uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
4 444
Підписники
+1624 години
+487 днів
+1 15030 днів
Архів дописів
#አንድ_ተሳቢ_ሀይል_አመድ_ሁኗል💪 #ቲሊሊ_ዘንገና_ብርጌድ_የደፈጣ_ጥቃት ‼ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክፍለ ጦር ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ ዛሬም ጀብድ ፈፅሟል‼ ለተከታታይ ሁለት ቀን ከቡሬ ወደ ቲሊሊ እየተግተለተለ ሲያልፍ በነበረ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ላይ #ቲሊሊ ከተማ አቅራቢያ #ኩርብ_ተራራ ላይ በተፈፀመ ጥቃት አንድ ተሳቢ ሀይል አመድ ሁኗል። ይህ አሸባሪ ቡድን የጣራሞት ሩጫ እያደረገ ባለበት በዚህ ወሳኝ ሰሃት እንሰለጥናለን፣ እንመረቃለን፣ እያጠቃን እየማረክነ እያታጠቅነ እንገኛለን። ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ ትላንት መስከረም 26/2018 ዓ.ም ከኮሰበር እስከ ወንድይ ሁለት ግንባሮች አስደማሚ ድል መፈፀሙ ሳይዘነጋ ዛሬም ሌላ ታምር ሰርቷል። ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ የደፈጣ ጠበብቶች የአገዉ ምድር ኩራቶች ዛሬም እንደ ትናንቱ በአራዊቱ በድን ላይ በወሰዱት ጥቃት አንድ ተሳቢ ሙሉ ሃይል አመድ አድርጎታል። ላንጨርስ የጀመርነዉ ትግል የለም💪💪💪 ፋኖ አለበል አወቀ የዘንገና ብርጌድ ህ/ ግንኙነት ኃላፊ 27/ዐ1/2018 ዓ.ም

አዲሱ ትውልድ መከራውን ሁሉ ተቋቁሞ ወደፊት እየገሰገሰ ነው። አብራጂት ብርጌድ

ሰበር‼️ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ ታምር ሰርቷል‼️. የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ ጠላትን አጭዶ ከምሮታል።

የቴወድሮስ ዕዝ ትንታጎች በመካነሰላም ሰማይ ስር !✈️ ከደባይ ጮቄ ብርጌድ እና አባ ኮስትር ብርጌድ የተውጣጡ አልሞ ተኳሾች ናቸው:: ለመስከረም 23ቱ ኦፕሬሽን አረንዛው ጎንቻ ብርጌድ እና ሶማ ብር
የቴወድሮስ ዕዝ ትንታጎች በመካነሰላም ሰማይ ስር !✈️ ከደባይ ጮቄ ብርጌድ እና አባ ኮስትር ብርጌድ የተውጣጡ አልሞ ተኳሾች ናቸው:: ለመስከረም 23ቱ ኦፕሬሽን አረንዛው ጎንቻ ብርጌድ እና ሶማ ብርጌድም የላኳቸው ጀግኖች ነበሩ:: የ8ተኛ እና 9ኛ ልዩ ኮማንዶዎች ከመካነሰላም እና ወግዲ ፋኖዎች ጋር ጀብዱ ፈጽመዋል። ማንኛውም አማራ የዕዝ ሰንሰለቱን ጠብቆ የፈለገበት ቦታ ሄዶ መታገል ይችላል:: የመካነሰላም እና ወግዲዎችም መርጦለማርያም ይሻገራሉ:: ከዚህ ቀደም መካነሰላሞች ተሻግረው ጀብዱ ፈፅመው ያውቃሉ:: ጎጃም መጣብን ቤተአማራ ወረረን ጎንደር ዘመተብን ሸዋ መታን ምናምን ብሎ ነገር የለም:: ክልላችን ውስጥ ያለው የአፋብኃ ሰራዊት በፈለገበት ቦታ በፈለገበት ዕለት ይገባል:: ሰራዊቱ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የማንንም ፍቃድ እንደማይጠይቀው ሁሉ አማራ ክልል ውስጥም የጎጥ አበጋዞችን ይሁንታ አይሻም:: አሁን አፋብኃ ተመስርቷል:: ድርጅታዊ እንቅስቃሴን መገደብ አይቻልም! አፋብኃ በደም የተመሰረተ ዕንቁ ደርጅታችን !

🟥 መረጃ ባህር ዳር‼️ የጥንቃቄ መረጃ ‼️ከባህርዳር ወደ ዘንዘልማ መስመር ትላንት ስንቅ ውሃ ወስዷል ዛሬ ደግሞ ሀይሉን ጭኖ እየሄደ ነው 👇👇👇👇 አስቸኳይ መረጃ‼️ ድጋሚ በቀን 27/01/2
🟥 መረጃ ባህር ዳር‼️ የጥንቃቄ መረጃ ‼️ከባህርዳር ወደ ዘንዘልማ መስመር ትላንት ስንቅ ውሃ ወስዷል ዛሬ ደግሞ ሀይሉን ጭኖ እየሄደ ነው    👇👇👇👇 አስቸኳይ መረጃ‼️ ድጋሚ በቀን 27/01/2018 ከባህር ዳር መኮድ የተነሳ ብዛቱ 50 ተሳቢ መከላከያ ዛሬ ወደ ጎንደር አቅጣጫ ወጠዋል በአንድ ዲሽቃ ብቻ ሙሉ ጥቁር ኮላሽ የታጠቀ ሀይል ነው በደፍጣ ቢደፈጠጥ ለወገን አድርሱልን ሲሎ ለአማራ ድምፅ አድርሰዋል። መረጃው በፍጥነት ይድረስ‼️

