ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more3 664
Subscribers
+2024 hours
+3787 days
+1 08530 days
Posts Archive
Repost from ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፤ እንደ አንበሳ ተከናንቦ፣ እንደ ንስር ታድሶና በብርሃን ፍጥነት በመጓዝ፣ የማንንም ባዕድ አጀንዳ ሳይቀበል ወደ መጨረሻው የነፃነት ድል እየገሰገሰ ይገኛል። በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎና በሸዋ አንድነቱን አጥንቶ የአባቶቹን ምድር ከወሮበላው የአብይ አህመድ ሥርዓት ሊያላቅቅ የመጨረሻውን የድል ፊሽካ ለመንፋት ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።
ይህንን ታሪካዊ የምስራች ለመስማትና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት፣ እኛ በቀጥታ ከግንባር ሆነን በቴሌግራም ሚዲያችን መረጃዎችን እያደረስንዎት እንገኛለን። ሚዲያችን ለመላው ሕዝባችን ተደራሽ እንዲሆንና ድምፃችን እንዲሰማ Share እና Like በማድረግ ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን! እርስዎም ይወዳጁን!!!!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+3
ቲም መሪው በስሩ የነበሩ ስድስት ወታደሮችን ይዞ ፋኖን ተቀላቀለ።
ደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ የሚገኘው የብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አባል የነበሩ 5 አድማ ብተና እና አንድ ልዩ ሀይል ሲበተን ወደ ፖሊስ ገብቶ የነበረ በአጠቃላይ በተሳሳተ መንገድ ከፀረ አማራው ስርዓት ጋር ተሰልፈው የነበሩ ስድስት ወታደሮች አፋብን ያቀረበውን የምህረት አዋጁና ጥሪን ተቀብለው ዛሬ የካቲት 11/2018 ዓ.ም በምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክፍለ ጦርን መቀላቀላቸውን ዕዙ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አሳውቋል።
የየጎፍ ክ/ጦር አመራሮችም ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
+2
የምህረት አዋጁን የተቀበሉ የአገዛዙ ሀይል አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ
================
በቀን 11/06/2018 ዓ/ም! በመፈራረስ ላይ ያለው የብርሃኑ ሰራዊት መማረክ የአባታቸው፤ መፈራረስ የዕለት ከለት ተግባራቸው፤ ሕዝብ ማሰቃየት ተልኳቸው ከሆነው ሰራዊት መካከል የአብይ የውንብድና ስርዓት ገብቶናል ሕዝብ አናሰቃይም ከሕዝባችን ጉን ነን ያሉ ስማቸው ሰፈፈ መኮ፣ዘሪሁን ንጉሴ ፣ማሜ ቤቲ የተባሉ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ከአንጀኔ በመውጣት 99ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።የምህረት አዋጁን በመቀበላቸው በምህረት ተቀብለናቸዋል።ኑ እጃችንን ዘርግተን እንቀበላችኋለን!!!
# መረጃው የ99ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ነው።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 11/2018 ዓ.ም
ያልተነገረለት የአርበኛው አሰግድ ልጅ የማጀቴው ጀግና አቡሸ!!
