fa
Feedback
هداية القلوب (የልቦች መሪ)

هداية القلوب (የልቦች መሪ)

رفتن به کانال در Telegram

https://t.me/httpYelbochMeriQuran

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
228
مشترکین
-124 ساعت
+197 روز
+1430 روز
آرشیو پست ها
● المعاصي والذنوب سبب حرمان طاعة علام الغيوب ● t.me/SleSlkachin

ሪያድ ያላቹህ እህቶ የሰአት ስራ ተመላላሽ ስራ ከሰማቹህ <@umu_afifah_ami_1> ንገሩኝ በአሏህ አድት ህእቴ ያለ አባት ልጅ ይዛ ተቸግራለች ተጨናንቃለች💦💦 እህህ እህቶቻቺን ተንገላቱ እየወለዳቹህ የምትጥሉ ወንዶች አሏህን ፍሩ ኧረ ተው በሴቶች ላይ እደዚህ ልባቹህ የደነደነው በጤናቹህ ነው አንዷ ስቶልድ ወደ ሌላዋ የምቴደው ያአሏህ💔💔 ምን አይነት ጉድነው ልባችን ደማ በምናየውና በምንሰማው በእህቶቻቺን ግፍ💦💦👇👇 @umu_afifah_ami_1

"ደብቁኝ ትያለሽ" የሚያንጸባርቀው ይሄ ድንቅ ውበትሽ፣ በድቅድቅ ጨለማ የሚያበራው ፊትሽ፣ ከጌጥ የተበቃቀለው ተክለ ሰውነትሽ፣ እንደ ሀር ፈክቶ የሚታየው ፀጉርሽ፣ ምድር አይንኩብኝ ያልሻቸው እግሮችሽ፣ ኩል የማያሻቸዉ ዥንጉርጉር አይኖችሽ፣ የጎረሽባቸው እኒያ ውብ ጣቶችሽ፤ ቀናት ቀርቷቸዋል በጅምላ ሊከዱሽ። ማራኪ ውበትሽ በእርግጥ ይከዳሻል፣ ወደ እርጅና ማማ ስቦ ይወስድሻል። ​እንዲያ እንዳልተዋብሽ፣ እንዳልተሸቀረቀርሽ፣ እዩኝ እዩኝ ብለሽ እንዳልተገላለጥሽ፣ ጊዜው ይደርስና ሲረግፍ ቁንጅናሽ፣ እንዲህ የተዋበው ተጨማትሮ ቆዳሽ፣ ውበትሽም ጠፍቶ ታፍሪና በራስሽ፣ እዩኝ እዩኝ እንዳልሽ ደብቁኝ ትያለሽ። እህቴ... ​ጸጸት ከሚወርስሽ የማይቀረው ደርሶ፣ አይኖቼ ከሚያዩ ተስፋሽ ተደርምሶ፣ በአላህ አሳይኝ ተቁዋሽ ተመልሶ፣ አይጠቅምሽምና በዚያን ጊዜ ለቅሶ!። ​ተመከሪ… ተመከሪ እህቴ! ✍አቡፈዉዛን https://t.me/abu_fewzan_abdu_shikur t.me/abu_fewzan_abdu_shikur t.me/abu_fewzan_abdu_shikur

🔖 يقول ابن تيمية - رحمه الله - :
[  والمسلم الصادق إذا عبد الله بما شرع فتح الله عليه أنوار الهداية في مدة قريبة ] .. ا📚 الإستقامة (100) . ~ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ - አላህ ይዘንለትና እንድህ ይላሉ፦  "እውነተኘ የሆነ አማኝ አላህ ባዘዘው መሰረት የሚሰራ ከሆነ በቅርብ ግዜ የሂዳያ ብረሐን ይከፈትለታል። t.me/SleSlkachin