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዐፄ ዘራያቆብ ኮር!! መስከረም 26/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘራያቆብ አን
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዐፄ ዘራያቆብ ኮር!! መስከረም 26/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ)  ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘራያቆብ አንደኛ ኮር ስር የሚገኘው የሰባት ለሰባ  ክፍለ ጦር  የአብይን ወንበር አስጠባቂ ቅጥረኛ በኤፍራታ ግድም ወረዳ አጣዬ ከተማ መቀመጫ በማድረግ በእዬግዜው ህዝባችንን ሰላም በማሳጣት የእለት ከለት ስራቸው ያደርጉትን ባንዳ ቅጥረኛ ሚኒሻ ቦታ ድርስ ዘልቆ በመግባት ትልቅ ስራ ሰረተዋል!! ሆኖም ነብሮቹ የሰባት ለሰባ ክፍለጦር ቃኝዎች እና የደመላሽ ሻለቃ ቃኚወች በጋር በመሆን የበላይኛው አጣዬ አካባቢ ተረተር ባቡር ሀዲዱ ላይ መሽጎ የነበረውን የብአዴን ሚሊሻ ከሌሊቶ አስር ሰአት ላይ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የድል ባለቤትነታቸውን በተግባር አሳይተውናል። የአገዛዝ ወነበር አስጠባቂ በሞትና በህይወት ሞቶ በሃሳበ በመወተርተር ላይ ያለው የቀንድ አውጣው ነፍስ ገዳይ ሚኒሻና የብርሃኑ ጁላ መከላከያ እያሰቃዩት ያለውን ህዝባችን ነፃ የምናወጣበት ግዜ ቅርብ ነው። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የአፂዘራያቆብ ኮር ህዘብ ግኑኝነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ         መስከረም 26/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

🔥#የአረመኔው የብልጽግና ሠራዊት የጨረቃ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቁሳቁስን አውድሟል‼️ በአማራና አማራነት ላይ ሁለንተናዊ ጥፋት እያደረሰ የሚገኘው የፋሽስታዊው የብልጽግና አገዛዝ ሥርዓት በሕዝባችን ላይ ጅምላ ፍጅት በማወጅ ይህንን የጥፋት አጀንዳውን ማስኬድ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። ይሁን እንጅ ይህንን አረመኔያዊ ተግባር በመቃወም የአማራ ሕዝብ በአንድነት ወጥቶ ሕልውናውን የማስከበርና ይህንን አውዳሚና ጨፍጫፊ ስርዓት ከገጸ ምድር  ለማስወገድ በሚያካሂደው እልህ አስጨራሽ ትግል ሽንፈቱን ያረጋገጠው ይህ ስርዓት የትውልድና የተማረ የሰው ኃይል ቅብብሎሹ እንዲቋረጥና መጭዎቹ ዘመናት ለአማራ አስቸጋሪ እንዲሁኑ ያለ እረፍት እየሰራ ይገኛል። ከእነዚህ መካከልም አማራው በተማረ የሰው ኃይል እጥረት ከፍተኛ ውድቀት እንዲገባ የትምሕርት ተቋማትን ማውደም ተቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ ይዞታል። በደምበጫ ከተማ ተወሽቆ ሕዝብን እያሰቃየ የሚገኘው የአረመኔው ብልጽግናና ወራሪ ሠራዊቱም በእነዚህ ተቋማት ላይ መጠነ ሰፊ እያደረሰ መሆኑን አስቀድመን መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ላየም ይህንን ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ለአብነት ያክልም በደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የምትገኝ የጨረቃ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን የወታደር ካምፕ በማድረግ በውስጡ ያሉ ንብረቶች መፅሐፎች፣ወንበሮች፣ብላክ ቦርዶች፣ኮምፒተሮች፣በሮች፣የመፅሐፍ መደርደሪያዎችና ሌሎች ንብረቶች በአገዛዙ ወንበር አስጠባቂው ሰራዊት ወድመዋል። ውሸታቸው የማያልቅባቸው የስርዓቱ ወንበር አስጠባቂ የትምህርት አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት በየጨረቃ አርበኞችና 2ተኛ ደረጃ ትምርት ቤቶች በተሳካ ሁኔታ ትምህርት አስጀምረናል እያሉ ሲያወሩና የውሸት ሪፖርታቸውን ሲነዙ የነበረ ቢሆንም እውነታው ግን ለትምህርት የሚሆኑ ቁሳቁሶች በሙሉ በወራሪ ሠራዊታቸው መውደሙን ማረጋገጥ ችለናል። መስከረም 27/2018 ዓ.ም ድል ለሕዝባችን! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ 27/ዐ1/2018 ዓ.ም

