uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Відкрити в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
914
Підписники
-324 години
-177 днів
+5330 днів
Архів дописів
✨ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ህብረት✨ 📜 ልዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት! 📜 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🌟 እንኳን ደስ አላችሁ ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎች! 🌟 በታላቅ ደስታ ና ፍቅር፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲን በመምረጥ እኛን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ላላችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታችንን እናቀርባለን። 🗓 የቅበላ ጊዜና የአቀባበል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲያችን የተማሪዎች ቅበላ መርሃ ግብር የሚከናወነው ጥቅምት 3 እና 4 ቀን 2019 ነው። በእነዚህ ቀናት፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ለእናንተ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሞቅ ያለና ደማቅ አቀባበል ያደርግላችኋል። በሰላም ወደ ግቢ እንድትገቡ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታገኙ የበኩላችንን እንወጣለን። 🤝 የእናንተ ትብብር ያስፈልገናል! ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት፣ የተሟላ አገልግሎት ለማግኘት እና የአቀባበል ቡድናችን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግላችሁ፡ የምዝገባ ፎርሙን ይሙሉ: https://forms.gle/F7gwvpVVsnsj843Z6 ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት እና የተሟላ አገልግሎት ለመቀበል፣ ማንነታችሁን ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ የቀና ትብብራችሁን በአክብሮት እንጠይቃለን።እንዲሁም ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ በቅድሚያ ከዚህ በታች ባሉት ስልኮች እየደወላችሁ የአቀባበል ቡድናችንን እንድታነጋግሩ በአክብሮት እንጠይቃለን። 📌 የአካባቢ ምደባ ማስታወሻ ወደ ግቢ ከመምጣታችሁ በፊት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ይለዩ፡- ✅ Natural Science ተማሪዎች፡- ወደ Main Campus ትመጣላችሁ። ✅ Social Science ተማሪዎች፡- ወደ Techno Campus ትመጣላችሁ። 📞 ለግንኙነትና ድጋፍ የስልክ ቁጥሮች ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ አስፈላጊውን መረጃ ለማግኘት ወይም የአቀባበል ቡድናችንን እንዲቀበሏችሁ ለማድረግ የሚከተሉትን ወንድሞች ማግኘት ትችላላችሁ፡-              📚   Main campus =>ሀሰን      ☎️        090 632 6702 =>አቡዱረዛቅ           ☎️    0942213321 =>ነቢል       ☎️   096 999 0090 =>ጂፋር    affan orromo          ☎️  +251972575000                                                      💻 Techno campu       =>ዐማር ☎️+251925882521                        =>መስዑድ affan oromo ☎️  +251937517651  =>አስዓድ   ☎️   0963298664       🧕 ለሴት እህቶች ልዩ ማስታወቂያ: የእህቶችን ስልክ ቁጥር ለምትፈልጉ እህቶች ብቻ፣ በስልክ ቁጥር ☎️ +251925882521 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።    🌹  አላህ   በሰላም ያገናኘን 🤲🌹 🎉መልካም የዩኒቨርሲቲ ቆይታ እንመኛለን!🎉

በአላህ ይዣችኋለሁ፣ነብዩን የሚወድ ... ሼር ያድርግ ለሚሉ ሰዎች መልስ 🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር !! 🍃https://t.me/abujemila25

ወዳጄ ሆይ፣ እውነተኛው መለያየት በዋነኛነት በሞት አይሆንም፤ እኛም አላህ ከፈቀደ በአኺራ እንገናኛለን። እውነተኛው መለያየት ግን አንዳችን በጀነት ሲሆን ሌላችን በእሳት ውስጥ መሆኑ ነው። ስለዚህ፣ አንድ ቀን በወንጀል ላይ ብታየኝ ሳትሰለች ምከረኝ፦ አላህን ፍራ! በለኝ። ለወንጀል አውሬ አትተወኝ አደራ። ምናልባት ከአንተ የምሰማው አንድ ቃል ለመዳኔ ምክንያት ይሆናል። አላህ እንዲህ ብሏል፦ [በዚያ ቀን ወዳጆች ከአላህ ፈሪዎች በስተቀር አንዳቸው ለሌላቸው ጠላቶች ይሆናሉ።] [አዝ-ዙኽሩፍ፡ 67] ይህንን መልዕክት ለወዳጅ ለዘመዶ በመላክ ያድርሱ።

