ru
Feedback
📖 የተቀደደው ማስታወሻ ©ሶፊ

📖 የተቀደደው ማስታወሻ ©ሶፊ

Открыть в Telegram

​🗒️ እንኳን ወደ «የተቀደደው ማስታወሻ» በደህና መጡ! ​ይህ ቻናል በፈጠራ ታሪኮች እና ልብ-ወለዶች የታጀበ፣ በግጥም ስንኞች የደመቀ፣ እና የዕለት ተዕለት ውሎዎችን እንዲሁም እውነተኛ ስሜቶችን በደብዳቤ እንዲሁም postcard story መልክ የምናጋራበት የግል ማስታወሻችን ነው። ​ከቃላት በስተጀርባ ራስን ፍለጋ...

Больше
Buy Ad
7 320
Подписчики
+624 часа
+237 дней
+9730 дней
Архив постов
"ሰው የተፈጠረው ለሥራ፣ ለዕውቀትና ለበጎ ነገር ነው። ዕድሜ ዘመን ብቻ ሳይሆን፣ በዘመኑ ውስጥ የተሠራ መልካም ነገር ነው።" ከጸሐፊ ተውኔት ከበደ ሚካኤል (“የታሪክ ማስታወሻ” እና የተለያዩ ድርሰ
"ሰው የተፈጠረው ለሥራ፣ ለዕውቀትና ለበጎ ነገር ነው። ዕድሜ ዘመን ብቻ ሳይሆን፣ በዘመኑ ውስጥ የተሠራ መልካም ነገር ነው።" ከጸሐፊ ተውኔት ከበደ ሚካኤል (“የታሪክ ማስታወሻ” እና የተለያዩ ድርሰቶቻቸው አንደምታ) ስለመልካም ምኞታችሁ እና ፍቅራችሁ አመሰግናለሁ ። ብቸኝነት እንዳይሰማኝ ስላደረጋችሁ አመሰግናለሁ ። ©ሶፊ

ልደቴን በማስመልከት... ደህና camera እና camera man ቢኖሩኝ... ...ገላዬን ታጥቤ፣ውብ ልብስ ከአንዱ ticktock-er ተውሼ (እንደኔ ቀጫጫ ሰው ላላገኝ እችላለሁ፡ቢኾንም ልብሱ እላዬ
ልደቴን በማስመልከት... ደህና camera እና camera man ቢኖሩኝ... ...ገላዬን ታጥቤ፣ውብ ልብስ ከአንዱ ticktock-er ተውሼ (እንደኔ ቀጫጫ ሰው ላላገኝ እችላለሁ፡ቢኾንም ልብሱ እላዬ ላይ ይውለብለብ) ፣ ፅድት ያለች ጫማ ለብሼ (ከየት አመጣለው ? እሱንም ተውሼ...እግሬ ረዠም ስለኾነ በኔ ሳይዝ ባላገኝም ይሁን ጣቴ እንጎረምሳ ልብ ጫማውን አሳቦጦት ) ፣ የሌለ የሚያምር ፤ ብራንድ ያለው የእጅ ሰዓት ከጓደኛዬ ተውሼ (ፕሮሞሽን አይደለም ጓደኛዬ ሰዓት ይሸጣል የምትፈልጉ በውስጥ አውሩኝ...እንዲህ የሚሉ ሰዎች ሲገርሙኝ ታዲያ ይሄ ምንድነው?) ...ብቻ በተውሶ እቃ እንዲህ ዝንጥ ብዬ...ሰዓቱ በአንድ በኩል ስለሚመዝን momentum እያስነጠረኝ...አንድ እንደኔ የቸገረው ሰው እፈልግና የማይመለስ ምሳ ልጋብዘው፤የሚመለስ ብር ልሰጠው ውል ተፈራርመን ስክሪፕት እናጠናለን። ዳሬክተር አንድ ደንፉዋም ጓደኛዬን እመርጣለው (ዳይሬክተሮች በፀባያቸው ተናዳጅ ናቸው አሉ)...በየመሀሉ እንዲተውን የተመረጠው ምስኪን ሰው ላይ cut እያለ ከምግቡ ያቋርጠዋል(የእናት አባቴ አምላክ ይከትክትህ ሳይለው አይቀርም።) ...እና ረድቼው(የሚመለስ ብሩን) ሰጥቼው፤መንታ መንታ እያነባ አታልቅስ ስለው፤ "እኔ የማለቅሰው ርቦኝ ያ ሰውዬ cut እያለ ሲያቋርጠኝ ነው" ሲል እኔ cut ብዬ ስጮህ....ብቻ ምርጥ ድራማ ሰርቼ በ ticktock እለቅላችሁ ነበር። ቲሽ አሁን በዚህ ምክንያት ድሀ ላልረዳ ነው? ©ሶፊ

