هداية القلوب (የልቦች መሪ)
رفتن به کانال در Telegram
228
مشترکین
+124 ساعت
+217 روز
+1530 روز
آرشیو پست ها
ከሰው አይን፣ ከድግምት.. ለሚፈሩ ሰዎች
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
በመስጊድ ውስጥ አንድ ሰውን አስታውሳለሁ፤ ከሶላት በኋላ ወደ እኔ ክፍል መጥቶ
'እኔ ሁልጊዜ ከዕይን (የሰው እይን)፣ ከድግምትና ከነዚህ ከመሰሉ ነገሮች እፈራለሁ' አለኝ። እኔም 'አላህና መልእክተኛው (ﷺ) ከማንኛውም ከምትፈራው ትልቅ ነገር ሊጠብቅህ የሚችል ዱዓ ሰጥተውሃል። ይህን ዱዓ ካልከው ከአላህ ፈቃድ ጋር ከአላስፈላጊ ነገር ሁሉ ይጠብቅሃል' አልኩት።
እሱም 'ምንድን ነው?' ብሎ ጠየቀኝ። እኔም 'ከቤትህ ስትወጣ፦ بِسْمِ اللهِ، تَوَكَّلْتُ عَلَى اللهِ، وَلاَ حَوْلَ وَلاَ قُوَّةَ إِلاَّ بِاللهِ. በአላህ ስም ገባን በአላህ ስምም ወጣን በጌታችንም ተመካን.’ ... اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَعُوْذُ بِكَ أَنْ أَضِلَّ، أَوْ أُضَلَّ، أَوْ أَزِلَّ، أَوْ أُزَلَّ، أَوْ أَظْلِمَ، أَوْ أُظْلَمَ، أَوْ أَجْهَلَ، أَوْ يُجْهَلَ عَلَيَّ. አላህ ሆይ! ከመጥመም ወይም ከማጥመም ፥ ከመዋረድ ወይም ከማዋረድ፥ ከመበደል ወይም ተበዳይ ከመሆን፥ ሰዎችን ስህተት ላይ ከመጣል ወይም ራሴ ስህተት ላይ ከመውደቅ በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ .’» ካልክ፤ (ለአንተ) «በቂህ ነው፣ ተመራህ፣ ተጠበቅህም» ይባላል' አልኩት።"
`ይላሉ 👇 🎙 الشيخ أ.د/ ياسر بن راشد الدوسري https://t.me/alruqyehsheriyeh https://t.me/alruqyehsheriyeh
መልካም ጁሙዓ 🌿
اللهم في يوم الجمعة، اجعل لنا من كل دعاءٍ نصيبًا، ومن كل خيرٍ أوفر الحظ والنصيب.
"አላህ ሆይ! በዚህ የጁሙዓ ቀን፣ ከምናደርገው እያንዳንዱ ዱዓ ድርሻ ስጠን፣ ከመልካም ነገርም ትልቁን ዕድልና ድርሻ አድርግልን።"
اللهم صلِّ وسلم وبارك على نبينا محمد ﷺ.
"አላህ ሆይ! በነቢያችን ሙሐመድ ﷺ ላይ ሰላትህን፣ ሰላምህንና በረካትህን አውርድ።"
أكثروا من الصلاة على النبي ﷺ، فإنها نورٌ للقلوب.
