es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Ir al canal en Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
913
Suscriptores
-324 horas
-177 días
+5330 días
Archivo de publicaciones
ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ። አሏህ ስሙን የሰየመለት ነብይ የሕያ ይባላል ።

እኛስ የት ነን!? ይህ ድንቅ ታሪክ...ታላቁ ዓሊም ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) «ረውደቱል ሙሒቢን» በተሰኘው ድንቅ ኪታባቸው ላይ የጠቀሱት ክስተት ነው!! 🎙ከቀጥታ ስርጭት ዳዕዋ ላይ የተወሰደ- አቡ ሱፍያን t.me/AbuSufiyan_Albenan

ምን አይነት ጀግና ነህ የእውነት ታታሪ የነብያት ወራሽ የተውሂድ ተጣሪ አላህ ይቀበልህ ወላህ ኡስታዝ ሳዳት ቃላት የለኝም አንተን የምገልፅበት። ሁላችንንም ዳዕዋችንን እንምሰል እንሁን! ✍️ አቡ ሹራ አህመድ

አጠር ያለች እውነተኛ ታሪክ ​ከሰላሳ ዓመታት የትዳርና የጋራ ሕይወት በኋላ፣ የሰውየው እይታ በባለቤቱ ላይ በድንገት ተለወጠ። እርስ በእርስ ያገናኟቸው ረጅም ዓመታት በልቡም ሆነ በትዝታው ውስጥ ምንም ዓይነት ምልክት እንዳልተወ ያክል። ​አንድ ቀን ልጆቹን በዙሪያው ሰብስቦ፣ እናታቸው እንዳረጀች፣ ፀጉሯም በሽበት እንደነጣ ፣ እናም ለውጫዊ ገጽታዋ ትኩረት መስጠት እንዳቆመች ነገራቸው። አክሎም፣ እሱ ራሱን እንደሚንከባከብ፣ እናም ከእሱና በሰዎች ፊት ካለው ገጽታ ጋር የምትመጥን ወጣት ሚስት እንደሚፈልግ ተናገረ፣ ​ከዚያም ወደ እናታቸው ሄደው ሌላ ሴት ለማግባት የወሰነውን ውሳኔ እንዲነግሯት ጠየቃቸው። ነገር ግን ሚስቱ እንደጠበቀው በዜናው አልደነገጠችም፤ ምክንያቱም የባህሪውንና የፍላጎቶቹን  ሁኔታ ከዓመታት በፊት ታውቀው ነበር፤ ቃላቱን ከመስማቷ በፊትም በዓይኖቹ ውስጥ ያለውን ለውጥ ታይ ነበር። ልጆቿን በእርጋታ ተቀብላ እንዲህ አለቻቸው፦ «ማግባት ለእሱ ሸሪዐዊ  መብቱ ነው፤ በሐላል መንገድ እንደሆነ ካመነበት እኔ አልቃወምም፤  ​አለች።  ይህ በእሷ ላይ ሲያገባ የመጀመሪያው ጊዜ አልነበረም፤ ከዚህ በፊት ከአንድ ጊዜ በላይ አግብቶ ነበር፣ ነገር ግን ከመጀመሪያው ትዳሩ ውጭ ምንም ዓይነት ትዳር አልዘለቀለትም ነበር፤ እሱን የምትታገሰው እሷ ብቻ ነበረች። በጣም የሚቆጣ ነበር፣ ለትናንሽ ምክንያቶች ይቆጣ ነበር፤ ሆኖም ግን እርሷ አኩርፋ  ከቤቷ ወጥታ አታውቅም ነበር፣ ይልቅስ ሁልጊዜ ትታገስ ነበር። ሰዎች በትዕግሥቷ በተደነቁ ቁጥር እንዲህ ትል ነበር፦ «ኢንሻአላህ አንድ ቀን ሁኔታው ይስተካከላል!» ▢ ​በእርግጥም ሰውየው ከልጆቹ ዕድሜ ጋር የምትቀራረብ ወጣት ሴት አገባ፤ እንደማይመለስ  