📖 የተቀደደው ማስታወሻ ©ሶፊ
رفتن به کانال در Telegram
🗒️ እንኳን ወደ «የተቀደደው ማስታወሻ» በደህና መጡ! ይህ ቻናል በፈጠራ ታሪኮች እና ልብ-ወለዶች የታጀበ፣ በግጥም ስንኞች የደመቀ፣ እና የዕለት ተዕለት ውሎዎችን እንዲሁም እውነተኛ ስሜቶችን በደብዳቤ እንዲሁም postcard story መልክ የምናጋራበት የግል ማስታወሻችን ነው። ከቃላት በስተጀርባ ራስን ፍለጋ...
نمایش بیشتر7 306
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-167 روز
-5230 روز
آرشیو پست ها
7 310
የእዮን ሞት ከሰማሁ ጀምሮ እጅግ ነው ያዘንኩት የሆነ በቅርብ እንደማውቀው ሰው ነው ሐዘኑ ልቤ የገባው። ከዛ I was obsessed with his interviews and his posts በርግጥ ድሮም አውራ reaction ደስ ይሉኛል አያቸዋለሁ ። እና እዮ ምን ሲል ሰማሁት አንድ interview ላይ :-
አሁን ላይ ካለፈ በኋላ ሳስበው የሚቆጨኝ ዮንቨርስቲ dropout አድርጌ ቤት በተቀመጥኩበት ጊዜ ተስፋ የለም ብዬ ማሰቤ ያበሳጨኛል ።It is deep 🔥 ጭስ was real bad man 💙
ነፍሱ በሰላም ትረፍ©ሶፊ
7 310
I have been busy lately... I apologize i can't post stories...
(እነኚህ post ዎች የሚለቀቁት በአንዳንድ member ጥያቄ መሰረት ነው።)
7 310
እንዲህ ባይሆን ደስ ይለኝ ነበር ። መፅሐፍ ላይ ያየናቸው ክፉ ገፀ-ባህሪያት ሩቅ የመሰሉን...ጓደኞቻችን ሆነው ባያስገርሙን ፤ ብቻ መፅሐፍ እና ፊልሞች የውሸት ናቸው ብለን እንዳሰብነው እንደዛው ውሸት ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር።
ኢ-ልብወለድ ህይወት¡
©ሶፊ
7 310
ለምን ተነካው የምል አይነት ሰው ነኝ፤ትንሽ እንቅፋት ሲገጥመኝ ቀኔን ለሊቴን ሁሉ ነገሬን ለችግሬ ታምኜ ሰጥቼ የምታመም አይነት ሰው ። ችግርህን ዋጥ አድርገህ በዙሪያህ ያሉ ሰዎች እንዳይረበሹ በሳቅህ እየሸፈንኽ ፤ እንደ ኖርማል ሰው አክት ማድረግ...ትልቅ ብስለት አይደል ?
መቼም ይሄ ቪዲዮ በቲክቶክ ሲዘዋወር አይታቹታል...አሁን ከነገርኳችሁ ጋር ስለሚያያዝ ልጋብዛችሁ።
እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2008 ዓ.ም አንድ አሜሪካዊ Press Secretary ሲጠበቅ ወደ ነበረው የውይይት መድረክ ወጥቶ በእርጋታ እንዲህ አለ :
ስላረፈድኹ ይቅርታ ፤ ባለቤቴ ቅርብ ሰዓት አርፋ(ሞታ) ነው። ዛሬ ብዙ አጀንዳዎች ነው ያሉን እንጀምር...እሺ ማቲው...ማቲው...
በጣም አዝናለኹ...ማለቴ ባለቤትህሴክሬቴሪው
አዎ እንደምትገምተው ህመሙ ከዚህ በፊት ከገጠሙኝ ህመሞች ሁሉ በጣም የከፋ ነው።ነገር ግን ዛሬ መስራት ያለብን ብዙ ስራ አለ።እሺ ቀጣይ ጥያቄ...ጂም፦ጂም...
ምን እንደተፈጠረ ልጠይቅ ? እ ጄኒ...ሴክሬተሪው
ጂም የተከሰተውማ ባለቤቴ ሞታለች ። የመኪና አደጋ ነው...ህዝቡን ሁሉ (እኔ ችግር ውስጥ ) ማቆም አንችልም።ስለዚህ ለፕሬዝዳንቱ ጥያቄ ያለው ይቀጥል።ይሄን ሲል ሲያለቅስ አይታይም...ከወረቀቱ ላይ እንደሚያነብ ሁሉ ጎንበስ ቀና እያለ ይመልሳል።ሰዎቹ የተደናገጡ ይመስላሉ ሌላ ነገር ማውራት አልቻሉም። ግራ ገብቷቸዋል። ከመሀል አንዱ ጠየቀ...
ማድረግ የምችለው ነገር አለ ?ሴክሬተሪው...