✨ የደስታችን ተካፋይ ይሁኑ!        — ታላቅ የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ✨ ​በአላህ ፈቃድ በደሴ ከተማ ልዩና ታላቅ  የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶልዎታል! ​📅 ቀን፦ እሁድ — ጥቅምት 1 / 2019 ዓ.ል 💢 ቦታ፦ ደሴ — መስጂደ አስ-ሱና ⏰ ሰዓት፦ ከጧቱ — 2:30 ​🎙 በፕሮግራሙ ላይ የሚገኙ የተከበሩ ዑስታዞች፣ ሸይኾችና ወንድሞች፦ 1) ​ሸይኽ ሙሐመድ መኪን 2) ​ሸይኽ ሙሐመድ አሚን 3) ​ሸይኽ ሙሐመድ ኋዛል 4) ​ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ 5) ​ሸይኽ ሐሰን አሊ 6)​ሸይኽ አሕመድ አወቀ 7) ​ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ 8)​ ሸይኽ ይማም ሰዒድ ​9) ሸይኽ ሰዒድ ሙሐመድ ሚጢቆሎ) 10)ሸይኽ አብዱልአዚዝ 11)ሸይኽ በድሩዲን ዩሱፍ 12) ሸይኽ ሑሴን ኡመር 13) ሸይኽ ሐሰን ነጃሽ        ( ከወንዲሞች) 14) ​ወንድም ሙርሰል ሰዒድ 15) ​ወንድም ኢዘዲን ሻፊ 16)​ ወንድም አቡ ሹራ 17) ​ወንድም አቡ ሒበቲላህ 18) ​ወንድም አቡ ሐፍሷ (ይማም) 19) ​ወንድም አሊ ሰዒድ 20)​ ወንድም አቡ ኢምራን (እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው ዑስታዞችና ወንድሞች ይገኛሉ) ​📢 ልዩ ጥሪ፦ ይህንን መልእክት ለሌሎች በማጋራትና በዕለቱ በአካል በመገኘት የዚህ ታላቅ በረካና ደስታ ተካፋይ ይሁኑ! ​📌 ለሁሉም እንግዶች ጥሪያችን ክፍት ነው!
ቻናል
https://t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ግሩፕ
https://t.me/yedesse_selfyochi_group
ሼር ይደረግ‼

