ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more3 678
Subscribers
+2624 hours
+3797 days
+1 10930 days
Posts Archive
የአርሶ አደሩን መሬት ለእርሻና ለመኖሪያ ቤት ለመቀራመት አሰፍስፎ የመጣው ሚሊሻ በከበባ ተመታ!!
===============
በዛሬው ዕለት የካቲት 12/2018 ዓ. ም ከምዕ/ጎጃሟ ቡሬ ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኛዋ ውንድጊ ቀበሌ ንጉስታ ጎጥ የሚገኘውን የአርሶ አደር መሬት ለአብይ ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻ ለቤት መስሪያና ለእርሻ ቦታ ለመከፋፈል የመጣውን አረመኔው ፍሽስቱ እና ጡት ቆራጩ የአገዛዙ ሰራዊትን 77ኛ ክ/ጦር አካል የሆነችው 5ተኛ ሻለቃ በመክበብ በአብሪ ጥይት ሲገርፉት አርፍደዋል፡፡
የቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር 5ተኛ ሻለቃ በአደረገችው መብረቃዊ ጥቃት ጠላት ጥምር ሀይል እያለ የሚጠራው የሚሊሻና የፖሊስ ስብስብ ሙትና ቁስለኛውን ሳያነሳ እገሬ አውጭኝ በማለት ወደ ቡሬ ከተማ ፈርጥጧል።
👉መረጃው የ77ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ነው!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 12/2018ዓ.ም
ሰበር ዜና!!
👉የ109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር አነፍናፊ አዳኝ ቡድን ፍኖተ ሰላም ከተማ የመሸጉ ሁለት ቅጥረኛ ባንዳ ሚሊሾችን በቁጥጥር ውስጥ አዋለ:-
=================
በትናንትናው ዕለት በቀን 11/06/2018 አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በክንደ ነበልባሉ 109ኛ ኮር የሚመራው የ77ኛ ክ/ጦር አነፍናፊው አዳኝ ቡድን የምዕራብ ጎጃም ዞን ርዕሰ መዲና ከሆነችው ፍኖተሰላም ከተማ ከምሽቱ 2:30 ሁለት ባንዳ ሚሊሻዎችን አንገታቸውን አጠንጥሎ ከእነ ነፍሳቸው በቁጥጥር ውስጥ በማዋል ከከተማ ይዟቸው ወጥቷል።
➡️ቅጥረኛ ባንዳ ሚሊሾች ለማምለጥ ተኩስ ቢከፍቱም #ከአቦ ሸማኔ በእጥፍ የሚፈጥነው ዘሎ ጠላት ተክሻ ላይ የሚከመረው ይህ አነፍናፊ አዳኝ ቡድን ከእነትጥቃቸው በቁጥጥር ውስጥ አውሏቸዋል።
➡️በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ውስጥ የዋሉት እነዚህ ቅጥረኛ ባንዳ #ሚሊሾች:-
👉#አንደኛው ፈጠነ አለሙ የሚባል ሲሆን የዞኑ ሰላምና ደህንነት #ተገኔ ከልካይ የእህት ባል
👉#ሁለተኛው ያለው የሻነህ የሚባሉ ሲሆኑ እስከ ተያዙበት ሰአት ድረስ የብልጽግና ካድሬ በሚሰጣቸው ግዳጅ ወጣቶችን እያስገደዱ ወደ መከላከያ ማሰልጠኛ ካምፕ ሲልኩ የነበረና ከአንድ ጎጥ ብቻ በህገወጥ መንገድ ከ80,000 ብር በላይ መሰብሰባቸውን በሰጡት የቃል ማስረጃ አረጋግጠዋል።
⛔️ይህ አነፍናፊ አዳኝ ቡድን የባንዳ መድሀኒት ሲሆን ከተማ መሽገው ህዝባቸውን የሚገሉና የሚያስገድሉ ባንዳዎችን ስርዓት ያስይዛል፣ በቁጥጥር ውስጥ ያውላል፣ እርምጃም ይወስዳል።
👉ምህረት ለሚፈልጉ የምህረት በራችን ክፍት ነው!!!
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 12/2018 ዓ.ም
ቆፍጣናው መሪ ኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ በቡልጋ ሰማይ ስር ከአድስ ምልምል የፋኖ ሰራዊታችን ጋር ያደረገው ቆይታ!!
