es
Feedback
Ethiopian Public Service University

Ethiopian Public Service University

Ir al canal en Telegram

ፐብሊክ አገልግሎት ልህቀት በተግባር ተኮር እውቀት

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Ethiopian Public Service University

El canal Ethiopian Public Service University (@epsutelegram) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 12 736 suscriptores, ocupando la posición 15 736 en la categoría Educación y el puesto 2 645 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 12 736 suscriptores.

Según los últimos datos del 13 julio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 112, y en las últimas 24 horas de 2, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 34.81%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 15.93% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 434 visualizaciones. En el primer día suele acumular 2 029 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 30.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
ፐብሊክ አገልግሎት ልህቀት በተግባር ተኮር እውቀት

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 14 julio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Educación.

12 736
Suscriptores
+224 horas
+217 días
+11230 días
Archivo de publicaciones
photo content

photo content
+1

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡ የውል ስምምነቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የመንግሰት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ለመፈጸም እና ለማስፈጸም በሚያስችል አደረጃጀት የሰው ኃይል ብቃትና ምዘና ሥርዓትን በተፈለገው መንገድ ለማራመድ ታስቦ የተካሄደ ሲሆን፣ በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተፈጸመ መሆኑ ታውቋል፡፡ የፊርማ ስነ-ስርዓቱን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንደተናገሩት፣ የመንግሰትን አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸው፣ “በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ሪፎርም ዓላማ፣ ከተለመደው ኋላቀር አሠራር ሙሉ በሙሉ ተላቀን፣ ዘመኑ በሚጠይቀው የዲጅታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ፣ ዜጎች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ፈጣንና ተገቢ ምላሽ መስጠት የሚያስችል አሰራርን በመዘርጋት እርካታን ማምጣት ነው፡፡” ብለዋል። ሚኒስትር መስሪያ ቤቱን ወክለው ፊርማቸውን ያኖሩት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲን በመወከል የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ለማ ጉዲሳ (ዶ/ር) ሲሆኑ፣ በስነስርአቱ ላይ እንደተናገሩት፣ “የኒቨርሲቲው የተጣለበት ኃላፊነት የትውልድ አደራ በመሆኑ፣ የሚጠበቅበትን ሚና ለመወጣት ብርቱ ጥረት ያደርጋል፡፡” ብለዋል፡፡ Visit our website: https://www.epsu.edu.et/user Follow our Facebook page: https://web.facebook.com/EPSUfb Follow our Telegram Channel: https://t.me/epsutelegram PR call: 0945746405

