en
Feedback
The AgriLancer

The AgriLancer

Open in Telegram

''Animal Farming Entrepreneur'' በወተት ከብት እርባታ | ዶሮ እርባታ | በቁም እንስሳት የመኖ ዘሮች እና የእርባታ ቁሳቁስ ቴክኖሎጂዎች ስፔሻላይዝ ያደረገ! ስለ AgriLancer ማብራሪያ introduction ያንብቡ 👉https://t.me/agrilancer/1455

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel The AgriLancer

Channel The AgriLancer (@agrilancer) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 25 638 subscribers, ranking 2 540 in the Business category and 1 308 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 25 638 subscribers.

According to the latest data from 10 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -291 over the last 30 days and by -18 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 22.58%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 8.94% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 5 790 views. Within the first day, a publication typically gains 2 293 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 14.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
''Animal Farming Entrepreneur'' በወተት ከብት እርባታ | ዶሮ እርባታ | በቁም እንስሳት የመኖ ዘሮች እና የእርባታ ቁሳቁስ ቴክኖሎጂዎች ስፔሻላይዝ ያደረገ! ስለ AgriLancer ማብራሪያ introduction ያንብቡ 👉https://t.me/agrilancer/1455

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 11 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Business category.

25 638
Subscribers
-1824 hours
-697 days
-29130 days
Posts Archive
⚡️የአልፋአልፈ ዘር ✨የዘር ኮድ 👉 Emiliana Erba Medica 📌የመብቀል አቅም 96% 📌የምርት ዘመን እድሜ 5 ዓመት አማካይ ⚔️በረሃ የሚቋቋም 👉ለሚታለቡ ላሞች 👉ለሚደልቡ የቁም እን
⚡️የአልፋአልፈ ዘር ✨የዘር ኮድ 👉 Emiliana Erba Medica 📌የመብቀል አቅም 96% 📌የምርት ዘመን እድሜ 5 ዓመት አማካይ ⚔️በረሃ የሚቋቋም 👉ለሚታለቡ ላሞች 👉ለሚደልቡ የቁም እንስሳት 👉ለዶሮዎች @AgriLancer

⚡️ለሽያጭ የቀረቡ ጊደሮች 🌾ዝርያ ሆልስቲን ፍሬሲያን 🌾ከ 4 እስከ 8 ወር ክበድ/ የመጀመሪያ 🌾ብዛት ከ 20 በላይ ይደውሉልን +251913323845 @AgriLancer

⚡️ለሽያጭ የቀረቡ ጊደሮች

⚡️በሰኔ ወር ለሽያጭ የቀረቡ የዶሮ ዝርያዎች 1. የ 2 ወር ቦቫን ብራውንስ 2. ለዘመን መለወጫ የሚደርሱ የስጋ ሳሶዎች 3. ፖችፎስትሩም ኮኮክ ከረምት ሳይገባ ያስገቡ አዲስ አበባ ነፃ ትራንስፖርት
⚡️በሰኔ ወር ለሽያጭ የቀረቡ የዶሮ ዝርያዎች 1. የ 2 ወር ቦቫን ብራውንስ 2. ለዘመን መለወጫ የሚደርሱ የስጋ ሳሶዎች 3. ፖችፎስትሩም ኮኮክ ከረምት ሳይገባ ያስገቡ አዲስ አበባ ነፃ ትራንስፖርት እንሰጣለን ይዘዙን +251913323845 @AgriLancer