አማራራው ተራራው ወደ ፊት #መቅደድ ብቻ ነው👂🙏
+1
የምህረት አዋጁን የተቀበለው ሶስት የ አድማ ብተና አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቀሉ::
ደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ የሚገኘው የብልፅግና የግለሰብ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አባል የነበሩ ሶስት የአድማ ብተና አባላት በተዛባ መንገድ ከተረኛው ስርዓት ጋር ተሰልፈው የነበሩ ምህረት አዋጁንና ጥሪችንን ተቀብለው የካቲት 12/2018 ዓ.ም አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። የየጎፍ ክ/ጦር አመራሮችም ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የየጎፍ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 12/2018ዓ.ም
#ኦህዴድን_ማጋለጥ‼️ በመንግስት መዋቅር የታገዘ የዘር ማጽዳት ዘመቻ እና የአማራ ህዝብ ራስን የማዳን የህልውና ትግል‼️
ባለፉት ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸሙት ግፎች የታሪክ ጠባሳ ሆነው የሚቀጥሉ ናቸው። ይህ ሂደት ከንግግር ተነስተው ወደ ስልታዊ ጭፍጨፋ እና መፈናቀል የተሸጋገሩ ድርጊቶች ድምር ውጤት ነው።
የጥላቻ ንግግር እና የፖለቲካ ሴራ
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ "ነፍጠኛን ሰበርን" በሚል የሰነዘሩት ንግግር እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት አማራውን እንደ "መጤ" እና "ወራሪ" አድርገው መሳላቸው፣ ለታችኛው ታጣቂ ኃይል እና ለጽንፈኛ ቡድኖች የጭፍጨፋ የሞራል ድጋፍ ሆኗል። ይህም ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ብቻ እንዲገደሉ መንገድ ጠርጓል።
የመረጃ እና የአሃዝ ማጠቃለያ
የንጹሃን እልቂት፦ በወለጋ፣ በቤኒሻንጉል እና በሌሎች አካባቢዎች ከ 5,000 በላይ ንጹሃን በግፍ ተጨፍጭፈዋል።
መፈናቀል፦ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ አማራዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ለከፋ ስቃይ ተዳርገዋል።
የቤት መፍረስ፦ በሸገር ከተማ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ከ100,000 በላይ ቤቶች በብሔር ማንነት ላይ ተመስርቶ እንዲፈርሱ ተደርጓል።
የጸጥታ መዋቅሩ ተባባሪነት፦ በወለጋ እና በቤኒሻንጉል በተፈጸሙ የጅምላ ጭፍጨፋዎች ወቅት፣ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጥቃቱ ከመፈጸሙ ጥቂት ሰዓታት በፊት አካባቢውን ለቀው መውጣታቸው እና ጥቃቱ ለሰዓታት ሲካሄድ በቅርብ ርቀት ሆነው ጣልቃ አለመግባታቸው በሪፖርቶቹ ላይ በዝርዝር ተመዝግቧል።
የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘገባ፦ CNN፣ BBC እና Al Jazeera የመሳሰሉ ተቋማት በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት "ዘግናኝ እና ስልታዊ" (Horrific and Systematic) በማለት የዘገቡት ሲሆን፣ ድርጊቱ በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አጋልጠዋል።
ህልውና ትግሉ አስፈላጊነት እና የጦርነቱ መንስኤ
