cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Amhara Education Bureau Books

Amhara Education Bureau Books Ethiopian New Curriculum Text books and teacher guides አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተማሪዎች እና የአስተማሪዎች መጽሐፍ

نمایش بیشتر
أثيوبيا5 388زبان مشخص نشده استآموزش38 437
پست‌های تبلیغاتی
2 988
مشترکین
+224 ساعت
+47 روز
+1130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መርሐ ግብር ይፋ ሆነ የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መርሐ ግብር ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡ የፈተና መርሐ ግብሩ በወረቀትና በበይነ መረብ የሚሰጠውን የፈተና የሚወስዱ ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ላሉ ተፈታኞች ነው ይፋ የተደረገው፡፡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው አካላት ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡ @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
نمایش همه...
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል 👉የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። 👉የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል። 👉በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #Entrance2016 @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
نمایش همه...
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር ይሰጣል12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል። የዩንቨርሲቲ መውጫ ፈተና ሰኔ መጀመሪያ ከተሰጠ በኋላ የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ይሰጣል። በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡ @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
نمایش همه...
ለ6ኛ ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኞች  ተማሪዎች 👉6ኛ ክፍል: ሞዴል ፈተና ከሚያዚያ 15 -18/8/2016 ዓ.ም - ክልል አቀፍ   ፈተና ከሰኔ  12-14/10/2016 ዓ.ም 👉የ8ኛ ክፍል : ሞዴል ሚያዚያ 15 -18/8/2016 ዓ.ም -  ክልል አቀፍ ፈተና  ከሰኔ 4-5/10/2016 ዓ.ም 👉12ኛ ክፍል : ሞዴል ፈተና ከሚያዚያ 15 -18/8/2016 ዓ.ም - ሀገር አቀፍ ፈተና  የሚምጥበት ቀን በቅርብ ይገለጻል! @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
نمایش همه...
በአራት ቢሊዮን ብር አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነው በአራት ቢሊዮን ብር አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሊገነባ መኾናቸውን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ በምዕራብ አማራ ዞኖች ከሚገኙ የትምህርት መሪዎች ጋር በወቅታዊ የትምህርት ሥራዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ኢየሩስ መንግሥቱ ክልሉ በዚህ ዓመት አራት ቢሊዮን ብር በመመደብ በደብረ ታቦር፣ በፍኖተ ሰላም እና በሰቆጣ ከተሞች አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡ በክልሉ 12ኛ ክፍልን ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች መካከል ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ነው ያሉት ኀላፊዋ ይህን በጎ ተሞክሮ ለማስፋፋት በቢሮው በኩል እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል። በአዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ለትምህርታቸው ሰፊ ጊዜ እንዲሰጡ እና እርስ በእርስ እንዲተጋገዙ ስለሚረዳ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ በኩልም የትምህርት ጥራትን ማምጣት ስለሚቻል መንግሥት ይህን ዘርፍ አጠናክሮ እየሠራበት ይገኛል ነው ያሉት፡፡ ወይዘሮ ኢየሩስ አክለውም ትምህርት ሚኒስቴር በራሱ ወጭ ደግሞ አንድ አዳሪ ትምህርት ቤት የሚገነባበት ቦታ እንዲሰጠው መጠየቁን ጠቁመዋል። በመኾኑም የባሕር ዳር ከተማ  አሥተዳድር የቦታ መረጣ እና ዝግጅት ሥራውን ወደ ማጠናቀቁ ደረጃ መድረሱን ተናግረዋል። @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
መምህር አይሸሽም ታከለ ይባላል በመተማ ዮሐንስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ያስተምራል፡፡ መምህር አይሸሽም የሚያስተምርበት ትምህርት ቤት አዲስና በ2012 የትምህርት ዘመን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ያስጀመረ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ይሁንና የትምህርት ቤቱ ቤተ መጽሃፍት የማጣቀሻ መጽሃፍት እጥረት ያለበት እና በአግባቡ ያለተደራጀ መሆኑ በእጅጉ አሳሰበው፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት መምህር አይሸሽም ፕሮጀክት በመቅረጽ የማጣቀሻ መጽሃፍትን ማሰባሰብ ጀመረ፡፡ በዚህም ከባጃጅ ሹፌሮች፣ ከወዛደር ማህበራት፣ ከግለሰቦች፣ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ከ 97 ሽህ ብር በላይ በማሰባሰብ በርካታ ማጣቀሻ መጽሐፍትን በመግዛት ለትምህርት ቤቱ አበርክቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መምህር አይሸሽም የመጽሐፍት መደርደሪያ ከሙያ አጋሩ ጋር በመሆን ለመስራት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ መረጃው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ነው:: @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
نمایش همه...
New Curriculum IT grade 8 Text Book Amhara @amhara_education
نمایش همه...
New Curriculum IT grade 7 Text Book Amhara @amhara_education
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ነባር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡ በዚህም የነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2016 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥር 2 እና 3/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለአንደኛ ዓመት እና ለሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ እሰከሚደረግ በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል:: #DebreTaborUniversity @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
نمایش همه...
የትምህርት ሚኒስቴር በአማራ ክልል ስላሉ ዩንቨርሲቲዎች የወሰነውን ውሳኔ መልሶ እንዲያጤነው የአማራ ተማሪዎች ማህበር ጠየቀ በአማራ ክልል የሚገኙ አስሩም የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ እንዲጀምሩ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ሚኒስቴሩ ይህንን ይበል እንጂ በክልሉ ያለው አሁናዊ ሁኔታ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራዎች ለመስራት ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት አስቻይ አለመሆኑ ይገለጻል፡፡ የአማራ ክልል ተማሪዎች ማህበር በበኩሉ በክልሉ ያለው የፀጥታ ችግር ባለበት እንደቀጠለ መሆኑ እየታወቀ የትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ይጀምሩ ማለቱ ትክክል አይደለም  ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው ይገባል ሲል ጠይቋል፡፡ የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አግማስ በየነ ተማሪዎቹ ለደህንነታቸው ዋስትና የሚሰጣቸው አካል በሌለበት ሁኔታ ወደ ተመደቡበት ትምህርት ተቋም መሄድ አዳጋች ነዉ ሲሉም አክለዋል፡፡ ከምንም ነገር በላይ የተማሪዎቹን ደህንነት መጠበቅ የሚቀድም በመሆኑ  ማህበሩ እንደ ተቋም ከሚኒስቴሩና ከትምህርት ተቋማት ጋር በመነጋገር ውሳኔውን ለማስቀልበስ የበኩሉን ጥረት እንደሚያደርግ አቶ አግማስ ገልጸዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ባሳለፍነው ሃሙስ ውሳኔውን ያሳለፈው ከክልሉ ኮማንድፖስት፣ የጸጥታ አደረጃጀቶችና የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ካደረገ በኋላ መሆኑን ገልጿል። ከክልሉ ዩንቨርስቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የባህር ዳር ዩንቨርሲም ተማሪዎቹ ሲመጡ ለደህንነታቸው ሃላፊነት መውሰድ ያለባቸው እራሳቸው ተማሪዎቹ እንደሆኑ በይፋ መግለጹ ይታወሳል፡፡ @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
نمایش همه...