fa
Feedback
هداية القلوب (የልቦች መሪ)

هداية القلوب (የልቦች መሪ)

رفتن به کانال در Telegram

https://t.me/httpYelbochMeriQuran

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
228
مشترکین
+124 ساعت
+217 روز
+1530 روز
آرشیو پست ها
አላህን መፍራት 🎙በሸይኽ ሙሐመድ ወሌ( ረሒመሁላህ) t.me/Sle_qelbachn1

⚠️በመንሐጅ ላይ መቀያየር ሰበቦቹና አደጋው። 🎙በአቡ ሂበቲላህ ሑሰይን ኢስማኢል t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

ሙሓደራ ቁጥር 241 ክፍል 5 ርዕስ= ረድ በ ሙስጠፋ አብደላህ ላይ "መስዓለቱል ዑዝር ቢል ጀሕል'' 🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሓቲም) https://t.me/UstazKedirAhmed

🍃 ብልህ ሴት መቸ መናገር እንዳለባት የት መናገር እንዳለባት እና እንዴት መናገር እንዳለባት ጠንቅቃ ታውቃለች 🌸 ዝም ብላ በየ ቦታው አትገኝም ድብቅ ስትር ናት በየሚድያው ክክ ሀሀ እያለች ማንነ
🍃 ብልህ ሴት መቸ መናገር እንዳለባት የት መናገር እንዳለባት እና እንዴት መናገር እንዳለባት ጠንቅቃ ታውቃለች 🌸 ዝም ብላ በየ ቦታው አትገኝም ድብቅ ስትር ናት በየሚድያው ክክ ሀሀ እያለች ማንነቷን አታስገመግምም 🌸 የት መሳቅ እንዳለባት ታውቃለች የት መዋብ እንዳለባት ታውቃለች ፍቅሯን ለማን መግለፅ እንዳለባት እንዴት መግለፅ እንዳለባት ታውቃለች በጥቅሉ ብልህ ሴት ከመስራቷ በፊት አስተዋይ ናት ════•••🌺🍃•••═══ t.me/qdemiy_letwuhide

ጥያቄዎችና መልሶቻችሁ ናቸዉ 🎙በኡስታዝ አወል አሕመድ
ከልብ ሆናችሁ አዳምጡ
!!

