179
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-630 days
Data loading in progress...
Similar Channels
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
September '26
September '260
in 0 channels
August '260
in 0 channels
Get PRO
July '260
in 0 channels
Get PRO
June '260
in 0 channels
Get PRO
May '26
+4
in 0 channels
Get PRO
April '26
+1
in 0 channels
Get PRO
March '260
in 0 channels
Get PRO
February '26
+9
in 0 channels
Get PRO
January '26
+7
in 0 channels
Get PRO
December '25
+3
in 0 channels
Get PRO
November '25
+3
in 0 channels
Get PRO
October '25
+3
in 0 channels
Get PRO
September '25
+11
in 1 channels
Get PRO
August '25
+13
in 0 channels
Get PRO
July '25
+4
in 0 channels
Get PRO
June '25
+12
in 0 channels
Get PRO
May '25
+5
in 0 channels
Get PRO
April '250
in 0 channels
Get PRO
March '250
in 0 channels
Get PRO
February '250
in 0 channels
Get PRO
January '25
+208
in 0 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 09 September | 0 | |||
| 08 September | 0 | |||
| 07 September | 0 | |||
| 06 September | 0 | |||
| 05 September | 0 | |||
| 04 September | 0 | |||
| 03 September | 0 | |||
| 02 September | 0 | |||
| 01 September | 0 |
Channel Posts
ውብ ሕይወት ለአንተ/ለአንቺ ምንድን ነው?
ብዙዎቻችን "ውብ ሕይወት" ሲባል ሀብት፣ ዝና ወይም ፍጹምነት ብቻ ይመስለናል። ነገር ግን እውነተኛ ውብ ሕይወት የሚጀምረው ከውስጥ ሰላም ነው።
ውብ ሕይወት ማለት፡
ከራስ ጋር ሰላም መሆን፦ ድክመትን አምኖ መቀበል፣ ጥንካሬን ማወቅ እና በየቀኑ በትንሹም ቢሆን የተሻለ ሰው ለመሆን መጣር።
በእውነተኛ ግንኙነቶች መከበብ፦ ከቅን እና ከሚያስቡልን ሰዎች ጋር አብሮ ማደግና መተሳሰብ።
የህይወት አላማን መኖር፦ ትንንሽ ነገሮች እንኳን ቢሆኑ በደስታና በምክንያት ማድረግ።
ምስጋና፦ ባለን ነገር መርካትና ሁልጊዜም ለተሰጠን አዲስ ቀንና እድል ማመስገን።
ውብ ሕይወት ከውጭ የምንፈልገው ሳይሆን፣ በውስጣችን የምንገነባውና የምንኖረው እውነታ ነው!
ላንተ/ላንቺስ ውብ ሕይወት ማለት ምን ማለት ነው? ✍️
| 2 | የፍርድ ቀን
በህልሜ ደሞ ይህንን አያለሁ። የአለም መጨረሻ ይመስለኛል። የፍርድ ቀን ነው። ፊት ለፊት ፈራጅ አለ። በጐን በኩል የተደረደሩ ለቁጥር የሚያታክቱ ብዙ የተጐሳቆሉ ሰዎች (The Grand Jury) አሉ። ለፍርድ የቀረብን የተወሰንን ሰዎች አለን።
ጥያቄው ይቀርባል...
"ስራብ አብልታችሁኛል? ስጠማ አጠጥታችሁኛል? ስታረዝ አልብሳችሁኛል?"
መጀመሪያ ፥ ጥያቄው ለመ'መለስ የቀረበ አልመሰለኝም ነበር። Rhetorical ጥያቄ አይነት መንፈስ ያለው መስሎኛል። ነገር ግን የሚመልስ ያስፈልግ ነበር። በእርግጥ ሁሉም ሰው መመለስ አልነበረበትም። ለፍርድ ከቆምነው ጥቂት ሰዎች መሃል (ምናልባት አስር እንሆናለን) የሚኮነን አንድ ሰው ነው። ከየምድቡ የሚኮነን ያ አንድ ሰው ግን ፥ "አቤት!" ማለት ነበረበት። ልክ እንደ ጥሎ ማለፍ አይነት ነገር ነበር።
"ስራብ አብልታችሁኛል? ስጠማ አጠጥታችሁኛል? ስታረዝ አልብሳችሁኛል?"
ወደ ተራቡት፣ ወደ ተጠሙት፣ ወደ ታረዙት አየሁ። እጅግ በጣም ብዙዎቹን አውቃቸዋለሁ። ያበላኋቸው፣ ያጠጣኋቸው፣ ያለበስኳቸው ናቸው። የአብዛኞቹ ፊት በፈገግታና በ'አለን እንመሰክራለን!' አበረታችነት ተቀበለኝ። ከእነሱ መሃል ፥ ስሜን እየጠሩ የእኔን ፃድቅነት የሚናገሩ እሰማለሁ። በአጭሩ ፥ በሜዳዬ እንደምጫወት አይነት ቲፎዞ ነበረኝ። ነገር ግን አሁንም ምንም እየተፈጠረ አልነበረም። በፍርድ ሕጉ መሰረት ፥ እራሱን አሳልፎ የሚሰጠው ፥ ባለ ፀፀት ሰው ይጠበቃል።
ዘወር ዘወር ብዬ ፥ ፍርድ ጠባቂዎቹን የኔን ቢጤዎች አየሁ። በፍፁም ፀጥታና መረጋጋት ቆመዋል። ማንም ምንም ቃል አያወጣም። ሰዓት ይሄዳል... አንድ ሰው ያስፈልጋል።
እንደገና አይኖቼ ወደ ግራንድ ጁሪው ሄዱ። ጥቂት የማላውቃቸውን እየመረጥኩ መመልከት ጀመርኩ። በመጀመሪያ ፥ በ'ምስክሮቼ' መሃል ጣል.. ጣል.. ብለው ፥ አልፈው አልፈው ነበሩ። ቀስ በቀስ ግን እየበዙብኝ መጡ። እየበዙ... እየበዙ... እኔም እየተጨነቅኩ እየተጠበብኩ መጣሁ። ልቤ ሲመታ፣ ሲደለቅ፣ ሲደባለቅ... ላቤ ሲወጣ፣ ሲንኳለል፣ ሲጐርፍ... ይታወቀኛል።
ፌሎው ፍርደኞችን አያቸዋለሁ። ዝም እንዳሉ።
ጨነቀኝ። ጥፋተኛው ሰው ፥ እኔ እንደሆንኩ ገባኝ። ሰዓት እየሄደ ነው...
ጉምጉምታ አለ። ፀጥታ አለ። ጩኸት አለ። መልሶ ዝምታ አለ። ቀጥሎ የኔ ለቅሶ ሆነ። አለቀስኩ...
ኃጥያተኛው መሆኔን እያለቀስኩ ተናገርኩ። "ስትራብ አለበላሁም እኔ። ስትጠማ አላጠጣሁም እኔ። ስትታረዝ አላለበስኩም እኔ።" እያልኩ ጭንቅላቴን ይዤ ጮህኩ። ይሄ ሲሆን ፥ ግራንድ ጁሪው በጠቅላላ ፥ የማውቃቸውም የማላውቃቸው ተቆጡ። ተቃወሙ። "እሱ አይደለም። እሱ አይደለም።" አሉ።
ጣቶቻቸውን በሙሉ ፥ አብረውኝ ወደቆሙት ጠቆሙ። "እሱን እናውቀዋለን። እነሱን አናውቅም። እሱን እናውቀዋለን። እነሱን አናውቅም። እሱን እናውቀዋለን። እነሱን አናውቅም።" የሚል ፥ እኩል የሚነበነብ አስፈሪ የህዝብ ድምፅ ያወጣሉ።
"የፍርድ ሕጉን ታውቃላችሁ። እንደዚህ አይነት አሰራር የለም። ፀጥታ ይሁን።" የሚል ድምፅ ተሰማ። ፀጥታም ሆነ።
እኔም ተለይቼ ስወሰድ ፥ ከጐኔ የነበሩትን አንዴ አየኋቸው። የሳቁብኝ መሰለኝ። "ምናባቱ ዝም አይልም?" "ይበለው" ምናምን የሚሉ ሀበሻዊ ንግግሮች ሰማሁ። እነዚህም በሙሉ ወደ ገነት ሲሄዱ ፥ እኔ የሲዖሉን መንገድ ጀመርኩ።
መንገድ ላይ ምን እንደሚገጥመን አይታወቅም ብዬ ተፅናናሁ። አሁንም የሳቁብኝ መሰለኝ። | 40 |
| 3 | ለውጥ ያስፈልግሀል!
አንድ ነገር ህይወትህ ላይ እየደጋገመ ከተፈጠረ እንድትወስድ የተፈለገ ለውጥ አለ ማለት ነው፤ ልብስህ አንዴ ወይ ሁለቴ ቢቀደድ ልታሰፋው ትችላለህ፤ መቀደዱ ከበዛ ግን ደግመህ አትለብሰውም፤ ትቀይረዋለህ።
በኑሮህ፣ በስራህ፣ በትምህርትህ ወይ ከሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት በተደጋጋሚ ደስተኛ ካልሆንክ ችግሩ ከነሱ አይደለም፤ ካንተ ነው። በተረጋጋ መንፈስ ህይወትህ ላይ ምን መቀየር እንደምትፈልግ አስብና ወስን፤ አንድ ውሳኔ እስከመጨረሻው ታሪክህን ሊቀይር ይችላል! | 41 |
| 4 | ለጥያቄዎቻችሁ መልስ ቁጥር 4
ጥያቄ፦
"ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ወሲብ መጥፎ ከሆነ፣ ታዲያ ለምን በጣም ደስ የሚል ጥሩ ስሜት ይሰጣል?"