አሁን በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለዉ ጦርነት በአጋጣሚ የተከሰተ ሳይሆን፣ ለዓመታት ለዘለቀው ስልታዊ ጭቆና እና ጥቃት የወለደዉ/ የተሰጠ የመጨረሻ ምላሽ ነው።
የመንግስት መዋቅር እንደ ጥቃት መሣሪያ፦ በአዲስ አበባ ዙሪያ "የሸገር ከተማ" በሚል ስያሜ የተካሄደው የቤት ማፍረስ ዘመቻ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆችን ለጎዳና እና ለረሃብ ዳርጓል። ይህ ተግባር በመንግስት መዋቅር የታገዘ የከተማ ውስጥ "የዘር ማጽዳት" (Urban Ethnic Cleansing) ተደርጎ ይወሰዳል።
ከጄኖሳይድ ራስን መከላከል፦ ሕዝቡ ከመንግስት ጥበቃ ከማጣት አልፎ፣ የመንግስት የጦር መሣሪያዎች (ድሮን እና ከባድ መሣሪያዎችን ጨምሮ) በእሱ ላይ ሲዘመቱ፣ ራሱን ከመጥፋት (Genocide) ለመከላከል እና መሰረታዊ ሰብአዊ መብቱን ለማስከበር ወደ ህልውና ተጋድሎ ገብቷል። ይህ ትግል የፖለቲካ ስልጣን ፍላጎት ሳይሆን፣ የመኖር እና በሰላም የመንቀሳቀስ መብትን የማረጋገጥ ጉዳይ ነው።
ማሳሰቢያ፦ የታሪካዊ እና ህጋዊ ተጠያቂነት ግዴታ
ለእነዚህ ሁሉ ዘግናኝ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ለንጹሃን ደም መፍሰስ እና ለሚሊዮኖች መፈናቀል የሚከተሉት አካላት ቀጥተኛ ተጠያቂነት አለባቸው፦
የብልጽግና ፓርቲ (ገዥው ፓርቲ)፦ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ባለመቻሉ እና በስሙ የሚመራው መዋቅር ለጥቃቶች መንገድ በመክፈቱ።
የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፦ የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት፣ በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ አማራዎችን ለታጣቂዎች አሳልፎ በመስጠት እና ስልታዊ መፈናቀልን በመምራታቸው።
የጸጥታ መዋቅር አዛዦች፦ ጥቃቶችን ባለማስቆማቸው እና በንጹሃን ላይ የሚፈጸሙ የጦር ወንጀሎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመደገፋቸው ተጠያቂ ይሆናል!!
12/ዐ6/2018 ዓ.ም
በደብረ ማርቆስ ከተማ የካድሬዎች የነፃ መሬት ወረራ !!
የካቲት 12/2018 ዓ.ም
========================================
ደብረ ማርቆስ ከተማ ጡረተኞችና የዘራፊዎች ህዝባቸውን በማሰቃየትና ለጠላት አሳልፈው በመስጠት የተካኑ እድሜ ጠገብ ካድሬውች ከየ ወረዳው ተሰባስበው የሚዶልቱባት፣ ግፍ ፈሶ የሚፈስባት መምህራን በገፍ ታስረው የተሰቃዩባት ሴቶች በቡድን የተደፈሩባትና ለመገመት የሚያዳግት የወጣቶች ግድያ የተበራከተባት መሆኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪ የሚያውቀው ሀቅ ነው።
በከተማዋ የተሰገሰጉ የአረመኔው ሰራዊት ካድሬዎች ጦርነቱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከነጋዴው ማህበረሰብ ከፍተኛ ዝርፊያ ፈፅመዋል።እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የደብረ ማርቆስ ሆስፒታል አልትራሳውንድ ማሽን ከተቀመጠበት ክፍል ተሰርቋል፣ የከተማዋ ሰፋፊ ነፃ መሬቶች በካድሬዎች ተወረው ህፃናት የሚቦርቁበት መስክ ሳይቀር ተሸንሽኖ ካድሪ ተቀራምቶታል፣በማህበራት እና የሊዝ ሽያጭ ሰበብ አሉ የተባሉ ነፃ መሬቶች ካድሬዎችና የጦር አበጋዞች በልጅ ልጅ ሳይቀር ዘመድ አዝማድ ተጠራርቶ በከተማዋ ቤት እየሰሩ መክረማቸውን የከተማው ማህበረሰብ በገፍ መረጃ አድርሶናል። እኒህን እና መሰል ነጭ ወንጀሎችን ተከታትለን የደረስንበት ሲሆን ከሙሉ ማስረጃዎች ጋር የካድሬዎች የመሬት ወረራ ከታች ቀርቧል።
