الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
رفتن به کانال در Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
2 151
مشترکین
-224 ساعت
+367 روز
+41730 روز
آرشیو پست ها
Repost from 🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
_የሱና እህቶቸ___
አልሀምዱሊላሂ ይመስገን ጌታችን
በማይቆጠረው ኒዕማው ላመቻቸን
የነብዩ ኡመት አድርጎን በእዝነቱ
በሱናቸው ግርጌ አስውቦን ሙሚቱ
በጅልባብ በኒቃብ ደምቀን ልንራመድ
ትዛዝ አመጣልን መጠጊያችን ሶመድ
የነብያት መሪ ኢማሙል ቃኢሚን
አሏህ ነገራቸው ተሸፈኑ እንዲሉን
ውበት ነው ማረግ ነው ለሱና መመረጥ
በተውሂድ ተውቦ በአንድነት ማጌጥ
የሱናዋ እህቴ የመንሀጇ ንግስት
ሁሌ ወድሻለሁ እያየሁ በስስት
አገናኘንና የመንሀጅ የአቂዳ ረመጥ
አለያየንና ያገር አቀማመጥ
በሙሀባሽ ግርጌ ሁሌ ስትናፍቂኝ
አለሁ ዛሬም ድረስ ልቤን ስትደልቂኝ
በርቀት ከንፌ ደስታሽን ስሰማ
ዳዕዋ ወጥነሻል በጠንካራው ማማ
አምልኩት በማለት አረሂሙ ሯህማ
በቂርአት ደምቀሽ ኢልምን ስትሾፍሪ
ከማዳም ቤት ሁነሽ ድካምን ሳትፈሪ
በአንድ እጅሽ ስትሞጥይ በአንዱ ስትሰሪ
እጅጉን ደስ አለኝ የብርታትሽ ድግሪ
የመንሀጅ እህቴ የሱናዋ ኮከብ
በአንድነት ደምቀን በመሀባው መርከብ
እንድንዘያየር ያሳካልን ያ ረብ
ወደድኩሽ ምን ላድርግ እንዴት ይሻለኛል
በድንገት ስትጠፊ ድብርት ይጫነኛል
የማረከኝ ወኔሽ የጥንካሬሽ አውድ
ትምርት ሁኖኛል ጀግና ነሽ የኔ ውድ
በአረብ በረሀ በሚንቀለቀለው
በብርዱ ታፍነሽ በሚቆራጠመው
ቁመሽ ተገትረሽ በአረቦች ስራ
ሳይበግርሽ ቅንጣት የምሽቱ ዳራ
ሳትንገዳገጂ ልንክ እንደተራራ
ትቀስሚያለሽ እውቀት ኢልምሽ እንዲያፈራ
የአንችን ገድል ታሪክ የወኔሽን ማጀት
አይዘልቀውምና የቃላት ቅንጅት
አሏህ ይጠብቅሽ ልበልሽ ጠቅልየ
የአኼራ እህቴ ውስጤ ነሽ እምዬ
ሀገርም ያላችሁ ባህር ወዳ ማዶ
በናንተ ሰቀቀን በናፍቆት ማገዶ
ልባችን ሊያልቅ ነው ተንዶ ተንዶ
እስገምንገናኝ ጀልባው ተሰርጉዶ
የተጋረደብን ሂጃቡ ተቀዶ
አትራቁን በጭራሽ በተቻለ መጠን
እንወዳችኋለን ባህሩን አቋርጠን
በመንሀጃችሁ ላይ_ ሳትንሸራተቱ
በተውሂድ ደምቃችሁ _ሽርክ ሳትወዝቱ
ሱንዩን አቅፋችሁ _ቃሚ ሳትገዝቱ
አድሩስ ሳታጨሱ _ ዱቤ ሳትገትቱ
በሱና ደምቃችሁ ኒቃብ ሳታወልቁ
በኢስላም መርህ ላይ ከፈሩ ሳትወልቁ
ከፀና አቋማችሁ ሳትነቃነቁ
ጠብቁኝ አልቀርም በናፍቆት ሰስቸ
በርቱ የኔ ጀግኖች ውድ ንግስቶቸ
ደግሞም ታምራለችሁ የሱና እህቶቸ
🔷ከምወዳችሁ እህታችሁ ኡሙ ሓቲም
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