ነገ የሶፊ ልደት ነው 😎

አትቀደምምና ምኞት ሁሌ ናት ተጓዥ የሆዴን ጉዳት ስቃይ ጥርሴ ብቻ ናት ፈዋሽ ስማ ራሴ ©ቴዲ አፍሮ
አትቀደምምና ምኞት ሁሌ ናት ተጓዥ የሆዴን ጉዳት ስቃይ ጥርሴ ብቻ ናት ፈዋሽ ስማ ራሴ ©ቴዲ አፍሮ

ሌላው የዛሬው መልእክት : know your worth...በቃ ዋጋችሁን እወቁት ፤ ማንም ቁልቁል እንዲመለከታችሁ አትፍቀዱ ። እንዲህ ስላችሁ ደግሞ ትዕቢተኛ ሁኑ ማለቴ አይደለም እናንተም ማንንም ቁልቁ
ሌላው የዛሬው መልእክት : know your worth...በቃ ዋጋችሁን እወቁት ፤ ማንም ቁልቁል እንዲመለከታችሁ አትፍቀዱ ። እንዲህ ስላችሁ ደግሞ ትዕቢተኛ ሁኑ ማለቴ አይደለም እናንተም ማንንም ቁልቁል አትመልከቱ ። በቃ ዋጋችሁን እወቁት ፤ ተጨማሪ እውቀት በመጨመር ፣ ራሳችሁ ላይ በመስራት ዋጋችሁን ጨምሩት ። ምንም አማራጭ እንደሌለው ሰው እጃችሁን አጣጥፋችሁ እንዳትቀመጡ ። ዋጋችሁን እወቁት ፤ ሰው ሁኑ ፤ የሰው ዋጋ ደግሞ በጣም ውድ ነው። የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ

So ዛሬ after a year አብርሆት ላይብረሪ ሄጄ ነበር ። አዲስ እንደነበረው ተደርጎ ተይዟል ። በእርግጥ አዳዲስ መፅሐፍት እንዲሁም እንደድሮው የማይቆራረጥ WiFi-ም ተጨምሯል ። አትክልቶቹ especially ground floor ላይ ያሉት አትክልቶቹ ፤ በጣም ማራኪና ሳቢ ተደርገው ነው የተያዙት። ምን ገጠመኝ መሰላችሁ ፤ የምሰራውን ነገር ጨርሼ እንደማንኛውም ሰው ልወጣ ስል ፤ በር ላይ የሚፈትሸው አንድ አስፈሪ ሰው ፤ ቦርሳዬን በርብሮና ፈትሾ ብቻ ያስወጣኛል ብዬ ስለጠበኩ ተፈትሼ ለመውጣት ስሰናዳ pcውን አብራና password-ዱን ክፈተው አለኝ ። እንደ ሌባ ተመለከተኝ ፤ ያመዋል እንዴ ብዬ እኔም እንደ ሌባ ተደናበርኩኝ ፤ ላፕቶፑን ቅርብ ግዜ ነው ከሰው የተቀበልኩት እና password-ዱ ይደናገረኛል። ላፕቶፑ እኪከፍት ሰላምለኪ ደገምኩ ፤ እንደ ከፈተ ስምንቱን ቁልፎች ተጭኜ enter ስለው አልከፈተም ። ይከፍታል እኮ ሰውየው ነው የማይከፍት ያስመሰለው። አመስግኜ ወጣው ከላይብረሪው። password የሌለው laptop የሌባ ሲሳይ ነው ማለት ነው? አብርሆት ላይብረሪ ©ሶፊ

