en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Open in Telegram
1 330
Subscribers
+324 hours
+87 days
+8330 days
Posts Archive
በአስተዳደሩ በዚህ በጀት አመት ባለፉት ወራት በዘርፉ አዲሱ ዕሳቤ ላይ እስከታችኛው የቢሮው መዋቅር የተፈጠረው ግንዛቤ ተናቦ ለመስራት ሁነኛ መሳሪያ ሆኖ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ተገለጸ። በሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ የተመራ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ ባለሙያዎች ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ለአምስት ቀናት ያካሄደው የድጋፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ሲጠናቀቅ በቢሮው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል የማዘመን እና ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራዎችን ተመልክቷል፡፡ የባለሞያዎች ቡድኑ ባካሄዳቸው ጉብኝት ላይ ከአስተዳደሩ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸውና ከቢሮው አመራሮች ጋር የተወያዩ ሲሆን በአስተዳደሩ ከዚህ ቀደም በተደረገው የድጋፋዊ ሱፐርቪዥን የተሰጡ ግብረመልሶችን እንደ ግብዓት በመውሰድ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ስራዎች አበረታች ሆነው ተመልክተዋቸዋል። የአቅም ግንባታ ስራዎች፣ የክህሎት ልማት፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ ኢንተርፕራይዝ ልማትና ሰላማዊ የኢንዱስትሪ የስራ እንቅስቃሴዎች ለመፍጠር የተከናወኑ ስራዎች አበረታች ናቸው በዚህም የበለጠ በማጠናከር የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ ጥረት መደረግ እንዳለበትም አስገንዝበዋል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በተካሄደው ድጋፋዊ የግምገማ ሂደት የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በተቀናጀ መንገድ በመተግበር አመታዊ ዕቅድን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት ጥረት እንደሚያደርጉ ለዚህም በተገኙ ውጤቶች በመርካት የማይቀመጥ መዋቅር መፈጠሩ ከፍ ያለ ውጤት ለማምጣት አቅም ይሆነናል ብለዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 25/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የግልና የመንግስት ኮሌጆች የተዘጋጀ  የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፤ የስልጠናው ዋና አላማ በቢሮው በተለይም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍን የሚመሩና የሚሰሩ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ጊዜው የሚጠይቀውን እና የሚፈልገውን ክህሎት ተላብሰው ተልዕኮ መፈጸም እንዲችሉ ታስቦ በተለያዩ ርዕሶች የተሰጠ መሆኑን የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ጀማል አደም ገልጸዋል፡፡ በዚህም ከኮሌጆቹ የተወጣጡ የትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪዎች፣ የስልጠና አስተባባሪዎችና የሬጅስትራር ክፍልን የሚመሩ በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን የሰልጣኞች ቅበላና ምደባ ፖሊሲ፣ የተቋም ውስጥ ምዘና እንዲሁም TVT Harmonized የዘርፉ ስርዓተ ሰነዶች በቢሮው ባለሙያዎች ቀርበው ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲው ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በስልጠናው ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት አመራሩ እና ከፍተኛ ባለሙያው ከዘመኑ ጋር ለመራመድ በወሰዱት ስልጠና እራስን የማብቃት ስራ በዚህ ስልጠና የሚጠናቀቅ እንዳልሆነና ክህሎታቸውን ለማዳበር ቢሮው መሰል ስልጠናዎችን በየጊዜው እንደሚያዘጋጅም ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 25/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኘውን አጠቃላይ የሥራና ክህሎት ስራዎች አፈጻጸም የመጨረሻውን የመስክ ምልከታ ውሎ አካሄደ። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ቴሬሳ የተመራው ቡድኑ አስተዳደሩ የሥራና ክህሎት ቢሮ በበጀት አመቱ የተሰሩ ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ ባለፉት ተከታታይ ቀናት ያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለት በስራ ዕድል ፈጠራ አንድ ማዕከላትን በማስተባበር የተፈጠሩ የስራ ዕድሎችን፣ በኢንተርፕራይዝ ልማት በዶሮ እና በከብት እርባታ የተገኙ ውጤት የተገኘባቸው ልማቶች እንዲሁም በክህሎት ልማት በሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች በስልጠና ከስልጠና ጎን ለጎን የተሰሩ ስራዎች ምልከታ ተደርጎባቸዋል። የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በአስተዳደሩ በነበረው ቆይታ በሰፊው የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ሰው ተኮር የሆኑ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ስራዎችን የተመለከቱ ሲሆን በነገው ዕለትም የድጋፍና ክትትሉ የመስክ ምልከታ ግብረመልስ ለቢሮው የሚቀርብና  የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 24/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