በታሪካዊቷ ማጀቴ ሰማይ ስር፣ እንደ ንስር ዓይኑ የሰላ፣ እንደ እሳተ ጎመራው ዙ-23 ይዞ የሚያንቀጠቅጥ ጀግናው አቡሽ ጌታሁን በመደበኛ ወታደር ብቻ አልነበረም፤ የብረት አሞራውን (ዙ-23) አዝዞና አሳምኖ ሰማዩን የማጥራት ጥበብ የተቸረው፣ "እንደ ንስር ተወርዋሪ" ተብሎ የተገጠመለት የጦር አውድማ ፈርጥ ከአራት ዓመታት በፊት፣ የሀገር መፈራረስ አደጋ በአራቱም ማዕዘን ሲያንዣብብ፣ "ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው!" የሚለው ጥሪ ተቀብሎ እንደ ማንኛውም አማራ በቁጭት የተነሳው።
አቡሽ ጌታሁን "ሀገሬ ካልኖረች እኔ ማን ነኝ?" በሚል የሞት ሽረት ስሜት፣ ደሙንና አጥንቱን ለመስጠት ወደ ግንባር የተመመው ። በበረሃው ቃጠሎ፣ በዝናቡ ቁርና በጥይት እሩምታ ውስጥ ሳይበገር፣ በአረመኔው በብልፅግና መሪነት በሰሜኑ ጦርነት የተጀመረውን ዘመቻ የጀመረው። መስዋዕትነት ከፍሎ፣ ጓደኞቹን አጥቶ፣ ሀገር ጸናች ሲባል ግን ያልጠበቀው የታሪክ ምዕራፍ በሚወደውና በሚያከብርው የአማራ ህዝብ ላይ ተከፈተ።
የእነ ጌታቸውና ረዳና የአረመኔው አብይ አህመድ የሴራ የፕሪቶሪያው ስምምነት ተፈረመ። ትናንት "ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ነው" የተባሉ ወገኖች በሰላም ሲቀመጡ፣ በድንገት አፈሙዙ ወደ አማራ ክልል እንዲዞር ተደረገ። "በአማራ ግዛት ፅንፈኛ አለ!" የሚል መመሪያ ለሰራዊቱ ከመከላከያ ወረደ አቡሽ ትዕዛዝ አክባሪ ወታደር ነውና በጥያቄ ውስጥ ሆኖም ግዳጁን ሊወጣ ተንቀሳቀሰ።
ሆኖም ግን፣ ነገሩ ሁሉ "ፅንፈኛን ማደን" ሳይሆን "ወገንን ማጥፋት" ሆኖ አገኘው። አንድ ምሽት አቡሽ ቆም ብሎ አሰበ። "እኔ የማን ጠባቂ ነኝ? የማንስ አጥቂ?" የሚሉ ጥያቄዎች በህሊናው ተመላለሱ። የትናንቱ የሀገር አለኝታነት ስሜት ዛሬ ወደ ወገን ጥቃት ሲቀየር አየው። በዚያች ሰዓት ታሪካዊ ውሳኔውን ወሰነ።
የተካነበትንና ጠላት የሚፈራውን ያን ግዙፍ የዙ-23 አየር መቃወሚያ፣ ዳግመኛ በወገኑ ላይ እሳት እንዳይተፋ ሙሉ በሙሉ አበላሽቶ ከጥቅም ውጭ አደረገው። ከዚያም የቅርብ ወዳጁን AK-103 ክላሽንኮፍ ጠመንጃውን ብቻ አንግቦ፣ ከቆመለት አላማ ይልቅ ወደሚወደው ወገኑ ወደ አማራ ፋኖ አመራ።
ጥይት እንደ በረዶ በሚዘንብበት በዚያ አስፈሪ የጦር ሜዳ፣ የነፍስና የሥጋ ግብግብ በማድርግ በነሐሴ 2016 ዓ.ም በወሎ ምድር ላይ የጎፍ ክፍለ ጦርና እና የይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦሮች በአንድነት በወሰዱት የጣላት ታሪካዊ ውጊያ፣ እርሱ ግንባር ቀደም በመሆን የጠላትን ምሽግ በመስበር የድልን በር ከፍቷል።
ዳግም በታህሳስ 2017 ዓ.ም በካራ ለጎማ፣ አደሮና ጉባ አካባቢ ዳግመኛ ታሪክ ፃፈ። የሰባት ለሰባ እና ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር ተባብረው በከፈቱት በዚያ ብርቱ ውጊያ፣ አሁንም ጀግና በለመደው ወኔ ምሽግ በመስበር ድል ከአደርገ በኃ ላሀገሬና ወገኔ ካለ እኔ ምን አለኝ በሚል ስሜት አካልን እስከ መስጠት በሚደርስ የላቀ መስዋዕትነት የጀግንነት ታሪኩን በደሙ አትመ።
ዛሬ አቡሽ ጌታሁን በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናነቄ በደቡብ አማራ ቀጠና፣ አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር በስሩ በሚያስተዳድራቸው ክፍለ ጦሮች ውስጥ ከሆነው በአፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር ውስጥ የአንበሳ ድርሻ በመውሰድ ክፍለ ጦሩን እያስተዳደረ ይገኛል። ትናንት ለሀገር ሉዓላዊነት የቆመው አቡሽ ጌታነህ፣ ዛሬ ለወገኑ ህልውና ብርዱና ተራራው ሳይበግረው እየሰራ ይገኛል።
"የቆምኩት ለሀቅ፣ የታጠቅኩት ለፍትህ ነው!" ይለናል አቡሸ ይቀጥላል....!