አድርጎም ከቀድሞ ቤቱ ራቀ። ከጥቂት ጊዜ በኋላም፣ #በአዲሷ_ሚስቱ ጥያቄ መሠረት፣ ፊት ለፊት ሳይጋፈጣት ወይም ለመጨረሻ ጊዜ ዓይኖቿ ውስጥ ሳይመለከት፣ የመጀመሪያ ሚስቱ ዘንድ የፍቺ ወረቀት ላከ።. ▢​ ከአዲሷ ሚስቱ ጋርም የጫጉላ ሽርሽር ለማድረግ ወደ አንዲት ሩቅ አገር ተጓዘ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ውብና በደስታ የተሞሉ መስለው የታዩትን ቀናት አሳለፉ። ወጣትና ውብ ስለነበረች የታደሰ የወጣትነት ስሜትን ትሰጠው ነበር፤ እሱም ደስታ በገንዘብ የሚገዛ መስሎት በገንዘብና በስጦታዎች በእንክብካቤ ይሸፍናት ነበር። ▢ ​ነገር ግን ወደ ቤታቸው እንደተመለሱ፣ ቀናቱ ድምቀታቸውን በሒደት ማጣት ጀመሩ፤ ሕይወትም ወደ ከባድ ልማድ፣ የማያልቁ ጥያቄዎችና እየጨመሩ ወደሚሄዱ ወጪዎች ተለወጠች። አዲሷ ሚስቱ ምንም ዓይነት እውነተኛ ኃላፊነት አይሰማትም ነበር፤ ወጪዎችን ለመቀነስ በሞከረ ቁጥር ተቆጥታ፣ ቤቱን ትታ ወደ ቤተሰቦቿ ትሄድ ነበር። እሱም በየጊዜው እሷን የማጣት ፍርሃት ስላደደረበት እሷን ለማስደሰት እጁን ይሰጥ ነበር፤ እሷ ደግሞ ወጣት መሆኗንና እንደፈለገች የመኖር መብት እንዳላት ታረጋግጥለት ነበር። ▢ ​ሕይወታቸው በዚህ ሁኔታ ላይ ያለ እረፍትና ያለ እርጋታ ቀጠለ፤ አንድ ቀን ያወቀው እረፍት አሁን እንደሌለ እስከሚሰማው ድረስ። የቀድሞ ቤቱ በሰላምና በመዋደድ የተሞላ እንደነበር አስታወሰ፤ በአዲሱ ቤቱ ግን ከመልክና ከጩኸት በስተቀር ምንም አላገኘም። ​በመካከላቸው ያለው አለመግባባት እያደገ ሄዶ ወደ ተዘጋ መንገድ እስኪደርስ ድረስ፤ ሁለተኛው ትዳርም በስነ-ልቦናና በገንዘብ ካደከመውና ባዶ እጁን ካስቀረው ረጅም ትግል በኋላ በፍቺ ተጠናቀቀ።💔 ​በዚያን ጊዜ ብቻ ነበር የጣላትን ሴት ዋጋ የተረዳው፤ በወጣትነት ቅዠት መንገድ ላይ ያባከነው የረጅም ዓመታትና የጋራ ሕይወት ጸጸት አሸነፈው። ​በልቡም እንዲህ አለ፦ «የሰማይ ቅጣት በኔ ላይ የወረደ ይመስላል!» ▢ ​ከዚያም በተሰበረ ድምፅ ወደ ልጆቹ ደውሎ እንዲህ አላቸው፦ «መፍትሔ መፈለግ አለባችሁ፣ የፈትዋ ሰዎችንም ጠይቁ። ተጸጽቻለሁ፣ ወደ እናታችሁና ወደ ቤቴ #መመለስ_እፈልጋለሁ፤ ውበት ብቻውን ደስታን እንደሚፈጥር ባሰብኩ ጊዜ ተሳስቼ ነበርና!»💔 ​ልጆቹም እንዲህ ብለው መለሱለት፦ «አባታችን ሆይ! ነገሩ ተጠናቋል  ምንም ዓይነት መፍትሔም የለም!» ​ከዚያም የእናታቸውን መልእክት አስተላለፉለትና እንዲህ አሉት፦ «እሷ ደህና እንደሆነች፣ ከ አንተ በኋላ ዛሬ እጅግ ደስተኛ እንደሆነች፣ ሕይወቷን የሚያበላሽ ምንም ነገር እንደሌለ፣ እና እፎይታ ከሰማይ እንደመጣላት እንድንንገርህ ነግራናለች።» ▢ ​ሰውየውም ያጣት ጊዜ ብቻ ዋጋዋን የተረዳትን ውድ ኃብት  ዘግይቶ ከተረዳ በኋላ፣ እጆቹን በጸጸት እየነከሰ ቀሪ ሕይወቱን አሳለፈ። ተፈፀመ

