es
Feedback
قَنَاةُ أَبِي عِمْرَانْ الْأَثَرِيِّ الْوَلوي (MURAD)

قَنَاةُ أَبِي عِمْرَانْ الْأَثَرِيِّ الْوَلوي (MURAD)

Ir al canal en Telegram

وَأَنَّ السَّاعَةَ آتِيَةٌ لَا رَيْبَ فِيهَا وَأَنَّ اللَّهَ يَبْعَثُ مَنْ فِي الْقُبُورِ ﴿٧﴾ https://t.me/+EMcH10oKjWdjZDVk Like share ለአስተያየተዎ እና ለጥያዎ @Abuimrann34352bot

Mostrar más
4 990
Suscriptores
-424 horas
+207 días
+3530 días
Archivo de publicaciones
يقولُ النَّبيُّ ﷺ: من غسَّلَ يومَ الجمعةِ واغتسلَ ثمَّ بَكَّرَ وابتَكرَ ومشى ولم يرْكب ودنا منَ الإمامِ فاستمعَ ولم يلغُ كانَ لَهُ بِكلِّ خطوةٍ عملُ سنةٍ أجرُ صيامِها وقيامِها. خلاصة حكم المحدث : صحيح

📌በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የደርስ ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት 📖«نُورُ التَّوْحِيدِ وَظُلُمَاتُ الشِّرْكِ» 📖ኑሩ ተውሂዲ ወዙሉማቱ ሽርኪ) ተ          ጀ               መ                          ረ      🎙በወንድም አቡ ኢምራን          ሐፊዘሁላሁ ተዓላ 👇ገባ ገባ በሉ ሸር ሸር አድርጉ https://t.me/sobabilelmesjide?videochat=a2a44a272416e9161a https://t.me/sobabilelmesjide?videochat=4a796df85d78ac6362

وعن عبدِ اللَّه بنِ عمرو بن العاص رضي اللَّه عنهما أَن رسول اللَّه ﷺ قال : «الدُّنْيَا مَتَاعٌ ، وَخَيْرُ مَتاعهَا المَرْأَةُ
وعن عبدِ اللَّه بنِ عمرو بن العاص رضي اللَّه عنهما أَن رسول اللَّه ﷺ قال : «الدُّنْيَا مَتَاعٌ ، وَخَيْرُ مَتاعهَا المَرْأَةُ الصَّالحةُ » رواه مسلم .  

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት ተ⭐️       ጀ🔴             መ⭐️                    ረ🔴 ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም! ሊንኩን ለሌሎችም ሼር አድርጉት 📥📥📥📥📥📥📥📥 https://t.me/Asselefiyah_Channel

وكلُّ سَهلٍ إذا لم يُوَفّّق الله صَعب.
وكلُّ سَهلٍ إذا لم يُوَفّّق الله صَعب.

ግን የኔ ቻናል 5k የምትሆነው መቼ ነው አረ ተው ግን ሸር አድርጉ

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ። የጀሀነም በር ጠባቂ መላዒካ ማሊክ ይባላል፡፡

ሁላችንም ይችን ቦታ አንድ ቀን እንረከባታለን ወላሂ
ሁላችንም ይችን ቦታ አንድ ቀን እንረከባታለን ወላሂ

⚠️ አስተውሉ❗️ በእስልምና የመጀመሪያው ኸሊፋ ማን ነው?

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ሰለፍይ ወሰለፍያት እህት ወንድሞች ኢንሻአሏህ ነገ ረቡዕ ምሽት ሙሀደራ ፕሮግራም ይኖረናል ፡፡ ⏰"በዕለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን ➊ ኡስታዝ አቡ ሀሳን
    السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ሰለፍይ ወሰለፍያት እህት ወንድሞች ኢንሻአሏህ ነገ ረቡዕ ምሽት ሙሀደራ ፕሮግራም ይኖረናል ፡፡ ⏰"በዕለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን ➊ ኡስታዝ አቡ ሀሳን 🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል ➋ ኡስታዝ አቡ ሻኪራ                🔖ርዕስ ​"በሰዓቱ ❸ ኡስታዝ አቡ ኡባይዳ 🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል ❹ ወንድም አቡ ሂበቱላህ 🔖ርዕስ "በሰዓቱ ❺ ኡስታዝ አቡ አመቲ ረህማን             🔖ርዕስ በሰዓቱ ❻ ወንድም አቡ ሹራ 🔖ርዕስ በሰአቱ ይነገራል ❼ ወንድም ኑረድን አቡ ፋሩቅ 🔖ርዕስ "በሰአቱ ይነገራል ❽ ወንድም አቡ ኢምራን 🔖ርዕስ "በሰአቱ ይነገራል 📖ቲላዋ የሚጋብዙ ወንድሞች 🎤ወንድም አቡ ኢምራን 🎤ወንድም አቡ ሀይደር 🎙 የፕሮግራሙ መሪ ወንድም አቡ ማሂ 🗓ቀን እለት ረብዑ ምሽት             ⏰ ሰአት           🇪🇹በኢቶ 3:00            🇸🇦በሳዑዲ 9:00              🇵🇸በዱባይ 10:00 ፕሮግራሙ የሚካሄድበት ሊንክ👇                 👇👇👇👇👇 https://t.me/Asselefiyah_Channel https://t.me/Asselefiyah_Channel