የመከላከያ ዘመቻ መሪው እና ሁለት የአድማ ብተና ቲም መሪወች ፋኖን ተቀላቅለዋል!!
የካቲት11/2018ዓ.ም
የአፋብን'ን የምህረት አዋጅ የተቀበሉ የአድማ ብተና ቲም መሪዎችና የመከላከያ ዘመቻ መሪ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።
➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽➽
የአገዛዙን ስርዓታዊ መዋቅራዊ የሴራ አካሔድ ቀድሞውኑ የተረዱትና ሁኔታዎች ለመውጣት አስቻይ ሳይሆኑ መቆየታቸውንና የአፋብን'ን የምህረት አዋጅ መጠቀም የውሳኔኣቸው የመጨረሻ እንደሆና በተግባር ፋኖን መቀላቀል እንዳስደሰታቸው አስረድተዋል።
1.ሀብታሙ አዲስ ...የመከላከያ ዘመቻ 25ኛክ/ጦር
2. አማረ ሽታ....አድማ ብተና
3.ማማሩ መለሰ...አድማብተና
4.ገብሬ በሌ.....ሚሊሻዎች ከሞጣ እና መርጦለማሪያም ካምፕ በመውጣት ሁሉም ከእነ ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ 54ኛ ክ/ጦርን ፋኖን የተቀላቀሉ ሲሆንበክፍለጦሩ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋለ።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ቀን ፦ የካቲት 10/2018 ዓ.ም
🔊 አዲስ የስልጠና ጥሪ ‼️
የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የአማራ ፋኖ ወደ ትጥቅ ትግል ከገባ 33 ወራትን ያስቆጠረ መሆኑ ይታወቃል። እስካሁን ድረስ በነበረን ትንሽ የሰዉ ኃይል የአብይ አህመድን መንግስት ፍርስርሱን እንዳወጣነው የአደባባይ ሀቅ መሆኑን ወገን ቀርቶ ጣላት እንኳን ያውቀዋል። በመሆኑም ይህንን የፈራረሰ ስርዓት ግብዓተ መሬት በመፈፀም ህዝባዊ መንግስት በማቋቋም ሀገራችንን ኢትዮጵያን የቀደመ ክብሯን እና ገናነቷን አስጠብቆ ለማስቀጠል ተጨማሪ ኃይል ማሰልጠን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር አዲስ ምልምል ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጁቱን አጠናቆ እናንተን በመጠበቅ ላይ ይገኛል።
የመመልመያ መሰፈርት፦
👉 በአማራ ብሔርተኛነት የሚያምን እና የቀበሌ መታወቂያ ያለው
👉 ብሔር :- አማራ
👉 ዕድሜ ፦ ከ 18 ዓመት - 35 ዓመት
👉 የትምህርት ደረጃ ፦ ከ 5ኛ ክፍል በላይ
👉 ፆታ :- ወንድ / ሴት
👉 ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት
👉 በትክክል ማየት እና መስማት የሚችል
👉 ምንም አይነት ወንጀል የሌለበት በማህበረሰቡ ዘንድ በስነምግባሩ የተመሰከረለት
👉 ከዚህ በፊት በፋኖ ተቋም ውስጥ አባል ያልነበረ
👉 ከዚህ በፊት በየትኛውም ወታደራዊ ተቋም ውስጥ ( ፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ ልዩ ኃይል ፣ መከላከያ ፣ ፌደራል ፖሊስ ..... ) አባል ያልነበረ
👉 ከማንኛውም ደባል ሱስ ነፃ የሆነ ( የማያጨስ፣ የማይቅም፣ የማይስክር ...)