~ ሃኪም እና ታማኝነት ~ ~ አንድ ሃኪም / ሃኪም ቤት ሊታከም ለመጣ ሰው ታማኝ መሆን አለበት። * የታካሚውን ሚስጥር ሊያወጣ አይፈቀድም። የታካሚውን ምስል ያለ ፈቃዱ ለሚዲያ ሊያቀርብ አይገባም።
~ ሃኪም እና ታማኝነት ~ ~ አንድ ሃኪም / ሃኪም ቤት ሊታከም ለመጣ ሰው ታማኝ መሆን አለበት። * የታካሚውን ሚስጥር ሊያወጣ አይፈቀድም። የታካሚውን ምስል ያለ ፈቃዱ ለሚዲያ ሊያቀርብ አይገባም። * ከአቅሙ በላይ የሆነ ነገር ከገጠመው ወደተሻለ ቦታ መጠቆም እንጂ የሰውን ልጅ መለማመጃ ሊያደርግ አይፈቀድም። ከባድ ወንጀል ነው። * ገንዘቡን ያላግባብ ሊያስወጣው አይፈቀድም። የሰው ገንዘብ ሐራም የሚሆነው በስርቆትና በዝርፊያ ብቻ አይደለም። ምርመራና መድሃኒት በማዘዝ፣ አስተኝቶ በማከም፣ በቀዶ ህክምና፣ በየትኛውም መንገድ ባልተገባ መልኩ የታካሚውን ገንዘብ ያስወጣ ሰው የሰው ገንዘብ እየዘረፈ ነው። ይህን ያደረገ ሰው እያንዳንዱ ሰው ገንዘቡን እንዴት እንዳመጣው እና በምን እንዳወጣው በሚጠየቅበት አስፈሪው የቂያማ ቀን ወዮለት። ዛሬ ያላግባብ ለተወሰደ ገንዘብ ሁሉ ነገ ጥብቅ ሂሳብ አለ። ብር በብር አይመለስም። ከመልካም ስራህ ነው ተላልፎ የሚሰጠው። እሱ ካልበቃ የተበዳይ ወንጀል ነው ባንተ ላይ የሚጣለው። ለማይረባ አላፊ ዱንያ ዘላለማዊ ህይወትን ከማጨለም መጠንቀቅ ይገባል። (ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 30/2014) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ከአህሉ - ተውሒድ መርከዝ ተማሪዎች የአንዱን ወንድማችን ግጥም ተጋበዙልን !! ~ ወይ ስልኬ!!💻💻 🗂 🗂 🗂 🗂 🗂 🗂 💬 🌐 🌐 🌐 .......አረ ስንቱ ይዘርዘር...... @Abu_lmran_Alaseriy @Abu_lmran_Alaseriy

ኢኽወቲ ወአኸዋቲ ፊ'ላህ! ~ አመለካከታችንም፣ ግንዛቤያችንም ስለሚለያይ የምፅፈው ሁሉ ለሁሉ ሰው ይስማማል ተብሎ አይታሰብም። የማንም የግል ፀሐፊ አይደለሁምና የማምንበትን እንጂ ሰው እንዳይከፋ እያልኩ እንደማልፅፍ ማሳወቅ አይጠበቅብኝም። ከዚህ በተቃራኒ፣ ሰው እንደመሆኔ ራሴን ማጥራራት ባልፈልግም፣ ማንንም ለማብሸቅና ለእልህ ከመፃፍም እጠነቀቃለሁ ብዬ አስባለሁ። መነገር አለበት ብዬ የማምንበትን ሃሳብ ሰዎችን እንደሚያስከፋ እያወቅኩም ለመናገር እሞክራለሁ። ይሄ አካሄዴ ለአንዳንዶቻችሁ እልህ፣ ለሌሎች የሒክማ ማጠር፣ ለሌሎች ደግሞ ከፋፋይነት ሊሆን ይችላል። የውስጤን አላህ ያውቃል። በኔ ቤት ለወገኔ ይበጃል የምለውን ማካፈሌ ነው። የሆነ ሆኖ ሃሳቤ በቀጥታ በፅሁፌ የማሰፍረው ነው። የምደብቀውም የለኝም፣ የምደብቅበትም ምክንያት የለኝም። ይህን የምለው "በዚህ ንግግሩኮ ይህንን ነው የፈለገበት" አይነት ትንታኔ ስለሚገጥመኝ ነው። ተወገዘም፣ ተወደሰም የምፈልገው የፃፍኩትን ነው፣ አለቀ። ሌላ ትርጉም የምትሰጡ ሁሉ! ሆነ ብላችሁ አጣማችሁ ሳይሆን መስሏችሁ ብትሳሳቱብኝ ከየትኛውም ቡድን ብትሆኑ ዐፍው ብያለሁ። ሆነ ብሎ ንግግሬን አጣሞ በመተርጎም ለሚከሰኝ ደግሞ ሂሳባችን ከአላህ ዘንድ ነው። እኔንም እናንተንም ልባችንን አላህ ለሐቅ ክፍት ያድርግልን። በሐቅ ላይም ይሰብስበን። ኣሚን። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

