ሪሳለቱል ሂጃብمعرفة الحجاب☀️
Open in Telegram
ስለ ሂጃብ እና መስፈርቶቹ ማወቅ ያለብን አስተማሪ ትምህርቶች የምንለቅበት ቻናል ነው ሀሳብ እና አስተያየት ካላቹ 👇 @Risaletulhijab_bot ኒቃቤን ስወዳት Join and Share 👇 @Risaletulhijab
Show more8 235
Subscribers
-424 hours
-487 days
-14130 days
Posts Archive
Repost from Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
የአንድን አባት እንባ ዛሬ ማታ እናብሳለን‼
=========================
(ኢንሻ አላህ – ዝግጁ?)
||
✍️ ያ ጀማዓህ... ባለፈ ስለ ህፃን ዘከሪያ ሁኔታ ነግሪያችሁ ነበር። ከሁለት ቀን በፊት የሰማሁት ግን አንጀቴን ነው የበላው!
አባቱ፣ ኢንጂነር ሸምሰዲን... ሙያው እያለው፣ ሰርቶ ሃብት ማፍራት ሲችል፣ አብዛኛውን ጊዜውንና ጉልበቱን ለዲን እና የሰዎችን ሐጃ በማውጣት ያሳለፈ ምርጥ ወንድማችን ነው። ዛሬ ግን ይህ ለሰው ደራሽ የሆነ አባት ከባድ ፈተና ገጥሞታል። ከትናንት ወዲያ
ወንድሞች ሲነግሩኝ፤ «ብሩ ስላልሞላለት፣ ልጁ በዓይኑ ስር እየሟሟበት፣ ቤቱን ዘግቶ ከታመመ ልጁ ጋር አቅም አጥቶ እያለቀሰ ነው» አሉኝ። ወላሂ ይህን ስሰማ ውስጤን ነው የነካው!
ዲን አገልጋይ የሆኑ መሰል ወንድሞቻችን እንዲህ ያለ ሙሲባ ሲገጥማቸው፣ የት አላችሁ ብለን ከጎናቸው ልንቆም ይገባል!
አል-ሐምዱ ሊላህ! እስካሁን በተደረገው ርብርብ 5,052,000 (አምስት ሚሊዮን ሀምሳ ሁለት ሺህ) ብር ተደርሷል!
ነገር ግን ህክምናው ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ይፈልጋል። በሽታው ደግሞ ፈፅሞ ጊዜ የሚሰጥ አይደለም። ዘከሪያ በየሰከንዱ እየተሰቃየ
ነው ያለው። ስለ በሽታው ሁኔታ የባለፈውን ጽሑፌን አንብቡት።
ወንድም እህቶቼ... ያለነው እኮ በዱንያ ላይ ካሉ ቀናት ሁሉ በላጭ በሆኑት፣ አላህ በቁርኣን በማለባቸው የዙል-ሒጃ 10 ወርቃማ ቀናት ውስጥ ነው! ይህ ለኛ የጀነት በር መክፈቻ፣ የአጅር መሸቀያችን ነው። አላህ ይህን ወንድማችንን የፈተነው፣ እኛን በእሱ ሰበብ ጀነት ሊያስገባን ይሆናልና ለራሳችን ብለን እንጠቀምበት።
አሁን የቀረን 1 ሚሊዮን ብር አካባቢ ነው!
ተረባርበን ኢንሻ አላህ ዛሬ አዳር ይህንን ክፍተት እንሞላታለን! ዝግጁ ናችሁ? ጥቂት ነው ብላችሁ አትናቁ፣ ያላችሁን አውጡና ቤቱን ዘግቶ የሚያለቅሰውን አባት ዛሬ ማታ በአላህ ፈቃድ እንባውን እናብስለት!
💰 ሶደቃ ለመሰደቅ፦
☑ የአካውንት ስም፦ ሸምሰዲን ዐብዱ (Shemsedin Abdu)
🏦 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
(CBE): 1000380970582
🏦 ህብረት ባንክ: 3459111371313012
🏦 ዳሽን ባንክ: 2904914060011
🏦 አዋሽ ባንክ (Awash Bank): 0142545355700
🏦 ሒጅራ ባንክ (Hijra Bank): 1005286530001
🏦 ራሚስ ባንክ (Rammis Bank): 1010067514201
📲 የሰደቃችሁበትን ደረሰኝ በውስጥ መስመር 👉 @Murad_Tadesse ላይ ላኩልኝ። እየደመርኩ ስንት እንደቀረን አሳውቃችኋለሁ!
ገንዘብ ማውጣት ያልቻላችሁ ይህንን ፖስት ቢያንስ Share በማድረግ የዘመቻው አካል ሁኑ!