በጣም ደስ የሚል፣ ልብን የሚያረካ ታላቅ ደስታ! የኡስታዝ ሳዳት ከማል ወንድም ተውበት አድርጓል። ከነበሩት ስህተቶች ታርሞ ወደ አላህ ተመልሷል።

قُـلْ لِلَّذِي اتَّـخَـذَ الـتَّـجَـهُّـمَ مَـرْكَـبًـا وَ رَآهُ دِيـنًـا و ارْتَــضَـاهُ مَـذْهَــــبًـا وَ لِـمَـذهَبِ الأَبـــرَارِ صَارَ مُـكَـذِّبـًـا إنْ كَانَ تَـابِـعُ أَحـمَــــدٍ مُـتَـوَهِّــبًـا فَـأَنـا الـمُــــقِـرُّ بِـأَ نَّـنِـي وَهَّـــابِي

👉ዱንያ ማለት እንዲህ ናት! ትኖራለህ - ትሞታለህ ታገኛለህ  - ታጣለህ ትደሰታለህ - ታዝናለህ ትስቃለህ   - ታለቅሳለህ ትበላለህ  - ትራባለህ ትወደሳለህ -ትወቀሳለህ ትዋደዳለህ -ትጣላለህ ትከበራለህ - ትዋረዳለህ ትወሳለህ  -  ትረሳለህ ታተርፋለህ - ትከስራለህ ዱንያ ማለት ይህች ናት። ለዚህ ሁሉ ሁነኛ መፍትሄው #ትዕግስት ማድረግ ነው። አላህ በሁሉም ነገር ትዕግስት ከሚያደርጉ ባሮቹ ያድርገን።

ደዕዋ ላይ ላለኸው ወገኔ ~ በደዕዋ ሂደትህ ላይ ጠላት አታብዛ። ከሁሉ ጋር አትጋጭ። በተለይ በአካባቢህ ደዕዋው ገና ዳዴ ላይ ከሆነ የማህበራዊ ሚዲያን ደዕዋ ወይም የተሻለ ድጋፍና መሰረት ያላቸውን አካባቢዎች አካሄድ ምሳሌ እንዳታደርግ። አቅምህን አገናዝብ። ደዕዋህን የፍጥጫ አታድርገው። የአካባቢህን ተጨባጭ ተረዳ። ተማሪዎችህ በችኮላ ለደዕዋው እንቅፋት እንዳይሆኑ ተቆጣጠር። ሁሉን ባንዴ አሳካለሁ ብለህ አታስብ። ብዙ ያሳደደ አንድ አይዝም። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ኢብኑል ቀይም 📿 እንዲህ ብለዋል፦ «በሰዎች ሙገሳና አድናቆት የተፈተነ፣ አላህ ነውሩንና ወንጀሉን በመሰወሩ የታለለ፣ እንዲሁም አላህ በሚሰጠው ጸጋዎች ቀስ በቀስ ወደ ጥፋት የሚሳብ «ሙስተድረጅ» ስንቱ አለ! እነዚህ ሁሉ ቅጣቶችና ውርደቶች ሆነው ሳለ፣ መሃይሙ ሰው ግን እንደ ክብርና ድንቅ ስጦታ ይቆጥራቸዋል።»
📚الدَّاء و الدَّواء/لابن القيم رحمه الله( 119 )
t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie

✨ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ህብረት✨ 📜 ልዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት! 📜 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🌟 እንኳን ደስ አላችሁ ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎች! 🌟 በታላቅ ደስታ ና ፍቅር፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲን በመምረጥ እኛን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ላላችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታችንን እናቀርባለን። 🗓 የቅበላ ጊዜና የአቀባበል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲያችን የተማሪዎች ቅበላ መርሃ ግብር የሚከናወነው ጥቅምት 3 እና 4 ቀን 2019 ነው። በእነዚህ ቀናት፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ለእናንተ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሞቅ ያለና ደማቅ አቀባበል ያደርግላችኋል። በሰላም ወደ ግቢ እንድትገቡ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታገኙ የበኩላችንን እንወጣለን። 🤝 የእናንተ ትብብር ያስፈልገናል! ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት፣ የተሟላ አገልግሎት ለማግኘት እና የአቀባበል ቡድናችን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግላችሁ፡ የምዝገባ ፎርሙን ይሙሉ: https://forms.gle/F7gwvpVVsnsj843Z6 ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት እና የተሟላ አገልግሎት ለመቀበል፣ ማንነታችሁን ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ የቀና ትብብራችሁን በአክብሮት እንጠይቃለን።እንዲሁም ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ በቅድሚያ ከዚህ በታች ባሉት ስልኮች እየደወላችሁ የአቀባበል ቡድናችንን እንድታነጋግሩ በአክብሮት እንጠይቃለን። 📌 የአካባቢ ምደባ ማስታወሻ ወደ ግቢ ከመምጣታችሁ በፊት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ይለዩ፡- ✅ Natural Science ተማሪዎች፡- ወደ Main Campus ትመጣላችሁ። ✅ Social Science ተማሪዎች፡- ወደ Techno Campus ትመጣላችሁ። 📞 ለግንኙነትና ድጋፍ የስልክ ቁጥሮች ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ አስፈላጊውን መረጃ ለማግኘት ወይም የአቀባበል ቡድናችንን እንዲቀበሏችሁ ለማድረግ የሚከተሉትን ወንድሞች ማግኘት ትችላላችሁ፡-              📚   Main campus =>ሀሰን      ☎️        090 632 6702 =>አቡዱረዛቅ           ☎️    0942213321 =>ነቢል       ☎️   096 999 0090 =>ጂፋር    affan orromo          ☎️  +251972575000                                                      💻 Techno campu       =>ዐማር ☎️+251925882521                        =>መስዑድ affan oromo ☎️  +251937517651  =>አስዓድ   ☎️   0963298664       🧕 ለሴት እህቶች ልዩ ማስታወቂያ: የእህቶችን ስልክ ቁጥር ለምትፈልጉ እህቶች ብቻ፣ በስልክ ቁጥር ☎️ +251925882521 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።    🌹  አላህ   በሰላም ያገናኘን 🤲🌹 🎉መልካም የዩኒቨርሲቲ ቆይታ እንመኛለን!🎉

በአላህ ይዣችኋለሁ፣ነብዩን የሚወድ ... ሼር ያድርግ ለሚሉ ሰዎች መልስ 🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር !! 🍃https://t.me/abujemila25

ወዳጄ ሆይ፣ እውነተኛው መለያየት በዋነኛነት በሞት አይሆንም፤ እኛም አላህ ከፈቀደ በአኺራ እንገናኛለን። እውነተኛው መለያየት ግን አንዳችን በጀነት ሲሆን ሌላችን በእሳት ውስጥ መሆኑ ነው። ስለዚህ፣ አንድ ቀን በወንጀል ላይ ብታየኝ ሳትሰለች ምከረኝ፦ አላህን ፍራ! በለኝ። ለወንጀል አውሬ አትተወኝ አደራ። ምናልባት ከአንተ የምሰማው አንድ ቃል ለመዳኔ ምክንያት ይሆናል። አላህ እንዲህ ብሏል፦ [በዚያ ቀን ወዳጆች ከአላህ ፈሪዎች በስተቀር አንዳቸው ለሌላቸው ጠላቶች ይሆናሉ።] [አዝ-ዙኽሩፍ፡ 67] ይህንን መልዕክት ለወዳጅ ለዘመዶ በመላክ ያድርሱ።

