es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

🌔የቀልብ ዶክተር🌔 طبيب القلب📿

🌔የቀልብ ዶክተር🌔 طبيب القلب📿

Ir al canal en Telegram

(إِنَّا فَتَحْنَا لَكَ فَتْحًا مُّبِينًا) #ጥቅማችን_ጀነት_ጥቅማችን_የአላህ_ውዴታ_ነው #ያስገኘንም_አላህ_እኛም_የርሱ_ባሮች_ሙስሊሞች_ነን👈 ዌብሳይት 👉 https://qalebdoctor.com ለህክምና 👉 @freeeeeeeeeeeere ወይም @UstazulQallb ያናግሩ #እያንዳንዱ_ቤት_እንገባለን_ኢንሻአሏህ! ☄️ #የውሾች_ጩሀት_የአንበሳውን_ጉዞ_አያስተጓጉልም

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram 🌔የቀልብ ዶክተር🌔 طبيب القلب📿

El canal 🌔የቀልብ ዶክተር🌔 طبيب القلب📿 (@qallbdoc) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 59 337 suscriptores, ocupando la posición 253 en la categoría Medicina y el puesto 563 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 59 337 suscriptores.

Según los últimos datos del 25 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 28 702, y en las últimas 24 horas de -52, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 2.14%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 1.15% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 1 273 visualizaciones. En el primer día suele acumular 686 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 11.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“(إِنَّا فَتَحْنَا لَكَ فَتْحًا مُّبِينًا) #ጥቅማችን_ጀነት_ጥቅማችን_የአላህ_ውዴታ_ነው #ያስገኘንም_አላህ_እኛም_የርሱ_ባሮች_ሙስሊሞች_ነን👈 ዌብሳይት 👉 https://qalebdoctor.com ለህክምና 👉 @freeeeeeeeeeeere ወይም @UstazulQallb ያናግሩ #እያንዳንዱ_ቤት_እንገባለን_ኢንሻአሏህ! ☄️ #የውሾች_ጩሀት_የአንበሳውን_ጉዞ_አያስ...”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 26 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Medicina.

59 337
Suscriptores
-5224 horas
-1 4237 días
+28 70230 días
Archivo de publicaciones
«ተበድዬ ነበር ተካስኩኝ፤ የኔ መታመም ለእናቴ አፍያ አመጣላት» ክፍል 11 እኔም ቶሎ አነባለሁ፣ ሙቀቴም ቶሎ ይጨምራል። ለመጮህ እሞክራለሁ፣ «ድረሱልኝ» ለማለት እሞክራለሁ፤ ግን አልቻልኩም። አነባለሁ ሙቀቴ ይጨምራል፤ አነባለሁ ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል፤ አነባለሁ አውራ ጣቴ ይንቀጠቀጣል። ዝም ብዬ ቁርዓኑ ላይ ትኩረቴን አድርጌ ሳነብ አፌ መንቀሳቀስ ጀመረ። ድምፅ እንደማላወጣ አውቃለሁ ግን አፌን እያንቀሳቀስኩኝ ቁርዓኑን እያልኩኝ፣ ልክ ሦስተኛውን ሉክ... ሦስተኛውን ገጽ ገልጥ ሳደርግ አፌ ድመፅ ማውጣት ጀመረ፤ ልሳኔ መሰማት ጀመረ። ለራሴ ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ቁርዓኑን በፍጥነት እየቀራሁት ነው ድምፄን ከፍ አድርጌ። «አወራለሁ፣ ማውራት ቻልኩ» ብዬ ለአጎቴ እና ለአክስቴ ልጅ እዛ ላሉት ደስታውን ባበስራቸው ደስ ባለኝ። ግን እኔ ጊዜ የለኝም፤ ከአላህ ጋር የመቃረቢያዬ ጊዜ ነው፤ ከአሁን ከአሁን እወድቃለሁ፣ ከአሁን ከአሁን እሞታለሁ፣ ከአሁን ከአሁን ወደ አኺራ እሄዳለሁ፣ አባቴን አገኛለሁ በምን ኸይር ስራዬ የሚለው ስላሳሰበኝ እኔ ቶሎ ቶሎ ቁርዓኔን እቀራለሁ። ኋላ ግን ቁርዓኑን ስቀራ ሞቅታዬ እየተስተካከለ ሲመጣ፣ «በቃ ይሄ ነገር ከላዬ ላይ ሲነሳ ልቤም ሲስተካከል ጤነኛ ሆንኩ ማለት ነው?» ብዬ ድምፄን ከፍ አድርጌ የአክስቴን ልጅ ጠራኋት። ወዲያው ማንም አልመጣልኝም። ምናልባትም የመኝታ ቤቱ በር ስለተዘጋ አይሰማቸው ይሆናል ብዬ ቀልጠፍ ብዬ ተነስቼ በሩን ከፋፈትኩና የአክስቴን ልጅ ጠራኋት። የአክስቴ ልጅ በድንጋጤ እየበረረች መጣች፤ አጎቴም፣ ጓደኞቹም በሙሉ ተደናግጠው እየሮጡ መጡ። በሩ ጋር ደርሰው ከእግር እስከ ራሴ ያዩኛል፤ ቆሜያለሁ፣ አወራለሁ፣ እናገራለሁ። «እንዴት ናችሁ? አጎቴ እንዴት ነህ? ናፍቀኸኝ ነበር፣ እስከ ዛሬ ድረስ አላየሁህም» አልኩት። አጎቴ «ኡ... ኡ...» ብሎ እንደ ለቅሶኛ፣ ሰው የሞተበት፣ ወንድሙ ተነስቶ እንደመጣ ሰው «ኡ... ኡ...» ብሎ አለቀሰ። ይቀጥላል፡፡ 🔸አዎ የዳኑ ሁሉ እየመሰከሩ ነው🔸 💡💡لا غالبَ إلا الله💡💡 💠ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇 ⭐️     https://t.me/Qallbdoc ህክምና ለማግኘት👇 https://t.me/freeeeeeeeeeeere 👆 ህክምና ለማግኘት👇 https://t.me/UstazulQallb 👆

