cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ስብዕናችን #Humanity

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ !! @EthioHumanity @Ethiohumanity ✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
30 140
مشترکین
-624 ساعت
-477 روز
-25230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
💡በየትኘውም የህይወት መንገድህ መልካም ስብዕናን አየዘራህ ስትጓዝ ባታይውም ለሌሎች ፍካት ሆኖ ይቆያል ።ደግነትህ ለብዙዎች የዕድሜ ማራዘሚያ ሰበብ ስለሆነ እንዳይከስም ጠብቀው። ለጋስ በመሆንህ በምላሹ ከሌሎች ምንም ነገር አትጠብቅ። የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ መልካም ነገር ሁሌም ከፈጣሪህ በጎ ምላሽ አለው። 📍ህሊናህ ይረካ ዘንድ ከመቀበል ይልቅ ሰጪ ሁን። በምግባርህ ፈጣሪህን ለማስደሰት ሁሌም ጥረት አድርግ። እርሱ ከወደደህ ደስታ በእጅህ ትገባለች። በመልካም ስነ ምግባር ሽቶ የተርከፈከፈ ስብዕና ከመሬት በታች አፈር ለብሶ እንኳ መዓዛው ያውዳል። 💡አስተሳስብህ ካለባበስህ የበለጠ ሲያምር መልካምነትህ ከምትቀባው ሽቶ የበለጠ ሲያውድ ስነምግባርህ ከመልክህ የበለጠ ሲያምር የዝነጣ ጣሪያ ላይ ደርሰሀል ማለት ነው። ላመነን ሰው መታመን ከህሊና ወቀሳ መዳን ነው። ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፡፡ በህይወታችን የምናሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም።   ውብ አዳር❤️ @Ethiohumanity @EthioHumanity @EthiohumanityBot
نمایش همه...
45👍 23
Photo unavailableShow in Telegram
📍ደፋር መሆን ይኖርብናል ያልተሄደበትን መንገድ ለመሄድ መድፈር ትእቢትን እልህን ጥላቻን ይሉኝታን ለመተው መድፈር ራስን ለማዳመጥ መድፈር 💡አዎ ብዙ በደል ፈፅመሀል ተፈፅሞብሀል። ብዙ ሰው ጠልተሀል፣ ተጣልተሀል ፣  ተጠልትሀል ፣ ልብህ ተሰብሯል፣ ልቦችን ሰብርሀል ፣ግን ደግሞ ከዚህ ሁሉ ጋር ታርቀህና ራስህን አስታርቀህ ዳግም ለመውደድ ፣ ዳግም ለማዘን ፣ዳግም ለመርዳት፣ ዳግም እርዳታ ለመጠየቅና በቅንነትና በፍቅር ለመኖር ድፈር። 📍መጀመርያ ግን ከራስህ ጋር ለመታረቅ ድፈር። ራስህን ከነሙሉ ስህተቶቹ፣ ግድፈቶቹ ፣እንከኖቹ፣ውሸቶቹ፣ ቅጥፈቶቹ፣ አስመሳይነቶቹ ሁሉ ለመቀበል ለማዳመጥና ለመውደድ ድፈር የፍቅር የይቅርታ ዘመን ነው ሲባል ወደሰማይ አታንጋጥ፣ ወደጎረቤቶችህና ጠላቶቸ ብለህ ወደፈረጅካቸው ሁሉ አታፍጥጥ መጀመርያ ከራስህ ጋር ለመታረቅ ወደውስጥህ ተመልከት፣ ወደራስህ ተመለስ ፣ ውስጥህን ፣ልብህን ፣ ህሊናህን አፅዳ፣ሰው የሚሰጥህ ክብር አንተ ለራስህ በምትሰጠው ሚዛንና መጠን ነውና ለራስህ ትልቅ ዋጋና ብዙ ክብር ይኑርህ 💡ራስን መመልከት ራስን ወደ መሆን የሚያደርስ ወሳኝ መንገድ ነው። ራስህን ስትመለከት የወንድምህን ጉድፍ ሳይሆን የአንተን ተራራ ታስተውላለህ፥ በዚህ ውስጥ ደግሞ ተራራህን እየነቀልክ ራስን ወደ መሆን ታድጋለህ። ራስህን ስትሆን ብዙ ነገሮችን ታሸንፋለህ፥ መሰናክሎችን በቀላሉ አልፈህ፥ የነከሰህን የመከራ ጥርስ ውሃ የማድረግን ጥበብ ትጎናጸፋለህ። 🔑ብቻ ምን አደከመህ ራስህን ስትሆን ብዙ የደረብካቸው አላስፈላጊ ኮተቶችን ከራስህ ላይ አውርደህ፥ ንጹህ አንተነትህን ብቻ ያነገበ ማንነት ስትገነባ ያን ጊዜ ሰው መሆን ትጀምራለህ።እናም ራስህን ለመውደድ ድፈር። ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanitybot
نمایش همه...
