cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ስብዕናችን #Humanity

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ !! @EthioHumanity @Ethiohumanity ✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Більше
Рекламні дописи
30 705Підписники
-424 години
-627 днів
-25830 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

🔴ብርጭቆህን ባዶ አድርግ!! ቻይና ውስጥ አንድ በጣም ጠቢብ የዜን ፍልስፍና (Zen Philosophy) መምህር ነበር።  ሰዎች የእርሱን እርዳታ ለማግኘት እና ጥበብ ለመቅሰም  ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ይጓዙ ነበር።   አንድ ቀን አንድ የተማረ (ምሁር) ምክር ለማግኘት መምህሩን ይጎበኛል።   ምሁሩም ስለ ዜን የህይወት ፍልስፍና ለመማር እንደመጣ ይናገራል። 🔹ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ውይይቱ ተጀመረ። ምሁሩ አእምሮው ‘በሁሉን አውቃለሁ ባይነት’ የተሞላ እና በእራሱ አመለካከት፣ አስተሳሰብ  እና እውቀት ፍፁምነት  ያምን ነበርና በንግግራቸው ወቅት መምህሩ የሚናገረውን እና የሚያስተምረውን ከመስማት እና ትኩረት ከመስጠት ይልቅ የራሱን ታሪክ እና ስለ ምሁርነቱ በማውራት መምህሩን የመናገር እድል ይነሳዋል።  🔹መምህሩም በእርጋታ አንድ ላይ ሻይ እንዲጠጡ ሐሳብ ያቀርባል። ለእንግዳው (ምሁሩ) ባቀረበው ብርጭቆም ሻይ ይቀዳለታል።  ብርጭቆው ሞላ።  🔹ነገር ግን መምህሩ እየፈሰሰም ቢሆን ሻይውን መቅዳቱን አላቆመም። ጠረጴዛው ላይ እስኪፈስ ድረስ ሻይ እየቀዳለት ነበር።  ሻይው ወለሉ ላይ ብሎም በምሁሩ ጃኬት ላይም ይፈስ ነበር።   ምሁሩም በመገረም እየተመለከተው ‘’“ተው እንጅ!  ብርጭቆው እኮ ሞልቷል።  ማየት አትችልም እንዴ ” ይላል። 🔸መምህሩ በፈገግታ “ብርጭቆህን ባዶ አድርግ! አንተም  ልክ እንደዚህ ብርጭቆ ሁሉ አእምሮህ ባረጁ ሃሳቦች እና እምነቶች የተሞላ ስለሆነ ከዚህ በላይ ምንም አዲስ እውቀትና ሃሳብ መቀበል አቁመሃል። ‘’ በማለት ተናግሮ ብርጭቆውን ባዶ አድርጎ እንዲመለስ መከረው።  . እኛም በህይወታችን ውስጥ በየቀኑ ተመሳሳይ ታሪክ ይከሰታል። ሁሉንም የምናውቅ ይመስለናል እናም ‘በትህትና ማዳመጥ እንዲሁም ከሌሎች መማር አያስፈልገንም!’ ብለን አእምሮአችንን ሞልተን ባዶ ማድረግ አቅቶናል!!! 🟢In Zen we don't Find the Answer , We loose the question" የምትል ግሩም አባባል አላቸው። ራስህን ባዶ አርገህ መማር ከፈለክ ዙሪያህ ሁሉ አስተማሪ ነው!  ሩቅ ሳትሄድ ከጎንህ ላለው ሰው ልብህን ክፈት፣ በመጠየቅ በመመለስ ሳይሆን በመረዳት እና በማስተዋል ነው አብርሆት የሚፈጠረው። 🟡የሰው ልጅ የነብሱን መንፈሳዊ ጎዳና ትክክለኝነት ማወቅ የሚችለው መንገደኛው ራሱ ነው..ስለ ሕይወትህ ችግር ከገጠመህ ወይም ጥያቄ ከተፈጠረብህ ዙርያህን አጥና... ያለህበት ሁኔታ ከሕይወትህ ጋር ያለውን አንድምታ መርምር በተለይ ትንሽ ትልቅ ሳትል በአቅራብያህ ያሉ ሰዎችን ህይወት በመመልከት ላንተ ምን መልእክት እንዳለው በትጋት ተከታተል ምክንያቱም የተፈጥሮ መንፈሳዊ አንደበት ናቸውና..." 🔴የተፈጥሮን መንፈሳዊ ቋንቋ ተማር ስትወድቅ ሆነ ስትነሳ ፍቺው ምን እንደሆነ ውስጥህን ጠይቅ  እውቀትን ሩቅ ፍልስፍና ወይም አንቃቂ ዲስኩሮች ውስጥ አትፈልግ፣ ከራስህ ጀምር ምክንያቱም የኩራዝ ብርሃንን ብታይ በደንብ የሚያበራው አቅራብያው ላለው ነው። አንተም ለራስህ ብርሀን ሁን መማር አታቁም፣ እድገትህን አትግታ፣ እራስህን አሻሽል፤  በአዳዲስ እውቀቶች እራስህን አንፅ! ሁሌም ብርጭቆህን ባዶ አድርገህ ተነስ!         ውብ ቅዳሜ ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Показати все...
