ግጥም
Open in Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Show more5 369
Subscribers
+1024 hours
+627 days
+20430 days
Posts Archive
5 367
ከጎረቤትህ ቤት ሞት መጥቶ ሲጣራ
በቀጣይ አንተ ነህ በመኖር አትኩራ
አለሁ አለሁ አትበል በስጋ ምቾትህ
ነገ ባለተራ አንተም ተከታይ ነህ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
#አልገባሽምና
በእኔ ሀዘን ሳቂ
ሳለቅስ ድመቂ
ምን በወጣሽ አንቺ ከቶ አትጨነቂ
ተራው እስኪደርስሽ ደምቀሽ ተፍለቅለቂ
አንቺም በሰው ፍቅር ተማርከሽ ስቶድቂ
ያኔ ነው ፈተናሽ ያኔ ነው ከልቤ ፈጥነሽ የምትርቂ።
በእኔ የሳቅሽው ሳቅ ተሰፍሮ በጥርስሽ
ይደርስሻል ዞሮ አፍቅረሽ ሲጠሉሽ።
ለዛሬው ግን ሳቂ አይክፋሽ የኔ ማር
አልገባሽምና ሲፈቀሩ መክበር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
ፀሐይ ብትጠልቅም ጨረቃዋን ጠብቅ
ጨረቃ ብጠፋም ከዋክብትን አድንቅ
ገንዘብ ቢቸግርህ መኖርህን ውደድ
በየምክንያቱ ማመስገንን ልመድ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
#ልጅነት_ቅርስ_ነው
የትላንቱ ውበት ያ መልካም ልጅነት
ተንኮል ያልበረዘው የልብ ቅንነት
ናፈቀኝ ዛሬ ላይ ክፋት ሲበረክት
ምነው ዞሮ ባየው ያ ደግ ልጅነት
ተመልሶ አይመጣም ቢመጣማ ዞሮ
መፈንደቅ መደሰት ከእኩያ ጋር አብሮ
ክፋት ምቀኝነት ተንኮል የማያውቀው
ከሁሉም የነጻ ልጅነት ቅርስ ነው!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
5 367
እንደሚታወቀው በዓለ ጥምቀት በ ኢትዮጵያ በደማቅ ሁኔታ ከሚከበበሩ የ ኦርቶዶክስ በዓላት ዋናው ነው : : ነገር ግን አብዛኞቻችን በተለይ ደሞ እኛ ወጣቶች በዓሉ የሚከበርበትን ምክንያት አልተረዳነውም : : አብዛኞቻችን ለጥምቀት ቀን የምኖጣው ለመታየት, ለመጨፈር,ጠጥቶ ለመስከር, ከዝሙት ያልተናነሱ ተግባራቶችን በአደባባይ ለመፈፀም ነው! በዛን ቀን ሁሉም ታቦቶች ከየአድባራቸው ይወጣሉ እዛ ቦታ ላይ መጨፈር እና መስከር ማለት እያንዳንዱ አቢያተክርስቲያናት ውስጥ ገብቶ ከመጨፈር ወይ ከመስከር አይተናነስም! በተቻለን መጠን በአሉን ለማክበር ከቤታችን ስንወጣ የምኖጣበትን ምክንያት ብናውቅ እና ደሞ ሃይማኖታችንን ባናሰድብ ባይ ነኝ : : ቤተክርስቲያን መጨፈርን መጠጣትን መስከርን ዝሙትን አላስተማረችንም : : አሁን ያለንበት ጊዜም ቢሆን በፀሎት የእግዚአብሔርን ምህረት የምንለምንበት እንጂ በታቦት ፊት መጥፎ ተግባራትን የምንፈፅምበት አይደለም : : ስለዚህ ሁላችሁም ኦርቶዶክሳዊ ወጣቶች ከአሁኑ የጥምቀት በዓል ውሏቹን አስተካክሉ ከጕደኞቻቹ ጋር ያቀዳቹሃቸው እቅዶች ካሉም ወደ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ቀይሯቸው : :😊
5 367
#ዛሬም_በመጠበቅ
ይመጣል እያልኩኝ የተሻለ ግዜ
ዛሬን አልፈዋል በተስፋ ትካዜ
