cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ስብዕናችን #Humanity

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ !! @EthioHumanity @Ethiohumanity ✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Mostrar más
Advertising posts
30 963Suscriptores
-724 hours
-497 days
-22630 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

❤️ነፍሴ ስትመክረኝ … የውስጥ ሰላም ከብር ፣ ከወርቅ ፣ ከአልማዝም ሆነ እንቁ ይልቃል ፤ ስኬታማነት ከውስጥ ሰላም ፣ ደስታና ፍቅር በጥብቅ የተቆራኘ ካልሆነ ትርጉሙ ጎዶሎ ነው። ወደ ሀቅ የምትጠራህ ነፍስህን በድለህ ሺህ ግዜ የምድር ሃብት ብትሰበስብ ሀብትም ሆነ ሌላ ነገርህ የውስጥ ሰላም እስካላስገኘልህ ድረስ ተሳካልህ ተብሎ አይታመንም ፤  በዚህ መልኩ የምታገኘው ነገር " ይዘህ ተገኘህ " እንጂ ተሳካልህ አያሰኝም።. 📍ሰላም የሚያሳጡ ፍጡራኖችን ያየህ እንደሆነ በሌሎች ሰዎች ዋጋና መስዋትነት ማትረፍ የለመዱ ፤ ከራሳቸው ጋር ሰላም መፍጠር ያልቻሉ ስግብግቦችና ወዝጋባዎች እንደሆኑ  ለሰከንድ አትጠራጠር። ከእንደዚህ ዓይነት ስግብግብነት ተጠቆጠብ የሰላም እሴትህን ጠብቅ ፣ ይዘው የተገኙት እየቀደሙህ እየመሰለህ የመልካምነት ጉዞህ መሐል ላይ አትወዛገብ ከመልካምነት እና ከሀቅ በላይ አድካሚና አሸልቺ ግን ደግሞ ፍሬው ጣፋጭ የሆነ እፁብ ድንቅ መታደልና መባረክ የለም። 💡አንዳንድ ጊዜ በራስህ ዓለም ዉስጥ ብቻ ለመኖር ሞክር፡፡፡ ወደ ምድር የመጣኸው ትርጉም ላለው ዓላማ ነውና ሁሉም ቦታ ላይ ጥቀም፡፡ በደረስክበት ቦታ ሀሉ መልካም ዝራ፡፡ 📍እቅድህን በመኖር ሂደት በሚገጥሙህ ፈተናዎች አታማር ከአሁን ቀደም የሆኑ ፣ እየሆኑ ያሉ ፣ ከአሁን በሁዋላ በፈለግከውም ሆነ ባልፈለግከው መንገድ የሚሆኑ ነገሮች ሁሉ በምክንያት ያጋጠሙህ እንደሆኑ እመን። የፈተና መብዛቱ ለበጎ ነው፡፡ አካሄድህን እንድታስተካክል ይረዳሃል፡፡ በችግሮች ዙሪያ ተጠበብ እንጂ አትጨነቅ ፤ ለመልካምነትና ከሀቅ ጋር ለመታረቅ የረፈደ የሚባል ግዜ የለም ፤ የቻልከዉን ያህል ስራና እረፍ ፤ ቀሪውን ለፈጠረህ ጌታ ተወው። ሀቀኝነትን ድፈር ፤ ሀሜተኝነትንና ዋሾነትን ፍራ 💡ደፋር ይሰማል ፣ ያደምጣል ፣ ይናገራል ፣ ይመረምራል ፣ ይፅፋል ፣ ይወስናል ፤ የሰማውን ሁሉ እንደ ሰነፎችና ፈሪዎች እውነት ብሎ አያምንምም አይፈርጅምም ፤ የሰማኸውን ሁሉ እንደ እውነት አምነህ ደግመህ ደጋግመህ ሳታረጋግጥ አታውራ ፤ ማጣራትን አስቀድም ፤ ሳትጠይቅ እና ሳታመዛዝን አትፍረድ። ስምህን ከምታውቀው በላይ እርግጠኛ ሁን 💡እንዲህ ስታደርግ ሁሉም የሚታየው ጭለማ ፣ የሚያወራው ስለጭለማ ቢሆን ላንተ የሚታይህ ብርሃን እንጂ ሌላ አይሆንም። አትጠራጠር ንስር አሞራ ፈተናዎቿን ከደመናው በላይ ከፍ በማለት እንደምትሻገረው አንተም ፈተናዎችን ከችግሮች በላይ ከፍ ብለህ በማለፍ የውስጥ ሰላምህን ቀጣይነት እያረጋገጥክ ማሳካት ወደ ምትፈልገው ግብ የማትደርስበት ቅንጣት ታክል ምክንያት አይኖርም። 