الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
前往频道在 Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
显示更多未指定国家未指定类别
2 186
订阅者
+2824 小时
+447 天
+45130 天
帖子存档
እህቶቼ፡ ራስን ማክበር እና የራስን ዋጋ ማወቅ?!
በዚህ ዘመን፣ ሴት ልጅ "አግባኝ" የሚል ድፍረት ብታሳይም ውጤቱ ግን በተቃራኒው እየሆነ መጥቷል። እውነት ነው በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘመን ሴቶች መብታቸውን በነፃነት ይገልጹ ነበር ነገር ግን ያኔ የነበረው የወንዶች ታማኝነት እና አክብሮት ዛሬ የለም። ዛሬ ላይ የዋህነትሽ እንደ መሳሪያ እየተወሰደ ነው። ዛሬ ላይ ብዙዎች የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ ስም ብቻ በመጥቀስ በተግባር ግን የሴትን ክብር የማይጠብቁበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ስለዚህ፡ አስቢ በደንብ ውዷ እህቴ ? ለምኖ አግብቶሽ በመካከላቹህ መገጫጨት ተፈጥሮ የራሱ ጥፋት የራሱ ችግር ሆኖ ሳለ አቺ ለትዳርሽ ብለሽ ይቅርታ ብትጠይቂው ይቅርታ ስላልሺኝ ነውጂ ድሮስ መች ... ብሎ የሚሰብርሺን እደት ነው አግባኝ የምትይው ነብዩን አይምሰልሽ ✅ በእርግጥ አሳፋሪ የሆነ ዘመን ላይ ደርሰናል። ጥፋተኛው ወንድ፣ ይቅርታ መጠየቅ ቀርቶ፣ ሴት ልጅ ይቅርታ እንድትለምነው የሚፈልግበት ደረጃ ላይ መድረሱ የቁልቁለት ጉዞ ነው ለራሱ ክብር ለሌለው ሰው ይቅርታ መጠየቅ ከበዳይሽ ፊት መውደቅ ነው። አንቺ ክቡር ነሽ ስለዚህ ክብርሽን በሚገፍፉ ሰዎች ፊት መዋረድ አያስፈልግም። ምናልባት አሏህ ያዘነላቸው ሊኖሩኮ ይቺላሉ ግን ግን ታገሺ በዱዓለይ ጠንከር በይ እንጂ አግባኝ አትበይው ?!
🙌🙌 አቁሚ እህት አለሜ ተናግሬለሁኝ
🎙 ፕሮግራሙ ጀምራል
ተ
ጀ
መ
ረ
ገባ ገባ በሉ
➘ ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘ ➘
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/+jP5daAxIoSllNDdk
ሸር ሸር አድርጉ ባረካላሁ ፊኩም
أصبحنا وأصبح الملك لله والحمد لله، لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملكُ وله الحمدُ وهو على كل شيء ٍ قدير، ربِّ أسألك خير ما في هذا اليوم وخير ما بعده، وأعوذ بك من شرِّ ما في هذا اليوم وشرِّ ما بعده، ربِّ أعوذُ بك من الكسل وسُوء الكِـبَـر، ربِّ أعوذ بك من عذابٍ في النارِ وعذابٍ في القبر.