naqaa.studio-2cd2c946f998f5d558459f8b9c4eae10(mp3).mp358.26 MB

~*አንድ* *ባለ* *ስልጣን* *ወይም* *ባለሀብት* ያለህበትን ጭንቅና መከራ ተመልክቶ አብሽር እኔ አለሁልህ ቢልህ ምን ይሰማሃል? ደስታ አይደል?! *እንግዲያውስ* የመስጠትም የመንሳትም ስልጣን ፣የ
~*አንድ* *ባለ* *ስልጣን* *ወይም* *ባለሀብት* ያለህበትን ጭንቅና መከራ ተመልክቶ አብሽር እኔ አለሁልህ ቢልህ ምን ይሰማሃል? ደስታ አይደል?! *እንግዲያውስ* የመስጠትም የመንሳትም ስልጣን ፣የመፍጠርም የማጥፋትም ኃይል ፣ የመሸለምም የመቅጣትም መብት ..... ያለው አሏህ ችግርህን በሚገባ ያውቃል ብሶትህንም በሚገባ ይረዳል እናም  እንዲህ ይልሃል፦ *وَبَشِّرِ* *الصَّابِرِين* « *ታጋሾችንም* *አብስር*!» አሏህ ታገስ ሲልህ ባልጠበቅከው መልኩና እጅግ በትልቁ ሊያስደስትህ ነውና ታገስ /ታገሽ እህቴ = https://t.me/httpYelbochMeriQuran