መልስ፦
አንድ ድርጊት የሚያስገኘው ሥጋዊ ደስታ ወይም ጥሩ ስሜት ብቻውን የድርጊቱን ትክክለኛነትና ሥነ-ምግባራዊነት ሊወስን አይችልም።
1. ስሜትና ሥነ-ምግባር የተለያዩ ናቸው
የስሜት ደስታ መልካምነትን አይገልጽም፦ አስገድዶ ደፋሪዎች ወይም ሕፃናትን የሚያንገላቱ አካላት ከድርጊታቸው ሥጋዊ ደስታን ያገኙ ይሆናል፤ ነገር ግን ድርጊታቸው እጅግ አሰቃቂና ኃጢአት መሆኑን ማንም አይጠራጠርም።
ሕመም ሁልጊዜ መጥፎ አይደለም፦ በአንጻሩ፣ አንድ ሰው ለሌላው ሲል ሕይወቱን አሳልፎ ሲሰጥ ከፍተኛ ሥቃይና ሕመም ይደርስበታል። ነገር ግን ይህ ድርጊት ትልቅ የእውነተኛ ፍቅርና የመሥዋዕትነት ማሳያ ነው።
በደስታ ብንመዝን ኖሮ፦ የአንድን ድርጊት መልካምነት የምንመዝነው በሚገኘው ደስታ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ አመንዝሮች "ደስታ ስላገኙ" ጻድቃን፤ ለአገራቸውና ለወገናቸው ሲሉ መከራ የተቀበሉ የጦር ጀግኖች ደግሞ "ሕመም ስለቀመሱ" ክፉዎች በተባሉ ነበር።
2. የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ
የአንድን ድርጊት ትክክለኛነትና ሥነ-ምግባራዊነት ለማወቅ ከፈለግን፣ የዚህን ዓለም ጊዜያዊ ፈቃድና ሥጋዊ ደስታ መከተል የለብንም።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ እንዲህ ሲል ያመላክተናል፦
"መልካሙና ደስ የሚያሰኘው ፍጹምም የሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ" (ሮሜ 12:2)።
በአጠቃላይ፣ ወሲብ በራሱ እግዚአብሔር ለተቀደሰ ትዳር የሰጠው ስጦታ በመሆኑ ጥሩ ስሜት መስጠቱ ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን ጥሩ ስሜት ስላለው ብቻ ከጋብቻ በፊት ሲደረግ ትክክል ይሆናል ማለት አይደለም። ድርጊታችን እውነተኛና መልካም የሚሆነው በእግዚአብሔር ሕግና ፈቃድ ወሰን ውስጥ ሲሆን ብቻ ነው። | 47 |
| 5 | አንቺን በማጣት የጥያቄ ቅድ የተዘለቀ
በጥያቄዎች ወዲና ወዲያ ተንቦረቀቀ
አንቺን ለማሰብ እግሬና እግሬ በተጣመረ
ድፍኑ መልሴ ወደ ብዙ ሀቅ ተመነዘረ
ተፈላሰፍኩኝ ተራቀቁበት ማሰብን ደርሶ
ሀሳቤ ሄደ የተሰመረ ድንበሩን ጥሶ
በመታዘብ ቤት የትየለሌ ቁብም ቆጠርኩኝ
ግዳም ሰው ልሆን ከቶ ግድ የለሽ እንዳልነበርኩኝ
ውሻ መውደድሽ በቀደዱው ልብ ብዙ ገባበት
አውላ ቤት ቀረ ቀዳዳው ሰርኩን እየሰፋበት
የመኖሮችን እያንዳንዱን ፈርጅ ይጠረጥራል
የህይወት መልክን ሙጃና ስንዴ ይመነጥራል
ያንቺን ለማሰብ ቁጭ ባለበት
አለም ጠፋበት
ያንቺም ጠፋበት | 32 |
| 6 | የሰው ልጅ በተፈጥሮው ራስ ወዳድ ነው፤በዚህ ምክንያት የራሱን ጥቅም ለማስከበር ሲል አንተን እንደ መሰላል ሊጠቀምብህ ይችላል።አብዛኛዎቹ ሰዎች ይህን መራራ እውነታ ካለመረዳታቸው የተነሳ ሁልጊዜ በሰዎች ጥቅመኝነት እየተሰበሩ ይኖራሉ።በዚህ ጊዜ ዓለም የምታከብረው ጠቃሚ እቃን እንጂ መልካም ሰውን አይደለም።ስለዚህ የራስህን ጥቅም ለማስከበር የዋህነትህን ልክ እንደ ሰዎቹ ተፈጥሮ ተለዋዋጭ አድርገው።ይሄ ማለት ደግ መሆን ባለብህ ጊዜ ደግ ሁን፤መጥፎ መሆን ባለብህ ጊዜም መጥፎ ሁን! | 35 |
| 7 | SkillMoney
Complete tasks and manage your rewards.