ድንጋይን ለማንቀሳቀስ ከመሞከር መንገድሽን ቀይረሽ ማለፍ ብዙ ጊዜ ከፍ ያለ ጥበብ ነው
አንዳንድ ጊዜ የሕይወት ውበት ያለው ድንጋዩን ሰብሮ በማለፍ ሳይሆን ድንጋዩን ትቶ ሌላ የሚያምር መንገድ በመምረጥ ላይ ነው።
ጉዞ ወደፊት✍️
Repost from قناة أبي عمار أمير بن محمد አሚር ሙሐመድ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ብስራት፡
ነገ (እሁድ) ምሽት ከ3፡00 ጀምሮ የኡስታዝ አቡ ዐማር አሚር ሙሐመድ እና የእህታችን ሱመያ ዐበዱልቃዲር የሰርግ ፕሮግራም መሰረት አድርገን የደዕዋ ፕሮግራም ማዘጋጀታችንን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
ስለሆነም ተጋባዥ ኡስታዞቻችን፦
=>ሸይኽ አቡ ዐማር አወል ቢን አሕመድ
=>ኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸዲር ቢን አሕመድ
=>ኡስታዝ አቡ ሙስዐብ አወል አሕመድ
=>ኡስታዝ ዐብዱልጀዋድ
=>ኡስታዝ አቡ ሉቅማን ሑሰይን
=>ኡስታዝ አቡ ዒምራን ዐጃኢቡ
=>ኡስታዝ አቡ ዑበይዳ ሰዒድ
=>ኡስታዝ አቡ አይመን ዐብዱልመሊክ
=>ኡስታዝ አቡ ጁለይቢብ ኢድሪስ መሕሙድ
*እሁድ ምሽትን ከእኛ ጋር!
የስርጭት ሊንክ፦
t.me/ABUOMAR_AMIRMUHAMMED
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
👉እስላማዊ Content ያላቺሁ የቻናል ባለቤቶች ቻናላቺሁን በነፃ ላሳድግላቺሁ ነዉ የቀረው ትንሽ ሰው ነዉ መግባት የምትፈልጉ ቶሎ አናግሩኝ
🚀
𝙉𝙪𝙧 ᴾʳᵒᵐᵒᵗⁱᵒⁿ🚀 👉 1k+ subscribers 👉 10k+ subscribers 👉 15k+ subscribers 👉 20k+ subscribers 👉 50k+ subscribers 👉 100k+ subscribers "🙅♂️ ከ1000 በታች ያላቹ እንዳትመጡ 👆 በቀን አንዴ ብቻ ስለሚለቀቅ ቻናላቺሁ ምንም አይጎዳም
ቤተሰብ ፈገግ በሉማ ሀቂቃ እኔ የለሁም ዛሬ😂
👇👇
የወደፊት ትውልድ ላይ ተፅዕኖ ልጆች ወላጆቻቸው ሲቃሙ እያዩ ያድጋሉ። ይህ ማለት ወላጆች ለልጆቻቸው "ሱስን" እንደ መደበኛ የአኗኗር ዘይቤ እያስተማሩዋቸው ነው ማለት ነው።
አህባሽ ስታገቢ እደዚህ ነሽ ከታች ያለውን አንብቢ
አንድ ባልና ሚስት ነበሩ። ሁለቱም በየቀኑ በምሽት ጫት መቃም ልማድ ነበራቸው። መጀመሪያ ላይ "አብረን የምንጨዋወትበት፣ የምንወያይበት ጊዜ ነው" ብለው ጀመሩት። ነገር ግን ጊዜ እየሄደ ሲሄድ ጫቱ የፍቅር መነጋገሪያ ሳይሆን፣ የሰዓት ስርቆት መሳሪያ ሆነባቸው።
ከዕለታት አንድ ቀን} ከልጆቻቸው መካከል ትንሹ በጠና ታመመ። ልጁ በከፍተኛ ህመም ላይ ሆኖ እያለ፣ ባልና ሚስቱ የጫት ሱስ ስላሸነፋቸው፣ ህመሙን በጊዜ አስተውለው ወደ ጤና ጣቢያ መውሰድ ተሳናቸው። በጫት መረበሽና ስካር ውስጥ የነበሩት ወላጆች፣ ልጁ ሲያለቅስ እንኳን መስማት ተስኗቸው በሱስ ላይ ቆይተው ነበር።