📍እናም እየነዳን ወዳጆቼ ሁሉንም ነገር በንቃት እየታዘብን እስከነዳን ድረስ  ፤ በችግር ውስጥ ሆኖ በመሳቅ ፣ በደስታ እና በውስጥ ሰላማችን እስካልተደራደርን ድረስ የማንሻገረው ፈተናና የማናሳካው  ግብ አይኖርም። ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
23👍 15
🔆ከራሱ ጋር የተስማማ ከተፈጥሮው ሁሉ ጋር ይስማማል! (Live in harmony with nature) 📍ተፈጥሮ የሰው አካል ነው፤ ሰውም የተፈጥሮ ውህድ ነው፡፡ ሰው ከተፈጥሮ ውጭ መሆን አይችልም፡፡ ከተፈጥሮው ውጪ ልሁን የሚል ሰው ካለ መጀመሪያ የሚጋጨው ከራሱ ጋር ነው፡፡ ሁለተኛም ከልዕለ የተፈጥሮ ሃይል ጋር ይላተማል፡፡ ብዙ ሰው ከሰው ጋር ተስማምቶ መኖርን ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከራሱና ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖርን አይደፍርም፡፡ ተፈጥሮው በማይፈቅደው መንገድ የሚተራመሰው ይበዛል፡፡ ያልሆነውን ለመሆን የሚፍጨረጨር የትየለሌ ነው፡፡ ሰው ከተፈጥሮው ከራቀና ከሰውነቱ ካፈነገጠ አደጋ ላይ ነው፡፡ አንድም አዕምሮው ማሰብ አቁማል፤ ሁለትም ጤንነቱ አጠራጣሪ ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ነው፡፡ 📍ጥንታዊው ሮማዊው ፈላስፋ ሴኔካ ለሚወደው ጓደኛው ለሉሲሊየስ በፃፈው ደብዳቤ ላይ፡- ‹‹ከተፈጥሮ ጋር ተስማምተህ ከኖርክ በጭራሽ ደሃ አትሆንም፡፡ ነገር ግን እንደሌሎች ሃሳብ መኖር ከፈቀድክ ግን መቼም ቢሆን ሀብታም አትሆንም›› ብሎት ነበር፡፡ ሴኔካ ሀብትን ከቁስ ጋር አያይዞ አይደለም ይሄን የተናገረው፡፡ እሱ ሃብት የሚለው የመንፈስ ሀብትን ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ከተፈጥሮ ጋር በመግባባት የሚገኝ ነው፡፡ ተፈጥሮን ማወቅ፣ መረዳትና ከተፈጥሮው ጋር ተጣጥሞና ተስማምቶ መኖር ሰውን በመንፈሳዊ ሃብት እንዲበለፅግ ያደርገዋል፡፡ ብዙዎቻችን በመንፈሳችን ያጣን የነጣን ደሃ የሆንነው አንድም ተፈጥሮውን ለመረዳት ባለመጣራችን ነው፤ ሁለትም ሰውነታችንን ከተፈጥሮው ጋር እያቃረንን ስለምንኖር ነው፡፡ 💡ብዙ ሰው በራሱ ሃሳብ ሳይሆን በሌሎች ሃሳብ ነው ኑሮውን የሚገፋው፡፡ ሰው ስለእሱ በሚሰጠው ፍረጃና አስተያየት እየተመራ ህይወቱን ሲኦል የሚያደርግ እልፍ ነው፡፡ በርግጥ የሁሉም ሰው አስተያየት