https://t.me/SkillMoney01_bot/earn?startapp=ref_E6F0F23A | 34 |
| 8 | መጥፎ ልማዶችን ማቆም ከባድ የሚሆንበት አንድ ትልቅ ሳይንሳዊ ምክንያት አለ። አብዛኛዎቹ መጥፎ ልማዶች ለምሳሌ ማጨስ፣ junk food መብላት፣ ሶሻል ሚዲያ ላይ ጊዜ ማጥፋት ድርጊቱን በፈፀምክ ቅፅበት ፈጣን እርካታ ይሰጡሃል። የሚያስከትሉት የጤና እና የህይወት ምስቅልቅል የሚመጣው ከወራት ወይም ከአመታት በኋላ ነው። እርካታው ዛሬ ነው፣ ቅጣቱ ግን ነገ ነው።
በተቃራኒው፣ ጥሩ ልማዶች፦ለምሳሌ ስፖርት መስራት፣ ማንበብ፣ ገንዘብ መቆጠብ ድርጊቱን በምትፈፅምበት ሰዓት ድካም እና ህመም አላቸው። ትርፋቸውን እና ደስታቸውን የምታገኘው ግን ከጊዜ በኋላ ነው። ቅጣቱ ዛሬ ነው፣ እርካታው ግን ነገ ነው። የሰው ልጅ አእምሮ ደግሞ የተሰራው የነገን ትርፍ ትቶ፣ የዛሬን ፈጣን እርካታ እንዲመርጥ ሆኖ ነው።
ስለዚህ መጥፎ ልማድን ለማሸነፍ የህይወት ህግን መቀበል አለብህ። ዛሬ ላይ ቀላል የሆኑ እና ፈጣን እርካታ የሚሰጡህን መጥፎ ልማዶች ከመረጥክ፣ የነገው ህይወትህ እጅግ ከባድ እና በፀፀት የተሞላ ይሆናል። ዛሬ ላይ ከባድ የሆኑትን ጥሩ ልማዶች በመምረጥ ህመሙን ከታገስክ ግን፣ የነገው ህይወትህ እጅግ ቀላል ይሆናል። ምርጫው ያንተው ነው! | 41 |
| 9 | some of you lot piss me off and have me laughing in disbelief in the same breath. አድናቆት or compliment እራሳቸውን ችለው መቆም የሚችሉ ለምን እንደማይመስላችሁ አላውቅም፣ የግድ የሆነች ሰንካላ criticism አብራ ካልታዘለች ያዞራችሗል ልማኦ።
i’ve observed this on TikTok for a while, especially on women creators. whether they’re painting, singing or playing an instrument. ወንዶችም ሆነው ትንሽ ልጅ ቢጤ ከመሰሉ እና እንደሚያውቅ ሰው ብታብጠለጥሏቸው ምንም እንደማያመጡ እርግጠኛ ስትሆኑ።
በሰላም ሀገር comment section ስር የሚደበሩ አንድ ሰውዬ ወይ ሴትዮ አይጠፉም
“እ ስዕሉ እኮ ቆንጆ ነበር ኮንሴፕቱ ጥሩ ሆኖ ሳለ፣ ትንሽ ካንቫሷ ተጣመመችብሽ፣ የሆነች ቀለም ቦርጨቅ ብላብሻለች እንጂ ጎበዝ ነሽ፣ በርቺ”
“ድምፅሽ ዋው! ግን ሀይ ፒች ሆነብሽ (it’s always high pitch lmao) እ መሀል ላይ ያወጣሻት ድምፅ አበላሸቸው እንጂ አቅም አለሽ፣ በርቺ”
see how insufferable that sounds?
criticism is necessary, but only if you have the expertise to do so or you’ve spent a long time on the subject you’re criticising.
the expertise ያለው ሰው criticise ሲያደርግ ያምርበታል፣ heartfelt and authentic advice እንደሆነ ያስታውቃል፣ a whole bunch of nonsense ስትሉም ያስታውቃል።
ካደነቃችሁ ዝምብላችሁ አድንቁ፣ አለበለዚያ አታስቁኝ። | 54 |
| 10 | መጀመሪያ ስለ ፖለቲካ ለማወቅ ለመጠየቅ ትንሽም interested የሆንኩት የመጀመሪያው የትግራይ ጦርነት ጊዜ ነበር። እድሜ ለ ትዊተር፣ በጣም ብዙ ሰው ይንገበገባል፣ ብዙ የሚፅፉት፣ የሚሟገቱት ነበራቸው። I remember feeling like an imposter among them, because I had no idea what was going on and as embarrassing as this is, I didn’t care. Because you know? As long as it’s not me or those who I care about it’s really not that important. እነ ማሚ የሚያውቋቸው ሰዎች ጋር ስልክ ሲደውሉ አይሰራም፣ የማውቃቸው የጊቢ ተማሪዎች ተጠሩ። ትንሽ ፐርሰናል ሆነ አይደል? ትንሽ አስብ ትንሽ እጨነቅ ትንሽ እፀልይ ጀመር።
ሰከንድ ይር ተማሪ ሆነን ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተበትነው ወደእኛ ጊቢ የመጡ ተማሪዎች ነበሩ፣ አኗኗሪ ነበሩ፣ ጥድፍ ጥድፍ ብሎ ሁሉም ነገር አልቆባቸው መቼ መጥተው መቼ እንደሄዱም አላስታውስም፣ ያሳዝኑኛል። ቀርቤ ባወራቸው እና ባይናቸው ያዩትን፣ the reality they lived ባወቅሁ ኖሮ ብዬ ይቆጨኛል።
አራተኛ አመት ደግሞ አማራ ክልልም ጦርነት ደረሰ፣ ሰለኖርኩበት ጓደኞች ስላሉኝ አንጀቴ ጋር የሚሰማኝ ህመም ነበር። 7 ወር ቁጭ ብለን ስንመለስ ብዙ PTSD የነበረባቸው ልጆች ነበሩ፣ ትንሽ ድምፅ trigger የሚያደርጋቸው። አብዛኞቹ were desensitised, አንድ እሁድ ማታ ግቢያችን ውስጥ የሚገርም ተኩስ ተከፍቶ እኛ በዳዴ ሮጠን ስንደበቅ ለሰከንድ ያልደነገጡ፣ እኛኑ አይዟችሁ ያሉን። ጦርነት እና ሰላም ማጣት እንዴት መልክ እንደሚቀይር፣ እንደሚያሳቅቅ፣ እንዴት የከተማ አየር እና ሽታ እንደሚቀይር፣ እንዴት helpless እንደሚያደርግ በጣም በትንሹ አይቻለሁ፣ ሰምቻለሁ።
የትግራይን እናቶች እያየሁ አይኔ በለቅሶ ብዛት ሊፈነዳ፣ ስንት እና ስንት ልጅ፣ ባል፣ ወዳጅ፣ ዘመድ ከቀበሩ በሗላ፣ ስንት inexplicable horror ካሳለፉ ከተተለተሉ በሗላ የትኛው አይዟችሁ እንደሚጠግናቸው አላውቅም፣ መጠገኑ ቀርቶ ሌላ ሊጨመርባቸው። I couldn’t imagine living in their reality for a minute እንጃ እኔ እንዴት መሽቶ እንደሚነጋላቸው። አንጀት ሲበሉ በየኮመንት ሴክሽን ስር ያሉት ወጣቶች፣ እኔ አላውቅም ብቻ።
ከየት እንደምጀምር፣ ለየትኛው እና እንዴት እንደሚፀለይም አላውቅበት ለዚህ የጉድ ሀገር። | 55 |
| 11 | whenever i go shopping, it’s the faces i see.