የወተት ላም እርባታ መጀመር ከፍተኛ ትርፍ የሚያስገኝ ግን ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ የሚጠይቅ የንግድ ዘርፍ ነው። ስኬታማ ለመሆን የሚከተሉትን ዋና ዋና ቅደም ተከተሎች መከተል ያስፈልጋል። 1. የገበያ ጥናት እና እቅድ (Business Plan) ፍላጎትን ማወቅ፦ በአካባቢዎ ያለውን የወተት እና የወተት ተዋጽኦ ፍላጎት ያጥኑ። ደንበኞችን መለየት፦ ወተቱን ለወተት ማቀነባበሪያዎች፣ ለሆቴሎች ወይስ በቀጥታ ለተጠቃሚዎች እንደሚሸጡ ይወስኑ። የፋይናንስ እቅድ፦ ለግዢ፣ ለቀለብ፣ ለቤት ግንባታ እና ለሰራተኛ የሚያስፈልገውን ወጪ ዝርዝር ያዘጋጁ። 2. ተስማሚ ቦታ መምረጥ ውሃ እና መብራት፦ በቂ የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና አስተማማኝ መብራት መኖሩን ያረጋግጡ። መጓጓዣ፦ መኖ ለማስገባት እና ወተት በፍጥነት ወደ ገበያ ለማድረስ መንገዱ ምቹ መሆን አለበት። የአየር ንብረት፦ ቦታው ለላሞች ጤንነት እና ለሳር ልማት ተስማሚ መሆኑን ያረጋግጡ። 3. የላሞች ዝርያ ምርጫ የሀገር ውስጥ ዝርያ፦ በሽታ የመቋቋም አቅማቸው ከፍተኛ ነው፤ ነገር ግን የሚሰጡት የወተት መጠን አነስተኛ ነው። የውጭ ዝርያ (ለምሳሌ ሆልስታይን ፍሪዥያን)፦ ከፍተኛ ወተት ይሰጣሉ፤ ነገር ግን ከፍተኛ እንክብካቤ እና መኖ ይፈልጋሉ። የተሻሻሉ (ቃሊቦ) ዝርያዎች፦ ለጀማሪዎች መካከለኛ ወጪና ጥሩ ምርት ለማግኘት ተመራጭ ናቸው። 4. የመኖ እና የውሃ አቅርቦት የመኖ ልማት፦ ወጪን ለመቀነስ በራስዎ መሬት ላይ ዝሆን ሳር፣ አልፋልፋ እና መሰል መኖዎችን ያልሙ። የተመጣጠነ ቀለብ፦ ለላሞቹ በቂ ፋይበር (ድርቆሽ) እና የኃይል ሰጪ መኖ (ፋብሪካ ፋጋሎ) ያቅርቡ። ንፁህ ውሃ፦ አንዲት የወተት ላም በቀን እስከ 100 ሊትር ንፁህ ውሃ እንደምትጠጣ አስበው ያዘጋጁ። 5. የላሞች መጠለያ (በረቶች) ግንባታ አየር ዝውውር፦ በረቱ በቂ አየር እና የፀሐይ ብርሃን የሚያገኝ መሆን አለበት። ንፅህና፦ ወለሉ በቀላሉ የሚታጠብ እና ሽንትና ፈሳሽ በቀላሉ የሚወጣበት መሆን ይኖርበታል። ቦታ፦ ለእያንዳንዱ ላም ለመተኛት፣ ለመመገብና ለመባዛት የሚሆን በቂ ስፋት ሊኖረው ይገባል። 6. የጤና እንክብካቤ እና አስተዳደር ክትባት፦ በአካባቢው ለሚከሰቱ በሽታዎች ወቅታዊ ክትባቶችን በባለሙያ ያስቡ። የወተት ንፅህና፦ ወተት በሚታለብበት ጊዜ የእጅ፣ የእቃ እና የላሟ ጡት ንፅህና መጠበቅ አለበት። መዝገብ መያዝ፦ የእያንዳንዱን ላም የወተት ምርት፣ የክትባት ጊዜ እና የሰንጋ ወቅት (መውለጃ) መዝግበው ይያዙ። ይህንን እቅድ የበለጠ ግልጽ ለማድረግ የሚከተሉትን በኢሜል ቢፅፉልን በትኜ መመለስ እችላለሁ፦ 1.እርባታውን ለመጀመር ያሰቡት ክልል ወይም አካባቢ የት ነው? 2.በስንት የላም ብዛት ለመጀመር አቅደዋል? 3.ለእርባታው የመደቡት የመነሻ ካፒታል በምን ያህል መጠን ነው? እነዚህን ዝርዝሮች መነሻ በማድረግ ለአካባቢዎ የሚስማማ የተለየ ምክር መስጠት እችላለሁ። ጊዜ ሰጥቼ መመለስ እንድችል በተቻለ መጠን ጥያቄዎ ግልፅ እና በመረጃ የተደራጀ መሆን ይኖርበታል። Email yonatan.lancer@gmail.com @AgriLancer