photo content
+2

photo content
+9

photo content
+9

በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፋይናነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት Validation ወርክሾፕ አካሄደ፤ በኢፐሰዩ የፋይናነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ (College of Finance & Economics) በዩኒቨርሲቲው አዲስ ምእራፍ ተልእኮ መሰረት፣ በመጀመሪያ ዲግሪ ሊሰጡ ለታቀዱት አራት የትምህርት መርሃ ግብሮች ሲያካሄድ የቆዬውን የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ተከትሎ፣ ታህሳስ 24 ቀን 2018 በዩኒቨርሲቲው የስልጠና ኢንስቲትዩት ስልጠና ክፍሎች Validation ወርክሾፕ አካሄደ፡፡ በወርክሾፑ ላይ የኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል የካሪኩለም ጥናት ኮሚቴ፣ የህዝብ ፋይናንስ አስተዳደር እና አካውንቲንግ የካሪኩለም ጥናት ኮሚቴ፣ የታክስ እና ከስተምስ አስተዳደር ካሪኩለም ጥናት ኮሚቴ እና የፕሮኪዩርመንት እና ንብረት አስተዳደር ካሪኩለም ጥናት ኮሚቴ ከየትምህርት ክፍሉ ለተውጣጡ መምህራን እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ለመጡ የየዘርፉ ባለሙያዎች የዳሰሳ ጥናት ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ተስፋዬ ጩፋና (ዶ/ር) በወርክ ሾፑ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፣ “የፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱ የተካሄደው፣ ዩኒቨርሲቲያችን ወደ ተግባር ዩኒቨርሲቲነት የሚያደርገውን ሽግግር መሰረት አድርጎ በመሆኑ፣ ሪፖርቱን ሰምታችሁ የግምገማ አስተያየታችሁን እንድትሰጡ እየጋበዝኩ፣ የምትሰጡት ሀሳብ እና አስተያየት፣ እዚህ ተምረው የሚወጡ ተመራቂዎች ያለምንም ተጨማሪ ስልጠና በቀጥታ ወደ ተግባር የሚሰማሩ መሆኑን ታሳቢ ያደረገ መሆን ይኖርበታል” በማለት ተሳታፊዎቹ በንቃት እንዲሳተፉ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡ ወርክሾፑ ለአራቱም የትምህርት ክፍሎች ሪፖርት አቀራረብ እንዲመች ሆኖ፣ በተለያዩ የመሰብሰቢያ አዳራሶች የተካሄ ሲሆን፣ የአካዳሚክ ዘርፍ ምክትል ፕሬዘዳንቱ ለማ ጉዲሳ (ዶ/ር) የታክስ እና ከስተምስ አስተዳደር (Tax & Customs administration) ካሪኩለም ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርት አዳምጠው ሀሳብ እና አስተያየታቸውን አካፍለዋል፡፡ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዐት ጀምሮ ለግማሽ ቀን የተካሄደው ወርክሾፕ፣ ጥናቱን አጠቃሎ ለማጽደቅ በሚያስችል ሁኔታ ግምገማ ተደርጎበት፣ ሀሳብ እና አስተያየት ተሰጥቶበት ከቀኑ 6፡30 ሰዐት ሲሆን ተጠናቋል፡፡ Visit our website: https://www.epsu.edu.et/user Follow our Facebook page: https://web.facebook.com/EPSUfb Follow our Telegram Channel: https://t.me/epsutelegram PR call: 0945746405

Dear EPSU Family, We have received several inquiries regarding the registration process for the recently advertised vacant position. Please be informed that registration is being conducted at the Federal Civil Service Commission, located near Dembel City Center, along the Meskel Adebabayi–Bole Road. For your convenience, you may access the location and directions via Google Maps using the link provided in this post. https://maps.app.goo.gl/2soXkAYdY4RDSZRY6

Dear Ethiopian Public Service University Family, Do you aspire to be part of a team shaping the future of Ethiopia’s public s
+2
Dear Ethiopian Public Service University Family, Do you aspire to be part of a team shaping the future of Ethiopia’s public sector? Here is an exciting opportunity to join us and contribute to our mission of modernizing and strengthening the larger Ethiopian public service. Don’t miss the chance to grow with us and make a meaningful impact! We also encourage you to share this opportunity with friends who might be interested. For full details on the position, criteria, and requirements, please see the attached job vacancy.

Dear Ethiopian Public Service University Family, Do you aspire to be part of a team shaping the future of Ethiopia’s public s
+1
Dear Ethiopian Public Service University Family, Do you aspire to be part of a team shaping the future of Ethiopia’s public sector? Here is an exciting opportunity to join us and contribute to our mission of modernizing and strengthening the larger Ethiopian public service. Don’t miss the chance to grow with us and make a meaningful impact! We also encourage you to share this opportunity with friends who might be interested. For full details on the position, criteria, and requirements, please see the attached job vacancy. Follow our Facebook page: https://web.facebook.com/EPSUfb Follow our Telegram Channel: https://t.me/epsutelegram #ethiopianpublicserviceuniversity PR call: 0945746405

