ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more4 436
Subscribers
+1624 hours
+487 days
+1 15030 days
Posts Archive
8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ ከእነማይ ወረዳ መምህራን ጋር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውውይት አካሔደ።
መስከረም 26/2018. ዓ.ም
የአፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ በእነማይ ወረዳ ላሉ ሁሉም መምህራን እና ርዕሰ መምህራን ጋር ባደረገው ጥሪ መሰረት በወቅታዊ ጉዳዬች፣በፍኖና በህዝብ መካከል ሊኖር በሚገባ ግንኙነት ላይ ጥልቅ ውውይት ተደርጓል።
የአረመኔ አብይ አህመድ የብልፅግና ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ ግልፅ ወረራ ከፈፀመበት ጊዜ አንስቶ በክልሉ ትምህርት የተቋረጠ በመሆኑ በቀጣይ የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስጀመር በሚያስችሉ ጉዳዬች ላይ የጋራ ምክክር በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
ትምህርትን ከፖለቲካ መሳሪያነት ከመጠቀም ባለፈ ህፃናት እንዲማሩ፣ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ሁሉም መረባረብ እንደሚገባው በውይይቱ የተነሳ ሲሆን ትምህርትን ለፖለቲካ መሳሪያነት መጠቀም ሊቆም እንደሚገባ እና ትምህርት ቤቶች ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ ሁነው የመማር ማስተማሩ ሒደት በገልተኛ አካል እንዲመራ በርካታ ተግባራት በአፋብኃ በኩል እየተከናወኑ መሆኑን በፕሮግራሙ ላይ የተገኘቱ አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ ለመምህራን ተናግረዋል።
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል ፣የክ/ጦር እና የብርጌድ አመራሮች በተገኙበት የተከናወነው ሰፊ የውውይት መድረክ አለም አቀፍ ተሞክሮዎች ፣የአፋብኃ ጥናታዊ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከፍተኛ አመራሮች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጠዋል።
ከዚህ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በመቅረፍ የአፋብኃ አመራርና አባላት ለመምህራን ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ እንደሚያደርጉ ጠቅሰው መምህራን አፋብኃ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በነፃነት መንቀሳቀስ እንዲሚችሉ ተገልጿል ።
አዲስ ትውልድ፤አዲስ አስተሳሰብ፤አዲስ ተስፋ!
ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
መስከረም 26/2018 ዓ.ም
አርበኛ ዘመነ ካሴ ለቡሬ ዳሞት ብርጌድ የኮማንዶ ተመራቂዎች ያስተላለፈው መልዕክት !!
በዛሬው እለት መስከረም 26/2018 አም በአፋብሃ ምእራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ፥የመንገሻ አቲከም አምስተኛ ክፍለጦር፣ቡሬ ዳሞት ብርጌድ ስር የምትመረቁ የኮማንዶ አባላት
እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለሁ።