"በነቢዩ ﷺ ላይ ሰላዋትን አብዙ፤ ምክንያቱም ለልቦች ብርሃን ናት።"
https://t.me/httpYelbochMeriQuran
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ራሳቸውን ወደ ሱና በሚያስጠጉ አካላት ላይ በሰፊው ከሚታዩ ነውረኛ ተግባራት ውስጥ አንዱ ሰዎችን በተመለሱበት ጉዳይ መክሰስ ነው። አንድ ሰው ከሆነ የተሳሳተ አቋም ወይም ጥፋት ከተመለሰ ያንን ጉዳይ #እያወቀ ሆነ ብሎ በሱ ላይ የሚለጥፍ ሰው
1ኛ፦ ዋሾ ነው።
2ኛ፦ ውሸትን የደዕዋው መንገድ አድርጎ የያዘ መጥፎ ሰው ነው።
3ኛ፦ ዓላማው ዲን ሳይሆን ቂም ማወራረድና ብሸሸቅ ነው።
ይሄ ነገር የሰውየውን መመለስ #ሳናውቅ ሊገጥመን ይችላል። መመለሱን ካወቅን በኋላ በተመለሰበት ጉዳይ መወንጀል ግን ያለ ወንጀሉ ሰውን መክሰስ ነው። ቡድናዊ ሽኩቻ ላይ ያነጣጠሩ "ረዶች" በብዛት ይሄ ችግር ጎልቶ ይታይባቸዋል።
ሰውን በተመለሰበት ጥፋት መክሰስ ባልፈፀመው ጥፋት እንደ መክሰስ ነው። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል:-
{ وَٱلَّذِینَ یُؤۡذُونَ ٱلۡمُؤۡمِنِینَ وَٱلۡمُؤۡمِنَـٰتِ بِغَیۡرِ مَا ٱكۡتَسَبُوا۟ فَقَدِ ٱحۡتَمَلُوا۟ بُهۡتَـٰنࣰا وَإِثۡمࣰا مُّبِینࣰا }
"እነዚያንም ምእምናንንና ምእምናነትን ባልሰሩት ነገር (በመዝለፍ) የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ፡፡" [አልአሕዛብ: 58]
ነብያችንም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
من قال في مؤمنٍ ما ليس فيه أسكنه اللهُ رَدْغَةَ الخَبالِ حتّى يخرُجَ ممّا قال
"በአማኝ ላይ የሌለበትን የተናገረ ሰው አላህ የጥፋት ማጥ ውስጥ ያኖረዋል፣ ከተናገረው ነገር እስከሚወጣ ድረስ።" [ሶሒሑ ተርጊብ: 2845]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ustaz Kedir Ahmed Al—Kemisse (Abu Juweyriya)
ሙሓደራ ቁጥር 239
ክፍል 3
ርዕስ= ረድ በ ሙስጠፋ አብደላህ ላይ
"መስዓለቱ ዑዝር ቢል ጀሕል''
🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሓቲም)
https://t.me/UstazKedirAhmed
Repost from የቡኻሪና ሙስሊም ሐዲሶች በአማርኛ
📣የሙዓዚንነት ልቅናና ምንዳ!
ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦
﴿المؤذِّنُ يُغفَرُ لهُ مدى صوتِه، ويُصدِّقُه كلُّ رَطبٍ ويابِسٍ ولهُ مثلُ أجرِ مَن صلّى معَه﴾
“ሙአዚን ድምፁ በሚደርስበት ልክ (ወንጀሉ) ይማርለታል። እርጥብም ሆነ ደረቅ ነገር ሁሉ እውነትነቱን (በቂያማ ለት) ይመሰክርለታል። ከእርሱ ጋር የሰገደም ሰው አጅር (ምንዳ) ተመሳሳዩን ያህል ያገኛል።”
📚 ሶሂህ አተርጊብ፡ 234
🟧🟧🟧🟧🟧🟧
🔸 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦
📱 Telegeram 📱 Whatsup
📱 Facebook 📱 Instagram
📱 X 📱 Youtube 📱 Tik tok
↙️ የሀዲሱን ማብራሪያ ከኮመንት መስጫው ስር ያገኛሉ።
*توكلي بالله اختي في الله*
➹ቆራጥ እሰት ከሆንሽ ይከብዳል የምትይው ሁሉ ቀሎ ታገኝዋለሽ ፈጥነሽ ተስፍ ለመቁረጥ አትሞክሪይ‼️
➹እደርሳለው ከምትይው ቦታ ትደርሻለሽ ሶብረኛ ሁነሽ ከቀጠልሽ‼️
➹ላኪን ነገር ግን ተሎ ተስፍ ከቆረጥሽ የጀመርሻቸው ሁሉ የሚልቁ መስለው አይታዩሽም መድርስ እፈልጋለው ያልሻቸው ቦታዎችም ሩቅ ሁነው ሊታዩሽ ይችላሉ ታገይ ታገሽ ለውጥ አትጭምና ቢኢዝኒ ጀለዋዓላህ‼️
➹በዓላህ የተመካች እሰት ሃሳቧ ሳይሳካላት አይቀርም ባዓላህ ፍቃድ ኢሻዓላህ‼️
አላህ ሆይ! ከሶብረኞች ከታጋሾች ባሬዎችህ አድርገን ‼️
የሰዎችን ነውር መሸፈን ማለት ምን ማለት ነው?