📌በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የደርስ ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት 📖«نُورُ التَّوْحِيدِ وَظُلُمَاتُ الشِّرْكِ» 📖ኑሩ ተውሂዲ ወዙሉማቱ ሽርኪ) ሊ          ጀ               መ                          ር     ነው 🎙በወንድም አቡ ኢምራን          ሐፊዘሁላሁ ተዓላ 👇ገባ ገባ በሉ ሸር ሸር አድርጉ https://t.me/sobabilelmesjide?videochat=8f387d20fa80c37aad

መስከረም ሲመጣ የግቢው አየር ሁሉ አዲስ ተስፋና መንፈስ ይዞ ነው የሚመጣው። ከረዥም የክረምት እረፍት በኋላ ወደ ግቢ ስመለስ፣ የደብተሩና የመፅሃፉ ሽታ ሳይሆን ከምንም በላይ ህሊናዬን የሚሞላው ያ ያሳለፍነው ወርቃማ ጊዜ ነው። ​የምር... ከካፌ ምሳችንን በልተን ወጣ ስንል፣ በያለንበት ተሰብስበን "ሀያ አለስ-ሶላህ" ጥሪን ተቀብለን በጅምላ ወደ መስጂድ የምንተመው ያ ጀምዓ ዛሬ በፅኑ ናፍቆኛል። ​ያ ሁሉ ተማሪ፣ ከአንዱ ህንፃ ወደ ሌላው ህንፃ ሳያይ፣ በአንድ አቅጣጫ በፍቅርና በደስታ ተያይዞ ወደ አላህ ቤት ሲገሰግስ የነበረው ትዕይንት ሁሌም በፊቴ ይዞራል። መንገድ ላይ እየተጫወትን፣ እየሳቅን፣ የትምህርቱንም ሆነ የህይወቱን ነገር እየተመካከርን የምናደርገው ያ አጭር ጉዞ... በወቅቱ ተራ ይመስል ነበር፤ ዛሬ ግን ትልቅ የህይወት ሀብት እንደነበረ ይገባኛል። ​መስጂድ ደርሰን ሶላታችንን አድርሰን ስንወጣ፣ በክበብ ተቀምጠን የምናወራው ያ ንጹህ ጭዋታ፣ የእርስ በእርስ ተቆርቋሪነትና እውነተኛ ወንድማማችነት የትም የማይገኝ ውብ ትዝታ ነው። ​ከተለየኋችሁ ገና የቅርብ ጊዜ መስሎኝ ነበር፤ ቀናቱ ግን ሳላስበው ነጉደው በቁጥርም ቢሆን አመት ወደሚለው ገቡ። ሳምንታትና ወራት ሲቀያየሩ "ገና ትላንት ነበር" እያልኩ ራሴን አማክራለሁ። በትዝታው ማዕበል ውስጥ ሆኜ ልቤ ሲመታብኝና ናፍቆታችሁ አቅሜን ሲፈታተነው ነው እንግዲህ ይህችን አጭር መልእክት የጫርኩት። ​ጊዜው አልፏል፣ የግቢው ህይወትም ከኋላችን ቀርቷል፤ ነገር ግን የመስከረም ወር በመጣ ቁጥር ያ የጀምዓችን ፍቅርና ወደ መስጂድ የተመምነው ያ ውብ ጊዜ እስከዛሬ ልቤ ውስጥ እንደ አዲስ ይነዝራል። ​በእውነት... ከአንደበቴ ከሚወጣው ቃል በላይ አብዝቼ ነው የምወዳችሁ! የትም ሁኑ የት፣ አላህ በጥበቃው ስር ያድርጋችሁ፤ እንደገና በፍቅርና በደስታ የምንገናኝበትን ቀን በጉጉት እጠብቃለሁ።