በማለዳ ሲነቁ ልጃቸው ሁኔታው በጣም ተባብሶ አገኙት። ወደ ሆስፒታል ሲሮጡ ሐኪሙ "አምስት ሰዓት ቀድማችሁ ብትመጡ ኖሮ ይህ ሁሉ መከራ አይገጥመውም ነበር" አላቸው። በዚያች ቅፅበት ባልና ሚስቱ ተያይዘው ተላቀሱ። በየዕለቱ የገዙት ያ ጫት} የልጃቸውን ጤናና የቤተሰባቸውን ሰላም እንደሚሰርቅ የገባቸው ያኔ ነበር።
የጫት ውድቀት
ጫት ለባልና ሚስት የሚሰጠው የሐሰት ደስታ እንጂ እውነተኛ መረጋጋት አይደለም። የሚከተሉትን ነጥቦች በማስተዋል እንመልከት፡
የጊዜ መባከን፡ በየቀኑ ለዚህ የሚጠፋው 4 እና 5 ሰዓት ለወደፊት ዕቅድ ለትምህርት፣ ወይም ከልጆች ጋር ጥራት ያለው ጊዜ ለማሳለፍ ሊውል የሚችል ነበር።
የስሜት መራራቅ፡ ጫት የሚቃምበት ሰዓት ላይ የሚፈጠረው የሐሳብ መበታተን፣ በባልና ሚስት መካከል መኖር ያለበትን የፍቅር ውይይት ይገድላል። ጫት የገባበት ቤት ሰላም ይወጣል ብስጭትና ጭቅጭቅ ይገባል
የኢኮኖሚ መሸርሸር ለጫት እና ለተያያዥ ወጪዎች (እንደ ሺሻ} ሲጋራ ወደ መጠጦች) የሚወጣው ገንዘብ፣ ለቤተሰብ ሀብት ግንባታ ቢውል ኖሮ ምን ያህል ለውጥ ያመጣ ነበር
ሶሉ አለነብይ
ነብዩ ሙሀመድ እድህ ብለዋል)
በቂያማህ ቀን ሀቆችን የበደል ካሳወችን ፦ ለባለቤቷ ትመልሳላቹህ።
ቀንድ ለሌላት በግ ቀንድ ባላት በግ መብቷ [በደሏ] እስኪመለስላት ድረስ]
ሙስሊም ዘግበውታል
ያአሏህ ታዳ ስቶቻቺን ነን የሰዎች ሀቅ ያለብን💧💧
ሶለዋትማውረድ እንብዛ
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
(أكثروا الصلاة عليَّ يوم الجمعة وليلة الجمع
فمن صلى عليَّ صلاة صلى الله عليه عشراً)
🌺اللهم صل وسلم على نبينا محمدﷺ
🌺اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
🌺اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
قال تعالى : "وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا أَصَابَكَ"
« አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፡- “በሚደርስብህ ነገር ላይ ታገስ።”
« قال الشيخ صالح بن فوزان الفوزان
حفظه الله :
«ሸይኽ ሳሊህ ኢብኑ ፈውዛን አል-ፈውዛን (አላህ ይጠብቃቸዉ) እንዲህ ብለዋል፡-
« الذي يأمر بالمعروف وينهى عن #المنكر يناله مشقة، يناله أذى من الناس، يناله لوم أو تهديد، فيصبر على ذلك.