መሰባሰባችን ይቀጥላል፥መሰልጠን ማሰልጠናችን ይቀጥላል።መታጠቃችን ይቀጥላል።ለህልውናችን መዋጋታችን ይቀጥላል።
ምክንያቱም በዘመኑ ልክ ያልተዘጋጀ ህዝብ ይጠፋል፥ዘመኑን ያልዋጀ ትውልድ ይበተናል።የትኛውም ማህበረሰብ አለም በየቀኑ ለምትደግሰው ጥፋት ዝግጁ ካልሆነ ይቀሰፋል።የየትኛውም ማህበረሰብ ቀጣይነት የሚረጋገጠው ለሚገጥመው ፈተና በሚሰጠው ምላሽ ልክ ነው።የገጠመን የህልውና ፈተና ነው።ለሱ ተገቢውን ምላሽ እየሰጠን ነው።ከከበቡን ጠላቶችና ነገና ከነገ ወዲያ ከሚፈጥሩልን መከራ አኳያ ሁሌም የበለጠ መዘጋጀት ስላለብን እንደዚህ መሰልጠንና መታጠቅ ጠላትን በልኩ መከላከል ይቀጥላል።እስከ ምፃት እንድንኖር እስከምፃት ዋዜማ እንሰለጥናለን፤ራሳችን እናዘጋጃለን።
የዛሬ ቁመናችን የትናንት ወዲያ ገናና ታሪካችን ካወረሰን ኩራትና የትናንት ውርደታችን ከፈጠረው ቁስላችን ላይ የበቀለ ነው።ክብርና ኩራታችን እንንከባከባለን።እናፋፋዋለን።በቁስላችን እንቆጫለን፤ እንንገበገባለን ፤ዳግም እንዳንቆስል ሌሊትና ቀን እንሰራለን።
ዛሬ የቀደመው ግርማዊ ማንነታችንም ፥ የትናንት ህመማችንም ወደ ሀይል ፥ወደ ገንቢ ጉልበት ቀይረነዋል።በመሆኑም ነጋችን ሰላማዊና ብሩህ ይሆናል።
የትናንትን ማራኪና አስቀያሚ መልኳን አንረሳም።ውርደታችን በፍጹም አይደገምም።ከዚህ በኋላ አንገት አንደፋም።እስከድል መሳሪያ አንዘቀዘቅም።
ትግላችን በብዙ ውጣውረዶችና ወጀቦች መሃል እያለፈ እዚህ ደርሷል።ዛሬ ላይ ተስፋና ድልን ያዘለ ነገን ጨብጧል።የቀን ጉዳይ እንጅ የማሸነፋችን ስንክሳር ሰማዩ ላይ በቀይ ቀለም ተፅፏል።ያፍረከረክነውን ጠላት በርግጠኝነት እናሸንፈዋለን።
ይህ ይሆን ዘንድ መፅናት ያስፈልገናል።የታጋይና የትግል ስኬት ቁልፍ ፅናት የሚባል ቃልና ፅኑ ስነልቦና ውስጥ ነው የተደበቀው።ያልፀና አያሸንፍም።ከሚሊዮን ሰራዊት እፍኝ ፅናት አሸናፊ ያደርጋል።አለምን የፀኑ ይገዟታልና እንፅና።
በቀን ተቀን የትግል ህይወታችን ውስጥ ከጎናችን ካለ ታጋይ ሊነሳ የሚችል ትግልን መቋቋም ትልቁና ከባዱ የትግሉ አካል ነው።መድሃኒቱ ቅንነት፥ወንድማማችነትና የምር ጓዳዊነት ነው።እርስበርስ እንዋደድ።የሰው ልጅ ቅን ሆኖ የከሰረው ክፉ ሆኖ ያተረፈው ነገር የለም።ቅን እንሁን።
የአማራ ትግል እየተሰበሰበ ነው።ከዚህ የበለጠ ቅልብጭ ብሎ መሸከፍ ይኖርበታል።ለድላችን በሚያስፈልገው ልክ ጥብቅ ብሎ መቋጠር ይኖርበታል።ተርፎን የምንተወው ታጋይና በቅቶን የምንጥለው አታጋይ አይኖርም።ይህም እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል።
በቅርቡ አለምን ጉድ የሚያስብሉ ዘመቻዎች ይኖሩናል።
በርቱ! በድጋሜ እንኳን ደስ ያላችሁ፥መልካም የትግል ጊዜ!
ይህ ትውልድ ለመከራ ሳይሆን ለድል የተኳለ ትውልድ ነውና እናሸንፋለን።
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!
አንድ አማራ!
እስከምፃት አማራ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!
አርበኛ ዘመነ ካሴ
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
➾የኦሮሙማው ተላላኪው ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ፋኖን አስተነፍሳለው ብሎ በትእቢት መዛቱ ይታወሳል‼
ባንዳው ተመስገን ጥሩነህ ሰሞኑን የፀጥታ አካላትን ሰብስቦ ባንዳ እያለ ሲያለቃቅስ ብዙዎችን አስገርሟል።
ባንዳነትንማ የሚያውቀው ምስለኔው ተላላኪው ብአዴንና መሠሎቹ ናቸው።
የአማራ ፋኖ ብአዴንን በሚገባ ካስተነፈሰው በኋላ አጨብጫቢው ተመስገን ባንዳ ያለው ራሱ ይሆን?