56👍 34
Repost from Ultra Bonda
Photo unavailableShow in Telegram
🔥አልትራ ቦንዳ ⚫️የስራ መደቡ:- የሽያጭ ሰራተኛ ⚫️የስራ ሰአት:- 3:00-1:00 ⚫️የስራ ቦታ:- ፒያሳ ⚫️ደሞዝ :- በስምምነት ⚫️የሽያጭ የስራ ልምድ ያላት እና ለፒያሳ አቅራቢያ ቦታ የሆነች ⚫️ፆታ:- ሴት ⚫ብዛት:- 1 ✅መስፈርቱን የማያሟሉ ከሆነ አይደውሉ በዚህ ሊያናግሩኝ ይችላሉ 👉@Nagayta
نمایش همه...
👍 6
🔴የሕይወት ግንድ ብዙ ቅርንጫፎች ነን!! 📍 አንድ ውቅያኖስ ላይ ነን  ‘የአንተ’ ታንኳ ሲናጥ ‘የእኔው’ ደንገል መንቀጥቀጥ ይጀምራል፣ ‘የእርሷ’ ጀልባ ሲቀዝፍ የባሕሩ ለመምቴ ይናጣል፣ የሰላምህ እርግብግቢት የሰላማችንን ንፋስ ይጠቅሳል… የሕመማችን ትንፋሽ የደስታ መንፈሷን ይበርዛል።ስለምን - ‘እኔም’፣ ‘አንተም’፣ ‘እርሷም’፣ ‘ሁላችንም' አንድ ነንና። 🔷መምህሩ ራማና ማሃርሺ … “How are we Supposed to treat others?” ብለው ቢጠይቁት… “There are no others” ሲል የመለሰው ለዚህ ነበር። በተገበርከው ክፋት ብቻ ሳይሆን በተብሰልስሎትህ ሂደት ነገር ዓለማችን ይታወካል። በተነፈስከው በጎ ቃል አይደለም ባሰላሰልካት ደግነትም መውጣት መግባታችን ይዋባል… ብቻህን አይደለህምና የብቻ ሰላም የለህም… አልተነጣጠልንምና የብቻ ሕመምም አይኖርህም የግዙፍ ውቅያኖስ አካል ነን ፣ እኛም ሆንን በዙሪያችን ያለው የተፈጥሮ ስንክሳር የውቅያኖሱ አንድ ጠብታ ነው ፣ አንዲት ጠብታ የምትፈጥረው ለመምቴ /Ripple/ የሌላውን ለመምቴ ትነካለች… እኒህ የሃሳብ፣ የስሜትና የድርጊት ለመምቴዎች በሌላኛው ተፈጥሮ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አላቸው… በበጎም በክፉም… ተመልሰው ግን ወደ ምንጫቸው ይመጣሉ፣ በመዋኛ ገንዳ ውስጥ የፈጠርከው የውሃ ለመምቴ የገንዳውን ግድግዳ ገጭቶ ወዳንተ እንዲመለስ ማለት ነው። 🔶ከኔ ቤት ላይ የረጨኸው እሳት ከሆነ ነበልባሉ ያንተን ቤት ይነካል ፣ ሽቶ ስትረጨኝ የመዓዛው ቅንጣቶች ለአፍንጫህ ውብ ጠረን ይለግሳ፣ “You reap what you saw”ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳል ፣ ይህን ምስራቃውያኑ Karma ሲሉት ሌሎች ደግሞ Boomerang ይሉታል… Boomerang አውስትራሊያኖቹ አቦርጂኒስቶች ከእንጨት የሚሰሩት ደጋን ቅርጽ ያለው የአደን መሳሪያ ሲሆን ወርዋሪው ዘንድ ተመልሶ እንዲመጣ ተደርጎ የሚነደፍ ነው። ለሃሳብ፣ ለስሜትና ድርጊትህ መጠንቀቅ የሚኖርብህ ወላፈኑ ‘ለእኔም’፣ ‘ለእርሷም’፣ ‘ለእነርሱም’ እንደሚተርፍ በማሰብ ነው… ምክንያቱም We are all One! 