«በመልካም ነገር የሚያዝ እና ከክፉ ነገር የሚከለክል ሰው ከሰዎች የሚመጣ ችግር፣ ጉዳት፣ ወቀሳ ወይም ዛቻ ያጋጥመዋል፣ እናም በዚህ መታገስ አለበት።»
📚التعليق على رسالة : وجوب الأمر بالمعروف ( ٣٢)
=
t.me/https_Asselefya1
አንብቡት ትጠቀሙበት አላችሁ ተቃጠልን እኮ ጎበዝ የሰው ባል መቀማት ጀመራችሁ ማለት ነው ❗
+2
ዛፈራን ተፈጥሯዊ የደስታ ስሜት እንዲፈጠር የሚያግዝ ንጥረ ነገር አለው ጭንቀትንና ድብርት ለመቀነስ ይረዳል።
በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል ለሰውነት ጉልበት ይሰጣል
ናና ቅጠል የሆድ መተንፈስን የሆድ ድርቀትን እና የምግብ አለመፈጨትን ችግሮች ያስታግሳል።
ጉንፋን በሚኖርበት ጊዜ የአፍንጫ መዘጋትን በመክፈት ለመተንፈስ ምቾት ይሰጣል።
ሁለቱ ቅመሞች ሲጣመሩ ሰውነትን የሚያዝናኑ የምግብ መፈጨትን የሚያስተካክሉ እና በተለይም በስራ ቀን የሚፈጠርን የድካም ስሜትና የውስጥ ጭንቀትን በማስወገድ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።
ይህ መጠጥ በተለይ ከምግብ በኋላ ወይም ለጥቂት እረፍት በሚወሰድበት ሰዓት በጣም ተስማሚ ነው።
ጠጡ ተብላቹሀል ቤተሰብ ደግሞ አታበሳጩኝ ... 👌✅
Repost from 🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
*_እህት አለም ሰወች ዘንድ ለመወደድና እነርሱን ለመምሰል ብለሽ አስመሳይና አጭረፋራፊ አትሁኝ ::*_
እየውልሽ እህቴ ሰወች እያስመሰሉ እያጭረፈረፉ ለግዜው ደስተኛና ስኬታማ የሆኑ ቢመስሉሽና ቢመስላቸው ግን እውነቱ ሌላነው
እነርሱ ማስመሰላቸው ማጭረፍረፋቸው ምን ያክል ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው ያውቃሉ ምክናየቱም ሰወች ናቸውና የማሰቢያ ጭንቅላት አላቸው ግን ችግሩ ከዛተግባር አልተወገዱም
እመኒኝ እህቴ ውሸታሞች አስመሳይወች ሳቃቸው አጭር ደስታቸው ትንሽ ስኬታቸው ከጫፍ ሳይደርስ የሚቀነጠስ ነው ፡፡
እውነተኞች ግን ሳቃቸው ቢያንስ ለግዜው ደስታ ቢያጡና የሚደሰቱበት ቀን አንሶ የሚያዝኑበትና የሚተክዙበት ቀን በጣም ቢበዛም የደስታቸውን የስኬታቸውን ማማ የሚደርሱበት / የሚያገኙበት ቀን ግን አይርቅም፡፡ ምክናየቱም እውነተኞች ናቸው ጌታቸውን ይፈራሉ በሰወች ፊት ቢዋሹ ቢያስመስሉ አሏህ እንደሚያዋርዳቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ ስለዚህ እውነትን ይዘው መጋፈጥን ነው የሚመርጡት
*_እናማ እልሻለሁ ውዷየ ከእውነተኞቹ እንሁን፡፡*_
ይህን ስታረጊ በዙሪያሽ ያሉሰወች ሊርቁሽ ሊያጣጥሉሽ ይችላሉ አንችግን በእውነተኝነትሽና በታማኝነትሽ ምንግዜም አሸናፊ ሁኝ፡፡
+1
ስደት ከሰው መራቅ ነው እንጂ ከሃይማኖት መራቅ አይደለም። በቲክቶክ ላይ የምትታዪው አጭር የደስታ ጊዜ በጀሀነም እሳት የምትከፍይው የረጅም ጊዜ ዋጋ አለው። እህቴ ሆይ! ስደትሽ የሂዳያ ሰበብ ይሁን እንጂ የፈሳድ መክፈቻ አትሁኚ። ተመለሺ / አላህ ከእርሱ የሚመለስን ባሪያውን ይወዳልና።
#ያረብ ....
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
ስደት ከሰው መራቅ ነው እንጂ ከሃይማኖት መራቅ አይደለም። በቲክቶክ ላይ የምትታዪው አጭር የደስታ ጊዜ በጀሀነም እሳት የምትከፍይው የረጅም ጊዜ ዋጋ አለው። እህቴ ሆይ! ስደትሽ የሂዳያ ሰበብ ይሁን እንጂ የፈሳድ መክፈቻ አትሁኚ። ተመለሺ / አላህ ከእርሱ የሚመለስን ባሪያውን ይወዳልና።
#ያረብ ....#
https://t.me/umu_afifah_ami_chanal
Repost from ስለ ቀልባችን
ዛሬ ላይ ሶሻል ሚዲያ የሁላችንም ትልቅ ፈተና ሆኗል። በቤትም ሆነ በመስጊድ ሳይቀር ቀልባችንን ሰርቆት ውድ ጊዜያችንን እየወሰደብን ይገኛል።
አንዳንዴ በሚዲያ ላይ የምናሳልፈው ጊዜ ለኽይር ነገር ቢሆን እንኳ፤ ቆም ብለን ራሳችንን መፈተሽ ብልህነት ነው። «ከዚህ ሚዲያ በስተጀርባ የተሻሉ መልካም ነገሮችን እያሳለፍኩ ይሆን? የዕለት ተዕለት ኃላፊነቴን በአግባቡ እየተወጣሁ ነው? ለልጆቼና ለትዳር አጋሬ የሚገባቸውን ትኩረትና ጊዜ እየሰጠሁ ነው ወይስ ማኅበራዊ ሚዲያው ሐቃቸውን እንዳጓድል መሰናክል ሆኖብኛል?» ብለን ራሳችንን እንጠይቅ።
በተለይ ይህንን የክረምት ወቅት በተሻለና ይበልጥ ፍሬያማ በሆነ መልኩ ለመጠቀም አሁኑኑ ፕሮግራም ብናወጣ መልካም ነው። አላህ ይገዘን!