⚡️የወተት ከብት እርባታ ስራ አጀማመር እና እቅድ
⚡️የወተት ከብት እርባታ ስራ አጀማመር እና እቅድ

⚡️አውቶማቲክ የከብቶች ውሃ መጠጫ 🌾የራሱ የከብቶች ፊት ሴንሰርያለው ✨ዋጋ:- 4,175 ብር ቫትን ያካተተ @AgriLancer

⚡️ሱቅ ላይ አሁንም በሽያጭ ላይ ያሉ እቃዎች 🌾ቾፐሮች - ከብራዚል የገቡ 🌾ማለቢያዎች - ከቱርክ 🌾ቢዶኒዎች - ከህንድ 🌾ማት/የከብቶች መተኛ - ከህንድ 🌾አውቶማቲክ የላሞች ውሃ መጠጫ - ከቱርክ 🌾የከብቶች ጥፍር መቁረጫ - ብራዚል ለመግዛት በማንኛውም የስራ ቀን ያገኛሉ @AgriLancer

⚡️ለዘመን መለወጫ የሚደርሱ የስጋ ዶሮዎችን ያስገቡ የ 35 ቀን እድሜ ያላቸው የስጋ ጫጩቶች። አዲስ አበባ ነፃ ትራንስፖርት አገልግሎት እንሰጣለን። ከወሰዱ በኋላም ሙያዊ ክትትል እንደተለመደው 🌾ጥ
⚡️ለዘመን መለወጫ የሚደርሱ የስጋ ዶሮዎችን ያስገቡ የ 35 ቀን እድሜ ያላቸው የስጋ ጫጩቶች። አዲስ አበባ ነፃ ትራንስፖርት አገልግሎት እንሰጣለን። ከወሰዱ በኋላም ሙያዊ ክትትል እንደተለመደው 🌾ጥሪያችንን ተቀብለው ብዙዎች አስገብተዋል 🌾እርሶም ያስገቡ 🌾ትዕዛዝ 50 እና ከዛ በላይ @AgriLancer