is you patient enough to handle my indecisiveness? or are you gonna stand over there and መገላመጥ me like you’re the one paying?
የእንጀራ ጉዳይ ሆኖ እንጂ most of the people working in customer service are not supposed to be working there. ሲሆን ሲሆን according to their personality they don’t even like interacting with people. ያሳዝኑኛል ሲመናቀሩ and i try to laugh it off. their lack of common decency is not justifiable but some part of me believes they’d be good at their jobs if they were working in a field they liked.
i don’t believe in working a job that i don’t like or one i wouldn’t grow into enjoying, i’m actually so serious about this.
”የት ነው የምትኖሪው Deborah?🙂” እንዳትሉኝ።
i’m very well aware of the reality most people live in and i have this opinion because i’m probably privileged enough to have it.
life is taxing enough as it is let alone finding yourself day in and day out in an environment that you hate.
ቢሆንልን i wish for people to earn a living from the things they love and care about, ህልም አይከለከል። | 55 |
| 12 | It took me years of wandering through oceans of friendships and connections to realise that my belief in me being unlovable came from the exposure to people who were not kind, people who projected so much of their insecurities and anger towards me and not because I was cursed.
Learning to accept that I’m lovable, people enjoy my company and look forward to our conversations has been the most bittersweet experience I’ve had. I had to unlearn the pattern of always looking for that hint of disgust, jealousy and competitiveness in the eyes of people.
I’m grateful to have learned that there are days where I have been the problem but that’s not always the case. For I write this from a place of knowing whatever unkindness, negativity and spite thrown at me has nothing to do with who I am as a human being. And I will not make the mistake of believing it determines how I speak and think about myself again. This statement stays even if you someday find yourself to be the problem too. | 33 |
| 13 | ሁለት ልጆች እየሮጡ መጡ። ስድስት አመታቸው ነው። አንደኛዋ ለመክሰስ አንደኛዋ ራሷን ለመከላከል ቸኩለዋል። በቅድሚያ ክሱን ሰማሁ። እንደኔ "ሚስተር" የሆነን ሌላ ሰውዬ ሲይዛትና ሲያቅፋት እንቢ ብላ 'Disrespect' ብጤ አሳይታ እንደመጣች ነገረችኝ። ቶሎ ተካሳሽ ቀበል አድርጋ አጥብቆ ይዟት እንደሆነ የመከላከያ ሀሳብ አነሳች። ከሳሽም ሆነ ተከሳሽ የምላቸውን በጉጉት ጠብቀዋል። ባለ ስልጣን ሚፈልገውን ያለ ጥያቄ በማድረግ "Good Girl" ሽልማቷን ማግኘት የለመደችው ከሳሽም፤ ያደረገችው ትክክል እንደሆነ የምታውቀው ነገር ግን እንደ ጥፋት የተቃጠረባት ተከሳሽም ጽድቋን ለመስማት ተጨንቃለች።
ከሳሽ ውስጥ የሆነች Trad Wife አየሁ። ገዢውን ስርአት በማስደሰት የሴትነት ጥበብ ምሳሌ ተደርጋ መታየትና ስርአቱ የሚያቀርበውን ጥቅማ ጥቅም ለመቋደስ የተንሰፈሰፈች። ተከሳሽ ጋር ጥሩ ተስፋ አየሁ። ራሷንና ፍላጎቷን፣ ትክክልና ስህተትን ታውቃለች። ድንበሯን ታሰምራለች። ድምጿንም ታሰማለች። እህቶቿን Under the Bus የምትወረውር ሴት ቅድምያ ራሷን የጣለች ናት። ይቺ ልጅ ጥሩ መስመር ላይ ናት። የወላጅ አያያዝ ልዩነት አየሁባቸው። አንደኛዋ ታላቆቿን ለማስደሰት፣ ራሷን ለመርሳት፣ "ለምን" ሳትል ለመገዛት ሕይወት Condition እየተደረገች ነው። ሌላኛዋ "ለምን" ብላ ስትጠይቅ ተገቢ መልስ እየተሰጣት ውሳኔዋና ምቾቷም እየተከበረላት Parent እየተደረገች ነው። እኔ የማደርገው አንድ ተግባር ፋይዳው ኢምንት ቢሆንም በሚጠቅማት እንጂ በሚሰብራት አቅጣጫ መሆን የለበትም።
ያ Creepy ሰውዬ ትልቅ ሆነም አልሆነም ካልተመቻት እንኳን ጨምቆ አቅፏት፣ እጇን ብቻ ቢይዝ ራሱ እንቢ የማለት ሙሉ መብት እንዳላት ገለጽኩ። "ግንኮ "ሚስተር" ነው" አለችኝ። "ይሁን" አልኳት። | 72 |
| 14 | It took me years of wandering through oceans of friendships and connections to realise that my belief in me being unlovable came from the exposure to people who were not kind, people who projected so much of their insecurities and anger towards me and not because I was cursed.