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
💎 "ልክ እንደ ውድ ሽቶ ሁኚ ሰዎች ባያዩሽ እንኳ መገኘትሽና ያማረው ንግግርሽ ሁሌም ደስ የሚል ጠረን ጥሎ ያልፋል።"
በሰዎች ልብ ውስጥ የምትተያት ትናንሽ መልካም ነገሮች ነገ በትልቅ ክብር ተመልሰው ዋጋሽ ይሆናሉ።
ገባ ገባ በሉ ተጋብዛቹሀል ✍🌸
https://t.me/Asslfyaa 👑
⚠️ተውሒድ ማለት እንዲሁ የምንሸመድደው የመጽሐፍ ገጽ፣ በብዕር የምንከትበው ቃል ወይም በሚንበሮች ላይ የሚደረግ ደረቅ ንግግር ብቻ አይደለም። ተውሒድ ማለት ከልብ ጥልቀት የሚመነጭ፣ በደም ስራችን ውስጥ የሚፈስና ሙሉ ሕይወታችንን ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ብቻ የምናስገዛበት የታላቅነት መገለጫ ነው። ተውሒድ ማለት በልብ ውስጥ ከአንድ አምላክ ከአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ውጭ ሌላን ኃይል አለማስገባት፣ በምክንያቶች ሳይሆን በምክንያቶች ፈጣሪ ላይ ብቻ
መመካት ነው።
እወቁ... ከአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى በስተቀር አድራጊ የለም! የሚጠቅመውም፣
የሚጎዳውም፣ የሚያከብረውም፣ የሚያዋርደውም፣ የሚያበለጽገውም፣ የሚያደኸየውም፣ ሕይወት የሚሰጠውም፣ የሚገድለውም እርሱ ብቻ ነው። ፍጡራን ሁሉ ደካሞች ናቸው፤ ሐኪሞች ይታመማሉ፣ መሐንዲሶች ይሳሳታሉ፣ ኃያላን ይወድቃሉ። አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ግን የዓለማቱ ጌታ፣ የሰማያትና የምድር ብቸኛ አስተናባሪ ነው። ፀሐይን ያለ ስህተት በምህዋሯ የሚያስኬደው፣ ሰማያትን ያለ ምሰሶ የጠበቃቸውና አንዲት ቅንጣት እንኳ የማታመልጠው ሐፊዝ (ጠባቂ) የሆነው ጌታ እርሱ ነው። አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ለነቢዩ ሙሳ عَلَيْهِ السَّلَامُ እንዳለው፦ "ሙሳ ሆይ! እኔ ብተኛ ኖሮ ሰማያት
በምድር ላይ ይወድቁ ነበር።" ነገር ግን እርሱ የማይተኛ፣ የማይረሳና ሁልጊዜም ከባሮቹ ጋር የሆነ ኃያል ጌታ ነው።
አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ካንተ ጋር ከሆነ ከማን ትሰጋለህ? በሕመምህ ሰዓት ወደ አላህ ተጠጋ። የትዳር አጋርህ ስታስቀይምህ ወደ አላህ ጩህ። ልጅህ ሲከዳህ ወደ አላህ ተመለስ። ጭንቀትህ ሲበዛና ሲሳዩ ሲጠብብህ የመውጫውን በር ከአላህ ዘንድ ፈልገው። ሰዎች ቢርቁህ ወደ አላህ ቅረብ፤ ምክንያቱም የሁሉ ነገር ቁልፍ ያለው በእርሱ እጅ ብቻ ነውና። እነዚያ ‹ኃያላን ነን›
ያሉትን ፈርዖንንና ሰሙድን አላህ የት እንዳደረሳቸው ታሪክ ምስክር ነው? በእርሱ ፊት የትኛው ምድራዊ ኃይል ይቆማል ነገር ግን? አላህ የፈለገውን ሰሪ ነው። የእርሱ ትእዛዝ አይመለስም፣ የእርሱ ኃይል አይገታም።
ስለዚህ በየትኛውም የሕይወት አጣብቂኝ ውስጥ ብንሆን፣ ልክ ነቢዩ መሐመድ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ በዋሻ ውስጥ ሆነው ለጓደኛቸው ለአቡ በክር رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ እንዳሉት እኛም ለነፍሳችን እንዲህ እንበላት፦ "አትዘን! አላህ ከእኛ ጋር ነው!"።
እውነተኛ ተውሒድ ይኸው ነው! ሰላም
የሚገኘው ወደ አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى በመቃረብና በእርሱ ውሳኔ በመርካት ውስጥ ብቻ ነው። ዛሬም ነገም
ለስኬትና ለደስታ የሚበቃው አላህን ብቻ መከታ ያደረገ ልብ ነው።
ኢላሒ..! በልባችን ውስጥ እውነተኛውን ተውሒድ ዝራብን። ካንተ ውጭ ላለ ማንኛውም ኃይል እንዳንሰግድና እንዳንዋረድ በእምነታችን አጽናን። መጨረሻችንንም በተውሒድ ቃል አሳምርልን።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
