1 321
Subscribers
+124 hours
+67 days
+14830 days
Posts Archive
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
በኮሌጁ የሚሰጡ ትምህርትና ስልጠናዎች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ አሰልጣኝ መምህራኖች ያላቸውን እምቅ አቅም አውጥተው ሊጠቀሙ ይገባል ተባለ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና ጥራትን ለማጠበቅ ያለመ ውይይት ከኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን ጋር በዛሬው እለት አከናወነ፡፡
ኮሌጁ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ የልህቀት ማእከል እንደመሆኑ መጠን በኮሌጁ የሚሰጡ የተለያዩ ስልጠናዎች ጥራታቸውን የጠበቁና ዘመኑን የዋጁ እንዲሆኑ ይገባል ያሉት በውይይቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ ዲኑ አክለውም ኮሌጁ በመደበኛነት ከሚሰጣቸው ስልጠናዎች በዘለለ በየጊዜው በአሰልጣኝ መምህራኖች የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች የአካባቢውን ማህበረሰብ እነዲሁም ኢንዱስትሪዎች ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች የሚፈልቁበት ተቋም እንዲሆን ሁሉም ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
አቶ ሰለሃዲን አያይዘውም በኮሌጁ የሚሰጡ ስልጠናዎች ተግባር ተኮር እንደመሆናቸው የግብአት አቅርቦቱ ወጥነት እንዲኖረው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በሙሉ በየትምህርት ክፍል ውስጥ የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራኖች በሙሉ የተሳተፉበት እንዲሆን ለቀጣይ አመት ከወዲሁ ዝግጅት እንዲደረግ ያሳሰቡ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በ5 የተለያዩ ዘርፎች ላይ የኢንተርፕራይዝ ፍቃድ ከአስተዳደሩ እንደማግኘቱ መጠን አሰልጣኝ መምህራኖች ያላቸውን ልምድ፣እውቀት እንዲሁም ክህሎት ወደ ገቢ ማስገኛነት ሊለውጡት ይገባል ብለዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ሂደትን በማሻሻል የስልጠና ጥራትን ማረጋገጥ እንዴት እንደሚቻል በጥናት የተደገፈ ሰነድ በዶ/ር ሲሳይ አበራ የቀረበ ሲሆን በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራኖች ጋርም ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በአሰልጣኝ መምህራኖች የተነሱትን ጥያቄዎች የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ እንዲሁም የኮሌጁ ም/ዲን አቶ ቢቂላ ተሰማ በኩል ምልሽ ተሰጥቷል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
የካቲት 18/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
በአስተዳደሩ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ላይ ለሚሰለጥኑ ሰልጣኝ ተማሪዎች በትምህርትና ስልጠና ተቋማት ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ።
መድረኩ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት በአንድ ቦታ የሚገናኙበት እንደመሆኑ መጠን ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭነቱን ለመቆጣጠር ቢሮዉ ከሚያዘጋጃቸው ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎች አካል መሆኑ ታውቋል፡፡
ቢሮው ሰልጣኝ ተማሪ ዜጋውን ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀና የተረጋገጠ የነገይቱን ኢትዮጵያ ተረካቢ ባለሙያ አድርጎ ለማፍራት የሚያስችል ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ ችሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በአስተደዳደሩ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ላይ ለሚሰለጥኑ ሰልጣኝ ተማሪዎች በትምህርትና ስልጠና ተቋማት ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ።
መድረኩ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት በአንድ ቦታ የሚገናኙበት እንደመሆኑ መጠን ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭነቱን ለመቆጣጠር ቢሮዉ ከሚያዘጋጃቸው ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎች አካል መሆኑ ታውቋል፡፡