Learning to accept that I’m lovable, people enjoy my company and look forward to our conversations has been the most bittersweet experience I’ve had. I had to unlearn the pattern of always looking for that hint of disgust, jealousy and competitiveness in the eyes of people.
I’m grateful to have learned that there are days where I have been the problem but that’s not always the case. For I write this from a place of knowing whatever unkindness, negativity and spite thrown at me has nothing to do with who I am as a human being. And I will not make the mistake of believing it determines how I speak and think about myself again. This statement stays even if you someday find yourself to be the problem too. | 62 |
| 15 | ራስን ማሳደግ በቀጣይ ሕይወትህን ለማሻሻል እጅግ አስፈላጊ ነው።
ከታች ቀላል የሆኑ ነገር ግን ለውጥ የሚያመጡ መንገዶች፦
1. ግብ አዘጋጅ
የምትፈልገውን ግብ ግልጽ አድርግ
የአጭር ጊዜ እና የረጅም ጊዜ ግቦችን አስቀምጥ
2. ንባብን ልማድ አድርግ
በየቀኑ ቢያንስ 10-20 ደቂቃ አንብብ
👉 ርዕሶች: ስነ-ልቦና, ስኬት, መንፈሳዊ
3. አዎንታዊ አስተሳሰብ ያዝ
“እችላለሁ” በል በራስህ ተማመን
4. የጊዜ አጠቃቀምን ተማር
አስፈላጊ ነገሮችን አስቀድመህ አድርግ
👉 To-do list ይጠቀሙ
👉not to-do list ይጠቀሙ
5. ጤናህን ጠብቅ
እንቅስቃሴ: ጤናማ ምግብ: በቂ እንቅልፍ
6. አዲስ ነገር ሁልጊዜ ተማር
ችሎታ (skills) አሳድግ
👉 ምሳሌ: ኮምፒውተር, ቋንቋ, ቴክኖሎጂ
7. መንፈሳዊ እድገት
ጸሎት
ማሰብ (meditation)
8. ከአዎንታዊ ሰዎች ጋር ጊዜ ይኑርህ
9. ራስህን ገምግም
የዕለት ግምገማ አድርግ
👉 “ዛሬ ምን ተማርኩ?”
10. ትዕግሥት ይኑርህ
ራስን ማሳደግ ጊዜ ይወስዳል
በቀጣይነት ነገሮችን መከወን
👍ትንሽ ትንሽ እያደግክ ትልቅ ሰው ትሆናለህ! | 95 |
| 16 | Pretty hurts
ብድግ ብዬ እንደነገሩ አስይዤው የምሄደው ፀጉር፣ ቆንጆ የምለው ፊት እስኪመጣልኝ መዘጋጀት ባይኖርብኝ፣ መጥቶልኝም እስካምነው ድረስ መስታወት ፊት ባልሻጥ፣ ስንት እድሜ አተርፍ ነበር?
ከተማ መወለድ ለብዙ ነገር ትርፋማ ቢያደርግም፣ ለመልክ ግን ገበያ ነው። ምን አይነ ግቡ ብንሆን የሚያወዳድሩብን በጣም የምታምር ደግሞ ሌላ አለች፣ እንደሷ ማማር ትችያለሽ የሚል ገንዘብ የሚያስበዘብዝ ማስታወቂያ በየስክሮሉ አለ።
ቆንጆ መባል ጎበዝ ከመባል እስኪበልጥብን፣ ሳናምር መውጣት ጠልተን መገኘት ከአለብን ቦታዎች እስክንቀር? ገና እግራችን ሲያደከድክ፣ ከወፌ ቆመች ቀጥሎ ስለመልካችን አስተያየት አልሰማንም ወይ? “አፍንጫዋ ነው እንጂ፣ ጆሮዋ ባይተልቅ፣ ፀጉሯስ ሶስት ፍሬ ናት፣ ሴት ስትቀላ ነው እንጂ፣ ተረከዟ ምን ያክላል?” እየተባልን ቅንጥ ቅንጣችንን ተብለን እሳት እንደነካው ላስቲክ ያልተሰበሰብን አምስት እንሞላለን ወይ?
