fa
Feedback
هداية القلوب (የልቦች መሪ)

هداية القلوب (የልቦች መሪ)

رفتن به کانال در Telegram

https://t.me/httpYelbochMeriQuran

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
228
مشترکین
-124 ساعت
+197 روز
+1430 روز
آرشیو پست ها
ስለ ዒልም አገብጋቢነት
🔖በወንድም ዐብደል ዉሀብ حفظه الله

🔖የዱንያ ስንቅ በአላቂዋ ህይወት ውስጥ ወደምትፈልጋቸው ነገሮች ያደርስሃል‥ ⇘የአኺራው ስንቅ ደግሞ በዘውታሪዋ ህይወት ውስጥ ወደምትመኛቸው ፀጋዎች ያደርስሃል ። (وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ) " ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው ፡፡" [📚አል-በቀራህ 197] t.me/SleSlkachin

ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ሌሎችን ያስታውስ!!!! "ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው፣ ያንን መልካም ስራ እንደሰራው ሰው አይነት ምንዳ (አጅር) አለው።"

ግልፅ ውይይት በ ቀጥታ ስርጭት በ ኡስታዝ ኸድር አህመድ እና አቡዘር መካከል። ብዙ ጠቃሚ አንገብጋቢ ርዕሶች አሉበት ይደመጥ ። ሙሉውን ለማዳመጥ ገብተው መከታተል ይችላል 👇

ሰው አወደሰህ አላወደሰህ ምንም አይጠቅምህ፤ምንም አይጎዳህ። የሰዎች ውዳሴ ረሃብ አያስታግስ፤ ነውርን አይሸፍን። ከሸይኽ ረስላን  መልእክት የተወሰደ🤌 •┈┈┈❁┈•✿❁📚❁✿•┈❁┈┈┈• 🔗رابط القناة على التيليجرام :

ተጋበዙ ደግሞ ሸር አድርጉ

" የምርመራው ቀን ማን ሂሳብ ይስራልህ ተብየ በአላህና በወላጆቼ መካካል ምርጫ ቢሰጠኝ አላህ እንደተሳሰበኝ እመርጣለሁ " ። ሐማድ ብን ሠለመህ በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ትልቅ አምልኮ ነው ። በሁለም ነገራችን በአላህ ውሳኔ ደስተኛ እንሁን የዛኔ ቀልብ ይረጋጋል ። አላህ ማለት ከነፍሳችን ፣ ከወላጅ እናታችን በላይ አዛኝ ነው ።

🔖የዱንያ ስንቅ በአላቂዋ ህይወት ውስጥ ወደምትፈልጋቸው ነገሮች ያደርስሃል‥ ⇘የአኺራው ስንቅ ደግሞ በዘውታሪዋ ህይወት ውስጥ ወደምትመኛቸው ፀጋዎች ያደርስሃል ። (وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ) " ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው ፡፡" [📚አል-በቀራህ 197] https://t.me/httpYelbochMeriQuran

ማንም ሳይያይህ ሌሊት ተነስተህ የሰገድከው ሶላት በድብቅ የሰጠኸው ሶደቃ እየራበህና እየጠማህ የፆምከው ፆም ላማኸውና ስሙን በመጥፎ ላነሳኸው ሰው ሲሰጥ አያሳዝንህም?

﴿وَجَعَلْنَا لَهُ نُورًا يَمْشِي بِهِ فِي النَّاسِ﴾
«أي: يَهْتَدِي بِهِ كَيْفَ يَسْلُكُ، وَكَيْفَ يَتَصَرَّفُ بِهِ. وَالنُّــورُ هُوَ: الْقُـــرْآنُ»
تفسير ابن كثير