ለራሱ ክብር ለሌለው ሰው ይቅርታ መጠየቅ ከበዳይሽ ፊት መውደቅ ነው። አንቺ ክቡር ነሽ ስለዚህ ክብርሽን በሚገፍፉ ሰዎች ፊት መዋረድ አያስፈልግም።✅👆
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
⛄️ለክረምት የሚነበቡ ምርጥ ኢስላሚክ ታሪክ ትፈልጋላችሁ⁉️
➦ ታሪክ
➦ ቁርአን
➦ ሐዲስ
➦ አጫጭር ምክሮች
👇🏽ከስር ያለዉን ነክተው መቀላቀል ብቻ ፍጠኑ እንዳያመልጣቺሁ 👇🏽
Repost from 🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
_የሱና እህቶቸ___
አልሀምዱሊላሂ ይመስገን ጌታችን
በማይቆጠረው ኒዕማው ላመቻቸን
የነብዩ ኡመት አድርጎን በእዝነቱ
በሱናቸው ግርጌ አስውቦን ሙሚቱ
በጅልባብ በኒቃብ ደምቀን ልንራመድ
ትዛዝ አመጣልን መጠጊያችን ሶመድ
የነብያት መሪ ኢማሙል ቃኢሚን
አሏህ ነገራቸው ተሸፈኑ እንዲሉን
ውበት ነው ማረግ ነው ለሱና መመረጥ
በተውሂድ ተውቦ በአንድነት ማጌጥ
የሱናዋ እህቴ የመንሀጇ ንግስት
ሁሌ ወድሻለሁ እያየሁ በስስት
አገናኘንና የመንሀጅ የአቂዳ ረመጥ
አለያየንና ያገር አቀማመጥ
በሙሀባሽ ግርጌ ሁሌ ስትናፍቂኝ
አለሁ ዛሬም ድረስ ልቤን ስትደልቂኝ
በርቀት ከንፌ ደስታሽን ስሰማ
ዳዕዋ ወጥነሻል በጠንካራው ማማ
አምልኩት በማለት አረሂሙ ሯህማ
በቂርአት ደምቀሽ ኢልምን ስትሾፍሪ
ከማዳም ቤት ሁነሽ ድካምን ሳትፈሪ
በአንድ እጅሽ ስትሞጥይ በአንዱ ስትሰሪ
እጅጉን ደስ አለኝ የብርታትሽ ድግሪ
የመንሀጅ እህቴ የሱናዋ ኮከብ
በአንድነት ደምቀን በመሀባው መርከብ
እንድንዘያየር ያሳካልን ያ ረብ
ወደድኩሽ ምን ላድርግ እንዴት ይሻለኛል
በድንገት ስትጠፊ ድብርት ይጫነኛል
የማረከኝ ወኔሽ የጥንካሬሽ አውድ
ትምርት ሁኖኛል ጀግና ነሽ የኔ ውድ
በአረብ በረሀ በሚንቀለቀለው
በብርዱ ታፍነሽ በሚቆራጠመው
ቁመሽ ተገትረሽ በአረቦች ስራ
ሳይበግርሽ ቅንጣት የምሽቱ ዳራ
ሳትንገዳገጂ ልንክ እንደተራራ
ትቀስሚያለሽ እውቀት ኢልምሽ እንዲያፈራ
የአንችን ገድል ታሪክ የወኔሽን ማጀት
አይዘልቀውምና የቃላት ቅንጅት
አሏህ ይጠብቅሽ ልበልሽ ጠቅልየ
የአኼራ እህቴ ውስጤ ነሽ እምዬ
ሀገርም ያላችሁ ባህር ወዳ ማዶ
በናንተ ሰቀቀን በናፍቆት ማገዶ
ልባችን ሊያልቅ ነው ተንዶ ተንዶ
እስገምንገናኝ ጀልባው ተሰርጉዶ
የተጋረደብን ሂጃቡ ተቀዶ
አትራቁን በጭራሽ በተቻለ መጠን
እንወዳችኋለን ባህሩን አቋርጠን
በመንሀጃችሁ ላይ_ ሳትንሸራተቱ
በተውሂድ ደምቃችሁ _ሽርክ ሳትወዝቱ
ሱንዩን አቅፋችሁ _ቃሚ ሳትገዝቱ
አድሩስ ሳታጨሱ _ ዱቤ ሳትገትቱ
በሱና ደምቃችሁ ኒቃብ ሳታወልቁ
በኢስላም መርህ ላይ ከፈሩ ሳትወልቁ
ከፀና አቋማችሁ ሳትነቃነቁ
ጠብቁኝ አልቀርም በናፍቆት ሰስቸ
በርቱ የኔ ጀግኖች ውድ ንግስቶቸ
ደግሞም ታምራለችሁ የሱና እህቶቸ
🔷ከምወዳችሁ እህታችሁ ኡሙ ሓቲም
