ru
Feedback
The AgriLancer

The AgriLancer

Открыть в Telegram

''Animal Farming Entrepreneur'' በወተት ከብት እርባታ | ዶሮ እርባታ | በቁም እንስሳት የመኖ ዘሮች እና የእርባታ ቁሳቁስ ቴክኖሎጂዎች ስፔሻላይዝ ያደረገ! ስለ AgriLancer ማብራሪያ introduction ያንብቡ 👉https://t.me/agrilancer/1455

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала The AgriLancer

Канал The AgriLancer (@agrilancer) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 25 621 подписчиков, занимая 2 503 место в категории Бизнес и 1 311 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 25 621 подписчиков.

Согласно последним данным от 01 июля, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило -93, а за последние 24 часа — -17, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 22.22%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 8.17% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 5 693 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 094 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 15.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
''Animal Farming Entrepreneur'' በወተት ከብት እርባታ | ዶሮ እርባታ | በቁም እንስሳት የመኖ ዘሮች እና የእርባታ ቁሳቁስ ቴክኖሎጂዎች ስፔሻላይዝ ያደረገ! ስለ AgriLancer ማብራሪያ introduction ያንብቡ 👉https://t.me/agrilancer/1455

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 02 июля, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Бизнес.

25 621
Подписчики
-1724 часа
-387 дней
-9330 день
Архив постов
Repost from The AgriLancer
⚡️ዘመናዊ H type የዶሮ ኬጅ ሙሉ ለሙሉ ብረት/Galvanized ስሪት የሆነ እና በተለያየ መጠን የቀረበ። 📌እንቁላል የሚያንሸራትት 📌 ለማፅዳት ቀላል የሆነ 📌ለዘመናት የሚቆይ 📌መመገቢያ እና መጠጫ የተገጠመለት 📌በቅድመ ትዕዛዝ ዋጋ በዶሮ ቁጥር ባለ 5 ዶሮ ቤት 10,500 ብር ባለ 10 ዶሮ ቤት  19,500 ብር ባለ 15 ዶሮ ቤት 26,000 ብር ባለ 20 ዶሮ ቤት 30,000 ብር ባለ 30 ዶሮ ቤት 38,000 ብር ባለ 40 ዶሮ ቤት 45,000 ብር ባለ 60 ዶሮ ቤት 58,000 ብር ባለ 80 ዶሮ ቤት 68,000 ብር ባለ 120 ዶሮ ቤት 80,000 ብር ባለ 160 ዶሮ ቤት 90,000 ብር 🪡ኬጅ ለሚያዙን ደንበኞች የዲካልብ ዋይት የእንቁላል ቄቦችንም እናቀርባለን:: Contact number+251913323845 Email yonatan.lancer@gmail.com @AgriLancer