ዘራፊዎች የእድር ድንኳን ወጥረው ስማችንን በሚያጠለሹበት በዚህ ጊዜ በከተማዋ ሰርገን በመግባት ካድሪው እየፈፀመ ያለውን አይን ያወጣ የመሬት ችርቻሮ ማሳያ የሚሆን ስርቆት እንደሚከተለው አቅርበናል ።
ወ/ሮ ታሪክ ሞትባይኖር የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የአብማ ክ/ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ስትሆን ዕድሜዋ 45 ያለፈ የሌቦች ካፒቴን ናት። ዕድሜዋም ሴትነቷም ሳይገድባት ለአረመኔው ሰራዊት እህቶቻችንን እያደነች ስታቀርብ የነበረችው ወ/ሮ ታሪክ ሞት ባይኖር የተሰጣትን የብልፅግናን ስልጣን በመጠቀም 8,879,200(ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሽህ ሁለት መቶ) ብር የሚገመት 500 ካሬ ሜትር በማጭበርበር በሁለት ህፃናት ልጆቿ ስም ቤት በመስራት የደብረ ማርቆስ ከተማ መሬትን መዝረፏን አረጋግጠናል።
ወ/ሮ ታሪክ ሞት ባይኖር ከወ/ሮ አቢዮት እጅጉ ጋር በመስማማት በደብረ ማርቆስ ከተማ አብማ ክ/ከተማ ቀበሌ 13 በሰሜን ሻምበል ምኑየለት፣ በደቡብ አዲሱ መለሰ፣ በምስራቅ ባዶ ቦታ፣ በምዕራብ መንገድ የሚያዋስነውን 500 ካሬ ሜትር የሆነውን የህዝብ መሬት ለመዝረፍ በመስማማት ወ/ሮ አቢዮት እጅጉ ከዚህ በፊት ከአባቷ ከአቶ እጅጉ ይግዛው በውርስ ከወንድሞቿ ጋር ያገኘችውን 500 ካሬ ሜትር መነሻ በማድረግ ወ/ሮ ታሪክ ሞትባይኖር ያላትን ስልጣን በመጠቀም ወ/ሮ አቢዮት እጅጉ በድጋሚ 500 ካሬ ሜትር ከአባቴ ከአቶ እጅጉ ይግዛው የውርስ መሬት ይገባኛል የሚል ጥያቄ እንድትታቀርብ በማድረግና ከዚህ በፊት ከወንድሞቿ ጋር ያገኘችውን የውርስ መሬት ማረጋገጫ ደረሰኞችን ለሌላ የ500 ካሬ ሜትር መቀበያ በማቅረብ በአንድ ደረሰኝ 1000 ካሬ ሜትር እንዲሸነሸን አድርጋለች።
ወ/ሮ ታሪክ ሞትባይኖር ባላት ስልጣን መሰረት የሰነድ መርማሪና አጽዳቂ በመሆን የወ/ሮ አቢዮት እጅጉ ጥያቄ በመቀበልና የተጭበረበረ ሰነድ በማጽደቅ 500 ካሬ ሜትር በ አቢዮት እጅጉ ስም እንዲተላለፍ ሁኗል። ይህንን በሚገባ ያሳካችው ወ/ሮ ታሪክ ሞትባይኖር በሁለት ህፃን ልጆቿ ማለትም በህፃን ኤልሳቤጥ ይትባረክ እና በህፃን ራክቤል ይትባረክ ስም በሞግዚትነት ከወ/ሮ አቢዮት እጅጉ ግዥን ፈፅሚያለው በማለት ከዚህ ቀደም በመመሳጠር ያገኙትን መሬት ለመከፋፈል በሚያመች መልኩ በህፃናቱ ስም በህገወጥ መንገድ 250 ካሬ ሜትር በመካፈል መሬቱ ላይ ቤት መስራቷን አረጋግጠናል።
ከታች የተቀመጠው የሰነድ ማስረጃ 8.8 ሚሊዮን ብር የሚገመተውን መሬት ከህዝብ በመዝረፍ የብልፅግና ካድሪን የዝርፊያ ሰንሰለት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን ትግሉን በማጠልሸት ላንቃቸው እስኪሰነጠቅ የሚጮኹ ሌባዎች ጉድ በዚህ መልኩ እየተከታተልን መሆኑን ህዝባችን እንዲያውቅ እንፈልጋለን ። ህዝብ በሚጨፈጨፍበት ወረራ መሀል የሚበለጽጉ ካድሬዎችን ከማጋለጥ ባለፈ ተከታትለን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን ።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
#በየቀኑ_የጠላት_ሀይል_እተመመ_ነው
በ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በጎዛምን ወረዳ ሊባኖስ ቀበሌ ውስጥ አንድን የአካባቢው ነዋሪ የሆነች ልጃገረድ አስገድዶ ለመድፈር ሙከራ ሲያደርግ የነበረን አንድ የአረመኔው ብልጽግና ልክስክስ ሚሊሻ አንድ የአካባቢው ነዋሪ የሆነ ጀግና ግንባሩን በዘነዘና ብሎ በመጣል ትጥቁን ይዞ ወጥቷል።
