: https://x.com/AmharaEducation
2 188