በዶሮ እርባታ ቦታዎች (poultry farm) የበሽታ አምጭ ተህዋስያን በቀላሉ ሊገቡ የሚችሉት በአዲስ ዶሮዎች፣ በሰዎች፣ በተሽከርካሪዎች፣ በመኖ እና ውሃ፣ እንዲሁም በዱር አእዋፍና አይጦች አማካኝነት ነው። በቂ የጥንቃቄ እርምጃዎችን(Biosecurity) ባለመውሰድ እነዚህን መንገዶች መቆጣጠር ትልቅ የገንዘብ ኪሳራ ያስከትላል። ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች መመልከት ይችላሉ። የዶሮ በሽታዎች ወደ እርባታ ቦታዎ የሚገቡባቸው ዋና ዋና መንገዶች በዶሮ እርባታ ውስጥ የስነ-ህይወት ደህንነት (Biosecurity) ማለት በሽታ አምጭ ተህዋስያን (ቫይረስ፣ ባክቴሪያ፣ ፈንገስ እና ጥገኛ ተህዋስያን) ወደ እርባታው ቦታ እንዳይገቡና እንዳይዛመቱ የምንቆጣጠርበት መንገድ ነው። በሽታ በዋናነት በሚከተሉት መንገዶች ወደ ውስጥ ይገባል፡ 1. በአዲስ ዶሮዎች አማካኝነት ከሌላ ቦታ የሚገዙ አዲስ ዶሮዎች ከበሽታ ነጻ መሆናቸውን አለማረጋገጥ፤ አዲስ የገቡ ዶሮዎችን ከቀድሞዎቹ ዶሮዎች ጋር በአንድነት ወዲያውኑ ማቀላቀል። 2. በሰዎች አማካኝነት (እርሻ ጎብኝዎችና ሰራተኞች) በበሽታ በተያዙ እርባታዎች የተዘዋወሩ ሰዎች ንጹህ ልብስና ጫማ ሳይቀይሩ የእርባታ ቦታዎን ሲጎበኙ፤እርሻው መግቢያ ላይ የእግር ማጠቢያ ገንዳ (Footbath) አለመጠቀም። 3. በተሽከርካሪዎች አማካኝነት መኖ የሚያመላልሱ፣ እንቁላል የሚጭኑ ወይም የሌሎች እርሻዎችን እቃዎች የሚያጓጉዙ መኪኖች ንጽህናቸውን ሳይጠብቁ በቀጥታ ወደ እርሻው ግቢ መግባት። 4. በመኖ እና በውሃ አማካኝነት መኖ ከተለያዩ ተባዮች (አይጥ፣ በረሮ) ወይም ወፎች በተበከለ ቦታ ሲዘጋጅ ወይም ሲከማች፤ ንጽህናው ያልተጠበቀ ወንዝ፣ ኩሬ ወይም ዝናብ ውሃ ለዶሮዎች መጠጫ መጠቀም። 5. በዱር አእዋፍ እና ተባዮች አማካኝነት እንደ ርግቦች፣ ድንቢጦች እና ሌሎች የዱር አእዋፍ ወደ ዶሮ ቤቶች በቀላሉ ሲገቡ፤ አይጦች፣ ዝንቦች እና ሌሎች ተባዮች ወደ መኖ ማከማቻ እና ዶሮ ቤት መግባታቸው። 6. በበሽታው በተያዙ እቃዎች ባለፈው ዶሮዎች የቆዩበትን መሣሪያ (እንደ መፈንገሻ፣ የውሃ እቃ) በደንብ ሳያጸዱና ሳያፀዱ ለአዲሶቹ ዶሮዎች መጠቀም። በሽታን ለመከላከል መወሰድ ያለባቸው ዋና ዋና እርምጃዎች 🌾የአጥር እና መግቢያ ቁጥጥር፡ እርሻዎ ግቢ አጥር እንዲኖረው ማድረግ። መግቢያ ላይ ሰራተኞች እና ጎብኝዎች የሚለብሱትን ልብስ የሚቀይሩበት እንዲሁም እግራቸውን በፀረ-ተህዋሲያን የሚያጥቡበት ሁኔታ ማመቻቸት። 🌾የተባዮች ቁጥጥር፡ የዱር አእዋፍ ወደ ዶሮ ቤት እንዳይገቡ መረብ ማድረግ። አይጥ እና ሌሎች ተባዮችን መቆጣጠር። 🌾የአዳዲስ ዶሮዎች መለያየት፡ አዲስ የሚገቡ ዶሮዎችን ቢያንስ ለ 21 ቀናት ከቀደምት ዶሮዎች ለይቶ ማቆየት። 🌾ክትባት እና ንፅህና፡ የዶሮዎችን የክትባት ጊዜ እና መድሃኒት መረጃ በቋሚነት መዝግቦ መያዝ። የዶሮ ቤትና እቃዎች በየጊዜው በፀረ-ተህዋሲያን (Disinfectants) ማጽዳት። @AgriLancer

⚡️በሽታ እንዴት ወደ ዶሮ እርባታ ሊገባ ይችላል ?
⚡️በሽታ እንዴት ወደ ዶሮ እርባታ ሊገባ ይችላል ?

✨Cow mat/ የከብቶች አልጋ ርዝመት 👉1.85×1.25 ቅጥነት👉 1.5cm ክብደት 👉 35 ኪሎ 🪡ከህንድ የገባ ዋጋ ✅16,900 ከነ ቫቱ ይደውሉ +251913323845 @AgriLancer
✨Cow mat/ የከብቶች አልጋ ርዝመት 👉1.85×1.25 ቅጥነት👉 1.5cm ክብደት 👉 35 ኪሎ 🪡ከህንድ የገባ ዋጋ ✅16,900 ከነ ቫቱ ይደውሉ +251913323845 @AgriLancer

