ሪሳለቱል ሂጃብمعرفة الحجاب☀️
Open in Telegram
ስለ ሂጃብ እና መስፈርቶቹ ማወቅ ያለብን አስተማሪ ትምህርቶች የምንለቅበት ቻናል ነው ሀሳብ እና አስተያየት ካላቹ 👇 @Risaletulhijab_bot ኒቃቤን ስወዳት Join and Share 👇 @Risaletulhijab
Show more8 235
Subscribers
-424 hours
-487 days
-14130 days
Posts Archive
ኢናሊላሂ ወኢና ኢላሂ ራጁዑን‼
ትላንት በጦራ ዳሎቻ ማዞሪያ በደረሰ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህች ዓለም ወደ አኺራ የተሸጋገሩት ሁለቱ እህትማማቾች ገና በወጣትነታቸው በቁርዓን ብርሃን የደመቁ ነበሩ። በለበሱት ኒቃብ ውስጥ ንጹህ ልብን በቃላቸው ውስጥ ደግሞ የአላህን ቃል ሰንቀው ለሌሎች ሴቶች መካሪና አስተማሪ በመሆን ይታወቁ ነበር።
ለቅሶ ቤቶች ላይና ሰዎች በሚበዙባቸው ስፍራዎች ተገኝተው ለሴት እህቶቻቸው ዳዕዋ ሲያደርጉና ወደ አላህ መንገድ ሲጠሩ የነበሩት እነዚህ ሙጃሂዶች ዛሬ ግን እነሱ ቤት ለቅሶ ገብቷል።
ለእምነታቸው የኖሩ በቁርዓን የተገሩና ሕይወታቸውን ለዳዕዋ የሰጡ ውድ እህቶቻችን! ዛሬ በሞት ብንለያችሁም ያስቀመጣችሁት በጎ ተጽዕኖና ያስተማራችሁት እውነት ምንጊዜም በልባችን ይኖራል።
አላህ ሆይ! የቁርዓን ብርሃን ቀብራቸውን ያብራላቸው። ለእህቶቻችን ጀነትን ወፍቃቸው። ለወላጆቻቸው፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው ሁሉ አላህ ሶብረንና ኢማንን ይስጣቸው። 💔
ትላንት ስብርብር ያልን የመሰለን ግዜ ... ከዚ ቦሀላ እሷ ሰው ሁና ትቆማለች ? እራሷን መች ሆነችና..... ወይኔ እሷ ተብሎ ጥርስ የተመጠጠልን ወቅት .... መኖር ደክሞናል ከዚህ ወዲያ በዚ ምድር መቆየታችን ጥቅም የለውም ብለን አስበን በተስፋ መቁረጥ ማፅበል በተናወጥንበት በዛ ትናንታችን .... ደርሶ ያዳነን ዳግም ያንሰራራን ድጋሚ ለመኖር የምንጓጎለትን ብዙ ፀጋ የሰጠን አላህ ነው ! አረህማን አልፈው ሲወሩ ቀላል የሚመስሉ.... ግን ዛሬ ላይ ቆመን ትዝ ብለውን ቁጭ ብለን ስናስባቸው እንኳን የእምባችንን ከረጢት ማቆም እስኪያቅተን የምናነባባቸው .... ብዙ የመውደቅ ተስፋ የማጣት የመሰበርና የመከዳት ታሪኮች ነበሩን ! አልሃምዱሊላህ ነበር ማለት ራሱ ደስ ይላል
አላህ ታሪክን ቀያሪ ነው ! አላህ ......ደግም የሞተ ልብን ህያው የሚያደርግ ....... ያደፈ ስብእናን በፀፀት የሚያነፃ .......ያ. እጅግ አዛኙ እጅግ ሩህሩሁ ጌታ ...... በደከመን ጉዳይ ላይ ሁሉ መበርታትን.. በከበደን ጉዳይ ላይ ሁሉ ጥንካሬን ይችረን ሁኔታችንን በተሻለ ኸይር ይለውጥልን 🤲
አብሽሩ ህይወት ለማንም ሙሉ አደለችም 🥰
✍🏽بنت بابا
አዋጅ... አዋጅ📢
አክሱም ላይ አዋጅ ወቷል፣ ልብን የሚያደማ
ህግን አፅድቀዋል፣ሙስሊሙን አግልለው፣
በአድባራት ብቻ፣ ስብሰባውን ጠርተው፤
በትምርት ገበታ፣ ሂጃብ ላይለበስ፤
በጁምዓ ቀን ሙስሊም በጠቅላላ፣ መስጅድ ደጅ ላይደርስ፤
ባካባቢው ያሉ መስጅዶች በሙሉ፣
ጀንበሯ ሳትጠልቅ፣ እንዲዘጋ አሉ፣
አዛን እንዳይሰማ በማጉሊያ በስፒከር፣
ህግን አውጥተዋል፣ ያለምንም ድንበር፤
ሙስሊም ከሞተ፣ ለመቅበር ሲሄዱ፣
ከልክለዋቸዋል፣ ጀናዛን ላይወስዱ...