♻️ ወደ ሐራም አከታትለህ አትመልከት !
ኢማናዊ ቆይታ
☑️ ጠላትህ ዝግጅቱን አጠናቋል ። በተጠንቀቅም ይጠባበቃል ። ቀስቱን ደጋኑ ላይ ወድሯል ። ቀስቱንም አስወነጨፈ ። ኢላማውን መታ .... መርዙ በመላ አካል ውስጥ ለመሰራጨት ግዜ አልፈጀበትም ። ልብ ታመመ ፤ ምላስ ተናገረ ፤ እግር ተራመደ ፤ አካል ተንቀሳቀሰ እናም ሁሉም ነገር በፍጥነት ተፈፀመ ። እይታ ... ፈገግታ ...ሰላምታ ... ንግግር ...ቀጠሮ ... ግንኙነት

ቁርአንን የሚወድ ሰው ዝም ሲል ሃሳቡ ቁርአን ነው የሚያሳስበው ነገር ቁርአኑን ብቻ ነው አንድ ሰው አንድ ነገር ሲወድ ዝም ሲል ከነፍሱ ጋር የሚያወራው ስለሚወደው ነገር ብቻ ነው ብቻውን ሲሆንም የሚጽናናው ስለሚወደው ነገር እያሰበ ነው

​🌱 ሁልጊዜ አስታውስ፦ የምትጓዝበት መንገድ ሁሉ.. ስኬት ወይም ውድቀት ሊገጥመው ይችላል፤ ወደ ቁርአን የሚወስደው መንገድ ብቻ ሲቀር! እሱማ በየአቅጣጫው በምንዳ (በአጅር) የተከበበ ነው፣ እንኳን በደንብ አንብበኸው ቀርቶ እየተንተባተብክበት እንኳ አጅር ታገኝበታለህ። ስለዚህ ካላችሁበት (ከቁርአን መስመር) ፈቀቅ አትበሉ፣ በአላህ እምላለሁ! እሱ አላህ ዘንድ ታላቅ ቦታ አለው። የቁርአን ባለቤቶች ሆይ! ፅኑ። ጌታችን ሆይ! እገዛህን፣ ቀጥተኝነትን፣ ፅናትን፣ ቁርጠኝነትን እና ስራችንን ለአንተ ብቻ ማጥራትን (ኢኽላስን) እንለምንሃለን። https://t.me/httpYelbochMeriQuran

"የራሱን ጉድ ሸፍኖ የሰውን ያነሳል!" የለተሞ ጀመዓ አክቲቪስት የሆነው ባህሩ ተካና በስሩ ያሉ ተከታዮቹ የስለፊዮችን አንድነት ለመከፋፈል በሚያደርጉት ጥረት ሌላውን "ሙብተዲዕ፣ ሙመይዕ፣ መጅሊስ የገባ" እያሉ በቢድዓ ሲፈርጁ ይኖራሉ። ራሳቸውን እንደ ንጹሕና ከጥፋት የራቁ አድርገው ለማቅረብ ቢሞክሩም፣ መሬት ላይ ያለው እውነት ግን የራሳቸውን ጥልቅ ግብዝነትና አቋም አልባነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። በጉራጌ ዞን የሚገኙት አብዛኞቹ የባህሩ ተካ ተከታዮች ራሳቸው "ኢኽዋን" ወይም "ሙመይዓ" በሚሏቸው ሰዎች ድጋፍ የሚተዳደሩና አብረዋቸው የሚሰሩ ናቸው። አስፈላጊ ከሆነ በጌቶ፣ በጉመር፣ በቸሃ፣ በእነሞርና በሌሎችም ወረዳዎች የሚገኙ የለተሞ ጀመዓ አባላት መጅሊስ ውስጥ ካሉና "የተበደዑ" ከሚሏቸው አካላት ጋር አብረው እንዴት እንደሚሰሩ አንድ በአንድ ይፋ ማድረግ እንጀምራለን። እንኳን ተከታዮቹ ይቅርና፣ ጉንችሬ የሚገኘው የባህሩ ተካና የለተሚዮች ዋና መፈልፈያ ማዕከል ሳይቀር ዋና ድጋፍ ሰጪዎቹ እነማን እንደሆኑ ይፋ ሲደረግ እውነተኛው "ሙመይዕ" ማን እንደሆነ ህዝቡ አይቶ ይፈርዳል። ለሌላው አካል በሌለበት ስም እየሰጡ በቢድዓ የሚፈርጁት እነዚህ አካላት፣ ራሳቸው ጥፋት ውስጥ ተዘፍቀው ሳለ ሌላውን በመክሰስ ራሳቸውን ለማጥራት መሞከራቸው የግብዝነት ጥግ ነው። ሼር በማድረግ አድርሱላቸው :: ሁላቸውም በማን ተቀጥሮና ከማን ጋር እንደሚሰሩ ስለሚያውቁ ቢያንስ አፋቸውን ይቆጥቡ ዘንድ ይጠቅማል:: https://t.me/Menhaje_Selef/

✅ከሰለፎች አንደበት! ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (🤎) እንዲህ ይላሉ፦ ﴿فإن الصلاة عليه (🤎) من أعظم الوسائل التي بها يُستجاب الدعاء، وقد أمر الله
✅ከሰለፎች አንደበት! ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (🤎) እንዲህ ይላሉ፦ ﴿فإن الصلاة عليه (🤎) من أعظم الوسائل التي بها يُستجاب الدعاء، وقد أمر الله بها، والصلاة عليه في الدعاء هو الذي دلّ عليه الكتاب والسنة والإجماع﴾ “በነቢዩ (🤎) ላይ ሰለዋት ማውረድ ዱዓእ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከሚያደርጉ ታላላቅ መዳረሻዎች ውስጥ ትልቁ ነው። አላህም በዚህ ላይ አዟል። በዱዓእ ውስጥ ሰለዋት ማድረግ በቁርዓን በሐዲስና በኡለማዎች ሙሉ ስምምነት የተረጋገጠ ነገር ነው።” 📚 መጅምዑል ፈታዋ፡ 1/347 Join: 📱Telegram Follow: 📱facebook

የልብ እረፍት ሁለት ሰከንድ "ኢስቲግፋር" በማለት የምታሳልፋትን አንዲት ቅጽበት በከንቱ አትቁጠራት። ከዚያች አጭር ቅጽበት ስንት የእዝነትና የሲሳይ በሮች እንደሚከፈቱልህ፣ ስንት የመከራና የፈተና ጭንቀቶችህ እንደሚገፈፉ አታውቅም። https://t.me/httpYelbochMeriQuran

አንዳንድ ነገር የሚዘገየው ለመጥፋት አይደለም… ምናልባት አላህ ከአንተ የዘገየው ነገር አንተ ከምታስበው በላይ በሚያምር መንገድ እንዲመጣ እያዘጋጀው ይሆናል። ስለዚህ የዘገየውን አትርገም፣ የተዘጋውን
አንዳንድ ነገር የሚዘገየው ለመጥፋት አይደለም… ምናልባት አላህ ከአንተ የዘገየው ነገር አንተ ከምታስበው በላይ በሚያምር መንገድ እንዲመጣ እያዘጋጀው ይሆናል።     ስለዚህ የዘገየውን አትርገም፣ የተዘጋውን በግድ አትክፈት፣ ያልሆነውንም ለምን ብለህ ልብህን አትድክም። አላህ የጻፈልህ ነገር ከአንተ አይርቅም፤ ያላልተጻፈልህም በምንም መንገድ ወደ አንተ አይመጣም። ልብህን አሳርፍ… የአላህ እቅድ ከአንተ እቅድ ይበልጣል።

ደካማ ወንዶች ትኩረታቸውን በሴቶች ላይ ያደርጋሉ፤ ሴቶችም ትኩረታቸውን በጠንካራ ወንዶች ላይ ያደርጋሉ፤ ጠንካራ ወንዶች ግን ትኩረታቸውን በዓላማቸው ላይ ያደርጋሉ። ስለዚህ ወንድሜ፣ ትኩረትህን በዓላማህ ላይ አድርግ፤ ጊዜህን አታባክን፣ ራስህን ገንባ፣ ዓላማህንም እስክታሳካ ድረስ በጽናት ቀጥል። አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba