ar
Feedback
Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና

Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና

الذهاب إلى القناة على Telegram

- እውነተኛ የህይወት ታሪኮች - ኢስላማዊ የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ። - ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ። - ሳምንታዊ ሽልማቶች ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ የአይምሮ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ ጥያቄ ለማቅረብ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
934
المشتركون
+2224 ساعات
+2867 أيام
+53530 أيام
أرشيف المشاركات
ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ/ኢልመ- ነፍስ ክፍል 4. አቅል -ፊጥራ -ነፍስ -ሩህ -አቅል/አይምሮ -ቀልብ/ልብ -ተዝኪየቱ ነፍስ/ራስን ከወንጀል ማፅዳት ለዛሬ አቅልን በጣም በአጭሩ እናያለን ኢንሸአላህ! አቅል ምንድነው? የአቅል (عقل) (mind) ስርወ - ቃል መሠረተ ትርጉም መገንዘብ ፣ መረዳት ፣ ማወቅ የሚል ትርጉም አለው። ይህ የሰው ልጅ በምክንያት/አምክንዮ የሚያስብበት ክፍል ሲሆን ፥ እውነትን ከውሸት የሚለይበት ፍጥረተ አለሙ የሚረዳበት እና የሚገነዘብበት የማስተዋያ ክፍሉ ነው። አቅል እስካሁን ካየናቸው የሰው ልጅ መሰረታዊ የማንነት ክፍሎች አንዱ ሲሆን ስለራሱ ስለሰዎች እና ስለፈጣሪው በትክክል እና በጥራት እንዲያስብ የሚያደረገው መሣሪያ ነዉ አቅል በኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ጥናት ውስጥ በኢስላሚክ/በኡስማኒክ ሳይኮሎጂ ውስጥ አቅል መስታወት ሆኖ ሰው አለምን የሚያይበት የመመልከቻ መነፅሩ ነወ። በተለያዩ ምክንያቶች የእውነት እና የፍትህ ሚዛኑ የተዛባ አይምሮን እና በሀቅ ላይ ቆሞ በጥራት ህይወትን መገንዘብ ያቃተውን አይምሮ በማገዝ የሰዎችን የማመዛዘን ተፈጥሯዊ ማንነት የማስመለስ ህክምናዊ እና ስነዘዴያዊ መንገዶችን ይከተላል። ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ መፅሀፍ አዘጋጅ እና ፀሀፊ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂስት ኡስማን ሙስጠፋ) ኢንሻአላህ ይቀጥላል...

Ai እና Gemini መጠቀም ከውድድሩ ያሰርዛል። ወይም ሽልማቱን ለ Ai እንሰጠዋለን 😆

#2 ሽልማት የሚያስገኝ ሀሳብን በፅሁፍ የመግለፅ ውድድር ርእስ እና የመወዳደሪያ መንገድ :- ምድር ላይ የሰው ልጅ ስለሚያጋጥመው ፈተና እና ተስፋ ከ 4-7 መስመር ባልበለጠ በጥሩ አገላለጽ እና ሳቢ
#2 ሽልማት የሚያስገኝ ሀሳብን በፅሁፍ የመግለፅ ውድድር ርእስ እና የመወዳደሪያ መንገድ :- ምድር ላይ የሰው ልጅ ስለሚያጋጥመው ፈተና እና ተስፋ ከ 4-7 መስመር ባልበለጠ በጥሩ አገላለጽ እና ሳቢ የአፃፃፍ ስልት ኮሜንት መስጫው ላይ በማስቀመጥ ተወዳደሩ! አሪፉ ፅሁፍ ታይቶ አሸናፊው ሽልማቱን ይወስዳል።ኢንሻአላህ! ሽልማቱ:- የ ፍፁም ሰው ፍፁም ነብይ መፅሀፍ እና የሳምንታዊ 780 ሜ.ባ የኢንተርኔት ፖኬጅ #ከኡስማኒክ_ኢስላሚክ_ሳይኮሎጂ መልካም እድል!

ጥያቄ 3 ልማር ወይስ ላቁም? እኔ የ18 ወጣት ስሆን ቀጣይ አመት የ 12ተኛ ክፍል ተፈታች ነኝ። ትምህርት የሚሆንልት አይነት ሰው ብሆንም ታላላቆቼ ተምረው ያሰቡትን ማሳካት አለመቻላቸውን ሳይ እና 'ትምህርት አያሳልፍልህም አርፈህ ተፍ ተፍ በል' የሚሉ መሰል ተደጋጋሚ ምክሮችን ስሰማ ተስፋ ስለቆረጥኩኝ። የ ቀጣይ አመት የ12ተኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ወስጄ የትምህርት አለምን ልሰናበት ወይ? በሚል ጥያቄ ራሴን እያፋጠጥኩኝ አለው። እባክህን ለኔ እና ለመሰል ጓደኞቼ በትምህርት ጉዳይ ያለህን አቋም ብታሳውቀን። አመሠግናለሁ። (መልስ እሰኪሰጥ ድረስ አስተያየታችሁን ታች አሰፍሩ)

-ናፍቆት' ወዳለፈው ዘመን የሚጎትት የኋሊት ሀዲድ ነው። በትዝታ ተሳፍረን ትናንትናችንን ልንጎበኝ የምንሄድበት የምልሰት ኑሮ። የናፍቆት ወላፈን በልጅነታችን ካለፍንባቸው መንገዶች ፣ ከወላጆቻችን አልባሳት ፣ ቤታችን ውስጥ ከቆመችው የዛፍ ጥላ ፣ ከእህት ወንድሞቻችን ድምፅ እየተነሳ ወደ ህሊናችን ይተናል። ናፍቆት የሰው ልጆች የማያመልጡት ያለፈ ታሪካቸው ዶሴ ላይ የተፃፈ ሰቀቀን ፣ የትካዜ ሀገራቸው መሠደጃ ነው።

"መነገር ያለበት ሁሉ አስቀድሞ ተነግሯል። ግን ማንም ሰው ስለማያዳምጥ፣ ሁሉም ነገር እንደገና መነገር አለበት።" - copy

ሂስድ/ምቀኝነት መንስኤዎች እና መዳኛዎቹ መልስ/ ክፍል ሁለት (የማጠቃለያ መልስ) የሰው ልጅ ትልቁ ፈተናው በነፍሱ ጉትጎታ ወንጀል ለመስራት ሲፈተን ባለው ትግል ውስጥ ነው።ይህን ሀሳብም ይበልጥ ግልፅ የሚያደርግ ዘውትር የምንሰማው ወይም የምንለው ግን ትርጉሙን ብዙም ያላስተዋልነው ታላቅ ዱአ አለ። أعوذ بالله من شرور أنفسنا ومن سيئات أعمالنا ትርጉሙም 'ከነፍሳችን ሸር እና ከመጥፎ ስራችን ውጤት ወይም ህይወታችን ላይ ከሚያስከትለው ተፅእኖ በአላህ እንጠብቃለን' ማለት ነው። የሰው ልጅ ትልቁ ጀሀዱ/ትግሉ ከሌሎች ጋር አይደለም። ከውስጣዊ መሻቱ እና ከተፈጥሮው መጥፎ ዝንባሌ ጋር የሚያደርገው እንጂ። ሰው በብስጭት ፣ በዝሙት በስርቆት እና በብዙ እኩይ የተግባር ዝንባሌዎች እንደሚፈተነው ሁላ በምቀኝነት/ሌሎችን በመመቅኘት ሊፈተን ይችላል። እህቴም ያጋጠማት ተመሳሳይ የችግር አይነት ነው።ይህ በሽታም ነፍስን ሳያቋርጡ በመፈተሽ ፣ በማፅዳት ፣ እና በመመርመር ወደ አላህ በተውበት በመመላለስ የሚድን የልብ ህመም ነው። እህቴ አንቺ የተፈተነሽበት ጉዳይ የአለምን ህዝብ እና የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ኡማ እየተገዳደረ ያለ የብዙ ቤተሰቦችን ህብረት የበጠሰ ለበርካታ ወንጀሎች መንስኤ በሆነው ነገር ነው። እህት እህቷን በመመቀኝነት ምክንያት ጎድታለች ፣ እናት እና ልጅ በዚህ ምክንያት ተቆራርጠዋል ፣ ልጅ አባቱን ገድሎ ወደ ዘላለማዊ የህሊና ወህኒ እና ለምድር እስር ቤት ተዳርጓል ፣ ወንድም ወንድሙ ላይ ተነስቷል ጓደኛማችነት ፈርሷል። የብዙ ሲህር የማድረግ መሠረታዊ መንስኤ ከስሩ ያልታከመ ምቀኝነት እንጂ ሌላ አይደለም። ቅናት የወለደው መጠላለፍ የሰው ልጆች የተተበተቡበት የፅልመት ድር ነው። እንዳንቺ የነፍሱን እኩይ ባህሪ ለይቶ እና አውቆ ፣አምኖ የሚፀፀት ሰው ጥቂት ነው። ይልቅስ ራሱን በማፅደቅ እና ነፍሱን ከእንከን የጠራች አድርጎ የሌሎችን ጎዶሎ ለማየት ሁሉም በሚጥርበት አለም ያንቺ ራስን የመፈተሽ አቅም እና እንከንን ለራስ ሳያደሉ ከነፍስያ መንቀስ መቻል ትልቅ የሚደነቅ ባህሪ ስለሆነ ቀጥይበት ለማለት እወዳለሁ። ለዛሬ ግን ለብዙ ቀናት ያንከባለልነውን ጥያቄ መፍትሔዎቹ ያልናቸውን የተወሰኑ ነጥቦች በመጥቀስ እናጠቃልላለን። 1ኛ, ይህ ስሜት ሲሰማሽ 'አኡዙቢላሂ ሚነሸይጧን ረጂም' (ከሰይጣን ተንኮል በአላህ እጠበቃለው) በማለት እኩይ የሆነውን የሰይጣን አላማ ቶሎ አክሽፊበት 2ኛ, እኛን ሊያስቀናን የሚችል ፀጋን ሰዎች ዘንድ ስናይ 'ማሻአላህ' ወይም 'ተባረከላህ' ማለት መርሳት የለብንም አላህ የተባረከ እና ብሩክ ነገሮችም በሙሉ ከሱ መገኘታቸውን እውቅና መስጠት እና የፀጋውን ምንጭ ወደሱ በመመለስ አስገኚውን ማክበር በማድነቅ እና በማመስገን ልብን በአላህ ውሳኔ ማረጋጋት ያስችላል ። 3ተኛ, ምንም ነገር ላንቺ ተፅፎልሽ የቀረ ወይም የሚቀር አለመኖሩን አስታውሺ በቀደር ያለሽን እምነት አዳብሪ። 4ተኛ, የዚችን አለም ማጣት እና ማግኘትም ፈተና ብቻ እንደሆኑ አውቀሽ የተመኘሽው ፀጋ ወዳንቺ ቢመጣ ምንአልባት ከአላህ ጎዳና የሚያርቅ እና ለሁለት አለም ኪሳራ ሊዳርግ በሚችል ፊትና ልትወድቂ ስለምትችይ አላህ ጠብቆሽ ሊሆን እንደሚችል በማስታወስ አላህን ማመስገን እና ውሳኔውን መውደድን ልመጂ። 5,ካንቺ በታች ያሉትን ሰዎች አስታውሺ። አንቺ ያለሽን ነገር ዘወትር እንዲያገኙ አላህን በሚማፀኑ ሰዎች እና አንቺ ያገኘሽውን ፀጋ ላንዳፍታ ቢያገኙ ትልቁ ህልማቸው እንደተሳካ በሚያልሙ ሚሊዮን የአለም ህዝቦች ጎን እራስሽን አስተያዪ። 6, ይህን ስሜት እንዲያጠፋልሽ አላህን በመጠየቅ በዱአ በርቺ። 7,የጠዋት እና የማታ አዝካሮችን አዘውትሪ። በተለይ ከሸር እና በሂስድ የሚታደጉትን ሁለቱን አያ አዘውትሪ :- ቁል አኡዙ ቢረቢናስ እና ቁልአኡዙ ቢረቢል ፈለቅ ✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ። ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን

ከህመም እረፍት በኋላ በምን እንጀምር ? (ከ8 ሰአት በኋላ የምርጫ ፖሉ ይዘጋል)
Anonymous voting

ተጨንቃችሁ ለደወላችሁልኝ ለፃፋችሁልኝም እንዲሁም በድብቅ ዱአቹህ ላሰባችሁኝ በሙሉ በአላህ ስም ከልብ አመሠግናለሁ። አሁን በተሻለ የጤንነት ደረጃ ላይ ስልምገኝ ጉዟችንን እንቀጥላለን።ኢንሻአላህ

"በታመመኩኝ ጊዜ እሱ ይፈውሰኛል!" እኔ የናንተ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂስት ከብዙ በጤና መንቀባረር እና መንደላቀቅ በኋላ ከህመም እንቅፋት ጠጠሯ አደናቀፈችኝ! 🥹😭 አልሃምዱሊላህ! 🙏 እመለሳለሁ! እስከዛው በዱአቹህ አትርሱኝ ሰላሙላሂ አለይኩም! ✨

አሁን ያሉበት ሁኔታ ? (status)
Anonymous voting

የሰው ልጅ ህይወት በብዙ የደሰታ እና የሀዘን ትዕይንት የተሞላ እስከ ሞት የተዘረጋ የእንቆቅልሽ መስመር ነው። ይህም የህይወት ታሪክ እህታችን ከዲያሪዋ (ከማስታወሻ ደብተሯ) ላይ የተወሰኑ መስመሮችን
+1
የሰው ልጅ ህይወት በብዙ የደሰታ እና የሀዘን ትዕይንት የተሞላ እስከ ሞት የተዘረጋ የእንቆቅልሽ መስመር ነው። ይህም የህይወት ታሪክ እህታችን ከዲያሪዋ (ከማስታወሻ ደብተሯ) ላይ የተወሰኑ መስመሮችን ከላከችልን የተወሰደ እና ለሰው እንዲጋራ የፈቀደችው ነው።

በተውበት/በንስሀ ውሀ ታጥበን ፣ በኢስቲግፋር ብርሀን የወንጀላችንን ትብታብ በጣጥሰን ፣ በአዝካር ጌጥ ደምቀን በሰለዋት ቁልፍ የህይወታችንን በር እንከፍታለን።

አሁን ምን እየተሰማችሁ ነው? What do u feel now?
Anonymous voting

የሳምንታዊ የኢንተርኔት ጥቅል ተሻለሚ 🏅🏆 - ሀያት በድሩ - ከ አዲስ አበባ - ቀድማ በመመለስ የሽልማቱ አሸናፊ መሆን ችላለች። ሁላችሁም ስለተሳተፋችሁ ከልብ እናመሠግናለን። ቀጣዩን ለማሸነፍ ዝ
የሳምንታዊ የኢንተርኔት ጥቅል ተሻለሚ 🏅🏆 - ሀያት በድሩ - ከ አዲስ አበባ - ቀድማ በመመለስ የሽልማቱ አሸናፊ መሆን ችላለች። ሁላችሁም ስለተሳተፋችሁ ከልብ እናመሠግናለን። ቀጣዩን ለማሸነፍ ዝግጁ ይሁኑ።

#1 ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ ደስታ ብለን ሀዘን ካልን ድህነት ብለን A.ብልፅግና B.ሀብት C.መትረፍረፍ የ 780 ሜ.ባ የኢንተርኔት ፖኬጅ ሽልማት የሚከተለውን ጥያቄ ቀድሞ ለመለሰ #ከኡስማኒክ_ኢስ
#1 ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ ደስታ ብለን ሀዘን ካልን ድህነት ብለን A.ብልፅግና B.ሀብት C.መትረፍረፍ የ 780 ሜ.ባ የኢንተርኔት ፖኬጅ ሽልማት የሚከተለውን ጥያቄ ቀድሞ ለመለሰ #ከኡስማኒክ_ኢስላሚክ_ሳይኮሎጂ

ከየት ናችሁ?
Anonymous voting

The final test of freedom is this: can u remain the same person praise, in insult, in gain, and in loss "ታላቁ የነፃነት ፈተና በአድናቆት በመሰደብ በማጣት ፣ በማግኘት እና በማጣት አንተ ያው መሆን ትችላለህ ወይ? የሚለው ነው።"