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
https://t.me/+o7ZrQFQjILVhNDVk
ድንጋይን ለማንቀሳቀስ ከመሞከር መንገድሽን ቀይረሽ ማለፍ ብዙ ጊዜ ከፍ ያለ ጥበብ ነው
አንዳንድ ጊዜ የሕይወት ውበት ያለው ድንጋዩን ሰብሮ በማለፍ ሳይሆን ድንጋዩን ትቶ ሌላ የሚያምር መንገድ በመምረጥ ላይ ነው።
ጉዞ ወደፊት✍️
Repost from قناة أبي عمار أمير بن محمد አሚር ሙሐመድ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ብስራት፡
ነገ (እሁድ) ምሽት ከ3፡00 ጀምሮ የኡስታዝ አቡ ዐማር አሚር ሙሐመድ እና የእህታችን ሱመያ ዐበዱልቃዲር የሰርግ ፕሮግራም መሰረት አድርገን የደዕዋ ፕሮግራም ማዘጋጀታችንን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
ስለሆነም ተጋባዥ ኡስታዞቻችን፦
=>ሸይኽ አቡ ዐማር አወል ቢን አሕመድ
=>ኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸዲር ቢን አሕመድ
=>ኡስታዝ አቡ ሙስዐብ አወል አሕመድ
=>ኡስታዝ ዐብዱልጀዋድ
=>ኡስታዝ አቡ ሉቅማን ሑሰይን
=>ኡስታዝ አቡ ዒምራን ዐጃኢቡ
=>ኡስታዝ አቡ ዑበይዳ ሰዒድ
=>ኡስታዝ አቡ አይመን ዐብዱልመሊክ
=>ኡስታዝ አቡ ጁለይቢብ ኢድሪስ መሕሙድ
*እሁድ ምሽትን ከእኛ ጋር!
የስርጭት ሊንክ፦
t.me/ABUOMAR_AMIRMUHAMMED
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
👉እስላማዊ Content ያላቺሁ የቻናል ባለቤቶች ቻናላቺሁን በነፃ ላሳድግላቺሁ ነዉ የቀረው ትንሽ ሰው ነዉ መግባት የምትፈልጉ ቶሎ አናግሩኝ
🚀
𝙉𝙪𝙧 ᴾʳᵒᵐᵒᵗⁱᵒⁿ🚀 👉 1k+ subscribers 👉 10k+ subscribers 👉 15k+ subscribers 👉 20k+ subscribers 👉 50k+ subscribers 👉 100k+ subscribers "🙅♂️ ከ1000 በታች ያላቹ እንዳትመጡ 👆 በቀን አንዴ ብቻ ስለሚለቀቅ ቻናላቺሁ ምንም አይጎዳም
ቤተሰብ ፈገግ በሉማ ሀቂቃ እኔ የለሁም ዛሬ😂
👇👇
የወደፊት ትውልድ ላይ ተፅዕኖ ልጆች ወላጆቻቸው ሲቃሙ እያዩ ያድጋሉ። ይህ ማለት ወላጆች ለልጆቻቸው "ሱስን" እንደ መደበኛ የአኗኗር ዘይቤ እያስተማሩዋቸው ነው ማለት ነው።
አህባሽ ስታገቢ እደዚህ ነሽ ከታች ያለውን አንብቢ
አንድ ባልና ሚስት ነበሩ። ሁለቱም በየቀኑ በምሽት ጫት መቃም ልማድ ነበራቸው። መጀመሪያ ላይ "አብረን የምንጨዋወትበት፣ የምንወያይበት ጊዜ ነው" ብለው ጀመሩት። ነገር ግን ጊዜ እየሄደ ሲሄድ ጫቱ የፍቅር መነጋገሪያ ሳይሆን፣ የሰዓት ስርቆት መሳሪያ ሆነባቸው።
ከዕለታት አንድ ቀን} ከልጆቻቸው መካከል ትንሹ በጠና ታመመ። ልጁ በከፍተኛ ህመም ላይ ሆኖ እያለ፣ ባልና ሚስቱ የጫት ሱስ ስላሸነፋቸው፣ ህመሙን በጊዜ አስተውለው ወደ ጤና ጣቢያ መውሰድ ተሳናቸው። በጫት መረበሽና ስካር ውስጥ የነበሩት ወላጆች፣ ልጁ ሲያለቅስ እንኳን መስማት ተስኗቸው በሱስ ላይ ቆይተው ነበር።
በማለዳ ሲነቁ ልጃቸው ሁኔታው በጣም ተባብሶ አገኙት። ወደ ሆስፒታል ሲሮጡ ሐኪሙ "አምስት ሰዓት ቀድማችሁ ብትመጡ ኖሮ ይህ ሁሉ መከራ አይገጥመውም ነበር" አላቸው። በዚያች ቅፅበት ባልና ሚስቱ ተያይዘው ተላቀሱ። በየዕለቱ የገዙት ያ ጫት} የልጃቸውን ጤናና የቤተሰባቸውን ሰላም እንደሚሰርቅ የገባቸው ያኔ ነበር።
የጫት ውድቀት
ጫት ለባልና ሚስት የሚሰጠው የሐሰት ደስታ እንጂ እውነተኛ መረጋጋት አይደለም። የሚከተሉትን ነጥቦች በማስተዋል እንመልከት፡
የጊዜ መባከን፡ በየቀኑ ለዚህ የሚጠፋው 4 እና 5 ሰዓት ለወደፊት ዕቅድ ለትምህርት፣ ወይም ከልጆች ጋር ጥራት ያለው ጊዜ ለማሳለፍ ሊውል የሚችል ነበር።
የስሜት መራራቅ፡ ጫት የሚቃምበት ሰዓት ላይ የሚፈጠረው የሐሳብ መበታተን፣ በባልና ሚስት መካከል መኖር ያለበትን የፍቅር ውይይት ይገድላል። ጫት የገባበት ቤት ሰላም ይወጣል ብስጭትና ጭቅጭቅ ይገባል
የኢኮኖሚ መሸርሸር ለጫት እና ለተያያዥ ወጪዎች (እንደ ሺሻ} ሲጋራ ወደ መጠጦች) የሚወጣው ገንዘብ፣ ለቤተሰብ ሀብት ግንባታ ቢውል ኖሮ ምን ያህል ለውጥ ያመጣ ነበር
ሶሉ አለነብይ
ነብዩ ሙሀመድ እድህ ብለዋል)
በቂያማህ ቀን ሀቆችን የበደል ካሳወችን ፦ ለባለቤቷ ትመልሳላቹህ።
ቀንድ ለሌላት በግ ቀንድ ባላት በግ መብቷ [በደሏ] እስኪመለስላት ድረስ]
ሙስሊም ዘግበውታል
ያአሏህ ታዳ ስቶቻቺን ነን የሰዎች ሀቅ ያለብን💧💧
ሶለዋትማውረድ እንብዛ
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
(أكثروا الصلاة عليَّ يوم الجمعة وليلة الجمع
فمن صلى عليَّ صلاة صلى الله عليه عشراً)
🌺اللهم صل وسلم على نبينا محمدﷺ
🌺اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
🌺اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
قال تعالى : "وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا أَصَابَكَ"
« አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፡- “በሚደርስብህ ነገር ላይ ታገስ።”
« قال الشيخ صالح بن فوزان الفوزان
حفظه الله :
«ሸይኽ ሳሊህ ኢብኑ ፈውዛን አል-ፈውዛን (አላህ ይጠብቃቸዉ) እንዲህ ብለዋል፡-
« الذي يأمر بالمعروف وينهى عن #المنكر يناله مشقة، يناله أذى من الناس، يناله لوم أو تهديد، فيصبر على ذلك.