በጣም ሳቢ እና ትምህርታዊ የሆነው የሙሐደራ ፕሮግራም ማክሰኞ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ በዩቲዩብ ይቀርባል። https://youtube.com/channel/UCnpWh-05VRARbBOb0zZU9vg?si=S
በጣም ሳቢ እና ትምህርታዊ የሆነው የሙሐደራ ፕሮግራም ማክሰኞ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ በዩቲዩብ ይቀርባል። https://youtube.com/channel/UCnpWh-05VRARbBOb0zZU9vg?si=Sf3QJR66tZyduv4A

🏴 #ቪድዮውን_ሳያዩ_ለህክምና_እንዳይመጡ 🔸አዎ የዳኑ ሁሉ እየመሰከሩ ነው🔸 💡💡لا غالبَ إلا الله💡💡 💠ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇 ⭐️     https://t.me/Qallbdoc ህክምና ለማግኘት👇 https://t.me/freeeeeeeeeeeere 👆 ህክምና ለማግኘት👇 https://t.me/UstazulQallb 👆 ዌብሳይት (ድህረ ገፅ) 👇 📱 https://qalebdoctor.com

🔍 በፍርሃት አሳሪ ጅኖች ጥቃት!🔍 ከዶክተር ኢብን ሙነወር (ረሂመሁሏህ) ክፍል 1 ምልክቶች 1. ⚡️#ቀፋፊ_ብቸኝነት፡- ብቸኝነት ስንል ሰው እንዴት ከሰው ጋር ተቀምጦ ብቸኛ ይሆናል፡፡ የሚያስብል አይነት ብቸኝነት ነው፡፡ ሰዎች መሃል ተቀምጠው ብቸኛ ናቸው፡፡ ውስጣቸው ጭንቀት አለ የሚረዳቸው የለም፡፡  2. 🛍#ልክ_ሰው_የማይፈልጋቸው ይመስላቸዋል፡፡ ሰው እወዳችኋለሁ ብሎ ቢምል ብገዘት ተፈላጊ የሆኑ አይመስላቸውም፡፡ ሰው ሁሉ የሚጠራቸው ነው የሚመስላቸው፡፡ ሰው ዘንድ ሚፈለጉ አይመስላቸውም፡፡ 3.⛔️#ብዙግዜ_በህይወታቸው_ለሚወስኑት ማንኛውም ውሳኔ እርግጠኞች አደሉም፡፡  በራስ መተማመን እጅግ አስፈላጊ ሁኖ ሳለ ጅኑ በነርሱ ላይ ሰሰፍሮ ጥርጣሬ ውስዋስን ይጨምርባቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት እርግጠኛ መሆን በራስ መተማመን አይችሉም፡፡ ምንም ውሳኔ እነርሱ አይወስኑም ሰው እንዲወስንላቸው ፈላጊዎች ናቸው፡፡ የሚወስኑትንም ውሳኔ አያምኑም ተጠራጣሪዎች ናቸው፡፡ 4🚫.#ዶዘር_የማያነሳቸው_ይሆናሉ ወዳቂነታቸው ያይላል፡-  እንዲህ አይነት ሰው ገጥሟችሁ ያቃል፡፡ ምንም ስራው ወይም የነካው ነገር በሙሉ በረካ የለውም፡፡ የሚያተርፍ ድርጅት ውስጥ ገብቶ እንኳ ድርጅቱን ያከስራል፡፡ አሏህም ይጠብቀን፡፡ ይህን እርሱ ይገነዘበዋል፡፡ ያን ግን ማስተካከል አይችልም፡፡ ይህ ሰው በጅን ተጠቅቶ ጅኖ ተጫውተውበት ሁሌም ቢሆን የሚነካው ነገር እድገት እንዳያገኝ አድርገው የነርሱ እስረኛ ሁኖ ይቆያል፡፡ በምንም ነገር ላይ እንደሌላው ቶሎ መገላገል ፈተና እንኳ ማለፍን አይችልም፡፡    5❗️. #ክፉ_ነገር_ማሰብ ። አንዳች መጥፎ ነገር ይፈጠራል ብለው ከመሬት ተነስተው