ለወተት ላም አርቢዎች ከወተት ሽያጭ በተጨማሪ ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ በፋርም ውስጥ የሚሰሩ የንግድ ሀሳቦች ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በኢትዮጵያ የወተት ፍላጎት በየጊዜው እያደገ በመምጣቱ፣ ከአርቢው ህብረተሰብ የሚጠበቀው የወተት ምርት ከፍ ብሏል። ይሁን እንጂ የወተት ሽያጭ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ የተገደበ ገቢ ላይ ጥገኛ ስለሚያደርግ ከወተት ሽያጭ ጎን ለጎን የሚከተሉትን ስልቶች በመጠቀም የገቢ ምንጮን ማሳደግ ይችላሉ። 1. የወተት ተዋጽኦዎችን አቀነባብሮ መሸጥ (Value Addition) እርጎ፣ ቅቤ እና አይብ ማዘጋጀት፡ የተጣራ ወተት በቀጥታ ከመሸጥ ይልቅ፣ በአካባቢው ገበያ የሚፈለጉትን የወተት ተዋጽኦዎች ማለትም እርጎ፣ ባህላዊ ቅቤ ወይም አጎንብሶ የተሰራ አይብ በማዘጋጀት ማቅረብ ከፍተኛ ትርፍ ያስገኛል። 2. ማዳበሪያና ባዮ-ጋዝ ማምረት (Manure and Bio-gas) የኦርጋኒክ ማዳበሪያ (ኮምፖስት) ሽያጭ፡ ከብቶች የሚያወጡትን እበት እና ሽንት በመሰብሰብ የደረቀ ጥራት ያለው ማዳበሪያ አዘጋጅተው ለአትክልት አብቃዮች ወይም ለጓሮ አትክልት መሸጥ። ባዮ-ጋዝ (Bio-gas): የከብት እበትን በመጠቀም ለቤተሰብዎ የሚሆን የሃይል/ጋዝ አቅርቦት ማመንጨት ይችላሉ። 3. የጥጆችና የእንስሳት እርባታ (Calf Rearing and Fattening) የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው ጥጆችን መሸጥ፡ በጥሩ ዝርያ የተዳቀሉ የወተት ጊደሮችን በማሳደግ እና ለገበያ በማቅረብ ወይም ለሌሎች አርሶ አደሮች በመሸጥ ገቢ ማግኘት ይቻላል። የከብት ማድለብ፡ የእርሻ ቦታዎን በመጠቀም ወተት መስጠት ያቆሙ ላሞችን እና የተወለዱ ወንድ ጥጆችን በጥሩ መኖ በማድለብ ለስጋ ገበያ ማቅረብ። 4. ቦታ ካሎት መኖ ማልማትና ማቀነባበር (Fodder Production and Processing) የተሻሻሉ የመኖ ዝርያዎችን ማዘጋጀት፡ እንደ አጃ (Oats)፣ ሮድስ ሳር (Rhodes grass) እና ሳይሌጅ የመሳሰሉ መኖዎችን በማልማት እንዲሁም ለክረምት የሚሆን ደረቅ ሳር (Hay) በመጫን ለሌሎች አርሶ አደሮች መሸጥ። 5. የወተት ማቀዝቀዣና መሰብሰቢያ ጣቢያ (Milk Collection & Chilling) የአካባቢው አርቢዎች ማዕከል መሆን፡ በአካባቢዎ ካሉ አነስተኛ አርቢዎች ወተት በመሰብሰብ እና በዘመናዊ ማቀዝቀዣዎች በማቆየት ለትላልቅ አቀነባባሪ ፋብሪካዎች ማቅረብ። 6. በእርባታ ተቋም ውስጥ ስልጠናዎችን እና የማስጎብኘት ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት(Training & Agri tourism) ብቃት ያለው ባለሙያን በመመደብ እና በፋርም ውስጥ የቡና ስነስርዓቶችን በማዘጋጀት ወደስራው የመግባት ፍላጎት ያለቸው እና እውቀት መቅሰም የሚፈልጉ ሰዎችን በክፍያ ትምህርታዊ ጉብኝት በመስጠት እና በማስተናገድ ለፋርሙ ተጨማሪ ገቢን መፍጠር ይቻላል። @AgriLancer

⚡️ከወተት ሽያጭ በተጨማሪ የገቢ ምንጭ ይፍጠሩ
⚡️ከወተት ሽያጭ በተጨማሪ የገቢ ምንጭ ይፍጠሩ

⚡️የከብት አርቢዎችን ስራ ያቀለለ ✨ትራፕ የመኖ ማቀነባበሪያ ቾፐር @AgriLancer

⚡️ረሆደስ ዘር (ክሎሪስ ጉያና) 🪡የ1 ኪሎ ዘር ዋጋ 1,800 ብር Contact number+251913323845 Email yonatan.lancer@gmail.com @AgriLancer
⚡️ረሆደስ ዘር (ክሎሪስ ጉያና) 🪡የ1 ኪሎ ዘር ዋጋ 1,800 ብር Contact number+251913323845 Email yonatan.lancer@gmail.com @AgriLancer