ካርድ እና አበባ ቢሮ መላክ ትችላለህ።በአጭሩ መለሰ። አሁንም ሌላ ድምፅ ከመሀል...
ልታወራው የምትችለው ሰው ትፈልጋለህ...ወይም ልረዳህ የምችለው ነገር አለ?ሴክሬተሪው
ሰዎች ይሄ ርዕስ ብቻ አይደለም የዛሬው አጀንዳችን...እመኑኝ ከምንም በላይ ይሄን መድረክ ትቼ ማልቀስ ነው የምፈልገው ግን አልችልም ምክንያቱም ትልቅ ሰው ነኝ ስራ አለኝ ፤ እናንተም እንደዛው ። ስለዚህ የባለቤቴን ነገር እንለፈውና አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ልውሰድ።ተሰብሳቢው ጆሮውን ማመን የከበደው ይመስላል።
እሺ ዊልሰንዊልሰን...
ልጆችህ ሰምተዋል?ሴክሬተሪው
ዊል ልጆቼ መኪና ውስጥ ከእናታቸው ጋር ነበሩ አንደኛዋ ኮማ ውስጥ አንደኛዋ እግሯን አጥታለች።
I mean እንዴት ነው ይሄ ሰውዬ ቆሞ የሄደው ? ጭራሽ ስራ ይመጣል ? ጭራሽ ከሰዎች ጋር ያወራል ?©ሶፊ
7 310
"ስለራስህ ንገረኝ? " አለች ። ...ለማወቅ እንደጓጓች ያስታውቃል።
"ምንም የሚነገር ነገር የለኝም..." ብዬ ላድበሰብስ ሞከርኩ...በርግጥም የለም።ደሞ ቢኖርስ እኔ እንዲህ ነኝ ተብሎ ይወራል? ነውር አይደለም?
" ሶፍ ?!" አለች ልምምጥ በታጀበው ድምፀት።
እንደ ክርስቶስ አንዳንዶች እንዲህ ይሉኛል...ሌሎች ደግሞ እንደዛ እያልኹ ልመልስላት?
ደግሞ ሰዎች ስለኔ ምን እንደሚሉ በምን አውቃለኹ?
ብዙ ካሠላሰልኹ በኋላ ድምፄ እየተቆራረጠ እንዲህ አልኋት...
"አንዳንድ ቀን በጠዋት ተነስቼ ቴክኖሎጂ ምን ያህል ትኩረታችንን እደበታተነብን ለራሴ ተንትኜ ስልኬን ወዲያ አሽቀነጥረው እና አንባቢ እሆናለኹ...ወደ አንዱ ካፌ ሄጄ፤ስልኬን አጠፋና መፅሐፌን አነባለኹ...ለወትሮ ኮሽታ የሚረብሸኝ ሰው፤በዛ ሁሉ ሰው መሀል ቁጭ ብዬ፥አንዳች ድምፅ ሳይረብሸኝ በተመስጦ ደራሲው ባሳፈረኝ ምናብ እየተጓዝኩ እውላለሁ።
አንዳንዴ ደግሞ እንኳን መፅሐፍ ላነብ ቀርቶ ረጅም ፅሁፍ ሳይ እራሱ እንደ እርጉዝ ሴት ያቅለሸልሸኛል።በየሶሻል ሚዲያው እገሌ አገባ፣እገሌ መኪና ገዛ፣ዱባይ ሄደ፣ዛሬ እገሌ ቺክን ሳላድ በላ...ስንት ላይክ አገኘው? ስንት ቪው ?እገሌ እንዴት ነው የኔን ፖስት ላይክ ያላደረገው...እያልኹ ስባክን እውላለኹ።
አንዳንድ ቀን ደግሞ ተስፋ እንደቆረጠ፣እንደታመመ፣በደዌ እንደተመታ ሰው ከአልጋዬ መውረድ ይቀፈኛል።ስለንጋት፣ስለረፋዱ፣ስለቀትር ግድ አይሰጠኝም...በወጣትነቴ ያረጀው ያህል ይሰማኛል...
አንዳንድ ቀን ደግሞ መናኒ እሆንና ለሊት ከወፎቹ ቀድሜ እነሳለኹ፤ከመሸ ሽንት ቤት መሄድ የምሰጋው ሰው የለሊቱ ግርማ ምንም ሳያስፈራኝ፥ደጀ ሰላም እሄዳለኹ።በፀሎት እና በምስጋና እተጋለኹ።ደግም ቢቆጠር የማያልቅ ኃጢአትን እንደሰራኹ እረሳና ከምእመኑ አቃቂር አወጣለኹ...
አየሽ እኔ ብዙ ሰው ነኝ።
አንተ ማነህ? ካልሽኝ እኔ የቱ እንሆንኹ አላውቅም።"
ከተቀደደው ማስታወሻ
#Repost
30/1/2015
©ሶፊ
