Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና
رفتن به کانال در Telegram
- ኢስላማዊ የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ። - እውነተኛ የህይወት ታሪኮች - ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ። - ሳምንታዊ ሽልማቶች ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ የአይምሮ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ ጥያቄ ለማቅረብ እና አገልግሎት ለማግኘት ሳይኮሎጂስት ኡስማን ሙስጠፋን@usmanoman ላይ ያናግሩ።
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
1 026
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+107 روز
+37430 روز
در حال بارگیری داده...
کانالهای مشابه
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
اکتبر '26اکتبر '26
اکتبر '26
+35
در 7 کانالها
سپتامبر '26
+505
در 10 کانالها
Get PRO
اوت '26
+530
در 11 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 13 اکتبر | +2 | |||
| 12 اکتبر | +7 | |||
| 11 اکتبر | 0 | |||
| 10 اکتبر | +2 | |||
| 09 اکتبر | +5 | |||
| 08 اکتبر | +2 | |||
| 07 اکتبر | +2 | |||
| 06 اکتبر | +7 | |||
| 05 اکتبر | +3 | |||
| 04 اکتبر | +2 | |||
| 03 اکتبر | +2 | |||
| 02 اکتبر | +1 | |||
| 01 اکتبر | 0 |
پستهای کانال
የአጂነብይ ሴት...👀 ሰውነት በማየት ሱስ በጣም ከተቸገርክ
ጀናዛ ሲታጠብ ለማየት ሞክር!
ቀብር መሔድም አዘውትር።
አሁን የምትቋምጥለት ገላ ምን ያህል ጭቃ እና ከንቱ ፣ ፈራሽ
መሆኑ ይገለጥልሀል።
ተፈኩር (ለማስተንተን) ለማድረግ ኒያ አድርገህ ቀብር ሲኖር ለመቅበር ሲቀበርም ለማየት ሒድ። የሴት ገላ የማየት ሱስን አላህ ይቀንስልሀል በኢኽላስህ ልክም አላህ ይፈውስሀል ኢንሻአላህ!
ግን ኢሔ የሚስትህን ሰውነት አይመለከትም ሀቢቢ¡😉😁
#Daily
#Islamic_resolution
#haram_sight_#hack
| 2 | የመጨረሻ ማስታወቂያ
የኢስላሚክ ሳይኮሎጂ (ኢልመ - ነፍስ) ቀላል በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ በጣም ጠቃሚ ትምህርት/'ኮርስ'
-ያለ እድሜ ገደብ ለሁሉም የሚጠቅም ሰዎች ራእያቸውን እንዴት በኢስላማዊ መንገድ መቅረፅ እንዳለባቸው የሚያስገነዝብ።
- መሠረታዊ የኢልመ ነፍስ/ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ እውቀቶችን የሚያስጨብጥ
- ትምህርት ለጨረሱ በሁሉም የእድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች ህይወታቸውን ዳግም እንዲፈትሹ የሚያነሳሳ
የሚሰጡት ትምህርቶች/ስልጠናዎች
- ተሰጥኦን ራስን እና አለምን በመገንዘብ እስከ አኼራ የተዘረጋ ራእይ ስለ መቅረፅ
-የኢስላሚክ ሳይኮሎጂ መሠረታዊያን
(የነፍስ ደረጃዎችን በመረዳት ራስን ከወንጀል መጠበቅ፣ ቀልብ፣አቅል፣ሩህን እንዳስሳለን)
- በጥራት የማሰብ አቅም ማሳደግን እናያለን
አዘጋጅ:- በሳይኮሎጂስት ፀሀፊ እና የኢልመ - ነፍስ ተመራማሪ ኡስማን ሙስጠፋ ለረጅም ጊዜ የተጠናባቸው እውቀቶች።
ምዝገባ: ለማካሄድ @usmanoman ላይ ማናገር ወይም ግሩፑን join በማለት መመዝገብ ይቻላል በቅርቡ ይጀመራል ኢንሻአላህ!