ለወላጅ መልካም መዋል እስከምን ድረስ? ~ በኢስላም የወላጅ ሐቅ በጣም የከበደ አደራ እንደሆነ ግልፅ ነው። ይህ ማለት ወላጆች ሁሌ ደጎች ስለሚሆኑ አይደለም። ወላጆች ሰዎች ናቸው። አላህ የጠበቃቸው
ለወላጅ መልካም መዋል እስከምን ድረስ? ~ በኢስላም የወላጅ ሐቅ በጣም የከበደ አደራ እንደሆነ ግልፅ ነው። ይህ ማለት ወላጆች ሁሌ ደጎች ስለሚሆኑ አይደለም። ወላጆች ሰዎች ናቸው። አላህ የጠበቃቸው ሲቀሩ ሰዎች ላይ የሚታዩ ክፋቶች ሊታዩባቸው ይችላሉ። ከወላጆች ውስጥ አመሉ ፈታኝ የሆነ አብሮ ለመኖር የሚከብድ ይኖራል። ከወላጆች ውስጥ ጥቅም ካላየ በስተቀር ለልጁ ጀርባ የሚሰጥ አለ። ከወላጆች ውስጥ በልጆቹ መሃል መርጦ የሚያዳላ ይኖራል። ከወላጆች ውስጥ የልጆቹን ክብር የሚያጎድፍ፣ ያላግባብ ስም የሚያጠፋ፣ አጥንት የሚሰብር ስድብ ከባዳ ፊት የሚሳደብ ይኖራል። ከወላጆች ውስጥ ለልጆቻቸው ትዳር እንቅፋት የሚሆኑ አሉ። ከወላጆች ውስጥ ከፊል ቤተሰባቸውን በከፊሉ ላይ እያሳደሙ በገዛ ልጆቻቸው መሀል ጥላቻን የሚዘሩ አሉ። ከወላጆች ውስጥ ሴት ልጃቸው ሁሌ በሰው ቤት ተቀጥራ እየደከመች ለነሱ ከመላክ ውጭ ትዳር መስርታ የራሷን ህይወት እንድትመሰርት የማይፈልጉ ራስ ወዳዶች አሉ። ሌሎችም ለመግለፅ የሚሰቀጥጡ ብዙ አይነት አመል ያለባቸው ወላጆችም ብዙ ናቸው። ከዚህም ሁሉ በላይ ክ^ህደት ውስጥ፣ ሺርክ ውስጥ የሚኖሩ ወላጆች ይኖራሉ። ይህ ሁሉ መኖሩ ከነ ጭራሹ ምንም አይነት ሐቅ የሌላቸው አያደርጋቸውም። አዎ! በጥፋት ላይ አላህ በሚጠላው ነገር ላይ አንተባበራቸውም። ይሁን እንጂ ከነሱ በኩል በሚገጥሙን ጥፋቶች ወይም በደሎች እልህና ቂም ይዘን ኋላ ፀፀት ላይ የሚጥለን፣ ከአላህ ጋር የሚያጣላን፣ አኺራችንን የሚያጨልም አካሄድ እንዳንሄድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በተለይ ሰዎች እድሜያቸው ሲገፋ፣ ኑሮ ሲከብዳቸው፣ ጤና ሲጎድላቸው ባህሪያቸውም ይቀያየራል። በእንዲህ ዓይነትና መሰል ምክንያቶች የሚመጡ የባህሪ ለውጦችን የግድ ልንታገስ ይገባል። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

በሪያል የተበደረ ሰው ብድሩን መመለስ ያለበት ወይ በሪያል ነው። ወይ ደግሞ ብድሩን በሚመልስበት እለት ባለው ምንዛሬ ተሰልቶ ነው። ዶላር ወይም ሌላ ከሆነም እንዲሁ። እንጂ ብድሩን ሲወስድ ጊዜ በነበረው ምንዛሬ መጠን መመለስ አይችልም። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

አንዳድ ሰዎች ጥሩ ነገር አስበዉ የሚናገሩትን ነገር። እናተ ደሞ ያ የተናገሩትን ነገር በራሳቹህ መንገድና አመለካከት ቀይራቹህ መጥፎ ነገር አትሰቡ። ያ ሰዉ የተናገረዉን ምን ነገርለማለት ፈልጎ እንደሆነ። ከአሏህና ከሰዉየዉ ዉጪ ማንም ሊያዉቅ አይችልምና። በሰዎችም መካከል ፍትሀዊ ሁኑ።ሰለፍያ በዚህ ዘመን ከአፍ ላይ ሲወጣ ንፋስ እየወሰደው ያለ ይመስላል። ከንግግር ያለፈ ተግባር የለም።

ኢላሂ ደካማ ባርያህ ነኝ።ወዳንተ በማደርገው ጉዞ እርምጃዬ ከበደኝ።ሌሎች ካንተ ምህረት የሚያገኙትን ስመለከት ካመለጠኝ ምህረት የተነሳ አንግቴን በሃዘን ደፋሁ።ልቤ ወዳንተ ቢሮጥም አካሌ ዘገየ። በ አንተ ዘንድ ከተከበሩት ባሮችህ መካከል እንደሆንኩ አይሰማኝም። ኢላሂ ወዳንተ በምጓዝበት መንገድ የተሰናከለውን እርምጃዬን  አቅና።ጥቂት የሆነውን ስራዬንም ተቀበለኝ።ትንሽ መልካም ስራም ቢሆን በ ሃፍረት ወዳንተ ይዤ እመጣለሁ።በመከራ እንደተጨነቀ ሰው ባንተ ላይ ተደግፌ፣ በጸጋህ ሙሉ አድርገህ እንደምታደርግልኝ ተስፋ አድርጌ እመጣለሁ።ኢላሂ እጄን  ባዶ አትመልስ። #ትዝብት