በሁለት ስሜት ስልት በቀነ ቀጠሮ
ተስፋና ትካዜ አብሮ ተደምሮ
እየወዘወዘኝ አዲስ ቀን ፍለጋ
አለሁ በክርስቶስ በተመስገን ጸጋ።
ይመጣል ያልኩት ቀን መምጫው እየራቀ
እድሜም እንደዋዛ ፈጥኖ እየዘለቀ
በማመስገን ዜማ በስጋት ቅልቅል
በተስፋ ትካዜ እያነሳሁ ስጥል
ዛሬም በመጠበቅ የተሻለን ዘመን
የለሁም አልልም ይኸው ዛሬም አለን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
#ተራርቆ_ከእውነት
ነፃነትን ሸጦ ገንዘብን ፍለጋ
በረከሰ ስደት በረከሰ ዋጋ
ህሊናን ለውጦ በሆድ አቆማዳ
እውነትን አስይዞ መግባት ትልቅ እዳ
ጎተራው ላይሞላ መሶቡ ላይፋፋ
ለኩርማን እንጀራ በውሸት ሲለፋ
አወይ ሰው ምስኪኑ ከትላንት አይማር
ውዱን እየሸጠ ለርካሽ የሚኖር
እርካታ ሳይኖረው ባለው ሳይደሰት
ሆዱ ይመራዋል ተራርቆ ከእውነት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
5 367
ለትንሹ ችግር አምላክን ሳማርር
ትልቁን አመጣው ማመስገን ሊያስተምር
እግር ሰጥቶኝ ጌታ በጫማ ስወቅሰው
አለማመስገኔ ተግባሬ ቢገርመው
ከፍ አድርጎ መጣ ከትላንቱ ዛሬን
ተመስገን እንድለው ትቼ ማማረሬን
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
5 367
#ይላል_መደብ_መደብ
ሀገሩ ሰፊ ነው ህዝቡም የከበረ
ምነው ፖለቲካው በሰፈር ታጠረ
ስሙም ደስ የሚለው ሀገር ሲባል ነበር
ክልል ክልል ብለው ይከልሉን ጀመር።
አሁን በዚህ ዘመን አሁን በዚህ ግዜ
የት ያድርሰን ይሆን የእኔ ብቻ አባዜ።
አሞራው በረረ ቅሉም ተሰበረ
ሁሉም በመንደሩ ድንበሩን አጠረ
ከትልቁ ወርዶ ከገዘፈው ሀገር
ይላል መደብ መደብ ተጣቦ ለማደር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
#እንደእንስሳ_ኖረ
ሰው ከመሆን አንሶ መኖር የመረጠ
ከከፍታው ወርዶ ቁልቁል የዘቀጠ
እንደ አህያ ስጋ በውርደት ያበጠ
አልጋ ሲሉት መደብ
ወርቅ ሲሉት መዳብ
ሀገር ሲሉት ሰፈር
ሰው ሲሉትም ብሔር
ምርጫው በጠቅላላ ወደታች ወደታች
ፍቅርን እየሸጠ ልጥላቻ ዘማች!!!
ጠጅ ሲሉት ጠላ ጤፍ ሲሉት ዘንጋዳ
ነገሩ በሙሉ ጠማማ ወልጋዳ!!!
ሰው " ሰው መሆን ከጠላ መውረድ ከጀመረ
አሞራው በረረ!!! በረረ!!! ቅሉም ተሰበረ
በአምላክ አምሳል ቀርቶ እንደእንስሳ ኖረ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
#ሰው_ባልሰራው_እውነት
አወይ አለማፈር አለመሸማቀቅ
በውሸት እስክስታ ከበሮ ሲደልቅ
በሀሰት እንቢልታ በምላስ ሲሰልቅ
ሰው ባልሰራው እውነት ከዙፋኑ ሲደምቅ
አወይ አለማፈር አለመሸማቀቅ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 367
#በተበዳይ_ዜማ
አንቺው እየበደልሽ
አንቺው እየከሰስሽ
አንቺው እየፈረድሽ
እንቺው እያለቀስሽ
የሰው እንባ ዘርፈሽ
ደረት እየደለቅሽ
የሰው ለቅሶ በልተሽ ዛሬ ጉድ ይሰማ
ሀዘን ድረሱ አትበይ በተበዳይ ዜማ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