29👍 24
46👍 18
✅የስራ ማስታወቂያ ⚫️የስራ መደቡ:- የሽያጭ ሰራተኛ (ልብስ ቤት) ⚫️የስራ ሰአት:- 3:00-1:00 ⚫️የስራ ቦታ:- 22 ⚫️ደሞዝ :- በስምምነት ⚫️የስራ ልምድ ያላት እና ለ22  አቅራቢያ ቦታ የሆነች ⚫️ፆታ:- ሴት ⚫️ብዛት:- 1 ✅ በተጨማሪም ለቤቱ የቪድዮ ማስታወቂያዎችን (Tiktok) ለመስራት ፍቃደኛ የሆነች መስፈርቱን የሚያሟሉ ከሆነ በዚህ ሊያናግሩኝ ይችላሉ 👉 @Nagayta
Показати все...
👎 4👍 1
🌗በአንድ ወቅት ጫካ ውስጥ መውለጃዋ የቀረበ አንዲት ሚዳቆ የመውለጃ ሰዐቷ ደርሶ ትግል ላይ ሳለች ድንገት አከባቢዋን ስትቃኝ ከፊት ለፊቷ ወንዝ ፣ ከኋላዋ ቀስት ያነጣጠረባትን አዳኝ፣ ወደ ጎን ስትዞር የተራበ አንበሳ አሰፍስፎባት ትመለከታለች። ይህም ሳይበቃት ጭማሪ ከፍተኛ ነጎድጓድና መብረቅ ያጀበው ደመና መጥቶ ሰማዩን ያጨልመዋል። መብረቁም ሀይለኛ ስለነበር ደኑን ይመታውና ከፍተኛ ቃጠሎን ያስነሳባታል። ምን ታድርግ? ወደ ፊት ሮጣ እንዳታመልጥ ጥልቅ ወንዝ ተደቀነባት፤ከኋላዋ አዳኙ፤ከጎኗ ደግሞ አንበሳው፤ወደ ጫካ ገብታ እንኳ እንዳትደበቅ ደኑ ከፍተኛ ቃጠሎ ላይ ነው... በዚያ ላይ የውልደት ህመም ነፍስ ውጪ ግቢ እያስባላት ነው ... 💡ሚዳቆዋ በዚህ ውጥረት ውስጥ ሆና ትኩረቷን መፈፀም ወደ ምትችለው ነገር ላይ ብቻ በማድረግ ቀሪውን ለፈጣሪ በመተው በመወለድ ላይ ስላለው ልጇ ብቻ ማሰብ ጀመረች..... አዳኙ ቀስቱን አነጣጥሮ ሊለቅ ባለበት ቅፅበይ ድንገት የመብረቁ ብልጭታ አይኑ ላይ ብዥታ ፈጠረበትና ቀስቱ ተስፈንጥሮ ወደ ተራበው አንበሳ ይሄድና አንበሳውን ይገለዋል። አጉበድብዶ የነበረው ደመናውም መዝነብ ይጀምርና የደኑን ቃጠሎ በቅፅበት አጠፋው። በጭንቅ ታጅባ የነበረችው ሚዳቆም በሰላም ተገላገለችና ወደ ቀደመው ህይወቷ ተመለሰች። አንዳንዴ በህይወትህ ውስጥ በብዙ ፈተናዎችና ጭንቀቶች ልትከበብ ትችላለህ፣ ያኔ አንተ ልትፈታው በምትችለው ነገር ላይ ብቻ አትኩርና ቀሪውን ለመፍትሄዎች ሁሉ ባለቤት ለሆነው ለፈጣሪህ ተወው። 💡መውጫ መፍትሄ አንተጋ እንጂ ፈጣሪህ ዘንድ አይጠፋም። አስታውስ ሁሌም ትላልቅ ወይም ከባባድ ፈተናዎች አሉብኝ ብለህ ለፈተናዎች እውቅና ከመስጠትህ ይልቅ የከባባድ ፈተናዎች አለቃ የሆነው ፈጣሪ አለኝ እያልክ ጭንቀቶችህን አቅልላቸው፣ሁሌም በፈጣሪህ ፈፅሞ ተስፋ አትቁረጥ!!! 📍ገጣሚ በረከት በላይነህ ''ሳይፀልዩ ማደር'' በምትለው ውብ ግጥሙ እንለየይ፣ ''ሳይፀልዩ ማደር'' የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ ሚዳቋ ፀለየች.... "አውጣኝ አውጣኝ" አለች - ለፈጠራት ጌታ ነብሩም ተርቦ ወደ አምላኩ ቀርቦ ሚዳቆዋን አይቶ - አንጀቱ ከሆዱ እንደጠጣበቀ ፈቅዶ እንዲሰጠው - አምላኩን ጠየቀ . የሁለቱን ማብላት - የሁላችን ሰሪ ፀሎታቸውንም - ሰማቸው ፈጣሪ አምላክም በድምፁ - ሚዳቆዋን አላት "እሩጠሽ አምልጪ - ከበረታ ጠላት" . ነብሩንም አለው - "እሩጥ ተከተላት ምግብህ አርገህ ብላት" ሚዳቆዋ ስትሮጥ ከነብር ለማምለጥ ነብሩም ሲከተላት ሆዱን ሊሞላባት . ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ ሆዱን ብትረግጠው የተኛው ከርከሮ ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር . አውጣኝ ያለው ወቶ - አብላኝ ያለው በላ ሳይፀልይ ያደረው - ከርከሮ ተበላ            ውብ አሁን ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Показати все...
98👍 42
💎አንተ ከነሱ የተለየህ በመሆንህ ሲስቁብህ አንተ ደግሞ አንዳይነት በመሆናቸው ሳቅባቸው! ንስር የጨለመውን ወጀብ ሰንጥቆ ያልፋል እንጅ ጨለማው እስኪያልፍ አይጠብቅምና ጀግናም ጥዋት በወጣበት ስታይል አይመለስም ለማለት ነው ። 😉 አለም ለደፋሮች ታደላለች። ወደ ከፍ ያለ ማንነት ጉዞ ስትጀምር የነፍስክ ጥንካሬ ተአምራዊ ወደ ሆነ ቦታ ያደርሥሀል። ሽብርቅርቅ ያለች ቅዳሜ ትሁንልን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Показати все...
88👍 32
✨ 💫እንኳን ለ 1445ኛው የዒድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!                  ❤️በመላው አለም የምትኖሩ የእስልምና እምነት ተከታይ ሙስሊም ወገኖቻችን እንኳን ለ1443ኛው የዒድ  በአል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን። ✨ የዒድ በአል የእዝነት ÷ የመተሳሰብ ÷ አብሮ የመብላትና የመፈቃቀር በአል በመሆኑ በየ አካባቢያችን በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን እያሰብን እንዋል።           ዒድ ሙባረክ !!!❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity
Показати все...
👍 19 15