👉 ስልጠና ካጠናቀቀ በኋላ በሚመደብበት የትኛውም ቦታ ተንቀሳቅሶ ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ የሆነ
👉 ከጠላት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው
#NB:- የመመዝገቢያ ቀን እና ቦታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 21/ 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር /ንጉስ ተክለሃይማኖት ) ጊዜያዊ መንግስት አሰተዳደር ቢሮ ደብረ ዘይት ዘወትር በስራ ስዓት በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይቻላል።
#ማሳሰቢያ ፦ ይህ የመመዝገቢያ ቀን እና ሰዓት ከማለፋ በፊት አማራ የሆነ ወጣት በሙሉ የእድሉ ተጠቃሚ በመሆን በማይደበዝዝ በወርቅ ቀለም ታሪኩን መፃፍ አለበት።
ባዬ ሽፈራው አስረስ ቀኜ
#ፋኖ #viralreelschallenge2025viralreelschallengejaiviralreelschallengeviralreelschallenge #አፋብን_ቴዎድሮስ_ዕዝ #NB #Ethiopia #Amhara #fano
ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ
አድርሱልኝ!!
የሰው ልጅ የሞተባት ምድር
ኢትዮጵያ
ለሰላም፣ ለፍትህ እና ለሰብዓዊ መብት መከበር አርአያ ለሆናችሁት ሀገራት በሙሉ
በጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት በነበረችው ኢትዮጵያ፣ ዛሬ የሰው ልጅ ህግ ፈርሷል። አለም የደንቆሮዎች መናገሻ የሆነች ይመስል፣ ንጹሃን የአማራ ተወላጆች፣ ጋዜጠኞች እና ምሁራን በጅምላ የሞት ፍርድ እየተፈረደባቸው ነው። ህሊናቸው ለነፃነት የቆመ ድንቆች በእስር ቤት እየማቀቁ፣ ፍትህ የናፈቀው ህዝብ ድምፅ ሰሚ አጥቷል።
የሞት ፍርድን የናቃችሁ እና ለሰው ልጅ ክብር ዋጋ የምትሰጡ ሀገራት ሆይ! ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር "አማራ ሆኖ መገኘት" ብቻውን ለሞት እና ለእስራት ምክንያት እየሆነ ነው። አለም ዝምታዋን ሰብራ ለዚህ ህዝብ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የጅምላ ፍርዶች እንዲቆሙ እና የታሰሩ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ድምፅ እንድትሆኑ በሰው ልጅነት ስም እንማጸናለን። ፍትህ በሌለበት ሰላም የለም!
በዩኒቨርሲቲ የምትገኙ የአማራ ተማሪዎች
መማር ለመዳን እንጂ ለመጥፋት አይደለም!
በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙ የአማራ ልጆች ሆይ፤
ዛሬ እናንተ በክፍል ውስጥ የታሪክ እና የሳይንስ መጽሐፍትን ስታገላብጡ፣ በውጪ ግን የታሪክ ባለቤት የሆነው ወገናችሁ ከምድረ-ገፅ እየተሰረዘ ነው። መማር ለነፃነት፣ ለክብር እና ለህልውና ካልሆነ ትርጉሙ ምንድነው?