በተያያዘ ዜናም በዚሁ ወረዳ ደስ አሳም አቦ ቀበሌ አካባቢ ነዋሪ የሆነ አንድ ነዋሪ ለቅለቂታ የሚገኝን ቢሆነኝ መርሻ የተባለን ቅጥረኛ የብልጽግና ሚሊሻ ግምባሩን በማለት ትጥቁን ተቀብሎት ሂዷል።
👉ሁለት የአረመኔው የብልጽግና ሠራዊት አባላት ከደብረ ኤልያስ ወረዳ ከተማ በመነሳት የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
የንጹሐንን ደም ሰይጣናዊ ተግባራትን በመፈጸም ለተገነባው የብልጽግና ዙፋን ማጽኛነት የሚጠቀመው የጸረ አማራውን የብልጽግና አገዛዝ በመቃወም ወደ ማሕበረሰባቸው የሚቀላቀሉት የአገዛዙ የሠራዊት አባላት ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል።
በዛሬው ዕለትም ብሩክ ጫሜባ ለሬቦና ፲ አለቃ ኤርሚያስ ሻታ የተባሉ ሁለት የመቶ መሪዎች ከደብረ ኤልያስ ከተማ በመክዳት የ14ኛ ክፍለ ጦርን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
©የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ዘመን ባሳዝነው
12/ዐ6/2018 ዓ.ም
" እነማን ምን ሲያደርጉ ተይዘው እንደተፈቱ እናውቃለን እዚህ ሀገር ! " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)
ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን ምን ጠየቁ ?
" በርካታ አማራዎች በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ፣ በማንነታቸው ታስረው ለረጅም ጊዜ በእስር ቤት እየተንገላቱ ነው።
እነዚህ ተራ ዜጎች አይደሉም። ማኅበረሰቡ ጉልሃን ብሎ የሚለያቸው ፣ ማኅበረሰቡ ሊህቃን ብሎ የሚያስቀምጣቸው የሃሳብ መሪዎች ናቸው።
- የፖለቲካ መሪዎች
- ጋዜጠኞች
- አክቲቪስቶች ናቸው። የህዝብ ተወካዮችም አሉበት። የተመረጡ የህዝብ እንደራሴዎች። እነዚህ እንዲፈቱ በናተ በኩል ጥያቄ አቅርባችሁ አስፈጻሚው አካል ምንም ያደረገው ነገር የለም። ይህንን ግን በናተ በኩል ለሚዲያዎችም ለኢትዮጵያ ህዝብም ስታሳውቁ አላይም። ' መንግሥትን ይሄን እንዲያደርግ ጠይቀን ለምክክር ሂደቱ እንዲያግዘን ይህን ጥያቄ አቅርበን በመንግሥት በኩል ትብብር አላገኘንም ' ብላችሁ ስትገልጹ አልሰማም። ከገለጻችሁትም በለሆሳስ ነው የምትገልጹት።
እኔ ከመጀመሪያው ይሄን ሂደት (የምክክር) ከመደገፍ ተነስቼ አሁን ስሜት አልባ ነኝ በዚህ ሂደት የሀገሪቱ ችግር ይቀረፋል የሚለው ተስፋዬን አጥቼበታለሁ፤ ባለው ሂደት ገምግሜ አይቼው።
አሁንም እየቀረቡ ያሉ በናተም በኩል በተወያዮችም በኩል የቀረቡ ጥያቄዎች በደምብ ጎልተው ለኢትዮጵያ ህዝብ መገለጽ አለባቸው።
አሁን በነገራችን ላይ ሌሎች ህዝቦች ሊህቃን ታሳሪዎች የላቸውም፤ ክብሩ ኮሚሽነር ለመረጀዎት ያክል። ከትግራይ የፖለቲካ ልሂቃን የታሰሩ አላውቅም እኔ ፤ ከኦሮሞም ብዙ የታሰሩ ሰዎች ነበሩ ተፈተዋል። በሰፊው ታስሮ ያለ ልሂቃኖቹ ከአማራ ህዝብ ያሉ ተወካዮች ናቸው። ነገ ' ልሂቃኖቼ ታስረውብኛል አልተወከልኩም ' ቢል ይሄ ህዝብ በቂ ምክንያት አለው ብዬ መከራከር እችላለሁ። ስለዚህ ይህ ጉዳይ መፍትሄ ይሰጠው አሁንም።
መንግሥት በትክክል ችግሩ እንዲፈታ የሚፈልግና በውይይት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሄ ያገኛሉ ብሎ የሚያምን ከሆነ ይሄ በጣም ትንሹ ነገር ነው።
እነማን ምን ሲያደርጉ ተይዘው እንደተፈቱ እናውቃለን እዚህ ሀገር። "
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ምን አሉ ?