አላህ በምትሰጡት ላይ በረካውን ያውርድላችሁ! የዚህን አባት እንባ እንዳበሳችሁ፣ አላህ የቂያማ ዕለት ጭንቀታችሁን ያርቅላችሁ! 🤲
Repost from Huda Wave
ፈጥኖ የመለሰ! 🚀
ትክክለኛውን መልስ ያገኘ ሰው 'Add' የሚለውን በመጫን ብዙ ጠቃሚ ቻናሎችን ያገኛል።
➡️ ቻናል ለማሳደግ
ጥያቄ፦ በአስሩ (የዙል-ሒጃህ) ቀናት ከሚሰሩ መልካም ስራዎች ይልቅ አላህ ዘንድ ይበልጥ የተወደደ መልካም ስራ የሚሰራበት ሌላ ምንም ቀን የለም።
ቁርኣንን መሐፈዝ የችሎታ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የትዕግስት እና የፍላጎት ውጤት ነው።
~
አንድ ገጽ በሐፈዝክ ቁጥር ወደ ጀነት አንድ ደረጃ ከፍ እያልክ መሆንህን አስብ። መንገዱ ረጅም ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን አላህ ለመረጣቸው ባሮቹ ቃሉን በልባቸው ውስጥ እንዲያኖሩ ይረዳቸዋል። ዛሬ የከበደህ ነገ የልብህ ብርሃን ይሆናል።
✍
ሁለት ዓይነት ተክቢራዎች አሉ!!
1ኛው, ልቅ የሆነ ተክቢራ ሲሆን;
2ኛው, የተገደበ ተክቢራ ነው።
ልቅ የሆነው ተክቢራ………
የዙል_ሒጃ ጨረቃ ከታየችበት ሰዓት ይጀመርና እስከ አያመ አል_ተሽሪቅ የመጨረሻው ቀን ፀሀይዋ እስክትጠልቅ ድረስ በየትኛውም ሰዓት እና ቦታ የሚባለው የተክቢራ ዓይነት ነው።
የተገደበው ተክቢራ፦
የዐረፋ ቀን ከፈጅር ሰላት ይጀመርና እስከ መጨረሻው የአያመ አል_ተሽሪቅ ቀን የዐስር ሰላት ድረስ ከአምስት አውቃት ሰላቶች በኋላ የሚደረገው ተክቢራ ነው።
/ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዑሰይሚን/
NB!
"አያመ አል_ተሽሪቅ" ማለት፦
ከዒድ ቀን በኋላ ያሉ 3ቱ ተከታታይ ቀናቶች ናቸው።
"የዐረፋ ቀን" ማለት፦
ከዒድ ቀን አስቀድሞ ያለው (የዒድ ዋዜማ) ቀን ነው።
በዚህም መሰረት………
አሁን ላይ በየትኛውም ቦታ ሆነን በየትኛውም ሰዓት ተክቢራ ማለት እንችላለን ማለት ነው።
🔊الله أكبر ..الله اكبر ..الله اكبر
لا اله الا الله
والله اكبر الله اكبر
ولله الحمد
አልሃምዱሊላህ ዱንያ ላይ ካሉ ቀናቶች መሃል በላጭ የሆኑት አስሩ የዙል ሂጃ ቀናትን አላህ አድርሶናል...
በእነዚህ ውድ ቀናቶች ....
በሰፋ እና መርዋ መሃል ሃጀርን እያሰብን ለመመላለስ ፣ አንተን ብቻ ብለው ከተሰደዱ ባሮችህ ስብስብ መሃል ሆነን ልናልቅህ ፣ እየጠወፍን የሆድ የሆዳችንን ልናወጋህ፣ ሚና እና ሙዝደሊፋ ልናነጋ ፣ ካማረው ግርግር መሃል ሆነን ተልቢያ ልንል ፣ ከሁጃጆች መሃል ልንሯሯጥ ፣ አረፋ ተራራ ላይ በእለቱ ቆመን ልንለምንህ ... ለጥሪህ ከመረጥካቸው ባሮችህ መሃል ተገኝተን እንኳን ባይሆንም "ለበይከ ረቢ🥺"
ለበይክ!... ለተለዩን ቤተሰቦቻችን እዝነትህን🤲
ለበይክ!... የቀሩት የመኖር ትርጉማችን የሆኑት ሰዎቻችን🤲
ለበይክ!... ዱንያ ያደከመቻትን ልባችንን🤲
ለበይክ!... ስክነት ፈላጊዋ ሩሃችንን🤲
ለበይክ!.... ፈርተንም ከጅለንህም🤲
ለበይክ!... በትእዛዞችህ እንድንቆም🤲
ለበይክ!... ከወጀላችን እንድንጠራ😥
ለበይክ!... አንተን ተማምነን የሰነቅናቸው ህልሞቻችንን🤲
ለበይክ!... ዱንያ አኺራችንንም🤲
ለበይክ!... የኢድ ልብሶቻችን ያስቦረቁን የነበረበት የልጅነት ጊዜ እንዳለፈው ሁሉ ይህ ወጣትነት እና ቁዋው ሳያልፍ የጓጓንለትን የኢህራም ልብስ እንድታለብሰን🤲
ለበይክ! እኛም በቀኖቹ በቦታው ቆመን ለበይክ እንድንልህ🤲🥺
በመልካም ዱአዎቻችን እንዳንረሳሳ በተለይ የአረፋ ቀን🥰
የዙልሂጃ 10ቱ ቀናት
📌በነዚህ 10 ቀናት ውስጥ የሚሰሩ መልካም ስራዎች፤ በረመዳን የመጨረሻዎቹ 10ቱ ቀናት ውስጥ ከሚሰሩት መልካም ስራዎች የበለጡ ናቸው
ማስታወሻ!