ይሰጋሉ!! ሰላም የሆነችን ቀን ማሳለፍ አይችልም፡፡ የሰላም አየር መተንፈስ አይችልም፡፡ በቃ ሁሌም ጭንቀት ነው፡፡ ስልክ ሲጠራ ፍርሃት፡፡ ሰው ሲያወራው ፍርሃት ፡፡ ሰው ሲያይ ፍራሀት፡፡ ሰላም ሁኖ ሁኖ ከመሬት ተነስቶ ስለ ንብረቱ ስለ ሚስቱ ልጆቹ እናት አባቱ ስለሚያቃቸው ሰዎች መስጋት፡፡ ሰላም ቢሆኑ ሁሉም ነገር ጦርነት ሳይኖር እንኳ ስለ ጦርነት ይሰጋሉ፡፡  6. ‼️#ተራ_በሆነው_ባልሆነው ይጎዳሉ፡- ምንም ነገር እነርሱን አይጠቅምም፡፡ ጓደኛ ይጎዳቸዋል፡፡ ሚስት ትከዳቸዋለች፡፡ ልጆቻቸው  ያምጹባቸዋል፡፡ ሰውነታቸው ይከዳቸዋል፡፡ ህመም ቁርጥማት በየቀኑ ያስተኛቸዋል፡፡  7.⁉️ #ርካሽነት_ይሰማቸዋል_ሰው ይፈርድባቸዋል ይገመግማቸዋል፡- አንተ አንድን ትንሽ ስራ ሰርተህ ምስጉን ስትሆን እነርሱ መርከብ ገንብተው ይወቀሳሉ ድርጅት ገንብተው ሰው እንከናቸውን ያያል፡፡ ትልቅ ስራ ሰርተው ሰው ይገመግማቸዋል፡፡ ሃታ ኩራት ሳይኖርባቸው አይናፋር ብቻ ስለሆኑ ሰው በኩራት ያይባቸዋል፡፡ ቀልድ ጫወታቸውን ሰው ንቀት ነው ብሎ ይገመግማቸዋል፡፡ ይቀጥላል፡፡ ከዚህ አይነት ሲህሮች በአሏህ ሃይል እንጠበቃለን፡፡ ከሸይጧን ጭፍሮችም ሸር እንዲሁ! በርሶ ላይ ማንኛውም አይነት ህመሞች ሲኖሩ በሲህርና በአለማዊ በሽታዎች ሲጠቁ አሏህም ካለ በኢስላማዊ እውቀት ብቁ የሆኑ የሩቅያህ ዶክተሮችን አለማዊ የሜዲካል ዶክተሮችን የሳይካትሪስት ዶክተሮችን ብሎም የሃዲስ ምሩቆችን እና የሸሪአ ምሩቅ ምሁሮችን ወደሚያገኙበት ወደ ቀልብ ዶክተር ቻናል በማምራት ዶክተር ወይም ኡስታዝ ብለው በማናገር ህክምናዎን በረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መንገድ ብቻ ያግኙ፡፡ ለሁላችሁም ከልብ አፊያን ተመኘሁ ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ!! 🔸አዎ የዳኑ ሁሉ እየመሰከሩ ነው🔸 💠ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇 ⭐️ https://t.me/Qallbdoc ህክምና ለማግኘት👇 ✈️https://t.me/freeeeeeeeeeeere 👆 ህክምና ለማግኘት👇 ✈️https://t.me/UstazulQallb 👆

🌙​"ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ 🌼 'የወንድሙን hጃ (ጉዳይ) ያሟላ ሰው፣ አላህ የእሱን ጉዳይ ያሟላለታል።' 💡የሰውን ሲያቀሉ የራስ ይቀላል፣ ወንድሙን ለረዳ አላህ ይደርስለታል።" ht
🌙​"ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ 🌼 'የወንድሙን hጃ (ጉዳይ) ያሟላ ሰው፣ አላህ የእሱን ጉዳይ ያሟላለታል።' 💡የሰውን ሲያቀሉ የራስ ይቀላል፣ ወንድሙን ለረዳ አላህ ይደርስለታል።" https://t.me/Qallbdoc ┄ 💡✽»🌹 ┄┄ 💡 ✽»🌹https://t.me/dr_of_heart

ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦“በእርግጥም አንድ ባሪያ ለመስገድ በሚቆምበት ጊዜ፣ ወንጀሎቹ (ኃጢአቶቹ) በራሱና በትከሻዎቹ ላይ ይቀመጣሉ። በሰገደ (ሩኩዕ ባደረገ) ወይም በደፋ (ሱጁድ ባደረገ
ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦“በእርግጥም አንድ ባሪያ ለመስገድ በሚቆምበት ጊዜ፣ ወንጀሎቹ (ኃጢአቶቹ) በራሱና በትከሻዎቹ ላይ ይቀመጣሉ። በሰገደ (ሩኩዕ ባደረገ) ወይም በደፋ (ሱጁድ ባደረገ) ቁጥር ሁሉ፣ እነዚያ ወንጀሎች ከእሱ ላይ ይረግፋሉ።” (ሰሒሕ ኢብን ሒባን 1734) #የቀልብ #ዶክተር #የአፊያዎ #መንደር https://t.me/Qallbdoc  🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴https://t.me/dr_of_heart

وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَانِ إِلَّا مَا سَعَىٰ ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡ 53:39 https://t.me/Qallbdoc ┄┄┉┉✽»🌹 ┄┄┉┉✽»🌹https://
وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَانِ إِلَّا مَا سَعَىٰ ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡ 53:39 https://t.me/Qallbdoc  ┄┄┉┉✽»🌹 ┄┄┉┉✽»🌹https://t.me/dr_of_heart

«ተበድዬ ነበር ተካስኩኝ፤ የኔ መታመም ለእናቴ አፍያ አመጣላት» ክፍል10 ኋላም እንደ ምንም ብዬ መተኛት እንደምፈልግ በምልክት ገለጽኩላቸው። አጎቴ ያን ቀን የራሱን መኝታ ቤት ፈቀደልኝ። «በቃ ሟች እንግዳ ነች፤ ምቾት ይሰማት» ብሎ ነው መሰለኝ። ለነገሩ ቀን ስለነበረ ሌላ የተዘጋጀ መኝታ ቤት አልነበረም። የሱ መኝታ ቤት ሄጄ ልተኛ ስል የተቀመጠ ቁርዓን አገኘሁኝና «እስኪ ኢማኔን እንኳን ልከምል፤ ራሴን ልንከባከብ፤ አላህ ጋር ብሄድ 'ምን ስራ ሰራሽ?' ከተባልኩኝ 'ይህን እንኳን ቁርዓን ታምሜ ቀርቻለሁ' ልበል» አልኩኝና ቁርዓኑን ገለጥኩት። ስገልጠው ሰውነቴ በሙሉ መርገፍገፍ ጀመረ። እስከ ዛሬ ድረስ ተሰምቶኝ የማያውቅ እልህ፣ ቁጭት፣ ስቃይ የወለደው እምባ በዓይኔ ላይ ዱብ ዱብ እያሉ መንከባለል ጀመሩ። አለቀስኩኝ ስቅስቅ ብዬ። ሰው ቁርዓን የሚከፍተው ለመቅራት፣ ከአላህ ጋር ለመገናኘት ነው፤ የኔ ቁርዓን አከፋፈት ግን ብሶቴን ለማውጣት ይመስላል። ለቅሶዬን ማን ያስቁመኝ! እንደ ምንም ራሴን ከሰዓታት በኋላ አረጋጋሁኝና «ቢያንስ እንኳን ፋቲሃን ልቅራ» ብዬ ከፍቼ ፋቲሃ ጋር ተፋጠጥኩ። ልቀራው ብሞክር ምንም አይነት ድምፅም፣ ውስጤም ማውራትም ማንቀሳቀስም አልቻለም፡፡ ቁርዓኑን አውቀዋለሁ፣ ሃርፉን አውቀዋለሁ፣ ፊደላቱን አውቀዋለሁ በአባቴ ነው የተማርኩት፤ ነገር ግን ሊመጣልኝ አልቻለም። «በቃ ይሄ ነገር አእምሮዬን ሳይወስደኝ በፊት እስቲግፋር እንኳን ልበል» አልኩኝና ቁርዓኑን እያየሁኝ እስቲግፋር ማለት ጀመርኩኝ። ወዲያው የማንበብ ክህሎቴ ተመለሰ፤ ፋቲሃ መጣችልኝ። «ቢስሚላሂር ረህማኒር ረሂም» ብዬ ፋቲሃን ቀጠልኩኝ። አንብቤ እስከ መጨረሻው ድረስ እስክጨርስ ሰውነቴ በሙሉ የመጋል እና የመሞቅ ስሜት ተሰማኝ። ልቤ ልክ መጀመሪያ ቀን ሊያዞረኝ ሲል እንደመታው አይነት ይመታል። «በቃ የመሞቻዬ ሰዓት ነው፤ ቁርዓን ይዤ ልሙት» ብዬ በዛው በነካ እጄ ሱረቱል በቀራህን ቀጠልኩኝ። ሱረቱል በቀራን ቀጥዬ ገና ልክ አንድ ገፅ ስገልጽ፣ ጭንቅላቴ እጅግ በጣም የሚያቃጥል ስሜት ተሰማኝ። ለራሴ ማመን አልቻልኩም። «ምንድነው ይሄ ስሜት?» ብዬ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ፤ ግን ያንን ስሜት የማዳምጥበት አልነበረም። «በቃ የመሞት ሰዓቴ እየቆጠረ፣ አላህ ዘንድ የምገናኝበት ሰዓት እየቀረበ ነው» ብዬ ቶሎ ቶሎ አነባለሁ፤ ሙቀቴም ቶሎ ይጨምራል። ይቀጥላል፡፡ 🔸አዎ የዳኑ ሁሉ እየመሰከሩ ነው🔸 💡💡لا غالبَ إلا الله💡💡 💠ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇 ⭐️     https://t.me/Qallbdoc ህክምና ለማግኘት👇 https://t.me/freeeeeeeeeeeere 👆 ህክምና ለማግኘት👇 https://t.me/UstazulQallb 👆