🔷ሰው ብቻ ሳይሆን ከዋክብቱ፣ ሕዋው፣ ምድሪቱ፣ እንስሳው… በሚታየውና በማይታየው ዓለም ያለው ነገር ሁሉ በአንዳች ተፈጥሯዊ ክር የተሳሰረ ነው… ማሰሪያው ስላልታየ መተሳሰሩ የለም አይባልም። ‘እዚያ ቤት ሲንኳኳ እኛ ቤት ይሰማል’ ‘ከወዲህ አንተን ሳማ እዚያ ከንፈር ትነክሳለህ’፣ ‘እከሊት ስታነሳኝ በስቅታዬ አውቀዋለሁ’፣ ‘የሰፈር ውሻ ሲያላዝን አንዱ አዛውንት ሊያልፉ ነው ማለት ነው’… ‘ውስጥህ ሲረባበሽ ራቅ ካለ ቤተሰብህ አልያም ወዳጅህ ቤት አንድ አደጋ አለ ማለት ነው’፣ 'ቅንድብህ ሲርገበገብ እንግዳ ሰው ልታይ ነው'፣ የጥንቶቹ ይሄ እውነት ስለገባቸው ይመስለኛል መሰል አባባሎች ያቆዩልን። ♦️በረከት በላይነህ "የመንፈስ ከፍታ" ላይ እንዲህ ይለናል👇 “የግልህ ወንዝ ስለሌለህ ብቻህን የምትሰራው ድልድይ የለም! የሰማዩ ርቀት፣ የምድሪቱ ስፋት በ’እኛ’ እንጂ በ’እኔ’ አይለካም፡፡ ውዱ ‘እኔ’ ከ’እኛ’ የተሰራው ነውና!” 🔷እዚህ ጋ ነው ስለ ዝምድናና ባዳነት ያለን ግንዛቤ መፈተሸ ያለበት፣ ስለ ዘርና ቀለም ያለን መረዳት መጤን ያለበት፣ Peter Russell “The Global brain” ብሎ ባሰናዳው ቪዲዮው ላይ አንድ በጨረቃ ላይ የተጓዘ የጠፈር ሳይንስ ተመራማሪ የተናገረውን ውብ ቃል ትሰማላችሁ “When you are up there you are no longer an American citizen or a Russian citizen. Suddenly those boundaries disappear. You are a planetary citizen.” 🔑ኑረዲን ዒሳ በአንድ ግጥሙ. “ባዳውን አፍቅሮ፣ ከባዳው ልጅ ፈጥሮ፣ እኔን ባዳዬ አለኝ - ሰባት ቤት ቆጥሮ፣ ልጁን ዘመዴ አለው - በፍቅር ታውሮ፡፡ ቅጠሉ ነኝና ለረጂሙ ሃረግ፣ እኔም ዘመዱ ሆንኩ - መቼስ ምን ይደረግ?” ብሏል… ❤️ፍቅር ሲገባን የልዩነት ቅዠት ይተናል ፣ ማንነት ሲገባን ሕብራችን ይታያል ፣ ጥበብ ሲያጥጠን ግን ልዩነት ያዜምልናል፣ ፍቅር ስንሰጥ በዙሪያችን ባሉት ላይ እርግብግቢቱ ፍቅርን ይወልዳል፣ክፉ ስናስብ ደግሞ በተቃራኒው ክፋት ይጠነሰሳል፣ከፊልዱ ውጭ እስካልሆንን ድረስ ከምላሹ ተጽዕኖ ልናመልጥ አንችልም።                              ✍ደምስ ሰይፉ @bridgeThoughts ውብ ቻናሉ ነው          We are all One!            ውብ ቅዳሜ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
نمایش همه...