"ያለ ህዝብ መጽሐፍ፣ ያለ ሀገር እውቀት ባዶ ነው!"
ህግ በሌለበት፣ የሰው ልጅ መብት በማይከበርበት እና ወላጆቻችሁ በጅምላ የሞት ፍርድ በሚፈረድባቸው ወቅት፣ እናንተ ዝምታን መምረጣችሁ የነገውን መጥፋት እያፋጠነ ነው። መማር ለመዳን እንጂ እንዲህ አይነቱን ግፍ በዝምታ ለመመልከት አይደለም። ዛሬ እነ መስከረም አበራን እና ሌሎች የታሰሩ ወገኖቻችሁን ካላስፈታችሁ፣ ነገ እናንተንም የሚታደጋችሁ አይኖርም።
የአለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ (UDHR) አንቀጽ 3 "እያንዳንዱ ሰው በህይወት የመኖር፣ የነፃነት እና የደህንነት መብት አለው" ይላል። ይህ ህግ በወገናችሁ ላይ ሲጣስ ዝም ማለት፣ ለጥፋቱ ተባባሪ መሆን ነው። ከእንቅልፋችሁ ንቁ! የሰውነት ግዴታችሁን ተወጡ። ህልውና የሌለው ህዝብ ተምሮ ለምንም አይበቃምና ቅድሚያ ለህልውናችሁ ቁሙ!
በፈጣሪ እምልላችኋለሁ ይህን ስፅፍ ጉልበቱ ላይ ጥይት እንደተቀረቀረበት ፋኖ ከንፈሬን አጥብቄ ነክሼ ሳይሆን ልጇ እመጣለሁ በሎ እንደቀረባት እናት እንባዬን እያፈሰሰኩኝ ነዉ። (ሀገሬ ትመለሳለች ብዬ ቀረችብኝ)
አሌክስ/አዲስ ነኝ ከፈረሰዉ መንደሬ✍
የ44ኛ ክፍለ ጦር ለግዳጂ ዝግጁ መሆኑን አሳወቀ‼️
የአ.ፋ.ብ.ን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር የአጭር ጊዜ የስራ ስምሪት ሰጧል ።
አ.ፋ.ብ.ን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር የ 44ኛ ክፍለ ጦር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና አዉዳሚዉ የብልፅግና ሰራዊት ባለፉት ሁለት ወራት ወረራ በመፈፀም ንፁሃንን ሲገድል፣ ሲያፈናቅል፣ ሲረሽን በአማራ ህዝብ ላይ ዘርፈ ብዙ ጥቃት እየፈፀመ ቆይታል።
በመሆኑ ይሄን ሰው በላ ቡድን እስከወዲያኛው በማስወገድ የማህበረሰቡ እረፍት ለመስጠት የቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች፣105ኛ ኮር አመራሮች እና የ 44ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች በተገኙበት ጥልቅ ዉይይት በማድረግ የነበሩትን አንዳንድ ችግሮች በመፍታት ለቀጣይ ስራዎች ዝግጁቱን አጠናቆ ከዛሬ 10/6/2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ተገብቷል።
105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር በኮሩ አጀረጃጅት ዙሪያ የነበሩ አንዳንድ ጉዳዮችን ለተከታታይ ቀናት በተደረገ ዉይይት ሁሉንም ባግባባ መልኩ እልባት ተሰጦበት ወደ ነበረበት ልዕልልና እና ጀብጀኝነት ተመልሶ የጠላትን ቅስም በአጭር ጊዜ ለመስበር በታላቅ ቁጭት እና ተነሳሽነት ወደ ስራ ገብቷል ሲል 105ኛ ኮር የ44ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ዘግቧል።
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳስብ፣ አዲስ ተስፋ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የጠላት ዙ-23 አደጋ ደረሰበት!!
በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር፣ አለፋ ወረዳ፣ ሻዉራ ከተማ ለቆ የወጣዉ የፋሽስቱ ዐብይ አህመድ ሰራዊት፣ ወደ አጎራባች ወረዳ፣ ደልጊን አድርጎ፣ ጎንደር ሊገባ የነበረዉ ፣ ጎይን አልፎ ፣ ድኩልአርባ ሊደርስ ሲል ፣ ዙ23ት የጫነው መኪና ተገልብጦ ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል ።
በተገለበጠው ዙ-23 የጠመደ ኦራል ተሳፍረው የነበሩ ከ10 በላይ ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ በተሽከርካሪውና በጦር መሳሪያው ላይ ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧል።
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
ሁለት የአድማብተና አባላት አራት መሣሪያ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ‼️‼️
የካቲት 10/2018 ዓ/ም የምህርት አዋጁን የተቀበሉ የአገዛዙ የአድማ ብተና አባላት 105ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ከአገዛዙ ጋር በመወገን ወገናቸውን ለሚወጉ የተለያዩ አባላት ማለትም አድማ ብተና፣ሚሊሻ፣ፓሊስ፣ መከላከያና ማንኛውም የብልጽግና አደረጃጀት ውስጥ ለሚያገለግሉ አባላት የምህረት አዋጂ ማውጣቱ ይታወቃል።
ስለሆነም፦
1ኛ.ፈንታሁን ውቤ
2ኛ. ምስጋናው ዳኘ የተባሉ የአድማ ብተና አባላት እያንዳንዳቸው ከያዙት ሙሉ ትጥቅ በተጨማሪ ሌላ ትጥቅ ደርበው በመያዝ፣ ከዳግላ ወረዳ ማከል አካባቢ ከመሸገው የጠላት ሀይል በመውጣት የ105ኛ ኮር ኮማድ ዩኒትን ተቀላቅለዋል።
ስሩ የተቆረጠው አገዛዝ አባላቱን ከ9ኛ ክፍል አፍሶ በግዴታ ወደብር ሸለቆ ማሠልጠኛ ማዕከል እንደወሳዳቸውና ለ3ወር ስልጠና እንደወሰዱ ገልጸው፣ የተሠጠን ተልኮ የአማራን ህዝብ መግደልና ማቆሳቆል መሆኑን ሲነገረንና ሲገባን ፣አማራን አማራ አይገድለውም ብለን ወደ ወንድሞቻችን ተቀላቅለናል ብለዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
ትናትና በሁሉት ዕዞች በአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ እና በደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በጋ በጥምርትበወረኢሉ ከተማና በዙሪያዋ በተደረገ ውጊያ የጦር መኮነኖችን ጨምሮ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ተገደሉ!
በውጊያው ከተገደሉት በተጨማሪ በርካቶች ቆስለው በአንቡላንስና በወታደራዊ ካሶኒ ተጭነው ለሕክምና ወደ ደሴ ከተማ ተወስደዋል።
ለተከታታይ 8:00 ሰዓታት በዘለቀው አውደ ውጊያ፡ የአገዛዙ ኃይል ከወደ ፋኖ የተከፈተበትን ጥቃት ለመመከት ከአየር መቃዎሚያ ጀምሮ ሞርተርና ሌሎች ከባባድ መሣሪያዎችን የተጠቀመ ቢሆንም፡ ነገር ግን የፋኖን ክንድ መቋቋም አቅቶት ከባድ የሆነ ሰብአዊ፣ ቁሳዊና ሞራላዊ ኪሳራ መከናነቡን ለማረጋገጥ ችለዋል።
#ፋኖ_እየጠነከረ_መሆኑ ብልፅግና እንዲመሰክርልን አንጠብቅም❗️ ፋኖ ከ Gurella Fighting ወጥቶ ወደ Conventional Fighting መግባቱና ከተሞች መቆጣጠር መጀመሩ እንደጠነከረ ትልቅ ማሳያ ነው። #በርቱ💪