🔹የከባድ ሲህር ምልክቶች በወንዶች ላይ፡፡ 🔹 ይህ ፅሁፍ ከዶክተር አቡ ፈርሃን ጥናታዊ መጣጥፎች ላይ የተወሰዱ ናቸው፡፡  1. 🔸 #የልክ_ወይም ከአግባብ ያለፈ ድፍረት አልያም ከአግባብ በላይ የሆነ ፍርሃት መኖር እነኚህ ጠቋሚ ምልከታዎች ናቸው፡ 2.🔸 #ቀን_ትሰራለህ ትደክማለህ ያስቀመጥከው ገንዘብ ያልቃል እንጂ የሚጨምር ነገር የለም፡፡ በህይወትህ ውስጥ ደስታም የለም፡፡ 3.🔸 #ልብህ_የሚወደውን ለመቅረብ ትቸገራለህ ብዙውን ግዜ ከጠላቶችህ ጋር ትወዳጃለህ፡፡ ኋላም በያንዳንዳቸው ጉዳት መጎዳት ይኖራል፡፡ 4. 🔸#ብዛት_ያለው የፀጉር መመለጥ ይህ ከሌሎች ምክንያቶች ጋር ሊያያዙ ይችላሉ ይሁንና እነኚህ የሲህር ምልክቶች ውስጥ የሚያዝበት ዋነኛ ምክንያት አንድ ሰው በሲህር ሲጠቃ ወንድም ይሁን ሴት የፀጉር መነጨት ይገጥማል፡፡ በቶሎም ራሰበርሀ ወይም መመለጥ ይኖራል፡፡ 5.🔸 #ዶክተር_እልባት ያላገኘለት ፍርሃት ከመግሪብ ኋላ ነው የሚጀምረው ሲመሽ ይጨንቀዋል፡፡ 6. 🔸#ክፉ_ጭንቀት አዛን በሚሰማበት ወቅት ይጨናነቃል ይፈራል፡፡ ጩህ ጩህ የሚለው ከሆነ ደግሞ የጅኑን መዳበር አመላካች ነው፡፡ 7.🔸 #ተጠቅመው_ጨርሰው ሽንትቤት ውስጥ ለረጅም ሰአት ይቀጣሉ፡፡ ይህ በሁለቱም ላይ የሚኖር ምልክት ነው ሴትም ወንድም ላይ፡፡ በይበልጥ ግን ወንድ ልጅ ሁኖ ሽንትቤት መቀመጥን የሚዘወትር ከሆነ እራሱን ሲመለከት የግድ ነው፡፡ 8.🔸 #ርኩስ_የጨጓራ ህመም፡፡ ይህ ህመም በቤተሰብ የሌለ ባንተም ላይ ባንቺም ላይ ኬት እንደመጣ የማይታወቅ ነው፡፡ ይሁንና በምንም አይነት ህክምና አይድንም ተመላልሶ ያው ነው፡፡ 9.🔸 #በሰላት_ላይ_ዝንጉ_መሆን፡፡ በተለይ የአስርን ሰላት ከመስገድ ተራራን መግፋት የሚመርጡ አሉ፡፡ ይህም የሲህሩን ከልካይነት አመላካች ነው፡፡ 10.🔸 #ብዙውን_ግዜ ቅዠቶችን ማስተናገድ፡፡ አላህ ይጠብቀን እና ህይወት በህልም ብቻም ምስቅልቅሏ ልትወጣ ትችላለች፡፡ ስለዚህም ህልም ለሰው ልጅ ህይወት ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ቅ|ዠቶች የሚደጋገሙ ከሆነ ደግሞ አፋጣኝ ህክምናን ይሻሉ፡፡ ምልክቶቹ ይቀጥላሉ ህክምናውም በቀልብ ዶክተር የቴሌግራም ቻናል ላይ ይቀጥላል። 🔸አዎ የዳኑ ሁሉ እየመሰከሩ ነው🔸 💠ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇 ⭐️ https://t.me/Qallbdoc ህክምና ለማግኘት👇 ✈️https://t.me/freeeeeeeeeeeere 👆 ህክምና ለማግኘት👇 ✈️https://t.me/UstazulQallb