ብዙ ሰው ለእርባታ ስራ ገንዘብ እና ቦታ ብቻ የሚያስፈልግ ይመስለዋል። ግን እሱ ብቻ በቂ አይደለም። የወተት ላሞ እርባታ እና የዶሮ እርባታ ሥራ ከመጀመራቸው በፊት እና በሂደቱ ውስጥ ሊኖሩ የሚገባቸውን ስነ-ልቦናዊ ዝግጅቶች እና አመለካከቶች ወሰኝ ናቸው። የእንስሳት እርባታ ከፍተኛ ትዕግስት፣ ትጋት እና ሳይንሳዊ አቀራረብ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ከአካላዊ ዝግጅት በተጨማሪ የአእምሮ ዝግጅት ወሳኝ ነው። 1. የወተት ላሞች እርባታ ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት የወተት ላሞች እርባታ "ቋሚ ሥራ" በመሆኑ እና ምርቱ በየቀኑ የሚገኝ በመሆኑ ለየት ያለ ስነ-ልቦና ይጠይቃል።  ለቋሚ ቁርጠኝነት መዘጋጀት፡ ላሞች በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት መታለብ፣ መመገብ እና መንከባከብ አለባቸው። ይህ በዓመት 365 ቀናት ያለዕረፍት የሚደረግ ስራ በመሆኑ፣ አርቢው ለረጅም ጊዜ ስራውን የማያቋርጥ ቁርጠኝነት ሊኖረው ይገባል። የትዕግስት እና የእንስሳት ፍቅር፡ ላሞች ተንቀሳቃሽ ፍጡራን በመሆናቸው ስሜታዊ እንክብካቤ ይፈልጋሉ። በጭንቀት መያዝ፣ አለመታዘዝ ወይም መታመም ሊያጋጥም ስለሚችል፣ አርቢው ተረጋግቶ ችግሮችን የመፍታት ትዕግስት ሊኖረው ይገባል። የቀውስ አስተዳደር (Resilience)፦ የምግብ እጥረት፣ የመኖ ዋጋ መጨመር፣ የበሽታ መከሰት እና የገበያ መዋዠቅ እንደ ዋና ተግዳሮቶች ይታያሉ። እነዚህን ችግሮች ሲያጋጥሙ ተስፋ ሳይቆርጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የመፈለግ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል። ንጽህናን ማክበር፡ የወተት ተዋጽኦዎች ጥራት እንዲኖራቸው የላሞቹ ቤት እና አርቢው እራሱ ንጽህናን የማክበር ከፍተኛ ስነ-ልቦና ሊኖረው ይገባል።  2. የዶሮ እርባታ ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት የዶሮ እርባታ በተለይም ዘመናዊው ስልት ፈጣን የእድገት መጠን ያላቸውን ዶሮዎች የሚያካትት በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይፈልጋል።  ለዝርዝር ሁኔታዎች ትኩረት መስጠት (Attention to Detail)፦ ዶሮዎች ለሙቀት፣ ለአየር ዝውውር እና ለበሽታ በጣም ስሜታዊ ናቸው። የዶሮ ቤት ንጽህና፣ የሙቀት መጠን እና የመብራት አቅርቦት ላይ የሰዓት ጥበቃ ማድረግን ይጠይቃል። ሳይንሳዊ አቀራረብን መከተል፡ ባሕላዊውን የእርባታ ዘዴ ትቶ ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ስራን ለመተግበር የሚፈልግ አርቢ፣ በአመጋገብ፣ በክትባት እና በበሽታ መከላከል ዙሪያ አዳዲስ እውቀቶችን ለመቀበል ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት ሊያደርግ ይገባል። የአደጋ ተጋላጭነትን መቀበል፡ የዶሮ በሽታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ መላውን እርባታ ሊያጠፉ ይችላሉ። ስለዚህ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ እና የባዮሴኪዩሪቲ (Biosecurity) መመሪያዎችን በመከተል የሚመጣውን አደጋ ለመቀነስ ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል።  3. ለሁለቱም እርባታዎች የሚረዱ አጠቃላይ ስነ-ልቦናዊ ነጥቦች ትምህርትን መቀበል፡ በወተት እና በዶሮ እርባታ ዘመናዊ የሙያ ብቃት (Skills, Knowledge, and Attitude) የሚጠይቁ ስልጠናዎች ላይ መሳተፍ እና የሚሰጡትን መመሪያዎች ለመተግበር ፈቃደኛ መሆን። ጥናታዊ አቀራረብ፡ የእንስሳት መረጃን መመዝገብ (Performance Recording)፣ የምግብ አዘጋገብ መከታተል እና የሚመጣውን ትርፍ እና ኪሳራ በንቃት መከታተል። ከትዕግስት ጋር መሥራት፡ የእንስሳት ምርታማነት በአንድ ጊዜ አይጨምርም። በሂደት የሚመጣን ለውጥ ማመን እና የተሻለ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን መከተል።  ማጠቃለያ የወተት እና የዶሮ እርባታ ስኬታማ የሚሆነው በእውቀት ላይ የተመሰረተ (ቴክኒካል) እና አእምሮአዊ ዝግጅት (ስነ-ልቦናዊ) ጥምረት ሲኖር ነው። አርቢው ለእንስሳቱ ፍቅር ያለው፣ ንጽህናን የሚያከብር፣ ተግዳሮቶችን በቋሚነት የሚቋቋም እና አዳዲስ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን የሚተገብር መሆን አለበት። @AgriLancer