በኡስታዝ አቡ ረያን
ርዕስ ተክፊርን በተመለከተ

ስለ ጀርህ ወታዕድል የተዳሰሰበት
🎙በኡስታዝ አቡ ሻኪራ

አጠር ያለች ምክር
🎙 በወንድም ሙሀመድ አያሌዉ

አጠር ያለ ምክር
🎙በሸይኽ ሙሀመድ ሑሰይን

ስለ ለተምዮች
በኡስታዝ አወል አህመድ https://t.me/httpYelbochMeriQuran

የማለዳ መልእክት (41) ~ የብዙ ፈተናዎችና ብጥብጦች ሰበብ ሶብር ማጣት ነው። በሚገጥሟቸው ፈተናዎች ተበሳጭተው ወደ ሃይልና ብጥብጥ በመግባታቸው የተነሳ ስንቶች ህይወታቸውን አጥተዋል?! ስንቶች አካላቸው ጎድሏል?! ስንቶች ንብረታቸው ወድሟል?! ስንቶች ለረጅም የወህኒ ቆይታ ተዳርገዋል?! ስንቶች ቤተሰቦቻቸውን አጥተው የቁጭት እሳት እየለበለባቸው ነው?! ስንቶች አገራቸውን ጭምር አጥተዋል?! ስንቶች መስጂዳቸውን፣ ደዕዋቸውን፣ ዲናቸውን አጥተዋል?! በሶብር ማጣት ስንቶች ትዳራቸውን አጥተዋል?! ስንቶች የተሻለ ስራቸውን አጥተዋል?! ሶብር ማጣት ብዙ ነገር ነው የሚያሳጣው። ብዙዎች ከሶብር የሚርቁት ወደ ዓላማቸው ለመድረስ ካላቸው ጉጉትና ችኮላ የተነሳ ነው። ነገር ግን የሚዘነጉት ነገር ሶብር በራሱ ወደ ዓላማ መቃረቢያ ሁነኛ መንገድ መሆኑን ነው። በሶብራቸው ደካሞች ካለሙበት ደርሰዋል። አላህ እንዲህ ይላል፦ { وَأَوۡرَثۡنَا ٱلۡقَوۡمَ ٱلَّذِینَ كَانُوا۟ یُسۡتَضۡعَفُونَ مَشَـٰرِقَ ٱلۡأَرۡضِ وَمَغَـٰرِبَهَا ٱلَّتِی بَـٰرَكۡنَا فِیهَاۖ وَتَمَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ ٱلۡحُسۡنَىٰ عَلَىٰ بَنِیۤ إِسۡرَ ٰ⁠ۤءِیلَ بِمَا صَبَرُوا۟ۖ وَدَمَّرۡنَا مَا كَانَ یَصۡنَعُ فِرۡعَوۡنُ وَقَوۡمُهُۥ وَمَا كَانُوا۟ یَعۡرِشُونَ } "እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች ያችን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምሥራቆቿንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው። የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስ ^ራኤል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች። ፈርዖንና ሰዎቹም ይሠሩት የነበረውን (ሕንጻ) ዳስ ያደርጉትም የነበረውን አፈረስን።" [አልአዕራፍ፡ 137] ፈተና ሲገጥመን ሶብር ላይ፣ ዱዓእ ላይ፣ ጥረት ላይ መበርታት ይገባል። ያኔ ፈተናው በአላህ ፈቃድ ይገፈፋል። ኸባብ ብኑል አረት ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦ شَكَونا إلى رَسولِ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم وهو مُتَوسِّدٌ بُردةً له في ظِلِّ الكَعبةِ، فقُلنا: ألا تَستَنصِرُ لنا، ألا تَدعو لَنا؟ فقال: قد كان مَن قَبلَكُم يُؤخَذُ الرَّجُلُ فيُحفَرُ له في الأرضِ، فيُجعَلُ فيها، فيُجاءُ بالمِنشارِ فيوضَعُ على رَأسِه فيُجعَلُ نِصفَينِ، ويُمشَطُ بأمشاطِ الحَديدِ ما دونَ لَحمِه وعَظمِه، فما يَصُدُّه ذلك عن دينِه، واللهِ لَيَتِمَّنَّ هذا الأمرُ، حتَّى يَسيرَ الرَّاكِبُ مِن صَنعاءَ إلى حَضرَمَوتَ، لا يَخافُ إلَّا اللهَ، والذِّئبَ على غَنَمِه، ولَكِنَّكُم تَستَعجِلونَ. "የአላህ መልእክተኛ ﷺ በከዕባ ጥላ ስር ኩታቸውን ተንተርሰው ሳሉ ስለሚደረስብን መከራ አቤቱታ አቀረብንላቸው፤ ‘እርዳታን አትለምንልንምን? ዱዓእ አታደርግልንምን?’ አልናቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ። ‘ከእናንተ በፊት በነበሩት ህዝቦች ዘንድ አንድ ሰው ተይዞ መሬት ይቆፈርለትና በውስጧ ይገባ ነበር፤ ከዚያም መጋዝ መጥቶ በራሱ ላይ ይደረግና ለሁለት ይከፈል ነበር። በብረት ማበጠሪያዎችም ሥጋው ከአጥንቱ ይበጠር ነበር። ይህ ሁሉ ግን ከሃይማኖቱ አይመልሰውም ነበር። በአላህ እምላለሁ! ይህ ጉዳይ (እስልምና) ሙሉ ይሆናል! ተጓዥ ከሰንዓ ተነስቶ እስከ ሐድረመውት ድረስ፣ ከአላህና በበጎቹ ላይ ከሚመጣ ተኩላ በስተቀር ምንም የሚያፈራው ነገር ሳይኖር የሚጓዝበት ጊዜ ይመጣል። ነገር ግን እናንተ #ትቸኩላላችሁ።’ " [አልቡኻሪይ፡ 6943] አስተውሉ! ያ ሁሉ የመከራ ዶፍ እየወረደባቸው ስሞታ ቢያሰሙ ነው "ትቸኩላላችሁ" ብለው የገሰጿቸው። ከዚህ የማይቀርቡ ፈተናዎችን መታገስ አቅቶን ለስንት የባሰ መከራ ተደርገናል?! ይልቁንም አስፈላጊ ሰበቦችን በማድረስ እንደታዘዝነው በመታገስ ፈረጃን ከአላህ እንጠብቅ። ካልሆነ ግን የሚቀረው ምርጫ የከፋና የመረረ ይሆናል። አዎ! ሶብርን መልቀቅ ለከፋ ፈተና መጋለጥ ነው። ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ عامة الفتن التي وقعت من أعظم أسبابها: قلة الصبر؛ إذ الفتنة لها سببان: إما ضعف العلم، وإما ضعف الصبر "የደረሱ ፈተናዎች (ሁከቶች) እንዳለ ከዋና መንስኤዎቻቸው ውስጥ አንዱ የትዕግሥት ማነስ ነው። ምክንያቱም ለፈተና ሁለት መንስኤዎች አሉት፡ ወይ የእውቀት ማነስ ወይም ደግሞ የትዕግሥት ማነስ ናቸው።" [አልፉሩዕ፡ 10/181] || (ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 16 /1448) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ይቅርታ መቼ? ~ ጥፋቱን አምኖ ደንግጦ፣ ተፀፅቶ ይቅርታ የጠየቀን ሰው በደሉ ከባድ እንኳ ቢሆን ይቅር ማለት ጥሩ ነው። በተለይ ይቅርታ ማድረጉ ፋይዳ ያለው ሲሆን "ምን ሲባል ተደፍሬ?" ማለት አይገ
ይቅርታ መቼ? ~ ጥፋቱን አምኖ ደንግጦ፣ ተፀፅቶ ይቅርታ የጠየቀን ሰው በደሉ ከባድ እንኳ ቢሆን ይቅር ማለት ጥሩ ነው። በተለይ ይቅርታ ማድረጉ ፋይዳ ያለው ሲሆን "ምን ሲባል ተደፍሬ?" ማለት አይገባም። በተለይ ሰውየው በደል የፈፀመብን ሆነ ብሎ፣ አስቦበት ሳይሆን በስህተት ከሆነ ይቅርታ ለማድረግ ልናንገራግር አይገባም። በይቅርታ የአላህ ውዴታ ይገኛል። በይቅርታ ውስጣችን የተከመረ የቂም ሸክም ይወርዳል። የውስጥ ሰላምና እረፍት ይገኛል። በሌላ በኩል ይቅር ማለትን ከቁም ነገር የማይቆጥር፣ በድሎ ምንም ዓይነት የጥፋተኝነት ስሜት የሌለው፣ ይቅር ማለትን እንደሞኝነት የሚያስብ ከሆነ፣ ወይም ምንም ሳይመስለው በጥፋቱ የሚቀጥል ከሆነ ይቅር ማለት አያስፈልግም። = የቴሌግራም ቻናል :- t.me/IbnuMunewor t.me/IbnuMunewor