ጥፋትን አለማሰራጨት፦ አንድ ሰው ወንድሙ ወይም እህቱ ላይ ስህተት፣ ነውር ወይም የኃጢአት ድርጊትቢያይ ወይም ቢሰማ፣ ያንን ለሰዎች ከመንገስና ከማሰራጨት ይልቅ ምስጢር አድርጎ መያዝ ነው።
ምክር መስጠት፦ ነውሩን ወይም ስህተቱን ያየንበትን ሰው ለብቻው በለስላሳ አንደበትና በሂክማ (በጥበብ) መምከር እንጂ በሰው ፊት በማዋረድ ስሙን ማጠልሸት አይደለም።
በቂያመ ቀን የሚገኝ ምንዳ (አጅር)
“አል-ጀዛኡ ሚን ጂንሲል-ዐመል” (ምንዳ እንደ ሥራው ዓይነት ነው)፦ አንድ ሰው በዚች ዓለም የሰዎችን ጥፋት ደብቆና ሸፍኖ የሰውን ክብር እንደጠበቀ ሁሉ፣ አላህም በቂያመ ቀን (በእስብራና በእሳቱ ፊት) የዚያን ሰው ስህተትና ኃጢአት በሰው ፊት ሳይገልጥበት ይሸፍንለታል።
አስቸጋሪ ቀን መደገፍ፦ የቂያመ ቀን ሁሉም ሰው የእጁን የሚያገኝበትና የሚጨነቅበት ቀን በመሆኑ፣ በዚያ ቀን አላህ ነውራችንን እንዲሸፍንልንና እንድንታደግ ትልቅ መንገድ ነው።
የሰዎችን ክብር መጠበቅ፦ የሰዎችን ስም ማጠልሸት፣ ሐሜትና ነውራቸውን መፈለግ በእስልምና ዘንድ በጣም የተከለከለ ነው
ይቅር ባይነትና ልበ-ሰፊነት፦ የሰዎችን ድክመት አይቶ አላዩ እንዳዩ መሆን የነፍስ ጥራትና የታላቅ አክላቅ (ሥነ-ምግባር) ምልክት ነው።
በስተመጨረሻ ማሳሰቢያ፦ ነውር መሸፈን የሚባለው አላህን በበደለና በራሱ ላይ ብቻ ስህተት በሰራ (በተገደበ)፣ ነገር ግን ጥፋቱን ግልጽ ባላደረገና ለሰዎች አደጋ ባልሆነ ሰው ላይ ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ መብት የሚያጣ ወይም ለሌሎች አደጋና በደል የሚያደርስ ከሆነ (ለምሳሌ፦ በዲን ላይ የሚዋሽ ወይም የተሳሳተ መረጃ/መልዕክት የሚያሰራጭ ከሆነ፣ ወይም ደግሞ አዳዲስ ጭማሬ በማደርግ ቢድዓ የሚያሰራጭ ከሆነ ሰዎች እንዳይሳሳቱና መንገድ እንዳይስቱ ከሱ ማስጠንቀቅ ግድ ይላል። ወይም ስርቆት ላይ የተሰማራ ሌባ ከሆነ፣ ወይም ደግሞ አደገኛ ወንጀለኛ ከሆነ) ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል እንዲደርስ ማድረግ የሕዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ማንነቱን ማጋለጥ አስፈላጊ ነው።
Repost from የቡኻሪና ሙስሊም ሐዲሶች በአማርኛ
✔️የሰውን ነውር መሸፈን!
ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦
﴿لا يَسْتُرُ عَبْدٌ عَبْدًا في الدُّنْيا، إلّا سَتَرَهُ اللَّهُ يَومَ القِيامَةِ.﴾
“አንድ ባሪያ የአንድን ባሪያ ነውር አይሸፍንም አላህ በቂያማ ለት የሱን ነውር የሚሸፍንለት ቢሆን እንጂ።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2590
🟧🟧🟧🟧🟧🟧
🔸 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦
📱 Telegeram 📱 Whatsup
📱 Facebook 📱 Instagram
📱 X 📱 Youtube 📱 Tik tok
↙️ የሀዲሱን ማብራሪያ ከኮመንት መስጫው ስር ያገኛሉ።
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
✅ ሸይኽ የሕያ & ሸይኽ ዓብዱ!
ዛሬ ሸይኽ ዓብዱል ሐሚድ አል'ለተሚይ - هداه الله - ይዞት የመጣው "በኢጅቲሃጃዊ ነጥብ የተቃረነውን አካል ኢልዛም" የማድረግ አዲስ ቢድዓ ትላንት የሕያ አልሐጁሪይ -هداه الله- ተብዲዕ ከተደረገባቸው ቢድዓዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው።
ያያዝኩት የድምፅ ፋይል ታላቁ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዲልወሃብ አል'ወሷቢይ -رحمه الله- ስለ የሕያ አል'ሐጁሪያ ተጠይቀው የመለሱበት ነው። ከንግግራቸው ውስጥ የሚከተውን ትኩረት ሰጥታቹህ አንብቡት አድምጡትም ባረከላሁ ፊኩም።
01:23
➡️
03:50
"فهُو ابتدعَ في الدِّين بدعًا كثيرة؛ ومنها على سبيل المثال وليس الحصر: إذا اختلف مع شخص في مسألةٍ اجتهاديّةٍ في مثل الشّيخ عبد الرّحمن العدني هل هُو حزبيّ أم لا؟! هُو يقول بأنّه حزبيّ! وبقيّة المشايخ من أهل السُّنّة والجماعة قالوا: بل هُو سُنِّي وليس بِحِزْبي، فانظُروا ماذا فعل مع المشايخ بدّع وضلّل وفسّق وقاطع وهَجَر وأمر طُلاّبه بالهجر وأنزلُوا الملازِمَ الكثيرة والأشرطة الكثيرة؛
نقول له: يا هذا هذه مسألة اجتهاديّة ما هي نصيّة، ما في وحي ينزل لنا فُلان حزبِي! أنتَ اجتهدتَّ هذا إذا أُحْسِنَ بك الظّنّ أنّك قُلت هذا عن اجتهادٍ! إن لم تُكن قُلتَه عن هوى! لِنفرض أنّك اجتهدتَّ وغيرُك اجتهد قال: ما هُو حزبي، المسائل الاجتهاديّة ما يجوز التّضليل فيها والتّبديع والتّحزيب والتّفسيق والتّفجير أنّهُم فَجَرَة أنّهُم فَسَقَة وأنّهُم مَكَرة وأنّهُم خونة... مسألة اجتهاديّة وسِّع بالَك، فهُو شرّع هذه البدعة الخبيثة الهجر والمُقاطعة والمُدابرة وعدم السّلام والكلام ولو كان لِسنين طويلة من أجل مسألة اجتهاديّة!