አሁን ላይ “ግን እኮ ቆንጆ ነሽ ለምን እንዲህ ይሰማሻል?” የሚልን አስተያየት ለመስማት ጆሯችን እንደሚያመነታ፣ አይናችን መስታወት ላይ ያለ ምስላችንን ለማመን እድሜውን ደርድሮ በቦውሊንግ ኳስ እንደረመረመ ያለሀፍረት እንዴት ማስረዳት እንችላለን?
ብንቆምም፣ ከገላችን ልክ አልቆም እያለ እንደ ሰፊ ውስጥ ልብስ ውልቅ ውልቅ የሚል ቅስም እንዳለን እንዴት ማውራት እንችላለን?
“ልጅን ሲወዱ...” ብሎ የተረተ ሀገር መች ከነ ወደደን? ፍቅራቸው በአፍንጫችን ቅናት እና ማጎንበስ አልተወሰነም? ሀሳባችንን ለመሸጥ ስንዝር የማይሞላ ወገብ እንደማይጠበቅብን ሁሉ፣ እድሜያችን 14 ሳይሆን ውሀ ቻፒስቲክ የልጅ ከንፈራችን ላይ ስናፈስ “እሱን ትተሽ ትምህርትሽ ላይ አታተኩሪም?” ተብለናል። በተንኳሽ አለም ተተንኳሽ ይጠነቀቃል:)
እኔን ትተህ ትምህርቴ ደጃፍ ላይ ተኮልኩለው የልጅነት ባቴን ከልጅነት ባቷ የሚያወዳድሩንን ጎረምሶች፣ ለገና ማርያምን ለመሆን ቅላት እንደሚያሰፈልግ የምታምነዋን አስተማሪ ተዪ፣ ተው አትልልኝም? አትሉልንም?
እድሜ ዘመን የሚከተል ድምፅ እንደምትሰጡን አታውቁም? የውስጥ ድምፃችን የትንኮሳ ቃል እና አሽሙር መሆኑ አያሳዝናችሁም? ስራችሁ ፍሬ አፍርቶ በሌላችሁበትም ለስላሳ ድምፃችንን አሸንፎ የሚወጣው ሸካራ ድምፃችሁ ነው።
የፀጉራችን ቴክስቸር ስንት ሚዶ በድዱ እንዳላስቀረ፤ በለስላሳ ሉጫ ፀጉር የሚሰራው ማስታወቂያ እኛን እንዳላየ አልፎን በየቲቪው የሰራጫል። በጥቁር ሀገር ቅላት ይሰበካል፣ ልጅ ያወጣው ፓውች ሁለት ሳምንት ከተቀመጠ የአእምሮ ጤናን የሚያናጋ አስተያየት በየመታጠፊያው እንደመንገድ አበባ ይቀጠፋል፣ በፀጉራችን መሆን ነውር እስኪመስል ድረስ የቀጠልን ለት በተውሶ ውበት በተለየ እንደነቃለን።
መጀመሪያ ኢንሴኪዩሪቲው ይሸጣል፣ ያን ኢንሴኪዩሪቲ ተጫርተን ቦዲ ዲስሞርፊያ እንገዛለን፣ ከዛ ጊዜያዊ መፍትሄ በተጋነነ ዋጋ ይከተላል፣ ያቺንም እንደያቅማችን እንቃረጣለን። መፍትሄው አልዘልቅ ሲል ማየት ከምንፈራው መልክ፣ ባዶ ኪስ እና ድባቴ ጋ እንቀራለን።
“በሰያፍ በኩል ስታይ ምን እመስል ይሆን?” ብላ በሶስት መስታወት ያንን አንግል ለማየት ያልሞከረች እንስት ለትምህርት እና ለሌላ የህይወት ቁምነገር በቂ የአእምሮ ቦታዋን ያልሰዋች እና መሽቶ በነጋ ቁጥር ለሚፈለፈሉ አሸን ኢንሴኪዩሪቲዎች ያልተሸነፈች ሴት ለኔ ጠንካራዋ እሷ ነች።
አብዛኞቻችን ግን ለሲስተሙ እና ለማህበረሰቡ አይን ተሸንፈንለታል። ካፒታሊዝም የቀናው በሴቶች ራስ አለመተማመን ላይ ነው። ገበያውም የጦፈው በሚቀጠለው ፀጉር፣ ጥፍር፣ ሽፋሽፍት፣ የተለያዩ ውበት መጠበቂያ(ማፅናኚያ) ሸቀጦች ነው።
ለሀበሻ ማስቀየም እንደንቀት ነው፣ how dare you look like this? Whats with the ድንች አፍንጫ?
