es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

Ir al canal en Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
321
Suscriptores
+124 horas
-77 días
+5830 días
Archivo de publicaciones
ይሄ ውብ አፕልኬሽን ተጋበዙልኝ ውድ ቤተሰቦቼ የፈለጋችሁትን የቁረአን አያ ከነትርጉሙ በዚህ መልኩ በፈለጋችሁት ከለር ኢሜጅ ማውጣት ትችላላችሁ በድምፅም አለው ምቹ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ ነው ለወንድማ
ይሄ ውብ አፕልኬሽን ተጋበዙልኝ ውድ ቤተሰቦቼ የፈለጋችሁትን የቁረአን አያ ከነትርጉሙ በዚህ መልኩ በፈለጋችሁት ከለር ኢሜጅ ማውጣት ትችላላችሁ በድምፅም አለው ምቹ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ ነው ለወንድማችን አላህ ሰደቀተል ጃሪያ ያርግለት ገብታችሁ አውርዱ

Repost from N/a
ቁርአን ትርጉም.apk20.42 MB

ባለንበት ዘመን ሁሉም ነገር በፍጥነት እየተቀያየረ ነው። አስተውላችሁ ከሆነም አብዛሀኛው ነገር ሁሉም  በሚባል ደረጃ ከቴክኖሎጂ ጋር እየተጣመረ ነው። በዚህ ሰአት ቴክኖሎጂን በደንብ የተዋወቁና መጠቀም የሚችሉ ሰዎች እንዲሁም ተቋማት ናቸው ከመንጋው ተለይተው የተሻለ ውጤታማ መሆን የሚችሉት። እኛም እንደሙስሊም ኡማ ወደኋላ ልንቀር አይገባም። ይህን ዘርፍ ተቀላቅለን ኢስላማዊ እሴቶቻችንን በጠበቀ መልኩ ራሳችንን ቤተሠባችንን እንዲሁም ሙስሊሙን ኡማ ልንጠቀምበት ይገባል። ሙስሊም ቀውይ ነው መፍዘዝና ወደኋላ መቅረት አያምርብንም። ሀይማኖታዊ እሴቴን ባከበረ መልኩ የት ልማር ብላችሁ ካሠባችሁ አንድ ተቋም ልጠቁማችሁ Riseup tech Solution ይባላሉ ሴቶችን በሴት እንዲሁም ወንዶችን በወንድ መምህራን 🖥 Fullstack(MERN) 💻 Python Programming 🖥 Basic Computer Skill 🎨 Graphic Design 🎬 Video Editing 🇬🇧 English 🇸🇦 Arabic እና ሌሎች ተፈላጊ ክህሎቶች ያስተምራሉ። የቴሌግራም  ቻናላቸውን @riseuptech ቤተሠብ በመሆን ሙሉ መረጃ እንዲሁም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ጠቃሚ  ሀሳቦችን ታገኛላችሁ። አሁን ላይ ለ10ኛ ዙር ምዝገባ ላይ ስለሆኑ ሳይሞላባችሁ ፈጥናችሁ በመመዝገብ በአካል ወይም በኦላይን በተመቻችሁ አማራጭ በመማር የቴክኖሎጂውን አለም ተቀላቀሉ።

🫀 ልብ ልክ ሁሉም ነገር በአላህ ቁጥጥር ስር መሆኑን ስትረዳ ትረጋጋለች።
አንተ የምትችለውን አድርግ፤ የተቀረውን ለአላህ ተወው። ምክንያቱም የምትፈራው ነገር ከአላህ ዕውቀት ውጭ አይደለም፤ የምትጠብቀውም ነገር ከአላህ ዕውቀት ውጭ አይደለም። የዛሬ ጭንቀትህ የነገ መጨረሻህን አይወስንም። የዛሬ መዘግየት የአላህ ውሳኔ እንደተረሳህ አያሳይም። አንድ በር ሲዘጋ ሁሉም በሮች ተዘግተዋል ማለት አይደለም። 🌿 ኢብኑ አባስ رضي الله عنهما እንዲህ ይላሉ፦ «وَاعْلَمْ أَنَّ مَا أَخْطَأَكَ لَمْ يَكُنْ لِيُصِيبَكَ، وَمَا أَصَابَكَ لَمْ يَكُنْ لِيُخْطِئَكَ.» “ያመለጠህ ነገር ሊደርስብህ አልተፃፈም፤ የደረሰብህም ነገር ሊያመልጥህ አልተፃፈም።” ይህን በልብህ በጥልቀት ስትረዳ፣ ሰዎች ከአንተ ሲርቁ አትፈራም፤ አንድ ነገር ሲዘገይ አትፈርስም፤ የፈለግኸው ነገር ሳይሆን ሲቀርም አላህ እንደሚያውቅ ታምናለህ። ⚠️ ኡመር ኢብኑል-ኸጧብ رضي الله عنه እንዲህ ብለዋል፦ «لَوْ كُشِفَ الْغِطَاءُ مَا ازْدَدْتُ يَقِينًا.» “መጋረጃው ቢነሳ እንኳ ያለኝ እርግጠኝነት አይጨምርም። እርግጠኝነት ማለት ሁሉንም ነገር አስቀድመህ ማወቅ አይደለም፤ ሁሉንም ነገር የሚያውቀውን አላህን ማመን ነው። 🫀 ●ስለዚህ የልብህን ጭንቀት አላህ ፊት አውጣ። ●ሰዎች ላይ ያልተቻለውን ከአላህ ጠይቅ። ●የሚያስፈራህን ነገር ለእርሱ አስረክብ። ●የምትፈልገውን በዱዓ ጠይቅ፤ ከዚያም “አላህ የሚመርጥልኝ ከእኔ ለራሴ ከምመርጠው ይሻላል” ብለህ ልብህን አሳርፍ። ⚠️ ምናልባት የምትለምነው ነገር ይዘገይ ይሆናል፤ ግን አላህ አልረሳህም። ⚠️ ምናልባት የምትወደው ነገር ከአንተ ይርቅ ይሆናል፤ ግን አላህ እያየህ ነው። ⚠️ ምናልባት የምትጠላው ነገር በሕይወትህ ይመጣ ይሆናል፤ ግን አንተ የማታየውን ጥበብ አላህ ያያል። «وَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ، وَعَسَىٰ أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ، وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ» 🌿 “ምናልባት እናንተ የሆነን ነገርን ትጠላላችሁ እርሱ ግን ለእናንተ ኸይር ይሆናል፤ ምናልባትም የሆነን ነገርን ትወዱታላችሁ እርሱ ግን ለእናንተ ሸር ይሆናል፤ አላህ ያውቃል፣ እናንተ ግን አታውቁም።” 🥀 ስለዚህ ልብህ ይረጋ። ● አላህ ሁሌም ካንተ ጋር ነው። ● አላህ ሁሉንም ያውቃል። ● አላህ ሁሉንም  ያያል። ● አላህ  ሁሉንም ይሰማል። ● አላህ ያዘጋጀልህ ነገር አይሳሳትም። የአላህ ውሳኔ ከአንተ ፍላጎት ጋር ባይመሳሰልም፣ የአላህ ምርጫ ሁሌም ከአንተ ዕውቀት ይበልጣል። 🫀 ልብ የሚረጋው የሚፈልገውን ሁሉ ሲያገኝ አይደለም፤ የሚያገኘውም ሆነ የሚያጣው ሁሉ በአላህ ዕውቀትና ጥበብ ስር መሆኑን ሲያምን ብቻ ነውና ጉዳዮችህን ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋ። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