" ' አማሮች ታስረዋል። በአብዛኛው የታሰሩት አማሮች ናቸው እነሱ እንዲፈቱ ምን ጥረት አድርጋችኋል ? ' ብሎ ለተነሳው ጉዳይ ሌላ ቦታ ምን ገጥሞኛል ' እንዴት ነው ትልልቆቹ የኦሮሞ ፓርቲዎች ከናተ ጋር አይሳተፉም ' በሚል ተነስቶብኛል።
የኛ ጥረት በዘር ሳይሆን በአጠቃላይ የሰው ልጆች መብት ተከብሮ ያለ አግባብ መታሰር የሌለባቸው መታሰር እንደሌለባቸው ግፊት ማድረግ ነው፤ አማሮችም ሆኑ ሌላም ዘሮች።
ግን ገፋ አድርገው ' መንግሥት ምንም እርምጃ ካልወሰደ ለምን ይሄን አላጋለጣችሁም ' ለተባለው ጥያቄ #እኛ_አክቲቪስቶች_አይደለንም። ስለዚህ ጥረት ነው የምናደርገው ያ ነገር እንዲሳካ።
በአጠቃላይ በጣም perfect ሁኔታ ቢኖር እኮ ሀገራዊ ምክክር አያስፈልግም። ችግሮች ስላሉና ችግሮችን ለመቅረፍ የመፍትሄ ፍለጋው አካል መሆን ነው መፍትሄው። የመፍትሄው ፍለጋ አካል በመሆን ሀገራችንን ለማዳን እንችላለን።
እኛ ህዝቦች አምነውን በየቦታውን ስናከራትታቸው ያመጣናቸው ህዝቦች አምነውን፣ መንግሥትም አምኖን ይሄን ስራ ለመስራት ስንጥር ምንም አትጠራጠሩ የበላነውን የጠጣነውን ያህል ጥረት እናደርጋለን የተሳካ እንዲሆን። "
♦ በታጠቁ የመንግስት ወታደሮች ታስሮ ተወስዶ የገባበት ጠፍቷል ፤ መነኩሴ እናቱ በማልቀስ አይናቸው ሳይጎዳ አይቀርም !
ዛሬ የምናስበው ወጣት:
ከጥቂት ወራት በፊት: በልደታ ከፍተኛው ፍ/ቤት: የእነዮሀንስ ቧያዋለው ችሎት ቀን: የእረፍት ሰአት ላይ: አንዲት ሰውነታቸውን እድሜ: ድሕነትና ሀዘን ያደከመው አረጋዊ: በከዘራ የተደገፉና በሌላ ሰው የሚታገዙ እናት: መነኩሴም ይመስላሉ: እንባቸውን እያፈሰሱ: ከጠበቆቹ ወዳንዱ ቀረቡ። እያለቀሱ ነበር። እንደውም በማልቀስ አይናቸው የባሰ ሳይጎዳ አይቀርም። ማንን ላናገር ብለው ግራ ግብት ብሏቸ ጠበቃውን አናገሩት።
ልጃቸው: የዛሬ አመት: የካቲት 10 ቀን: 2017 በወታደሮች እንደተወሰደ: አልተመለሰም። የአማኑኤል የማነብርሃን አቻምየለህ እናት ናቸው።
አማኑኤል ከመቐለ ዩኒቨርሰቲ አዲሃቂ ካምፓስ ተመራቂ ነው። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዛጉዌ ህንፃ ልደታ ቅርንጫፍ ሰራተኛ እያለ ነው ወታደሮች የወሰዱት። ለአረጋዊ እናቱ አንድ ልጅ: አንድ ረዳት ነበር። አረጋዊ እናቱ: ወደጠበቃው ቀርበው: "ልጄ ነው እንደው የምትረዳኝ ነገር ካለ: ለወራት ተንከራተትኩ: ከአቅም በላይ ሆነ ሞክሬ ሞክሬ የሱንም ድምፅ ማግኘት አልቻልኩም" ብለው ለመኑት። ጠበቃው ሊረዳቸው አልቻለም።
አማኑኤል የማነብርሀን: የቀድሞ የኢዜማ አባል እና የተያዘበት ሰሞን ላይ ንጋት ኮከብ ፓርቲ ምስረታ አንቅስቃሴ ላይ ነበር። የዛሬ አመት ታስረው የት እንደገቡ ከማይታወቁ የአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል አንዱ ነው።
የብልጽግና ፓርቲ እንዲሕ ያለውን ግፍ እየፈጸመ ነው ራሱን እንደ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ቆጥሮ ለምርጫ የተሰለፈው። fake election። አማኑኤል በፖሊስ በስርአት ታስሮ ክስ አልተመሰረተበትም። የዛሬ አመት በታጠቁ የመንግስት ወታደሮች ታስሮ ተወስዶ የገባበት ጠፍቷል። ፍትሕ በግፍ ለታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች።
We keep remembering those who are unjustly arrested and forcibly disappeared !
A few months ago, at the Lideta High Court, on the hearing day of the case involving Yohannes Buayalew and others, during a recess, an elderly woman approached one of the defense lawyers.
