fa
Feedback
Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና

Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና

رفتن به کانال در Telegram

- እውነተኛ የህይወት ታሪኮች - ኢስላማዊ የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ። - ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ። - ሳምንታዊ ሽልማቶች ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ የአይምሮ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ ጥያቄ ለማቅረብ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
761
مشترکین
+2324 ساعت
+1617 روز
+36130 روز
آرشیو پست ها
ሀሰድ/ምቀኝነት ወይም መጥፎ ቅናት ብዙ ሰው የሚፈተንበት የቀልብ ህመም አይነት ነው። ነፍሳችን የታችኛው ደረጃ ላይ ሆና መጥፎ ሀሳቦችን እና ተግባሮችን ሳታቋርጥ በምታመነጭበት እርከን ላይ

የታመመ ልብ __ይፈወሳል
Anonymous voting

'ብቸኝነት' ማለት ምን አልባት ሁልጊዜ ብቻህን መሆን ማለት ላይሆን ይችላል ብቸኝነት በሰዎች ተከበህ ማንም ውስጥህን እንዳልተረዳው ሲሰማህ ነው። ብዙ ጊዜ እኛ ግንኙነትን በመልእክት ቅይይሮች ፣ በተከታይ ብዛት እና በውይይቶች እንለካ ይሆናል ግን 'መገናኘት' እና 'ግንኙነት' የተለያዩ ነገሮች ናቸው ። anonymous ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ

ሩህ/መንፈስ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ قُلْ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي ۖ وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا ስለ ሩ
ሩህ/መንፈስ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ قُلْ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي ۖ وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا ስለ ሩህ (መንፈስ) ይጠይቁሀል። "ሩህ (መንፈስ) ከጌታዬ ነገር ነው ከእውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም" በላቸው ቁርአን ምዕራፍ 17 አንቀፅ 85 ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ

4.ከድህነት እና የሰውን እጅ ከማየት ለመጠበቅ የሚባል ዱአ      ▪ اللّهُمَّ أَغْنِنِي بِفَضْلِكَ عَمَّن سِوَاكَ አላሁመ አግኒኒ ቢፈድሊከ አመን ሲዋክ "አላህ ሆይ ከአንተ ውጪ ከሆነ አካል ከጃይ/ፈላጊ እንዳልሆን በፀጋህ አብቃቃኝ" የዚህ ዱአ ስነልቦናዊ እና መንፈሳዊ ጠቀሜታዎች - ከአላህ ውጪ ካሉ አካላት ከጃይ ከመሆን እንጠበቃለን - አላህ የፀጋዎቹን በሮች ይከፍትልናል - ባለን ነገር የመብቃቃትን ትሩፋት እናገኛለን