ሰው ከተለገሳቸው እጅግ ውብ ነገሮች አንዱ፦ አላህን የሚፈራ፣ የሚቀናበት/ባታል፣ ዋጋውን/ዋን የሚያውቅ፣ እናም ከቅልቅል፣ ከመዝሙር/ዘፈንና ከእፍረት ማጣት ረከሰቶች እርቆ ከፈተና ቦታዎች እንዲጠበቅ
ሰው ከተለገሳቸው እጅግ ውብ ነገሮች አንዱ፦ አላህን የሚፈራ፣ የሚቀናበት/ባታል፣ ዋጋውን/ዋን የሚያውቅ፣ እናም ከቅልቅል፣ ከመዝሙር/ዘፈንና ከእፍረት ማጣት ረከሰቶች እርቆ ከፈተና ቦታዎች እንዲጠበቅ የሚጓጓ የህይወት አጋር ማግኘት ነው። ​• ይህ የበላይነት ማሳየት ወይም ማጨናነቅ ሳይሆን፣ በዲን ላይ ከመፍራትና ቤቱ ከፈተና ቦታዎች የራቀ ሆኖ እንዲቀጥል ከመጓጓት የመጣ ነው። ​• ነገር ግን በትዳር አጋሩ ላይ አላህን የማይፈራ፣ ክብርን የማይጠብቅ፣ ደረጃን የማያውቅ፣ እንዲሁም በመጀመሪያው አጋጣሚ የሚዋሽ ወይም የሚከዳ፤ እርሱ ምንኛ የከፋ ባልና አጋር ነው! እርሷም ምንኛ የከፋች ሚስትና አጋር ናት! ​• ስለዚህ መልካም መረጣን ምረጡ። ​• ውበትን ብቻ አትፈልጉ፣ ሀብትን ብቻ አትፈልጉ፣ ውብ ንግግርን ብቻ አትፈልጉ፤ ይልቁንም ዲንን፣ ትክክለኛውን ዐቂዳ፣ አላህን መፍራትን (ተቅዋን)፣ መልካም ስነ-ምግባርንና ታማኝነትን ፈልጉ። ​• ምክንያቱም ደግ ባል ዝም ብሎ ባል አይደለም፤ ደግ ሚስትም ዝም ብላ ሚስት አይደለችም። ​• ይልቁንም ሁለቱም ከአላህ በመቀጠል ለሌላው ደጋፊ፣ በመታዘዝ መንገድ ላይ አብሮ ተጓዥ፣ በዱንያ እረፍት፣ እና ልጆችን በቁርኣንና በሱና ላይ በሰለፎች (ቀደምት ደጋግ ሰዎች) ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ አጋር ናቸው። ​• አላህ ደግ ባልን ወይም ደግ ሚስትን የለገሰህ/ሽ እንደሆነ፣ በዚህ ጸጋ ላይ አላህን አመስግን/ኚ፣ ጠብቀው/ቃት፣ መልካም አኗኗርንም ኑር/ሪ። ​• ቤታችሁን ስትገቡበት ሰላም የሚሰማው፣ ቁርኣን የሚሰማበት፣ እና አንደኛችሁ ሲደክም ሌላው እጁን ይዞ የሚያበረታታበት ቤት አድርጉት፤ ይህም ሰው በዚህች ዱንያ ከተለገሳቸው እጅግ ውብ ነገሮች አንዱ ነው። አላህ ከመልካሞች ያድርገን