“ኧረ በመቤቴ ማሰብ ይሻላል?” ብንልም
“ዱላ በማይመልሰዉ ነገር አንስማም” የሚለው ብዙ ነው። ደግሞ እኮ nose job, boob job, face lifting, tummy tuck? ካልን ኪሳችንም እንደማህበረሰቡ መሳለቁ አይቀሬ ነው። ይሄ ሁሉ ተደማምሮ ጢባጢቤዉን የሚጫወተው በራስ መተማመናችን ላይ ነው።
ገና በልጅነታችን በራስ ያለመተማመን ከጉድሞርኒንግ ሻይ ጋር ነው የሚሸጥልን። "መሆን አለመሆን" የሚለው ጥያቄ የሚጀምረው እዛላይ ፒግቴል ያሲያዘችውን ቆንጆ ትንሽ ልጅ ስናይ ነው። እናማ የውበት ኢንደስትሪው በለጋ እድሜያችን ለበረዶ ባስቀመጥነው ሳንቲም ነው ፐርም(የፀጉር ማለስለሻ) የሚያስገዛን።
ቀጭን ሆኖ መታየት፣ ሸንቃጣ መሆንን ያላለመች ሴት፣ በሆርሞን፣ በስራ፣ በኑሮ ምክንያት አልመች ብሏት ከገዛ ሰውነቷ ተኮራርፋ የምትኖረዋም፣ በተገኘው ለማስተካከልም ከጂም ጀምሮ የተለያዩ የሚጠጡ፣ የሚዋጡ ነገሮችንም ያልሞከረች ሴት ቤት ይቁጠራት። ብጉር፣ ማዲያት፣ ዲስከለሬሽን የመሳሰሉትን ለማጥፋት አለ በተባለው ፕሮዳክት ገንዘቧን ያልከሰከሰች ሴት መኖሯም አጠራጣሪ ነው።
ስንት ብራ የልጅነት ቀናችን፣ ሮጦ መስሪያ ወጣትነታችን በነዚህ መነጫንጮች ያላግባብ አልፈዋል፣ ፊታችን ላይ ሀፍረት ተሸክመን ኖረናል። አንገታችን በውድድር ብዛት አጎንብሷል።
አንዳንዶቻችን ድርድር ያላለ ወጣ ገባ ጥርሳችንን ጮክ ብለን “ሲያምር” ለማለት 34 አመት ፈጅቶብናል።
Ain't got no doctor or pill that can take the pain away
The pain's inside and nobody frees you from your body
It's the soul, it's my soul that needs surgery
(It's my soul that needs surgery)
Plastic smiles and denial can only take you so far
Then you break when the fake façade leaves you in the dark
You're left with shattered mirrors and the shards of a beautiful past | 99 |
| 17 | የፍቅረኛን ምራቅ መቅመስ (በመሳም ሂደት ውስጥ) ሰፊ የሳይንስና የፍቅር ትርጉም አለው።
ጥቅሙ
✅የሆርሞን መለዋወጥ፡ በመሳም ወቅት ምራቅ ሲለዋወጥ ኦክሲቶሲን (Oxytocin) የተባለው የፍቅር ሆርሞን ይረጫል። ይህም በመካከላችሁ ያለውን መተማመንና ቅርበት ይጨምራል።
✅ጭንቀትን መቀነስ፡ በምራቅ ንክኪ አማካኝነት ኮርቲሶል (Cortisol) የተባለው የጭንቀት ሆርሞን መጠን ይቀንሳል።
✅የበሽታ መከላከል አቅም (Immunity)፦ የሚገርመው ነገር፣ መጠነኛ የባክቴሪያ ልውውጥ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓት አዳዲስ ጀርሞችን እንዲለምድና እንዲጠነክር ይረዳዋል ይባላል።
✅ (Biological Matchmaking)
ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ፣ በመሳም ወቅት የምራቅ መለዋወጥ ሳያውቁት የትዳር አጋርን ለመምረጥ ይረዳል። በምራቅ ውስጥ ያሉ ኬሚካሎች "ይህ ሰው ለእኔ ይስማማል?" የሚል መልዕክት ለጭንቅላታችን ያስተላልፋሉ። | 97 |
| 18 | ደስተኛ መሆን!
ደስተኛ የመሆን ትልቁ ሚስጥር ገና የሚመጣውን ማሰብ ብቻ አይደለም፤ ወደ ህይወታችን የመጣውንም ማሰብ ነው። ወደ ህይወታችን ከመጣው ምርጥ ስጦታ አንዱ የዛሬው ቀን ነው።
የዛሬዋን ቀን ከዚህ በፊት ቀድሞ ያየው አለ? የለም! አዲስ ስጦታ ነው። ለሀብታሙም ለደሀውም፣ ለትልቁም ለትንሹም፣ ለሴቱም ለወንዱም ከፈጣሪ የተሰጠ ልዩ ስጦታ! እየተነፈስክ ተደሰትና ፈጣሪህን አመስግን ወዳጄ። | 120 |
| 19 | https://t.me/Az123l4l | 101 |
| 20 | አሁኑኑ ጀምር!
አንተ የምትችለውን ሁሉ ስታደርግ ፈጣሪ ደግሞ የማትችለውን ሁሉ ያደርግልሀል፤ በተኛህበት ግን የሚመጣ እድል የለም! መሮጥና መጣር ስትጀምር ሰዎች እንኳን "ምን እናግዝ? ከጎንህ ነን!" ይሉሀል፤ ያልጠበከው ሲሳይ እጅህ ላይ ይወድቃል። ወዳጄ አንተ ብቻ ያሰብከውን አሁኑኑ ጀምር ሁሉም ምርጥ ሲሆን ታየዋለህ! | 98 |