photo content
+3

photo content
+9

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መገናኛ ዲስትሪክት ጋር የCBE በእጀ አገልግሎት የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዩጵያ ንግድ ባንክ መገናኛ ዲስትሪክት ጋር ለመምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ያለማስያዣ የብድር አገልግሎት ማስገኘት የሚችል CBE በእጀ የተባለ የስምምነት ሰነድ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈራረመ፡፡ የስምምነት ሰነዱን በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በኩል ፕሬዚዳንቱ ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መገናኛ ዲስትሪክት በኩል የዲስትሪክቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሊያ ተስፋዬ ፈርመዋል፡፡ ስምምነቱ፣ የዩኒቨርሲቲውን መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች CBE በእጀ የድጅታል አነስተኛ ብድር እና ቁጠባ አገልግሎት /DMSL/ ተጠቃሚ ማድረግን ዓላማ ያደረገ መሆኑ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡ የፊርማ መርሐ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ እስካሁን ባለው አሰራር ባንኮች የብድር አገልግሎት የሚሰጡት ማስያዣ ማቅረብ ለሚችል ባለሀብት እና እራሳቸው ለሚያስተዳድሯቸው ሰራተኞቻቸው ብቻ እንደነበረ አስታውሰው፣ “ዛሬ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የምንፈራረመው ስምምነት፣ ባንኩ ተደራሽነቱን ወደ ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍል እያሰፋ ለመሆኑ እንደማሳያ የሚወሰድ ነው፤ ከዚህም አልፎ ዜጎች ለባንኩ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ተግባር ነው” ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመገናኛ ዲስትሪክት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሊያ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለላፉት 83 ዓመታት ሀገራችንን በፋይናንስ ዘርፍ እያገለገለ እና የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እየደገፈ የተሻገረ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋም መሆኑን አውስተው፣ “ባንካችን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀብት እንደመሆኑ መጠን፣ የደንበኞቻችንን የረጅም ጊዜ ጥያቄ መሰረት በማድረግ ለሁሉም ደንበኞቻችን የብድር አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የተመቻቸውን CBE በእጀ የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስናቀርብ ታላቅ ደስታ ይሰማናል” ብለዋል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ሰራተኞች ባንኩ የሚሰጣቸውን የአጭርና የረጅም ጊዜ የብድር አገልግሎቶች አስመልክተው ላቀረቧቸው ጥያቄዎች የባንኩ ሙያተኞች ማብራሪያ እና ገለጻ ሰጥተው የፊርማ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡ Follow our Facebook page: https://web.facebook.com/EPSUfb Follow our Telegram Channel: https://t.me/epsutelegram #ethiopianpublicserviceuniversity PR call: 0945746405

photo content
+7

በኢፐሰዩ የከተማ ጥናት ኮሌጅ የመጀሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞቹን የዳሰሳ ጥናት አጸደቀ፡፡ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የከተማ ጥናት ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው በተሰጠው የአዲስ ምእራፍ ተክእኮ መሰረት ሲያካሂዳቸው የነበሩትን እና ግምገማ የተደረገባቸውን ስድስት የትምህርት ፕሮግራሞችን የዳሰሳ ጥናት ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ/ም በኮሌጁ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አጸደቀ፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዲን ደጉ በቀለ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ዩኒቨርሲቲው በጀመረው የአዲስ ምእራፍ ጉዞ ቀደም ሲል ያልነበሩ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ለማስጀመር ሰፊ ስራ ሲያከናውን መቆየቱን ጠቅሰው፣ “ዛሬ በኮሌጅ ደረጃ የምናጸድቃቸው ስድስት የትምህርት ፕሮግራሞች የዳሰሳ ጥናቶች ፣ በተለያዩ ደረጃዎች ግምገማ ተካሂዶባቸው እና በተቀመጠው መለኪያ መሰረት አልፈው የመጡ ናቸው” ብለዋል፡፡ ኮሌጁ ያጸደቃቸው የትምህርት ፕሮግራ የዳሰሳ ጥናቶች የከተማ ፕላንና ዲዛይን ፕሮግራም ዳሰሳ ጥናት፣ የከተማ መሬት ሥራ አመራርና እንፎርሜሽን ስስተም ፕሮግራም ዳሰሳ ጥናት፣ የንብረት ግመታ ፕሮግራም ዳሰሳ ጥናት፣ የከተማ ምህንድስና ፕሮግራም ዳሰሳ ጥናት፣ የቅየሳ ምህንድስና ፕሮግራም ዳሰሳ ጥናት እና የእንቫይሮንሜንታል ሳይንስ ፕሮግራም ዳሰሳ ጥናት የሚሉት ናቸው፡፡፡ በእለቱ የዳሰሳ ጥናቶቹን ከማጽደቅ በተጨማሪ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ደጉ በቀለ ከትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና ከሌሎች የኮሌጅ ኃላፊዎች ጋር ከትምህርት ሚኒስቴር በመጣው ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያ /KPI ላይ ተፈራርመዋል፡፡ Follow our Facebook page: https://web.facebook.com/EPSUfb Follow our Telegram Channel: https://t.me/epsutelegram #ethiopianpublicserviceuniversity PR call: 0945746405