#Dark_humor ጀለስ ፦ ይኸው ዛሬ ደግሞ ምን ሰማው ፤ ስሟን እንኳን የማላውቀው የስራ ባልደረባዬ ይወደኛል እያለች ታሶራለች አሉ ። ይጠጣል እያሉ እንደሚያሶሩብኝ ታውቃለህ ? አሁን ደግሞ ይዘሙታል ብለው ሊያሶሩብኝ እኮ ነው አለ ። ጓደኛዬ በሰው ወሬ እጅግ ተማሮ ። ይሄኔ አንዱ ጠላቱ አሶርቶበት ነው። እኔ ፦ አንተ ስለሰው ወሬ ለምን ትጨነቃለህ ፤ ስለሆንከው እና ስለምትሆነው ተጨነቅ ። አስቱ ምን አለች መሰለህ ስለሰው ስለሰው ቀድጄ ልልበሰው ። ጀለስ ፦ የቷ አስቴር ? አስቴር ፋይናንሷ ? እኔ ፦ አቦ አንተ ከቢሮ ውጣ እንጂ አሁን የምሳ ሰዓት ነው። አደረቀኝ እኮ ©ሶፊ

የሆስፒታል ግድግዳ ከእምነት ቦታዎች ግድግዳ የበለጠ የጭንቅ ፀሎት ተሰምቶባቸዋል የሚል ፅሁፍ አየሁ ፤ እውነትም የሆነ ጭንቅ ካልገጠመን እኮ አምላክ እንዳለን እራሱ ትዝ አይለንም ።

Elements የሚል ፀዴ series book ጀምሬያለኹ። Especially የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ትወዱታላችሁ አንብቡት ። ማንበብ እያሳሳኝ በቀን 10 page ነው የማነበው እንዳያልቅብኝ። በፈጠራችሁ የPdf እንዳትጠይቁኝ። ©ሶፊ

Real story #101 ዛሬም በስራ ጉዳይ መሸብኝ እና ታክሲ አጥቼ አጎቴ ጋር አሳድረኝ ልለው ደወልኹ...         ...ስልኩ ጠራ... አጎቴ አነሳው (አጎቴ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው...) : "ልጅ ሶፎንያስ የጌታ ሰላም ይብዛልህ እንደምን አለህ?" መልሴን አልጠበቀም "ምነው በዚህ ሰዓት ደወልኽ በሰላም ነው?" እኔ : "አዎ አጎቴ በሰላም ነው መሸብኝና ለእናንተ አካባቢ ቅርብ ስለኾንኹ መጥቼ ለማደር ላስፈቅድህ ነው..." አጎቴ : "ቤትህ አይደለም ምን ታስፈቅደኛለህ ? በጌታ ሰላም ና ።" መልሱ ፈገግ እያሰኘኝ ስልኩን ዘጋውት እና ወደቤታቸው ሄድኹ። ቤታቸው ስደርስ ቤቱን ደመቅመቅ አድርጎት ጠበቀኝ...ደስ አለኝ...አጎቴም ሲያየኝ ደስ አለው "ሸምግለህ የለ እንዴ ልጅ ሶፎንያስ ሃሃሃ በጌታ መንፈስ ተመርተህ እቤቴ መጣህ..." "ታክሲ አጥቼ ነው አጎቴ " አለኹት ከፈገግታ ጋር ድንገት መምጣቴን ለመንገር..."ቢኾንም ጌታ ካልፈቀደው የሚኾን የለም..." አለኝ ንግግሬን አቋርጦ እንድቀመጥ እየጋበዘኝ... ቡና ተፈልቶ ቴሌቪዥን መመልኽት እንደጀመርን አስታውሳለሁ...በቴሌቪዥን መስኮት የጦር አውሮፕራኖች እየታዩም ነበር...አጎቴ ወሬውን ትክዝ ብሎ "አለም ላይ ያሉት ኃያላን ሀገራት ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ እናሸንፈዋለን ብለው ነው ጦራቸውን የሚያደራጁት ..." ብሎ እንደዠመረ አስታውሳለሁ...ነገር ግን በየት በኩል መፅሐፍ ቅዱስ ገልጦ ከዘፍጥረት ዠምሮ መተንተን እንደዠመረ አላስታውስም...አኹን የእስራኤላውያን ታሪክ ላይ ደርሰናል...እስከ ነገ ጌታ ከፈቀደ አዲስ ኪዳን እንደርሳለን...አጎቴ ደስ በሚል Energy እያብራራ ነው...እኔ እንቅልፍ እያማለለኝ ነው በዚህ ሰዓት ምንም ቢለኝ እስማማለሁ...ሲነጋ ግን የሐይማኖት አቋሜን አስቀምጬ ነው የምወጣው... በጌታ ሰላም- ሰላም እደሩ ©ሶፊ