ከታች የተያያዘውን የስልጠና ግሩፕ ጆይን ስትሉ ተጨማሪ የምዝገባ እና ተያያዥ መረጃዎች ይላክላችኋል።
ኢንሻአላህ? ወይም @usmanoman ላይ አናግሩኝ
👇👇👇👇
https://t.me/+0TCu-4pUn005ZDA0 | 381 |
| 3 | “أحسن الحُسن حُسن الأدب” —🫧
''ምርጡ ቁንጅና የፀባይ ውበት
ነው"
❤️ ❤️
❤️ ❤️
🫧Arab proverb
@ISLAMIKA_BORN_MUSLIM789 | 358 |
| 4 | ኢስላማዊ የማንነት መፈተሻ ቅፅ መሙያ ከኢስላሚክ ሳይኮሎጂ / Islamic Personality Assessment
ይህ በብዙ ምርምር የተቀረፀ የአኽላቅ/ስነምግባር እና እምነት መፈተሻ በቀላሉ ሞልተው ሰለራስዎ ብዙ ማወቅ ይቻላሉ።
100 ሰዎችን የመፈተሽ ቻሌንጅ።
ጥቅሞቹ
-ከአላህ ጋር ያለንን ቅርበት ይለካል የራሳችንን ችግር እንድንፈትሽ ይረዳል
- ያለንበትን የስብእና ጥራት ደረጃ ይለካል።
- ከውጤቱ በመነሳት የምክር አገልግሎት ይሰጣል።
- ስለ ራሳችን በደንብ እንድናውቅ ያግዛል።
ፎርሙን ለመሙላት
👇ሰማያዊን ፅሁፍ ይንኩ
ራስን ለማወቅ | 435 |
| 5 | የኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ አባል በመሆን የሚገኙ ጥቅማጥቅሞች
- የኡስማኒክ ሳይኮሎጂ ዲጂታል የአባልነት መታወቂያ ማግኘት
- የሚኖሩ ስልጠናዎችን በቅናሽ ወይም በነፃ ማግኘት
- ካውንስሊንጎችን/ኢስላሚክ የማማከር አገልግቶችን በቀነሰ ዋጋ መጠቀም
- በማዕከሉ የሚሰጡ ኮርሶችን እና ፈተናዎችን በቀነሰ ዋጋ እና በነፃ ተፈትኖ ሰርተፍኬት ማግኘት
- ብዙ ሰዎች የሚታገዙበትን ይህን ኢስላማዊ የስነልቦና ማዕከል በማገዝ የሚገኝ ስነልቦናዊ እርካታ እና አኼራዊ ጥቅም
ለጊዜው ይህ የአባልነት ውል በየ ሁለት ወሩ የሚታደስ ሲሆን አንድ አባል የሆነ ሰው ጊዜው ከማለቁ በፊት ምንም አገልግሎቶቹን ካልተጠቀመ ያልተጠቀማቸውን አገልግሎቶች ሁሌም መጠቀም የሚችል ይሆናል።
"አባል በመሆን አብሮነታችሁን አሳዩን"
ታላቅ ኡማ በመገንባት ጉዟችን ላይ አብራችሁን ሁኑ!
ከላይ ፖሉ ላይ አባል ለመሆን ቃል የገባችሁ ሰዎች እንዲሁም አባል በመሆን አብራችሁን መጓዝ የምትፈልጉ የአባልነት መመዝገቢያ ቅፅ እና ዲጂታል መታወቂያ ስላዘጋጀን @usmanoman ላይ አናግሩኝ።
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች ካሉ አሳውቃለሁ ኢንሻአላህ!
ጀዛኩሙለሁ ኸይረን!! | 1 |
| 6 | ማለዳችሁን በታላቅ ራእይ ሙሉት
اللَّهُمَّ بِكَ أَصْبَحْنَا، وَبِكَ أَمْسَيْنَا، وَبِكَ نَحْيَا، وَبِكَ نَمُوتُ، وَإِلَيْكَ النُّشُورُ
"አላህ በአንተ (ፍቃድ) ወደ ንጋት ገባን ፥ በአንተም አመሸን በአንተም ህያው ሆንን ፥ በአንተም እንሞታለን ወደ አንተም ተመላሾች ነን።
ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ | 413 |
| 7 | እስቲግፋር ማድረግ ከጭንቀት ይገላግላል | 333 |
| 8 | ኢስቲግፋር ማድረግ ከጭንቀት ይገላግላል | 1 |
| 9 | በአላህ መንገድ የተወዳጁ ሰዎች
#ሱህባ
ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ | 329 |
| 10 | https://t.me/usmanic_psychology | 1 |
| 11 | ይህን ቻናል ብዙ ሰው ጋር እንዲዳረስ boost የሚለውን በመንካት አሳድጉት ተጨማሪ አገልግሎቶችን እና ጠቃሚ ነገሮችን እናቀርብላችኋለን። ኢንሻአላህ!