በዶሮ እርባታ ስራ የስራው ፍቅር ብቻ አይደለም። ዝግጅትም ይፈልጋል: ዶሮዎች ከገቡ በኋላም በስሜት ሳይሆን በጥበብ እና በ principle ማስተዳደር ወሳኝ ነው። የእውነት ለዶሮ እርባታ ስራ ፍቅር አለክ? ስኬታማ የዶሮ አርቢዎች የሚከተሏቸው 10 የእርባታ ህጎች እንደሚከተለው 1. ማስተዳደር የምትችለውን የዶሮ ቁጥር ብቻ አስገባ። ከአቅም በላይ ተወጣጥረህ እና ተጨናንቀህ የምታስተዳድራቸው ዶሮዎች ውጥንቅጡ ለወጣ አሰራር እና ውጤት አሳልፈው ይሰጡሃል። በአግባቡ የተመገቡ እና የተያዙ 300 ዶሮዎች በአግባቡ ካልተያዙ እና ከተራቡ 1,000 ዶሮዎች የተሻለ ውጤት ይሰጡሃል። በዶሮ እርባታ ስራ ውስጥ ቁጥር ብቻ በቂ አይደለም: ንፅህና: ጥሩ መኖ እና የተረጋጋ አካባቢን ያገኙ ሰላም ያላቸው ዶሮዎች ጤነኛ:ምርታማ እና ትርፋማ ናቸው። 2.በስራው ላይ የጠለቀ ልምድ ከሌለክ ብር ተበድረክ የዶሮ እርባታ ስራ እንዳትጀምር። በጊዜ ገደብ የተሰጠ ብድር ከበድ ያለ ጫናን ያስከትላል። የዶሮ እርባታ ስራ ደሞ አንዳንዴ ፈፅሞ ባልጠበከው ነገር surprise ያደርግሃል። የወሰድከው ስልጠናም ሆነ ያቀድከው እቅድ መሬት ስትወርድ ከጠበከው በተቃራኒ ሊቀበልህ ይችላል: በቀን ተቀን የምትማረው ልምድ ብቻ ነው ትምህርት የሚሰጥህ እና ነፃ የሚያወጣህ። ባለህ ነገር ብቻ ጀምር አትበደር። ልምድህን አጠናክር ከዛም እራስህን እና አቅምህን እያደራጀህ አስፋፋ። 3.አይኖችህ ሁሉ የዶሮዎችህን እንቅስቃሴ እንደመርማሪ ይመልከቱ። በዶሮ እርባታ ስራ ላይ ችላ የተባሉ ጥቃቅን ክምችቶች ስራህን ሊያበላሹ ይችላሉ።  ጠዋት ጠዋት ዶሮዎችህን በሚገባ ተመልከታቸው: አረማመዳቸውን ተመልከት: አመጋገባቸውን እና ቅልጥፍናቸውን። በዶሮዎቹ ላይ ትንሽ የምትባልም ወጣ ያለች ባህሪ በጊዜ ማወቅህ ከብዙ ችግር ያድናሃል። 4. የዶሮዎችህን ማስጠንቀቂያ ምልክት እወቅ። ዶሮ እርባታ ውስጥ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ዶሮዎችህ ምልክት ይሰጣሉ። ምግብ አለመብላት: ባልተለመደ መልኩ ዳር መያዝ: ያልተገባ ጠረን ወይንም ዝግም ያለ እንቅስቃሴ ችግር እንዳለ ምልክቶች ናቸው። የዶሮዎችህን ተፈጥሮ ጠንቅቀህ እወቅ: የተባለው አይነት ችግሮች ስታይ ፈጥነህ ምላሽ ስጥ። 5.የለመዱትን መኖ ብድግ ብለህ አትቀይር። በድንገት የተለወጠ የመኖ አቅርቦት በዶሮዎቹ ላይ አካላዊ ሲስተማቸውን ያናጋዋል። ጭንቀት ውስጥ የመክተት እና መቅበዝበዝንም/መንቀዥቀዥ ውስጥም ይከታቸውል እንዲሁም ምርታቸው ላይ የመቆራረጥ ሁኔታንም ያስከትላል። መኖ መቀየር ካለብህ የለመዱትን 75% አዲሱን 25% ከዛ 50% በ50% እያልክ ቀስ በቀስ በሽግግር ቀይርላቸው። 6. ከዶሮዎችህ አጠገብ ውሃ እንዳይለይ። ውሃ ህይወት ነው። ዶሮ ያለምግብ ቀነት መቆየት ትችላለች: የለውሃ ግን ሰዓታት ብቻ በቂ ናቸው። ውሃ በአግባቡ ያለገኙ ዶሮዎች በሙቀት ለሚመጣ ጭንቀት ይዳረጋሉ: ይበላላሉ: ይሞታሉ። ሁልጊዜ ያለመሰልቸት ንፁህ ውሃ አቅርብላቸው: በግማሽ ቀን ውስጥ ቀይርላቸው። 7.ለዶሮዎችህ የምትሰጠው ውሃ አንተ የምትጠጣው ይሁን። ውሃ ወለድ በሽታዎች በጣም ሃይለኛ ሲሆኑ ለመቆጣጠርም ከባድ ነው። የውሃው ንፅህና አንተ የማትጠጣው ከሆነ ዶሮዎችህንም አታጠጣ። ንፁ የሆነ ውሃ ለዶሮዎችህ ጤና ረዦም እድሜ እና ጥንካሬ ይሰጣቸዋል። 8.ንፁ አካባቢን ፍጠርላቸው። የቆሸሸ እና ኩስ የተከመረ የዶሮ ቤት ቅንቅን ያፈራል። መሬታቸውም እርጥብ ከሆነ ለኢንፌክሽን ይዳርጋቸዋል። ቤታቸውን ንፁ አድርግ: መሬቱ ደረቅ ይሁን: አየር እና ብርሃን በበቂ ሁኔታ መግባትም አለበት። 9. ዶሮዎችህን በትህትና ያዛቸው። ዶሮ ቤት ውስጥ ስትገባ ይከቡሃል ይከተሉሃል በዚያን ጊዜ ዶሮዎችህን በመሰላቸት በካልቾ እያልክ እና በመጥረጊያ እየጨረገድክ እንዲሁም በጭካኔ የምታስተዳድር ከሆነ ትጎዳቸዋለህ:ማህፀናቸው ውስጥ እንቁላል ትሰብራለህ እንዲሁም ለደካማ ውጤት ትዳረጋለህ። 10. ለቀጣዮ እርምጃ ቀድመህ አቅድ። የዶሮ እርባታ እቅድ የሚጀምረው ዶሮዋ ፋርም ከመግባቷ በፊት ነው። 🌾የመኖ ቅድመ ዝግጅት አድርግ። 🌾ክትባቶችን ከድመህ አዘጋጅ በተለይ የፈንግል። 🌾ዝግጁ ከሆንክ ወረርሺኝ ገባ ስትባል መራወጥ አይጠበቅብህም። 🌾ዶሮዎችህ የዕንቁላልም ሆኑ የስጋ ለቀጣይ ገበያ ቀድመህ ዝግጁ ሁን። እንቁላል ከመጀመራቸው በፊት ሊኖርህ የሚችለውን ሳምንታዊ ምርት ገምተህ የገበያ ቅድመ ትስስር ፍጠር። ምርት ከተጠራቀመ በኋላ አትስተጓጎል። ዝግጁ መሆን ጊዜ: ጉልበት እና ገንዘብ ያተርፍልሃል። የዶሮ እርባታ ስራ ዘርፍ ጠንቃቃ የሆኑትን: እራሳቸውን ለስራው አሳልፈው የሚሰጡትን እና ትዕግስተኞችን ይሸልማል። ''አንተ የማትጠጣውን ውሃ ለዶሮዎችህ አትስጥ'' @AgriLancer