«ኢንተርኔት ፈጣሪው‼️» ------------------------------- በደል ያረገዘ ተፈትሾ ውስጥህ፡ ሚዲያ ፈጣሪው የስራህን ይስጥህ፡ ፕላንህ ይሳከር ይጥፋ መላቅጥህ፡ ፍሬን የበጠሰ መኪና ይዳጥህ‼️ በርግጥ አውቃለሁኝ እንዳለ እልፍ-መልካም፡ ግን ጥመት አብሳሪ ይበዛል ዱካካም፡ የሽርክ አመፀኛ የቢዲዓ እከካም፡ የሚዲያው አለም አይወድም ኸይረኛ፡ ታዋቂ እሚያደርገው መናጢ ሸረኛ፡ ቫይራል የሚያወጣው ባለጌና እረኛ፡ ትኩረት የሚስበው ክፉ መተተኛ!! ብዙ መንጋ ያለው ጦርነት ሰባቂ፡ ሰባኪው ክፋትን በደልን ደባቂ፡ ለዚህ ነው ሚዲያን አምርሬ እማወግዘው፡ ስንቱን ብልጥ በሳል አታሎ አፈዘዘው!? ህዝቤ ሰላም ነበር በNokia ዘመን፡ ሁሉም በየአቅጣጫው አቤት ሲተማመን!? ዛሬማ ሰው ጠፍቶ በኢንተርኔት ተመን!? የፌስቡክ አርበኛ ወይ የቴሌ-ግራም፡ ድስኩረኛ በዝቶ ሞልቶብን ሰካራም፡ ሁሉም ሚዲያ ነው መሬት አንድ አይሰራም፡ ሁሉም በመሰለው እየተቧደነ፡ መንጋነት ዘምኖ ሀቅ እየታደነ፡ ህሌና ደረቀ ልብ ደነደነ፡ ሁሉም ታጋይ ነኝ ባይ ሁሉም ሆኖ አዋቂ፡ መሀይሙ ሁሉ ህብረተሰብ አንቂ፡ የመንጋው ስብስብ ተራ ሰው አድማቂ፡ ስንመራመረው በአርቆ አሳቢ አይን፡ ውሎና አዳራችን ሆኖ በኦን-ላይን፡ በቲክቶክ ተረቶች ሰላማችን ጠፋ፡ ውርደት ተሰራጨ ክፋት በአለም ሰፋ፡ ነውር ጌጥ ሆነብን ሆነ በወረፋ፡ ውሸትና ቅጥፈት ድፍረትም ዘረፋ፡ በሚዲያው አለም ተጀምሯል ይፋ፡ ይህንን እያየሁ እኔም ወጉ ደርሶኝ፡ የሚዲያው አለም ፀፀትን አውርሶኝ፡ ከህልሜ ከእቅዴ ከአላማ አሳንሶኝ፡ አውጥቼው አውርጀው ህሌናዬ ወቅሶኝ፡   የOnline ዘመን ጎድቶኛል አውቃለሁ፡   በዚህም ፀፅቶኝ ይህንን ብያለሁ፡ የቲክቶክን አባት አምርሬ ረገምኩት፡ የፌስቡክን አባት ዘርህ ይምከን አልኩት፡ ምን ብጠቀመውም ብዙ አውድ ብሰራም፡ ሚዲያ መጥፎ ነው ኢሞም ቴሌ-ግራም፡ ከጥቂቶች ውጭ ማንም ኸይር አይሰራም፡ ሁሉም ያሰማናል የውሻሸት ሰበር፡ አሊ-ባባ ያሁ ጎግልና ቫይበር፡ የዘር የክፉ አሳብ የተንኮል ማዲያ፡ ለኔ ዘመን ወጣት ካንሰር ነው ሚዲያ፡ ይህንን ሁሉ ጉዳት አውጥቼው አውርጀው፡ ጥቅምና ጉዳቱን አጥፍቸው አንድጀው፡ ውስጤ ሲብሰለሰል ልቤን ግፍ ሲፈጀው፡ ሁሉን ረገምኩት በመጥፎ ፈርጀው፡ እንደ ሞኝ አፍጥጬ ስልኬ ላይ እንዳረጅ፡ ኢንተርኔት የሚባል የፈጠርከው ፈረንጅ፡ እኔ እሮኬት የለኝ የማስወነጭፈው፡ የአለማት አምላክ ጥርስህን ያርግፈው፡ ሐቅ የምታጠለሽ ተንኮል አቃጣሪው፡ የውሸት ጠበቃ እውነት አባራሪው፡ የበጎነት ጥላት መጥፎ ክፉ ሰሪው፡ የስራህን ይስጥህ ኢንተርኔት ፈጣሪው⁉️     «በጎ ነገሩንም እንዳልዘነጋሁ አስቡ!!»           «በኑረዲን አል-አረብ» http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi

🧷ስራህ ሰው ስላላየው ብቻ ኢኽላስ አለህ አያስብልህም!! ብዙኃኖች ዘንድ የተለመደ ስህተት አመለካከት፦ አንድ ስራ ከሰዎች ዕይታ ስለ ተሰተረ ብቻ በኢኽላስ የተሰራ ይመስላቸዋል። ኢኽላስ፦ ቦታው ልብ
🧷ስራህ ሰው ስላላየው ብቻ ኢኽላስ አለህ አያስብልህም!! ብዙኃኖች ዘንድ የተለመደ ስህተት አመለካከት፦     አንድ ስራ ከሰዎች ዕይታ ስለ ተሰተረ ብቻ በኢኽላስ የተሰራ ይመስላቸዋል። ኢኽላስ፦   ቦታው ልብ ሲሆን ግንኙነቱም ከአላህ ጋ ብቻ ነው። ልብህ የአላህን ፊት ብቻ እስከፈለገ;   ሰላትህ፣ ሰደቃህ፣ ሐጅህ፣ ቂርኣትህ፣ አሕላቅህ አእላፍ ሰዎች ቢያዩት ቢሰሙት የሚጎዳህ ነገር የለም።    በድቅድቅ ጨለማ ማንም ሳያይህ ግንባርህ እስኪላጥ ብትደፋ;    የልብህ ፍላጎት ሌላ ከሆነ አይጠቅምህም። ዋና ቁም ነገሩ ያለው፦    ውስጣዊ ፍላጎትህ ላይ እንጂ የሰዎች ዕይታ ላይ አይደለም!!    [የተደበቀ ስራ ለኢኽላስ ቅርብ መሆን ልብ ይሏል]   