ሰውን ገደል ይከታል ማለት አይደለም፡፡ የዛኑ ያህል የተሰጠን አስተያየት ሁሉ የመጨረሻው እውነትም አይደለም፡፡ በሁለቱ መካከል ማሰብና መመርመር የሚባል ነገር አለ፡፡ የትኛውንም መጤ ሃሳብ በአዕምሮ ወንፊትነት ማጣራት ግድ ይላል፡፡ ሳያኝኩ እንደሚውጡ ሳያስቡ የሰውን ሃሳብና አስተያየት የሚተገብሩ ራሳቸውን አደጋ ውስጥ ይከታሉ ለማለት ነው፡፡ 💎ታዋቂውን የግሪኩን ፈላስፋ ዲዮጋንን አንዱ እንዲህ ብሎ ጠየቀው፡- ‹‹በሕይወትና በሞት መሐል ልዩነቱ ምንድነው?›› ዲዮጋንም፡- ‹‹ምንም ልዩነት የለውም›› አለው፡፡ ‹‹ታዲያ አንተ ለምን በሕይወት ትኖራለህ? ራስህን አታጠፋም ነበር?›› ሲለው፤ ዲዮጋንም፡- ‹‹እሱም ቢሆን ምንም ልዩነት የለውም!›› አለው ይባላል፡፡ ዲዮጋን ሞትንም ሕይወትንም አንድ ያደረገው ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ስለሆኑ ነው፡፡ ሞት ያለሕይወት፤ ህይወትም ያለሞት አልተፈጠረምና፡፡ ህይወትን ተቀብለህ ሞትን መተው አትችልም፡፡ ብዙዎች ከማያመልጡት ወጥመድ መሸሽ ይፈልጋሉ፡፡ ሞት የህይወትህ አካል ነው፡፡ የትም ብትሄድ አታመልጠውም፡፡ ይልቁንስ ህይወትንም ሞትንም ጠልቀህ ከተገነዘብክ አኗኗርህንና አኳኋንህን፤ መካከሉን ሕይወትህን እንድታስተካክል ይረዳሃል፡፡ 📍የብዙዎቻችን አወዳደቅ ራሳችንን አለመሆናችን ነው፡፡ የእኛ የህይወት መስመር ከሌላው ጋር የሚወዳደር አይደለም፡፡ ብዙዎቻችን ከራሳችን ተፈጥሮ ጋር ተራርቀን ስላለን ደረጃችንን የምንወስነው በሌሎች መለኪያ ነው፡፡ ዋናውና ስሜትን የሚጎዳው አወዳደቅ ደግሞ በትናንት ውድቀታችን ዛሬአችንን ስናወሳስበው ነው፡፡ ሁለቱም አወዳደቆች ከተፈጥሯችን ጋር በመጋጨት የሚመጡ ናቸው፡፡ 💎ወዳጄ ሆይ... ከተፈጥሮው ጋር ተስማምተህ ኑር፡፡ ከራስህ አትራቅ፡፡ የአንተነትህን ተመን ራስህ አውጣ፡፡ ደስታም ይሁን ሀዘን ያለው አዕምሮህ ውስጥ ነውና በሌሎች መለኪያ ሕይወትህን አታወዳድር፡፡ ደረጃህን በራስህ ወስን፡፡ ሌሎች ምንም ብትሆን አቃቂር ከማውጣት አይቦዝኑም፡፡ ሌሎች እንዲያመሰግኑህ ብለህ ራስህን አትጣል፡፡ 📍ለህሊናህ ታመን፡፡ ውስጥህን አድምጥ! ተፈጥሮህን እወቀው፤ እውነትን ተከተል፡፡ አንተነትህን አናግረው፡፡ መንፈስህን አበልጽገው፡፡ ዕለት ዕለት ከራስህ ጋር ትነጋገር ዘንድ ልመድ! ሞት የሕይወትህ ክፋይ መሆኑን አትዘንጋ፡፡ መሄድህ ላይቀር ጥሩ ነገር ሰርተህ እለፍ! ከተፈጥሮውና ከተፈጥሮህ ተማር! ቀድመህ ከራስህ ጋር ተስማማ፤ ሌላው ቀሊል ነው!! ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
👍 36 22
