ch
Feedback
Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና

Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና

前往频道在 Telegram

- እውነተኛ የህይወት ታሪኮች - ኢስላማዊ የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ። - ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ። - ሳምንታዊ ሽልማቶች ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ የአይምሮ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ ጥያቄ ለማቅረብ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን።

显示更多
未指定国家未指定类别
802
订阅者
+3124 小时
+1807 天
+39230 天
帖子存档
አሁን ያሉበት ሁኔታ ? (status)
Anonymous voting

የሰው ልጅ ህይወት በብዙ የደሰታ እና የሀዘን ትዕይንት የተሞላ እስከ ሞት የተዘረጋ የእንቆቅልሽ መስመር ነው። ይህም የህይወት ታሪክ እህታችን ከዲያሪዋ (ከማስታወሻ ደብተሯ) ላይ የተወሰኑ መስመሮችን
+1
የሰው ልጅ ህይወት በብዙ የደሰታ እና የሀዘን ትዕይንት የተሞላ እስከ ሞት የተዘረጋ የእንቆቅልሽ መስመር ነው። ይህም የህይወት ታሪክ እህታችን ከዲያሪዋ (ከማስታወሻ ደብተሯ) ላይ የተወሰኑ መስመሮችን ከላከችልን የተወሰደ እና ለሰው እንዲጋራ የፈቀደችው ነው።

በተውበት/በንስሀ ውሀ ታጥበን ፣ በኢስቲግፋር ብርሀን የወንጀላችንን ትብታብ በጣጥሰን ፣ በአዝካር ጌጥ ደምቀን በሰለዋት ቁልፍ የህይወታችንን በር እንከፍታለን።

አሁን ምን እየተሰማችሁ ነው? What do u feel now?
Anonymous voting

የሳምንታዊ የኢንተርኔት ጥቅል ተሻለሚ 🏅🏆 - ሀያት በድሩ - ከ አዲስ አበባ - ቀድማ በመመለስ የሽልማቱ አሸናፊ መሆን ችላለች። ሁላችሁም ስለተሳተፋችሁ ከልብ እናመሠግናለን። ቀጣዩን ለማሸነፍ ዝ
የሳምንታዊ የኢንተርኔት ጥቅል ተሻለሚ 🏅🏆 - ሀያት በድሩ - ከ አዲስ አበባ - ቀድማ በመመለስ የሽልማቱ አሸናፊ መሆን ችላለች። ሁላችሁም ስለተሳተፋችሁ ከልብ እናመሠግናለን። ቀጣዩን ለማሸነፍ ዝግጁ ይሁኑ።

#1 ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ ደስታ ብለን ሀዘን ካልን ድህነት ብለን A.ብልፅግና B.ሀብት C.መትረፍረፍ የ 780 ሜ.ባ የኢንተርኔት ፖኬጅ ሽልማት የሚከተለውን ጥያቄ ቀድሞ ለመለሰ #ከኡስማኒክ_ኢስ
#1 ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ ደስታ ብለን ሀዘን ካልን ድህነት ብለን A.ብልፅግና B.ሀብት C.መትረፍረፍ የ 780 ሜ.ባ የኢንተርኔት ፖኬጅ ሽልማት የሚከተለውን ጥያቄ ቀድሞ ለመለሰ #ከኡስማኒክ_ኢስላሚክ_ሳይኮሎጂ

ከየት ናችሁ?
Anonymous voting

The final test of freedom is this: can u remain the same person praise, in insult, in gain, and in loss "ታላቁ የነፃነት ፈተና በአድናቆት በመሰደብ በማጣት ፣ በማግኘት እና በማጣት አንተ ያው መሆን ትችላለህ ወይ? የሚለው ነው።"

አገጋሚነት/ Resiliency "በመከራዎች ሰርጥ ውስጥ አልፈዋል። ጥልቅ ህመም እና መከራ በሳቸው ላይ ተነባብሮ ሄዷል።  ፈተና ረሀብ እና ተቀባይነትን ማጣት መገፋት እና ውድቀት ለሳቸው የነገ ሻማቸውን የሚለኩሱበት የማገገም ሀይላቸው እንጂ ተሽመድምደው የሚወድቁበት ጋሬጣቸው አይደለም። ጠንክረው አገግመው ይነሳሉ መውደቃቸው የሚበረቱበት ፅናት ነው ትግላቸው ዳግም ህያው የሚያደርጋቸው ብርሀን ነው። በመሰበራቸው ባህር ውስጥ የፅናታቸውን መርከብ ሰርተዋል። በመውደቃቸው ረጅም መንገድ የማይፈርስን ድልድይ ገንብተዋል" (ገፅ 32 'ፍፁም ሰው ፍፁም ነቢይ' መፅሀፍ ከ ነቢዩ ስነ ባህሪያት የተወሰደ (ፀሀፊ ኡስማን ሙስጠፋ ) ይህ የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስነልቦናዊ የፅናት ተምሳሌትነት ነው። እኛም ጥንካሬን ከሳቸው እንማር ወድቆ መነሳትን ተሰብሮ መጠገንን ከአርአያችን እንቅሰም።