በዛሬው ዕለት ሳዑዲ ዓረቢያ የዙል-ሒጃህ ወር ጨረቃ መታየት የምትከታተል በመሆኑ፣ የሚከተሉት ቀናቶች ይወሰናሉ፦
• የዙል-ሒጃህ ወር መጀመሪያ
• የዓረፋ ቀን መቼ እንደሚሆን
• የዒድ አል-አድሓ (የአረፋ በዓል) ዕለት
ዛሬ ትኩስና ወቅታዊ የሆኑ የዙል-ሒጃህ ወር መረጃዎችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን። እስከዚያው ተከታተሉን!
Repost from N/a
📝 ማስታወሻ!
➖➖➖➖
በዛሬው ዕለት ሳዑዲ ዓረቢያ የዙል-ሒጃህ ወር ጨረቃ መታየት የምትከታተል በመሆኑ፣ የሚከተሉት ቀናቶች ይወሰናሉ፦
• የዙል-ሒጃህ ወር መጀመሪያ
• የዓረፋ ቀን መቼ እንደሚሆን
• የዒድ አል-አድሓ (የአረፋ በዓል) ዕለት
🔴 ዛሬ ትኩስና ወቅታዊ የሆኑ የዙል-ሒጃህ ወር መረጃዎችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን። እስከዚያው ተከታተሉን!
=
ቻናሉን ለመቀላቀል፦
https://t.me/FuadKemal
https://t.me/FuadKemal
*✍🏻10ሩ የዙልሂጃ ቀናቶች*
*ان شاءالله*
*✍🏻ተጠባበቋቸው።*
ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ የተባሉ የ ዙል-ሂጃ አስርቱ ቀናቶች ሊገቡ 3 ቀናት ብቻ ይቀሩናል ።
የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم
በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ
"أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّة.
ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ቀናቶች አስርቱ የዙል ሂጃ ቀናቶች ናቸው!!
በሌላም ሀዲስ እንዲህ በማለት በነዚህ ቀናቶች የሚሰራ ስራ ያለው ደረጃ ያስቀምጣሉ።
ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله من هذه الأيام العشر،
قالوا ولا الجهاد في سبيل الله؟
قال ولا الجهاد في سبيل الله، إلاّ رجلا خرج بنفسه وماله فلم يرجع من ذلك بشيء
ከነዚህ ከአስር ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራ ወደ አላህ ሚወደድበት ቀን የለም አሉ
ሰሀቦችም በአላህ መንገድ ላይ መታገል መጋደል ቢሆንም? ብለው ሲጠይቋቸው አው በአላህ መንገድ መታገል ቢሆንም ግን አንድ ሰው ሲቀር አሉ እሱም በአላህ መንገድ ለመታገል ነፍሱንም ንብረቱንም ይዞ ወጥቶ እስከ ንብረቱ እዛው የቀረ'' አሉ አላህ በሰላም አድርሶን ተጠቅመንባቸው የምናልፍ ያድርገን يارب
اتق الله حيثما كنت
ቢስሚላህ
ነገ ቅዳሜ (ግንቦት 8/ 2018) የዙልቃዒዳ የመጨረሻ ቀን ሊሆን ስለሚችል ኡድሒያ የማረድ እቅድ ያለው ሰው ከሰውነቱ መነሳት የሚያስፈልጋቸው ፀጉሮችንና ጥፍሩን ነገ እስከ ከመግሪብ በፊት ባሉ ሰዓቶች አስቀድሞ ማንሳት ይጠበቅበታል።
እንደ መላመድ ክፉ አለ ያአላህ በጣምም ከባድ ነው ከተላመዱት ከልብ ከሚወዱት መራራቅ ወላሂ አላህ አይፈትነን 🥺💛
የተራራቃቹ የተነፋፈቃቹ ሁሉ አላህ መልሶ ያገናኛቹ
Repost from Huda Wave
ፈጥኖ የመለሰ! 🔤
ትክክለኛውን መልስ ያገኘ ሰው 'Add' የሚለውን በመጫን ብዙ ጠቃሚ ቻናሎችን ያገኛል።
➡️ ቻናል ለማሳደግ
ጥያቄ፦ አንድ ባሪያ ወደ አላህ ይበልጥ የሚቀርበው በሱጁድ ላይ እያለ ነው።
🔆ቁርአን ከቃኢዳ ጀምሮ እንዲሁም አጫጭር 👉ኪታቦች መቅራት የምትፈልጉ
☑️በቴሌግራም ቀጥታ (live) እና
☑️በኢሞ በቀጥታ (live) በተጅዊድ ከፈተና ጋር መቅራት የምትፈልጉ
በዚህ አናግሩን 👇👇
👉@Umu_asiya65
👆በዚህ ኑ