የሴቶች ፈተና በወንድም አቡ ሱፍያን አላህ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው https://t.me/Sle_qelbachn1

"በእንቁላሌ በቀጣሽኝ!" ~ "ከነቢ ሙሐመድ በኋላ ሌላ ነብይ አይመጣም። ይገባሀል አይደል? እንዲህ ተቸገርን። ወልይ ካልኩትስ ምን ትላለህ?" ይሄ እንግዲህ ሰሞኑን በመጅሊሱ መሪ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበ መወድስ ነው። ይህንን ንግግር እንደ ሙስሊም የምንቃወመው የመንግስት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ወይም ያኮረፉ አሕባሾች በሚያዩት መነፅር እየተመለከትን አይደለም። ይልቁንም ከኢስላማዊ መርህ አንጻር ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙስሊም አለመሆን የሚታወቅ ነው። ሙስሊም ያልሆነን አካል በዚህ መልኩ መግለፅ ደግሞ ከባድ ጥፋት ነው። እንኳን ሙስሊም ያልሆነን ሰው፣ ሙስሊም የሆነን ደግ መሪ እንኳ በዚህ መልኩ መግለፅ ድንበር ማለፍ ነው። በኢስላም በደጋጎች ላይ ድንበር ማለፍን የሚያስጠነቅቁ የሸሪዐ ማስረጃዎችና የዑለማእ ማሳሰቢያዎች ብዙ ናቸው። ዛሬ ዛሬ ግን ሙስሊም ባልሆኑ አካላት ላይ ድንበር ስለማለፍ እንድንነጋገር እየተፈረደብን ነው። አላሁል ሙስተዓን! ልብ በሉ! እንዲህ ዓይነት ጥፋት ሲገጥመን የመጀመሪያችን አይደለም። ምን ማለት ፈልጌ ነው? እንዲህ አይነት ጥፋቶችን ማውገዝ ያለብን የጠቅላዩ ሁኔታ ሲደብረንና ስናኮርፍ እየጠበቅን አይደለም። እንዲህ አይነቱ አካሄድ የፖለቲከኛ እንጂ የዲን አካሄድ አይደለም። የአሁኑ የሐጂ ኢብራሂም ጥፋት ጫጫታ የበዛበት ጥፋቱ ከባድ ስለሆነ ብቻ አይደለም። ይልቁንም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያኮረፈው ህዝብ ስለበዛ ነው። እንጂ ከዚህ ጥፋት ጋር ተመሳሳይ ወይም የሚቀርቡ ብዙ ጥፋቶች ከዚህ በፊት ተፈጽመዋልኮ። ያኔ ግን ልክ እንዳሁኑ የሐጂ ኢብራሂም ሁኔታ አብዛኛው ህዝብ ምርቃና ላይ ነበር። በዚያን ሰሞን ስለ ጠቅላዩ የተባሉትን ላስታውሳችሁ:- * አደም ካሚል፡ "ሙሳም ቢመጡ፣ ዒሳም ቢመጡ ፣ ነብያችን ሙሐመድም ቢመጡ..." እያለ ዘግናኝ ንፅፅር ሲሰራ አይተናል። ያኔ ይህንን ንግግር ስንተች አሁን ከሚንጫጫው ውስጥ ቀላል የማይባለው ሲሰድበን ነበር። ሌላው ደግሞ ጥፋቱን እንዳላየ እንዳልሰማ ፀጥ ብሎ ነበር። የአደም ካሚል ንግግር ከአሁኑ የመጅሊሱ መሪ ንግግር ያነሰ ነው ወይ? * የ"ሙፍቲ" ዑመር ደጋፊዎች በአሁኑ የሐጂ ኢብራሂም ጥፋት ጮቤ ሲረግጡ እያየን ነው። "ሙፍቲው" ጠቅላይ ሚኒስትሩን "ከሰማይ የወረደ መለይካ ይመስላል" ያሉበትን የረሳን መስሏቸው ይሆን? ወይስ ይሄኛው ጥፋት ቀላል መስሏቸው ነው? "መለስ የጀነት ነው" ሲል የነበረው የነ ያቁተል ዐርሽ ጀማዐ ዝም ቢል ይሻለው ነበርኮ። * "ያ በዲዐ ዘማን" የሚል ረጅም መወድስ በዐረብኛ የፃፈ ዳዒያም አለ። አሁን ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ኢማም መሰለኝ። የአፄዎቹን ዜና መዋእል ሲፅፉ የነበሩትን ደብተራዎች የሚያስታውስ አካሄድኮ ነው የሄዱት። * ጠቅላዩ ሙስሊም ነኝ ባላለበት "ከፊርዐውን ቤት የወጣ ሙሳ ነው"፣ "ከዑመር ብኑ ዐብዲል ዐዚዝ ወዲህ አምሳያው አልታየም"፣ "ከዐረብ መሪዎች ይሻላል"፣ "ከሸይኽ ረቢዕ ይሻላል" እየተባለ ሲፃፍ አይተናልኮ። * አቡበክር አለሙ:- (إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاهُ عَلَيْكُمْ وَزَادَهُ بَسْطَةً فِي الْعِلْمِ وَالْجِسْمٌِ) በማለት ስለ ጧሉት በቁርኣን የተወሳውን ሙስሊም ላልሆነው ሰው ሲሸልም ነበር። * የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ልክ እንደ ደዕዋ መስጂድ ውስጥ ከፍተው በማይክ ሲያሰሙ የነበሩ አካላት አሉኮ። የሚገርም እብ^ ደትኮ ነው ያለፈው። * "መኖር ከጀመርን ገና ሶስት ወራችን" እስከማለት የደረሱም ነበሩ። እንዲያውም ይሄ በንፅፅር ቀላሉ ነው። ይሄ ሁሉ ሲሆን "ኧረ አላህን እንፍራ!" በማለት ባደባባይ ደፍሮ የተናገረ ምን ያህል ሰው ነበር?! በሃገራችን አንድ አባባል አለ። ልጅ ከጎረቤት እንቁላል እየሰረቀ ሲያመጣ እናት እየተቀበለች ስትበላና ስታበላ ቆይታ፣ ልጅ አመሉ ስር ሶዶ አ^ህያ ሰርቆ ይያዛል። አ^ህያው ላይ አስቀምጠው በህዝብ መሀል "እኔን ያየ ይቀጣ" እያስባሉ ሲያዞሩት እናት አይታ ስትሸማቀቅ ልጅ ምን አላት? "በእንቁላሌ በቀጣሽኝ!" ብቻ የሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ዘግናኝ ንግግር ጥፋትነቱ ለማንም የማይሰወር ነው። እንደምናየውም ብዙ ሰው እየጮኸበት ነው። ከመሆኑም ጋር ትኩረት የሚሹ ነገሮች አሉ። 1ኛ፦ የሐጂ ኢብራሂም ንግግር በሐዲሥ የተገለፀው "አላህ ሆይ! አንተ ባሪያዬ ነህ፤ እኔ ጌታህ ነኝ" በማለት በደስታ ብዛት እንደተሳሳተው ሰው አይነት ጥፋት ነው የሚል አይቻለሁ። ይሄ በጭራሽ ልክ አይደለም። በሐዲሡ ላይ የተገለፀው ሰውየኮ አስቦበት አይደለም ጥፋቱን የተናገረው። ሳያስበው ነው በስህተት ያመለጠው። ያሁኑ እንደዚያ እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡ በምርቃና/ በነሻጣ መናገር እና ሳያስቡት የሆነ ቃል ማምለጥ የተለያዩ ናቸውኮ። ደግሞም ጥፋቱ ሲስሰማ መደንገጥና ማረም ሳይሆን በተክቢራ ማጀብ ነው የተሰማው። ስለዚህ የጥፋቱን ክብደት ለማቃለል አላስፈላጊ ንፅፅር መጠቀም ተገቢ አይደለም። ተሰራ የተባለው ልማት በዚህ ደረጃ 0ቅልን የሚያስት አድርጎ ማቅረቡም ሌላ የሚገርም ነገር ነው። 