cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🇪🇹 ኢትዮ Students

Our Bot : @EthioExamBot Contact : @ethioexamsupport Or @Etssupport

نمایش بیشتر
Advertising posts
56 896مشترکین
-3224 ساعت
-2447 روز
-91030 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

በአውስትራሊያ በቀጥታ ስርጭት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ጳጳስን ጨምሮ አራት ሰዎች በስለት ተወጉ፡፡ በጩቤ ከተወጉት መካከል የአሶራውያን ኦርቶዶክስ ጳጳስ ብጹዕ ቢሾፕ ማር ማሪ ይገኙበታል፡፡ በዋክሌይ በሚገኘው የክርስቶስ በጎ እረኛ ቤተክርስቲያን ድንገተኛ ሁከት ከተከሰተ በኋላ ውጥረት ነግሷል ተብሏል፡፡ ክስተቱ የተፈጸመው በምዕራብ ሲድኒ ዋክሌይ በሚገኘው የክርስቶስ መልካም እረኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው ሲል Anadolu Agency ዘግቧል። የጥቃቱ ዝርዝር ሁኔታ እስካሁን አልተረጋገጠም ያለው ፖሊስ ነገር ግን ብቻውን እንደፈፀመ የሚታመንበት ወንጀለኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛል ሲል አስታውቋል። (ቪዲዮው ከላይ ተያይዟል) @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
نمایش همه...
18 ሰዓታት በፈጀ  የቀዶ ህክምና 20 ሳ.ሜ ከፍታ ያለው የጭንቅላት እጢ በተሳካ ሁኔታ ተወገደ 18 ሰዓታት በፈጀ የጭንቅላት እጢ በቀዶ ህክምና ማስተካከል መቻሉን የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።በሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አለምሰገድ ጫኔ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በቀዶ ህክምናው ዋና ዋና ተግባራት በጭንቅላቱ ላይ የነበረውን 20 ሳንቲሜትር ከፍታ የለው እብጠት በቀዶ ህክምና እንዲወጣ ተደርጓል ። አያይዘውም እብጠቱ የወጣበትን ቦታ በሌላ የሰውነት ክፍል የመተካት ተግባር ተከናውኗል።በሶስተኛ ደረጃ ከታካሚው ከተለያዮ የሰውነት ክፍሎች ማለትም ከእጆቹ ላይ ደም ቅዳና ደም መልስ ተመሳሳይ ደም ስሮችን ወደጭንቅላቱ እንዲደርስ ተደርጓል  በማለት ለጣቢያችን ገልፀዋል። በአራተኛ ደረጃ ደግሞ በቀዶ ህክምና  ወቅት በሰውነት ክፍሉ የደም መፍሰስ ችግር እንዳይኖር አስቀድሞ በቂ ደም የመያዝና  የደም ስሮችን የመቋጠር ተግባር  መከናወኑ ተገልጿል።በመጨረሻም ታካሚው ከ18 ሰአታት በኋላ በፅኑ ህሙማን ክፍል እንደቆየ ተደርጓል ያሉት አቶ አለምሰገድ በአሁኑ ሰአት  በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል። በዚህም የተሳካ ቀዶ ህክምና የተሳተፉ የተለያዩ  ስፔሻሊስቶች ፣  ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች፣ አኒስቴትክስ፣ ነርሶች ፣ፖርተሮች እና ፅዳቶች  ሲያከናውኑ የነበሩ የቡድን አባላቶች ስራ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ  ተጠቅሷል።ዶ/ር አብዱራዛቅ  የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ስፔሻሊስት ባለሙያና የማክሮ ሰርጀሪ ሰብ ስፔሻሊስት በዚህ ህክምና ላይ ለተሳተፉ አጠቃላይ ሰራተኞች  ምስጋናቸውን  አቅርበዋል። #ዳጉ_ጆርናል @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
نمایش همه...
በሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በዛሬው እለት ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ያደረጉ ሁለት ግለሰቦች ሲገደሉ ፖሊሶች ቆሰሉ 👉🏼 ተጨማሪ ሌላ አንድ መንገደኛ ግለሰብም ተገድሏል በዛሬዉ እለት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ካደረጉ ሰዎች ዉስጥ ሁለቱ ሲገደሉ ሌላኛዉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። የአዲስአበባ ፖሊስ ፤ ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት ሰዎች በአዲስአበባ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሼባቸዋለሁ ያለ ሲሆን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆን ተኩስ ከፍተዋል ብሏል። ግለሰቦቹ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም  ከፖሊስ አባላት ጋር ተኩስ በመክፈታቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ገልጿል። በተጨማሪም ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል ተገድሏል ብሏል ፖሊስ፡፡ ሌላዉ አቤኔዘር ጋሻው አባት የተባለው ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ በመግለጫው መጥቀሱን ዳጉ ተመልክቷል፡፡ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ መቁሰላቸዉንም ፖሊስ አረጋግጧል። ሌላዉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ ታጣቂዎቹ  በመኪናቸው እንዲጭኗቸው  ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በታጣቂዎቹ ተገድለዋል ሲል ፖሊስ ወንጅሏል፡፡  አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ  80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ  ጨምሮ ገልጿል ፡፡ #ዳጉ_ጆርናል @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
نمایش همه...
😢 10👍 8 3😱 2🔥 1
በሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በዛሬው እለት ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ያደረጉ ሁለት ግለሰቦች ሲገደሉ ፖሊሶች ቆሰሉ 👉🏼 ተጨማሪ ሌላ አንድ መንገደኛ ግለሰብም ተደግሏል በዛሬዉ እለት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ካደረጉ ሰዎች ዉስጥ አንዱ ሲገደል ሌሎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። የአዲስአበባ ፖሊስ ፤ ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት ሰዎች በአዲስአበባ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሼባቸዋለሁ ያለ ሲሆን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ፅንፈኞቸ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆን ተኩስ ከፍተዋል ብሏል። ግለሰቦቹ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም  ከፖሊስ አባላት ጋር ተኩስ በመክፈታቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ገልጿል። በተጨማሪም ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል ተገድሏል ብሏል ፖሊስ፡፡ ሌላዉ አቤኔዘር ጋሻው አባት የተባለው የቡድኑ አባል ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ በመግለጫው መጥቀሱን ዳጉ ተመልክቷል፡፡ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ መቁሰላቸዉንም ፖሊስ አረጋግጧል። ሌላዉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ  ፅንፈኞቹ በመኪናቸው እንዲጭኗቸው  ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በታጣቂዎቹ ተገድለዋል ሲል ፖሊስ ወንጅሏል፡፡  አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ  80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ  ጨምሮ ገልጿል ፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
#ትዝብት_ከ_ቲክቶከር👇😂😂😂🙄 ለ2 አራት ምግብ በልተው ሂሳብ ሲባሉ የለንም ሰሃን እንጠብ አሉ። አይቻልም ደውላችሁም ቢሆን አስመጡ ተባሉ ። ቲክቶከሮች ነን በልቶ ያለመክፈል ቪዲዮ እየሰራን ነው ብለው የቆዩ ቪዲዮዎቻቸውን አሳዩ። ለሬስቶራንቱም ማስታወቂያ ነው ብለው ሰከሱ ። ባለቤቱና ጥበቃዎች ጓዳ አስገብተው መከሯቸው። ሰሃኑንም አጠቡ። ለማስታዎሻ ይህንን ፎቶ አነሷቸው ። ችግሮችን በመመካከር መፍታት ይቻላል። #huleadismedia @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENST
نمایش همه...
🔥 23👍 14😢 3👏 2 1
ሶፎኒያስ የገደሉት ተይዘዋል ወጣት ሶፎኒያስ አስራትን ገድለው ተሽከርካሪውን ዘርፈው የተሰወሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ውስጥ ከዘረፉት ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ወንጀሉን የፈፀሙ አካላትን ለመቆጣጠር  የምርመራና የክትትል ቡድኑ ሌት ከቀን በመስራት ውጤት ማምጣቱ ገልፆል፡፡                               በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አሽከርካዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተ-ክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ወጣት ሶፎኒያስ አስራት ተገድሎ ይገኛል፡፡ የወጣቱ መገደል ሪፖርት የደረሰው አዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ እና የክትትል ቡድኖችን በማዋቀር የገዳዩቹን   ማንነት ለማወቅ ወንጀለኞቹን ህግ ፊት ለማቅረብ ወደ ስራ ይገባል፡፡ ሟች ወጣት ሶፎኒያስ  መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ናሆም ሆቴል አካባቢ ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው የማይታወቁ ሦስት ግለሰቦችን በግል በተደረገ ስምምነተ‍ ያለአፕልኬሽን ምዝገባ በኮድ 2 ቪትዝ አሳፍሮ ወደ ቦሌ ሚካኤል ለማድርስ መሄዱን ጉዳዩን ለመመርመር የተቋቋመው የምርመራና የክትትል ቡድን  አባላት ባሰባሰቡት ማስረጃ ያረጋግጣሉ፡፡  ወንጀል ፈፃሚዎቹ ወንጀል ለመፈፀም አቅደው እና ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊ መስለው ሹፌሩን በመቅረብ ካሳፈራቸው በኋላ አንገቱን በገመድ አንቀው በመግደል አስክሬኑን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ በመጣል  አይነቷ ቪትዝ የሴሌዳ ቁጥር ኮድ 2A 93488 ተሽከርካሪ ጨምሮ ሁለት ሞባይል ስልኮችን ዘርፈው ይሰወራሉ፡፡ ፖሊስ ወንጀሉ ከተፈፀመበት ጊዜ አንስቶ ቀን ከሌት  ባደረገው ብርቱ ክትትል ልዩ ልዩ ፖሊሳዊ ቴክኒኮችን በመጠቀም ወንጀል ፈፃሚዎቹ የሰረቁትን ተሽከርካሪ ፣ ሦስቱን ዋና ወንጀል ፈፃሚዎች እና የሰረቁትን መኪና እንዲሁም ሶስት አባሪዎቻቸውን ጨምሮ በብርቱ ክትትል መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም ከወንጀል ፈፃሚዎቹ እጅ ላይ ባለቤታቸው  የማን እንደሆኑ የማይታወቁ 7 የስልክ ሲም ካርዶችን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን ጨምሮ ገልፆል፡፡ ምንም እንኩዋን ወንጀሉ በስውር የተፈፀመና  ማንነታቸው የማይታወቁ ቢሆን በተደረገ ብርቱ ክትትል ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ  በመለየት ሦስት ዋና ወንጀል ፈፃሚዎችንና ሦስት ግብራበሮቻቸውን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡ በመጨረሻም ለዚህ ስራ ስኬታማነት ቀና ትብብር ላደረጉ አካላት አዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቦ የምርመራ ሥራው እንዳበቃ የፍርድ ሂደት ውጤቱን በቀጣይ ለህዝብ እንደሚገለፅ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ፡፡ የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ህጉን ጠብቀው አገልግሎት ሲሰጡ በአፕልኬሽኑ ተመዝግበው እንዲሆን ፖሊስ እንደሁልግዜውም አሁንም ያሳስባል። Via AAP @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
نمایش همه...
👍 36 4👏 2😢 2
ይህ ፓስታ ሳይሆን ሐዋሳ ከተማ ከ8 ዓት ህፃን ጉሮሮ በቀዶ ህክምና የወጣ ትል/ፓራሳይት/ ነው። ትሉ የልጁን ጉሮሮ በመዝጋት ከተበከለ በኋላ በቀዶ ጥገና ተወግዷል። እነዚህ ትሎች/ፓራሳይቶች/ ወደ አንጀታችን የሚገቡት የእጃችንን ንፅህና ባለመጠበቅ ነው። በተጨማሪም ንፁህ ያልሆኑ/የተበከሉ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን በመመገብ ወደ እኛ ይተላለፋል። ስለዚህ የምግብ ንፅህናን በመጠበቅ እራሳችንን እና ሌሎችን ከበሽታው እንጠብቅ! (ዶክተር ናፊያ),Photo credit hakim @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
نمایش همه...
😱 34👍 13👏 6 1
ንግድ ባንክ በ4ኪሎ 😁 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ መልኩ ገንዘብ አልመለሱም ያላቸውን ደንበኞቹ ምስል በየቅርንጫፍ መለጠፍ ጀምሯል። @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
نمایش همه...
😱 14👍 11😢 5👏 3 1
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ108ሺ እስከ 305ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ይፋ አደረገ! በባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ያለአግባብ ከባንካችን የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት 10,857 የሚሆኑ ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መመለሳቸውን ባንኩ ገልጿል፡፡ ባንኩ "የተሰጠውን ተደጋጋሚ እድል ተጠቅመው ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦች አሉ ያለ ሲሆን ባንካችን ገንዘቡን ለማስመለስ በተከታታይ ስለሚወስዳቸው እርምጃዎች በተደጋጋሚ ባሳወቀው መሠረት እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ በባንካችን ድረ-ገጽ እና የማህበራዊ ትስስር ገፆች ለማውጣት ተገደናል ብሏል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ባንካችን የተለያዩ ምክንያቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት የገንዘብ መመለሻ ጊዜውን ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ያራዘመ በመሆኑ፣ ይህን የመጭረሻ እድል ተጠቅማችሁ ገንዘቡን እድትመልሱ እያሳሰብን፣ በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ የምናቀርብ መሆኑን በድጋሚ እናሳስባለን ብሏል፡፡ ከ108ሺ እስከ 305ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ይፋ አድርጓል። https://combanketh.et/list-of-customers 😁😁 @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
نمایش همه...
👍 24 5😢 5🥰 2
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በአንድ አካል ሁለት ጭንቅላት ያላቸው ልጆች ተወለዱ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግሥት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮንፕረሲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአንድ አካል ጭንቅላታቸው የተያያዙ መንታ ልጆች አንዲት እናት መገላገሏን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዳነ ደስታ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በትላንትናው እለት ከምሽቱ 3፡30 ገደማ የወለደችው እናት እድሜዋ 40 ዓመት ሲሆን የአምስት ልጆች እናት መሆኗ ተገልፆል፡፡ ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱት ህፃናቶቹ እና እናትየው በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል በሆስፒታሉ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከባድ እንደሆነ እና ወደ አዲስ አበባ ሪፈር እንደሚደረጉ ነገር ግን ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከባድ መሆኑን  በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግሥት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮንፕረሲቨ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዳነ ደስታ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ሁለት እና ሦስት መንትያ ልጆች ተወልደው ቢታወቅም ይህ ክስተት  የመጀመሪያ ነው ሲሉ ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በደምቢ ዶሎ ዩንቨርስቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ሁለት ጭንቅላት ያለላቸው ልጆች መወለዳቸው ይታወሳል፡፡ በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
😱 33👍 19😢 10 5👏 1