Her body was worn down by age, poverty, and grief. She leaned on a cane and was being physically supported by another person. Tears streamed down her face as she stood before the lawyer, crying uncontrollably. Her eyes were visibly strained and injured by the intensity of her weeping. Confused and desperate, unsure of whom to turn to, she spoke to the lawyer.
Her child, she said, had been taken by soldiers exactly one year ago, on Yekatit 10, 2017 (E.C.), February 2025, and had never returned. That old lady is the mother of Amanuel Yemanebirhan Achameleh.
Amanuel is a graduate of Mekelle University, Adihaki Campus. At the time of his abduction, he was working as an employee of the Commercial Bank of Ethiopia, Lideta branch, Zagué Building.
To his elderly mother, Amanuel was her only child, her sole support and caregiver. Standing before the lawyer, she pleaded: “He is my child. If there is anything at all you can do to help me. I have wandered for months. I have tried beyond my strength. I have searched and searched, but I have not even been able to hear his voice.” The lawyer was obviously unable to help her.
Amanuel Yemanebirhan is a former member of ETHZEMA and, at the time of his arrest, was involved in politics, organizing for the establishment of the Nigit Kokeb Party. He is one of the many Addis Ababa youth who were arrested one year ago and taken to unknown location, without any information about where they are or whether they are alive.
The Prosperity Party, while committing abuses of this nature, presents itself as a democratic party and participates in elections. A fake election. No charges were laid on Amanuel. Neither court appearances nor disclosure of detention site occurred so far.
We demabd Justice for the Addis Ababa youth who have been detained through repression and injustice.
💪💪💪አትልፋ💪💪💪🤣
እኛ ማለት፤
ስትገሉን የምንበዛ
ግፋችሁ የማይሰብረን
ጭካኔያችሁ ጀብደኛ የሚያደርገን
ከፍቅር ውጭ የምንም ልጓም የማያስቆመን
ግፍን የምንፀየፍ እና ፍትህን አብዝተን የምንወድ
የዛ የረመጡ ትውልድ ቃርሚያዎች ነን። ዛሬ በቃርሚያነታችን እንዲህ ከሆናችሁ አባቶቻችን ሰገነት ላይ የደረስን ለት .....!!!