♦️♦️♦️የትዳር ውበት በግል ይጠበቃል ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ…ተስማምታቹኋል አይደል? አደራ መልስ እጠብቃለሁ 📍ገና ወደ ትዳር እንደገባችሁ ለምን የቤታችሁን ውስጣዊ ሕይወት ለሁሉም ለማሳየት ትቸኩላላችሁ? ወንዱም፦ “የኔ ሚስት እኮ ውብ ናት፣ የዲን እውቀት አላት፣ ታዛዥ ናት፣ አሳቢ ናት… እንደ እሷ ያለች የለችም!” ሴቷም፦ “የኔ ባል እኮ ቆፍጣና ነው፣ በዲኑ ላይ ጠንካራ ነው፣ ለኔ እንደ አባት ነው፣ እንደ ወንድምም ነው፣ እንዲህ ያለ ባል በማግኘቴ …” እንዲህ እያላችሁ የቤታችሁን ውስጥ ለምን ለሁሉም ታሳያላችሁ? ለማን ነው? ምን ለማረጋገጥ ነው? ሰዎች እንዲያደንቁአችሁ? እንዲቀኑባችሁ? ወይስ “የኔ ትዳር እንዲህ ነው” ብላችሁ ለማሳየት? እስቲ ራሳችሁን ጠይቁ፦ በሚዲያ ላይ የምትጽፉትን ሕይወት በእውነት እየኖራችሁት ነው? 📍ሁሉም እንዲህ ነው አልልም። በእውነት የሚዋደዱ፣ የሚከባበሩ፣ በዲንና በመልካም ሕይወት የሚኖሩ ባለትዳሮች ብዙ ናቸው። ነገር ግን ከሚናገሩት ተቃራኒ የሚኖሩ፣ በሚዲያ ላይ ፍጹም ትዳር የሚያሳዩ እና በቤታቸው ግን የተለየ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎችም አሉ። አንዳንዶቹንም ከጥቂት ጊዜ በኋላ በመለያየት ይታያሉ። ያኔ የሚያሳዝነው መለያየታቸው ብቻ አይደለም፤ ትናንት ለሰዎች ያሳዩት ምስልና ዛሬ የሚኖሩት እውነታ ሲጋጭ መታየቱ ነው። ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ትዳር መድረክ አይደለም። የሚያጨበጭብልህ ታዳሚ አያስፈልገውም። 📍ትዳር ሁለት ሰዎች በግል የሚገነቡት ቤት ነው። ፍቅሩም በሰዎች አይን ሳይሆን በሁለቱ ልብ ውስጥ የሚኖር ነው። ሌሎችን ማስተማር ከፈለጋችሁ፣ በግል የቤታችሁን ሚስጥር ከማውጣት ይልቅ ጠቃሚ ምክር ስጡ፦ “ባልና ሚስት እንዲህ ይከባበሩ፣ እንዲህ ይተዛዘኑ፣ ከዚህ ይታቀቡ፣ በዲናቸው ላይ እንዲህ ይተባበሩ…” ይህ ሌሎችን ይጠቅማል። 📍ነገር ግን የቤታችሁን ሚስጥር፣ የባለቤታችሁን የግል ባሕሪ፣ በእናንተ መካከል ያለውን ልዩ ቅርርብና የግል ነገር ሁሉ ለሰዎች አታውጡ። ምክንያቱም አንዳንድ ውብ ነገሮች ለማሳየት ሳይሆን ጠበቀን ለናቆያቸው የሚገቡ ናቸው። የባለቤትህን መልካምነት ለማወቅ ሰዎች ማወቃቸው አያስፈልግም። የባልሽን መልካምነት ለማድነቅ የሰዎች ማጨብጨብ አያስፈልግም። እሱ ለአንቺ መልካም ባል ከሆነ፣ አንቺም ለእሱ መልካም ሚስት ከሆንሽ፣ ያ በቂ ነው። ሰዎች ሳያውቁትም ትዳራችሁ ሊያምር ይችላል። ሰዎች ሳያደንቁትም ፍቅራችሁ ሊጠነክር ይችላል። ሰዎች ሳያዩትም ቤታችሁ በሰላም ሊሞላ ይችላል። እናም አደራ… የግል የሆነን ጉዳይ በሚዲያ ላይ አናውጣ። ትዳራችሁን ለሰዎች ከማሳየት ይልቅ ለአላህ አስውቡት። ፍቅራችሁን ለሰዎች ከመናገር ይልቅ እርስ በርሳችሁ ኑሩት። የቤታችሁን ሚስጥር ለሕዝብ ከመንገር ይልቅ እንደ አደራ ጠብቁት። ምክንያቱም የትዳር ውበት ሁሉም ሰው ሲያየው አይደለም፤ ባለቤቶቹ ብቻ እያዩት ሲጠብቁት ነው። ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

አሰላሙአለይኩም ወንድም እና እህቶቼ من أصول عقيدة أهل السنة والجماعة للشيخ صالح الفوزان ሚን ኡሱሊ አቂደቱ አሕሊ ሱነቲ ወልጀመኣ ኪታብ ሙሉ ቂርኣት ከነ ፒዲኤፉ ከሚከተለው አስፈንጣሪ (ሊንክ) ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከክፍል 1-10 https://t.me/Kitaboch/1832 https://t.me/Kitaboch/1822 https://t.me/Kitaboch/1823 https://t.me/Kitaboch/1824 https://t.me/Kitaboch/1825 https://t.me/Kitaboch/1826 https://t.me/Kitaboch/1827 https://t.me/Kitaboch/1828 https://t.me/Kitaboch/1829 https://t.me/Kitaboch/1830 https://t.me/Kitaboch/1831

*ጥፍርን የማሳደግ ብያኔ! 💅 የሴቶች ጥፍርን ማሳደግ ከነቢዩ ﷺ ሱናና ከፊጥራ ጋር የሚጋጭ ነው። ጥፍርን መቁረጥ ለወንዶችም ለሴቶችም ከተደነገጉ የፊጥራ ሱናዎች መካከል አንዱ ነው። • የጊዜ ገደብ
*ጥፍርን የማሳደግ ብያኔ! 💅 የሴቶች ጥፍርን ማሳደግ ከነቢዩ ﷺ ሱናና ከፊጥራ  ጋር የሚጋጭ ነው። ጥፍርን መቁረጥ ለወንዶችም ለሴቶችም ከተደነገጉ የፊጥራ ሱናዎች መካከል አንዱ ነው። • የጊዜ ገደብ፡ ጥፍር ሳይቆረጥ ከ40 ቀናት በላይ መቆየት የለበትም። ሶሃቢዩ አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ) እንዲህ ይላል ነቢዩ ﷺ ከ40 ቀናት በላይ እንዳናቆይ ጊዜ ወስነውልናል። ያለ ምንም ምክንያት ጥፍርን ማሳደግ የተጠላ (መክሩህ) ነው። ነገር ግን ካሀዲያኖችን ወይም ፋሲቆችን ለመመሳሰል ታስቦ ከተደረገ፣ ወይም ከጥፍሩ ስር ቆሻሻ ተከማችቶ የውዱእ ውሃ ወደ ቆዳ እንዳይደርስ ካገደው (ውዱእ እና ሶላትን ስለምያበላሽ) ሃራም ይሆናል። https://t.me/ibrahim_furii

ሰዉን ለመክዳት ብዙ ሺህ መንገዶች አሉ። ትልቁ ክህደት ግን... የማይወዱትን ሰው እወድኃለሁ ብሎ ማስመሰል፣ የማያፈቅሩትን ሰው እሞትልኃለሁ ብሎ መዋሸት፣ ሊያገቡት ልብ ያልፈቀደን ሰው አገባሃለሁ ብሎ ማዘናጋት፣ ሆነ ብሎ በሰው ሂወት ሙድ መያዝ፣ የወደደን ልብ ማንገላታት፣ በንፁህ ፍቅር ግፍ መሥራት፣ በሰው ዕድልና ዕድሜ መቀለድ፣ በአጉል ተስፋውም በሰው ዕድሜ መጫወት ነው። ​ልብን ውጭ አስቀምጦ ከአንገት በላይ ሰውን ማውራት የለየለት ንፍቅና ነው!። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

ارْحَمُوا مَنْ فِي الأَرْضِ يَرْحَمْكُمْ مَنْ فِي السَّمَاءِ በምድር ላይ ላሉት እዘኑ በሰማይ ያለው ያዝንላችኋል። እዝነትና ርህራሔ የአማኝ ልብ ዋነኛ መገለጫዎችና
ارْحَمُوا مَنْ فِي الأَرْضِ يَرْحَمْكُمْ مَنْ فِي السَّمَاءِ በምድር ላይ ላሉት እዘኑ በሰማይ ያለው ያዝንላችኋል። እዝነትና ርህራሔ የአማኝ ልብ ዋነኛ መገለጫዎችና ወደ አሏህ የሚያቀርቡ ታላላቅ የኢባዳ መንገዶች ናቸው። ነብዩ (ﷺ) «በምድር ላይ ላሉት እዘኑ በሰማይ ያለው ያዝንላችኋል » ብለውናል ። ለሰዎችም ሆነ ለሌሎች ደካማ ፍጥረታት የምናሳየው ርህራሔ የረህማንን ሰፊ እዝነትና በረከት ወደ ህይወታችን የሚስብ ታላቅ ቁልፍ ነው። በምድር ላይ ያለን ፍጡር በደግነት የመንከባከብና የማዘን ባህሪ ከአሏህ ዘንድ ምህረትና ይቅርታን እንድናገኝ ምክንያት ይሆናል። ስለሆነም እያንዳንዱን ቀን በደግነትና በበጎ ተግባር ልንሞላው ይገባል። ለተቸገረ ወንድማችን እጅ ከመዘርጋት ጀምሮ እስከ እንስሳትና ወፎች ድረስ ውኃና ምግብ ማቅረብ በአሏህ ዘንድ ቀላል የማይባል ታላቅ አጅር አለው። ልባችንን ከጨካኝነት አፅድቀን ለእዝነት እንክፈተው ዛሬ በምድር ላይ ላለው ፍጡር ሁሉ አዛኝና ሩህሩህ ስንሆን የሰማዩ ጌታ አሏህ በህይወታችን በቤታችንና በስራችን ሁሉ እዝነቱንና በረከቱን ያወርድብናል። ╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ- = t.me/FKR_ESKE_JENET

ከሞት በኋላ ላለው ሀገር መዘጋጀት 🎙በሸይኽ ከማል 🕌በደገር ከተማ  መስጂድ ኑር ላይ የተደረገ የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Yedeger_selefioch_jemea

●➝ይኑራችሁ°° ኸይር እንዲገጥማችሁ መራቂ እናት አባት፤ አብሽር ባይ መከታ ታማኝ ወንድም እህት፤ ተጨንቆ ጠያቂ አክስትና አጎት፤ በሀዘን በደስታው ከጎን የሚሆኑ፤ ይኑራችሁ ዘመድ ሞልቶ በግገኑ፤ በችግር አበርቺ ደርሶ ወጋገኑ፤ አትጡ ቤተሰብ የደስታ ሞሰብ፤ እናት ይኑራችሁ በሩቅ የምታስብ፤ ስትደክሙ አበረታች አብሽር ባይ አናብስት፤ የችግር ተካፋይ የጀግንነት አርስት፤ ሚስት ትኑራችሁ ከሩቅ የምትሰስት፤ አብሽር ባይና አፅናኝ ከጎንሽ የሚቆም፤ ይኑርሽ ውድ ባል ሰርቶ የማይደክም፤ ሚስጥርን ተካፋይ አማካሪ ወንድም፤ የምትወዱት ከልብ በሙቀት በበብርድም፤ አቤት የሚል ታማኝ ጓደኛ እሚያምናችሁ፤ አበረታች ወገን ሁሌም ይኑራችሁ፤ ✍ወንድማችሁ አቡ ሹራ https://t.me/Sobabilalmesjid https://t.me/Sobabilalmesjid

