ግጥም
Открыть в Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Больше4 823
Подписчики
+324 часа
+557 дней
+23030 день
Архив постов
4 827
#የጌታ_ደብዳቤ
የድሮ ሰው ደጉ
በ…30…ዲናር
ጌታዉን ካስማማ
ምንኛ ይከፋል
ያሁኑ ሠዉማ
ስለዚህ አትምጣ
ለምፅዓት ቀኑ
ዲናር እንዳይመስልህ
ዶላር ነው ያሁኑ
ይቅር በለኝ አምላክ
አይሁንብኝ ድፍረት
እንዳስቀመጥከው ነው
"ሠው" የሚሉት ፍጥረት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
4 827
#በጎች_ተጠንቀቁ
በቀበሮ መንጋ በግ እያስጠበቁ
ተበልተው ተበልተው በየተራ አለቁ
እረኛ ባሉት ነው ሁሉም የሚጠቁ
በቀበሮ ዘመን በጎች ተጠንቀቁ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
#ማንነት_ሲምታታ
የራስ ምስል ገዝፎ በሌላ ገጽታ
ጠላት ይመስለዋል ማንነት ሲምታታ
ከነበረው እውነት ገዝፎ ሲቀርብ ሀሰት
የራስ ጥላ ሳይቀር ከመሰለው ጠላት
ሳይሻል አይቀርም ከራስ ጋር መታረቅ
ሸንጎ ከመሰብሰብ ሌላን ለማስታረቅ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
Repost from ዝባዝንኬ thought🗽
I really felt it when አስቴር አወቀ said "በል እራሴን በለኝ እንካ ዘነዘና" cause, boy do i wish to be caved with a ዘነዘና in my head🚶🏾
4 827
በአህያ ሞት አዝኖ ጅብ ለቅሶ ቢቀመጥ
ለማመቻቸት ነው ሲመሽ ለመለወጥ
በግ ጠፋብኝ አትበል ለቀበሮ መንጋ
ይልቅ ለአምላክ ንገር ወርዷል ለፍለጋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
እንቅልፍ ያጡ ዓይኖቼ ማረፍን የፈሩ
በሀሳብ ነበልባል በቅዠት ያደሩ
በመስታወት መስኮት ሳያቸው ሲነጋ
እጅግ አሳዘኑኝ ለከፈሉት ዋጋ!!!
እረፍት ነፍጊያቸው በሽህ ሀሳብ ስሌት
በማይጠቅም እህ በማይነጋው እውነት
አሳርን እያዩ ማረፍ ሲናፍቁ
ደፍርሰው ያዩኛል አድረው ሲጨነቁ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
ተመስገን ማለት ነው ዛሬ ያደረሰን
ስንቱን ክፉ ዓመታት ሰላም ያሻገረን
በማመስገን ትግስት ሆዳችን ባይሰፋ
ያሳለፍነው ፍዳ ከዚህም በከፋ!!!
ይመስገን ፈጣሪ ብዙ ዓመት አልፈናል
የጊዜውስ መክፋት ቀን በቀን ይጥላል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
#መልካም_ምሽት_አይላቭዪ_React_ምታደርጉ 🫶
4 827
#ምንድን_ነው_ሰውነት?
የሰው ሚዛን ወርዶ
ቁስ አካል ተወዶ
ፍቅርም ተሰዶ
ጥላቻ ተለምዶ
አንድነት ተንዶ
ሰላም ጥሎን ሄዶ
ሰው እየተናቀ
ቁስ ከተደነቀ
ምንድን ነው ሰውነት? የክብር መስፈሪያው
ሁሉም ተነጣጥሎ ጥላቻ እየመራው !!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
ፈገግ በል ጥርሴ
ተቆጠብ ምላሴ
ቅን አስቢ ነፍሴ
ጠላት ሆኜ እንዳልቀር እራሴው ለራሴ
ከአምላክ አታጣላኝ ሰከን በል ከርሴ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
Уже доступно! Исследование Telegram 2025 — ключевые инсайты года 