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ደጋዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ከመሸገው የአገዛዙ ሀይል ጋር በተደረገ አውደውጊያ በጠላት ላይ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ አደረሰ።
===============================
በዛሬው ዕለት በቀን 11/07/2018 ዓ.ም
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር የሻለቃ ሶስት እና የሻለቃ አራት ከደጋ ዳሞት አባት አርበኞች ጋር በፈጠሩት ድንቅ ጥምረት ፈረስቤት ከተማ የመሸገውን ጠላት እያጨዱ ሲከምሩት ውለዋል።
የቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር #99ኛ ክ/ጦር አመራሮች እና አባላት የጠላትን እንቅስቃሴ በጥልቀት በማጥናት የጠላትን አከርካሪ ለመሰበር ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩ የሻለቃ ሶስት እና የሻለቃ አራት አባላት ከአባት አርበኞች ጋር በመቀናጀት ከ5:30 - 10:30 ድረስ በተደረገ እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያ በርካታ የአገዛዙ ሀይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
👉የአይበገሬዎችን የፋኖን ምት መቋቋም ያልቻለው የጠላት ሀይል በሞርተርና በዙ23 የንጹሀንን ቤት አውድሟል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 11/2018 ዓ.ም
+1
የአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ የደጃዝማች 4ኛ ኮር አመራሮች አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ጥልቅ ውይይት አድርገው በየቀጠናው ፍትህ አስፋኝ ኮማንድ አቋቁመዋል።
በጀግናው ፋኖ አማካኝነት አማራ መር መንግስት እየተዋቀረ በነጻነት ተፋላላሚው ፋኖ ፍትሃዊ አስተዳደር እየሰፈነ ይገኛል።
የአረመኔው የብልጽግና ሠራዊት በቸርተከል ቀበሌ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ውድመትን አድርሷል‼️
የካቲት 11/2018 ዓ.ም
የአሸባሪው አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ገረዶች አድማ ብተና ፣ ሚኒሻ ፣ ፖሊስ ፣ መከላከያ በጋራ በመሆን ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ በቀን 2/ 06/ 2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት በቸርተካል ቀበሌ በፋኖ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ቢሞክርም የአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የ14ኛ ክ/ጦር ፋኖዎች እና የጎዛምን ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት በጋራ በመናበብ ጠላትን እቅድ እንዲከሽፍ ተደርጓል።
ነገር ግን የጠላት እቅድ ባስበው ልክ ውጤታማ ባለመሆኑ ከዐ2/06/2018 ዓ.ም እስከ 08/06/2018 ዓ.ም ለ6 ተከታታይ በቸርተከል ቀበሌ ሲቆይ በርካታ አሰቃቂ እና አስነዋሪ ችግሮችን ፈፅሟል ። ከችግሮች መካከል ጥቂቶቹ እንደሚከተለዉ ይቀርባሉ።
1. በቸርተከል ቀበሌ ግለሰቦች ልጆቻቸው ለጋብቻ ወግ ማዕረግ በመድረሳቸው ለሰርግ ፕሮግራም የተዘጋጁ ዱቄት፣ የጠላ ድፍድፍ በአሸባሪው የአብይ አህመድ ወታደር ወጦ ተደፍቶባቸዋል።
2. በቸርተከል ከተማ ቁጥሩ በጣም ብዙ የሆነ ቤት ቁልፉን በመስበር የግለሰቦች ቤት በአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሠራዊት ተፈፅሟል ።
3. የአብይ አህመድ ዘራፊ ቡድን በቸርተከል ቀበሌ በአማሪት ጎጥ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የመፅሐፋ Store ክፍሎችን ቁልፍ በመስበር መፅሐፎችን አውድሟል።
4. የግለሰቦችን ቤት በከባድ መሳሪያ አውድሟል። በርካታ ሕጻናትንም ቁስለኛ አድርጓቸዋል።
5. ሦስት ቤቶችን በእሳት ለማቃጠል ቢሞክርም በህዝብ ርብርብ የእሳት አደጋው ቁሟል።
6. በቸርተከልና አማሪት ጎጥ የእንስሳት የህክምና ጣቢያዎች የህክምና ማቴሪያሎች፣ መድኃኒቶች ሙሉ በሙሉ በአሸባሪው መንግስት ወድመዋል።
7. በቸርተከል ከተማ የሚገኝ የግለስብ ፎቅ መስታወቱ በአሸባሪው አብይ አህመድ ጦር ረግፏል።
8. በቸርተከል እንዶዳም ጎጥ የግለሰቦች የሽንኮራ አገዳ አትክልት በአሸባሪው የአብይ አህመድ ወታደር ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
መረጃው የጎዛምን ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር የሚዲያና ግንኙነት ክፍል ነው።
©የ206 ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል።