ለፈገግታ ~ ከወሎ ወደ አዲስ አበባ የመጣች ሙስሊም ናት። ክርስቲያን ዘመዶቿ ልጃቸው ትምህርት ጨርሶ ተመርቆ ኖሮ ድል ያለ ድግስ አዘጋጅተዋል። እቤታቸው እንደገባች ግድግዳ ላይ የተሰቀለ "የእየሱስን" ምስል ተመለከተች። "ይሄ ነው የተመረቀው ልጃችሁ?" ብላ ጠየቀቻቸው። እሷ እንዴት ብላ የ"ፈጣሪያቸውን" ምስል ይሰቅላሉ ብላ ታስብ? እውነተኛ ገጠመኝ ነው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️ ⓵:- ፌስቡክ 🗂 👇👇👇 ተቀላቀሉ https://www.facebook.com/abw.mran.alathry m/abw.mran.alathry ⓶:- ቴሌግራም🗂 👇 https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy ⓷:- የ አረበኛ ደርሶች ትምርት መስጫ👇 https://t.me/Al_arebiyeh ⓸:- የአረበኛ ትምርቶች ኦዲዮ ማስቀመጫ👇 https://t.me/Adurusu_alarebiyeh ⓹ :-በአህሉል አሰር የሚሰጡ ደርሶች ኦዲዮ ማስቀመጫ👇 https://t.me/Abu_im_ran ⓺:- ስለ ኡዙር ቢል ጀህል መረጃ ማስቀመጫ👇 https://t.me/Al_ouzru_biljehl https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ አል አቅሷ መስጂድን የገነባው ነብይ ማን ነው ?

እስኪ ማን ነው ጭራሽ ምንም ያላጠፋ? ኧረ እስኪ ማነው ጥሩነት ለሱ ብቻ የሆነው? ከየመኑ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ አል ኢማም _አልኢባና .. ከተሰኘው ኪታብ ያገኘሗት ጣፋጭ ጥቅስ ነች ።
እስኪ ማን ነው ጭራሽ ምንም ያላጠፋ? ኧረ እስኪ ማነው ጥሩነት ለሱ ብቻ የሆነው? ከየመኑ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ አል ኢማም _አልኢባና .. ከተሰኘው ኪታብ ያገኘሗት ጣፋጭ ጥቅስ ነች ።