በመጀመሪያ አባትሽ ባያሳድግሽም ቂም እና ቅያሜ ውስጥ ሳትገቢ ዝምድና ለመቀጠል እና ላለመቁረጥ ያሳየሽው ተነሳሽነት የልብሽ መልካምነት እና አላህን የመፍራት ምልክት በመሆኑ በጣም የሚያስደስት እና ተስፋ የሚሰጥ ነገር ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ሰዎች ከወላጅ አባት ተለይቶ በማደግ ምክንያት የተለያየ ችግር ውስጥ ሰዎች በሚያልፉበት አለም አንቺ መልካም እንጀራ አባት ማግኘትሽ አላህ መልካም ውለታ እንደዋለልሽ እና እድለኛ እንደሆንሽ ማሳያ ነው።እሳቸውንም ለበጎነታቸው ሳላመሰግን አላልፍም። ወደ ዋናው ያስጨነቀሽ ጉዳይ ከመዝለቃችን በፊት ከአቅም በላይ በሆነ ጉዳይ ተጠምደን ለመልስ በመዘግየታችን ከልብ ይቅርታ እየጠየቅኩኝ ለጥያቄሽ ቀጥተኛ መልስ እንኳን ባይሆን ሀሳብ እና ማብላያ ይሆናሉ ያልኳቸውን ነጥቦች ልጠቃቅስ ኢንሸአላህ! ወላጅ አባትሽን ለማወቅ እና ለማዋራት ውስጥሽ ሲነሳ ተፈጥሯዊ ማንነትሽን እና መገኛሽን ለማወቅ ካለሽ ተፈጥሯዊ ራስን የማወቅ ጉጉት የመነጨ መሆኑን ማየት ይቻላል። ሰዎች በተሟላ እና ምንም ባልጎደለበት አካባቢ ውስጥ እንኳን እየኖሩ የስጋ ወላጆቻቸውን ፍለጋ ሲባዝኑ መገኝት የሰው ልጅ ባህሪ ነው። የወላጆቻችን ሀቅ የሚመነጨው እኛን በማሳደጋቸው ብቻ ሳይሆን በተፈጥሯዊ ወላጅነታቸውም ጭምር ነው። እንጀራ አባትሽ ባይወልደሹም በ አባትነት ስላሳደጉሽ ያለብሽ የውለታ እና የፍቅር እዳ መከበር ያለበት እና በጣም በክብር ሊጠበቅ የሚገባው ዝምድና መሆኑ ግን በአፅንኦት ይሰመርበት። ወላጅሽን በምትፈልጊበት በዚህ ወቅት የአሳዳጊ አባትሽ ቀልብ እንዳይሰበር እና የመተው እና 'አሳድጌ አሳድጌ' ወደ ወላጇ ሄደች የሚል ችላ የመባል ስሜት እንዳይፈጠርባቸው መጠንቀቅ እና በስነስርዓት ቁጭ ብሎ በመነጋገር አባትሽን ማግኘት እና ዝምድናውንም ማስቀጠል እንደምትፈልጊ የማሳመን ስራ የመስራት ሀላፊነት ይጠብቅሻል። ወላጅሽን መፈለግሽ የነሱን ውለታ መካድ እና መተው አለመሆኑን በሚረዱት ቋንቋ እና በትህትና ንገርያቸው።እንዲያምኑበት የሚወስደውንም ጊዜ በትእግስት ጠብቂ ለሚፈጠርባቸው ግርታ እና ቅሬታ መሠል ሀዘንም ራስሽን አዘጋጂ። እናትሽን በተመለከተ የሚፈልገው የማሳመን ሂደት እና ሁኔታ ከአሳዳጊ አባትሽ የተለየ እና ጠንካራ ሊሆን ይችላል። እናትነቷ ፣ በሱ ላይ ያላት ቅሬታ ፣ እና አንቺን ያለአባትሽ ድጋፍ ማሳደጓ ስለ ዚህ ጉዳይ ያላትን የማቅማማት ደረጃ ከፍ ያደርገዋል። ይህም የሚጠበቅ ነው። ከሁለቱም ጋ የመነጋገሩን እና የማሳመኑን ሂደት በአግባቡ ጨርሰሽ አባትሽን ለማወቅ ግንኙነታችሁንም ለማሳመር ሞክሪ አላህ የመልካም ስራሽን ምንዳ ይከፍልሻል ።ኢንሻአላህ! ✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ። ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን።

ሩህ? (እስካሁን ካየናቸው የኢልመ ነፍስ/የኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ትምህርት ጥያቄ)
Anonymous voting

The Mere Exposure Effect (በብዛት በመጋለጥ ምክንያት መውደድ/መልመድ( የ effecቱ ውጤት መላመድ ነው) ይህን የስነልቦና ዘዴ የማስታወቂያ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዲስቶች ፣ ሀሳብ የሚሸጡ የአለም ሴረኞች ይጠቀሙበታል (በተቃራኒው በጎ ሀሳብን ለመትከልም መዋል የሚችል የስነልቦና ዘዴ መሆኑ አይረሳ!) ይህ ፅንሰ ሀሳብ በአጭር እና በቀላል አማርኛ (exposed) ለአንድ ነገር ተጋላጭ በሆንን መጠንን አንድን ነገር እንለምደዋለን፤ ከዚህ በፊት የምንጠላው ወይም ከእምነታችን ጋር የሚጋጭ ወይም ለህይወታችን የሚያሰጋ ቢሆንም እንኳ። ከዛም የኑሯችን አካል የህይወታችን ተጣማሪ ይሆናል። ብዙ በመጋለጥ ምክንያት ስንት ነገር ለምደን ይሆን? ነውር ያልነውን ለምደነው ተራ ሆኖብናል አስደንጋጭ የነበረው ቀሎናል። በተፈጥራዊ የህይወት ዑደት ምክንያት የተላመድነው ነገር ቢኖርም አሁን ግን ለማየት የፈለግነው ይህ ዘመን በማላመድ ሸፍኖ ስለሚሸጥበት መንገድ ነው። ከተኛንበት ጥልቅ እንቅልፍ ወጥተን በመንፈሳዊነት እንንቃ ከድንዛዜያችንን እንባንን አለምን በኢስላም መነፅር እንያት ከዛ አንድ የማቃናት አሻራችንን እናኑር።

Life is nothing but a constant cycle of reinventing yourself. "ህይወት ሌላ አይደለችም ቋሚነት ያለው እራስን አፍርሶ የመገንባት ሂደት እንጂ'