ከዝንብ ማር አንጠብቅም ! ከኢሕዴን ብአዴን አዴፓ ብልፅግና የአማራ ህዝብ ጠላትን በ ቀዳዳ አንቀልባ  አዝለው ከ አማራ ህዝብ ጫንቃ ላይ  ያስቀመጠው  ፥ ለሄደ ለመጣው የአማራ ጠላት እንደ ሕዳር አህያ ጀርባውን የሚያከራያው ተላላኪው ዳውላ አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዴት የተከበረውን የአማራን ህዝብ  ''ተላላኪ ባንዳ'' ብሎ የእራሱን መጠሪያ ስም ለህዝባችን ሊሰጥ ቻለ ? ብለን ከጠየቅን ፥ መልሱ "የእማየን ወደ አባየ" ነው ። ስልጣን ለማግኘት ባንዳነት መስፈርት እና የስራ ልምድ ሲሆን  በጊዜ ሂደት ከጤና ጣቢያ ዘበኝነት ወደ ምክትል ጠቅላይ ሚንስቴርነት እንደሚያበቃ በዓይናችን ያየነው በተመስገን ጥሩነህ ነው ። አባቶቻችን እና እናቶቻችን " አሟሟቴን አሳምርልኝ" የሚሉት በህዝብ ዘንድ የማይረባ ፣ ከንቱ እና የትውልዱ ዕዳ ሆኖ ላለመሞት ነው ። ዳሩ ግን ተመስገን ጥሩነህ አጎብዳጅነት እና ተላላኪነት በህይወት ዘመናቸው ጊዜ አሳጥቷቸው ስለነበረ የአማራን ህዝብ እሴት፣ ባህል፣ ታሪክ እና ጀግንነት አልኖሩትም። ለዚህ ይምስለኛል በስራቸው ተገልጠው ሲቀመሱ "ባንዳ ባንዳ" የሚሉት ። በተግባራቸውም "የአማራን ህዝብ ስለገደላችሁት ክብር ይገባችኋል" በማለት ከአገኘሁ ተሻገር ጋር በመሆን የብልፅግና ከፍተኛ አመራር ባህር ዳር በመጣ ቁጥር ለአማራ ህዝብ ጠላቶች ካባ ለመሸለም ማንም የማይቀድማቸው ። ካባ ሸልሞ ጠላትን ማሞገስ በጌቶቹ ዘንድ የተሻለ ስልጣን እንደሚያስገኝ የብአዴን ታሪካዊ አመጣጥም ያስረዳናል ። ሁሌም በተሸናፊነት Hat - trik የማያልፈው ብአዴንም ምንጩ ባንዳነት መሆኑን የተረዳነው ገና ጫካ ሳንገባ ስለሆነ አሁን ይህን አሉ ብለን አልተገረምንባችውም ። ምን አልባትም ተናጋሪው አቶ ተመስገን ጥሩነህ ቢረሱትም እኛ ግን የክልሉን የምስለኔ ምክር ቤት ስብሰባ አቋርጠው "እንኳን ደስ አላችሁ አርበኛ ዘመነ ካሴን ገድለነዋል" ብለው አዳራሹን በጭብጨባ ጮቤ ያስረገጡ "ባለ ሁለት እግር የጋማ ከብት" መሆናቸውን ለቅፅበትም ፈፅሞ አንረሳውም ። ምንም እንኳን ከአዳራሹ ከወጡ በኋላ ማፈሪያ እንደሆነ ህዝቡ ቢገልፅላቸውም ። ይሄን የቆሸሸ የጋርዮሽ አስተሳሰብ በአዲሱ ትውልድ አስተሳሰብ ለመጫን የሚሞክሩ ከንቱዎች ባህርዳር እየመጡ እንደ በቀቀን  የሚጮሁት አብይ ተቆጥቶ እና ገላምጦ ስለሚልካቸው አለቃቸውን ለማስደሰት ሁሉንም የመፈፀም በእድሜ የካበተ የባንዳነት ልምድ ስላላቸው ነው ። በዚህም አንፈርድባችሁም ለምዶባችሁ ነው ¡ በተከበረው ህዝባችን ላይ አቶ ተመስገን ጥሩነህ አፋቸውን ሲከፍቱ ጭንቅላታቸው እውነትም ከ ፊደል ነፃ መሆኑን ያለ መጋረጃ ተገልጦ አይተናል ። በዚህም እኛ አልተደነቅንም። ምን አልባትም አቶ ተመስጠን ጥሩነህ ሽመልስ አብዲሳ የ ኦሮሚያ ፕሬዝዳንትነት ሳይለቅ የአማራ ህዝብን 6 ፕሬዝዳንት በተቀያየረበት ቅፅበት 4ኛው የአማራ ህዝብ ፕሬዝዳንት ነበሩ ። ለዚህ ደረጃ ያበቃውም ጓደኞቹን በሴራ ማስገደሉ እና በመካድ ማሳሰሩ ነው ። ስለዚህ "ከዝንብ ማር" አንጠብቅም ። በመጨረሻም ጓድዎት ግርማ የሺጥላ ፥  አለቃዎቹን ለማስደሰት በአንደበቱ የተናገረው ንግግር "የውኃ ሽታ" ሆኖ እንዲቀር እንዳደረገው መቼም አይዘነጉትም ። እርስዋ "ባንዳ" ሲሉ የጠሩት የአማራን ህዝብ ባንዳ ሳይሆን ፥ ነጭ ያላሸነፈው ኩሩ እና ጀግና ህዝብ ነው ። ስለዚህ የእርስዎ ፣ የዳንኤል ክብረት፣ የአረጋ ከበደ ፣የአገኘሁ ተሻገር እና ደቀ መዝሙሮቻችሁ ከአማራ ህዝብ እሴት፣ ባህል፣ ወግ ፣ታሪክ እና ጀግንነት የተፋታችሁት ገና ያኔ ድሮ "ለሔደ ለመጣው" ገዢ ቡድን ለመላላክ እና ባንዳ ለመሆን  የወሰናችሁ ጊዜ ነው ። በመሆኑም ያልኖራችሁትን አሁን ከየትም አታመጡትም። ይልቁንስ አዲሱ የአማራ ትውልድ ታሪክ ሊያደርጋችሁ ከቦ ፊሽካ እስኪነፋ ብቻ ነው ሚጠብቀው ፤ በትዕግስት ጠብቁ፤ ያለ መርሐ ግብራችን አታቻኩሉን ። በድንገት የህዝብ ማዕበል መግቢያ መውጫ እንደሚያሳጣ እረስታችሁት ከሆነም በተግባር እናስታውሳችኋለን ። ማንም ወደደም ጠላም ፤ ማንም መረረውም ጣፈጠውም የነገ ታሪክ በእኛ እጅ ይፃፋል ! አርበኛ መምህር ግሩም ምሳሌ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ምክትል የፖለቲካ መምሪያ ሃላፊ አንድ አማራ ! አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ

#ሚሊሻ_እየተበተነ_ነው‼️ በቀን 26.01.2018 ዓ.ም አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ፩ኛ ክፍለጦር ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድን ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው የተቀላቀሉ ሚሊሻዎች 1አተነህ ም
+1
#ሚሊሻ_እየተበተነ_ነው‼️   በቀን 26.01.2018 ዓ.ም አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ፩ኛ ክፍለጦር  ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድን ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው የተቀላቀሉ ሚሊሻዎች 1አተነህ ምስጋናው  2 ጸጋየ ዳምጤ 3 ጥላየ ባለው 4.ከፌ በላይነህ 5.መኳንት አየለ በቀጣይም ከውጊያ ጎን ለጎን ስቦ ማስከዳት ላይ አጠነክረን እንሰራለን።   ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዝ 1ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት 27/ዐ1/2018 ዓ.ም

ጥንታዊቷ እና የጀግኖች መብቀያ ምድር ቡሬ ዳሞት የዓለም የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የሚኮሩበትን የዓደዋ ድል በደማቸው ቀለም ከፃፉ ሥመ_ጥር  አርበኞች ከራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም(አባ ገድብ)፤ የፀረ-ጣሊያን ትግል ጀማሪው ደጃዝማች በቀለ ካሳ ( አባ ቆራጥ) እስከ አሁኑ የአማራ ትግል ጠንሳሽ ፋኖዎች  በማፍራት አዛውንት ስሟ በታሪክ ማኅደር ተከትቦ በግንባር ቀደምትነት ተቀምጧል ። ....................................................... በ2ኛው የጣሊያን ወረራ ወቅት ከማይጨው ጦርነት ሽንፈት በኋላ አዲስ አበባ በጣሊያን ሥር በወደቀች ጊዜ የመጀመሪያው ጸረ- ፋሽስት ኢጣሊያ እንቅስቃሴ የተጀመረው በጎጃም ሲሆን ትግሉን በይፋ የጀመሩት የቡሬ ዳሞቱ ደጃዝማች በቀለ ካሳ  ( አባ ቆራጥ) ናቸው። የቡሬ ዳሞት ጀግኖች በአለፉት ሁለት ዓመታት የዘመኑ ጥቁር ፋሽት ዐቢይ አሕመድ እስከ አፍንጫው አስታጥቆ የላከውን ወራሪ ሠራዊት አከራካሪው የተሰበረበት የዉንድጊ ተራራ ህያው ምስክር ነው።   ዛሬም እንደ ትናንቱ ማኅፀነ ለምለሟ ቡሬ ዳሞት የአማራ ህዝብ መመኪያ የሆኑ እልፍ አዕላፍ ጀግኖችን በማፍራት ያለስስት ልጆቿን ሰጥታለች❗️ ቡሬ ዳሞት ጀግና መውለድ ብቻ ሳይሆን ጀግና ማክበርም ልዩ መገለጫዋ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም ።ለዚህም ነው የአዲሱ ትውልድ የትግል ምልክታችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ስም ሻለቃ ተሰይሞ ከፍተኛ ተጋድሎ የሚደረግበት አካባቢ መሆኑ ለጀግና ልዬ ክብር ያለው መሆኑ ገላጭ ነው አዲሱ የአማራ ትውልድ የአያት ቅደመ አያቶቹን የጀግንነት ውርስ በፋኖነት  ተሰልፎ  የቀደምቶችን ታሪክ በመድገም ላይ ነው። የአማራን ህዝብ ከህይዎት መዝገብ ለመሰረዝ ስንቅና ትጥቅ የሚሰፍሩለት የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ተልዕኮ አስፈፃሚው ፋሽት ዐቢይ አሕመድ ወራሪ ሠራዊት በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፅመውን የዘር ማጥፋትና ማፅዳት ወንጀል የሚያንገበግባቸው በግንባር የወራሪውን ሠራዊት ለመፋለም ተሰልፈው የፋኖነት ስልጠና ለመውሰድ ተደጋጋሚ ጥያቄ ከሚያቀርቡት የአማራ  ወጣቶች መካከል ላለፉት 4 ወራቶች ልዬ የኮማንዶ ስልጠና ሲዎስዱ የነበሩ ተተኪ ፋኖዎቻችን የምርቃ ሥነ _ሥነ ሥርዓት  በመከዎን ላይ ነው። ውድ ተመራቂዎች! ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥ ሆናቸሁ አስቸጋሪውን የኮማንዶ ስልጠና በማጠናቀቅ ብቁ ሆናችሁ ለዚኽች ታሪካዊ የምርቃት  ቀን በመድረሳችሁ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ  ኃይል የምዕራብ አማራ ቀጠና የዳግማዊ ቴዎድሮስ ዕዝ የስልጠና መመሪያ ሥም እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የተሰማኝን ልባዊ ደስታ ለመግለጽ እዎዳለሁ❗️‼️           "ታዬ ብርሃኑ" የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና የዳግማዊ ቴዎድሮስ ዕዝ ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ

የአብይ አህመድ መንግሥት የሚለውን ማዕረግ ያሸከመው አካል ሰው ሳይሆን እንስሳ ነው ። ባለፈው ሳምንት አስመረኩት ያለው መጽሐፍ በ6 ኪሎ ዩኒቨርስቲ የፊሎሶፊ መምህራን በኩል የተፃፈ መሆኑ መረጃው እጃችን ላይ አለ። ለአንድ ገፅ 100 ሺህ ብር እየተከፈላቸው ከፃፉት መምህራን መካከል፡- 1.ዶክተር ዳኛቸው 2.ዶክተር ዘላለም ተፈራ 3.እያሱ ባሬንቱ እና 4.ዶክተር መሐመድ አሊ ዋነኞች ናቸው። ገበያ ላይ የሚሸጥን የሰው መጽሐፍ ገልብጠው የመደመር ትውልድ ብለው ከፃፉለት በኋላ በድጋሜ የመደመር መንግሥት ብለው ተመሳሳይ አሮጌ ሐሳብ አንዛዝተው አቅርበውታል። በአሁኑ ወቅት ሁሉም የአዲስ አበባ የብልፅግና ካድሬዎች 5 መጽሐፉ ተሸክመው በየመንደሩ እየዞሩ የሰው ግቢ ቤት እያንኳኩ1ሺህ ብር ግዙን እያሉ ይገኛሉ። አብዛኛው ሕዝብ በከፍተኛ ሁኔታ ኑሮው አማሮናል ቁጭ ብለን የምናነብት ጊዜ የለንም...ቢላቸው የሚሠሙ አልሆኑም። ትልቁ የአብይ አህመድ ቆሻሻ ስብእና መፅሑፉን በግድ እንዲሸጥ ማስገደዱ ብር ፈልጎም ብቻ ሳይሆን ራሱ ስላልፃፈው አድናቆት፥ጭብጨባ እና ታሪክ ፍለጋ መሆኑ ሕዝብ ተረድቶት እየሳቀበት ይገኛል። ስለዚህ መዘናጋት አያስፈልግም እና ቤተሰቦቻችሁ እንዳይገዙት አድርጉ እላለሁ። ድል ለአፋብሐ ብቻ የኔ ነፃነት መከበሪያ ዋልታ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎     

ቢቡኝ መዝገበ ዋለልኝ ብርጌድ በስሩ ላሉ የሻለቃ አመራሮች ለሁሉም የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕ/አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክ/ጦር ቢቡኝ መዝገበ ዋለልኝ ብርጌድ   25/01/2018ዓ.ም በተከታታይ ለ5ቀናት            አማራነትን በሃገረ-መንግስት ምስረታውና በሃገር ወዳድነቱ ነገዳውያን እንደ ችግር ቆጥረውበት ፤  ሃገርን ህዝብን አዋዶና አስማምቶ ለብዙ ሺህ ዘመናት ሃገር ማቆየቱና ኢትዮጵያ ሃገራችን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የጥቁርነት #የድል አሻራ በር በመክፈቷ ብሎም ድሉን በኩራት የእኛ ብሎ ከመቀበል ድሉን እምዬ ምኒሊክ ናቸው የመሩት ነገዳቸውም አማራ ነው በማለት በሴረኞችና በራስ ጠሎች የሴራ ፖለቲካ ተሰርቶበትና ሀገር በቀል የሴራው ሌጋሲ አስቀጣዮች ትውልዱን የውጭ እድል በሚል በትምህርት ሰበብ  "ሀገራዊ ውሌታ ሌላ ምሁር ሌላ" ሁኖበት አማራነት ወንጀል ሁኖ ለብዙ ዘመናዊ አንድ አታጋይ የጋርዮሽ ድርጅት ሳይኖረው የአማራ የለመለሙ አዕምሮዎች በየጊዜው በስርዓቱ ሲጠፉ ኖረዋል። በዚህም የአማራ እናት ማህፀኗ ለምለም ነውና በየጊዜው የሚጠይቁ ሰላማዊ ታጋዮች ተፈጥረዋል።  ወደ አንድ ማዕከላዊ የትግል ተቋም /ድርጅት/ ባለመምጣታቸው በገዢዎች ስርዓታዊ ተልዕኮ አጥተናቸዋል። እናም እነዚህ በነገድ የተደራጁና ነገድነትን የትግል ሪዕዮት ያደረጉና የነገዳቸው መነሻ ፖለቲካዊ ግንዛቤ ከሴረኝነት የመነጨና ሃገርን ያላገናዘበ አካታችነትን የተፀየፈ በተለይ ዘውዳዊነትን ነጥሎ ለአማራ በመስጠት  በተንሸዋረረም መረዳትም  ፤    አማራ ጠል በመሆን  የእነዚህ አማራ ጠል ኃይሎች እድገትና በሃሪቱ መንገስ (መንግስት መሆን)  ለአማራ ህዝብ ለብዙና ዘርፈ ብዙሃነት ችግር ሁኖበት ባይተዋር ሁኖ ፤ እንዳይሰራ ተረጋግቶና የእኔ የሚለው የሃብትና የንብረት እንዳይኖረው ብሎም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነኝ ሲል የማሸማቀቅ ስልትና ችግር (እስር) እንዲደርስበት ሲደረግ ቆይቷል። እናም አማራ በደረሰበት መዋቅራዊና ስርዓታዊ የህልውና ስጋት በሰላማዊ ሲጠይቅ ከቆዬ በኋላ ራሱን ለማኖር   (ለማስከበር)  የማንንም ፍቃድ ሳይጠይቅ በህዝቡና በልጆቹ እንቢተኝነት #በፋኖነት የትግል ዓርማ ተደራጅቶ ደርጅቶ ጎምርቶ አንድ አታጋይ የራሱ ድርጅት /አፋብኃ መስርቷል።        በዚህ ትግል አማራ የሆነ ፤ ለአማራም የሆነ የማይናገረው እንስሳቱ እንኳ ሳይቀር ፤  ፆሙን የሚውለው ውሻው ሳይቀር እንኳ ፤  አማራ ምድር ላይ የበቀለውን ዛፍ እፅዋቱን ጭምር ጠላት(የብልጽግና ስርዓት) አይፈልገውም ።  ጠላትን ከ47ጊዜ በላይ ፊትለፊት የተፋለመና ድል ሁሌም የማይለየው  በአውደ ውጊያ በምርኮና በስቦ ማስከዳት ከጠላት  የጦር መሳሪያውን የሟላ ታሪካዊ ምድር (ቢቡኝ)  አማራነትን በዚህ ስልተ_ስልጠና አማራዊ ፖለቲካዊ ግንዛቤ  ተዋረዳዊ #ከድርጅቱ መሪዎች የስልጠና ስምሪት በመውሰድ ተመሳሳይ አማራዊ አስተውሎትና ብሔራዊ ቁጭት በመፍጠርና ተልዕኮ በብርጌዱ ስር ለሚገኙ ሻለቃዎች በተመረጡ የስልጠና አጀንዳዎች ማሰልጠን ተችሏል። የዚህ-ህዝብ ባላደራዎች/ሰልጣኞች ታሪክን በምልዐት በመቀበል በቀጣይ ተልዕኮውን በመቀበልና በመረዳት የማሰልጠን ስራ መስራት እንደሚችሉም በመዝጊያው ገልፀዋል። አዲሱ ትውልድ የአማራነትን ከፍታ ለማምጣት ከገባበት የተንሸዋረረ የሌሎች አረዳድ፤ አረዳዱ እንዲቀየርና የትናንቱን የአማራነት አካታችነትና ሃገራዊ ስነልቦናዊ በፖለቲካ ዝማኔና በመንግስትነት የአስተዳደር ስራና አፈፃፀም የሚታይ ስራ እየሰራ ይገኛል። አዲስ ትውልድ ! አደስ አስተሳሰብ!   አዲስ ተስፋ! መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎     

በሀገራችን የነበረውን የባሪያ ንግድ የሚከለክለውን አዋጅ የተቃወሙት እራሳቸው የባሪያ ንግድ ሰለባዎች ነበሩ። ተመስገን ጥሩነህ ከዓመታት በፊት የአንድ የመንግስት ተቋም ጥበቃ ነበር። መከላከያን ተቀላቅሎ በህወሃት ከተመለመለ በኋላ በአማራ ክልል ገጠር መንገድ፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን መስተዳድር፣ በኋላም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆኖ ሰርቷል። ኢንሳ፣ ብሔራዊ መረጃ ከመስራቱ በፊት ሰውዬው አማራ አማራ ክልል ላይ የሚታወቅባቸው ሌጋሲወቹ አሳምነው ፅጌን በህይወት እንዳይተርፍ ባደረገው ጥረት፣ በኋላም አስከሬኑ እንዲጎተት በማድረግ፣ እንደገናም እነ ሻለቃ መሣፍንት ተስፉ ላይ ታንክን ያካተተ ወታደራዊ ስምሪት በመስጠት ነው። ከሶስት ዓመታት በፊት "ተገዳዳሪ ኃይል ተፈጥሮብናል" በሚል የሞት አዋጅ ያወጀብንም አይዘነጋም። በህወሃት መሰላል ስልጣን ላይ የተንጠላጠለው ይህ ግለሰብ ዛሬ ህወሃት ሊመጣብኝ ነው ብሎ አቅሉን ስቷል። የህወሃት መሰላል ሲወድቅ ሰባራው የአብይ መሰላል ላይ ተንጠልጥሎ በደመ ነፍስ እየነጎደ ነው። ከሰሞኑ ባንዳ ብሎ አማራን በዘለፈበት ንግግሩ ውስጥ የአማራ ህዝብ ላይ ይፋዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል አውጇል። በነገራችን ላይ ባንዳነት እና ተላላኪነት ማንን ይመስላል ቢባል ራሱን ተመስገንን ነው ምላሹ። አብይን የወለደችልን ጅማ ትባረክ የሚለው ተመስገን ጥሩነህ የራስ ጠልነት እና የማህበራዊ መበስበስ መገለጫ ምሳሌ ነው። ከላይ እንደጠቀስነው ልክ የቀደምት የባሪያ ፍንገላ ሰለባወች ብቻቸውን ማሰብ፣ ብቻቸውን መኖር፣ ብቻቸውን መወሰን እና ኃላፊነት መሸከም ስላልተለማመዱ ባርነትን ደግፈው አርነትን ተቃውመዋል እንደሚባለው ሁሉ ተመስገን እና መሰሎቹም የአማራ ህዝብ የሚያደርገውን የነፃነት ተጋድሎ ሊደግፋት አይችሉም። ከኖሩበት የአገልጋይነት እና የተላላኪነት መስመር ለመውጣት መቻሉን ሲያስቡት ይፈራሉ። እናም ብዙም አያስገርምም በቀደም ግዜ የህወሃት ሰወች ዛሬ ደግሞ የኦህዴድ ትራፊወች እያሰቡ የሚያኖሩት ግለሰብ የአማራ ህዝብ ከሌሎች ጋር የሚያደርገው ትብብርም ሆነ ተጋድሎ ሊገባው ስለማይችል በባርነቱ ፀንቶ ይቀጥላል። አርበኛ አስረስ ማረ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎     