42👍 21👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
11👍 3
نمایش همه...
Hamster Kombat

Just for you, we have developed an unrealistically cool application in the clicker genre, and no hamster was harmed! Perform simple tasks that take very little time and get the opportunity to earn money!

👍 2👎 1
🛑 ኢኮኖሚክስ ላይ 'Water & Diamond paradox' የሚባል እሳቤ አለ... ለኑረት ወሳኙ ነገር ውሃ ነው ፣ ግን 'እርካሽ' ነው። አልማዝ ለህላዌ የሚያበረክተው ድንቡሎ የለም  ግን ውድ ነው። ለዚህም ይመስላል አንስታይን "The important things are always simple" ማለቱ... ዘግይቶም ቢሆን የሚገባህ እውነት ነገሮችን በውድና ርካሽ የሚፈርጀው አስተሳሰብ እንጂ የነገሩ ወሳኝነት አለመሆኑ ነው። እርግጥ ማሕበረሰባዊ ስምምነቶች ለተፈጥሮ ህግ ከመገዛት ይልቅ መንጋነትን ያበረታሉ። ለምሳሌ፦ ፨ ዋናው ቁምነገር አብሮነትና ፍቅሩ ቢሆንም ውዱ ግን ሰርጋችን ነው... ፨ ትልቁ እውቀት ራስን ማወቅ ቢሆንም ውዱ ግን ከአስኳላ የምንገዛው ነው። ፨ ጠቃሚው ውበት ጸጥታ ቢሆንም የምንከፍለው ግን ለሚበጠብጠን ጩኸት ነው። ፨ ጤናችን ያለው ንጹህ ውሃ ውስጥ ቢሆንም ብዙ የምንከፍለው ግን ለመታመሚያችን አልኮል ነው... ወዘተ እልፍ ርቀት ሮጠህ ስታበቃ ቆም ብለህ 'ለዚህ ጉዳይ ይህን ያህል ዋጋ መክፈል ነበረብኝን?' ብለህ ብትጠይቅም መሮጥህን ግን አታቆምም። በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ጡዘትህን እንጂ ቆምታህን አያበረቱም ፣ ይልቁን በውድድር ውስጥ እንድትቆይ ይገፉሃል ከጓደኛህ ትወዳደራለህ ፣ ከጎረቤትህ ትወዳደራለህ፣ከባልደረባህ ትወዳደራለህ ፣ ከንግድ አቻዎችህ ትወዳደራለህ... እናም በምስሉ ላይ እንደምታየው ማቆሚያ በሌለው ዙረት [Vicious circle] ውስጥ ትቧችራለህ። ዛሬ የሆነ ነገር ለማግኘት ትሮጣለህ... ደርሰህ ስትይዘው ይቀልብሃል፣ነገ ሌላ ለመጨበጥ ትዘረጋለህ፣ ደርሰህ ስታየው 'ለዚህ ነው በሬዬን ያረድኩት?' ያስብልሃል... እንደገና ሌላ ሩጫ. እንደገና ሌላ ፍለጋ... እንደገና ሌላ መባከን... እጅህ ላይ ያለው ካላስደሰተህ እርግጠኛ ሁን ሊመጣ ያለውም አያረካህም። በበርህ አበባ ሳትፈነድቅ በገነት ውበት አትመሰጥም። ደስታን ከውጭ ከመፈለግ በላይ ጉድለት የሚመስለኝ ይህ ነው። እየፈለጉ መቀጠልን ማቆም ባይቻል በደረሱበት አለመብቃቃት ትልቅ ጉዳት ነው የደረስክበት ደግሞ 'አሁን' ነው ይህ ቅጽበት.