“በእውነት ዘረኝነት እየሠራ ነውን? ወይስ የምንወቅሰው የግሩፑ ስም ብቻ ነው?” ምክንያቱም ስሙን ተመልክተን የሰውን ኒያ መፍረድ አንችልም። እንዲሁም አንድ ሰው ተሳስቶ ከተገኘ፣ ምክር እንስጠውጅ፤ ሰውን በነገር አንውጋ። የሰለፊያ መንሐጅ የሚያስተምረን እውነትን በእውነት እንድንመዝን እንጂ ሰዎችን በግምትና በጥርጣሬ እንድንመዝን አይደለም። 🌍 ከአካባቢ ተነስተን ለሁሉም ተውሒድን ሱናን ሰለፊያን እናድርስ! በእውነት የሚያምረው አካሄድ ይህ ነው፦ የደሴ ልጆች የደሴን ልጆች ይሰብስቡ። የራያ ልጆች የራያን ልጆች ይሰብስቡ። የወረባቦ ልጆች የወረባቦን ልጆች ይሰብስቡ። የመርሳ ልጆች የመርሳን ልጆች ይሰብስቡ። የሀርቡ ልጆች የሀርቡን ልጆች ይሰብስቡ። የአዲስ አበባ ልጆች የአዲስ አበባን ልጆች ይሰብስቡ። ሁሉም በያለበት ይሰባሰብ ይዋደድ ይከባበር ይተጋገዝ አንዱን አንዱ አይጥላ አንዱ ከሌላው የተሻልኩ ነኝ ብሎ አያስብ በሰለፊያ ላይ አንድ እንሁን። ነገር ግን ከዚያ በኋላ፦ ሁላችንም በተውሒድ እንሰብሰብ፣ በሱና እንሰብሰብ፣ በቁርኣን እንሰብሰብ፣ በኸይር እንተባበር፣ በአካባቢ ሳንለያይ በእስልምና በሱና እንደጋገፍ። ይህ ነው የሚያምረው። አንድ አካባቢ ልጆች ተሰብስበው ቁርኣን ይቀራሉ፤ ሌላው አካባቢ ደግሞ ይህንን አይቶ ይማራል። “እነሱ እዚያ ተሰብስበው ቁርኣን እየተማሩ ነው፤ እኛም በአካባቢያችን እንጀምር እንጠክር!”ይላል። ከዚያ ሌላ አካባቢ ይነሳል። ከዚያ ሌላ። በመጨረሻም በውጭ ሀገርም በሀገር ውስጥም የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች፦ ቁርኣን የሚቀሩ፣ ኪታብ የሚያጠኑ፣ ደዕዋ የሚያደርጉ፣ ወላጅ አልባን የሚረዱ፣ መስጂድን የሚገነቡ፣ መርከዝን የሚደግፉ፣ እርስ በርሳቸው የሚጠናከሩ ትውልድ ይፈጠራል ከዛም ትልቅ የኸይር ንቅናቄ ሊፈጥሩ ይችላሉ። ⚠️ የመጨረሻ ምክሬ ለሰፊይ ወንድምና እህቶቼ የሰለፊይ ወንድማማችነት እንዳይሰበር እንጠንቀቅ። የምንሠራውን ኸይር እንመርምር፤ የምንተቸውንም ሰው በፍትሕ እንመርምር። የአካባቢ ስም መጠቀም በራሱ ዘረኝነት አይደለም። የአካባቢን ስም በመጠቀም ሌሎችን መንቀፍና ማጥላላት ግን የሚወገዝ ነው። የአካባቢን ልጆች ለማጠናከር መሰብሰብ የሚከለከል አይደለም፤ ሌሎችን በማሳነስ ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ግን አይፈቀድም። የሰለፊይ ወንድማማችነት ከደሴ ይበልጣል፤ ከራያ ይበልጣል፤ ከወረባቦ ይበልጣል፤ ከአዲስ አበባ ይበልጣል ከስልጤ ይበልጣል ከኦሮሞ ከአማራ ከትግራ ከሶማሌ ከአሜሪካ ከቻይና ከቱርክ ከሳዑድ ከሁሉ ይበልጣል የትም ሀገር ቢሆን ሰለፊይ አስከሆነ ድረስ ወንድማችን ነው እህታችን ናት ይሄ ነው ሚዛናችን። ስለዚህ ከአካባቢያችን እንነሳ፤ ነገር ግን በአካባቢያችን አንወሰን ደዕዋውን እናስፋው። ከሰፈራችን እንነሳ፤ ነገር ግን ሌላውን አንግፋ። የእኛን ልጆች እናጠናክር፤ ነገር ግን የሌላውን ልጅ አንጠላ አንርሳ። በተውሒድ እንሰብሰብ፣ በሱና እንጠናከር፣ በኸይር እንተባበር፤ የአካባቢ ልዩነታችን ደግሞ የምንተዋወቅበት መንገድ እንጂ የምንለያይበት ግድግዳ አይሁን። 🌿 አላህ ልባችንን በተውሒድና በሱና ላይ ያሰባስበን፤ በኸይር ላይ እንድንተባበር ያድርገን፤ ከጃሂሊያ የወገንተኝነት መንፈስም ይጠብቀን። አሚን። 🌿 ከአካባቢ ተነስተን—ለኡማው  ተውሒድና ሱናን እናድርስ! ውድ ሰለፊይ እህትና ወንድሞች በዚህ ፅሁፍ ላይ ስህተት ካገኛችሁ መታረም ያለበት ነገር ካለ ጠቁሙኝ አስተካክሉኝ ይሄን ፅሁፍ በመልካም ተረዱት መልካም ነገር ታስቦ የተፃፈ ነውና። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