ሃሳብ ስጡበት ለዚህ ሰውዬ
+2
በፋኖ መሪነት የሚመራው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ መላው የአማራ ህዝብ የሚሳተፍበት፣ አስተያዬት እና ሀሳቡን የሚሰጥበት እንዲሆን የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት ስንሰራ መቆዬታችን ይታወቃል።
እነሆ በዛሬው እለትም ከምስራቅ ጎጃም እነማይ ወረዳ የተውጣጡ ከ1200 በላይ መምራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር አንድ ቀን የፈጀ ውይይት አድርገናል። መምህራኑ ካቀረቧቸው ጥያቄወች መካከል ትምህርትን በተመለከተ ወጥ አሰራር እንዲኖር፤ መምህራን በግላዊ እንቅስቃሴያቸው ደህንነታቸው እንዲጠበቅ እንዲሁም የትምህርት ጉዳይ ቀጣይ ስለሚኖረው አቅጣጫ የሚመለከቱት ይገኝባቸዋል።
በእኛ በኩል መምህራንን ጨምሮ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ከጠላት ተልዕኮ ወስዶ እስካልሰራ ድረስ በማንኛውም ቦታ እና ሁኔታ በነፃነት መንቀሳቀስ እንዲችሉ ለመዋቅራችን መመሪያ መውረዱን፣ የትምህርትን ጉዳይን ወጥነት በተመለከተ እንደ አፋብኃ በሚሰጥ ውሳኔ እንዲፈፀም እንደምንሰራ እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ከወታደራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ነፃ ሆነው እና የወደሙ ተቋማት ተጠግነው ትምህርት ይቀጥል ዘንድ አገዛዙ ላይ ጫና እንዲያደርጉ እና በእኛ በኩል እነኝህን ሁኔታወች የሚያስተካክል ፕሮጀክት እንዲፈፀም ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን አሳውቀናል። በዚህ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀ የመፍትሔ ሀሳብን የያዘ ሰነድ ላይም ውይይት አድርገናል።
መድረኩን ላመቻቹልን የአባ ኮስትር ብርጌድ አመራር ምስጋና እናቀርባለን!!
~ አፋብኃ በላይ ዘለቀ እዝ እንደጎንደር ቀጠና ያሉ ልዩነቶችን በመፍታትና ወደ አንድት ለመምጣት በሙሉ ሀይሉ በመስራት ላይ ይገኛል ሁሉንም ሀይላችን ወደጠላት አዙረን ለመረባረብ በፍፁም ሀቀኝነትና እዉነተኝነት እንትጋ።
ሳሙኤል ባለ ድል
መታወቅ ያለበት እና ትልቁ ጉዳይ፦ የአምሓራ ጀኖሳይደር ጠላቶች እና ተላላኪ ባንዳዎች፡ በየትም ስፍራ፣ በየትም ቦታ እና አካባቢ ተገኝተው፣ ተደብቀው እና ተከልለው በፋኖ ከመቀጣት አይድኑም።
በሸክ እና ሀጂ
በመርጌታ እና ቄስ
በፖስተር እና ነብይ የእምነት የማዕረግ ስሞች እንዲሁም የጎጥ እና ጎሳቸው ጭንብልነት፣ በእምነት ተቋማት ምሽግነት ተከልለው ከፋኖ ፍትሃዊ ቅጣት ሊተርፉ አይችሉም።
የአገዛዙ፣ የሴራ ግድያዎች፣ የእምነት ግጭት ለማስፋፋት እንደሚሰራ ከማሳወቃችን ለጥቆ፣ አጥፊዎችን ያለአንዳች ድንበር ዘልቆ የመቅጣት ህልውናዊ ግዴታ ውስጥ ያለ ፋኖ መብት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል!!!
🔥የብልፅግና አመራር ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ መኪና ላይ እርምጃ ተወስዶበታል‼️
መስከረም 26/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ከቡሬ ከተማ በመነሳት ወደ ቲሊሊ ከተማ ሲግተለተል በነበረው የአረመኔዉ ሀይል ላይ የጎጃም አገዉ ምድር ፈርጦች #ቲሊሊ_ዘንገና_ብርጌድ #ዉንድይ ተብሎ ከሚጠራዉ አካባቢ ደፈጣ በመያዝ በጠላት ላይ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት አድሰዋል
የብልፅግና አመራርና የአሸባሪዉ ሹማምንት ይዛ በነበረች መኪና ላይ የታለመ ድብደባ ተፈፅሞ መኪናው ከጥቅም ውጭ ሁኗል‼
በዚህ የተበሳጨው ገዳይ በቡድን ቲሊሊ ከተማ አቅራቢያ አባ ጌ ይታይህ ደሴ የተባለ ከብት የሚጠብቀዉን የ75 አመት ሽማግሌ በጥይት ደብድበው ረሽነውታል!!