⚡️የእርባታ ስራ እና ስነልቦናዊ ዝግጁነት
⚡️የእርባታ ስራ እና ስነልቦናዊ ዝግጁነት

⚡️ማለቢያ ማሽን ዋጋ ማስተካከያ ተደርጓል ✨ብራንድ Barbaros/ባርባሮስ ✨ቱርክ ሰራሽ/Made in Turkish ✨ሲንግል ፌዝ ኤሌክትሪክ 📌ሁለት ላም አንዴ የሚያልብ ማሽን አንድ ባለ 40 ሊትር
⚡️ማለቢያ ማሽን ዋጋ ማስተካከያ ተደርጓል ✨ብራንድ Barbaros/ባርባሮስ ✨ቱርክ ሰራሽ/Made in Turkish ✨ሲንግል ፌዝ ኤሌክትሪክ 📌ሁለት ላም አንዴ የሚያልብ ማሽን አንድ ባለ 40 ሊትር ወተት ማጠራቀሚያ ኮንቲነር ያለው ✅ዋጋ 182,911 ብረ ከነ ቫቱ 📌ሁለት ላም አንዴ የሚያልብ ከሁለት ባለ 30 ሊትር ወተት ማጠራቀሚያ ኮንቲነር ጋር ✅ዋጋ 204,750 ብር ከነ ቫቱ ይደውሉ +251913323845 #ማስታወሻ:- ማለቢያ ማሽን የሚገዛ ማንኛውም ደንበኛ የግብርና ስራ ፈቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ናሽናል መታወቂያ ኮፒ አድርጎ ማምጣት አለበት። @AgriLancer

የላም ንጣፎች/የከብቶች መኝታ (Cow Mats) የወተት ላሞችን ጤና ለመጠበቅ፣ የተሻለ የእረፍት ጊዜ እንዲያገኙ እና የወተት ምርታማነትን ለማሳደግ እጅግ ወሳኝ ሚና አላቸው። የላም ንጣፍ (Cow Mat) በወተት ላሞች እርባታ የሚሰጠው ፋይዳ: የላም መኝታ ምቾት እና የምርት መጨመር፡ ላሞች በቀን ቢያንስ ለ 12 ሰዓታት ያህል መተኛት እና ማረፍ አለባቸው። ጠንካራ የሲሚንቶ ወለል ላሞችን ያደክማል፣ በመገጣጠሚያዎቻቸው ላይ ውጥረት ይፈጥራል እንዲሁም ጭንቀት ይፈጥርባቸዋል። ለስላሳ ንጣፍ መጠቀም ላሞች በምቾት እንዲተኙ እና ወደ አውጪው አካል የሚደረገውን የደም ዝውውር ስለሚጨምር የወተት ምርት በከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ ያደርጋል። የሰኮና ጤና (Hoof Health) እና ጉዳት መቀነስ፡ ጠንካራ እና እርጥብ ወለል ለላሞች ሰኮና መጎዳት እንዲሁም የመነከስ/የመሰነጣጠቅ አደጋ ያመጣል። ንጣፎች ከወለል ጋር የሚኖረውን ግጭት በማስተካከል የመንሸራተት አደጋን ስለሚከላከሉ ላሞች በልበ ሙሉነት እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋሉ። ንፅህና እና የበሽታ መከላከል፡ ከሲሚንቶ ወለል በተለየ መልኩ ላም ንጣፎች ለማጽዳት በጣም ቀላል ናቸው። አንድ ጊዜ ውሃ መልቀቅ ብቻ ነው የሚጠበቅብዎ። ፈሳሾችን ወደ ታች የሚያንጠባጥቡ ወይም የማይመጡ በመሆናቸው እርጥበትን ይቆጣጠራሉ። ይህም እንደ ማስቲቲስ (Mastitis) ያሉ የእንስት አጥቢ እጢ ኢንፌክሽኖችን እንዲሁም ሌሎች የባክቴሪያ በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳል። በአካባቢዎ ወይም አዲስ አበባ ውስጥ እንደነዚህ ያሉ የወተት ላም ንጣፎችን ለማግኘት እና የዘመናዊ የወተት እርባታ አስተዳደርን ለመተግበር የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይችላሉ። @AgriLancer