✨ የደስታችን ተካፋይ ይሁኑ!        — ታላቅ የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ✨ ​በአላህ ፈቃድ በደሴ ከተማ ልዩና ታላቅ  የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶልዎታል! ​📅 ቀን፦ እሁድ — ጥቅምት 1 / 2019 ዓ.ል 💢 ቦታ፦ ደሴ — መስጂደ አስ-ሱና ⏰ ሰዓት፦ ከጧቱ — 2:30 ​🎙 በፕሮግራሙ ላይ የሚገኙ የተከበሩ ዑስታዞች፣ ሸይኾችና ወንድሞች፦ 1) ​ሸይኽ ሙሐመድ መኪን 2) ​ሸይኽ ሙሐመድ አሚን 3) ​ሸይኽ ሙሐመድ ኋዛል 4) ​ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ 5) ​ሸይኽ ሐሰን አሊ 6)​ሸይኽ አሕመድ አወቀ 7) ​ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ 8)​ ሸይኽ ይማም ሰዒድ ​9) ሸይኽ ሰዒድ ሙሐመድ ሚጢቆሎ) 10)ሸይኽ አብዱልአዚዝ 11)ሸይኽ በድሩዲን ዩሱፍ 12) ሸይኽ ሑሴን ኡመር 13) ሸይኽ ሐሰን ነጃሽ        ( ከወንዲሞች) 14) ​ወንድም ሙርሰል ሰዒድ 15) ​ወንድም ኢዘዲን ሻፊ 16)​ ወንድም አቡ ሹራ 17) ​ወንድም አቡ ሒበቲላህ 18) ​ወንድም አቡ ሐፍሷ (ይማም) 19) ​ወንድም አሊ ሰዒድ 20)​ ወንድም አቡ ኢምራን (እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው ዑስታዞችና ወንድሞች ይገኛሉ) ​📢 ልዩ ጥሪ፦ ይህንን መልእክት ለሌሎች በማጋራትና በዕለቱ በአካል በመገኘት የዚህ ታላቅ በረካና ደስታ ተካፋይ ይሁኑ! ​📌 ለሁሉም እንግዶች ጥሪያችን ክፍት ነው!
ቻናል
https://t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ግሩፕ
https://t.me/yedesse_selfyochi_group
ሼር ይደረግ‼

ለወላጅ መልካም መዋል እስከምን ድረስ? ~ በኢስላም የወላጅ ሐቅ በጣም የከበደ አደራ እንደሆነ ግልፅ ነው። ይህ ማለት ወላጆች ሁሌ ደጎች ስለሚሆኑ አይደለም። ወላጆች ሰዎች ናቸው። አላህ የጠበቃቸው
ለወላጅ መልካም መዋል እስከምን ድረስ? ~ በኢስላም የወላጅ ሐቅ በጣም የከበደ አደራ እንደሆነ ግልፅ ነው። ይህ ማለት ወላጆች ሁሌ ደጎች ስለሚሆኑ አይደለም። ወላጆች ሰዎች ናቸው። አላህ የጠበቃቸው ሲቀሩ ሰዎች ላይ የሚታዩ ክፋቶች ሊታዩባቸው ይችላሉ። ከወላጆች ውስጥ አመሉ ፈታኝ የሆነ አብሮ ለመኖር የሚከብድ ይኖራል። ከወላጆች ውስጥ ጥቅም ካላየ በስተቀር ለልጁ ጀርባ የሚሰጥ አለ። ከወላጆች ውስጥ በልጆቹ መሃል መርጦ የሚያዳላ ይኖራል። ከወላጆች ውስጥ የልጆቹን ክብር የሚያጎድፍ፣ ያላግባብ ስም የሚያጠፋ፣ አጥንት የሚሰብር ስድብ ከባዳ ፊት የሚሳደብ ይኖራል። ከወላጆች ውስጥ ለልጆቻቸው ትዳር እንቅፋት የሚሆኑ አሉ። ከወላጆች ውስጥ ከፊል ቤተሰባቸውን በከፊሉ ላይ እያሳደሙ በገዛ ልጆቻቸው መሀል ጥላቻን የሚዘሩ አሉ። ከወላጆች ውስጥ ሴት ልጃቸው ሁሌ በሰው ቤት ተቀጥራ እየደከመች ለነሱ ከመላክ ውጭ ትዳር መስርታ የራሷን ህይወት እንድትመሰርት የማይፈልጉ ራስ ወዳዶች አሉ። ሌሎችም ለመግለፅ የሚሰቀጥጡ ብዙ አይነት አመል ያለባቸው ወላጆችም ብዙ ናቸው። ከዚህም ሁሉ በላይ ክ^ህደት ውስጥ፣ ሺርክ ውስጥ የሚኖሩ ወላጆች ይኖራሉ። ይህ ሁሉ መኖሩ ከነ ጭራሹ ምንም አይነት ሐቅ የሌላቸው አያደርጋቸውም። አዎ! በጥፋት ላይ አላህ በሚጠላው ነገር ላይ አንተባበራቸውም። ይሁን እንጂ ከነሱ በኩል በሚገጥሙን ጥፋቶች ወይም በደሎች እልህና ቂም ይዘን ኋላ ፀፀት ላይ የሚጥለን፣ ከአላህ ጋር የሚያጣላን፣ አኺራችንን የሚያጨልም አካሄድ እንዳንሄድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በተለይ ሰዎች እድሜያቸው ሲገፋ፣ ኑሮ ሲከብዳቸው፣ ጤና ሲጎድላቸው ባህሪያቸውም ይቀያየራል። በእንዲህ ዓይነትና መሰል ምክንያቶች የሚመጡ የባህሪ ለውጦችን የግድ ልንታገስ ይገባል። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