2ኛውና ዋናው ማንሳት የምፈልገው በመንግስትም ሆነ በመጅሊስ ኃላፊነት ላይ በየተዋረዱ ላላችሁ መልእክት ማስተላለፍ ነው። እንዲህ አይነት የእምነትን መርሆዎች እየጨፈለጉ ሰዎችን ማወደስ የምታስቡትን ትርፍ ሊያስገኝላችሁ ቀርቶ ውርደትና መንናቅን ነው የሚያመጣባችሁ። አንደኛ ህዝብ ይተፋችኋል። ይሄ ትልቅ ኪሳራ ነው። ሁለተኛ በሹማምንቱም ዘንድ ያስንቃችኋል። ትልቁ አደጋ ደግሞ ከአላህ ጋር መጣላታችሁ ነው፡፡ በተሳሳተ መንገድ ጥቅምንና ክብርን መሻት ውርደትን ነው የሚያመጣው። 3ኛ፦ እንዲህ ዓይነት ጥፋት ሲከሰት በምንም መነሻና ማመሀኛ መከላከል አይገባም። ቢያንስ ዳግም እንዳይደገም ጥፋቱን ማመንና ጫን አድርጎ መነጋገር ነው የሚሻለው። (አንዳንዶች እንደሚሉት ማስተካከያ ይሰጣሉ ብዬ አልገምትም። ከሆነ ቀላል ነገር አይደለም።) ይልቅ እነዚህ የሚያሳቅቁ ጥፋቶች እንዲቆሙ ጫና መፍጠር ነው የሚሻለው። ከሁለት ዓመት በፊት እዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተናገርኩትን ደግሜ ልናገር፦ "አንዳንድ በመጅሊስ አመራሮች ሚዲያ ላይ የሚቀርቡ ንግግሮች የሚያሳቅቁ ናቸው። አድማጭን የሚያሳቅቅ ወይም ከዲን ጋር የሚጋጭ ንግግር ከሚወጣ ወይ ቀድሞ መዘጋጀት አልያ ፅፎ ማንበብ ይሻላል።" ያሁኑ ይባስ! የሆነ ሆኖ ጩኸታችን መርህ ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል። ውግንናችንም ሆነ ተቃውሟችን እንደ ሙዳችን የሚቀያየር መሆን የለበትም። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መንግስት ለሙስሊሞች ያለው ቀረቤታና አያያዝ ካለፉት ስርአቶች ይሻላል ወይስ ይብሳል በሚለው ላይ አተያያችን ልዩነት እንደሚኖረው የሚጠበቅ ነው። ችግሩ ግን ደጋፊውም ሆነ ተቃዋሚው በአመዛኙ "እኔ የያዝኩትን አቋም ካልያዛችሁ" የሚል ፅንፈኛ ነው። የፈለገ ቢሆን ግን ድጋፍም ይሁን ተቃውሞ ዐቅል ሊያሳጣን አይገባም። በዚህ አጋጣሚ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት የሐጂ ኢብራሂምን ንግግር በማስታከክ እንደለመዱት "ወሃ^ቢያ" እያሉ እያላዘኑ፣ "ሙፍቲ ዑመር አማራ ስለሆኑ ነው የተገለሉት" እያሉ ወደ ኋላ ተመልሰው ሙሾ እያወረዱ እያየን ነው። እነ አባይ ፀሐዬን እየቀሰቀሰ ህዝበ ሙስሊሙን ለማስመታት ሲሰራ እንደነበረ በራሱ አንደበት የመሰከረን አካል በመና ^ፈቅ የምንቆዝም እንዳይመስላችሁ። የዛሬ ጥፋት ትናንትን አያስናፍቀንም። የዛሬን ለማውገዝ ትናንት ውስጥ አንወሸቅም። በግራም በቀኝም ካለ የዘር ትብታብም ውስጥ አንገባም። ችግር ያለበት ባይጠፋም፣ አብዛኛው ሙስሊም የትናንቱም የዛሬውም ጥፋት ያለምንም ሽፋን

•• እንዴት ያለን ሚስኪን ነን.. ራሳችንን ለማስተካከልና የአላህ ቅርብ ሰው ለመሆን እየታገለን ያለን ይመስለናል ነገር ግን የሆነ ወንጀል በተመቻቸለን ጊዜ እንወድቅበታለን ❗️🌿.