የሰሜን ወሎዋ የዋድላ ወረዳ መቀመጫ የሆነችው ኮን ከተማ በጀግናው ፋኖ ቁጥጥር ስር ውላለች! ይች ከተማ ስትራቴጂክ ቦታ ተብላ ከምትታወቀው ጋሸና ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኝ መሆኗን ልብ በሉ። ፋኖ
የሰሜን ወሎዋ የዋድላ ወረዳ መቀመጫ የሆነችው ኮን ከተማ በጀግናው ፋኖ ቁጥጥር ስር ውላለች! ይች ከተማ ስትራቴጂክ ቦታ ተብላ ከምትታወቀው ጋሸና ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኝ መሆኗን ልብ በሉ። ፋኖ ወደፊት

የጥንቃቄየ ‼️መልእክት ለሸዋ ደራ አማራዎች ብልጽግና በሸዋ ደራ የመለመላቸው ከ350  ስከ400 የሚጠጉ  የኦሮሞ ሚሊሻዎች  እያስጨፈረ ወዴ ፍርድቤቱ  ግቤ አስገብቷቸዋል እኔህ በዘረኝነት ተጠምቀው የተመለመሉት  ቡድኖች አማራን ለማፅዳት ስለሆነ ሁሉም አማራ በንቃት እድጠብቃ እና እራሱን ከጥቃት እንድከላከል መልእክታችንን እናስተላልፋለን ። ለዚህ ፀረ አማራነት በነቂስ  ከወጡ የብልጽግና ቅጥረኞች ጎን የቆማችሁ የአማራ ባንዳዎች ግን ከወድሁ ቆም ብላችሁ ብታስቡበት ምክራችነው  በስተመጨረሻም ግልገል ፋኖ ተብለህ የመታነቂያ ገበዱ ባንገት መግባቱ የማይቀር ሃቅነው ድል ለአማራ ፋኖ ድል ለ አማራ ሕዝብ

➾የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ኃላፊ አርበኛ ስለሺ ከበደ ለተመራቂ ኮማንዶዎች ያስተላለፈው መልዕክት ‼ የአፋብኃ ምዕራብ  አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ የ5ኛ ክፍለ ጦር የቡሬ ዳሞት ብርጌድ  በደማቅ ሁኔታ ኮማንዶዎችን አስመርቋል።በዚህ የኮማንዶ ምርቃት ላይ ያስተላለፍሁት መልዕክት ነው። የተከበራችሁ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች፣ የተከበሩ ሻለቃ የኔዓለም ዘለቀ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ም/ወ/አዛዥ ፣ የተከበሩ  ሀምሳ  አለቃ ታየ ብርሃኑ  የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ  ፣ የተከበራችሁ የድርጅታችን ከፍተኛ አመራሮች ፣ የተከበራችሁ የአፋብኃ ቢዛም ዕዝ አመራሮች ፣ የተከበራችሁ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ  የ5ኛ ክፍለ ጦር   ከፍተኛ አመራሮች፣ የተከበራችሁ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ  የ3ኛ ክፍለ ጦር የጊዮንና ብርጌድ   ከፍተኛ አመራሮች፣ የ5 ክፍለ ጦር የቡሬ ዳሞት  ብርጌድ አመራር እና አባላት፣ የተከበራችሁ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ኮማንድ እጩ የሰራዊት አባላት፣ የተከበራችሁ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ክቡራት እና ክቡራን በቅድሚያ አድካሚ የሆነውን ወታደራዊ ስልጠና በብቃት በመውሰድ እና የታለፈባቸውን ውጣ ውረዶች በማለፍ ለዚህ የምረቃ እለት የበቃችሁ እጩ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ! ዛሬ ይሄንን ደማቅ የፋኖ ሰራዊት ምረቃ ስናካሂድ ህዝባችን ያለፈበትን መከራ፥ መፈናቀል ፣ ስደት፣ ግድያ ፣ ዘረፋና መሰል ስርዓትና መዋቅር ወለድ ችግሮች እና ያንን ለመከላከል የተደረገውን ተጋድሎ ማስታወስ ያስፈልጋል። አብይ አህመድ እና ግብረ አበሮቹ በሰሜኑ ጦርነት ከፍተኛ ዋጋ የከፈለው የአማራ ህዝብ አፅሙ በትክክል ሳያርፍ፣ ከጉዳቱ ሳያገግም፣ የተደፈሩ እህቶች እና እናቶች ስብራት ሳይጠገን፣ በቅጡ እንኳን መስዋዕትነቱ ሳይነገር ነበር ወደ ሌላ ዙር ጦርነት አስገባን። የስርዓቱ ዋነኛ ምክንያት አረመኔው የብልፅግና አገዛዝ እና አማካሪወቹ ያቀዱት አማራን ትጥቅ የማስፈታት ፕሮጀክት እንደሆነ በአደባባይ ቢታወቅም ስውር ዓላማው ደግሞ አማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈፀም፣ የዲሞግራፊ ለውጥ በማምጣት፣ መብቱንም ማንነቱንም የማይጠይቅ በስነ ልቦናም በቁጥርም የኮሰመነ አማራን በማምጣት የኢትዮዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በመለወጥ በአዲስ ቀመር ሀገሩን አፍርሶ መስራት ነበር። የአማራ ልዩ ሀይልን በይፋ በማፍረስ ምልክቱ ሲታይ በታሪክ አጋጣሚ እንደገና የተወለደው የፋኖ መዋቅር የፀረ-አረመኔ አገዛዝን ትግል በጠመንጃ በመምራት በወሰደው አቋም የሀገሪቱም የቀጠናውም ፖለቲካ ከፖለቲካ ተንታኞች ግምት ውጭ ሆኖ፣ የአብይ አህመድን አማራን የማጥፋት ቅዠትም ህልም ሆኖ፣ አብይም ከገባበት የጦርነት አረንቋ መውጫ አጥቶ፣ አማራውም ትላንት በምላሱ ያጭበረበረውን አሸባሪ አገዛዝ ከማስወገድ ውጭ አማራጭ እንደሌለው አውቆ በመተናነቅ ላይ ይገኛል። በጥቂት ቆራጦች የተጀመረው ተጋድሎ ዛሬ ብዙወችን ከጎኑ ያሰለፈ ቢሆንም ዓላማው  ስርዓታዊና መዋቅራዊ ለውጥን ለማምጣት ያለመ እንደመሆኑ መጠን ስርዓት እና መዋቅር ያለው ተዋጊ ኃይል ማሰልጠን ፣ ማስታጠቅ፣ ማደራጀት ፣ ማሰማራት እና መቆጣጠር የሁልጊዜም ተግባሮቻችን ናቸው። ይህ የዛሬው የምረቃ ፕሮግራም የዚሁ ተልዕኮ አካል መሆኑ ይታወቃል። ይህ ትግል ስርዓት የመንቀል እና የመትከል ነው ስንል ከሌሎች ኃይሎች ጋርም የምንተባበርበት እንደመሆኑ የምንገነባው ኃይል የምናሰለጥነው ሰራዊት ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ኢትዮጵያውያንም ተስፋ መሆን ይገባዋል። አብይ አህመድ እንደሚያሰማራው 120 ጥይት ከነ ክላሽ እና ቦንቡ ታጥቆ መቀነት ቆራጭ የሆነ ማፈሪያ ሰራዊት ሳይሆን የእናቶችን እምባ የሚያብስ፣ ለአባቶች መከታ፣ ለህፃናቱ ከለላ ለሁሉም ጋሻ ፣ ለሀገሩ አለኝታ የሆነ ሰራዊት መገንባት ያስፈልጋል። ይህ የሚመጣው በስራ ነው። ላለፉት ሶስት አመታት ይህንን ስናደርግ ቆይተናል፣ እያደረግንም ነው። ከዚህ አንፃር የዛሬ ተመራቂወች ለፖለቲካ ገበያ የሚቀርብ ጨዋነት እና ዲስፕሊን የአማራ ህዝብ ከእናንተ የሚጠብቅ መሆኑን አውቃችሁ ችግሮችን  ተቋቁማችሁ በመፅናት እንድታኮሩን አደራ ማለት እፈልጋለሁ። በየውሏችን የተለያዩ ጀብዱወች እና ተቆጥሮ የማያልቅ ገድል የበዛበት ልዩ ታሪክ እየተፃፈ ያለው ጥቂት የማይባል ጊዜ በወሰደ የመደራጀት፣ የመመራራት፣ የመደማመጥ፣ የመደጋገፍ በዋናነት በቅንነት ላይ የተመሰረተ መስተጋብር ስላለ ነው። ይህ የበለጠ ሰፍቶ እና ተደራጅቶ መቀጠል ይገባዋል። አገዛዙ የታጠቀውን ጠመንጃ በገፍ ነጥቀነዋል። ዛሬ የምናሰለጥናቸው እና የምናስመርቃቸው የሰራዊት አባላት የሚታጠቁት ከጠላት የተማረከ መሳሪያ ነው። የዛሬ ተመራቂወችም ማርካችሁ የማስታጠቅ ልዩ ተልዕኮ ይጠብቃችኋል። መሬት ያለውን ሰራዊት በኃይል እየተማረከ፣አራት ኪሎ ያለው ትዛዝ ሰጭ ደግሞ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ መንገድ ጠፍቶበት እየተተራመስ ያለበት ወሳኝ ጊዜ ላይ  እንደመገኘታችን መጭው ጊዜ በተለይም መጭው ወራት እስከአሁን ከነበረውም በተለየ  ትጋት እና ፅናት የምንሰራባቸው በመሆናቸው የክፍለ ጦር እና የብርጌድ አመራር እና አባላት ትልቁን አላማችንን ታሳቢ ያደረገ የሞራል ዝግጅት እንዲኖራችሁ ማስታወስ እፈልጋለሁ። አፋብኃ የፀረ-አገዛዝ ትግሉን በማስተባበር በኩል የተሻለ ሚና እንዲወጣ መሪወቻችን ያልሳለሰ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከእኛ የሚጠበቀውም አመራሮች የሚወስኑትን ውሳኔ መቀበል እና መፈፀም፣ የሚሰጡ ወታደራዊ ግዳጆችን ያለመሸራረፍ መከወን ነው። ውድ ተመራቂወች በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ። አመሰግናለሁ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎     

በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ሙጃ ግንባር የተማረኩት የጊዳን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አበራ አንዳርጌ እና የሚሊሻ አመራር መልክት!