ወይኔ እችና ተበላች 😔 Abrish ይመቸው 😭👍 ።

እችና 😁

በticktok ለሚሰዳደቡ ሰዎችን ETFC እዲዋጣላቸው መድረኩን እንደሚያመቻች ይታወቃል ። ታዲያ ምነው እኔና ex-ሴን ችላ አለን ፤ የኢትዮጵያ ህዝብስ ምነው ዝም አለ ።
አላለም አንዱ ታክሲ ውስጥ ፤ አስበኸዋል አስገብታ ብትቀጠቅጠው 😁

ሴዶ ቢያሸንፍ ብዬ እመኛለሁ ፤ በፊት አይመቸኝም ነበር ግን ይሄ ሁሉ struggle የሚያደርገው ያው attention (ማስታወቂያ ለመስራት ፣ የእንጀራ ነገር ሆኖበት ይመስለኛል።) አሳዝኖኛል። Johnny ደግሞ very skilled man ነው as we know ። የሚሆነው አይታወቅም ። good luck for Sedo 😊

ETFC ማን ያሸንፋል ?!
Anonymous voting

Repost from Thoughts
አስጠኚ ይፈልጋሉ? እኛ ጋር ብቁ አስጠኚዎች የእናንተን ፍቃድ ብቻ ይጠብቃሉ። ከእናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት ስልኮች መደወል ብቻ ነው። ከሚፈልጉት አስጠኚ ጋር እናገናኛችኋለን። ☑️Group: http
አስጠኚ ይፈልጋሉ? እኛ ጋር ብቁ አስጠኚዎች የእናንተን ፍቃድ ብቻ ይጠብቃሉ። ከእናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት ስልኮች መደወል ብቻ ነው። ከሚፈልጉት አስጠኚ ጋር እናገናኛችኋለን። ☑️Group: https://t.me/grandtutorss 💬Account: @grandtutors1 🗣️ Phone number: 0980806056

ከፍ ካለ የሞራል ልሕልና ላይ ቁጭ ብለህ ስትታዘበው ፤ አብዛኛው ሰው የውሸት ማንነቱን ለመሸፈን የሚጋጋጥበት መንገድ ያስቅሃል። እንደ ማህበረሰብ ምን አይነት የማንነት ቀውስ ውስጥ ነን ? እንደ አዲ
ከፍ ካለ የሞራል ልሕልና ላይ ቁጭ ብለህ ስትታዘበው ፤ አብዛኛው ሰው የውሸት ማንነቱን ለመሸፈን የሚጋጋጥበት መንገድ ያስቅሃል። እንደ ማህበረሰብ ምን አይነት የማንነት ቀውስ ውስጥ ነን ? እንደ አዲስ አበባ መንገዶች ገፅታችንን ብቻ መገንባት ላይ ተጠምደናል ፣ ማሸብረቅ ብቻ ላይ... የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