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ሰለፍይ ወሰለፍያት እህት ወንድሞች ኢንሻአሏህ ነገ ረቡዕ ምሽት ሙሀደራ ፕሮግራም ይኖረናል ፡፡ ⏰"በዕለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን ➊ ኡስታዝ አቡ ሀሳን
    السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ሰለፍይ ወሰለፍያት እህት ወንድሞች ኢንሻአሏህ ነገ ረቡዕ ምሽት ሙሀደራ ፕሮግራም ይኖረናል ፡፡ ⏰"በዕለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን ➊ ኡስታዝ አቡ ሀሳን 🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል ➋ ኡስታዝ አቡ ሻኪራ                🔖ርዕስ ​"በሰዓቱ ❸ ኡስታዝ አቡ ኡባይዳ 🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል ❹ ወንድም አቡ ሂበቱላህ 🔖ርዕስ "በሰዓቱ ❺ ኡስታዝ አቡ አመቲ ረህማን             🔖ርዕስ በሰዓቱ ❻ ወንድም አቡ ሹራ 🔖ርዕስ በሰአቱ ይነገራል ❼ ወንድም ኑረድን አቡ ፋሩቅ 🔖ርዕስ "በሰአቱ ይነገራል ❽ ወንድም አቡ ኢምራን 🔖ርዕስ "በሰአቱ ይነገራል 📖ቲላዋ የሚጋብዙ ወንድሞች 🎤ወንድም አቡ ኢምራን 🎤ወንድም አቡ ሀይደር 🎙 የፕሮግራሙ መሪ ወንድም አቡ ማሂ 🗓ቀን እለት ረብዑ ምሽት             ⏰ ሰአት           🇪🇹በኢቶ 3:00            🇸🇦በሳዑዲ 9:00              🇵🇸በዱባይ 10:00 ፕሮግራሙ የሚካሄድበት ሊንክ👇                 👇👇👇👇👇 https://t.me/Asselefiyah_Channel https://t.me/Asselefiyah_Channel

إذا لم تتزوج من تعينك على دينك ودنياك فبقاؤك عازب خير لك በዲንህም ሆነ በዱንያህ የምታግዝህን ሴት ካላገባህ... ላጤ ሁኖ መቅረትህ እጅጉን የተሻለ ነው። ✍🏼ሞሮኮአዊው ኡስታዝ ያሲን ኡምሪ t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

➵በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የደርስ ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት በኡስታዝ አበል ሁበይብ ሚንሀጅ ፊርቀቱል ነጂያ ደርስ ሊ        ጀ               መ                          ር ገባ ገባ በሉ ሸር ሸር አድ አድርጉ t.me/sobabilelmesjide?videochat=c42e18a35fffc2daf4 https://t.me/sobabilelmesjide?videochat=ceb38d4b752e8119d8

ውዱ ነብያችን ሲያርፉ በሚስታቸው እቅፍ ውስጥ ሆነው ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ሚስት እስከመጨረሻው መንገድ ድረስ የሕይወት ጓደኛ መሆኗን ነው፡፡ ከሷ ውጭ ማን አለህ? እሷስ ካንተ የበለጠ ማን አላት?
ውዱ ነብያችን ሲያርፉ በሚስታቸው እቅፍ ውስጥ ሆነው ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ሚስት እስከመጨረሻው መንገድ ድረስ የሕይወት ጓደኛ መሆኗን ነው፡፡ ከሷ ውጭ ማን አለህ? እሷስ ካንተ የበለጠ ማን አላት? ባል ሲታመም ሚስቱ ምን ያህል እንደምትወደው ይገነዘባል፡፡ ሚስት ስትደክም፣ ስትሰበር፣ ስትተክዝ ... ባል ምን ያህል እንደሚያስብላት ትረዳለች፡፡ በማስመሰል ዓለም እየኖራችሁ እውነተኛውን ዓለም አትርሱ፡፡ ለማኅበራዊ ሚዲያው ሰፊ ጊዜ እየሠጣችሁ ማኅበራዊ ኑሮውን አትዘንጉ፡፡ እውነተኛውን ቤት መገንባት ትታችሁ የውሸት ፎቅ አትሥሩ፡፡ በሶሻል ሚዲያ ከሺዎች  በላይ ሰው ይከተለኛል፡፡ በታመምኩ ጊዜ ግን ከጎኔ የምትሆነው ሚስቴ ብቻ ናት፡፡😊

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ። የጀነት በር ጠባቂ መላዒካ ረድዋን  ይባላል፡፡

ከአባቷ እና ከእናቷ ተደብቃ ወንድን ማገኘት የለመደች ሴት መቼም እንዳታገባ የሆነ ቀን ከአንተም ተደብቃ ለማገኘቷ ዋስትና የለህም ሀቢቢ በቃ ጀማሮህ አንድ ነገር ላይ ይሁን።

