cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

🇪🇹 ኢትዮ Students

Our Bot : @EthioExamBot Contact : @ethioexamsupport Or @Etssupport

Mostrar mĂĄs
Advertising posts
56 628Suscriptores
-4124 hours
-1757 days
-92430 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ስለ ጊዜ..... ኒዉዬርክ ከካሊፎርኒያ በ 3 ሰዓት ትቀድማለች ነገር ግን ይህ ካሊፎርኒያን ቀርፋፋ አያደርጋትም ምክንያቱም የራሷ ጊዜ አላትና ፡፡ አንዳንድ ሰዉ በ22 አመቱ ይመረቃል ነገር ግን ጥሩ ስራ ለመያዝ 5 አመት ይፈጅበታል፡፡ አንዳንዱ በ25 አመቱ የድርጅት ሃላፊ ሆኖ በ5ዐ አመቱ ሲሞት ሌላዉ በ50 ዓመቱ ሃላፊ ሆኖ እስከ 9ዐ ዓመት ይኖራል፡፡ ኦባማ በ55 ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጨረሰ ነገር ግን ትራምፕ በ7ዐ ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጀመረ! ይሄ ትራምፕን ኀላ ቀር አያደርገዉም፡፡ ጊዜ በሕይወታችን ወሳኝ ነገር ነዉ ፡፡ ፈጣሪ በጊዜዉ ሁሉን ነገር ዉብ ያደርጋል ስለዚህ.... ከሁሉ በኋላ የቀረን ወይም ወደፊት የቀደምን አይምሰለን ሁሉም ሰዉ የራሱ የሆነ የኑሮ ሩጫና የተፈጠረበት አላማ አለዉ! ሁላችንም የራሳችን የሆነ የጊዜ ክልል አለን! Dr. Mihret Debebe
Mostrar todo...
❤ 55👍 28🔥 2🥰 1👏 1
በስለት የተወጉት የኦርቶዶክስ ጳጳስ ጥቃት አድራሹን “ይቅርታ ብያለሁ” አሉ ባለፈው ሰኞ በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ በቀጥታ በሚተላለፍ ሰብከት ላይ ሳሉ በስለት ጥቃት የደረሰባቸው አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በፍጥነት እያገገሙ እንደሆነ ገልጸው ጥቃቱን እንዳደረሰ ለተጠረጠረው ግለሰብም ይቅርታ እንዳደረጉ ተናግረዋል። ጳጳሱ በተቀረጸ ድምጽ ባስተላለፉት መልዕክት ህብረተሰቡ እንዲረጋጋም ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ሳምንት በተፈጸመው ጥቃት አራት ሰዎች ተጎድተዋል። ፖሊስ ጥቃቱ ሃይማኖታዊ መነሻ ያለው የሽብር ድርጊት ነው ብሏል። ከክስተቱ በኋላ ጳጳሱ በሚያገለግሉበት ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ሁከት ተፈጥሯል። ጥቃቱን እንዳደረሰ የተጠረጠረ እና ራሱም የተጎዳው የ 16 ዓመት ታዳጊ በቁጥጥር ስር የዋለ ቢሆንም እስካሁን ክስ አልተመሰረተበትም። ባለስልጣናት የታዳጊውን እምነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል። ታዳጊው በአረብኛ ሲጮህ እና “ነብዩ” የሚልበትን ቪዲዮ የሀገሪቱ የስለላ ቢሮ እየመረመረው እንደሆነ የተቋሙ ኃላፊ ተናግረዋል። አራት ደቂቃ ርዝማኔ ባለው እና በቤተክርስትያኑ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው ድምጽ ላይ ጳጳሱ “ማንም ይሁን ማን” ይህንን ላደረገው ግለሰብ ይቅርታ አድርጌያለሁ ሲሉ ይደመጣሉ። “እናም ለአንተ ሁልጊዜ እጸልያለሁ። ይህንን እንድታደርግ የላኩህ ማንም ይሁኑ ማን በኃያሉ ኢየሱስ ስም ይቅርታ አድርጌላቸዋለሁ” ብለዋል። “የክርስቶስን ተግባር እንድትፈጽሙ እፈልጋለሁ። ጌታችን ክርስቶስ እንድንጣላ በፍጹም አላስተማረንም። መጥፎ ስራ እንድንሰራ አላስተማረንም” ብለዋል። #ዳጉ_ጆርናል @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
Mostrar todo...