ቢሮው ሰልጣኝ ተማሪ ዜጋውን ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀና የተረጋገጠ የነገይቱን ኢትዮጵያ ተረካቢ ባለሙያ አድርጎ ለማፍራት የሚያስችል ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ ችሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ወደ ሪፎርም የሚገቡ ተቋማት ለይቶ ወደ ስራ እንዲገቡ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የመንግስት አገልግሎት ዘርፉን የማሻሻል/ሪፎርም/ የማድረግ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛል፤ በድሬዳዋ አስተዳደርም በተተገበሩት የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት እንደተመዘገበና ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠልም ወደ ሪፎርም ከገቡ ተቋማት መካከል የሥራና ክህሎት ቢሮ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህም የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ዕቅድን መነሻ በማድረግ የቢሮው ዕቅድ መዘጋጀቱንና ሪፎርም አስተግባሪ ኮሚቴዎችንም ከቢሮው እስከ ወረዳ አንድ ማዕከላት ድረስ እንዲሁም በፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በማዋቀር በቢሮው ማኔጅመንት እንዲጸድቅ ማድረግ ተችሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች እየተዘጋጁ መሆኑንና ለአጠቃላይ ሰራተኛው በቀጣይ መድረክ ተዘጋጅቶ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እንደሚሰራ የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
+7
በድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ 2 ቅርንጫፍ 2 አንድ ማዕከል ስር የሚገኙና በቢሮው ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደግ የሚያስችል የተደረገ የመስክ ምልከታና ልየታ በምስል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 11/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
+9
በአስተዳደሩ ወረዳ 7 አንድ ማዕከል ስር የሚገኙና በቢሮው ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደግ የሚያስችል የመስክ ምልከታና ልየታ ተደረገ።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 11/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
+1
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም ወር በሰላም አደረሳችሁ።
ረመዳን ከሪም !!
በአጫጭር ስልጠና ዘርፍ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ የስልጠና ተቋማቱን አቅም ለመገንባት ያለመ የክትትልና ድጋፍ መርሃግብር ተካሄደ፤
በዚህም የድጋፍና ክትትል መርሃግብር የአጫጭር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት በዕቅድ መሠረት ስለመመራታቸው፤ በቂ የስልጠና ግብዓት ስለመኖሩ፤ የስልጠና ፍቃድ በተመለከተ በተሰጠው ፈቃድ ልክ እየሰሩ ስለ መሆናቸውና እንዲሁም የማሰልጠኛ ማንዋሎችና መሳሪያዎች በሚገባ መኖራቸውን ጨምሮ የአጠቃላይ ሰልጣኞችን መረጃ በማደራጀት እረገድ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከትና በቀጣይ በተከታታይ ድጋፍ የሚያገኙበትን አግባብ ለማመቻቸት ተችሏል፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል አደም እንደተናገሩት ይህ የድጋፍና ክትትል ልክ መደበኛ ስልጠና እንደሚሰጡ ተቋማት ሁሉ አጫጭር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማትም ዜጎችን በማሰልጠን የሚያበቁ ናቸው ስለሆነም ትምህርትና ስልጠና ተቋማቱን አቅም ለመገንባትና በቅርበት በመከታተል መደገፍ አላማው አድርጎ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 10/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+6
የኮሌጁን አሰልጣኝ መምህራንን በየጊዜው የሚሰሯቸውን የሚያሻሽሏቸውን ቴክኖሎጂዎች ተገቢውን የእሴት ሰንሰለት ትንተና በማድረግ ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በመደበኛው እና በአጫጭር ስልጠና ሰልጣኞችን ተቀብሎ ከማሰልጠን በተጨማሪ ለአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ለኢንዱስትሪው ግብአት መሆን የሚችሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር እንዲሁም በማሻሻል የማህበረሰቡን እና የኢንዱስትሪውን ጫና መቀነስ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን መፍጠር እና ማሻሻል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡ በዚሁ መሰረት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች ተገቢውን የእሴት ሰንሰለት ትንተና ሊደረግባቸው ይገባል፡፡
ይህንንም ተግባር ለማከናወን የሚረዳ ስልጠና በዛሬው እለት በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ ትምህርት ክፍል ውስጥ ስልጠናን ለሚሰጡ አሰልጣኝ መምህራን እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የኮሌጁ ም/ዲን እና የኢ/ኤ/ቴ/ሽ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ በስልጠናው መክፈቻ ላይ በመገኘት እንደገለጹት በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን የሚሰሩ እንዲሁም የሚሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች የማህበረሰቡን ችግር እንዲሁም የኢንዱስትሪውን ጫና መቅረፍ የሚችሉ እንዲሆኑ ተገቢውን የእሴት ሰንሰለት ትንተና ማድረግና ትንተናውን ተከትሎ መስራት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን አያይዘውም የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራንና ሰልጣኝ ተማሪዎች የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እንዲፈጥሩና ለማህበረሰቡ ማቅረብ እንዲችሉ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