https://t.me/usmanic_psychology?boost | 310 |
| 12 | ጥያቄ 6
"በፀፀት ራሴን እየቀጣው ነው እባክህ መፍትሔ ካለው ከዚህ ስቃይ ታደገኝ"
አሰላሙአለይኩም ወንድሜ በቅድሚያ ጭንቀታችንን የምንገልፅበትንና መፍትሄ የምንፈልግበትን ቦታ/ማዕከል ስላዘጋጀህልን ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ....። ጥያቄዬን እንደሚከተለው አቀርባለሁ።
እኔ የ23 አመት ወጣት ስሆን በጣም በትኩስነት የአፍላ አስራዎቹ እና ሀያ መጀመሪያ እድሜዬ አካባቢ ፥ በቅጡ ሳላገናዝብ የፈፀምኳቸውን ተግባራት ሳስብ በራስ መበሳጨት ፀፀት እና ወቀሳ ይሰማኛል ይህም ልቆጣጣረው የማልችለው ራስን የመጥላት ስሜት ራሴን ለማጥፋት እንስካስብ ድረስ ይወስደኛል።
አንዳንዴም ራሴን በመጥላት በብዙ ነገር ነፍሴን እጎዳለው ምግብ ባለመብላት ፣ ራስን በመጣል እና ለራሴ ጥሩ ነገር ባለማድረግ ...ያኔ ትንሽ ራሴን የቀጣሁት ይመሰለኛል።
አሁን ላይ ተውበት አድርጌ ራሴንም የበደልኳቸውንም ሰዎች ይቅርታ ጠይቄ ነው ምኖረው ግን ከህሊና ቅጣት አሁንም አልዳንኩም። ይህ የፀፀት ስሜት ተወኝ ስል ያገረሽብኛል ረሳሁት ስል ትዝ ይለኛል። በአጠቃላይ ሙሉ እረፍት የለውም ህይወቴ ምን ትመክረኛለህ
ባለፈ መጥፎ ተግባሩ በፀፀት የሚቀጣ ወንድምህ ካለሁበት
አመሠግናለሁ !
(መልሱን በቅርቡ ይጠብቁ ኢንሻአላህ!)
ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ | 329 |
| 13 | በዱአ እናንኳኳ!
ይከፈታል
ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ | 313 |
| 14 | ከመልሶቻችን ማራኪ አንቀፆች
ያለፉ ታሪኮቻችን እና የልጅነት ዘመን ጠባሳዎች አሁን ላለን ስብእና እና ማንነት የራሳቸውን ሚና ሊጫወቱ ቢችሉም የሰው ልጅ ግን ገደብ በሌለው የመለወጥ እና የመታደስ (resiliency) አቅሙ ምክንያት ራሱን መስራት መቀየር እና ከትናንትና ህመሙ በላይ መሆን ይችላል። | 325 |
| 15 | እስካሁን በኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ተጠይቀው ስነልቦናዊ መልስ እና ማብራሪያ የተሰጠባቸው ፖስቶች። የመረጡትን በመንካት ታነቡ ዘንድ ጋበዝኳችሁ!
1, ጥያቄ 1 የ 31 አመት ሴት ስሆን እስካሁን የትዳርን ወግ አላየሁም።
ለ ጥያቄ 1 የተሰጠ መልስ
2, ጥያቄ 2 እኔ የ 27 አመት ወጣት ወንድ ነኝ።በአንድ አሳሳቢ ነገር ተለክፍያለው።
ለጥያቄ 2 መልስ ክፍል 1
ለጥያቄ 2 መልስ ክፍል 2
3, ጥያቄ 3 ቅናት እና ምቀኝነት ፈተነኝ!
የጥያቄ 3 መልስ - ክፍል 1
ለጥያቄ 3 መልስ -ክፍል 2
4, ጥያቄ 4 ትምህርቴን ልማር ወይስ ላቋርጥ?
ለ ጥያቄ 4 የተሰጠ መልስ
5, ጥያቄ 5 "የማልቆጣጠረው ብስጭት ብዙ ነገሬን አመሳቀለ።"
ለ ጥያቄ 5 የተሰጠ መልስ
ጥያቄ ለመላክ ወይም አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ይፃፉልን። | 433 |
| 16 | بدون متن... | 307 |
| 17 | #2 ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ
በትከሻው ይሸከሙኛል ፥ መራመድ አልችልም መስጊዱን የሀዘን ድባብ ሞልቼው እወጣለሁ ፥ ሰዎች ምህረት አገኝ ዘንድ ይለምኑልኛል
እኔ ማን ነኝ?