ነቢዩ መሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል: " " እርግጥም አላህ (ሱ.ወ) ሕያው እና ለጋስ ነው። አንድ ሰው እጆቹን ወደ እርሱ ሲያነሳ፣ ባዶና ውድቅ አድርጎ ለመመለስ ያፍራል።" https://t.m
ነቢዩ መሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል: " " እርግጥም አላህ (ሱ.ወ) ሕያው እና ለጋስ ነው። አንድ ሰው እጆቹን ወደ እርሱ ሲያነሳ፣ ባዶና ውድቅ አድርጎ ለመመለስ ያፍራል።" https://t.me/Qallbdoc ┄ 💡✽»🌹 ┄┄ 💡 ✽»🌹https://t.me/dr_of_heart

እንግዳን ማክበር በኢስላም ስላለው ትልቅ ቦታ የሚያስተምር ሲሆን፥ በታዋቂው የሀዲስ መጽሐፍ ሪያዱ አስ-ሳሊሂን (ሀዲስ 706፣ ሰሂህ አል-ቡኻሪ እና ሰሂህ ሙስሊም) ላይ የተጠቀሰውን ነቢያዊ መመሪያ
እንግዳን ማክበር በኢስላም ስላለው ትልቅ ቦታ የሚያስተምር ሲሆን፥ በታዋቂው የሀዲስ መጽሐፍ ሪያዱ አስ-ሳሊሂን (ሀዲስ 706፣ ሰሂህ አል-ቡኻሪ እና ሰሂህ ሙስሊም) ላይ የተጠቀሰውን ነቢያዊ መመሪያ (ሱና) የዕለቱ ሱና (የነቢዩ መንገድ)፦ እንግዳህን አክብር።የአሏህ መልክተኛ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው እንግዳውን ያክብር።"እሳቸውም (ሰ.ዐ.ወ) እንደገለጹት፥ ለእንግዳ የሚደረግ ልዩ መስተንግዶ (ልዩ እንክብካቤ) ለአንድ ቀንና ለአንድ ሌሊት ሲሆን፥ መደበኛው የእንግድነት መስተንግዶ ግን እስከ ሦስት ቀናት ድረስ ይረዝማል። ከዚያ በላይ የሚደረገው መስተንግዶ ግን እንደ ሰደቃ (ምጽዋት) ይቆጠራል። #የቀልብ #ዶክተር #የአፊያዎ #መንደር https://t.me/Qallbdoc  🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴https://t.me/dr_of_heart

🎧 #የምሽት #ስንቅ #ለቀልብዎ 🎧        📖📖 ቁርዓን📖📖 #የቀልብ #ዶክተር #የአፊያዎ #መንደር https://t.me/Qallbdoc  🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴https://t.me/dr_of_heart