አሁንና እዚህ። አንድ ጊዜ የምረቃዬ መጽሔት ላይ ከፎቶ ስር ለሚሰፍር ጽሑፍ 'የእኔ ቀን ነገ ናት' የሚል ቃል ሰጥቼ ነበር... አሁን ላይ ቆም ብዬ ሳስብ 'ምን ሆኜ ነው ግን' እላለሁ. እንዴት ሰው እርግጠኛ ከሚሆንበት ዛሬ ይልቅ በማያውቀው ነገ ላይ የደስታውን ውበት ያንጠለጥላል?  ደስታ ኑረትን ግድ ይላል እኮ... 'ነገ እንትን ሳገኝ እደሰታለሁ' የምትል ከሆነ ለመደሰት ቀጠሮ እየሰጠህ ነው፣ ከዚያም በላይ ደስታህን በነገሩ መኖር አለመኖር ላይ እየመሰረትክ፣ ደግሞስ 'ለደስታ ምን ያህል ነው የሚበቃን?' ስንት ብር? ስንት መኪና? ምን ያህል ቁስ? በዙሪያዬ ብዙ 'ያላቸው' - ተነጫናጮች እና ደግሞ 'ምንም የሌላቸው' ደስተኞች አየሁ ፣ ብዙ ሃብታም የበሽታ ቋቶችና ድሃ ፍልቅልቅ ፊቶችን ሳስተውልም ይሄ ጥያቄ ትዝ ይለኛል፦ . . መልሱ እኮ በአጭሩ "ደስታ ውስጣዊ እንጂ ቁሳዊ [ሰበባዊ] አይደለም" የሚለው ነው። ሆኖም በተግባባንበት መንገድ ሄጄ 'ለመደሰት ስንት ያስፈልገናል?' እላለሁ ፦ ምንም አይበቃንም!!* ምናልባት ምድርን የሚያህል ሃብት ቢኖረን እንኳ ሌላ ፕላኔት ማሰሳችን አይቀርም፣ ደስታ ግን ከብዛትም ሆነ ከነገር ጋር አትቆራኝም። አዎን... ደስተኛ መሆን ካሻህ ባለህ ተብቃቃ Be Content እልሃለሁ!! 📍'የሰው ልጅ ፍላጎት ገደብ የለውም' በሚል ከንቱ ስብከት እየተነዱ 'ያለኝ ይበቃኛል' ማለት እንደሚከብድ ግልጽ ነው።ያም ሆኖ በፍላጎታችን ላይ የምንሰለጥን እንጂ ፍላጎት የሚሰለጥንብን እንዳልሆንን ማወቅም ጠቃሚ ይመስለኛል። አግበስባሽነት በማግኘት ላይ እንድትመሰጥ እንጂ ባለህ ደስታ እንድትፈጥር ፣ አሁን ያለህን ሐይወት እንድታጣጥም ዕድል አይሰጥምና።                             ✍ደምስ ሰይፉ                   @BridgeThoughts      [ ውብ ቻናሉ ነው ፣ አለን በሉት ]             ውብ አሁን ❤️ @Ethiohumanity @EthioHumanity @EthiohumanityBot
نمایش همه...