ከላይ የተጠቀሰውን ጥያቄ ቀድሞ በትክክል ለመለሰ ሳምንታዊ የ 780 ሜ.ባ የኢንተርኔት ፖኬጅ ሽልማት ያገኛል።
#ከኡስማኒክ_ኢስላሚክ_ሳይኮሎጂ | 296 |
| 18 | እውነተኛ ታሪክ…
~
•ነገሩ እንድህ ነው…ከጥቂት ወራት በፊት ኸውለት በነፍሷ ውስጥ ትልቅ ባዶነት ይሰማት ነበር። ወደ ጌታዋ መቅረብ፣ ቁርኣን መቅራትና ዲኗን ማወቅ ተጠማች። በዚህ መሃል ነበር በአንድ የቴሌግራም ግሩፕ ላይ "ኡስታዝ" ተብሎ የሚጠራውንና በጣፋጭ አንደበቱ ቁርኣን የሚቀራውን ያንን ወንድም ያወቀችው። የእሱ የድምፅ ቅላጼና ስለ አላህ ፍቅር የሚናገራቸው ቃላት የኢማኔ መጨመሪያ ይሆናል የሚል ተስፋ በውስጧ አሳደሩ።
መጀመሪያ ላይ «ኡስታዜ ይህን አንቀጽ አብራራልኝ» በሚል ጥያቄ ጀመረች። እሱም በክብር መለሰላት። ቀስ እያለ ግን ጥያቄው ከዲን ወጣና «ዛሬ ውሎሽ እንዴት ነበር?» ወደሚል የግል ትኩረት ተቀየረ። «እንደ አንቺ ያለች ጠንካራ እህት ማግኘት መታደል ነው» የሚሉ የማባበያ ቃላት በዲን ካባ ተጠቅልለው መምጣት ጀመሩ።
ኸውለት ሳታስበው በዚያ ሰው ፍቅር ወደቀች። አሁን ቂርኣኑን የምትከታተለው ለአላህ ብላ ሳይሆን የእሱን ድምፅ ለመስማት ሆነ። ሌሊት ቆማ ስትሰግድ አላህን ከመለመን ይልቅ የኡስታዙ መልዕክት በስልኳ ላይ "Typing..." የሚል ምልክት ማሳያውን በጉጉት መጠበቅ ጀመረች። ሐያእ ቀስ በቀስ ተገፈፈ። በመካከላቸው ያለው ወግ አጎል ቀልድ እና ክልክል የሆኑ የፍቅር ቃላት ወረሩት።
ጊዜው እየገፋ ሲሄድ ግን አንድ እውነት ተገለጠ። ያ "ኡስታዝ" የተባለው ሰው ለኸውለት የነበረው ፍላጎት በዲን ስም ስሜቱን ማርካት እንጂ እሷን ወደ አላህ ማቅረብ አልነበረም። እሷ ግን ልቧን ሰጥታዋለች። በሄደችበት ሁሉ እሱን ታስባለች። የቁርኣኑ ጥፍጥና ጠፋባት። ልቧ ደረቀ። ሶላቷ ላይ ትኩረት አጣች። የነፍሷ ሰላም ተናወጠ።
በመጨረሻም ያ የጠበቀችው ትዳር ሳይሆን መገለል ሆነ። ኡስታዝ ተብዮው ካለበት ቻናል እና ግሩፕ ጠቅላላ ወጣች። ያ ኡስታዝ ሌላ አዲስ ተማሪ አገኘና እሷን እንደ አሮጌ እቃ ወረወራት። ኸውለት ዛሬ ብቸኛ ናት።
በአንድ ወቅት ወደ አላህ ያቀርበኛል ብላ ያሰበችው ሰው፣ ዛሬ ከጌታዋ ያራቃት ትልቁ ሰበብ ሆነ። እንባዋ አይደርቅም፤ አበጃለሁ ባይ አጥፊ ገጠማት።ኸውለት ግን ከበፊቱ አሁን ላይ በ ኢማኗ በጣም ጥሩ ላይ ነች።ጠንክራለች። ቁርኣንም መሐፍዝ ጀምራ 15 ጁዝ ላይ ደርሳለች። ኸውለት… ታሪኳን እዚህ ላይ ላቁመው።
ልብሽን ጠብቂ፤ እሱ የአላህ ቤት ነውና!
©️/መንቁል | 332 |
| 19 | እውነተኛ ታሪክ…

©️/መንቁል | 1 |
| 20 | "ፊታቸው በፈገግታ የተሞሸረ ለተመለከታቸው በሙሉ ደስታን የሚያጋባ የሀሴት ድግስ ነው። በትህትና የተቀመረ የማማር አክሊልል ደፍተዋል ፣ በነቢይነት ስክነት ሞገስ እና በሰውነት ጨዋ ማንነት ገፃቸው የረጋ ነው...።"
መሰል ውብ አንቀፆችን ስለ ውዱ (ﷺ) ነብይ የሚያገኙበትን 'ፍፁም ነብይ ፍፁም ሰው' መፅሐፍ በመግዛት ከመልእክተኛው ጋር በጥልቀት እና በውበት ይተዋወቁ።
ርእስ= ፍፁም ሰው ፍፁም ነብይ
ፀሀፊ = ኡስማን ሙስጠፋ
የህትመት ጊዜ= ነሀሴ 2015 ዓ.ል
መፅሐፉን ለማግኘት በቴሌግራም ዩዘርኔም @usmanoman ወይም በስልክ 0921390122/ 0912027023 ላይ ያናግሩን | 331 |