የካቲት 10/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
የአካባቢውን ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ዘርፎች እና በዲጂታል ክህሎት የበቁ እንዲሆኑ ሁሉን አካታች ስራ እየሰራ እንዳለ ኮሌጁ ገለጸ፡፡
አካታችነት፣ዲጂታላይዜሽን፣የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና መልሶ የመጠቀም እንዲሁም የኢንዱስትሪ ትስስር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡ በዚሁ መሰረት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰጡ ስልጠናዎች አካታች እንዲሆኑና ትምህርትና ስልጠና መጪውን ዘመን የዋጀ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ይጠበቃል፡፡
የትኩረት አቅጣጫውን ወደ ተግባር ለመለወጥ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ምን እንደሚመስሉ በጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ የሚመራው CIFA for People (Second Life) ፕሮጀክት ተወካዮች ተጎብኝቷል፡፡
የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት የአካባቢውን ወጣቶችን በተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፎች በማሰልጠን ወደ ሥራ እንዲገቡ እያደረገ ይገኛል።ያሉ ሲሆን አያዘውም በኮሌጁ የሚሰጡ ስልጠናዎች ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ እንዲሰማሩና የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ እንዲመሰርቱ የሚያስችል እንዲሁም መጪውን ዘመን የዋጀ የኢንዱስትሪ ትስስር በመፍጠር ሰልጣኞች ገበያው ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያደርጉ ሰልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ከኤጀንሲው ጋር በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና መልሶ አጠቃቀም፣በዲጂታላይዜሽን እንዲሁም ከኢንዱስትሪ ትስስር ጋር በስፋት የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡
በኮሌጁ ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉት በጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ የሚመራው CIFA for People (Second Life) ፕሮጀክት ተወካዮች በበኩላቸው በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እየተከናወነ ያለው ተግባር መልካም መሆኑን ገልጸው በተለይም ወጣቶች የሚያገኙትን እውቀት ወደ ገቢ ምንጭ በመቀየር የተሻለ ህይወት እንዲመሩ እየተደረገ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ይህንንም የኮሌጁን ጥረት በተለያዩ ለመደገፍ በጋራ የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
የካቲት 7/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ለሶስተኛ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠና ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምርቃት እና የማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ
" ብቃት ፣ ክህሎት ፣ ስኬት " በሚል መሪ ሀሳብ ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሶስተኛ ዙር ማጠቃለያ መርሀ ግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል።
በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሮቤል ጌታቸው ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን መቀጠል ያልቻሉ ወጣቶችን ለ 12 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና በመስጠት በአስተዳደሩ ባሉ ድርጅቶች ላይ ለስድስት ወራት የስራ ላይ ልምምድ አድርገው በቋሚነት ተቀጣሪ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል ።
አቶ ሮቤል አክለውም ወጣቶች በተለያዩ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ስራቸውን በትጋት እያከናወኑ እንደሚገኙ አስታውቀው የስራ ባህላቸውን የቀየረ ኢንዱስትሪዎችም በዳበረ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል እንዲመሩ ማድረግ ያስቻለ ፕሮጀክት መሆኑን ነው አቶ ሮቤል በእለቱ ያስታወቁት ።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ እንዳሉት በብቃት ፕሮጀክት ፕሮግራም እንደ ሀገር 60 ሺህ 399 ወጣቶች ተመዝግበው ከ 54ሺ በላይ እንዳጠናቀቁና ለ 52 ሺህ ወጣቶች ደግሞ ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን ገልፀው በድሬዳዋ አስተዳደርም በሶስት ዓመታት 2 ሺህ 846 ወጣቶች ታቅፈው ከ 2 ሺህ 700 በላይ የሚሆኑት እንደተመረቁና ከነዚም መካከል 60 በመቶ ወጣት ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል ።
©️ DGC የካቲት 7/2018
"ብቃት" የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ለሶስተኛ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠና ላጠናቀቁ 946 ሰልጣኞች የምርቃት እና የማጠቃለያ መድረክ አካሄደ።
በመርኃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ እንዳሉት በብቃት ፕሮጀክት ፕሮግራም እንደ ሀገር 60ሺ 399 ወጣቶች ተመዝግበው ከ54ሺ በላይ የሚሆኑት ያጠናቀቁ እንዲሁም ለ52ሺ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን ገልፀዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደርም በሶስት ዓመታት 2ሺ 846 ታቅፈው ከ2ሺ 700 በላይ የሚሆኑት የተመረቁ እንደሆነ አመላክተዋል። ከእነዚም መካከል 60 በመቶ ወጣት ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ሚንስትር ዴኤታው አያይዘው ዛሬ የተመረቁት 946 ወጣቶች ብቁ ሆነው መውጣታቸው ትልቅ ተስፋ ነው ያሉ ሲሆን ስኬት የሚገኘው በትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን በስራ ቦታ ትጋት ነው ብለዋል።
የግሉ ዘርፍም ወጣቶችን ተቀብሎ እውቀት በማጋራት የስራ እድል በመፍጠር ሀብታቸውን ሳይሰስቱ በራቸውን ከፍተው ስለከፈቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንዳሉት ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን መቀጠል ያልቻሉ ወጣቶችን ለ12 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና በመስጠት በአስተዳደሩ ባሉ ድርጅቶች ላይ ለስድስት ወራት የስራ ላይ ልምምድ አድርገው በቋሚነት ተቀጣሪ ማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል።
ወጣቶች በተለያዩ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ስራቸውን በትጋት እያከናወኑ የሚገኙ እንደሆነ ገልፀው የስራ ባህላቸውን የቀየረ ኢንዱስትሪዎችም በዳበረ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል እንዲመሩ ማድረግ ያስቻለ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።
©️ DireTvአማርኛ | የካቲት 07 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
"ብቃት" የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ለሶስተኛ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠና ላጠናቀቁ 946 ሰልጣኞች የምርቃት እና የማጠቃለያ መድረክ አካሄደ።
በመርኃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ እንዳሉት በብቃት ፕሮጀክት ፕሮግራም እንደ ሀገር 60ሺ 399 ወጣቶች ተመዝግበው ከ54ሺ በላይ የሚሆኑት ያጠናቀቁ እንዲሁም ለ52ሺ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን ገልፀዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደርም በሶስት ዓመታት 2ሺ 846 ታቅፈው ከ2ሺ 700 በላይ የሚሆኑት የተመረቁ እንደሆነ አመላክተዋል። ከእነዚም መካከል 60 በመቶ ወጣት ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ሚንስትር ዴኤታው አያይዘው ዛሬ የተመረቁት 946 ወጣቶች ብቁ ሆነው መውጣታቸው ትልቅ ተስፋ ነው ያሉ ሲሆን ስኬት የሚገኘው በትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን በስራ ቦታ ትጋት ነው ብለዋል።
የግሉ ዘርፍም ወጣቶችን ተቀብሎ እውቀት በማጋራት የስራ እድል በመፍጠር ሀብታቸውን ሳይሰስቱ በራቸውን ከፍተው ስለከፈቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንዳሉት ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን መቀጠል ያልቻሉ ወጣቶችን ለ12 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና በመስጠት በአስተዳደሩ ባሉ ድርጅቶች ላይ ለስድስት ወራት የስራ ላይ ልምምድ አድርገው በቋሚነት ተቀጣሪ ማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል።
ወጣቶች በተለያዩ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ስራቸውን በትጋት እያከናወኑ የሚገኙ እንደሆነ ገልፀው የስራ ባህላቸውን የቀየረ ኢንዱስትሪዎችም በዳበረ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል እንዲመሩ ማድረግ ያስቻለ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።
©️ DireTvአማርኛ | የካቲት 07 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