#ምክር ለወዳጅ 📍ወዳጄ ሆይ ! ያወቅከው እውቀት ቢመስጥህ የመጨረሻ እውቀት አይደለም ። በገዛ ድምፁ ባብቶ የሚያለቅስ እንዳለ ሁሉ ያወቀውም እውቀት ሲያስቀውና ሌላውን ሲያስንቀው የሚውል ሞኝ አለ ። የሞትከው ትምህርት ያቆምክ ቀን ነው ። በዓይኖችህ የምታየው ወዳጅህን በጆሮህ አትመዝነው ። ስለ ወዳጅህ ሐሜትን ይዘህ አትምጣ ፣ የሰማህበት ቦታ መልስ ስጥ ። የወዳጅ ልኩ ለወዳጅ ጠበቃ መሆን ነውና ። ደጋጎች ባይኖሩ ዓለም እንደ ቆሰለች ትቀር ነበር ። አንተም በደግነትህ የዓለምን ቍስል አድርቅ ።ማፍቀርህን እንደ ውለታ አትቍጠረው ፣ እውነተኛ ሰው ሌላውን ከመውደድ ውጭ ምንም አማራጭ የለውምና ። 📍ወዳጄ ሆይ ! የተዳፈነ እሳት አይሞቅም ። ያልተገለጠ ፍቅርም አያስደስትም ። ፍቅር ተግባር ከሌለው ሐሰተኛ ነው ። የሚሠራውን ሰው የማይሠራ ሰው ከነቀፈው ፣ የተማረን ያልተማረ ካረመው ፣ ፊደል ያላጣራ ደራሲውን ሂስ ከሰጠው ያ ዘመን ፣ ዘመኑ ዘመነ ግልብ ነውና በትዕግሥት አሳልፈው  ። 💡ወዳጄ ሆይ ! ተዘቅዝቀህ ስታይ ሁሉም ሰው የተዘቀዘቀ ይመስልሃል ። ስትወድቅ ሁሉም ሰው ውዳቂ ይመስልሃል ፣ ስትረክስም የሰው ሁሉ ርኩሰት ይታይሃል ። በእግርህ ቆመህ በጭንቅላትህ አስብ ። በእግር መቆም ባመኑበት መጽናት ፣ በጭንቅላት ማሰብ ማስተዋል ነው ። 📍ወዳጄ ሆይ ! ገንዘብህን ይውሰዱብህ እንጂ አመልህን እንዲወስዱብህ አትፍቀድላቸው ። ስምህን ባገኙት ጭቃ ሊያቆሽሹት ይችላሉ ፣ አንተነትህን ግን አንተ ብቻ ትለውጠዋለህ ። ከሰረቁህ ይልቅ የምትጥለው እንዳይበዛ ተጠንቀቅ ። 💡ወዳጄ ሆይ ! በወንድምህ እጅ ያለውን ክብር ለእኔ ቢሆን ብለህ አትናፍቅ ። ምኞት ምቀኛ ፣ ምቀኝነትም ክፉ እይታ ፣ ክፉ እይታም ነፍሰ ገዳይ ያደርጉሃልና ።  ዕድሜህ እንዳያጥር ትልቅ አዋራጅ አትሁን ። መኖርህ ለሚያስደስታቸው ቅድሚያ ስጥ ። ለሚጸልዩልህ ምርኮህን አካፍላቸው ። ያልተቀበረ ሬሳ እየገደለህ ይመጣል ። ያልተሻረ ቂምም እየመረዘህ ይመጣል ። ወዳጄ ሆይ ! ተቃውሞን ከፈራህ ሥራ አትጀምር ። ነቀፋን ከሰጋህ ከቤትህ አትውጣ ። ውግረትን ካልጠበቅህ ባለ ራእይ አትሁን ። ለማግኘት ማጣት ፣ ለመክበር መዋረድ አስፈላጊ ነው ። ጸጋ ፈጣሪ የሚበዛልህ በሁለት ነገሮች ነው ። የመጀመሪያው በትሕትና ፣ ሁለተኛው በባለጌዎች በመሰደብ ነው ። 📍እናም ወዳጄ ! ጥቅም ለማግኘት ብለህ የተዋጋኸው ውጊያ በመጨረሻ ባለጠጋ እንጂ ባለ ኒሻን አያደርግህም ። ከገንዘብ ክብር እንደሚበልጥ ተረዳ ። የረዳህን ፈጣሪ አልሰጠኝም ብሎ ማማት ነውና እያለህ ከሌላቸው ጋር አትሻማ፣ የረዳህን ፈጣሪ አልሰጠኝም ብሎ ማማት ነውና እያለህ ከሌላቸው ጋር አትሻማ ። የሌለህን ስትመኝ ያለህን እንደምታጣ ተገንዘብ ። ግማሽ ደግነት የክፋት ያህል ነውና ለጉዳይህ ብለህ ቸር አትሁን ። የጎደለ እንስራና ባዶ አዳራሽ ድምፅ ያበዛሉና በእውቀትና በመንፈስ ሙሉ ሁን ።            ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanityBot
Mostrar todo...