66👍 43👎 2
01:59
Video unavailableShow in Telegram
24.41 MB
👍 5 5
Photo unavailableShow in Telegram
💎የመሰብሰብ ጉጉትህ ላይ እስካልሰለጠንክ ድረስ የሚበቃ ነገር የለም፤ ጊዜ በጨመረ - ቀን በተቆጠረ ልክ የፍላጎት አድማስ እየሰፋ፣ የመጨመር ሃሳብ እየተንሰራፋ ይቀጥላል... 💡የመጨመር ጉጉት ጉድለት ላይ ብቻ ከመቆዘም የሚፈጠር ህመም ነው፤ በቃኝ አለማወቅ ልክን የመሳት አባዜ ነው... ምን 'ሀብታም' ብትሆን በፍላጎትህ ላይ ገዢ እስካልሆንክ ድረስ የደስታን ደጅ አትረግጥም... 📍በሕይወት ውስጥ በቃኝ የማለትን ያህል ምልዓት የለም!! ብዙ ሰው "ያለኝ ይበቃኛል" እያለ ያጣቅሳል - እንደ ጥቅሱ ግን አይኖርም፤ ጥያቄው ታዲያ 'ያለው ስንት ሲሆን ነው የሚበቃው?' የሚለው ነው፤ የኑሮ ቅንጦት የበዛበትም፣ መኖር ቅንጦት የሆነበትም እኩል 'ያለኝ ይበቃኛል' ካለ ልክ አይሆንም... ስሜትም አይሰጥም። 📍ቁምነገሩ 'ያለህ መብቃቱ' ሳይሆን ባለህ መብቃቃቱ ነው... ሁሉም ሰው 'ያለኝ ይበቃኛል' ሲል 'የሚገባውን' ብቻ ይዞ ላይሆን ይችላል... የተትረፈረፈለትም - ትራፊ ያጠጠበትም አንድ ሊሆን አይችልም... ግና የሚብቃቃ ሰው በውስንነት ውስጥ ሆኖም ጉድለት አይሰማውም... 💎ስትብቃቃ ያለህ ምንም ያህል ይሁን ደስታ ሳይርቅህ ትኖራለህ፤ ስታግበሰብስ ግን ምድሪቱ ሙሉ ስጦታ ሆና ብትቀርብልህ እንኳ በቃኝ አያውቅህም...አንተ ዘንድ የበዛው ከሌላው ጎድሎ ነው፤ በማትፈልገው ጊዜ በስብሶ ሳትጥለው በሚፈልገው ጊዜ ለሚጠቀመው ስጠው!! ✍ደምስ ሰይፉ @BridgeThoughts [የግል ቻናሉ ነው ተቀላቀሉት ] ውብ አዳር ❤️ @Ethiohumanity @EthioHumanity @EthiohumanityBot
نمایش همه...
38👍 23👎 1
00:54
Video unavailableShow in Telegram
📍አንዳንዴ ምን ሆነሀል ስትባል የማትመልሰው ብዙ መሆን አለ። ለመናገር የማይመች ለመተው የማይቀል ብዙ ስሜት አለ ..ለአንተ የከበደ ለሌላው የቀለለ ነገር አለ ። 💡እንዴ ይሄ እኮ ቀላል ነው ይሄ እኮ አያስጨንቅም በሚባል ቃል የሚሸነፍ ለአንተ/አንቺ ግን የከበደ ስሜት አለ ። ምን ሆነሀል ስትባል ምንም ብለክ የምታልፈው ውስጥህ ብቻ የምታንሸራሽረው እያዳመጥክ የምትታመምበት ።ከባድ ስሜት አለ ከባድ ❤️ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል፣ ብሆንም ተስፋ አትቁረጥ ፣ ተስፋ የመኖር ምክንያት ነውና፣ እየኖርን ነው በሰው ሳይሆን በፈጣሪ  ! ትላንት በ"ነበር ይተካል፣ ሰዎችም ነበሩ ይባላል፣ ፈጣሪን ግን ነበር ብለን አናወራውም ያለና የሚኖር ፣ በዛሬያችን ,በነጋችን አልፎም በዘላለም ውስጥ ኗሪ ነው ። " የትላንት ነበሮቻችን በእሱ መኖር ተረስተዋል እናም ወዳጄ አትድከም ፣ አትዘን ። ማንያውቃል ሸክምህ ህመምህ ሁሉ ተራግፎ ሌላ ሰው ሆነህ ትነሳ ይሆናል። ያለን ፈጣሪ እንኳን በአንድ ሙሉ ሌሊት፣ በቅጽበት ጊዜ ዉስጥም ብዙ ተዓምር ይሠራል። 💡ንፋስ የማይወዘዉዘው ዛፍ የለም። ሀሳብ ወስዶ የማይመልሰው ሰዉም የለም። እንዲህም ሆኖ የማይወድቅ ዛፍ አለ። በፈተና የሚፀና የሚበረታ ሰዉም አለ። ዐሳብህ ጉልበትህ ሥሮችህ ታክቶዋቸው በደከሙ ጊዜ ልብህ ብቻ ፈጣሪን ይዞ ይበርታ።           ውብ ምሽት❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanityBot
نمایش همه...
6.48 MB
128👍 41
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.