ፋኖ አለበል አወቀ የዘንገና ብርጌድ ህ/ግንኙነት ኃላፊ
26/ዐ1/2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)
ተጠናክሮና በድል ታጅቦ በቀጠለው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ወልድያ ሐራ መገንጠያ ጉምሩክ ኬላ ላይ አንድ ፓትሮል የብልፅግና ካድሬ እስከ አጃቢዎቻቸው በአርፒጂ ተደመሰሱ::
አሳምነው ክፍለጦር 2ኛ ሻለቃ ቃኝ ዛሬ መስከረም 26/2018 ዓ.ም ማለዳ ሐራ አድረው ወደ ወልድያ ይጓዙ የነበሩ የሰሜን ወሎ እና ወልድያ ከተማ የተለያዩ የፀጥታና የፖለቲካ አመራሮች መካከል አንዱን ፓትሮል ሙሉ ለሙሉ በአርፒጂ ያጋዩት ሲሆን አንድ መቶ አለቃ አመራርን ጨምሮ ሶስቱ ወዲያው ሲሞቱ የጉባላፍቶ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዝናቤ አከለን ጨምሮ አምስቱ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል::
ጥቃቱ የተፈፀመው የብልፅግና አመራሮቹ ወልድያ ከተማ ማደር ስለማይችሉ ሐራ ከተማ አድረው ማለዳ ወደ ወልድያ ከተማ እየተጓዙ ባሉበት ሲሆን ይህንን መሰሉ እርምጃ በቀጣይም ባንዳና አገር አፍራሽ ላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
መስከረም 26/2018 አ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥#ተቋማዊ_ፍተሻው_ተጠናክሮ_ቀጥሏል‼️
የአፋብኃ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ከወታደራዊ ኦፐሬሽኖችና ከሕዝብ አስተዳደር ባሻገር ተቋም የማዘመን ስራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በዚህም መሠረት የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ 6ኛ ክ/ጦር አመራሮች ከማቻክል በላይ ዘለቀ ብርጌድ አመራሮች ጋር ጥልቅ የሆነ ውይይት አድርጓል።
በውይይቱም የብርጌድ አመራሩ ደካማና ጠንካራ ጎኖች የተገመገሙ ሲሆን አመራሩ የነበሩባቸውን ድክመቶች እንዲያርሙና ጠንካራ ጎኖችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የ6ኛ ክ/ጦር ህ/ግ
26/ዐ1/2018 ዓ.ም
የአድማ ብተና አባላት ብሬን ይዘው ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ዛሬ መስከረም 26/2018 ዓ/ም ስቦ ማስከዳቱን በውጤት አጠናቋል ።
ጎንደርና ጠዳ ከተሞች የነበሩ የአገዛዙ አድማ ብተና አባላት ለመንግስት ሎሌ መሆንና ህዝብ ላይ መተኮስ በቃን በማለት የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አሀድ የሆኑትን ፋሲለደስ እና ቃኘው ብርጌድን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ ።
የአድማ ብተና አባላቱ 1ብሬን ፣ 11 ክላሽንኮቭ 13 ቦንብ፣ 23 ካዝና እና በርካታ ተተኳሾች ይዘው በፍቅር የተቀላቀሉ ሲሆን 1 ብሬን ከ3 ክላሽ ቃኘው ብርጌድን 8 ክላሽ ደግሞ አፄ ፋሲል ብርጌድን ምርጫቸው አድርገዋል።
አሁን ላይ ጠዳ ከተማ ያሉ የአገዛዙ የፖለቲካ አመራሮች ፣የአድማ ብተና እና ፖሊስ አባላት ከስቦ ማስከዳቱ እጃችሁ አለበት በማለት ተጠራርገው ታስረዋል ውጥረቱም አይሏል ምን አልባት የእርስ በርስ ግጭት ሊነሳ ይችላል ።
ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦርንም ማንም የአማራ ተወላጅ ለበሰበሰ ስርዓት ማገዶ መሆን የለበትም በማለት ኑ እራሳችሁን ከሞት ታደጉ ሁሌም ከመተኮሳችን በፊት ከመጣችሁ በራችን ክፍት ነው እያልን ለጊዜው ስማቸውን እና ፈቷቸውን ለደህንነት ሲባል ከመግለፅ ተቆጥበናል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና
በላይ ዕዝ