በሪያል የተበደረ ሰው ብድሩን መመለስ ያለበት ወይ በሪያል ነው። ወይ ደግሞ ብድሩን በሚመልስበት እለት ባለው ምንዛሬ ተሰልቶ ነው። ዶላር ወይም ሌላ ከሆነም እንዲሁ። እንጂ ብድሩን ሲወስድ ጊዜ በነበረው ምንዛሬ መጠን መመለስ አይችልም። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

አንዳድ ሰዎች ጥሩ ነገር አስበዉ የሚናገሩትን ነገር። እናተ ደሞ ያ የተናገሩትን ነገር በራሳቹህ መንገድና አመለካከት ቀይራቹህ መጥፎ ነገር አትሰቡ። ያ ሰዉ የተናገረዉን ምን ነገርለማለት ፈልጎ እንደሆነ። ከአሏህና ከሰዉየዉ ዉጪ ማንም ሊያዉቅ አይችልምና። በሰዎችም መካከል ፍትሀዊ ሁኑ።ሰለፍያ በዚህ ዘመን ከአፍ ላይ ሲወጣ ንፋስ እየወሰደው ያለ ይመስላል። ከንግግር ያለፈ ተግባር የለም።

ኢላሂ ደካማ ባርያህ ነኝ።ወዳንተ በማደርገው ጉዞ እርምጃዬ ከበደኝ።ሌሎች ካንተ ምህረት የሚያገኙትን ስመለከት ካመለጠኝ ምህረት የተነሳ አንግቴን በሃዘን ደፋሁ።ልቤ ወዳንተ ቢሮጥም አካሌ ዘገየ። በ አንተ ዘንድ ከተከበሩት ባሮችህ መካከል እንደሆንኩ አይሰማኝም። ኢላሂ ወዳንተ በምጓዝበት መንገድ የተሰናከለውን እርምጃዬን  አቅና።ጥቂት የሆነውን ስራዬንም ተቀበለኝ።ትንሽ መልካም ስራም ቢሆን በ ሃፍረት ወዳንተ ይዤ እመጣለሁ።በመከራ እንደተጨነቀ ሰው ባንተ ላይ ተደግፌ፣ በጸጋህ ሙሉ አድርገህ እንደምታደርግልኝ ተስፋ አድርጌ እመጣለሁ።ኢላሂ እጄን  ባዶ አትመልስ። #ትዝብት