photo content
+7

በኢፐሰዩ የተማሪዎች ተሰጥኦ መለያ እና ማልሚያ ማንዋል ተገመገመ፤ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል ታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ/ም በህዳሴ አዳራሽ ባካሄደው የአንደኛ መንፈቅ አመት ስብሰባ፣ “የኢፐሰዩ የተማሪ ተሰጥኦ እና ማልማት ማኑዋል (EPSU Student Talent & Development Manual)” ተብሎ በተዘጋጀው ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ የውይይት መርሐ ግብሩን የመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በመክፈቻው እንደተናገሩት፣ “አንድ ዩኒቨርሲቲ ዋና ተግባሩ ተማሪዎቹን ወደ መዳረሻቸው እንዲሄዱ መደገፍ ነው፤ መዳረሻቸው ደግሞ የንድፈሀሳብ ትምህርት ብቻ ላይሆን ይችላል፤ ስለዚህ፣ ከንድፈ ሀሳብ ትምህርት ባለፈ ስነምግባራቸውን እየመራን፣ እምቅ ችሎታቸውን እንዲያወጡ እየረዳን፣ ተሰጥኦዋቸውን እንዲለዩ እያስቻልን እና ወቅቱ የሚጠይቀውን ክህሎት እያለማን መሄድ እንድንችል Talent Development and essential soft skill በሚል ይህንን አደረጃጀት ፈጥረን፣ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡” በማለት ስለሚቀርበው ረቂቅ ማንዋል የካውንስሉ አባላት የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ አድርገዋል፡፡ ከዚያም የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ዲን አብዱ ሙሀመድ (ዶ/ር) የተዘጋጀውን ረቂቅ ማንዋል ለካውንስሉ አባላት ሲያቀርቡ፣ የተማሪዎችን ተሰጥኦ (talent) ለይቶ በማውጣት ጥቅም ላይ እንዲውል የማድረግ ስራ፣ በአንድ ሰው ወይም በአንድ የስራ ክፍል ብቻ የሚሰራ ስራ እንዳልሆነ እና ተማሪዎቹ ከዲግሪ ባሻገር ምን ይዘው ይውጡ የሚለው የዩኒቨርሲቲያችን ዋና የትኩረት ማእከል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመቀጠልም፣ “ሁላችንም የተለያየ ተሰጥኦ (talent) አለን፤ ያንን ተሰጥኦ ለተማሪዎቻችን በማካፈል ያላቸው እምቅ ችሎታ ተፈልቅቆ እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅብናል፤ ተሰጥኦ በመምረጥ ብቻ የምናመጣው አይደለም፤ ከመምረጥ ባሻገር የማያቋርጥ ክትትል እና እንክብካቤ በማድረግ የምናሳካው ጉዳይ ነው፡፡” በማለት ተናግረዋል፡፡ አስከትለውም በረቂቅ ማንዋሉ የተዘረዘሩ ዋና ዋና ተግባራትን እና የአፈጻጸም አቅጣጫዎችን አቅርበዋል፡፡ በመቀጠልም ተሰብሳቢዎቹ በቀረበው ረቂቅ ማንዋል ላይ ሀሳብ እና አስተያየት ሰጥተዋል፤ ከሰጡት ሀሳብ እና አስተያየቶች መካከል፣ በፕሮግራሙ የኤክስቴንሽን እና የቅዳሜ እና እሁድ ተማሪዎች ቢካተቱበት መልካም ነው፤ ተሰጥኦ ያላቸው የአካዳሚክ እና የአስተዳደር ሰራተኞችም ቢሳተፉበት አይከፋም፤ ለማሰላሰል እና ሀሳብ ለማመንጨት ምቹ የሆኑ ማእዘኖች ቢዘጋጁ መልካም ነው፤ የሚሉ ይገኙበታል፡፡ በማጠቃለያውም የቀረቡት ሀሳብ እና አስተያቶች ተካተውበት ረቂቅ ማኑዋሉ እንደሚጸድቅ ፕሬዘዳንቱ ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) ገልጸው ውይይቱ አብቅቷል፡፡

photo content
+6

ኢፐሰዩ ባካሄደው የካውንስል ስብሰባ የ1ኛ መንፈቅ አመት ሪፖርቱን አጸደቀ፤ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ/ም በህዳሴ አዳራሽ ለግማሽ ቀን ባካሄደው የካውንስል ስብሰባ፣ በአንደኛ መንፈቅ አመት በተሰሩ መደበኛ ተግባራት፣ በሪፎርም ስራዎች እና ቁልፍ የውጤት አመላካች አፈጻጸም መለኪያዎች መሰረት በተከናወኑ ተግባራት ላይ የቀረበውን ሪፖርት ገምግሞ አጸደቀ፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ዛሬ ለካውንስሉ የሚቀርበው የአንደኛ መንፈቅ አመት ሪፖርት፣ ከአብዛኛው የካውንስል አባል ጋር በተለያዩ የኮሚቴ ስብሰባዎች፣ የጋራ መድረኮች እና በሪፎርም ቡድን ውይይቶች ንግግር ሲደረግበት የቆዬ መሆኑን ጠቅሰው፣ “የዩኒቨርሲቲው ማናጅመንት አፈጻጸማችንን ገምግሞ፣ የትኛው ላይ ጥሩ እንደሰራን፣ የትኛው ላይ ተጠናክረን መቀጠል እንዳለብን እና ቀጣዩ የትኩረት አቅጣጫችን የቱ መሆን እንዳለበት ለይቷል፤ ከዛሬው ውይይታችን የሚጠበቀው ሪፖርቱን ገምግሞ ማጽደቅ እና ለቀጣይ ምን እንስራ? በሚለው ላይ ካውንስሉ ሀሳብ እና አስተያየት እንዲሰጥበት ነው፡፡” በማለት ስብሰባውን ከፍተዋል፡፡ ከመክፈቻው በኋላ የፕሬዘዳንት ጽ/ቤት ኃላፊው አብርሃም ሐጎስ (ዶ/ር) የአፈጻጸም ሪፖርቱን አቅርበዋል፤ ሪፖርቱ፣ መሰረታዊ መረጃዎች፣ በእቅዱ መሰረት በ14 ግቦች የተቀመጡ ዋና ዋና ተግባራት፣ ቁልፍ የውጤት አመላካች አፈጻጸም፣ በመንፈቅ አመቱ እንደ ውጤት የሚታዩ ተግባራት እና በቀጣዩ መንፈቅ አመት ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ተግባራት በሚል ተደራጅቶ የቀረበ መሆኑን፣ ከሪፖርቱ አቀራረብ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ በመቀጠልም ከተሰብሳቢዎቹ ጥያቄና አስተያየት ቀርቦ በፕሬዘዳንቱ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡ በመጨረም ፕሬዘዳንቱ ውይይቱን ሲያጠቃልሉ፣ “ማኔጅመንቱ ያስቀመጠውን አቅጣጫ፣ በዛሬው ውይይት ያገኘናቸውን ግብአቶች እና በቀጣይ ከመላው ሰራተኛ ጋር በሚደረገው ውይይት የምናገኘውን ሀሳብ እና አስተያየት አዳምረን፣ ለቀጣዩ ስድስት ወር አፈጻጸም ተገቢ የሆነ የእቅድ ማሻሻያ እናደርጋለን” ብለዋል፡፡

ፐብሊክ አገልግሎት ልህቀት በተግባር ተኮር እውቀት