«ተበድዬ ነበር ተካስኩኝ፤ የኔ መታመም ለእናቴ አፍያ አመጣላት» ክፍል 9 በዚህ መሃል «ሆስፒታል መሄድ አለብን» ተብሎ የሆስፒታል ቀጠሮ ተቀጥሮ፣ አጎቴ ልክ ወንድሙን እንደሚያክም፣ እንደ ወንድሙ ሃላፈነት አድርጎ እኔን እጅግ በጣም ይንከባከበኝ ጀመር። «ወንድሜን ያጣሁት በቀላሉ ነው፣ በዋዛ ፈዛዛ ነው፤ የወንድሜን ልጅ አላጣም» እያለ ሁሌ በቁጭት ያወራል። ማሻአላህ በጣም ብዙ ጓደኞችም አሉት፤ እነሱም ሊያግዙን፣ ሊተባበሩን ፈቃደኞች ናቸው። አንድ ቀን በማለዳ በሌሊት መኪና መጥቶ ወደ ሆስፒታል ተወሰድኩኝ። እዛም ሆስፒታል የጭንቅላት ስካን እና የተለያዩ ነገሮች እንደሚያስፈልግ ተነግሮኝ፣ ኋላም ተራዬን ጠብቄ ተደረገ፤ ሁሉም ምርመራ ተከናወነ። የምርመራው ውጤት ከሰዓት የሚመጣ ነው ተብለን ጠበቅን። ከሰዓትም ውጤቱ ሲመጣ እጅግ በጣም የሚያስደነግጥ ሆነ። ያም፦ «በጭንቅላቷ ላይ እንደ እጢ ያለ እብጠት ይታይባታል» ተባለ። እኔ የምሞት ነበር የመሰለኝ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም የመጨረሻዬ መሰላቸው። ለዚህ ቀን ላበቃኝ ጌታ ግን ሁሌም አመስጋኝ ነኝ። ያንን ካሉኝ በኋላ ውስጤ አንዲት ስጋት ተሰማኝ። «በቃ ከዚህ በኋላ ምንም አይነት ህክምና እንዲሞከርልኝ አልፈልግም፤ እናቴን እያየሁ ልሙት» አልኩኝ። ነገር ግን ሃሳቤን ማን አውጥቶ ይናገርልኝ? ዱዳ ነኝ። ውስጤ እጅግ በጣም ፍርሃት ተሰማው፤ ጨነቀኝ። ወደ ቤት ተመለስን። ሁሉም በጣም አዝነዋል፤ ማንም ሰው ወሬ ማውራት ተስኖት ፍዝዝ ብለው እርስ በእርስ ይተያያሉ። በዛ ሰዓት አፍ ቢኖረኝና መናገር ብችል «እባካችሁ አባቴ የገባበት ጉድጓድ ነው የምገባው፤ የሚያሰጋ ነገር የለም፣ አባቴ ናፍቆኛል» ማለት ነው የምፈልገው። ነገር ግን ያንን የመናገር ጉልበት አልነበረኝም። ይቀጥላል፡፡ 🔸አዎ የዳኑ ሁሉ እየመሰከሩ ነው🔸 💡💡لا غالبَ إلا الله💡💡 💠ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇 ⭐️     https://t.me/Qallbdoc ህክምና ለማግኘት👇 https://t.me/freeeeeeeeeeeere 👆 ህክምና ለማግኘት👇 https://t.me/UstazulQallb 👆

✉️  በልብስ ላይ የሚሰሩ ሲህሮች 🖍 (በዶ/ር ኡሙ ሚስባህ) ​ክፍል 2፡ ምልክቶቹ ​7. #የመፍራት_ባህሪ ድንጉጥ መሆን ዋና መለያ ነው። ከእንቅልፍ በርግጎ መነሳት፣ ኮሽ ባለ ቁጥር መደንገጥና በተለይ የአዛን ድምፅ ሲሰማ ውስጣዊ መረበሽ ይፈጠራል። ከሰው ተገልሎ መቀመጥን ይመርጣሉ። ​8. #ሰላትን_መጥላት ሰላት መቆም እንደ ሞት ይከብዳቸዋል። በምንም አይነት አስገዳጅ ሁኔታ እንኳ ለመስገድ ፍቃደኛ አይሆኑም። ሌላ ሰው ሲሰግድ ማየትም ከፍተኛ ጭንቀትና መሸሽ ያመጣባቸዋል። ​9. #የሰላም_እጦት ሁልጊዜ በጭንቀትና በጥብብ መኖር፣ በፍርሃት መሸበርና ሰውን ማየት መጥላት የዘወትር ስሜታቸው ይሆናል። ሰላምን ማጣት እጅግ ትልቅ ቅጣት ነው። ​10. #የማይለቅ_መጥፎ_ሽታ ከአፍ፣ ከብብት ወይም ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚወጣና በዲዮድራንት የማይጠፋ ሽታ ይፈጠራል። ቢታጠቡና ቢታጠኑ እንኳ ሽታው ስለማይለቅ ሰዎች አጠገባቸው መቆም ይቸገራሉ። ​11. #መደበርና_ራስን_ማግለል ምልክቶቹ ሲደራረቡ ተስፋ መቁረጥ ይከተላል። "አልጠቅምም፣ መሞት አለብኝ" ብሎ ማሰብ፣ ሰዎችን መጠርጠርና ሁልጊዜ መቆዘም መገለጫቸው ይሆናል። ​12. #አስፈሪ_ህልሞች ከከፍታ መውደቅ፣ እባብና አይጥ፣ እንዲሁም ጥቁር አስፈሪ ፍጥረታት ሲያፍኗቸው ማለም የተለመደ ነው። ​13. #የበረካ_እጦት ታካሚው ስኬታማ ነጋዴ ቢሆን እንኳ ገንዘቡ በረካ አይኖረውም። የት እንደሚገባና በምን ላይ እንደሚወጣ ለማሰብ ሲሞክሩ አእምሮአቸው ይታመማል። ​14. #የሆድ_መነፋት ሆድ እንደ እርጉዝ ሴት ይነፋል፤ እጅግም ይወጠራል። በሆድ ውስጥ የሚገላበጥ ነገር እንዳለ ይሰማቸዋል። ​ህክምናው ✅ #ተዝኪር፦ ጠዋትና ማታ አላህን ማስታወስና ቁርአን መቅራት። ✅ #ልብሱን_ማስወገድ፦ የሚጠረጥሩትን የልብስ አይነት ከቤት ማውጣት። ✅ #ውሃ_መጠጣት፦ በብዛት ውሃ መጠጣት። ✅ #ሱሶችን_ማቆም፦ ቡና፣ ጫት፣ ኮካ፣ ሺሻና መሰል ሱሶችን መተው። ✅ #ሩቅያህ፦ በአፋጣኝ ሩቅያህ መጀመርና ኢማንን ማጠናከር። ✅ #ዳእዋ፦ ጠቃሚ ዳእዋዎችን ዘወትር ማዳመጥ። ​ህክምናው በቀልብ ዶክተር ቴሌግራም ቻናል ላይ ይቀጥላል... ​#ሲህር #የልብስ_ሲህር #ሩቅያ #ቀልብ_ዶክተር #ኢስላማዊ_ህክምና #ጤና #ፈውስ ​💡 لا غالبَ إلا الله  ​💠 ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇 ⭐️ https://t.me/Qallbdoc ​ህክምና ለማግኘት 👇 ✈ https://t.me/freeeeeeeeeeeere ​ህክምና ለማግኘት 👇 ✈️ https://t.me/UstazulQallb ​ዌብሳይት 👇 📱 https://qalebdoctor.com