Repost from Abu Hayder Aliy
🌿🌿🌿🌹🌹🌹❤️❤️❤️ልባችንን ከምቀኝነት እንጠብቅ፤ ደግነትን እንለማመድ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ! አንድ ሙስሊም ሰው ልቡን ከሚያበላሹ ነገሮች መጠበቅ ይገባዋል። ከእነዚህም መካከል ምቀኝነት፣ ጥላቻ፣ ቂምና ለሌላ ሰው የሚደርሰውን መልካም ነገር አለመውደድ ናቸው። በተቃራኒው ደግነት፣ መልካም ምግባር፣ ለሌሎች መልካም መመኘትና ልብን ከጥላቻ ማጽዳት ከታላላቅ የኢስላም ባሕርያት ናቸው። 1. ምቀኝነት አደገኛ የልብ በሽታ ነው አላህ سبحانه وتعالى ምቀኝነትን ከክፉ ነገሮች መካከል ጠቅሶ እንዲህ ብሏል፦ ﴿وَمِن شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ﴾ «ከሚቀና ሰው በሚቀናበት ጊዜ ከሚያመጣው ክፋት እጠበቃለሁ።» — ሱረቱል-ፈለቅ፦ 5 ይህ አንድ ትልቅ ትምህርት አለው፤ ምቀኝነት በልብ ውስጥ ብቻ ተቀምጦ የሚቀር ሳይሆን ሰውን ወደ ክፉ ተግባር ሊመራው ይችላል። ስለዚህ ሙስሊም ሰው ልቡን ይመርምር፦ «ወንድሜ በረከት ሲያገኝ ደስ ይለኛልን? ወይስ ከእኔ እንዲወገድ እመኛለሁ?» ብሎ ራሱን መጠየቅ ይገባዋል። 2. ነቢዩ ﷺ እርስ በርሳችን እንዳንቀና አስጠንቅቀዋል ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «لا تَحاسَدوا، ولا تَباغَضوا، ولا تَدابَروا، وكونوا عبادَ اللهِ إخوانًا» «እርስ በርሳችሁ አትቀናኑ፤ አትጠላሉ፤ እርስ በርሳችሁ ጀርባ አትስጡ፤ የአላህም ባሮች እንደ ወንድማማች ሁኑ።» — ሶሒሕ አል-ቡኻሪ፣ ሶሒሕ ሙስሊም እዚህ ላይ ነቢዩ ﷺ ምቀኝነትን ከጥላቻና ከመተያየት ጋር አብረው ጠቅሰዋል። ምክንያቱም ምቀኝነት ካልታከመ ጥላቻን ያመጣል፤ ጥላቻም ወደ ግጭትና ወደ ዝምድና መቋረጥ ሊመራ ይችላል። 3. ለወንድምህ የምትወደውን ለራስህ ውደድለት ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «لا يؤمن أحدكم حتى يحب لأخيه ما يحب لنفسه» «ከእናንተ አንዳችሁ ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ ፍጹም አማኝ አይሆንም።» — ሶሒሕ አል-ቡኻሪና ሶሒሕ ሙስሊም ይህ ሐዲስ ምቀኝነትን ለማስወገድ ትልቅ መድኃኒት ነው። አንተ ገንዘብ እንዲኖርህ እንደምትፈልግ፣ ለወንድምህም እንዲኖረው ውደድ። አንተ ጤና እንዲኖርህ እንደምትፈልግ፣ ለወንድምህም ጤና ውደድ። አንተ አላህ እንዲመራህ እንደምትፈልግ፣ ለወንድምህም ሂዳያ ውደድ። ይህ ነው እውነተኛ የእምነት ባሕርይ። 4. ለሌሎች መልካም ማድረግ አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ይላል፦ ﴿إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالإِحْسَانِ﴾ «እርግጥ አላህ በፍትሕና በመልካም ሥራ ያዛል።» — ሱረቱ አን-ነሕል፦ 90 ደግነት በገንዘብ ብቻ አይደለም። ጥሩ ቃል መናገር፣ የተቸገረን መርዳት፣ የተራበን ማብላት፣ የታመመን መጠየቅ፣ ለሰው መልካም መመኘትና ከሰዎች ጉዳትን ማራቅም ደግነት ነው። 5. የምቀኝነት ተቃራኒ የሆነው መልካም ልብ አላህ سبحانه وتعالى ስለ ምእመናን እንዲህ ብሏል፦ ﴿وَالَّذِينَ جَاءُوا مِن بَعْدِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَا اغْفِرْ لَنَا وَلِإِخْوَانِنَا الَّذِينَ سَبَقُونَا بِالإِيمَانِ وَلَا تَجْعَلْ فِي قُلُوبِنَا غِلًّا لِّلَّذِينَ آمَنُوا﴾ «ከእነርሱ በኋላ የመጡትም፦ ‘ጌታችን ሆይ! ለእኛና በእምነት ከእኛ በፊት ለቀደሙት ወንድሞቻችን ምሕረትን ስጠን፤ በልባችንም በአማኞች ላይ ቂም አታድርግብን’ ይላሉ።» — ሱረቱል-ሐሽር፦ 10 ይህ ለእያንዳንዱ ሙስሊም ታላቅ ዱዓ ነው። ልባችን ከቂም፣ ከጥላቻና ከምቀኝነት እንዲጸዳ አላህን እንጠይቅ። 6. ምቀኝነት ሲመጣ ምን እናድርግ? አንድ ሰው አንተ የሌለህ ነገር ቢያገኝ፣ ልብህ ቢቀና፣ ወዲያውኑ እንዲህ በል፦ «اللهم بارك له، وارزقني من فضلك» «አላህ ሆይ! ለእርሱ በረከት ስጠው፤ ከችሮታህም ለእኔ ስጠኝ።» ከዚያም ለእርሱ መልካም ዱዓ አድርግ። ይህ ልብህን ከምቀኝነት ለማጽዳት ይረዳሃል። አላህ የሰጠውን በማየት ከመቀናት ይልቅ የሰጠህን ተመልከት፤ አላህም ከችሮታው እንዲጨምርልህ ጠይቅ። 7. ደግነት የሰውን ልብ ይለውጣል የሙስሊም ሰው ባሕርይ ለሌሎች መልካም መሆን ነው። እርሱ ቢበደልም በቻለው መጠን ይቅር ይላል፤ ሰው ቢያስቸግረውም እርሱ ግን ክፉን በክፉ ለመመለስ አይቸኩልም። አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ይላል፦ ﴿وَالْكَاظِمِينَ الْغَيْظَ وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ﴾ «ቁጣቸውን የሚቆጣጠሩ፣ ከሰዎችም የሚምሩ ናቸው፤ አላህም መልካም አድራጊዎችን ይወዳል።» — ሱረቱ አሊ ዒምራን፦ 134 ስለዚህ ወንድሜና እህቴ! ልብህን አጽዳ። ለሰዎች መልካም ተመኝ። የሌላውን በረከት አትመኝ። አላህ ለሌላው የሰጠውን አንተም እንዲሰጥህ ጠይቅ። የሌላው ስኬት የአንተ ውድቀት አይደለም፤ አላህ ለእያንዳንዱ ባሪያ የሚሆነውን ያውቃል። 👇👇 ☝️☝️ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነገር አንድ ታሪክ እንዲህ ይተረካል፦ አንድ ጊዜ አንድ ሸይኽ ነበሩ። አንዲት ሴትንም አግብተው ነበር። ባለቤታቸው ግን ሁልጊዜ ጥያቄ መጠየቅ ትወድ ነበር። አንድ ቀን፦ «የሸይኽ ሆይ! ሰውን ጀነት እንዲገባ ከሚያደርጉት ነገሮች ታላቁ ምንድን ነው?» ብላ ጠየቀቻቸው። ሸይኹም፦ «ደግነትና መልካም ስነ-ምግባር ነው» ብለው መለሱላት። ከጊዜ በኋላ ሸይኹ ለጉዞ ሊወጡ ሲሉ ከቤተሰባቸው ተሰናብተው ለመሄድ ፈቃድ ጠየቁ። ባለቤታቸው ግን የባሏን ምክር ትታ፣ በልቧ ምቀኝነት ተሞልታ ነበር። እንዲህም አለች፦ «ቆይ፣ ስንቅ ልስጥህ» ብላ ስንቅ አዘጋጀችላቸው። ነገር ግን በስንቁ ውስጥ መርዝ አድርጋ ሰጠቻቸው። ሸይኹ ግን ይህንን ሳያውቁ የተሰጣቸውን ስንቅ ይዘው ጉዟቸውን ቀጠሉ። ወደ ሰፈራቸው ሲደርሱ ምግብ ፍለጋ የወጡ ሁለት ደረሶች ከሸይኹ ጋር ተገናኙ። ሸይኹም ልጆቹን አይተው በደግነት፦ «አቦ! ከእኔ ይልቅ እናንተ ትበሉት» ብለው፣ የያዙትን ምግብ ለሁለቱ ልጆች ሰጧቸው። ልጆቹም ምግቡን በሉ። ምግቡ ግን መርዝ ስለነበረበት ሁለቱም ልጆች ሞቱ። የሰፈሩ ነዋሪዎችም ልጆቹ የሷ መሆናቸውን  የሚያውቁት ስለነበሩ፣ ሟቾቹን ወደ እናታቸው ወስደው አደረሱላት። እናታቸውም ልጆቿን ሞተው ባየች ጊዜ እጅግ አዘነች፣ እያለቀሰችም እንዲህ አለች፦ «ቀን ሳለቅስ ውዬ ደገምኩት ሌሊቱን፤ ሥራ ይጓዳል ወይ እንዲህ ባለቤቱን!» ይህ ታሪክ እንደ ተረት ቢነገርም፣ የሚያስተምረን ትምህርት ግን ከቁርኣንና ከሶሒሕ ሐዲስ መሠረቶች ጋር የሚስማማ ነው፤ ማለትም ምቀኝነትንና ጥላቻን መተው፣ ለሌሎች መልካም መመኘትና ደግነትን መለማመድ ነው። የመጨረሻ ምክር ወንድሜ! ከሰዎች ጋር ስትኖር ልብህን አታበላሽ። ማንም ሰው አላህ የሰጠውን በረከት ሲያገኝ አትቀና። ይልቁንም በረከቱ እንዲጨምርለት ዱዓ አድርግ። አላህ ልባችንን ከምቀኝነት፣ ከጥላቻና ከቂም ያጽዳልን። ለሙስሊሞች ሁሉ መልካም የምንመኝ ባሮቹ ያድርገን። ደግነትንና መልካም ምግባርን ይስጠን። ከእኛም የሚወደውን ይቀበል። اللهم طهّر قلوبنا من الحسد والحقد والبغضاء، واجعلنا من أهل الإحسان وحسن الخلق، ووفّقنا لمحبة الخير للمسلمين، وبارك لنا ولهم فيما أعطيتنا وأعطيتهم. آمين. https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy

ትራሳችን ያውቃል የአዕምሮን ጭንቀት ቢተርከው ራስ፡ በየግል ጓዳችን በእንባ በመራስ፡ ያሳለፍነው ጊዜ ቢተረክ ቢወራስ፡ ስለማይችል እንጂ አፍ መፍታቱን ትራስ፡ ማንም አይገባውም .... ከቀኑ ሳቃችን ፈገግታችን  ጀርባ፡ ዕልፍ ሲቃ እንዳለ ሆድን የሚያባባ፡ ማንም አይገባውም ውስጣችን ካልገባ፡ እናም አትቅኑብን በፊት ፈገግታችን ፡ ከውስጥ ተቀብሯል ብዙ ገመናችን፡ መፅናኛ ስላቅ ነው ፊትና ጥርሳችን፡ ይህ እውነታ በጣም እጅጉን ይደንቃል፡ የተደገፍንበት ትራሱ ግን ያውቃል .. መናገር ባይችልም ባይተነፍስም  ቃል ... ....N.... t.me/nuredinal_arebi

ለፍች ኬክ ተዘጋጅቶ ባይ ባይ እየተባለ በሚቆረስበት ዘመን ላይ ነን ።ብቻ ከባድ ነው አላህ ይዘንልን አሏሁል ሙስተዓን
ለፍች ኬክ ተዘጋጅቶ ባይ ባይ እየተባለ በሚቆረስበት ዘመን ላይ ነን ።ብቻ ከባድ ነው አላህ ይዘንልን አሏሁል ሙስተዓን