⚡️10 የዶሮ እርባታ ህጎች
⚡️10 የዶሮ እርባታ ህጎች

⚡️ዝናብ ሳይጀምር የመኖ አዝዕርቶን ይዝሩ 🌾የዘር አይነቶች 1.Alfalfa ( አልፋአልፋ) 2.Rhodes Grass (ረሆደስ/ክሎሪስ ጎያና) 3.Sudan grass (የሱዳን ሳር) 4.Vetch (ቬች
⚡️ዝናብ ሳይጀምር የመኖ አዝዕርቶን ይዝሩ 🌾የዘር አይነቶች 1.Alfalfa ( አልፋአልፋ) 2.Rhodes Grass (ረሆደስ/ክሎሪስ ጎያና) 3.Sudan grass (የሱዳን ሳር) 4.Vetch (ቬች) 5.Oat (የአጃ ዘር) 6.Palaris (ፓላሪስ) 7.Desmudium (ጭሜሮ) 8.Pigeon pea (የእርግብ አተር) 9.Lab lab ( አሞራ ጓያ) 10.Coro pea (ኮሮ አተር) 11.Sesbania (ጊራንጊሬ) 12.Leucine (ሉሲኒያ) 13.Tree lucern (የሉስረን ዛፍ) 📌ትንሹ ትዕዛዝ 5 ኪሎ ዘር ይደውሉ +251913323845 Email yonatan.lancer@gmail.com @AgriLancer

⚡️የአመቱ የመጨረሻ ትውልድ የ 2 ወር የኮኮክ ፑሌቶች 🌾ወደ አዲስ አበባ ነፃ ትራንስፖርት 🌾ዋጋ 450 ብር ብቻ 🌾ትዕዛዝ 50 እና ከዛ በላይ The Agri-Lancer

የዶሮ ቤት (Cage System) በኢትዮጵያ ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ፣ በተለይም የእንቁላል አምራች ዶሮዎችን በብቃት ለማርባት የሚረዳ ዘዴ ነው። ይህ ሥርዓት በተለይ በመሬት ጥበት እና በምግብ ብክነት ምክንያት የሚመጡ ኪሳራዎችን በመቀነስ በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። በተለይም በከተማ እና በአካባቢው (Peri-urban) ቦታ በሌለበት፣ ዶሮዎችን በአቀባዊ (Vertical) 3 ወይም 4 እርከን በመደርደር በአነስተኛ ቦታ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዶሮዎች ማርባት ያስችላል። ይህን H type ዘመናዊ ኬጅ አሁንም ለማህበረሰቡ እያቀረብን እንገኛለን። @AgriLancer

✨Cow mat/ የከብቶች አልጋ ለከብቶች ተስማሚ የሆነ የመኝታ ቦታ (Bedding) ማዘጋጀት የወተት ምርታማነትን ለመጨመር፣ የከብቶችን ጤና ለመጠበቅ እና የውጥረት ስሜትን ለመቀነስ ወሳኝ ሚና አለው
✨Cow mat/ የከብቶች አልጋ ለከብቶች ተስማሚ የሆነ የመኝታ ቦታ (Bedding) ማዘጋጀት የወተት ምርታማነትን ለመጨመር፣ የከብቶችን ጤና ለመጠበቅ እና የውጥረት ስሜትን ለመቀነስ ወሳኝ ሚና አለው። የመኝታ ምቾታቸው ያልተጠበቀ የወተት ላሞች መስጠት ከሚችሉት አቅማቸው ከ 20% እስከ 50% ዝቅ አድርገው ነው ምርት የሚሰጡት። ከህንድ ያስገባነው ራበር ማት እጅግ በጣም ምቹ እና ለማፅዳት ቀላል በመሆኑ ብዙ ደንበኞቻችን ከሞከሩት በኋላ ደጋግመው እየወሰዱ ይገኛሉ። እርሶም ይውሰዱ 🌾ርዝመት 👉1.85×1.25 🌾ቅጥነት👉 1.5cm 🌾ክብደት 👉 35 ኪሎ 🪡ከህንድ የገባ ዋጋ ✅16,900 ከነ ቫቱ ይደውሉ +251913323845 @AgriLancer

የላም ጡት በሽታ (Mastitis) በኢትዮጵያ የወተት ላም እርባታ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ኪሳራ ያስከተለ እና አርቢውን ያማረረ የጡት እብጠት በሽታ ነው። በሽታው በንፅህና ጉድለት በባክቴሪያ አማካኝነት የሚመጣ መሆኑን በቀደመው ፅሁፍ ተመልክተናል። ቅድሚያ ምልክት ሳያሳይ ወተት የሚቀንስ (Subclinical) ወይም ግልጽ የሆነ እብጠትና የወተት መበላሸት የሚያሳይ (Clinical) ሊሆን ይችላል። የበሽታውን መነሻ፣ ምልክቶች፣ የሕክምና ዘዴዎች እና መከላከያ መንገዶችን እንመልከት። የጡት በሽታ ምልክቶች የወተት መለወጥ፦ ወተቱ ሲታለብ መርጋት፣ ውሃ መምሰል፣ መቅላት ወይም መጥቆር። የጡት መለወጥ፦ የላሟ ጡት ማበጥ፣ መቅላት፣ መጋል (ሙቀት) እና ሲነካ መጥመም (ህመም ማሳየት)። የላሟ አጠቃላይ ጤና፦ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ትኩሳት እና መዛል። የላም ጡት ማቅለጥ ሕክምና (Treatment) ሕክምና ከመጀመርዎ በፊት ሁልጊዜ ከአካባቢዎ የእንሰሳት ሐኪም ጋር መማከርና ትክክለኛውን መድኃኒት መምረጥ ተገቢ ነው። ዋና ዋናዎቹ የሕክምና እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦ አንቲባዮቲክስ በጡት ቀዳዳ ማስተላለፍ (Intramammary Infusion) የታመመውን የላም ጡት በደንብ አልቦ ጨርሶ ማድረቅ። የጡቱን ጫፍ በ70% አልኮሆል (የሕክምና አልኮሆል) በደንብ ማፅዳት። ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የአንቲባዮቲክ መድኃኒት (ለምሳሌ Cephapirin Sodium ወይም Amoxicillin) ቱቦ ጫፍ በጥንቃቄ ወደ ጡቱ ቀዳዳ ማስገባት። መድኃኒቱን ከጭመቁ በኋላ ወደ ላይኛው የጡት ክፍል በረገገ እጅ ማሸት። በመርፌ የሚሰጥ ሕክምና (Systemic Antibiotics) በሽታው ከአንድ በላይ ጡት ላይ ከበዛ ወይም ላሟ ከፍተኛ ትኩሳት ካላት ሐኪሙ በጡንቻ ወይም በደም ስር የሚሰጥ መርፌ ያዝዛል። የሕመም ማስታገሻና እብጠት መቀነሻ (Anti-inflammatory) መድኃኒቶች አብረው ሊሰጡ ይችላሉ። የተፈጥሮ እና የቤት ውስጥ እንክብካቤ ተደጋጋሚ ማለብ፦ የታመመውን ጡት በቀን ከ3 እስከ 4 ጊዜ አልቦ ወተቱን ማፍሰስ ባክቴሪያው እንዲቀንስ ይረዳል። በረዶ ወይም ሙቅ ውሃ መጫን፦ እብጠቱን ለመቀነስ ንጹህ ጨርቅ በበረዶ ውሃ በመንከር ጡቱ ላይ መጫን። ማግለል፦ የታመመችውን ላም ከሌሎች ጤነኛ ላሞች ለይቶ ማቆየት። የመከላከያ ዘዴዎች (Prevention & Control) የጡት ማቅለጥን ለማከም ከሚወጣው ወጪ የመከላከያው መንገድ በጣም ርካሽና ውጤታማ ነው። የአለባብ ቅደም ተከተል፦ ሁልጊዜ መጀመሪያ ጤነኛ የሆኑ ወጣት ላሞችን አልቦ፥ የታመሙትን ወይም ሕክምና ላይ ያሉትን መጨረሻ ላይ ማለብ። ንጽህናን መጠበቅ፦ ከመታለቡ በፊት የላሟን ጡት በንጹህ ውሃ ታጥቦ በደረቅ ጨርቅ ማድረቅ። እያንዳንዱ ላም የራሷ መጥረጊያ ጨርቅ ሊኖራት ይገባል። ከማለብ በኋላ ጡትን መንከር (Post-Milking Teat Dipping)፦ ላሟ ታልባ እንደተጠናቀቀች የጡቷን ጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የፀረ-ባክቴሪያ ፈሳሽ (ኬሚካል) ውስጥ መንከር። የበረቱ ንጽህና፦ ላሞቹ የሚተኙበት ወለል ደረቅ፣ ንጹህና ከእርጥበት የጸዳ መሆኑን ማረጋገጥ። ማሳሰቢያ፦ በአንቲባዮቲክ የታከመች ላም ወተት ለሰው ልጅ ፍጆታ መዋል የለበትም። መድኃኒቱ ከሰውነት እስኪወጣ ድረስ (Withholding Period) ወተቱን ለይቶ ማፍሰስ ግዴታ ነው። @AgriLancer

⚡️ማሲታይተስ Treatment ፅሁፍ.2
⚡️ማሲታይተስ Treatment ፅሁፍ.2

⚡️የዶሮ ኬጅ ሙሉ ለሙሉ ብረት ስሪት የሆነ እና በተለያየ መጠን የቀረበ። 📌እንቁላል የሚያንሸራትት 📌 የኩስ ማውጫ ፓትራ ያለው/ለማፅዳት ቀላል የሆነ 📌ለዘመናት የሚቆይ 📌መመገቢያ እና መጠጫ
⚡️የዶሮ ኬጅ ሙሉ ለሙሉ ብረት ስሪት የሆነ እና በተለያየ መጠን የቀረበ። 📌እንቁላል የሚያንሸራትት 📌 የኩስ ማውጫ ፓትራ ያለው/ለማፅዳት ቀላል የሆነ 📌ለዘመናት የሚቆይ 📌መመገቢያ እና መጠጫ የተገጠመለት 📌በቅድመ ትዕዛዝ ዋጋ በዶሮ ቁጥር ባለ 5 ዶሮ ቤት 10,500 ብር ባለ 10 ዶሮ ቤት  19,500 ብር ባለ 15 ዶሮ ቤት 26,000 ብር ባለ 20 ዶሮ ቤት 30,000 ብር ባለ 30 ዶሮ ቤት 38,000 ብር ባለ 40 ዶሮ ቤት 45,000 ብር ባለ 60 ዶሮ ቤት 58,000 ብር ባለ 80 ዶሮ ቤት 68,000 ብር ባለ 120 ዶሮ ቤት 80,000 ብር ባለ 160 ዶሮ ቤት 90,000 ብር Contact number+251913323845 Email yonatan.lancer@gmail.com @AgriLancer

ከከተማ ውጪ ያላቹ ከብት አርቢዎች ልክ እንደከተማ ግብርና መጋዘን መሰል ዝግ ሼዶችን በፎፁም መጠቀም የለባችሁም። በምስሉ ላይ በምትመለከቱት መልኩ የሚሰሩ ቀላል በረቶች በከፍተኛ ሁኔታ ወጪ ከመቀነስ በተጨማሪ ለወተት ለከብቶች እጅግ በጣም ተፈጥሮአዊ እና ምቹ ናቸው። በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ የተሻሻሉ የወተት ላሞች (እንደ ሆልስታይን ፍሪዢያንና ክሮስ ብሬድ) ከፍተኛ ሙቀት ባለባቸው ወቅቶች ለከባድ የሙቀት ጭንቀት (Heat Stress) ይጋለጣሉ። ክፍት የአየር ጥላ ሥርዓት በረቶች (Open Air Shade System) በወተት ላሞች እርባታ ላይ የሚከተሉት በርካታ ጥቅሞች አሉት። 1. የሙቀት ጭንቀትን መቀነስ (Reducing Heat Stress) ጥላ ማግኘት የላሞቹን የሰውነት ሙቀትና የትንፋሽ ፍጥነት ይቀንሳል። ንጹህ አየር ዝውውር: ክፍት ዲዛይኑ የተፈጥሮ ነፋስ በነፃነት እንዲዘዋወር በማድረግ አካባቢውን ያቀዘቅዛል። 2. የወተት ምርትንና ጥራትን መጨመር (Improving Milk Production) በሙቀት ምክንያት የሚቀንሰውን የወተት ምርት እስከ 7.5% - 10% ያድናል። የምግብ ፍላጎት መጨመር: ላሞች ቀዝቃዛ ጥላ ሲያገኙ የምግብ አወሳሰዳቸውና የመብላት ፍላጎታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። 3. የወሊድና የርባታ ብቃትን ማሻሻል (Enhancing Fertility) የሙቀት ጭንቀት ሲቀንስ የላሞች የፅንስ መያዝ (Conception Rate) ብቃት ይጨምራል። የእንቁላል እድገት ማስተካከል: ከመጠን ያለፈ ሙቀት በእንቁላል (Follicle) እድገት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ይከላከላል። 4. የወተት ላሞችን ጤንነትና ደህንነት መጠበቅ (Animal Welfare & Health) ጥላ ማግኘታቸው የላሞቹን በሽታ የመከላከል አቅም (Immunity) ያጠናክራል። የባክቴሪያ ስርጭትን መቀነስ: ተንቀሳቃሽ ወይም ሰፊ ክፍት ጥላዎች ፍግና ጭቃ በአንድ ቦታ ላይ እንዳይከማች በማድረግ የጡት በሽታን (Mastitis) ይከላከላሉ። ክፍት የአየር ጥላ ሥርዓት ሲገነባ ሊታሰቡ የሚገቡ ነጥቦች መስፈርት የሚመከር መመሪያ የጥላ ስፋት ለአንድ ላም ቢያንስ ከ3.6 እስከ 4 ስኩዌር ሜትር የጥላ ቦታ ያስፈልጋል። የጥላው ከፍታ ቁመቱ ከ5 ሜትር እስከ 8 ሜትር መሆን አለበት (ከፍተኛ ጥላ ለአየር ዝውውር ይመረጣል)። አቅጣጫ ጥላው ከምስራቅ ወደ ምዕራብ (East-West) እንዲጋርድ ተደርጎ መገንባት አለበት። በበረቱ ዙሪያ መረሳት የሌለባቸው ተጨማሪ ቤቶች 🌾የመኖ ስቶር 🌾የውሃ ታንከር ወይንም ጉድጓድ 🌾የጥጃ ክፍል 🌾የሰራተኛ ክፍል 🌾ማለቢያ ክፍል 🌾ወተት ማጠራቀሚያ ክፍል እንዲሁም በረቱ ዙሪያ በቂ መሬት ካለ ለሳይሌጅነት የሚውል የበቆሎ ዘርን እና ሌሎች ለወተት ከብት አስፈላጊ የሆኑ የመኖ አዝዕርቶችን መጠቀም። የከብቶቹን ፍግ በበረቱ ዙሪያ ላለው ለዚሁ እርሻ እንደ ማዳበሪያነት በማዋል ስነምህዳርን የጠበቀ ውጤታማ እርባታን ማሳለጥ አስፈላጊ ነው። @AgriLancer

⚡️ከከተማ ውጪ የሚሰራ በረት
⚡️ከከተማ ውጪ የሚሰራ በረት