እስኪ እራሳቹን ፈትሹ... ‼️ ታክመው የዳኑ ሙእሚኖች ላይ 99 በመቶ ስላገኘነው ነው! 1.እዚህ ስትመጣ ይጨንቅሀል?/ይጨንቅሻል? 2.ስለምልክቶች ስታነብ/ስታነቢ ከመፍራት ውጭ ውስጥ ጭንቀት ይፈጠራል? 3.ከመሬት ተነስቶ ስለኛ ምንም ሳታውቅ ትጠላናለህ ? ትጠይናለሽ? 4.ውስጥህ ወይም ውስጥሽ በባዶ መሬት እኛ ላይ ቂም መያዝ እልክ መያዝስ አለ? 5.እኛን ማውራት እየፈለግክ/ሽ ተራራ መግፋት ሆኖብሻል/ሆኖብሀል? ግድ የሎትም አብሽሩ እነኚህ ምልክቶች በርሶ ላይ የጅን ሁናቴን ሊያመላክቱ ይችላሉ። ይቅረቡን ኢንሻአሏህ ይህን አልፈው ታክመው የዳኑ ሰዎችን ምስክርነት በራሶ ቃል አሳምረው ይመሰክራሉ ቢኢዝኒሏህ። አፊያዎን ይሸምቱ🤲

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦"በረከቱ ከምግቡ በየትኛው ክፍል ውስጥ እንዳለ አያውቅምና ማናችሁም ጣቶቹን ሳይልስ (ሳይጠርግ) እጁን በጨርቅ አይጥረግ።"(ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2033ለ፣ ትክክ
ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦"በረከቱ ከምግቡ በየትኛው ክፍል ውስጥ እንዳለ አያውቅምና ማናችሁም ጣቶቹን ሳይልስ (ሳይጠርግ) እጁን በጨርቅ አይጥረግ።"(ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2033ለ፣ ትክክለኛ ሐዲስ)የሐዲሱ ዋና መልዕክቶች እና አስተምህሮቶችበረከትን መፈለግ፦ በምግባችን ውስጥ የሚገኘው በረከት በየትኛው ፍርፋሪ ወይም ክፍል ላይ እንዳለ ስለማይታወቅ፣ እጅን ከመታጠብ ወይም ከመጠረግ በፊት ጣቶችን መላስ (መጥረግ) ይወደዳል።ምግብን አለማባከን፦ ይህ ተግባር ምግብን ከመጣል። እና ከመናቅ ይጠብቃል።ትህትና፦ ከምግብ በኋላ ጣትን መላስ የአላህን ጸጋ ማክበርንና በትህትና መመገብን ያሳያል። #የቀልብ #ዶክተር #የአፊያዎ #መንደር https://t.me/Qallbdoc  🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴https://t.me/dr_of_heart

🎧 #የምሽት #ስንቅ #ለቀልብዎ 🎧        📖📖 ቁርዓን📖📖 #የቀልብ #ዶክተር #የአፊያዎ #መንደር https://t.me/Qallbdoc  🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴https://t.me/dr_of_heart