እውቀት በአፍ አይረጋገጥም 🎙አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

♦️♦️እውቀት በአፍ አይረጋገጥም 📍አንድ ሰው «እኔ አዋቂ ነኝ፣ እውቀት አለኝ» ስላለ ብቻ አዋቂ አይሆንም። ሰዎችም ስሙን በማንሳት፣ በማወደስና በማራገብ ብቻ እውነተኛ የእውቀት ባለቤት አያደርጉትም።
እውቀት በንግግር ሳይሆን በሥነ-ምግባር፣ በትህትና፣ በጥበብና በተግባር ይታወቃል።
📍እውነተኛ አዋቂ ሰው እውቀቱ እየጨመረ ሲሄድ ራሱን ከፍ አያደርግም፤ ይልቁንም ትህትናው ይጨምራል። ምክንያቱም ትክክለኛ እውቀት የሰውን ድንቁርና ያሳየዋል። ሰው የሚያውቀው ነገር ሲጨምር የማያውቀው ነገር ምን ያህል እንደሚበዛ ይገነዘባል። 📍ስለዚህ ሰዎች ስለአንድ ሰው ብዙ ቢናገሩ፣ ቢያደንቁት፣ ቢያሞግሱት ወይም «አዋቂ ነው» ቢሉት፣ ይህ ብቻ የእውቀቱ ማረጋገጫ አይደለም። እውቀት በማስታወቂያ አይረጋገጥም፤ በማስረጃ፣ በትክክለኛ ንግግር፣ በተግባርና በመልካም ባሕርይ ይታወቃል።
እውቀት ካለህ ሰዎች እንዲያውቁህ አትጩህ፤ እውቀትህ ራሱ ይመስክርልህ።
📍የእውነተኛ አዋቂ ሰው ምልክት ሁሉን እንደሚያውቅ ማሳየት አይደለም፤ የማያውቀውን «አላውቅም» ለማለት የሚያስችለው ትህትና ነው። 📍ስለዚህ ሰዎች ምን እንደሚሉህ ከመመልከት ይልቅ፣ እውቀትህ ምን ያክል እንደለወጠህ ተመልከት። ንግግርህ ብዙ ሳይሆን ጥበብ ይኑረው፤ እውቀትህ ማስመሰያ ሳይሆን መመሪያ ይሁን፤ ሰዎች የሚያደንቁህ ከመሆን ይልቅ አንተ የምታውቀውን ለአላህ ብለህ በትህትና መጠቀምህ ይበልጥ ይጠቅምሃል።
እውቀት ክብር ለማግኘት ሳይሆን ራስን ለማስተካከል ነው።
አላህ ጠቃሚ እውቀትን ይስጠን አሚን‼️ ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

السَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ ዩኒቨርሲቲያችን ደብረ ማረቆስ ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጲያ ውስጥ ካሉ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑ ይታወቃል።በመሆኑም በ2018 አመተ ልደት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈትናችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ  ፈሬሽማን ወንድም እና እህቶቻችን እንድሁም በሪሚዲያል ፕሮግራም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ አድስ ገቢ ወንድምና እና እህቶቻችን  እንዳይቸገሩ በማሰብ ከዚህ በታች ስልክ ቁጥሮችን አስቀምጧል : : በተጨማሪም ጀማዓችን ወደፊት  የእንኳን ደህና መጣችሁ መልክቱን እያስተላለፈ ከታች በተቀመጠው ስልክ ቁጥር በመደወል ስለ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንድሁም ሌሎች መረጃዎች ካስፈለጋችሁ መጠየቅ እንደምትችሉ ሲያሳውቅ በታላቅ ደስታ ነው ። 1.   ወንድም ጅብሪል ካሴ                 0929628329 2.  ወንድም ሱዴይስ አወል               0906137910 3.  ወንድም ታጅዲን 0921865701:- አማርኛ ለማይችሉና በኦሮምኛ ቋንቋ ብቻ ለምትግባቡ ወንድሞች                                             ማሳሰቢያ : እህቶች በ 0906137910 በመደወል የእህቶችን  ቁጥር ማግኘት ትችላላችሁ : : እንዲሁም የቻናል ባለቤት የሆናችሁ ወንድም እና እህቶች share በማረግ ለሁሉም እንዲዳረስ እንድታደርጉልን በአላህ ስመ እንጠይቃለን። وَالسَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ            our telegram channel https://t.me/dmumsj

አስታውስ! አስታውሽ! እናስታውስ! 👉አንድ ቀን እኛ እራሳችን የለበስነውን ልብስ ሰዎች አገላብጠው የሚያውልወቁልን ቀን ይመጣል። የተከፈተ አፋችንን እና አይናችንን ሰዎች የሚዘጉልን ቀን ይመጣል። 👉ተራምደን ከሄድንበት ቦታ ሰዎች ተሸክመውን የሚያስወጡብን ቀን የ ☞ ቤተሰብሽን እንኳን ታፍሪ የነበርሽው በሰው እጅ ገላሽ የሚታጠብበት ቀን ☞ጌጣጌጥሽ ሁሉ ከላይሽ ላይ የሚወልቅበት ቀን ✘✘✘✘✘✘✘✘✘✘ ፌስቡኬ ★Friend request ይላካል ዝም ★አሰላሙ አለይኩም ጭጭ ★ኧረ አናግሪኝ፣ ለምን ዘጋሺኝ? መልስ የለም !!! ማን ይመልስ? እኔ ወደማይቀረው አለም ሄጃለሁ ያ ራህማን !! አጂብ ልብ የሚነካ ታሪክ እባከወን ያንብቡት ¶እናት ከልጇ ሞት በኋላ ያጋጠማት ልዩ ታሪክ¶ .................. ¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶ ልጅ በአንድ የዲን ዩንቨርስቲ ተማሪ ስትሆን ልዩ ድምጽም ነበራት፡፡ በዚህም ሁለ ግዜ ለሊት ቁርአን ትቀራ ነበር፡፡ ቂራአቷም እጅግ ያማረ ነበር፡፡ እናት ወደ ክፍሏ ስትሄድ ከልጇ ከፍለ በር ላይ በመቆም ያማረ ቂራአቷን ሁል ግዜ ታዳምጥ ነበር፡፡ በዚህ አየነት ቀናቶች ያልፉ ነበር፡፡ ከእለታት አነድ ቀን ይህች ልጅ ታመመች፡ ቤተሰቦቿም ወደ ሀኪም ቤት ወሰዷት፡፡ በሆስፒታሉም ለቀናት ቆየች፡፡ ማገገም አልቻለችም ህይወቷ በሆስፒታሉ ውስጥ አለፈ፡፡ ቤተሰብ በጣም አዘነ በተለይ እናት በልጇ ሞት እጅጉን አዝናለች፡፡ የመጀመሪያው እናት ለጇን ያጣችበት ቀን የአመት ያክል ረዘመባት፡፡ መሽቶ ወደ ክፍሏ የምትሄድበት ሰአት ላይ እናት እንደለመደችው ከልጇ ክፍል በር ላይ ቆመች ይሄኔ አንድ አስደንጋጭ ነገር ሰማች ከክፍሉ ወስጥ ብዙ ሆኖ ዝግ ባለ ድምጽ ለቅሶ ይሰማል፡፡ ወደ ውስጥ ለመግባት ፈራች፡፡ እስኪነጋ ጠብቃ እናት ሌሊት ከልጇ ቤት ወስጥ የሰማቸውን ለቤተሰብ ነገረች፡፡ ወደ ከፍሉ ገቡ ምንም ነገር የለም፡፡ በሁለተኛው ቀን እናት እንደለመደችው በተመሳሳይ ሰአት ወደ ልጇ ክፍል ስትሄድ ትላንት የሰማችውን ድመጽ በድጋሚ ሰማች የሰማችውንም ለባለቤቷ ነገረችው፡፡ ባለቤቷም ሲነጋ የሰማሽው ምን እንደሆነ እናጣራለን አሁን ተኚ ይላታል፡፡ ጠዋት ላይ ወደ ከፍሉ ሲሄዱ ምንም ነገር የለም፡፡ እናት ግን ድምጹን መስማቷን እርግጠኛ ነበረች፡፡ የሰማችውን ለአነድ ጓደኛዋ ትነግራታለች፡፡ ጓደኛዋም አንድ አዋቂ ሰው ብታማከር የተሻለ እንደሆነ ትነግራታለች፡፡ እናትም አንድ ሸኽ ጋር በመሄድ ስለ ሁኔታው ነገረቻቸው፡፡ ሼኹም በሁኔታው በመገረም በሰአቱ በመገኘት ሁኔታውን ማየት አለበኝ በማለት ተነስተው ሄዱ፡፡ ከዚህ ቀደም ልጅ በቤቱ ወስጥ ትሰራው የነበረውን ሁሉ እናት ለሸኹ ነገረቻቸው፡፡ ልክ ሰአቱ ሲደርስ ወደ ክፍሉ ተጠጉ፡፡ እናት ከዚህ ቀደም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስትሰማው የነበረው የለቅሶ ድምጽ ዛሬ ለሶስተኛ ግዜ ተሰማ፡፡ሼኹ ይህንን ሲሰሙ አለቀሱ እናትም ያ ሸይኽ ምንድንው የሚያስለቅሳቹ ስትል ጠየቀች፡፡ ሸይኹም አላሁ አክበር ይህ እኮ የመላኢኮች የለቅሶ ድምጽ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ሁል ግዜ ሌሊት ልጅሽ እያለች ከሰማይ በመውረድ እየተሰበሰቡ ቁርአን ያዳምጡ ነበር አሁን ያንን ድምጽ በማጣታቸው ነው የሚያለቅሱት፡፡ ሱብሀነላህ እርሶ ዘንድ እንዲቀር አይፍቀዱ Share ያርጉት —    ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተናገሩ"አንድ ሰው በሞተ ጊዜ ዘመዶቹ በቀብር ሥነስርአቱ ላይ ሲጨናነቁ አንድ እጅግ ያማረ ቆንጆ ሰው በጭንቅላቱ በኩል ይቆማል።ጀናዛውም እንደተከፈነ ያ ሰው በከፈኑ እና በሞተው ሰው ደረት መሀል ይሆናል።ከቀብር ሥነስርአቱም በህዋላ ቀባሪ ቤተሰቦቹ ወደ ቤት  ሲመለሱ ሁለት ሙንከር እና ነኪር የተባሉ ምላኢኮች ወደ ቀብሩ በመምጣት ጀናዛውንና ያንን ቆንጆ ሰው በመለያየት ያንን የሞተውን ሰው በእምነቱ ጉዳይ  ብቻውን በጥያቄ ሊያፋጡት ይሞክራሉ ። ሆኖም ያ ቆንጆ ሰው ይናገራል "ይህ ሰው አጋሬም ጋደኛዬም ነው ብቻውንም ልተወው አልችልም። እናንተ እንድትጠይቁት ከተመደባቹ ስራችሁን መሥራት ትችላላቹ እኔ ግን ወደ ጀነት መግባቱን ሳላረጋግጥ ትቼው እልሄድም"። ከዝያም ወደ ሞተው አጋሩ በመዞር እንዲህ ይለዋል "እኔ አንዳንዴ ድምፅህን ከፍ አርገህ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀስ ብለህ ስታነበኝ የነበርኩት ቁርአን ነኝ ምንም አትጨነቅ፤ ከሙንከርና ነኪር ጥያቄና መልስ በኃላ ምንም ጭንቀት አይኖርብህም"፤ጥያቄና መልሱም ካለቀ በኃላ ያ ቆንጆ ሰው አል ማሉል አላ በተባሉ የጀነት መላኢኮች የተዘጋጀ በመልካም ሽታ የሚያውድ እና ከ ሀር በተሰራ ልብስ የተዘጋጀ  አልጋ ያዘጋጅለታል። 2. ረሰል(ሶ.ዐ.ወ) እንደተናገሩት   በቂያማ ቀን በአላህ ሱ.ወ ፊት ስንቆም ከቁርአን የበለጠ  ለኛ ሚከራከርልን አይኖርም ከነብይያትም ከ መላኢኮችም በበለጠ። 3. እባክዎን ይህን መልእክት የቻሉትን ያህል ያስተላልፉ። ረሱል (ሶ.ዐ.ወ) እውቀትን ከኔ ለሌላው አስተላልፉ አንድም አረፍተ ነገር ብትሆን እንኩዋን ብለዋል። 4. ይህ መልእክት በ አላህ ፍቃድ በቀጣይ 7 ቀናት ቢያንስ 5 ሚልዬን ሰዎች እንዲዳረስ ዱአ እያደረግን ነው። እባክዎን ይህን መልእክት ለ ቤተሰብዎ፣ ለዘመድዎትና ላሚያውቅዋቸው ሁሉ በማስተላለፍ ከተትረፈረፈው የአላህ ምንዳ ተጠቃሚ ይሁኑ። *እርስዎ ቁርአንን ሲይዙ ሰይጣን ራሱን ያመዋል። *ሲከፍቱት ይወድቃል። *እያነበቡት ሲያይ ራሱን ይስታል። *ይህንን መልእክት ሊያስተላልፉ ሲያስቡ ላማዳከምና ለማስነፍ ይሞክራል። እኔ አሸነፍኩት ምክንያቱም ለእርስዎ መላክ ችያለሁ። 🌸🌸🌸😊 5. እባክዎን ሸይጣንን ያሸንፉና ይህንን መልዕክት ቢያንስ ለ5 ሰው በ 5 ደቄቃ ውስጥ ያስተላልፉ።