Repost from Abu Hayder Aliy
🛑 ما نصيحتكم للشبــــــاب ، و خـــــــاصة طلبـة العلـــــم 🍁⁉️ الشيخ صالح الفوزان حفظه اللّه ጥያቄ (السؤال): በዚህ ጊዜ ለወጣቶች፣ በተለይም ለሃይማኖት ዕውቀት ፈላጊዎች (ተማሪዎች) የሚሰጡት ምክር ምንድን ነው? የሼክ ሳሊህ አል-ፈውዛን መልስ ባጭሩ (إجابة الشيخ): የወጣቶች አስፈላጊነት፡ ወጣቶች ከአላህ በመቀጠል የሕዝቡ (ኡማው) ፍሬና መሠረት ናቸው፤ ምክንያቱም ከአባቶቻቸው በኋላ ይህንን ታላቅ ኃላፊነትና የበላይነት የሚወርሱትና ለሰው ልጅ የሚያደርሱት እነሱ ናቸውና። ኃላፊነትና ጥንቃቄ፡ ለወጣቶች ትኩረት መስጠት ይገባል፤ ወጣቶችም ግዴታቸውን አውቀው ኃላፊነትን ለመሸከም ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው። ከተሳሳቱ አስተሳሰቦች መጠበቅ፡ በተለይም በዚህ ዘመን ወጣቶች ከባዕድ አስተሳሰቦች እና ወደ ጥመት ከሚጠሩ አካላት (ለምሳሌ፡ የኸዋሪጅ፣ የሙርጂኣ፣ የሙዕተዚላ እና የሌሎች መንገድ ተከተዮች አደገኛ አስተሳሰቦች) መጠንቀቅና ንቁ መሆን አለባቸው። ትክክለኛውን መንገድ መከተል፡ የነቢዩ ባልደረቦች (ሶሓባዎች)፣ ተበእዮችን፣ የተመሰገኑት ክፍለ ዘመናት ሰዎች፣ አራቱ አኢማዎችና በጎ ተከታዮቻቸው የጸኑበትን የአህል-ሱና ወል-ጀማዓን መንገድ አጥብቆ መያዝ አስፈላጊ ነው። https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy

قال الشيخ حمَّاد الأنصاري رحمه الله: ... لم يؤلِّف وينشر ويطبع ضدَّ الدعوة السلفية أحد في الدُّنيا مثل تركيا ودولة الروافض في إيران، فإنَّ العقيدة السلفية ما قلَّ انتشارها حتَّى حكم الأتراك وهم نقشبندية، والنقشبندية أعداء للعقيدة السلفية ... [المجموع: 2 - 691 ]