❤ 95👍 19🥰 14👏 8😢 5
በአውስትራሊያ በቀጥታ ስርጭት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ጳጳስን ጨምሮ አራት ሰዎች በስለት ተወጉ፡፡ በጩቤ ከተወጉት መካከል የአሶራውያን ኦርቶዶክስ ጳጳስ ብጹዕ ቢሾፕ ማር ማሪ ይገኙበታል፡፡ በዋክሌይ በሚገኘው የክርስቶስ በጎ እረኛ ቤተክርስቲያን ድንገተኛ ሁከት ከተከሰተ በኋላ ውጥረት ነግሷል ተብሏል፡፡ ክስተቱ የተፈጸመው በምዕራብ ሲድኒ ዋክሌይ በሚገኘው የክርስቶስ መልካም እረኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው ሲል Anadolu Agency ዘግቧል። የጥቃቱ ዝርዝር ሁኔታ እስካሁን አልተረጋገጠም ያለው ፖሊስ ነገር ግን ብቻውን እንደፈፀመ የሚታመንበት ወንጀለኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛል ሲል አስታውቋል። (ቪዲዮው ከላይ ተያይዟል) @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
Mostrar todo...
😢 38😱 19👍 16❤ 4🔥 2
18 ሰዓታት በፈጀ  የቀዶ ህክምና 20 ሳ.ሜ ከፍታ ያለው የጭንቅላት እጢ በተሳካ ሁኔታ ተወገደ 18 áˆ°á‹“ታቾ በፈጀ የጭንቅላት እጢ በቀዶ ህክምና ማስተካከል መቻሉን የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።በሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አለምሰገድ ጫኔ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በቀዶ ህክምናው ዋና ዋና ተግባራት በጭንቅላቱ áˆ‹á‹­ የነበረውን 20 ሳንቲሜትር ከፍታ የለው እብጠት በቀዶ ህክምና እንዲወጣ ተደርጓል ። አያይዘውም እብጠቱ የወጣበትን ቦታ በሌላ የሰውነት ክፍል የመተካት ተግባር ተከናውኗል።በሶስተኛ ደረጃ ከታካሚው ከተለያዮ የሰውነት ክፍሎች ማለትም ከእጆቹ ላይ ደም ቅዳና ደም መልስ ተመሳሳይ ደም ስሮችን ወደጭንቅላቱ እንዲደርስ ተደርጓል  በማለት ለጣቢያችን ገልፀዋል። በአራተኛ ደረጃ ደግሞ በቀዶ ህክምና  ወቅት በሰውነት ክፍሉ የደም መፍሰስ ችግር እንዳይኖር አስቀድሞ በቂ ደም የመያዝና  የደም ስሮችን የመቋጠር ተግባር  መከናወኑ ተገልጿል።በመጨረሻም ታካሚው ከ18 ሰአታት በኋላ በፅኑ ህሙማን ክፍል እንደቆየ ተደርጓል ያሉት አቶ አለምሰገድ በአሁኑ ሰአት  በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል። በዚህም የተሳካ ቀዶ ህክምና የተሳተፉ የተለያዩ  ስፔሻሊስቶች ፣  ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች፣ አኒስቴትክስ፣ ነርሶች ፣ፖርተሮች እና ፅዳቶች  ሲያከናውኑ የነበሩ የቡድን አባላቶች ሾል እጅግ ከፍተኛ መሆኑ  ተጠቅሷል።ዶ/ር አብዱራዛቅ  የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ስፔሻሊስት á‰Łáˆˆáˆ™á‹ŤáŠ“ የማክሮ ሰርጀሪ ሰብ ስፔሻሊስት በዚህ ህክምና ላይ ለተሳተፉ አጠቃላይ ሰራተኞች  ምስጋናቸውን  አቅርበዋል። #ዳጉ_ጆርናል @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
Mostrar todo...
👏 36👍 25😱 6❤ 5🔥 1
በሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በዛሬው እለት ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ያደረጉ ሁለት ግለሰቦች ሲገደሉ ፖሊሶች ቆሰሉ 👉🏼 ተጨማሪ ሌላ አንድ መንገደኛ ግለሰብም ተገድሏል በዛሬዉ እለት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ካደረጉ ሰዎች ዉስጥ ሁለቱ ሲገደሉ ሌላኛዉ በቁጥጥር ሾር መዋሉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። የአዲስአበባ ፖሊስ ፤ ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት ሰዎች በአዲስአበባ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሼባቸዋለሁ ያለ ሲሆን በቁጥጥር ሾር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆን á‰°áŠŠáˆľ ከፍተዋል ብሏል። ግለሰቦቹ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም  ከፖሊስ አባላት ጋር ተኩስ በመክፈታቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ገልጿል። በተጨማሪም ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል á‰°áŒˆá‹ľáˆáˆ ብሏል ፖሊስ፡፡ ሌላዉ አቤኔዘር ጋሻው አባት የተባለው ሳይቆስል በቁጥጥር ሾር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ በመግለጫው መጥቀሱን ዳጉ ተመልክቷል፡፡ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ሾር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ መቁሰላቸዉንም ፖሊስ አረጋግጧል። ሌላዉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ á‰łáŒŁá‰‚ዎቚ  á‰ áˆ˜áŠŞáŠ“ቸው እንዲጭኗቸው  ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በታጣቂዎቹ ተገድለዋል ሲል ፖሊስ ወንጅሏል፡፡  አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ  80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ  ጨምሮ ገልጿል ፡፡ #ዳጉ_ጆርናል @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
Mostrar todo...
👍 14😢 13❤ 5😱 2🔥 1
በሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በዛሬው እለት ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ያደረጉ ሁለት ግለሰቦች ሲገደሉ ፖሊሶች ቆሰሉ 👉🏼 ተጨማሪ ሌላ አንድ መንገደኛ ግለሰብም ተደግሏል በዛሬዉ እለት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ካደረጉ ሰዎች ዉስጥ አንዱ ሲገደል ሌሎቹ በቁጥጥር ሾር መዋላቸውን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። የአዲስአበባ ፖሊስ ፤ ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት ሰዎች በአዲስአበባ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሼባቸዋለሁ ያለ ሲሆን በቁጥጥር ሾር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ፅንፈኞቸ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆን á‰°áŠŠáˆľ ከፍተዋል ብሏል። ግለሰቦቹ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም  ከፖሊስ አባላት ጋር ተኩስ በመክፈታቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ገልጿል። በተጨማሪም ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል á‰°áŒˆá‹ľáˆáˆ ብሏል ፖሊስ፡፡ ሌላዉ አቤኔዘር ጋሻው አባት የተባለው የቡድኑ አባል ሳይቆስል በቁጥጥር ሾር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ በመግለጫው መጥቀሱን ዳጉ ተመልክቷል፡፡ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ሾር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ መቁሰላቸዉንም ፖሊስ አረጋግጧል። ሌላዉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ  ፅንፈኞቹ á‰ áˆ˜áŠŞáŠ“ቸው እንዲጭኗቸው  ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በታጣቂዎቹ ተገድለዋል ሲል ፖሊስ ወንጅሏል፡፡  አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ  80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ  ጨምሮ ገልጿል ፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
Mostrar todo...
#ትዝብት_ከ_ቲክቶከር👇😂😂😂🙄 ለ2 አራት ምግብ በልተው ሂሳብ ሲባሉ የለንም ሰሃን እንጠብ አሉ። አይቻልም ደውላችሁም ቢሆን አስመጡ ተባሉ ። ቲክቶከሮች ነን በልቶ ያለመክፈል ቪዲዮ እየሰራን ነው ብለው የቆዩ ቪዲዮዎቻቸውን አሳዩ። ለሬስቶራንቱም ማስታወቂያ ነው ብለው ሰከሱ ። ባለቤቱና ጥበቃዎች ጓዳ አስገብተው መከሯቸው። ሰሃኑንም አጠቡ። ለማስታዎሻ ይህንን ፎቶ አነሷቸው ። ችግሮችን በመመካከር መፍታት ይቻላል። #huleadismedia @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENST
Mostrar todo...
🔥 28👍 21😢 5❤ 4👏 2
ሶፎኒያስ የገደሉት ተይዘዋል ወጣት ሶፎኒያስ አስራትን ገድለው ተሽከርካሪውን ዘርፈው የተሰወሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ውስጥ ከዘረፉት ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር ሾር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ወንጀሉን የፈፀሙ አካላትን ለመቆጣጠር  የምርመራና የክትትል ቡድኑ ሌት ከቀን በመስራት ውጤት ማምጣቱ ገልፆል፡፡                               በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አሽከርካዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተ-ክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ወጣት ሶፎኒያስ አስራት ተገድሎ ይገኛል፡፡ የወጣቱ መገደል ሪፖርት የደረሰው አዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ እና የክትትል ቡድኖችን በማዋቀር የገዳዩቹን   ማንነት ለማወቅ ወንጀለኞቹን ህግ ፊት ለማቅረብ ወደ ሾል ይገባል፡፡ ሟች ወጣት ሶፎኒያስ  መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ናሆም ሆቴል አካባቢ ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው የማይታወቁ ሦስት ግለሰቦችን በግል በተደረገ ስምምነተ‍ ያለአፕልኬሽን ምዝገባ በኮድ 2 ቪትዝ አሳፍሮ ወደ ቦሌ ሚካኤል ለማድርስ መሄዱን ጉዳዩን ለመመርመር የተቋቋመው የምርመራና የክትትል ቡድን  አባላት ባሰባሰቡት ማስረጃ ያረጋግጣሉ፡፡  ወንጀል ፈፃሚዎቹ ወንጀል ለመፈፀም አቅደው እና ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊ መስለው ሹፌሩን በመቅረብ ካሳፈራቸው በኋላ አንገቱን በገመድ አንቀው በመግደል አስክሬኑን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ በመጣል  አይነቷ ቪትዝ የሴሌዳ ቁጥር ኮድ 2A 93488 ተሽከርካሪ ጨምሮ ሁለት ሞባይል ስልኮችን ዘርፈው ይሰወራሉ፡፡ ፖሊስ ወንጀሉ ከተፈፀመበት ጊዜ አንስቶ ቀን ከሌት  ባደረገው ብርቱ ክትትል ልዩ ልዩ ፖሊሳዊ ቴክኒኮችን በመጠቀም ወንጀል ፈፃሚዎቹ የሰረቁትን ተሽከርካሪ ፣ ሦስቱን ዋና ወንጀል ፈፃሚዎች እና የሰረቁትን መኪና እንዲሁም ሶስት አባሪዎቻቸውን ጨምሮ በብርቱ ክትትል መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም ከወንጀል ፈፃሚዎቹ እጅ ላይ ባለቤታቸው  የማን እንደሆኑ የማይታወቁ 7 የስልክ ሲም ካርዶችን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን ጨምሮ ገልፆል፡፡ ምንም እንኩዋን ወንጀሉ በስውር የተፈፀመና  ማንነታቸው የማይታወቁ ቢሆን በተደረገ ብርቱ ክትትል ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ  በመለየት ሦስት ዋና ወንጀል ፈፃሚዎችንና ሦስት ግብራበሮቻቸውን በቁጥጥር ሾር ማዋሉን አስታውቋል፡፡ በመጨረሻም ለዚህ ሾል ስኬታማነት ቀና ትብብር ላደረጉ አካላት አዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቦ የምርመራ ሥራው እንዳበቃ የፍርድ ሂደት ውጤቱን በቀጣይ ለህዝብ እንደሚገለፅ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ፡፡ የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ህጉን ጠብቀው አገልግሎት ሲሰጡ በአፕልኬሽኑ ተመዝግበው እንዲሆን ፖሊስ እንደሁልግዜውም አሁንም ያሳስባል። Via AAP @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
Mostrar todo...
👍 38❤ 4👏 2😢 2
ይህ ፓስታ ሳይሆን ሐዋሳ ከተማ ከ8 ዓት ህፃን ጉሮሮ በቀዶ ህክምና የወጣ ትል/ፓራሳይት/ ነው። ትሉ የልጁን ጉሮሮ በመዝጋት ከተበከለ በኋላ በቀዶ ጥገና ተወግዷል። እነዚህ ትሎች/ፓራሳይቶች/ ወደ አንጀታችን የሚገቡት የእጃችንን ንፅህና ባለመጠበቅ ነው። በተጨማሪም ንፁህ ያልሆኑ/የተበከሉ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን በመመገብ ወደ እኛ ይተላለፋል። ስለዚህ የምግብ ንፅህናን በመጠበቅ እራሳችንን እና ሌሎችን ከበሽታው እንጠብቅ! (ዶክተር ናፊያ),Photo credit hakim @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
Mostrar todo...
😱 34👍 14👏 6❤ 1
ንግድ ባንክ በ4ኪሎ 😁 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ መልኩ ገንዘብ አልመለሱም ያላቸውን ደንበኞቹ ምስል በየቅርንጫፍ መለጠፍ ጀምሯል። @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
Mostrar todo...
😱 15👍 12😢 5👏 3❤ 1