Repost from N/a
ቁርዓንን ለማስተንተን የሚረዱ አስር ነጥቦች ~~~ 1. በእራስ ላይ የተረጋጋና የመተናነስን ተፅዕኖ እያሳደሩ ማንበብ። እንዲሁም የአንባቢው ግብ ሱራውን መጨረስ ብቻ መሆን የለበትም። 2. አንባቢው የተናጋሪውን የአላህን ጥራት ይገባውና ልቅና በሚያነብበት ጊዜ በልቡ ሊያስገኝ ነው። ለአላህ ቃል ነቃ ሊል! ልቡም ሊረጥብና ሊፈራ! እንዲሁም የአላህን ረህመት ሊከጅል በዚህም ሊደሰት ይገበዋል። 3. ከሸይጧን በአላህ ይጠበቅ። ከሸይጧንም የመጠበቁን እገዛ በልቡ አላህን ሊያስቀምጥ ነው። ምክንያቱም ሸይጧን አንባቢውን የአላህን ቃል አንብቦ እንዳይጠቀምበት ለማድረግ ይሸቀዳደማል። 4. ቁርዓን የሚቀራው ሰው ድምፁን ዝቅ አድርጎ አሳምሮ ልክ ትርጉሙን እንደሚፈልግና እንደሚያጠና መፍጠንንም እንደሚፈራ ሆኖ የአንቀፁን ሀሳብ ባልቋጨበት ቦታ ከማቆምና አለያም ሀሳቡ ምን እንደሆነ ሳያጤናው ማለፍ የለበትም። 5 ቁርዓንን ለማስተንተን ከሚረዳው ነገር ትልቁና አንዱ ከሰማይ ወደ ምድር እንዴት እንደወረደና ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለመሰ እንዴት እንደያዙት፣ ከዚያም ሶሃቦች ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የመጀመሪያ በሰሙት ጊዜ በነፍሳቸው ላይ ምን አይነት ተፅዕኖ እንዳሳደረባቸውና እንዴት ተቀብለው እንደተገበሩት ማወቅ ነው። 6.ሌላው ወሳኝ ነጥብ በየትኛውም ሁኔታ ስንኖር ለሕይወታችን ቁር0ንን መድኃኒት ማድረግ ነው። እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ስለ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነ-ምግባር ስትጠየቅ "ስነ-ምግባራቸው ቁርኣን ነበር" ብላ ነው የመለሰችው። 8. አንባቢው በነቢያቶችና በደጋጎች ላይ የአላህን ውዳሴ ካነበበ አላህ እያናገረው መሆኑን ያውቃል። ነቢያቶችንና ደጋጎችን መከተሉ ተፈላጊ መሆኑንም ያውቃል። አላህ ወንጀለኞችንና በደለኞችን የሚወቅስበትን ቦታ ካነበበ አላህ እያናገረው መሆኑን ያውቃል። የሚፈለገውም ከነሱ ባህሪ መጠንቀቁና መራቁ እንደሆነ ሊያውቅ ይገባል። 8. አንቀፆችን በተደጋጋሚ እንደ አዲስ ማስተንተንና አንዴ ብቻ በማስተንተን አለመገደብ፣ አንዲትን አንቀፅ አንዴ ካስተነተናት በኋላ በዛው ከልቡ ልትቋረጥ አይገባውም። ሊደጋግማትና ወደርሷም መለስ እያለ ሊያየስተውላት ይገባል።ትርጉሟም በልቡ እስኪታተም ከአንቀጿ ሊቋረጥ አይገባውም። 9. ወደራሱ ሊመለከትና ራሱንም ሊፈትሽ ይገበዋል። እውነት ከልቤ አስተንትኜዋለሁ?ወይስ አላስተነተንኩትም? ብሎ እራሱን ሊጠይቅ ይገበዋል። በውስጣዊና በውጪያዊ ስራው ቁርኣን በሕይወቱ በኢባዳው በአምልኮው ተፅዕኖ መፍጠር አለመፍጠሩን እራሱን ሊፈትሽ ይገበዋል። 10.ከቤተሰባችን ከልጆቻችን በምንቀማመጥበት ጊዜና በምንመካከርበት፣ ሙሃደራ በምናደርግበት፣ እንዲሁም መድረክ ላይ ቆመን ንግግር በምናደርግበት ጊዜ ንግግራችን ሁሉ ሊሆን የሚገባው ቁርዓንን ስለ ማስተንተንና በቁርዓን ስለመተግበር ሊሆን ይገባል። እርግጥ ነው አላህ ግንዛቤውንና ማስታወሱን አግርቶልናል። ከፍጥረተ  ዓለሙ ሁሉ በላይ ከፍ ያለው፣ የላቀው አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል፦ “ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፣ ተገንዛቢ አለን?። " አል-ቀመር 17 አላህ በአግባቡ በትክክለኛው መንገድ ለመገንዘብና ለማስተንተን በህጎቹም በትክክል ለመተግበር፣ ስነ-ምግባራችን ቁርዓን  እስኪሆንና በአኼራም "ዱኒያ ላይ ታነበው እንደነበረው አንብብ" እስክንባል ይወፍቀን። አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና። = የቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/Abulabas1444 https://telegram.me/Abulabas1444.