61👍 30
👍 6 1
🌗 ቅብጥብጡ ውሻ ✨የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡ 💡በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡ የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡ 💡የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን እንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡ 💡ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡ ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . . 💎ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡ ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ! ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው!     ✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ ውብ ጊዜ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
107👍 56
📍ወዳጄ ሆይ አትድከም፣ አትዘን ማን ያውቃል ሸክምህና ህመምህ ሁሉ ተራግፎ ሌላ ሰው ሆነህ ትነሳ ይሆናል። ያለን ፈጣሪ እንኳን በአንድ ሙሉ ሌሊት፣ በቅጽበት ጊዜ ዉስጥም ብዙ ተዓምር ይሠራል። በቀልባቸው ንፅህና ብቻ ሰላማቸው የበዛ ሰዎች አሉ። ቀልባችሁ ንፁህ ሲሆን ሰላማችሁ ይበዛል፣  ለሌሎች መልካም ስትመኙ በረከታችሁ ይሰፋል። ልብህ የተጠራጠረዉን ነገር ተው፤ ልብ ከዐይን በላይ ያያልና።ወደ ፊት የሚሆነውን ሳትበሳጭ ሳትሰለች በትግስት ጠብቅ።የማይረባና ጥቅም የሌለው ነገር በመከተል ጉልበትህን አታባክን። ወዳጄ ሆይ ከሐዘን በኋላ ደስታ እንጂ ምን አለ! ማጣትን ማግኘት እንጂ ሌላ ምን ይከተለዋል! ምሽቱስ እየነጋ አይደል የሚሄደው?? ከጨለማ በኋላ ብርሃን እንጂ ምን ይመጣል፡፡ የጨለመው ይበራል ፣ የጠፋዉም ይገኛል ። ሕይወትህን መስዋዕት ያደረግህለት ሥራህ በፈረሰና በተናደ ጊዜ ይህንን ክፋ ፈተና ተቀብለህ ተስፋ ሳትቆርጥ የጠፋውን ሁሉ መልሰህ ለማቋቋም በደከመ መሣሪያ ለመሥራት ሳታመነታ ተነሣ።ያለነው የፈተና ምድር ውስጥ ነው። በበሽታ መፈተን አለ። በኀጢአት መፈተን አለ። በዕዳ መፈተን አለ ፣ የምድር ፈተናዎቿ ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም። እናም ወዳጄ ያለህን የሌለህን ገንዘብህን ሁሉ አንድነት አከማችተህ ስትሰራበት ሁሉንም ባንድ ጊዜ ስትከሥር አጣሁ ከሠርኩ ብለህ ቃል ሳትተነፍስ አሁንም ሰርተህ ለማተረፍ ከሥር ጀምረህ እንደ ገና አንድ ብለህ ድከም። ዐሳብህ ጉልበትህ ሥሮችህ ታክቶዋቸው በደከሙ ጊዜ ልብህ ብቻ ይበርታ። ንፋስ የማይወዘዉዘው ዛፍ የለም። ሀሳብ ወስዶ የማይመልሰው ሰዉም የለም። እንዲህም ሆኖ የማይወድቅ ዛፍ አለ። በፈተና የሚፀና የሚበረታ ሰዉም አለ።             ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
58👍 26
📍በሠዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም እንኳ ዋናው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ያለው ተስፋችን ነው። ሕይወት ጠመዝማዛ ብትሆንም ውብና ተስፋን የተሞላች ናት። 💡በዚህ አለም ሁሉ ነገር አበቃ፣ አከተመ ባልንበት ጊዜ የሚቀጥል የተሻለ እድል፣ የምናውቀውና የተለመደው በር የተከረቸመ ቢመስልም ወለል ብሎ የሚከፈት ሌላ በር፣ ዙሪያችን ጭው ያለ በረሃ ቢሆንም የለመለመ መስክ የሆነ ስፍራ ላይ እንዳለ ተምሬያለሁ። 📍ህይወት እንደ ሳንቲም ናት ሁለት ገፅታዎች አሏት ፣ ተቃራኒ ግን ማይነጣጠሉ ገፅታዎች ። በህይወት እስካለን ካአንዱ ገፅ ብቻ ስንኖር ማለፍ የለም፣ እያንዳንዷ ሁኔታ ከጀርባዋ ተቃራኒ ገፅ አላት እናም ሳንቲም ያለ ግልባጭ ገፁ ምሉዕ እንደማይሆነዉ ያለ ሀዘን ደስታ ፣ ያለ ሞት ህይወት ፣ ያለ  ለቅሶ ሳቅ ፣ያለ ድህነት ሀብት ፣ ህይወትን ከነ ህብረ ቀለሟ አምነን መቀበል አለብን ፡፡ 💡እድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜ እንኳ ቢሆን አብዝቶ በትጋት መጓዝ እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም። ትጋት የተስፋ ልጅ ናት። ተስፋ ደግሞ በእኛና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና! "ዛፍ ቢቆረጥ ደግሞ ያቆጠቁጥ ዘንድ፣ ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው" ። ✍አለማየሁ ዋሴ ውብ አሁን♥️ @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanityBot
Mostrar todo...
49👍 20
Inicia sesión y accede a información detallada

Te revelaremos estos tesoros después de la autorización. ¡Prometemos que será rápido!