عليهِ أن يتُوبَ إلى الله عزّ وجلّ من هذه البِدعة التي هِي بدعة ضلالة وتُعتَبر من الكبائر أنّه ضلّل؛ لو فَعَل هذا العُلماء! لو فعل هذا السّلف الصّالح! لو فعل هذا الأئمّة الأربعة ما بَقِيَ مودّة بين مُسْلِمَيْن؛ هذا يرى كذا وهذا يرى خلاف ذلك ومُقاطعة ومُهاجرة؛ لم تبقى مودّة بين اثنين! لهذا قُلنا: بأنّها بدعة"
📝 ትርጉም፦
"እርሱ (የሕያ አልሐጁሪይ) በዲን ውስጥ ብዙ ቢድዓዎችን ፈብርኳል። ከእነዚህም መካከል ለምሳሌ እንጂ ሁሉን ለመዘርዘር ሳይሆን፦ በአንድ ኢጅቲሃዳዊ ጉዳይ ላይ ከሌላ ሰው ጋር ሲለያይ፣ ለምሳሌ፦
"ሸይኽ ዐብዱረሕማን አልዐደኒ ሒዝቢይ ናቸው ወይስ አይደሉም?" በሚለው ጉዳይ፤ እርሱ "ሒዝቢይ ናቸው" አለ፤ ሌሎች የሱና መሻኢኾች ደግሞ "አይደሉም፤ ሱንይ ናቸው" አሉ። እንግዲህ ከዚያ በኋላ ከመሻኢኾች ጋር ያደረገውን ተመልከቱ፤ አንዳንዶቹን ሙብተዲዕ አላቸው፣ አንዳንዶቹን ጠማማ አላቸው፣ ሌሎችን ፋሲቅ አላቸው፣ ከእነርሱም ራሱን አራቀ፣ ተማሪዎቹንም እንዲርቋቸው አዘዘ፤ ብዙ ኢልዛማቶችን አወረዱ፣ ብዙ የድምፅ ቅጂዎችም ተለቀቁ።
እኛ ግን እንለዋለን፦ "አንተ! ይህ ኢጅቲሃዳዊ ጉዳይ ነው፤ በቁርጥ ነስ (ግልጽ የቁርኣንና የሐዲስ ማስረጃ) የመጣበት አይደለም። ከሰማይ ወሕይ ወርዶ "እገሌ ሒዝቢይ ነው" ብሎ አይነግረንም። አንተ በኢጅቲሃድህ እንዲህ አልክ፤ - ይህም ስለ አንተ መልካም ግምት ብናደርግና በስሜት ሳይሆን በኢጅቲሃድ ብቻ ተናግረሃል ብለን ካልን ነው - ሌላው ደግሞ በኢጅቲሃዱ "ሒዝቢይ አይደለም" አለ።"
እንደዚህ ባሉ ኢጅቲሃዳዊ ጉዳዮች ሰዎችን ማጥመም፣ የቢድዓ ባለቤት ማለት፣ ሒዝቢይ ማለት፣ ፋሲቅ ማለት፣ "ፋጅር ናቸው፣ ሴሬኞች ናቸው፣ ከዳተኞች ናቸው፣ አታላዮች ናቸው…" እያሉ መፍረድ አይፈቀድም። ኢጅቲሃዳዊ ጉዳይ ነው። ልብህን ሰፋ አድርገው።
ይህ (የሕያ አልሐጁሪይ) ይህችን ፀያፍ ቢድዓ መንገድ አደረገ። ማኩረፍ፣ መቋረጥ፣ ጀርባ መሰጣጠት፣ ለብዙ ዓመታት እንኳ ሰላም አለመባባል፣ ንግግርን መተውንና ግንኙነትን ማቋረጥን እንደ ሃይማኖታዊ መርህ አድርጓል።
ከዚች ቢድዓ ወደ አላህ ሊመለስና ሊጸጸት ይገባዋል፤ ምክንያቱም ይህ ጥመት ቢድዓ ሲሆን፣ ሰዎችን ያለ ትክክለኛ ማስረጃ ማጥመም ከታላላቅ ኃጢአቶችም አንዱ ነው።
በእርግጥ ዑለማዎች፣ መልካም ቀደምቶች፣ አራቱ የፊቅህ ኢማሞች እንዲህ ቢያደርጉ ኖሮ፣ በሁለት ሙስሊሞች መካከል ፍቅርና ወንድማማችነት ባልቀረ ነበር። ይህ አንድን አቋም ይይዛል፣ ያ ደግሞ በተቃራኒው ይላል፤ ከዚያም መቋረጥና መራራቅ ይጀምራል፤ በመጨረሻም በሁለት ሰዎች መካከል ፍቅር አይቀጥልም ነበር። ለዚያም ነው ይህችን ቢድዓ ነች ያልነው።"
✅ ጥያቄ ለለተሞ ተከታዮች፦
✈️ በተወሳው ነጥብ ሸይኽ የሕያ አልሐጁሪይ እና ሸይኽ ዓብዱ ልሐሚድ አልለተሚይ ልዩነታቸው ምንድነው? ሸይኽ የሕያ ሸይኽ ዓብዱረሕማንን ተብዲዕ በማድረግ ኢልዛም እንዳደረገው ሁሉ ሸይኽ ዓብዱ ልሐሚድም ሸይኽ ኢልያስንና መሰል ሰዎችን ተብዲዕ በማድረግ ኢልዛም ያደርጋል። እና የሰዎች መለያየት የነገሩን ቢድዓነት ያስወግዳልን?
✈️ ሸይኽ ዓብዱል ሐሚድ የተብዲዕ ጉዳይ ኢጅቲሃጅን አያስተናግድም የሚል አቋም እንዳላቸው ይታወቃል። ዑለማኡ ሱና ደግሞ ከእርሱ በተቃራኒ ናቸው። t.me/Abu_lmran_Alaseriy/3616
እና በዚህ ነጥብ ማነው መንገድ የሳተው ሸይኻቹህ ወይስ እነዚህ ታላላቅ የሱና ዑለማኦች?
✈️ የዚህ አይነት ፍንትው ያለ ጉዳይ ሲደርሳቹህ ቆም ብላቹህ ከማሰብና ማስረጃን ከመመልከት ይልቅ "በምን መልኩ መልስ ልስጠው?" ብላቹህ መጨነቅና መጠበብ ቢቀርባቹህ አይሻል ወይ? ለመሆኑ እስከመቸ ነው ይህ የለተሞ ሸይኽ በጎተታቹህ እየተጎተታቹህ ከማስረጃ ተጣልታቹህ ከሱና ዑለማእ ተቃርናቹህ የምትቀጥሉት? ብሽሽቅና ነቆራውን ትታቹህ ሳይመሽባቹህ ወደ ሩሽዳቹህ ብትመለሱ፣ ከእንቅልፋቹህ ብትነቁ አይሻልም? ብዥታስ ካለ በውይይት መፍታትና ሐቅ ወዳለበት ሁኖ በእውነት ላይ መሰባሰብ አይሻልም? ተው ልብ ግዙ ወንድሞቸ! አላህ ልቦና ይስጣቹህ ይስጠን።
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
የምሽት ሁኔታ በቀን ውሎ ላይ የመመርኮዝ ሒደቱ የሰፋ ነው። አንዳንዴ በጠራራ ፀሀይ ለእኛ ብቻ የጨለመ መስሎን፣ አይሆኑ ውሎ እንውላለን። ህይወት ያደክማል፤ መሯሯጥ፣ መውጣትና መውረድ ይሰለቻል። ቀን ላይ በሁሉም አካሎቻችን እንባክናለን፤ በምሽት ግን ሁሉንም አካሎቻችንን ወክሎ አዕምሯችን ይባክናል።
አለማሰብ መልካም አይደለም፤ ማሰብ የሚገባንን ሀሳብ መምረጥ ግን ብልህነት ነው። የአዕምሯችንን ዝለት ለመቀነስና ምሽታችንን ለማድመቅ፣ ጎደለብን ብለን የምንለውን ማሳደድ አቁመን ያለንን የገዘፈ ነገር እያሰብን አላህን እናመስግን።
በዚህ ድቅድቅ ሌሊት፣ ያለምንም ሀሳብና ያለምንም ትዝታ ራሳችሁን ትራስ ላይ አሳርፋችሁ "ለሽሽሽ" ብላችሁ የተኛችሁ ሰዎች... አእምሯችሁን በስንት ትሸጡልናላችሁ ?
ልቤ ሆይ!!
~
ልቤ ሆይ ልብ አድርግ - ለመልካሙ ትጋ - ከክፋት ተገታ
ምላሴ ሆይ እረፍ - ጦስህ ያስፈራኛል - በጧትም በማታ
እጄ ሆይ ተመከር - "እጄን በ’ጄ" እንዳልል - በሚያስጨንቅ ቦታ
እግሬ እግር አታብዛ - ታዋርደኛለህ - በጭንቁ ቀን ለታ
አዋጅ ሰምቻለሁ - እጅግ የሚያስፈራ - ከሰማዩ ጌታ።
(يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ)
"በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሰሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡" [አንኑር: 24]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 7/2016 )
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