«በመልካም ነገር የሚያዝ እና ከክፉ ነገር የሚከለክል ሰው ከሰዎች የሚመጣ ችግር፣ ጉዳት፣ ወቀሳ ወይም ዛቻ ያጋጥመዋል፣ እናም በዚህ መታገስ አለበት።»
📚التعليق على رسالة : وجوب الأمر بالمعروف ( ٣٢)
=
t.me/https_Asselefya1
አንብቡት ትጠቀሙበት አላችሁ ተቃጠልን እኮ ጎበዝ የሰው ባል መቀማት ጀመራችሁ ማለት ነው ❗
+2
ዛፈራን ተፈጥሯዊ የደስታ ስሜት እንዲፈጠር የሚያግዝ ንጥረ ነገር አለው ጭንቀትንና ድብርት ለመቀነስ ይረዳል።
በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል ለሰውነት ጉልበት ይሰጣል
ናና ቅጠል የሆድ መተንፈስን የሆድ ድርቀትን እና የምግብ አለመፈጨትን ችግሮች ያስታግሳል።
ጉንፋን በሚኖርበት ጊዜ የአፍንጫ መዘጋትን በመክፈት ለመተንፈስ ምቾት ይሰጣል።
ሁለቱ ቅመሞች ሲጣመሩ ሰውነትን የሚያዝናኑ የምግብ መፈጨትን የሚያስተካክሉ እና በተለይም በስራ ቀን የሚፈጠርን የድካም ስሜትና የውስጥ ጭንቀትን በማስወገድ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።
ይህ መጠጥ በተለይ ከምግብ በኋላ ወይም ለጥቂት እረፍት በሚወሰድበት ሰዓት በጣም ተስማሚ ነው።
ጠጡ ተብላቹሀል ቤተሰብ ደግሞ አታበሳጩኝ ... 👌✅
Repost from 🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
*_እህት አለም ሰወች ዘንድ ለመወደድና እነርሱን ለመምሰል ብለሽ አስመሳይና አጭረፋራፊ አትሁኝ ::*_
እየውልሽ እህቴ ሰወች እያስመሰሉ እያጭረፈረፉ ለግዜው ደስተኛና ስኬታማ የሆኑ ቢመስሉሽና ቢመስላቸው ግን እውነቱ ሌላነው
እነርሱ ማስመሰላቸው ማጭረፍረፋቸው ምን ያክል ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው ያውቃሉ ምክናየቱም ሰወች ናቸውና የማሰቢያ ጭንቅላት አላቸው ግን ችግሩ ከዛተግባር አልተወገዱም
እመኒኝ እህቴ ውሸታሞች አስመሳይወች ሳቃቸው አጭር ደስታቸው ትንሽ ስኬታቸው ከጫፍ ሳይደርስ የሚቀነጠስ ነው ፡፡
እውነተኞች ግን ሳቃቸው ቢያንስ ለግዜው ደስታ ቢያጡና የሚደሰቱበት ቀን አንሶ የሚያዝኑበትና የሚተክዙበት ቀን በጣም ቢበዛም የደስታቸውን የስኬታቸውን ማማ የሚደርሱበት / የሚያገኙበት ቀን ግን አይርቅም፡፡ ምክናየቱም እውነተኞች ናቸው ጌታቸውን ይፈራሉ በሰወች ፊት ቢዋሹ ቢያስመስሉ አሏህ እንደሚያዋርዳቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ ስለዚህ እውነትን ይዘው መጋፈጥን ነው የሚመርጡት
*_እናማ እልሻለሁ ውዷየ ከእውነተኞቹ እንሁን፡፡*_
ይህን ስታረጊ በዙሪያሽ ያሉሰወች ሊርቁሽ ሊያጣጥሉሽ ይችላሉ አንችግን በእውነተኝነትሽና በታማኝነትሽ ምንግዜም አሸናፊ ሁኝ፡፡