ከአላህ መራቅ ለጭንቀት ያጋልጣል
Anonymous voting

በአመስጋኝነት ፀጋን የሚያቆይ ዱአ رَبِّ أَوْزِعْنِي أَنْ أَشْكُرَ نِعْمَتَكَ 'ረቢ አውዚእኒ አን አሽኩረ ኒእመተክ' ትርጉም ጌታዬ ያደረክልኝን መልካም ነገር አመሠግን ዘንድ እውቀት እና ግንዛቤ ስጠኝ የዚህ ዱአ ስነልቦናዊ ጠቀሜታዎች -አመስጋኝነትን ያሳድጋል -ከውድቀት የማንሰራራት አቅም ይሰጣል -በጎ አስተሳሰብን ያሳድጋል

የተፈተናችሁበት የራሳችሁ አስቸጋሪ ባህሪ? (ሌላውን ሊጎዳ የሚችል)
Anonymous voting

ተዝኪየቱ ነፍስ/ነፍስን ለማፅዳት 4 ነገር መቀነስ 1 ነገር ማብዛት - ወሬን - ምግብን - ልክ የሌለው ከሰዎች ጋር መቀላቀልን - እንቅልፍ ቀንሱ! 1 ነገር ማብዛት - አዝካር/አላህን ዘውትር ማስታወስ

እዚህ የሚሰጠውን ኢስላማዊ የስነልቦና አገልግሎት
Anonymous voting

ጥያቄ 3 ቅናት እና ምቀኝነት ፈተነኝ! እኔ የ28 አመት ወጣት ሴት ስሆን ።ውስጤን እረፍት የሚነሳኝ የስብእና ቀውስ እና ህመም እንዳለብኝ ይሰማኛል።ይህም ሂስድ/ምቀኝነት ነው ብዬ አምናለሁ። ሰዎች
ጥያቄ 3 ቅናት እና ምቀኝነት ፈተነኝ! እኔ የ28 አመት ወጣት ሴት ስሆን ።ውስጤን እረፍት የሚነሳኝ የስብእና ቀውስ እና ህመም እንዳለብኝ ይሰማኛል።ይህም ሂስድ/ምቀኝነት ነው ብዬ አምናለሁ። ሰዎች በእውቀት በገንዘብ እና በውበት ከኔ የተሻሉ ከመሰለኝ  እርቃቸዋለው። አንዳንዴ በምቀኝነት ተነሳስቼ ልጎዳቸው አስቤ አላህን በመፍራት ትቼዋለው። ከኔ የተሻሉ ሰዎች ሳይ ያላቸው ነገር እንዲጠፋ እፈልጋለው ከስረው ወይም ታመው ማየት ውስጤ ይመኛል። በቃ ውስጤ ሰዎች ከኔ አንሰው እንጂ በልጠው ማየት አይፈልግም። በራሴ ክፋት ተፈተንኩኝ። እረፍት አጣሁኝ። በኢስቲግፋር እና በተውበት ፈጣሪዬ ደጅ ተመላለስኩኝ ህመሜ ግን ጋብ ብሎ ዳግም ያገረሻል። እባክህ ከዚህ ነገር የምድንበትን ምክር ብትለግሰኝ። በፀፀት ታማሚዋ እህታቹ ነኝ። (የጥያቄውን ምላሽ ቻናላችን ላይ ይጠብቁ ኢንሻአላህ!) #ኡስማኒክ_ኢስላማዊ_ስነልቦና ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን።

2. ለ ትእግስት እና ለፅናት የሚጠቅም ዱአ رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا "ረበና አፍሪጝ አለይና ሶብረን ወሰቢት አቅዳመና" "ጌታችን ሆይ! ትእግስትን በኛ ላይ አዝንብ እግራችንንም አፅና(አደላድል) " የዚህ ዱአ ስነ-ልቦናዊ ጥቅሞች ወደ አላህ መጠጋት - ይህ ፀሎት በችግር ወቅት ወደ አላህ መጠጋት እንደሚያስፈልገን በማስታወስ ሰዎች ከሚያስጨንቃቸው ችግር ጋር የመታገልን አቅም ይለግሳቸዋል። ፅናት - የመፅናትን እና የማገገምን ውስጣዊ አቅም ያሳድጋል። ትእግስት • በትዕግሥት ከባድ የህይወት ውጣ ውረዶችን ማለፍ እንደሚቻል ያስታውሳል።

ሰዎችን በሀሜት ማንሳት ማቆም ካቃታችሁ ከሰዎች ጋር ስትገናኙ ስለ ዲን እውቀት ፥ ስለ ፖለቲካ ወይም ስለ ቴክኖሎጂ ብቻ አውሩ ወይም ስለ ስራ። ግን በዛው ባልደረባችሁን ድንገት ማማት እንዳትጀምሩ¡ እየተጠነቀቅን!😉#anti_backbiting_method_Muslims #hamet_hack

የቀልብ/የልብ በሽታዎች
Anonymous voting