ሙሓደራ ቁጥር 239 ክፍል 4 ርዕስ= ረድ በ ሙስጠፋ አብደላህ ላይ "መስዓለቱል ዑዝር ቢል ጀሕል'' 🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሓቲም) https://t.me/UstazKedirAhmed

ማነው መጤው? ~ ሙስሊሙ መብቱን በጠየቀ፣ ጭቆናን በተቃወመ፣ እምነቱን ባስተማረ ቁጥር "እናንተ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ስትገቡ አክብረን በተቀበልን እንዴት ውለታችን ይረሳል?" እያሉ በቅጥፈት ለሚመፃደቁ አካላት "እንዴ! እኛ እኮ ኢትዮጵያውያን እንጂ መጤዎች አይደለንም" እያሉ በከንቱ መድከም አያስፈልግም ብዬ በፅኑ አምናለሁ። ሰዎቹ እንዲህ አይነት አመክንዮ የሚገባቸው አይደሉም። ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው። መፍትሔው ማጥቃት እንጂ መከላከል አይመስለኝም። በራሱ ቋንቋ አናግረው። በዚህ ድንቁ ^ ርና ላይ በሰፊው የሚታወቁት በዋናነት የአንድ እምነት ተከታዮች ናቸው። እነሱ ናቸው "የእስላም አገሩ መካ፣ የአሞራ አገሩ ዋርካ" የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ፈጥረው ድንቁርናቸውን ከትውልድ ትውልድ የሚያሻግሩት። እንዴት አድርገው እንደሚጠርቧቸው እንጃ በዚህ ዘመን እንኳ አልተቀየሩም። የለውጥ ተስፋ የሚታይባቸውም አይደሉም። አስቂኙ ነገር ደግሞ ራሳቸውን የአይ^ሁድ ዘር አድርገው መኮፈሳቸው ነው። ሃገሪቱን ለሰባት መቶ ዓመታት በላይ የቦጠቦጠው ራሱን "ሰለሞናዊ መንግስት" ብሎ የሚጠራው መዥገር ስርአትኮ ባህር ተሻግሮ የሰሎሞን ዘር ነኝ የሚል ነው። መጤ ነኝ ማለት አይደል ይሄ? አፄ ምኒልክ "ዳግማዊ" ምኒልክ የተባለው ጥንት ከንጉስ ሰለሞን የተገኘ "ቀዳማዊ" ምኒልክ ነበር ብለው ስለሚያምኑ ነው። "የናዝሬቱ እየሱስ፣ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ቃና ዘገሊላ፣ ቤተልሄም፣ እየሩሳሌም፣ ... " እያለ እምነቱን ከባህር ማዶ ጋር የሚያይዝ አካል እንዴት ሙስሊሞችን መጤ ሊያደርግ ይዳፈራል?! የሙስሊሙን ኢትዮጵያዊነት መቀበል የከበዳቸው ጭንቅላቶች "ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት" የሚል ያረጀ ያፈጀ ተረት ዛሬም ይተርታሉ። ለመሆኑ እነሱ ዘንድ ኢትዮጵያ ማለት የቷ ናት? ለመሆኑ ኢትዮጵያ ሲሉ አፋርን፣ ሶማሊን፣ ሀረርን፣ ስልጤን፣ ከፊል ጉራጌን፣ ሰፊውን ኦሮሚያን፣ ሀላባን፣ አብዛኛው ወሎን፣ አብዛኛውን በኒሻንጉልን፣ ድሬዳዋን፣ አርጎባን፣ ... ይጨምራል ወይ? እስኪ እነዚህን አካባቢዎች ቆርጠው ያውጡና የደሴቷን ካርታ ይመልከቱ። ካርታው ላይ የሚታየው ቀዩ ክፍል ነው የሚቀራቸው። ከዚያ የቀራችሁን የክርስቲያን ደሴት ተመልከቷት! የምትዘምሩላት ኢትዮጵያ ይቺ ናት? ለማንኛውም "በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል የሰለሞን ዘር ነን"፣ "ነገደ ይሁዳ ነን"፣ "የይሁዳ አንበሳ ነን" የሚለውን የአባቶቻችሁን ተረት የምታምኑበት ከሆነ መጤዎች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ መስክራችኋል። እኛ ሙስሊሞች ዐረቦች ነን አላልንም። ኢትዮጵያውያን ነን። እናንተ "የሁ^ዶች ነን" ካላችሁ እኛ ነን የተቀበልናችሁ። "አይ" ካላችሁ "አይ^ሁድ ነን" የሚለውን የአባቶቻችሁን ተረት ውሸት እንደሆነ አስረግጣችሁ ወርውራችሁ ጣሉ። ከዚያ በኋላ ራሳችሁን የኢትዮጵያዊነት አከፋፋይና ድርጎ ሰፋሪ አድርጋችሁ ማየታችሁን አቁሙ። የነውረኝነታችሁ ዳፋ ለደካሞች ይተርፋልና ጥፍራችሁን ሰብስቡ። በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት የከረፋ ሃሳብ ስታንፀባርቁ ታንኩም ባንኩም በእጃችሁ በነበረበት የቀደመው ዘመን ያደረሳችሁትን ማሰብም ይሰቀጥጣል። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