የህይወት እይታ ጥራት (clarity) ሲጎድለን ፤ ያስተካክለዋል
Anonymous voting

የህይወታችን እይታ ጥራት (clarity) ሲጎድለን ለማጥራት ___?
Anonymous voting

የጥያቄ ሶስት መልስ ክፍል 1 በጎ ስራዎችን በልቶ የሚጨርሰው ;የልብ በሽታ' ምቀኝነት/ሀሰድ - (حسد/envy) -: ኢስላማዊ ፍቺው የተመቀኘነው ሰው ያገኘው ፀጋ እንዲወገድ መመኘት ማለት ነው። ሀሰድ/ምቀኝነት ወይም መጥፎ ቅናት ብዙ ሰው የሚፈተንበት የቀልብ/የልብ ህመም አይነት ነው። ነፍሳችን የታችኛው ደረጃ ላይ ሆና (ነፍሱል - አማራ-) መጥፎ ሀሳቦችን ሳታቋርጥ በምታመነጭበት እርከን ላይ የውስጥ መጥፎ (ውስዋስ) ጉትጎታ እና ደመነፍሳዊ ራስን ያለ ቅጥ የመውደድ ሁሉንም ለራስ ብቻ የመከጀል የተዛባ ውስጣዊ ባህሪ ነው። ጤናማ ቅናት (Benign Envy):- በሀብት እና በእውቀት ከኛ የተሻለ ሰው ጋር ለመድረስ የሚደረግ ጤናማ ውድድር ልኩን እስካላለፈ ድረስ ለእድገት ይጠቅማል። በሁለት የሰው አይነትም መቅናት እንደሚቻል ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ነግረውናል። እሱም አላህ ሀብት ሰጥቶት በልኩ በሚለግስ ሰው እና እወቀት ተሰጥቶት በስርአት በሚሰራበት ሰው ነው። ይህ ይቅናት አይነትም ለበጎ ምግባር የሚያነሳሳ ነው። የቅናታችን ደረጃ ልኩን አልፎ ተንኮልን ሲይዝ ወይም የሌላውን ሰው የፀጋ መወገድ ልባችን ሲከጅል አሁን ስሜታችን ከጤነኛ የቅናት ደረጃ ወደ ምቀኝነት ተሸጋግሯል። ምቀኝነት ሌላው ትርጉሙ አላህ ለሌላ ሰው የመደበው ፀጋ ለሱ አይገባውም ማለት ስለሆነ ከአላህ ውሳኔ/ቀደር ጋር ያላትማል። ስለዚህ ሂስድ- ተውበት/ንስሐ የሚፈልግ ድብቅ ውስጣዊ የወንጀል አይነት ነው። ነቢዩ ሙሀመድም (ሰ.ዐ.ወ) ከዚህ ነገር ሲያስጠነቅቁ እንዲህ ብለዋል – "ምቀኝነትን ተጠንቀቁ እሳት ነገራትን አቃጥሎ እንደሚጨርሰው ምቀኝነትም መልካም ስራን ይበላል"።ብለዋል (አቡዳውድ) (ይህ ስለ ነገሩ አሳሳቢነት ጥያቄውን እንደመነሻ በመጠቀም የቀረበ የክፍል 1 ማስታወሻ ሲሆን ለእህታችን ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ በክፍል 2 ምላሽ ላይ ይሰጣል) ኢንሻአላህ ✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ። ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን።

ሀሰድ/ምቀኝነት ወይም መጥፎ ቅናት ብዙ ሰው የሚፈተንበት የቀልብ ህመም አይነት ነው። ነፍሳችን የታችኛው ደረጃ ላይ ሆና መጥፎ ሀሳቦችን እና ተግባሮችን ሳታቋርጥ በምታመነጭበት እርከን ላይ

የታመመ ልብ __ይፈወሳል
Anonymous voting

'ብቸኝነት' ማለት ምን አልባት ሁልጊዜ ብቻህን መሆን ማለት ላይሆን ይችላል ብቸኝነት በሰዎች ተከበህ ማንም ውስጥህን እንዳልተረዳው ሲሰማህ ነው። ብዙ ጊዜ እኛ ግንኙነትን በመልእክት ቅይይሮች ፣ በተከታይ ብዛት እና በውይይቶች እንለካ ይሆናል ግን 'መገናኘት' እና 'ግንኙነት' የተለያዩ ነገሮች ናቸው ። anonymous ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ

ሩህ/መንፈስ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ قُلْ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي ۖ وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا ስለ ሩ
ሩህ/መንፈስ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ قُلْ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي ۖ وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا ስለ ሩህ (መንፈስ) ይጠይቁሀል። "ሩህ (መንፈስ) ከጌታዬ ነገር ነው ከእውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም" በላቸው ቁርአን ምዕራፍ 17 አንቀፅ 85 ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ

4.ከድህነት እና የሰውን እጅ ከማየት ለመጠበቅ የሚባል ዱአ      ▪ اللّهُمَّ أَغْنِنِي بِفَضْلِكَ عَمَّن سِوَاكَ አላሁመ አግኒኒ ቢፈድሊከ አመን ሲዋክ "አላህ ሆይ ከአንተ ውጪ ከሆነ አካል ከጃይ/ፈላጊ እንዳልሆን በፀጋህ አብቃቃኝ" የዚህ ዱአ ስነልቦናዊ እና መንፈሳዊ ጠቀሜታዎች - ከአላህ ውጪ ካሉ አካላት ከጃይ ከመሆን እንጠበቃለን - አላህ የፀጋዎቹን በሮች ይከፍትልናል - ባለን ነገር የመብቃቃትን ትሩፋት እናገኛለን