♦️♦️♦️የትዳር ውበት በግል ይጠበቃል ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ…ተስማምታቹኋል አይደል? አደራ መልስ እጠብቃለሁ 📍ገና ወደ ትዳር እንደገባችሁ ለምን የቤታችሁን ውስጣዊ ሕይወት ለሁሉም ለማሳየት ትቸኩላላችሁ? ወንዱም፦ “የኔ ሚስት እኮ ውብ ናት፣ የዲን እውቀት አላት፣ ታዛዥ ናት፣ አሳቢ ናት… እንደ እሷ ያለች የለችም!” ሴቷም፦ “የኔ ባል እኮ ቆፍጣና ነው፣ በዲኑ ላይ ጠንካራ ነው፣ ለኔ እንደ አባት ነው፣ እንደ ወንድምም ነው፣ እንዲህ ያለ ባል በማግኘቴ …” እንዲህ እያላችሁ የቤታችሁን ውስጥ ለምን ለሁሉም ታሳያላችሁ? ለማን ነው? ምን ለማረጋገጥ ነው? ሰዎች እንዲያደንቁአችሁ? እንዲቀኑባችሁ? ወይስ “የኔ ትዳር እንዲህ ነው” ብላችሁ ለማሳየት? እስቲ ራሳችሁን ጠይቁ፦ በሚዲያ ላይ የምትጽፉትን ሕይወት በእውነት እየኖራችሁት ነው? 📍ሁሉም እንዲህ ነው አልልም። በእውነት የሚዋደዱ፣ የሚከባበሩ፣ በዲንና በመልካም ሕይወት የሚኖሩ ባለትዳሮች ብዙ ናቸው። ነገር ግን ከሚናገሩት ተቃራኒ የሚኖሩ፣ በሚዲያ ላይ ፍጹም ትዳር የሚያሳዩ እና በቤታቸው ግን የተለየ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎችም አሉ። አንዳንዶቹንም ከጥቂት ጊዜ በኋላ በመለያየት ይታያሉ። ያኔ የሚያሳዝነው መለያየታቸው ብቻ አይደለም፤ ትናንት ለሰዎች ያሳዩት ምስልና ዛሬ የሚኖሩት እውነታ ሲጋጭ መታየቱ ነው። ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ትዳር መድረክ አይደለም። የሚያጨበጭብልህ ታዳሚ አያስፈልገውም። 📍ትዳር ሁለት ሰዎች በግል የሚገነቡት ቤት ነው። ፍቅሩም በሰዎች አይን ሳይሆን በሁለቱ ልብ ውስጥ የሚኖር ነው። ሌሎችን ማስተማር ከፈለጋችሁ፣ በግል የቤታችሁን ሚስጥር ከማውጣት ይልቅ ጠቃሚ ምክር ስጡ፦ “ባልና ሚስት እንዲህ ይከባበሩ፣ እንዲህ ይተዛዘኑ፣ ከዚህ ይታቀቡ፣ በዲናቸው ላይ እንዲህ ይተባበሩ…” ይህ ሌሎችን ይጠቅማል። 📍ነገር ግን የቤታችሁን ሚስጥር፣ የባለቤታችሁን የግል ባሕሪ፣ በእናንተ መካከል ያለውን ልዩ ቅርርብና የግል ነገር ሁሉ ለሰዎች አታውጡ። ምክንያቱም አንዳንድ ውብ ነገሮች ለማሳየት ሳይሆን ጠበቀን ለናቆያቸው የሚገቡ ናቸው። የባለቤትህን መልካምነት ለማወቅ ሰዎች ማወቃቸው አያስፈልግም። የባልሽን መልካምነት ለማድነቅ የሰዎች ማጨብጨብ አያስፈልግም። እሱ ለአንቺ መልካም ባል ከሆነ፣ አንቺም ለእሱ መልካም ሚስት ከሆንሽ፣ ያ በቂ ነው። ሰዎች ሳያውቁትም ትዳራችሁ ሊያምር ይችላል። ሰዎች ሳያደንቁትም ፍቅራችሁ ሊጠነክር ይችላል። ሰዎች ሳያዩትም ቤታችሁ በሰላም ሊሞላ ይችላል። እናም አደራ… የግል የሆነን ጉዳይ በሚዲያ ላይ አናውጣ። ትዳራችሁን ለሰዎች ከማሳየት ይልቅ ለአላህ አስውቡት። ፍቅራችሁን ለሰዎች ከመናገር ይልቅ እርስ በርሳችሁ ኑሩት። የቤታችሁን ሚስጥር ለሕዝብ ከመንገር ይልቅ እንደ አደራ ጠብቁት። ምክንያቱም የትዳር ውበት ሁሉም ሰው ሲያየው አይደለም፤ ባለቤቶቹ ብቻ እያዩት ሲጠብቁት ነው። ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba