ru
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
3 664
Подписчики
+2024 часа
+3787 дней
+1 08530 дней
Архив постов
በደብረ ማርቆስ ከተማ የካድሬዎች የነፃ መሬት ወረራ !! የካቲት 12/2018 ዓ.ም ======================================== ደብረ ማርቆስ ከተማ ጡረተኞችና የዘራፊዎች ህዝባቸውን በማሰቃየትና ለጠላት አሳልፈው በመስጠት የተካኑ እድሜ ጠገብ ካድሬውች ከየ ወረዳው ተሰባስበው የሚዶልቱባት፣ ግፍ ፈሶ የሚፈስባት መምህራን በገፍ ታስረው የተሰቃዩባት ሴቶች በቡድን የተደፈሩባትና ለመገመት የሚያዳግት የወጣቶች ግድያ የተበራከተባት መሆኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪ የሚያውቀው ሀቅ ነው። በከተማዋ የተሰገሰጉ የአረመኔው ሰራዊት ካድሬዎች ጦርነቱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከነጋዴው ማህበረሰብ ከፍተኛ ዝርፊያ ፈፅመዋል።እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የደብረ ማርቆስ ሆስፒታል አልትራሳውንድ ማሽን ከተቀመጠበት ክፍል ተሰርቋል፣ የከተማዋ ሰፋፊ ነፃ መሬቶች በካድሬዎች ተወረው ህፃናት የሚቦርቁበት መስክ ሳይቀር ተሸንሽኖ ካድሪ ተቀራምቶታል፣በማህበራት እና የሊዝ ሽያጭ ሰበብ አሉ የተባሉ ነፃ መሬቶች ካድሬዎችና የጦር አበጋዞች በልጅ ልጅ ሳይቀር ዘመድ አዝማድ ተጠራርቶ በከተማዋ ቤት እየሰሩ መክረማቸውን የከተማው ማህበረሰብ በገፍ መረጃ አድርሶናል። እኒህን እና መሰል ነጭ ወንጀሎችን ተከታትለን የደረስንበት ሲሆን ከሙሉ ማስረጃዎች ጋር የካድሬዎች የመሬት ወረራ ከታች ቀርቧል። ዘራፊዎች የእድር ድንኳን ወጥረው ስማችንን በሚያጠለሹበት በዚህ ጊዜ በከተማዋ ሰርገን በመግባት ካድሪው እየፈፀመ ያለውን አይን ያወጣ የመሬት ችርቻሮ ማሳያ የሚሆን ስርቆት እንደሚከተለው አቅርበናል ። ወ/ሮ ታሪክ ሞትባይኖር የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የአብማ ክ/ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ስትሆን ዕድሜዋ 45 ያለፈ የሌቦች ካፒቴን ናት። ዕድሜዋም ሴትነቷም ሳይገድባት ለአረመኔው ሰራዊት እህቶቻችንን እያደነች ስታቀርብ የነበረችው ወ/ሮ ታሪክ ሞት ባይኖር የተሰጣትን የብልፅግናን ስልጣን በመጠቀም 8,879,200(ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሽህ ሁለት መቶ) ብር የሚገመት 500 ካሬ ሜትር በማጭበርበር በሁለት ህፃናት ልጆቿ ስም ቤት በመስራት የደብረ ማርቆስ ከተማ መሬትን መዝረፏን አረጋግጠናል። ወ/ሮ ታሪክ ሞት ባይኖር ከወ/ሮ አቢዮት እጅጉ ጋር በመስማማት በደብረ ማርቆስ ከተማ አብማ ክ/ከተማ ቀበሌ 13 በሰሜን ሻምበል ምኑየለት፣ በደቡብ አዲሱ መለሰ፣ በምስራቅ ባዶ ቦታ፣ በምዕራብ መንገድ የሚያዋስነውን 500 ካሬ ሜትር የሆነውን የህዝብ መሬት ለመዝረፍ በመስማማት ወ/ሮ አቢዮት እጅጉ ከዚህ በፊት ከአባቷ ከአቶ እጅጉ ይግዛው በውርስ ከወንድሞቿ ጋር ያገኘችውን 500 ካሬ ሜትር መነሻ በማድረግ ወ/ሮ ታሪክ ሞትባይኖር ያላትን ስልጣን በመጠቀም ወ/ሮ አቢዮት እጅጉ በድጋሚ 500 ካሬ ሜትር ከአባቴ ከአቶ እጅጉ ይግዛው የውርስ መሬት ይገባኛል የሚል ጥያቄ እንድትታቀርብ በማድረግና ከዚህ በፊት ከወንድሞቿ ጋር ያገኘችውን የውርስ መሬት ማረጋገጫ ደረሰኞችን ለሌላ የ500 ካሬ ሜትር መቀበያ በማቅረብ በአንድ ደረሰኝ 1000 ካሬ ሜትር እንዲሸነሸን አድርጋለች። ወ/ሮ ታሪክ ሞትባይኖር ባላት ስልጣን መሰረት የሰነድ መርማሪና አጽዳቂ በመሆን የወ/ሮ አቢዮት እጅጉ ጥያቄ በመቀበልና የተጭበረበረ ሰነድ በማጽደቅ 500 ካሬ ሜትር በ አቢዮት እጅጉ ስም እንዲተላለፍ ሁኗል። ይህንን በሚገባ ያሳካችው ወ/ሮ ታሪክ ሞትባይኖር በሁለት ህፃን ልጆቿ ማለትም በህፃን ኤልሳቤጥ ይትባረክ እና በህፃን ራክቤል ይትባረክ ስም በሞግዚትነት ከወ/ሮ አቢዮት እጅጉ ግዥን ፈፅሚያለው በማለት ከዚህ ቀደም በመመሳጠር ያገኙትን መሬት ለመከፋፈል በሚያመች መልኩ በህፃናቱ ስም በህገወጥ መንገድ 250 ካሬ ሜትር በመካፈል መሬቱ ላይ ቤት መስራቷን አረጋግጠናል። ከታች የተቀመጠው የሰነድ ማስረጃ 8.8 ሚሊዮን ብር የሚገመተውን መሬት ከህዝብ በመዝረፍ የብልፅግና ካድሪን የዝርፊያ ሰንሰለት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን ትግሉን በማጠልሸት ላንቃቸው እስኪሰነጠቅ የሚጮኹ ሌባዎች ጉድ በዚህ መልኩ እየተከታተልን መሆኑን ህዝባችን እንዲያውቅ እንፈልጋለን ። ህዝብ በሚጨፈጨፍበት ወረራ መሀል የሚበለጽጉ ካድሬዎችን ከማጋለጥ ባለፈ ተከታትለን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን ። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

#በየቀኑ_የጠላት_ሀይል_እተመመ_ነው በ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በጎዛምን ወረዳ ሊባኖስ ቀበሌ ውስጥ አንድን የአካባቢው ነዋሪ የሆነች ልጃገረድ አስገድዶ ለመድፈር ሙከራ ሲያደርግ የነበረን አንድ የአረመኔው ብልጽግና ልክስክስ ሚሊሻ አንድ የአካባቢው ነዋሪ የሆነ ጀግና ግንባሩን በዘነዘና ብሎ በመጣል ትጥቁን ይዞ ወጥቷል። በተያያዘ ዜናም በዚሁ ወረዳ ደስ አሳም አቦ ቀበሌ አካባቢ ነዋሪ የሆነ አንድ ነዋሪ ለቅለቂታ የሚገኝን ቢሆነኝ መርሻ የተባለን ቅጥረኛ የብልጽግና ሚሊሻ ግምባሩን በማለት ትጥቁን ተቀብሎት ሂዷል። 👉ሁለት የአረመኔው የብልጽግና ሠራዊት አባላት ከደብረ ኤልያስ ወረዳ ከተማ በመነሳት የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። የንጹሐንን ደም ሰይጣናዊ ተግባራትን በመፈጸም ለተገነባው የብልጽግና ዙፋን ማጽኛነት የሚጠቀመው የጸረ አማራውን የብልጽግና አገዛዝ በመቃወም ወደ ማሕበረሰባቸው የሚቀላቀሉት የአገዛዙ የሠራዊት አባላት ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል። በዛሬው ዕለትም ብሩክ ጫሜባ ለሬቦና ፲ አለቃ ኤርሚያስ ሻታ የተባሉ ሁለት የመቶ መሪዎች ከደብረ ኤልያስ ከተማ በመክዳት የ14ኛ ክፍለ ጦርን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል። ድል ለአማራ ፋኖ! ©የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ዘመን ባሳዝነው 12/ዐ6/2018 ዓ.ም

" እነማን ምን ሲያደርጉ ተይዘው እንደተፈቱ እናውቃለን እዚህ ሀገር ! " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን ምን ጠየቁ ? " በርካታ አማራዎች በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ፣ በማንነታቸው ታስረው ለረጅም ጊዜ በእስር ቤት እየተንገላቱ ነው። እነዚህ ተራ ዜጎች አይደሉም። ማኅበረሰቡ ጉልሃን ብሎ የሚለያቸው ፣ ማኅበረሰቡ ሊህቃን ብሎ የሚያስቀምጣቸው የሃሳብ መሪዎች ናቸው። - የፖለቲካ መሪዎች - ጋዜጠኞች - አክቲቪስቶች ናቸው። የህዝብ ተወካዮችም አሉበት። የተመረጡ የህዝብ እንደራሴዎች። እነዚህ እንዲፈቱ በናተ በኩል ጥያቄ አቅርባችሁ አስፈጻሚው አካል ምንም ያደረገው ነገር የለም። ይህንን ግን በናተ በኩል ለሚዲያዎችም ለኢትዮጵያ ህዝብም ስታሳውቁ አላይም። ' መንግሥትን ይሄን እንዲያደርግ ጠይቀን ለምክክር ሂደቱ እንዲያግዘን ይህን ጥያቄ አቅርበን በመንግሥት በኩል ትብብር አላገኘንም ' ብላችሁ ስትገልጹ አልሰማም። ከገለጻችሁትም በለሆሳስ ነው የምትገልጹት። እኔ ከመጀመሪያው ይሄን ሂደት (የምክክር) ከመደገፍ ተነስቼ አሁን ስሜት አልባ ነኝ በዚህ ሂደት የሀገሪቱ ችግር ይቀረፋል የሚለው ተስፋዬን አጥቼበታለሁ፤ ባለው ሂደት ገምግሜ አይቼው። አሁንም እየቀረቡ ያሉ በናተም በኩል በተወያዮችም በኩል የቀረቡ ጥያቄዎች በደምብ ጎልተው ለኢትዮጵያ ህዝብ መገለጽ አለባቸው። አሁን በነገራችን ላይ ሌሎች ህዝቦች ሊህቃን ታሳሪዎች የላቸውም፤ ክብሩ ኮሚሽነር ለመረጀዎት ያክል። ከትግራይ የፖለቲካ ልሂቃን የታሰሩ አላውቅም እኔ ፤ ከኦሮሞም ብዙ የታሰሩ ሰዎች ነበሩ ተፈተዋል። በሰፊው ታስሮ ያለ ልሂቃኖቹ ከአማራ ህዝብ ያሉ ተወካዮች ናቸው። ነገ ' ልሂቃኖቼ ታስረውብኛል አልተወከልኩም '  ቢል ይሄ ህዝብ በቂ ምክንያት አለው ብዬ መከራከር እችላለሁ። ስለዚህ ይህ ጉዳይ መፍትሄ ይሰጠው አሁንም። መንግሥት በትክክል ችግሩ እንዲፈታ የሚፈልግና በውይይት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሄ ያገኛሉ ብሎ የሚያምን ከሆነ ይሄ በጣም ትንሹ ነገር ነው። እነማን ምን ሲያደርጉ ተይዘው እንደተፈቱ እናውቃለን እዚህ ሀገር። " የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ምን አሉ ? " ' አማሮች ታስረዋል። በአብዛኛው የታሰሩት አማሮች ናቸው እነሱ እንዲፈቱ ምን ጥረት አድርጋችኋል ? ' ብሎ ለተነሳው ጉዳይ ሌላ ቦታ ምን ገጥሞኛል ' እንዴት ነው ትልልቆቹ የኦሮሞ ፓርቲዎች ከናተ ጋር አይሳተፉም ' በሚል ተነስቶብኛል። የኛ ጥረት በዘር ሳይሆን በአጠቃላይ የሰው ልጆች መብት ተከብሮ ያለ አግባብ መታሰር የሌለባቸው መታሰር እንደሌለባቸው ግፊት ማድረግ ነው፤ አማሮችም ሆኑ ሌላም ዘሮች። ግን ገፋ አድርገው ' መንግሥት ምንም እርምጃ ካልወሰደ ለምን ይሄን አላጋለጣችሁም ' ለተባለው ጥያቄ #እኛ_አክቲቪስቶች_አይደለንም። ስለዚህ ጥረት ነው የምናደርገው ያ ነገር እንዲሳካ። በአጠቃላይ በጣም perfect ሁኔታ ቢኖር እኮ ሀገራዊ ምክክር አያስፈልግም። ችግሮች ስላሉና ችግሮችን ለመቅረፍ የመፍትሄ ፍለጋው አካል መሆን ነው መፍትሄው። የመፍትሄው ፍለጋ አካል በመሆን ሀገራችንን ለማዳን እንችላለን። እኛ ህዝቦች አምነውን በየቦታውን ስናከራትታቸው ያመጣናቸው ህዝቦች አምነውን፣ መንግሥትም አምኖን ይሄን ስራ ለመስራት ስንጥር ምንም አትጠራጠሩ የበላነውን የጠጣነውን ያህል ጥረት እናደርጋለን የተሳካ እንዲሆን። "

♦ በታጠቁ የመንግስት ወታደሮች ታስሮ ተወስዶ የገባበት ጠፍቷል ፤ መነኩሴ እናቱ በማልቀስ አይናቸው ሳይጎዳ አይቀርም ! ዛሬ የምናስበው ወጣት: ከጥቂት ወራት በፊት: በልደታ ከፍተኛው ፍ/ቤት: የእነዮሀንስ ቧያዋለው ችሎት ቀን: የእረፍት ሰአት ላይ: አንዲት ሰውነታቸውን እድሜ: ድሕነትና ሀዘን ያደከመው አረጋዊ: በከዘራ የተደገፉና በሌላ ሰው የሚታገዙ እናት: መነኩሴም ይመስላሉ: እንባቸውን እያፈሰሱ: ከጠበቆቹ ወዳንዱ ቀረቡ። እያለቀሱ ነበር። እንደውም በማልቀስ አይናቸው የባሰ ሳይጎዳ አይቀርም። ማንን ላናገር ብለው ግራ ግብት ብሏቸ ጠበቃውን አናገሩት። ልጃቸው: የዛሬ አመት: የካቲት 10 ቀን: 2017 በወታደሮች እንደተወሰደ: አልተመለሰም። የአማኑኤል የማነብርሃን አቻምየለህ እናት ናቸው። አማኑኤል ከመቐለ ዩኒቨርሰቲ አዲሃቂ ካምፓስ ተመራቂ ነው። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዛጉዌ ህንፃ ልደታ ቅርንጫፍ ሰራተኛ እያለ ነው ወታደሮች የወሰዱት። ለአረጋዊ እናቱ አንድ ልጅ: አንድ ረዳት ነበር። አረጋዊ እናቱ: ወደጠበቃው ቀርበው: "ልጄ ነው እንደው የምትረዳኝ ነገር ካለ: ለወራት ተንከራተትኩ: ከአቅም በላይ ሆነ ሞክሬ ሞክሬ የሱንም ድምፅ ማግኘት አልቻልኩም" ብለው ለመኑት። ጠበቃው ሊረዳቸው አልቻለም። አማኑኤል የማነብርሀን: የቀድሞ የኢዜማ አባል እና የተያዘበት ሰሞን ላይ ንጋት ኮከብ ፓርቲ ምስረታ አንቅስቃሴ ላይ ነበር። የዛሬ አመት ታስረው የት እንደገቡ ከማይታወቁ የአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል አንዱ ነው። የብልጽግና ፓርቲ እንዲሕ ያለውን ግፍ እየፈጸመ ነው ራሱን እንደ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ቆጥሮ ለምርጫ የተሰለፈው። fake election። አማኑኤል በፖሊስ በስርአት ታስሮ ክስ አልተመሰረተበትም። የዛሬ አመት በታጠቁ የመንግስት ወታደሮች ታስሮ ተወስዶ የገባበት ጠፍቷል። ፍትሕ በግፍ ለታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች። We keep remembering those who are unjustly arrested and forcibly disappeared ! A few months ago, at the Lideta High Court, on the hearing day of the case involving Yohannes Buayalew and others, during a recess, an elderly woman approached one of the defense lawyers. Her body was worn down by age, poverty, and grief. She leaned on a cane and was being physically supported by another person. Tears streamed down her face as she stood before the lawyer, crying uncontrollably. Her eyes were visibly strained and injured by the intensity of her weeping. Confused and desperate, unsure of whom to turn to, she spoke to the lawyer. Her child, she said, had been taken by soldiers exactly one year ago, on Yekatit 10, 2017 (E.C.), February 2025, and had never returned. That old lady is the mother of Amanuel Yemanebirhan Achameleh. Amanuel is a graduate of Mekelle University, Adihaki Campus. At the time of his abduction, he was working as an employee of the Commercial Bank of Ethiopia, Lideta branch, Zagué Building. To his elderly mother, Amanuel was her only child, her sole support and caregiver. Standing before the lawyer, she pleaded: “He is my child. If there is anything at all you can do to help me. I have wandered for months. I have tried beyond my strength. I have searched and searched, but I have not even been able to hear his voice.” The lawyer was obviously unable to help her. Amanuel Yemanebirhan is a former member of ETHZEMA and, at the time of his arrest, was involved in politics, organizing for the establishment of the Nigit Kokeb Party. He is one of the many Addis Ababa youth who were arrested one year ago and taken to unknown location, without any information about where they are or whether they are alive. The Prosperity Party, while committing abuses of this nature, presents itself as a democratic party and participates in elections. A fake election. No charges were laid on Amanuel. Neither court appearances nor disclosure of detention site occurred so far. We demabd Justice for the Addis Ababa youth who have been detained through repression and injustice.

💪💪💪አትልፋ💪💪💪🤣 እኛ ማለት፤ ስትገሉን የምንበዛ ግፋችሁ የማይሰብረን ጭካኔያችሁ ጀብደኛ የሚያደርገን ከፍቅር ውጭ የምንም ልጓም የማያስቆመን ግፍን የምንፀየፍ እና ፍትህን አብዝተን የምን
💪💪💪አትልፋ💪💪💪🤣 እኛ ማለት፤ ስትገሉን የምንበዛ ግፋችሁ የማይሰብረን ጭካኔያችሁ ጀብደኛ የሚያደርገን ከፍቅር ውጭ የምንም ልጓም የማያስቆመን ግፍን የምንፀየፍ እና ፍትህን አብዝተን የምንወድ የዛ የረመጡ ትውልድ ቃርሚያዎች ነን። ዛሬ በቃርሚያነታችን እንዲህ ከሆናችሁ አባቶቻችን ሰገነት ላይ የደረስን ለት .....!!!

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ደጋዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ከመሸገው የአገዛዙ ሀይል ጋር በተደረገ አውደውጊያ በጠላት ላይ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ አደረሰ። =============================== በዛሬው ዕለት በቀን 11/07/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር የሻለቃ ሶስት እና የሻለቃ አራት ከደጋ ዳሞት አባት አርበኞች ጋር በፈጠሩት ድንቅ ጥምረት ፈረስቤት ከተማ የመሸገውን ጠላት እያጨዱ ሲከምሩት ውለዋል። የቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር #99ኛ ክ/ጦር አመራሮች እና አባላት የጠላትን እንቅስቃሴ በጥልቀት በማጥናት የጠላትን አከርካሪ ለመሰበር ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩ የሻለቃ ሶስት እና የሻለቃ አራት አባላት ከአባት አርበኞች ጋር በመቀናጀት ከ5:30 - 10:30 ድረስ በተደረገ እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያ በርካታ የአገዛዙ ሀይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። 👉የአይበገሬዎችን የፋኖን ምት መቋቋም ያልቻለው የጠላት ሀይል በሞርተርና በዙ23 የንጹሀንን ቤት አውድሟል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ የካቲት 11/2018 ዓ.ም

የአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ የደጃዝማች 4ኛ ኮር አመራሮች አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ጥልቅ ውይይት አድርገው በየቀጠናው ፍትህ አስፋኝ ኮማንድ አቋቁመዋል። በጀግናው ፋኖ
+1
የአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ የደጃዝማች 4ኛ ኮር አመራሮች አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ጥልቅ ውይይት አድርገው በየቀጠናው ፍትህ አስፋኝ ኮማንድ አቋቁመዋል። በጀግናው ፋኖ አማካኝነት አማራ መር መንግስት እየተዋቀረ በነጻነት ተፋላላሚው ፋኖ ፍትሃዊ አስተዳደር እየሰፈነ ይገኛል።

የአረመኔው የብልጽግና ሠራዊት በቸርተከል ቀበሌ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ውድመትን አድርሷል‼️ የካቲት 11/2018 ዓ.ም የአሸባሪው አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ገረዶች አድማ ብተና ፣ ሚኒሻ ፣ ፖሊስ ፣ መከላከያ በጋራ በመሆን ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ በቀን 2/ 06/ 2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት በቸርተካል ቀበሌ በፋኖ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ቢሞክርም የአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የ14ኛ ክ/ጦር ፋኖዎች እና የጎዛምን ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት  በጋራ በመናበብ ጠላትን እቅድ እንዲከሽፍ ተደርጓል። ነገር ግን የጠላት እቅድ ባስበው ልክ ውጤታማ ባለመሆኑ ከዐ2/06/2018 ዓ.ም እስከ 08/06/2018 ዓ.ም ለ6 ተከታታይ በቸርተከል ቀበሌ ሲቆይ በርካታ አሰቃቂ እና አስነዋሪ ችግሮችን ፈፅሟል ። ከችግሮች መካከል ጥቂቶቹ እንደሚከተለዉ ይቀርባሉ። 1. በቸርተከል ቀበሌ ግለሰቦች ልጆቻቸው ለጋብቻ ወግ ማዕረግ በመድረሳቸው ለሰርግ ፕሮግራም የተዘጋጁ ዱቄት፣ የጠላ ድፍድፍ    በአሸባሪው የአብይ አህመድ ወታደር ወጦ ተደፍቶባቸዋል። 2. በቸርተከል ከተማ ቁጥሩ በጣም ብዙ የሆነ ቤት ቁልፉን በመስበር የግለሰቦች ቤት በአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሠራዊት ተፈፅሟል ። 3. የአብይ አህመድ ዘራፊ ቡድን በቸርተከል ቀበሌ በአማሪት ጎጥ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የመፅሐፋ Store ክፍሎችን ቁልፍ በመስበር መፅሐፎችን አውድሟል። 4. የግለሰቦችን ቤት በከባድ መሳሪያ አውድሟል። በርካታ ሕጻናትንም ቁስለኛ አድርጓቸዋል። 5. ሦስት ቤቶችን በእሳት ለማቃጠል ቢሞክርም በህዝብ ርብርብ የእሳት አደጋው ቁሟል። 6. በቸርተከልና አማሪት ጎጥ የእንስሳት የህክምና ጣቢያዎች የህክምና ማቴሪያሎች፣ መድኃኒቶች ሙሉ በሙሉ በአሸባሪው መንግስት ወድመዋል። 7. በቸርተከል ከተማ የሚገኝ የግለስብ ፎቅ መስታወቱ በአሸባሪው አብይ አህመድ ጦር  ረግፏል። 8. በቸርተከል እንዶዳም ጎጥ የግለሰቦች የሽንኮራ አገዳ አትክልት በአሸባሪው የአብይ አህመድ ወታደር ሙሉ በሙሉ ወድሟል። መረጃው የጎዛምን ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር የሚዲያና ግንኙነት ክፍል ነው። ©የ206 ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል።

የአብይ ሰራዊት የሚበለው በልቶ የሚዘርፈውን ዘርፎ የቀረውን የአማራ አርሶ አደር እህል በዚህ መልኩ አየበተነ እያወደመው ነው ምርጫችን ማሸነፍ ብቻ ነው ትግላችን የህልውና ነው የምንል በምክንያት የው።

👉ከአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ከር የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች ማህበረሰባችንን የፋኖ አባላት ነን ብር አስገቡ እያሉ የአቢሲኒያና የተለያዬ አካውንት እየሰጡ  የዝርፊያ ስራ ላይ የተሰማሩ አጭበርባሪዎች እንዳሉ ከማህበረሰባችን በደረሰን ጥቆማ አረጋግጠናል። እነዚህ ወንበዴዎች:- ➡️1ኛ ከፋኖ መደበኛው ሰራዊት ውጭ የሆኑና ከጥርናፌ ውጭ የሆኑ ኑሯቸውን ዝርፊያ ላይ መሰረት ያደረጉ ናቸው ➡️2ኛ ከብልጽግና ተልዕኮ በመቀበል የስለላ ስራ የሚሰሩ ቡድኖች መሆናቸውን የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉ 👉ለመላው የደንበጫ ወረዳ ማህበረሰብና ሌሎች አጎራባች ወረዳዎች በመሉ ከእንደዚህ አይነት ዘራፊዎች እራሱን እንዲጠብቅ እና በስልክ እየደወሉ ብር አስገቡ የሚሉ ግለሰቦችን ስልክ ቁጥርና የባንካ አካውንት ቁጥር በውስጥ አድራሻችን ጥቆማውን እንድትሰጡ ሲል #አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር በጥብቅ ያሰጠነቅቃል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር የካቲት 11/2018 ዓ.ም

ከሰሞኑ እነዚህን መኪኖች እያዳነቁ በማህበራዊ ሚዲያ ለሚለጠፉት በማወቅም ይሁን በአለማወቅ ለብልጽግና ፕሮፖጋንዳ ከመስራት የማይተናነስ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። እነዚህ መኪኖች ለምን አይነት warfare [ውጊያ] እንደሚጠቅሙ እንኳ መጀመሪያ መረዳት ያለብን ይመስለኛል። እነዚህን መሰል የወታደራዊ ተሽከርካሪ ኮንቮይን አገልግሎት ከመስጠት የዘለለ ግፋቢል የተቆጣጠርካቸው ቀጠናዎች ላይ የእጀባና የከተማ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ልትከላከልበት ትችል ይሆናል እንጂ ከብረት ለበስ ባለጎማ ተሽከርካሪ በተለምዶ ፔንፔ ከምንው ወታደራዊ ተሽከርካሪ  የሚበልጥ ተግባር እንኳ የለውም። ነገር ግን አብይ አህመድ ደርሶ ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገ ለመመስል የሚሰራ የማይሰራውን ብረት ለብስ በሎቤድ እየጫነ በአማራው ላይ የተለየ የጦርነት ስነልቦና ለማሳየት ቢሞክርም ስንጀምረውም ይሄ ሁሉ አንደ አለው አውቀን እና እንደምንረከበው አምነን የጀመርነው ትግል ነው። ሲጀመር የቀረን ብረት ለበሱ ይሆናል እንጂ የመካከለኛው እርቀት መሳሪያ በገፍ እንደተረከብነው ሀገሬውም አለምም የሚያውቀው ነው። አሁን ደግሞ የቀረንን ታንኮችና መድፎች ከትግራይና ኤርትራ ጋር ጦርነት ልጀምር ነው በሚል ነገር ግን ስትራቴጂካዊ በሆነ ስልት አማራውን የመክበብ ሁኔታን እየተከተለ እንደሆነ በግሌ ይሰማኛል። በአጭሩ ስለዚህ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ግር የተሰኛችሁ ካላችሁ ዲሽቃ የጫነ የኮንቮይን ወታደራዊ ተሽከርካሪ መሆኑን ተረዱ። [ መኪናው አይዋጋህ] እኛ ፋኖዎች ደግሞ በርከት ያለ ፀረ-ዲሽቃ ሹተር ከታጠቅን ቆየን። ይህ መኪና በሰርሳሪ ጥይት በፀረ-ዲሽቃ ከጥቅም ውጭ ይሆናል። ሀሳቡን ለእኛ ሜዳ ላይ ለአለነው ተውልን። ~የተጻፈው ለግንዛቤ ማስጨበጫ ብቻ ነው። ©️ ግሩም ሰው

ቀን 11/06/2018 በደቡብ ጎንደር በሐሙሲት ከተማ የአገዛዙ አሽከር የሆኑት አድማ ብተና እና ሚኒሻ ፖሊስ  ከ02/062018እስከ 04/06/2018   ከአንበሳሜ እሰከ ሐሙሲት ከተማ በተደረገ አውደ ውጊያ በደረሰበት መመደምሰስ እና ያየዘውን የቡድን መሳሪያ 02 ድሽቃ 02ብሬን 167ክላሽ 32አብራረው አንድ አይሱዙ ሙሉ የድሽቃ ተተኳሽ 6 ወታደራዊ ፖትሮል ምሮኮ የሆነበት  የአብይ አሽከር ሐሙሲት ላይ ከደባርቅ መጦ የተቀመጠው ሐይል የሐሙሲትን ከተማ ህዝብ የአስኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት ከቀኑ 10:00 ሰዓት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ በመከልከል ከቀኑ 11:00 ሰዓት የሰው እንቅስቃሴ በመከልከል የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአብይ አማሮች በሱቪሉ ማህበረሰብ ላይ ቤት ለቤት ፍተሻ በሚል ሰበብ ማህበረሰቡን እየዘረፋ እና እያ ገላቱ ይገኛሉ።አመጣጡ የአማራን ህዝብ መጨፍጨፍ አላመው አድርጎ የተነሰው የአብይ አህመድ ስርዓት  ከከተማው ማህበረሰብ በተጨማሪ አረሶ አደሮችንም ወደ ገቢያ ሲሂዱ ፍጣ እንዳይለብሱ እና ብትር እንዳይዙም ከልክላል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ጣና ገላውዲዎሰ ክ/ ጦር ህ/ግ ፋኖ ፍቅሩ ባየ

የአፋብን 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ከደብረ ኤልያስ ወረዳ ጃቢ ገነት ዙሪያ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። የአማራ ፋኖን የሕልውና ትግል ከጫፍ ለማድረስና የነገ የትግል ፍኖታችንን የቀናና የተስተካከለ ለማድረግ ከሕዝባችን ጋር የሚደርጉ የተጠናከሩ የውይይት መድረኮች ወሳኝ ሚና አላቸው። በዚህም መሠረት በክፍለ ጦራችን የሚደረጉ የሕዝብ ንቅናቄ መድረኮች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በዛሬው ዕለትም የ14ኛ ክፍለ ጦር የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ከጃቢ ገነት ቀበሌ ማሕበረሰብ ጋር ታላቅ ሕዝባዊ ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ የአማራ ፋኖ የትግል ሂደት ከትናንት እስከ ዛሬ፣የሕዝባችን በትግሉ ውስጥ፣ የጊዜያዊ መንግስት አወቃቀርን በተመለከተና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይቶችን በማድረግ የቀበሌ አመራሮችን በመሾም የዕለቱ የውይይት መድረክ ተጠናቋል። ድል ለአማራ ፋኖ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር14ኛ ክፍለ ጦር የሕዝብ ግንኙነት