መስከረም 26/2018 ዓ/ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሻለቃ መሪውን መደምሰስ ያስቻለ የደፈጣ ጥቃት ተፈፀመ።
በትናንትናው ዕለት በምሽት ከደጋዳሞት ወደ ደንበጫ ሲንቀሳቀስ በነበረ ጠላት ላይ እንጀኔ ከተማ ላይ የኢንጅነር ክበር ተመስገን ልጆች ጥቃት በመፈፀም ሻለቃ መሪውን ጨምሮ በርካታ የአረመኔው ሰራዊት አመራሮችን ደምስሰዋል።
በደፈጣው ከ13 በላይ ሰራዊት የተደመሰሰ ሲሆን ሻለቃ ማዕረግ ያለው ፣ሻንበል መሪ፣ የሰው ኃይል አመራር የነበሩ ከተደመሰሱት መካከል መሆናቸውን ከመታወቂያቸው ላይ ማረጋገጥ ተችሏል።
አረመኔው ሰራዊት ይንቀሳቀስበት የነበረውን 5 መኪና ጎማውን በመምታት ውጊያው የተጀመረ ሲሆን በርካቶችንም ቁስለኛ ማድረግ ችለዋል።
ሊደመሰስ መሆኑ የገባው ጠላት ዙ23 እና ፔንፔ ከደንበጫ ከተማ በማምጣት ቀሪዎችን ይዞ ወደ መደበቂያ ኮንክሪት ምሽጉ ገብቷል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
መስከረም 26/2018 ዓ.ም
ሰበር ‼️
የደፈጣ ጥቃት ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ‼️
የብልፅግና አመራር ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ መኪና ላይ እርምጃ ተወስዶበታል።
መስከረም 26/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ከቡሬ ከተማ በመነሳት ወደ ቲሊሊ ከተማ ሲግተለተል በነበረው የአረመኔዉ ሀይል ላይ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የጎጃም አገዉ ምድር ፈርጦች #ቲሊሊ_ዘንገና_ብርጌድ #ዉንድይ ተብሎ ከሚጠራዉ አካባቢ ደፈጣ በመያዝ በጠላት ላይ ሰብአዊ ቁሳዊ ጉዳት አድርሰዋል።
የብልፅግና አመራርና የአሸባሪዉ ሹማምንት ይዛ በነበረች መኪና ላይ የታለመ ድብደባ ከጥቅም ውጭ ሁኗል‼️
ይቀጥላል ገና‼️
ይበልጣል የዉነቱ ጀግናዉ
የህዝባዊ ንቅናቄ መድረኮች እንደቀጠሉ ናቸው።
መስከረም 26/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አመራሮች በደባይ ጥላትግን ወረዳ እመውላድ ቀበሌ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ተካሂዶል።
በመድረኩም የክፍለ ጦር እና የብርጌዱ አመራሮች በተገኙት በእመውለድ ቀበሌ ህዝብ በመሰብሰብ ሰለ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድረገዋል።
በውይይቱም የመልካም አሰተዳደር ችግሮች በተመለከተ፤የፋኖ እና የህብረተሰብ ግንኙነት በተመለተ፣የጎበዝ አለቆች የሰራ አፈፃፀም በመገምገም ከአባት አርበኞች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎል።
በውይይቱ የተገኙት ተሳታፊዎች የአ.ፋ.ብ.ኃ የሚታየው አንድነት እንዳስደሰታቸው ጠቅሰው በአጠቃጣይ ትግሉን ለመደገፍ ከድርጅቱ ጋር እንደሚቆሙ በጥብቅ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ውይይቱን የመሩት የክፍለ ጦር አመራሮች ፋኖ እያደረገ ለሚገኜው የህልውና ትግል ማህበረሰባችን በሎጀስቲክ፣በመረጃ እንዲሁም በሆላ ደጀንነቱ እንዲቀጥል አቅጣጫ በመስጠት ውይይቱ በሰላም ተጠናቋል።
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አመራሮች እንድሁም የዛምበርሃ ብርጌድ አመራሮች ወታደሩን ከማንቃት ጎን ለጎን በደጀን ወረዳ የሚገኙ ቀበሌወች ላይ በመዘዋወር ተከታታይ የምክክር መድረክ በማዘጋጀት ህዝብን እያነቁ እና የፍትህ አሰጣጥ ሂደቱ የተሳለጠ እንዲሆን የፍትህ አካላትን አዋቅረዋል።
አዲስ ትውልድ፤አዲስ አስተሳሰብ፤አዲስ ተስፋ!
ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
መስከረም 26/2018 ዓ.ም