وَقَدْ ذَكَرَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ فِي غَيْرِ مَوْضِعٍ مِنْ كِتَابهِ اليَدَ وَالسَّمْعَ وَالبَصَرَ، فَتَأَوَّلَتِ الجَهْمِيَّةُ هَذِهِ الآيَاتِ فَفَسَّرُوهَا عَلَى غَيْرِ مَا فَسَّرَ أَهْلُ العِلْمِ، وَقَالُوا: إِنَّ اللَّهَ لَمْ يَخْلُقْ آدَمَ بِيَدِهِ، وَقَالُوا: إِنَّ مَعْنَى اليَدِ هَاهُنَا القُوَّةُ. وقَالَ إِسْحَاقُ بْنُ إِبْرَاهِيمَ: إِنَّمَا يَكُونُ التَّشْبِيهُ إِذَا قَالَ: يَدٌ كَيَدٍ، أَوْ مِثْلُ يَدٍ، أَوْ سَمْعٌ كَسَمْعٍ، أَوْ مِثْلُ سَمْعٍ، فَإِذَا قَالَ: سَمْعٌ كَسَمْعٍ، أَوْ مِثْلُ سَمْعٍ، فَهَذَا التَّشْبِيهُ. وَأَمَّا إِذَا قَالَ كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى يَدٌ، وَسَمْعٌ، وَبَصَرٌ، وَلَا يَقُولُ كَيْفَ، وَلَا يَقُولُ مِثْلُ سَمْعٍ، وَلَا كَسَمْعٍ، فَهَذَا لَا يَكُونُ تَشْبِيهًا، وَهُوَ كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى فِي كِتَابهِ: {لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ البَصِيرُ} “በርግጥም አላህ - ዐዘ ወጀል- በቁርኣኑ ብዙ ቦታዎች ላይ እጁን፣ መስማትና ማየቱን ጠቅሷል። ጀህሚያዎች ግን እነዚህን አንቀፆች ቆልምመው (‘ተእዊል’ አድርገው) ዑለማዎች ባልፈሰሩት መልኩ ፈሰሯቸው። ‘አላህ ኣደምን በእጁ አልፈጠረም’ አሉ። ‘እዚህ ላይ የእጅ ትርጓሜ ሃይል (ቁዋ) ነው’ አሉ። ኢስሓቅ ብኑ ኢብራሂም እንዲህ ብለዋል፦ ‘ማመሳሰል የሚሆነው ‘እጁ እንደ እጄ ወይም የእጅ አምሳያ ነው፤ መስሚያው እንደ መስሚያዬ ወይም የመስሚያ አምሳያ ነው’ ሲል ነው። ‘መስሚያው እንደ (ፍጡር) መስሚያ ወይም አምሳያ ነው’ ካለ፣ ይሄ ነው ማመሳሰል። ያለ አኳኋን (ከይፍያ)፣ ያለ አምሳያ አላህ እንዳለው ብቻ ‘እጅ’፣ ‘መስሚያ’፣ ‘መመልከቻ’ አልለው’ ካለ ግን ይሄ ማመሳሰል አይሆንም። ይህም ከፍ ያለው አላህ በቁርኣኑ እንዲህ እንዳለው ነው፦ {የሚመስለው ምንም ነገር የለም። እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነው።}” [ሱነኑ ቲርሚዚይ፡ ሐዲሥ ቁ. 662] እውነታው በዚህ ልክ እንደ ፀሐይ ፍንትው ብሎ ሳለ የሚጨናበሱ ሰዎች መኖራቸው የቢድዐ ዳፍንት ምን ያክል ከባድ እንደሆነ ነው የሚያሳየው። “አሽዐሪዮች እና ወራሾቻቸው አሕ-ባሾችስ ለአቋማቸው ማጠናከሪያ ምን ይጠቅሳሉ?” ካላችሁ “እጅ የለውም” የሚል ቀጥተኛ ማስረጃ ከቁርኣንም፣ ከሐዲሥም፣ ከሰለፎች ንግግርም አንዲትም መረጃ መቼም አያመጡም። ሐቅ ፈላጊ ሆናችሁ በነሱ ማምታቻ የተሸወዳችሁ ሁሉ! “እጅ የለውም” የሚል ቀጥተኛ ማስረጃ አምጡ ብላችሁ አፋጧቸው። የራሳቸውን ከንቱ ትንታኔ እንጂ አንድም አያቀርቡላችሁም። ይልቁንም የሚጠቅሱት እንዲሁ ማምታቻ ነው። [ማምታቻ አንድ]፡- “የሚመስለው የለም” የሚለውንና መሰል አንቀፆችን በመጥቀስ ከሶሐቦች ያልተገኘ የራሳቸውን ትርጉም መስጠት። “ምን አገናኘው?” ካላችሁ እነሱ ዘንድ “እጅ አለው” ማለት በፍጡር ማመሳሰል ነው። በቃ! “እንዲያ ከሆነ ቁርኣኑ የማመሳሰልና የሺርክ ሰነድ ነው ማለት ነው” ብትሏቸው ምንም ሳያፍሩ “አዎ ዟሂሩ ኩ^ f ^ር ነው” ይላሉ። እንዲያ ከሆነ የመጀመሪያ አመሳሳዮች አላህና መልእክተኛው ናቸው ማለት ነው! አዑዙ ቢላህ! ሐቂቃው ግን አላህን እራሱን በገለፀበት፣ ነብዩም ﷺ አላህን በገለፁበት መግለፅ ፈፅሞ ማመሳሰል አለመሆኑ ነው። የቡኻሪ ሸይኽ የሆኑት ኑዐይም ብኑ ሐማድ አልኹዛዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- مَنْ شَبَّهَ اللَّهَ بِشَيْءٍ مِنْ خَلْقِهِ فَقَدْ كَفَ-رَ وَمَنْ أَنْكَرَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ فَقَدْ كَفَ-رَ فَلَيْسَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ وَرَسُولُهُ تَشْبِيهٌ “አላህን ከፍጡሩ በየትኛውም ያመሳሰለ በርግጥም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበትን የካደም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበት እና መልእክተኛው (እሱን የገለፁበት) ማመሳሰል አደለም።” [ላለካኢይ፡ ቁ. 936] ይሄ የኑዐይም ንግግር በአላህ መገለጫዎች ዙሪያ ቁልፍ የሆነ ቀመር ነው። ከውስጡ ሶስት ወሳኝ ህጎችን እናገኝበታለን። እነሱም፡- 1ኛ፡- አላህን በፍጡር ማመሳሰል ክህ -ደት ስለሆነ መጠንቀቅ እንደሚገባ፣ 2ኛ፡- አላህ እራሱን የገለፀበትን ማስተባበል ክህ^ደት እንደሆነ፣ 3ኛ፡- በቁርኣንና በሐዲሥ ውስጥ ፈፅሞ ማመሳሰል የሚባል ነገር እንደሌለ። (በርካታ አሽዐሪዮች ግን ቁርኣንና ሐዲሥ በማመሳሰል የታጨቀ ነው ብለው ነው የሚያምኑት።) [ማምታቻ ሁለት]፡- ሌላኛው የሚጠቅሱት “ማስረጃቸው” በታዋቂ ዑለማዎች ማስፈራራት ነው። ቁርኣንና ሐዲሥ ስትጠቅሱላቸው እነሱ “ነወዊይ፣ ኢብኑ ሐጀር፣…” ይላሉ። ከቁርኣንና ሐዲሥ በተቃራኒ ፍፁም ያልሆኑ ሰዎችን ማጣቀስ ነውር ነው። “እናንተ ቁርኣኑንና ሐዲሡን ከነሱ በላይ ልታውቁት ነወይ?” ይላሉ። መልካም! እነሱስ ቁርኣኑንና ሐዲሡን ከሰለፎች በላይ ሊያውቁት ነውን? እስኪ የሰለፎቹን ተፍሲር መርምሩና አደብ ይኑራችሁ። የአሕ-ባሽ አቋም ሌላው ቀርቶ “እንከተላቸዋለን” ከሚሏቸው የአቡል ሐሰን አልአሽዐሪ አቋም ጋር እንኳን አይገጥምም፡፡ አቡል ሐሰን የአህሉ ሱና፞ን ዐቂዳ ሲዘረዝሩ እንዲህ ብለዋል፡- وأن الله سبحانه على عرشه كما قال: الرحمن على العرش استوى وأن له يدين بلا كيف كما قال: خلقت بيدي وكما قال: بل يداه مبسوطتان “የጠራው አላህ ‘አረ፞ሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ’ እንዳለው በዐርሹ ላይ ነው። ሁለት እጆች እንዳሉትም እንዲሁ ያለ አኳኋን መስጠት (ያፀድቃሉ)። ‘በሁለት እጆቼ ፈጠርኩ’ እንዳለው፤ ‘ይልቁንም ሁለት እጆቹ የተዘረጉ ናቸው’ እንዳለውም (እንዲሁ ያፀድቃሉ)።” [መቃላቱል ኢስላሚዪ፞ን፡ 290] ከዚያም የአህሉ ሱና፞ን አቋም በሰፊው ከዘረዘሩ በኋላ “እነዚህ ባጠቃላይ (የሱና፞ ሰዎች) የሚያዝዙባቸው፣ የሚተገብሯቸውና የሚያምኑባቸው ናቸው። በዘረዘረነው አቋማቸው ሁሉ እናምናለን። እንጓዝበታለንም” ብለው ቋጭተዋል። [መቃላት፡ 297] ሲጠቃለል "አላህ እጅ አለው" ማለት ፈጣሪን በፍጡር ማመሳሰል ነው የሚል አካል ነብዩም ﷺ በሐዲሣቸው፣ ሰለፎቹም፣ ኢማማችን የሚሏቸው አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም አመሳሳይ ሙጀሲማ ናቸው እያለ ነው። ቁርኣን ራሱ ዟሂሩ ተጅሲም የሆነ መልእክት ስለያዘ አሳሳች ነው እያሉ ነው። ሙግታቸው ከኛ ጋር ሳይሆን ከአላህ፣ ከነብዩ ﷺ፣ ከሰለፎቹ እና ኢማማችን ከሚሏቸው አቡል ሐሰን አልአሽዐሪ ጋር ነው። (ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር፡ 12/2012) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ኹጥባ የቁርኣን ትልቅነት https://t.me/SadatKemalAbuMeryem