⚡️የከብቶች ማት ጥቅም
⚡️የከብቶች ማት ጥቅም

⚡️ለዶሮ አርቢ ደንበኞቻችን የዓመቱን የቄብ/የፑሌት ስርጭት ፕሮግራም ዘግተናል። በዓመቱ ፕሮግራማችን እኛን መርጣቹ ለተረከባችሁን እና አብራችሁን ስትሰሩ ለቆያቹ እጅግ በጣም ብዙ ደንበኞቻችን ታላቅ
⚡️ለዶሮ አርቢ ደንበኞቻችን የዓመቱን የቄብ/የፑሌት ስርጭት ፕሮግራም ዘግተናል። በዓመቱ ፕሮግራማችን እኛን መርጣቹ ለተረከባችሁን እና አብራችሁን ስትሰሩ ለቆያቹ እጅግ በጣም ብዙ ደንበኞቻችን ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን። በመጪው ዓዲስ ዓመት 2019 መስከረም ዳግም የሽያጭ ፕሮግራም የሚጀምር ሲሆን: ከመጀመራችን ቀደም ብለን እናሳውቃለን። 🌻እስከዛው ለስራው ጠቃሚ ያልነውን ትምህርታዊ ፅሁፍ በዚሁ ቻናል መስጠታችንን እንቀጥላለን። 🌻ክረምቱ አልፎ ፀሃይ ስትወጣ በፈጣሪ ፈቃድ ዳግም እንገናኛለን። ሰላም ቆዮ። ከምስጋና ጋር @AgriLancer

የሰው ሃይል እጥረት እጅግ በጣም ትክክለኛ እና በኢንዱስትሪው ውስጥ በተግባር የሚታይ ትልቅ ማነቆ ነው። የወተት ላሞች አላቢ (Milker) እና ተንከባካቢ/እረኛ (Dairy Herder/Caregiver) በቀጥታ ከላሞቹ ጤና፣ ከወተቱ ጥራትና ምርታማነት ጋር የሚገናኙ የዘርፉ የጀርባ አጥንቶች ናቸው። በኢትዮጵያ የወተት ዘርፍ ውስጥ የላም አላቢ እና የተንከባካቢ እጥረት የሚያስከትላቸው ዋና ዋና ችግሮች እና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው። 1. የላም አላቢ እና የተንከባካቢ እጥረት ዋና ምክንያቶች የሙያው ዝቅ ተደርጎ መታየት (Social Stigma): በብዙ አካባቢዎች ከብት ማገድ እና ወተት ማለብ እንደ ዝቅተኛ ወይም የኋላ ቀር ሰው ሥራ ተደርጎ ስለሚወሰድ፣ ወጣቶች ሙያውን እንደ ቋሚ የሥራ መስመር መምረጥ አይፈልጉም። የሚገርማቹ ግን ከሃገር ተሰደው በውጪ ሃገራት ብዙ ዲዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ይህንን ስራ ለውጪ ፋርሞች ሲሰሩ ተስተውለዋል። ችግሩ ለራሳቸው አገር ሲሆን ማድረግ አይፈልጉም። የሥራው ባህሪ ድካምና እረፍት ማጣት: ላሞች በየቀኑ (ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ) በማለዳ ከ 11:00 ሰዓት ጀምሮ መታለብና መመገብ አለባቸው። ይህ የ24/7 የሥራ ቁርጠኝነት ሠራተኞች የግል ሕይወት እንዳይኖራቸው ስለሚያደርግ በቶሎ ሥራቸውን እንዲለቁ ያደርጋል። ዝቅተኛ ክፍያ እና ማበረታቻ ማጣት አብዛኞቹ የወተት እርሻ ባለቤቶች ለአላቢዎችና ለተንከባካቢዎች የሚከፍሉት ደሞዝ ከሥራው ድካም ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ ሠራተኛን ማቆየት (Staff Retention) ትልቅ ፈተና ሆኗል። የስደት እና የከተማ ፍልሰት በገጠር እና በከፊል ከተማ ያሉ ንቁ ሠራተኞች ወደ ትላልቅ ከተሞች ለሌላ የቀን ሥራ ወይም ወደ አረብ ሀገራት ለመሰደድ ስለሚመርጡ የግብርና ሠራተኛ እጥረት በየቀኑ እየተባባሰ ነው። 2. በእርሻዎች ላይ የሚያስከትለው ከባድ ተፅዕኖ የማስቲቲስ (የጡት በሽታ) መስፋፋት አላቢዎች በየጊዜው ሲቀያየሩ ወይም የሰለጠነ አላቢ ሲጠፋ፣ የላሞች ጡት አያያዝ እና ንፅህና ይጓደላል። ይህ ደግሞ ላሞች በጡት በሽታ (Mastitis) እንዲያዙና ምርት እንዲቀንሱ ያደርጋል። የወተት ምርት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ላሞች ለለመዱት አላቢ እና ተንከባካቢ ፍቅርና መረጋጋት ያሳያሉ። አላቢ በየሳምንቱ ሲቀየር ላሞች ይጨነቃሉ (Stress ይባላል)፤ በዚህም ምክንያት ወተት የመያዝ (Milk let-down failure) ችግር ያጋጥማቸዋል። የእንስሳት ጤና ክትትል መጓደል የቅርብ ተንከባካቢ/እረኛ ሲጠፋ ላሞች መቼ እንደሚያረግዙ (Heat Detection)፣ መቼ እንደሚታመሙ ወይም መቼ እንደሚወልዱ በቅርብ የሚከታተል ስለሚታጣ እርሻው ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ ይገባል። 3. ተግባራዊ መፍትሔዎች 🌾የተሟላ ጥቅማጥቅም እና የተሻለ ደሞዝ ማዘጋጀት: ለአላቢዎች ከደሞዝ በተጨማሪ በምርት መጠን ላይ የተመሰረተ ማበረታቻ (Bonus)፣ ነፃ ምግብ እና መጠለያ ማዘጋጀት ሠራተኛን ለማረጋጋት ይረዳል። 🌾የሥራ ፈረቃ (Shift) መፍጠር: አንድ ሠራተኛ ብቻ በሳምንት 7 ቀናት ከመጠቀም ይልቅ፣ ሁለት ሠራተኞችን በመቅጠር የዕረፍት ቀናት እንዲኖራቸው ማድረግ የሥራ ድካምን ይቀንሳል። 🌾በከፊል በቴክኖሎጂ መታገዝ: አነስተኛ እና መካከለኛ የወተት ማለቢያ ማሽኖችን  መጠቀም አላቢዎች በሰው ኃይል የሚፈጅባቸውን ድካም ስለሚቀንስላቸው በሥራቸው እንዲረኩ ያደርጋል። 🌾አጫጭር ተግባራዊ ሥልጠናዎች: አዳዲስ ሠራተኞችን ቀጥሮ ስለ ላም አያያዝ፣ ንፅህና እና በሽታ መከላከያ አጫጭር ሥልጠናዎችን በየእርሻው ላይ መስጠት። @AgriLancer

⚡️የወተት ላሞች አላቢ እና ተንከባካቢ እጥረት በኢትዮጵያ
⚡️የወተት ላሞች አላቢ እና ተንከባካቢ እጥረት በኢትዮጵያ

⚡️ማለቢያ ማሽን ✨ብራንድ Barbaros/ባርባሮስ ✨ቱርክ ሰራሽ/Made in Turkey ✨ሲንግል ፌዝ ኤሌክትሪክ 📌ሁለት ላም አንዴ የሚያልብ ማሽን አንድ ባለ 40 ሊትር ወተት ማጠራቀሚያ ኮንቲነር
⚡️ማለቢያ ማሽን ✨ብራንድ Barbaros/ባርባሮስ ✨ቱርክ ሰራሽ/Made in Turkey ✨ሲንግል ፌዝ ኤሌክትሪክ 📌ሁለት ላም አንዴ የሚያልብ ማሽን አንድ ባለ 40 ሊትር ወተት ማጠራቀሚያ ኮንቲነር ያለው ✅ዋጋ 182,911 ብር ከነቫቱ 📌ሁለት ላም አንዴ የሚያልብ ማሽን ሁለት ባለ 30 ሊትር ወተት ማጠራቀሚያ ኮንቲነር ያለው ✅ዋጋ 204,750 ብር ከነቫቱ ይደውሉ +251913323845 ✨ማለቢያ ማሽን ሲገዙ የእርባታ ስራ ፈቃድ እና መታወቂያ ኮፒ ይዘው መምጣት ይጠበቅቦታል@AgriLancer

⚡️የወተት ጊደሮች በሽያጭ ላይ የትኛውንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የአየር ንብረት ተላምደው ምርት የሚሰጡ ከሆላንድ የተመዘዘ ዘር ያላቸው ክበድ የሆልስቲን ፍሬሲያን ሃይብሪድ የወተት ጊደሮች እያቀረብን እንገኛለን። 🌾ዝርያ :- ሆልስቲን ፍሬሲያን እና አይሪሽ ደም 🌾የደም % መጠን:- ከ 80 - 90% 🌾0 እና 2 የሰበሩ/ ከ 4 እስከ 8 ወር የመጀመሪያ ክበድ 🌾ከብዛት አማራጭ ጋር 📌መርጠው ይውሰዱ @AgriLancer

⚡️የእንቁላል ጣይ ቄቦች በሽያጭ ላይ የ60 ቀን እድሜ ያላቸው የ ቦቫን ብራውን ቄቦችን ለሽያጭ አቅርበናል። 🌾Fully vaccinated አዲስ አበባ ነፃ ትራንስፖርት አገልግሎት እንሰጣለን። ትንሹ
⚡️የእንቁላል ጣይ ቄቦች በሽያጭ ላይ የ60 ቀን እድሜ ያላቸው የ ቦቫን ብራውን ቄቦችን ለሽያጭ አቅርበናል። 🌾Fully vaccinated አዲስ አበባ ነፃ ትራንስፖርት አገልግሎት እንሰጣለን። ትንሹ የሽያጭ ቁጥር 100 ቄብ ሲሆን ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ ደንበኞች ማዘዝ ይችላሉ። ይደውሉ +251913323845 @AgriLancer

⚡️ዘመናዊ H type የዶሮ ኬጅ ሙሉ ለሙሉ ብረት/Galvanized ስሪት የሆነ እና በተለያየ መጠን የቀረበ። 📌እንቁላል የሚያንሸራትት 📌 ለማፅዳት ቀላል የሆነ 📌ለዘመናት የሚቆይ 📌መመገቢያ
⚡️ዘመናዊ H type የዶሮ ኬጅ ሙሉ ለሙሉ ብረት/Galvanized ስሪት የሆነ እና በተለያየ መጠን የቀረበ። 📌እንቁላል የሚያንሸራትት 📌 ለማፅዳት ቀላል የሆነ 📌ለዘመናት የሚቆይ 📌መመገቢያ እና መጠጫ የተገጠመለት 📌በቅድመ ትዕዛዝ ዋጋ በዶሮ ቁጥር ባለ 5 ዶሮ ቤት 10,500 ብር ባለ 10 ዶሮ ቤት  19,500 ብር ባለ 15 ዶሮ ቤት 26,000 ብር ባለ 20 ዶሮ ቤት 30,000 ብር ባለ 30 ዶሮ ቤት 38,000 ብር ባለ 40 ዶሮ ቤት 45,000 ብር ባለ 60 ዶሮ ቤት 58,000 ብር ባለ 80 ዶሮ ቤት 68,000 ብር ባለ 120 ዶሮ ቤት 80,000 ብር ባለ 160 ዶሮ ቤት 90,000 ብር 🪡ኬጅ ለሚያዙን ደንበኞች የዲካልብ ዋይት የእንቁላል ቄቦችንም እናቀርባለን:: Contact number+251913323845 Email yonatan.lancer@gmail.com @AgriLancer