Repost from Huda Wave
ፈጥኖ የመለሰ! 🚀
ትክክለኛውን መልስ ያገኘ ሰው 'Add' የሚለውን በመጫን ብዙ ጠቃሚ ቻናሎችን ያገኛል።
ጥያቄ፦ አንድ ሙስሊም ያለ በቂ ምክንያት (በቸልተኝነት) ሦስት የጁሙዓ ሶላቶችን በተከታታይ ከተወ አላህ ልቡ ላይ ማኅተም ያደርግበታል (ያሽግበታል)።
◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍
የጁሙዓ ቀን ሱናዎች - سنن يوم الجمعة
❶ ገላ መታጠብ
❷ ጥሩ ልብስ መልበስ
❸ ሽቶ መቀባት
❹ መፋቂያ መጠቀም
❺ በጊዜ መስጂድ መሄድ
❻ ሱረተል ከህፍን መቅራት
❼ ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ
❽ ዱዓ ማብዛት
❾ በነቢያችን ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት
◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍
ከወንዶች መካከል ገንዘብን በመፈለግ የሚያገባ አለ። ከነሱም መካከል አይኑን ለመሙላት እና አእምሮውን ለማስደሰት የተዋቡ ሴቶችን የሚፈልጉ አሉ። እውነተኛ ውበት የሚባለው፡ ውስጣዊ ውበት፣ ጥብቅነት እና ያማረ ፀባይ መሆኑን አላወቁም።
ኡሙ ሰለማህ አድዷሊዒያ
Repost from Ďaŵud Apologetics◍﷽
ضوابط في الفتن يحتاجها كل مسلم
• #ዶዋቢጡ_ፊል_ፊተን
• ማንኛዉንም ሙስሊም የሚያስፈልገው
የፈተና ግዜ መርሆዎች
√ ሸይኽ ሱለይማን ብኑ አርሩሐይሊ
ሞት ማለት እንዲህ ነው። የቱንም ያህል ብትወደድ፣ የቱንም ያህል ብትከበር፤ መጨረሻህ ግን «ፀሐይ ሳይበረታ ቀብረን እንመለስ» በሚል መመሪያ ይቋጫል። ሁሉም ወደ ራሱ ኑሮ ለመመለስ ይቸኩላል።
❌❌ التيك توك ❌❌
⭕️ቲክቶክን ተጠንቀቁ ⭕️
🛑👉ለምን ብትሉኝ መልሱን ለናንተው ትቸዋለሁኝ
🛑👉ቲክ ቶክ ማለት ዋና የተመሰረተበት ምክንያት
( بالمعصية ) በሀራም ላይ የተመሰረተ ነው👉🛑
🛑👉በቲክ ቶክ ላይ የተገላለጡ ሴቶች (وتبرج النساء )
🛑👉በቲክ ቶክ ላይ ሴት እና ወንድ መደባለቅ (إختلاط الرجال بالنساء )
🛑👉በቲክ ቶክ ላይ የሽርክ መዳረሻ መንዙማዎች (الشركيات
🛑👉በቲክ ቶክ ላይ ሙዚቃ ( الغناء الأناشد الإسلامية )
🛑👉በቲክ ቶክ ላይ ውሸት (الكذب)
🛑👉በቲክ ቶክ ላይ ስድቦች (السب)
🛑👉በቲክ ቶክ ላይ ............... ከዚህም በላይ ብዙ ነገራቶች አሉበት❌ ተጠንቀቁ ተጠንቀቁ ተጠንቀቁ❌
🛑👉የሙስሊሞች ባህሪ የሚቀይር የእስልምናን መዋቢያ አደቦችን( አቅጣጫ የሚያስት) ትልቅ አፕ ነው።
✅ ሙስሊም እህቴ ሙስሊም ወንድሜ
⭕️إحذر من التيك توك ❌
🛑👉ከቲክ ቶክ ተጠንቀቁ አስጠንቅቁ❌
#أذكار_المساء የማታ አዝካር
((اللَّهُمَّ عَالِمَ الغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَاطِرَ السَّمَوَاتِ وَالْأَرْضِ، رَبَّ كُلِّ شَيْءٍ وَمَلِيكَهُ، أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ نَفْسِي، وَمِنْ شَرِّ الشَّيْطانِ وَشَرَكِهِ، وَأَنْ أَقْتَرِفَ عَلَى نَفْسِي سُوءاً، أَوْ أَجُرَّهُ إِلَى مُسْلِمٍ)).
የምድር ሴቶች ባጠቃላይ ቢራቆቱ!.
ወንድ ልጅ አይኑን ባለመስበሩ ይጠየቃል
የምድር ወንድ ሁሉ አይኑን ቢሰብርም
ሴቶች ስለ አለባበሳቸው ይጠየቃሉ ።