እነዚህን 7ት ሴቶች እንዳታገባ 1. አል-አናናህ (الأنانة) - "ሁልጊዜ አማሪሪዋ" ይህች ሴት በማንኛውም አጋጣሚ ማማረር እና ማጉረምረም የምታበዛ ናት። ያላት ነገር አያስደስታትም፤ ሁልጊዜም ያልተሟላላት ነገር እንዳለ ይሰማታል። በትንሽ በትልቁ ራሷን እንደታመመች በማስመሰል (በማቃሰት) የባሏን ሀሳብ እና ጉልበት ትጨርሳለች። 2. አል-መናናህ (المنانة) - "ውለታ ቆጣሪዋ" ለባሏ ወይም ለቤተሰቡ ያደረገችውን ማንኛውንም ጥሩ ነገር ሁልጊዜ የምታነሳ እና የምትመፃደቅ ናት። "እኔ እንዲህ አድርጌልህ፣ የኔ ቤተሰቦች እንዲህ ረድተውህ..." እያለች በተፈጠረችው ክፍተት ሁሉ ባሏን በውለታዋ ልታሸማቅቀው ትሞክራለች። በእስልምና ውለታ መቁጠር (መን) መልካም ስራን ከሚያበላሹ ነገሮች አንዱ ነው። 3. አል-ሐናናህ (الحنانة) - "ወደ ኋላ ናፋቂዋ" ይህች ሴት አሁን ካለችበት ትዳር ይልቅ ትኩረቷ እና ልቧ ያለው ያለፈ ህይወቷ ላይ ነው። ከዚህ ቀደም አግብታ ከነበረ የቀድሞ ባሏን፣ ወይም ደግሞ የቤተሰቦቿን ቤት ሁልጊዜ በናፍቆት እያነሳች አሁን ያለችበትን የትዳር ህይወት እና ባሏን ዝቅ የምታደርግ ናት። 4. አል-ሐዳቃህ (الحدّاقة) - "አይኗ ያረፈበትን ሁሉ ፈላጊዋ" በአጭሩ ቁሳቁስ ወዳድ (Materialistic) የሆነች ሴት ናት። አይኗ ያረፈበትን እና ያየችውን እቃ ሁሉ እንዲገዛላት ትፈልጋለች። የባሏን አቅም እና የኪስ ሁኔታ ከግምት ሳታስገባ፣ "ይሄ ካልተገዛልኝ፣ ያንን ካላመጣህልኝ" በማለት ባሏን በፋይናንስ እጅግ ታስጨንቀዋለች። 5. አል-በራቃህ (البرّاقة) - "ለውጫዊ ውበቷ ብቻ ተጨናቂዋ" ሁለት ትርጉሞች አሏት፦ አንደኛው፣ አብዛኛውን ጊዜዋን በመስተዋት ፊት በማሳለፍ ለውጫዊ ገፅታዋ (ለሜካፕ እና ለመዋቢያ) ብቻ ከልክ በላይ የምትጨነቅ እና የቤት ውስጥ ሀላፊነቷን የምትዘነጋ ናት። ሁለተኛው ትርጉም ደግሞ፣ ምግብ ሲቀርብላት ሁልጊዜ የምትነቅፍ እና በምንም ነገር የማትረካ ማለት ነው። 6. አል-ሸዳቃህ (الشدّاقة) - "ለፍላፊዋ" በጣም ብዙ የምትናገር፣ ዝምታን የማታውቅ ችግር ሲፈጠር ጎረቤት እስኪሰማ የምትጮህ  እና በየሰዉ ጉዳይ የምትገባ ናት። በንግግሯ የሰውን ሚስጥር የምታወጣ፣ ሐሜት የምታበዛ እና ምላሷ ባሏን የሚጎዳ (የማይገታ) ነው። 7. አል-ሙኽተሊዓህ (المختلعة) - "ሁሌም ፍቺ ጠያቂዋ" በጣም ቀላል እና መፍትሄ ሊያገኙ በሚችሉ የትዳር ውስጥ አለመግባባቶች ሁሉ ትዕግስት አጥታ "ፍታኝ! ካልፈታኸኝ..." እያለች ቃለ-ፍቺን (ጦላቅን) እንደ ማስፈራሪያ እና የዘወትር ዛቻ የምትጠቀም ናት። ነብዩ (ሰለሏህ ወአለይሂ ወሰላም ) ያለ በቂ የሸሪዓ ምክንያት ፍቺን የምትጠይቅ ሴት የጀነትን ሽታ አታገኝም ብለዋል።    ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌እነዚህን 7ት ሴቶች እንዳታገባ 1. አል-አናናህ (الأنانة) - "ሁልጊዜ አማሪሪዋ" ይህች ሴት በማንኛውም አጋጣሚ ማማረር እና ማጉረምረም የምታበዛ ናት። ያላት ነገር አያስደስታትም፤ ሁልጊዜም ያልተሟላላት ነገር እንዳለ ይሰማታል። በትንሽ በትልቁ ራሷን እንደታመመች በማስመሰል (በማቃሰት) የባሏን ሀሳብ እና ጉልበት ትጨርሳለች። 2. አል-መናናህ (المنانة) - "ውለታ ቆጣሪዋ" ለባሏ ወይም ለቤተሰቡ ያደረገችውን ማንኛውንም ጥሩ ነገር ሁልጊዜ የምታነሳ እና የምትመፃደቅ ናት። "እኔ እንዲህ አድርጌልህ፣ የኔ ቤተሰቦች እንዲህ ረድተውህ..." እያለች በተፈጠረችው ክፍተት ሁሉ ባሏን በውለታዋ ልታሸማቅቀው ትሞክራለች። በእስልምና ውለታ መቁጠር (መን) መልካም ስራን ከሚያበላሹ ነገሮች አንዱ ነው። 3. አል-ሐናናህ (الحنانة) - "ወደ ኋላ ናፋቂዋ" ይህች ሴት አሁን ካለችበት ትዳር ይልቅ ትኩረቷ እና ልቧ ያለው ያለፈ ህይወቷ ላይ ነው። ከዚህ ቀደም አግብታ ከነበረ የቀድሞ ባሏን፣ ወይም ደግሞ የቤተሰቦቿን ቤት ሁልጊዜ በናፍቆት እያነሳች አሁን ያለችበትን የትዳር ህይወት እና ባሏን ዝቅ የምታደርግ ናት። 4. አል-ሐዳቃህ (الحدّاقة) - "አይኗ ያረፈበትን ሁሉ ፈላጊዋ" በአጭሩ ቁሳቁስ ወዳድ (Materialistic) የሆነች ሴት ናት። አይኗ ያረፈበትን እና ያየችውን እቃ ሁሉ እንዲገዛላት ትፈልጋለች። የባሏን አቅም እና የኪስ ሁኔታ ከግምት ሳታስገባ፣ "ይሄ ካልተገዛልኝ፣ ያንን ካላመጣህልኝ" በማለት ባሏን በፋይናንስ እጅግ ታስጨንቀዋለች። 5. አል-በራቃህ (البرّاقة) - "ለውጫዊ ውበቷ ብቻ ተጨናቂዋ" ሁለት ትርጉሞች አሏት፦ አንደኛው፣ አብዛኛውን ጊዜዋን በመስተዋት ፊት በማሳለፍ ለውጫዊ ገፅታዋ (ለሜካፕ እና ለመዋቢያ) ብቻ ከልክ በላይ የምትጨነቅ እና የቤት ውስጥ ሀላፊነቷን የምትዘነጋ ናት። ሁለተኛው ትርጉም ደግሞ፣ ምግብ ሲቀርብላት ሁልጊዜ የምትነቅፍ እና በምንም ነገር የማትረካ ማለት ነው። 6. አል-ሸዳቃህ (الشدّاقة) - "ለፍላፊዋ" በጣም ብዙ የምትናገር፣ ዝምታን የማታውቅ ችግር ሲፈጠር ጎረቤት እስኪሰማ የምትጮህ  እና በየሰዉ ጉዳይ የምትገባ ናት። በንግግሯ የሰውን ሚስጥር የምታወጣ፣ ሐሜት የምታበዛ እና ምላሷ ባሏን የሚጎዳ (የማይገታ) ነው። 7. አል-ሙኽተሊዓህ (المختلعة) - "ሁሌም ፍቺ ጠያቂዋ" በጣም ቀላል እና መፍትሄ ሊያገኙ በሚችሉ የትዳር ውስጥ አለመግባባቶች ሁሉ ትዕግስት አጥታ "ፍታኝ! ካልፈታኸኝ..." እያለች ቃለ-ፍቺን (ጦላቅን) እንደ ማስፈራሪያ እና የዘወትር ዛቻ የምትጠቀም ናት። ነብዩ (ሰለሏህ ወአለይሂ ወሰላም ) ያለ በቂ የሸሪዓ ምክንያት ፍቺን የምትጠይቅ ሴት የጀነትን ሽታ አታገኝም ብለዋል። https://t.me/Sobabilalmesjid https://t.me/Sobabilalmesjid    ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