''እያገረሸ የመጣዉን የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ ስርጭት ለመግታት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል። ''  * የሥራና ክህሎት ቢሮ: ህዳር 24/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የኤች ኤድስ ቀንን ''ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤች አይ ቪ አገልግሎት ለሁሉም'' በሚል መሪ ቃል አከበሩ። በአሉ በሽታዉን መከላከልና መቆጣጠር እንዲቻል በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል መነቃቃትና ግንዛቤ መፍጠር አላማ አድርጎ ይከበራል። እያገረሸ የመጣዉን የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ ስርጭት ለመግታት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በበዓሉ ላይ ተናግረዋል፤ መዘናጋቱን ተከትሎ በሀገራችን ብሎም በአስተዳደራችን እየተስፋፋ የመጣዉን የበሽታዉን ስርጭት ለመቀነስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። በበዓሉ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ዉይይት ተደርጓል በዚህም የሁሉንም ማህበረሰብ ሰብዓዊ መብት ባከበረ መልኩ የኤች አይ ቪ ኤድስ የጤና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቁሟል፤ በሽታዉ በርካታ አምራች ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለና ስርጭቱ እየጨመረ የመጣ በሽታ በመሆኑ ሁሉም ማህበረሰብ አስከፊነቱን በመረዳት ስርጭቱን ለመግታት ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል። በዓሉ በዓለም ለ37ኛ በሀገራችን ለ36 ኛ ጊዜ ''ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤች አይ ቪ አገልግሎት ለሁሉም'' በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል።

photo content
+9

በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አመቻችነት የኮሌጆችን አቅም ለማሳደግና የአሰልጣኝ መምህራንን የክህሎት ክፍተት መሙላት የሚያስችል ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የማኑፋክቸሪንግ ትምህርት ክፍል በአሰልጣኝ መምህራን የውስጥ አቅም በኮሌጁ የማሽን ሾፕ የሚገኙ በተለያየ ምክንያት የተበላሹ ሶስት ማሽኖች (Conventional Lathe Machine, Conventional Milling Machine and CNC Lathe Machine) ተጠግነው ወደ ስራ እንዲገቡ ተደረገ፤ የማሰልጠኛ ማሽኖቹ ጥገና በአሰልጣኝ መምህራኑ መካከል የልምድና የእውቀት ሽግግር አንዳቸው ለሌላቸው በማድረግ አሰልጣኝ መምህራኑ የክህሎት አቅማቸውን በአንድ በኩል ሲያሳድጉ ከዚሁ ጎን ለጎን ማሽኖቹን ጠግነው ለትምህርትና ስልጠናው ዝግጁ በማድረግ ጥቅም ላይ እንዲውሉ አድርገዋል፤ በማጠቃለያውም የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ እንደተናገሩት ለ15 ቀናት በተከናወነው የጥገና ስራ በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን ዘንድ ያለውን የክህሎት ክፍተት መሙላት ከመቻሉ ባሻገር የነበረውን የማሽን ብልሽት ችግር ለመፍታት ያስወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ማስቀረት መቻሉን ገልጸው በኮሌጁ የውስጥ አቅም የተከናወነ መሆኑ ደግሞ የኮሌጁን አቅም የሚያጠናክር እንደሚሆንና በተለይም በሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች በሚገኙ ዲፓርትመንቶች የጥገና ቡድን መቋቋሙ ውጤት የሚያስገኝ መሆኑንና በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም በተመሳሳይ  የሚቀጥል መሆኑን  ገልፀዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 24/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+7

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ የሚመራ የሱፐርቪዥን ቡድን በድሬደዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የተሰሩ ስራዎችን እየጎበኙ እንደሚገኝ ተገለጸ። በሚኒስትር ዴኤታው የተመራው ቡድን በዛሬው ዕለት በዋናነት በአሰሪና ሰራተኛው ዘርፍ በኢንደስትሪዎች እና በኤጀንሲዎች ያለውን አጠቃላይ የስራ ሁኔታ እና የሙያ ደህንነትና ጤንነት ያለበትን ደረጃ ምልከታ ያደረገ ሲሆን በስራ ዕድል ፈጠራ እና ከኢንተርፕራይዝ ልማት አኳያ በወረዳ 08 እና 09 የተተገበሩና የስራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ያስገኛቸው ውጤቶችና ተጠቃሚ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተመልክቷል። የሱፐርቪዥን ቡድኑ ድሬዳዋ የተገኘበት ዋና አላማ እንደ ሀገር በሥራና ክህሎት በኩል የሚሰሩ ስራዎች በህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ረገድ የታሰበላቸውን ውጤት እንዲያስገኙ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ መሆኑን ገልፀው በጉብኝታቸውም በከተማዋ በሥራና ክህሎት በኩል የህብረተሰቡ  ተጠቃሚነት ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለመመልከት ነዉ ብለዋል። ዛሬን ጨምሮ በቀጣይ በአስተዳደሩ በሚኖራቸው ቆይታም እንደ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በተቀመጡ አራት ዋና ዋና ጉዳዮች መሠረት ማለትም የተቋማት ግንባታ፣ የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይና የኢንዱስትሪ ሰላም በአስተዳደሩ በምን አይነት ሁኔታ እየተጓዘ እንዳለ ምልከታ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ሚኒስቴር ዴኤታው ገልጸዋል። አቶ ዳንኤል አክለውም በድሬደዋ የተመለከቷቸውን የሥራ ዕድል ፈጠራ እንደ ሀገር ሚናቸው የላቀ እንዲሆን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአስተዳደሩ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራና ብሎም አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ነው ያረጋገጡት። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 23/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን ድሬዳዋ ገባ። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ቴሬሳ የተመራው ቡድኑ አስተዳደሩ የሥራና ክህሎት ቢሮ በበጀት አመቱ የተሰሩ ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ የሚያደርግ ይሆናል። በዛሬው ውሎም በመስክ ምልከታው ከክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ አሠሪና ሠራተኛ ግንኙት እና ከተቋማት ግንባታ አኳያ የተሰሩ ሥራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶባቸዋል። በዚህም ቡድኑ የተመረጡ የግልና የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን፣ ኢንተርፕራይዞችን፣ የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራንና ኢንዱስትሪዎችን ተዘዋውሮ የሚመለከት ይሆናል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 21/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የግል ኮሌጆች  ከመንግስት  ኮሌጆች  ጋር  በቅንጅት  እና በመተባበር  ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ  ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት  ድጋፍ ለማድረግ  የመግባቢያ  ሰነድ  ተፈራረሙ ። ከሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረሙ የግል ኮሌጆች የሚከተሉት ናቸው፦ ✍️ አዲስ አበባ ቢዝነስና  ሜዲካል  ኮሌጅ ✍️ ኦልብራይት ኢንተርናሽናል  ኮሌጅ ✍️ ሉሲ ኮሌጅ ✍️ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ✍️ ሲቲ ጤናና  ቢዝነስ ኮሌጅ   ✍️ ሻሎም ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ በዚህም በአስተዳደሩ የሚገኙ ከላይ የተዘረዘሩት ኮሌጆች ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ማለትም የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ጋር በክላስተር የተደለደሉ ሲሆን በአጭር ጊዜ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ስራ የሚገቡ መሆኑን የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 21/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

ችግር ፈቺ በሆነ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለቢሮ ባለሙያዎች እና ለኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ተሰጠ፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የኢንዱሰትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን በዘርፉ የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን እና ባለሙያዎች እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ድጋፍ ያደርጋል። በዚህም ከቢሮው ለተወጣጡ ባለሙያዎች እና ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ለተወጣጡ የአሰልጣኝ መምህራን በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ላይ ያተኮረ ስልጠና በማዘጋጀት አቅም የሚገነቡበትን ዕድል ፈጥሯል፤ ይህም ስልጠና መሰረታዊ ጥናትና ምርምር ከተግባራዊ ጥናትና ምርምር ያለው ልዩነት፤ የአጠናን ስነ-ዘዴን በማወቅ የተቋማዊ ችግሮች ልየታ፤ ምልከታ በማድረግ ለተግባራዊ ጥናትና ምርምር ማድረግ በሚያስችሉ ጽንሰ ሃሳባዊና ተግባራዊ ዝግጅት ማድረግ የሚያስችል ይሆናል። ስልጠናውም ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመጡ አሰልጣኝ የተሰጠ ሲሆን  የስልጠናውም ዋና ዓላማ ባለሙያዎችና አሰልጣኝ መምህራኑ በስራ ቦታቸው ላይ  ያሉ ችግሮችን ተግባራዊ ልየታ በማድረግ በጥናትና ምርምር ላይ ተመስርቶ እንዲፈቱ በሚያስችል አቅም ለመገንባት ታሳቢ ያደረገ ነው። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 21/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