የፍቺ ጉዳይ ~ በኢስላም የፍቺ ጉዳይ ልቅና ገደብ የለሽ አይደለም። ሶስት ፍቺ የፈፀመ ሰው ዳግም ሚስቱን ለመመለስ ነገሩ ከባድ ነው። ባጭሩ ሸርጡን ባሟላ ኒካሕ ሌላ ሰው አግብታ የተፈታች ከሆነ ነው የመጀመሪያው መመለስ የሚችለው። አንድ ሰው ለመጀመሪያው ባል ሐላል ለማድረግ አስቦ ቢያገባት ራሱ ድርጊቱ ከባድ ወንጀል ከመሆኑም ጋር ለመጀመሪያውም ባል ሐላል ማድረግ አይችልም፡፡ እንዲህ አይነት ጣጣ እንዳይገጥም ፍቺ ውስጥ ከመግባት በፊት ቀድሞ ደግሞ ደጋግሞ ማሰብ ይገባል። እለታዊ ግጭቶች ያልፋሉ። ነገሮች ሲበርዱ ቁጭት ሊከተል ይችላል። ፍቺ ቀላል ነገር አይደለም። የሚከተሉት ውሳኔዎች ይኖራሉ። በተለይ ልጆች ሲኖሩ ተፅእኖው ከባድ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ፍቺን እለታዊ ግጭትን ሰበብ በማድረግ ሳይሆን በጥልቀት ካሰቡ በኋላ መፈፀም ይሻላል። በችኮላ ኒካሕ አውርደው ከዚያ መውጫ ቀዳዳ ፍለጋ የሚባዝኑ፣ ተጨንቀው የሚያስጨንቁ ብዙ ሰዎች አሉ። "ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ፣ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ" ይሆናል ነገሩ። በነገራችን ላይ ፍቺን ዑለማኦች ለሁለት ይከፍሉታል፣ ሱናዊ የሆነ እና ቢድዐዊ በመሆኑ የተወገዘ ብለው። እውነታው ይህ ከሆነ ሱናውን የጠበቀ የፍቺ ስርዓትን መለየት ያስፈልጋል ማለት ነው። ይህም ሴቷ ከወር አበባ ንፁህ በሆነችበት ወቅት ላይ፣ ግንኙነት ሳይፈፀም በፊት የሚፈፀም ፍቺ ነው። ሁለት መስፈርቶች አሉት ማለት ነው። 1ኛ:- ሚስት ከወር አበባ ንፁህ መሆን አለባት። በወር አበባ ወቅት ላይ ፍቺ መፈፀም ጥፋት ነው። 2ኛ፦ በንፅህናዋ ወቅትም ቢሆን ግንኙነት ሳይፈፀም በፊት መሆን አለበት። በዚህ የንፅና ወቅት ላይ ግንኙነት ተፈጽሞ ከሆነ፣ ፍቺ ቢያስብ የወር አበባ እስከሚመጣ መጠበቅ ይኖርበታል። ከዚያ ከወር አበባዋ ንፁህ ስትሆን የፍቺ ውሳኔው እንዳለ ከሆነ ግንኙነት ሳይፈፅም በፊት ፍቺውን መፈፀም ይችላል። ይሄ ሂደት የፍቺውን ውሳኔ በወቅታዊ ግጭት በደመነፍስ እንዳይፈፀም ማሰቢያ ጊዜ ይሰጣል። ይሄ ሂደት ቢጠበቅ ስንት ትዳር በወቅታዊ ግጭት ሰበብ ከመፍረስ እንደሚድን አስቡት። (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 10/2018) = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor