ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

前往频道在 Telegram
1 319
订阅者
无数据24 小时
+127 天
+14830 天
帖子存档
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም ወር በሰላም አደረሳችሁ። ረመዳን ከሪም !!
+1
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የረመዳን ፆም ወር በሰላም አደረሳችሁ። ረመዳን ከሪም !!

በአጫጭር ስልጠና ዘርፍ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ የስልጠና ተቋማቱን አቅም ለመገንባት ያለመ  የክትትልና ድጋፍ መርሃግብር ተካሄደ፤ በዚህም የድጋፍና ክትትል መርሃግብር   የአጫጭር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት በዕቅድ መሠረት ስለመመራታቸው፤ በቂ የስልጠና ግብዓት ስለመኖሩ፤ የስልጠና ፍቃድ በተመለከተ በተሰጠው ፈቃድ ልክ እየሰሩ ስለ መሆናቸውና  እንዲሁም የማሰልጠኛ ማንዋሎችና መሳሪያዎች በሚገባ መኖራቸውን ጨምሮ የአጠቃላይ ሰልጣኞችን መረጃ በማደራጀት እረገድ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከትና በቀጣይ በተከታታይ ድጋፍ የሚያገኙበትን አግባብ ለማመቻቸት ተችሏል፡፡ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል አደም እንደተናገሩት ይህ የድጋፍና ክትትል ልክ መደበኛ ስልጠና እንደሚሰጡ ተቋማት ሁሉ አጫጭር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማትም ዜጎችን በማሰልጠን የሚያበቁ ናቸው ስለሆነም ትምህርትና ስልጠና ተቋማቱን አቅም ለመገንባትና በቅርበት በመከታተል መደገፍ አላማው አድርጎ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 10/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኮሌጁን አሰልጣኝ መምህራንን በየጊዜው የሚሰሯቸውን የሚያሻሽሏቸውን ቴክኖሎጂዎች ተገቢውን የእሴት ሰንሰለት ትንተና በማድረግ ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በመደበኛው እና በአጫጭ
+6
የኮሌጁን አሰልጣኝ መምህራንን በየጊዜው የሚሰሯቸውን የሚያሻሽሏቸውን ቴክኖሎጂዎች ተገቢውን የእሴት ሰንሰለት ትንተና በማድረግ ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በመደበኛው እና በአጫጭር ስልጠና ሰልጣኞችን ተቀብሎ ከማሰልጠን በተጨማሪ ለአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ለኢንዱስትሪው ግብአት መሆን የሚችሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር እንዲሁም በማሻሻል የማህበረሰቡን እና የኢንዱስትሪውን ጫና መቀነስ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን መፍጠር እና ማሻሻል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡ በዚሁ መሰረት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች ተገቢውን የእሴት ሰንሰለት ትንተና ሊደረግባቸው ይገባል፡፡ ይህንንም ተግባር ለማከናወን የሚረዳ ስልጠና በዛሬው እለት በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ ትምህርት ክፍል ውስጥ ስልጠናን ለሚሰጡ አሰልጣኝ መምህራን እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የኮሌጁ ም/ዲን እና የኢ/ኤ/ቴ/ሽ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ በስልጠናው መክፈቻ ላይ በመገኘት እንደገለጹት በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን የሚሰሩ እንዲሁም የሚሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች የማህበረሰቡን ችግር እንዲሁም የኢንዱስትሪውን ጫና መቅረፍ የሚችሉ እንዲሆኑ ተገቢውን የእሴት ሰንሰለት ትንተና ማድረግና ትንተናውን ተከትሎ መስራት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን አያይዘውም የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራንና ሰልጣኝ ተማሪዎች የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እንዲፈጥሩና ለማህበረሰቡ ማቅረብ እንዲችሉ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን የካቲት 10/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የአካባቢውን ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ዘርፎች እና በዲጂታል ክህሎት የበቁ እንዲሆኑ ሁሉን አካታች ስራ እየሰራ እንዳለ ኮሌጁ ገለጸ፡፡ አካታችነት፣ዲጂታላይዜሽን፣የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና መልሶ የመጠቀም እንዲሁም የኢንዱስትሪ ትስስር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡ በዚሁ መሰረት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰጡ ስልጠናዎች አካታች እንዲሆኑና ትምህርትና ስልጠና መጪውን ዘመን የዋጀ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ይጠበቃል፡፡ የትኩረት አቅጣጫውን ወደ ተግባር ለመለወጥ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ምን እንደሚመስሉ በጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ የሚመራው CIFA for People (Second Life) ፕሮጀክት ተወካዮች ተጎብኝቷል፡፡ የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት የአካባቢውን ወጣቶችን በተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፎች በማሰልጠን ወደ ሥራ እንዲገቡ እያደረገ ይገኛል።ያሉ ሲሆን አያዘውም በኮሌጁ የሚሰጡ ስልጠናዎች ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ እንዲሰማሩና የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ እንዲመሰርቱ የሚያስችል እንዲሁም መጪውን ዘመን የዋጀ የኢንዱስትሪ ትስስር በመፍጠር ሰልጣኞች ገበያው ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያደርጉ ሰልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ከኤጀንሲው ጋር በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና መልሶ አጠቃቀም፣በዲጂታላይዜሽን እንዲሁም ከኢንዱስትሪ ትስስር ጋር በስፋት የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ በኮሌጁ ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉት በጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ የሚመራው CIFA for People (Second Life) ፕሮጀክት ተወካዮች በበኩላቸው በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እየተከናወነ ያለው ተግባር መልካም መሆኑን ገልጸው በተለይም ወጣቶች የሚያገኙትን እውቀት ወደ ገቢ ምንጭ በመቀየር የተሻለ ህይወት እንዲመሩ እየተደረገ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ይህንንም የኮሌጁን ጥረት በተለያዩ ለመደገፍ በጋራ የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን የካቲት 7/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ለሶስተኛ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠና ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምርቃት እና የማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ       " ብቃት ፣ ክህሎት ፣ ስኬት " በሚል መሪ ሀሳብ ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሶስተኛ ዙር ማጠቃለያ መርሀ ግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል።     በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሮቤል ጌታቸው ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን መቀጠል ያልቻሉ ወጣቶችን ለ 12 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና በመስጠት በአስተዳደሩ ባሉ ድርጅቶች ላይ ለስድስት ወራት የስራ ላይ ልምምድ አድርገው በቋሚነት ተቀጣሪ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል ።      አቶ ሮቤል አክለውም ወጣቶች በተለያዩ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ስራቸውን በትጋት እያከናወኑ እንደሚገኙ አስታውቀው የስራ ባህላቸውን የቀየረ ኢንዱስትሪዎችም በዳበረ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል እንዲመሩ ማድረግ ያስቻለ ፕሮጀክት መሆኑን ነው አቶ ሮቤል በእለቱ ያስታወቁት ።      የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ እንዳሉት በብቃት ፕሮጀክት ፕሮግራም እንደ ሀገር 60 ሺህ 399 ወጣቶች ተመዝግበው ከ 54ሺ በላይ እንዳጠናቀቁና ለ 52 ሺህ ወጣቶች ደግሞ ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን ገልፀው በድሬዳዋ አስተዳደርም በሶስት ዓመታት 2 ሺህ 846 ወጣቶች ታቅፈው ከ 2 ሺህ 700 በላይ የሚሆኑት እንደተመረቁና ከነዚም መካከል 60 በመቶ ወጣት ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል ። ©️ DGC የካቲት 7/2018

"ብቃት" የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ለሶስተኛ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠና ላጠናቀቁ 946 ሰልጣኞች የምርቃት እና የማጠቃለያ መድረክ አካሄደ። በመርኃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ እንዳሉት በብቃት ፕሮጀክት ፕሮግራም እንደ ሀገር 60ሺ 399 ወጣቶች ተመዝግበው ከ54ሺ በላይ የሚሆኑት ያጠናቀቁ እንዲሁም ለ52ሺ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን ገልፀዋል። በድሬዳዋ አስተዳደርም በሶስት ዓመታት 2ሺ 846 ታቅፈው ከ2ሺ 700 በላይ የሚሆኑት የተመረቁ እንደሆነ አመላክተዋል። ከእነዚም መካከል 60 በመቶ ወጣት ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል። ሚንስትር ዴኤታው አያይዘው ዛሬ የተመረቁት 946 ወጣቶች ብቁ ሆነው መውጣታቸው ትልቅ ተስፋ ነው ያሉ ሲሆን ስኬት የሚገኘው በትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን በስራ ቦታ ትጋት ነው ብለዋል። የግሉ ዘርፍም ወጣቶችን ተቀብሎ እውቀት በማጋራት የስራ እድል በመፍጠር ሀብታቸውን ሳይሰስቱ በራቸውን ከፍተው ስለከፈቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንዳሉት ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን መቀጠል ያልቻሉ ወጣቶችን ለ12 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና በመስጠት በአስተዳደሩ ባሉ ድርጅቶች ላይ ለስድስት ወራት የስራ ላይ ልምምድ አድርገው በቋሚነት ተቀጣሪ ማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል። ወጣቶች በተለያዩ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ስራቸውን በትጋት እያከናወኑ የሚገኙ እንደሆነ ገልፀው የስራ ባህላቸውን የቀየረ ኢንዱስትሪዎችም በዳበረ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል እንዲመሩ ማድረግ ያስቻለ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል። ©️ DireTvአማርኛ | የካቲት 07 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ    

"ብቃት" የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ለሶስተኛ ዙር የህይወት ክህሎት ስልጠና ላጠናቀቁ 946 ሰልጣኞች የምርቃት እና የማጠቃለያ መድረክ አካሄደ። በመርኃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ እንዳሉት በብቃት ፕሮጀክት ፕሮግራም እንደ ሀገር 60ሺ 399 ወጣቶች ተመዝግበው ከ54ሺ በላይ የሚሆኑት ያጠናቀቁ እንዲሁም ለ52ሺ ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን ገልፀዋል። በድሬዳዋ አስተዳደርም በሶስት ዓመታት 2ሺ 846 ታቅፈው ከ2ሺ 700 በላይ የሚሆኑት የተመረቁ እንደሆነ አመላክተዋል። ከእነዚም መካከል 60 በመቶ ወጣት ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል። ሚንስትር ዴኤታው አያይዘው ዛሬ የተመረቁት 946 ወጣቶች ብቁ ሆነው መውጣታቸው ትልቅ ተስፋ ነው ያሉ ሲሆን ስኬት የሚገኘው በትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን በስራ ቦታ ትጋት ነው ብለዋል። የግሉ ዘርፍም ወጣቶችን ተቀብሎ እውቀት በማጋራት የስራ እድል በመፍጠር ሀብታቸውን ሳይሰስቱ በራቸውን ከፍተው ስለከፈቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንዳሉት ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን መቀጠል ያልቻሉ ወጣቶችን ለ12 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና በመስጠት በአስተዳደሩ ባሉ ድርጅቶች ላይ ለስድስት ወራት የስራ ላይ ልምምድ አድርገው በቋሚነት ተቀጣሪ ማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል። ወጣቶች በተለያዩ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ስራቸውን በትጋት እያከናወኑ የሚገኙ እንደሆነ ገልፀው የስራ ባህላቸውን የቀየረ ኢንዱስትሪዎችም በዳበረ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል እንዲመሩ ማድረግ ያስቻለ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል። ©️ DireTvአማርኛ | የካቲት 07 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ    

#አሁን #Happening_Now ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሶስተኛ ዙር ማጠቃለያ መርሃ-ግብር የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የካቲት 7/2018 ዓ.ም
+2
#አሁን #Happening_Now ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሶስተኛ ዙር ማጠቃለያ መርሃ-ግብር የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የካቲት 7/2018 ዓ.ም

#በአጭር ጊዜ የራስዎን ድርጅት መክፈት ይፈልጋሉ? #ፈጠራ እና ውበት ያላቸውን የEPOXY ምርቶችን አምርተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ገበያው ላይ ተፈላጊ መሆን ከፈለጉ አንድ አንጋፋ ኮሌጅ ልጠቁማችሁ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ #በተመጣጣኝ ዋጋ እጀ ወርቅ እናደርግዎታለን ይምጡ ይሰልጠኑ ባለሙያ ይሁኑ #አድራሻችን ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ወደ ኤርፖርት በሚወስደው መንገድ ላይ እንገኛለን

የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 ይጀምራል ፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ **** የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀመር አ
የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 ይጀምራል ፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ **** የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀመር አስታወቀ። ቦርዱ እስካሁን ያከናወናቸውን የቅድመ ምርጫ ሥራዎችና ተያያዥ ውሳኔዎችን አስመልክቶ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት፣ ቀደም ሲል የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 7 እስከ መጋቢት 7 ቀን ለማከናወን ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ቀሪ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለማጠናቀቅ ሲባል የምዝገባው መጀመሪያ ቀን ወደ የካቲት 28 እንዲራዘም ተደርጓል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የእጩዎች ምዝገባ ማብቂያ ጊዜም ወደ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ተራዝሟል። 109 ቀናት የቀሩት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቦርዱ ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ አስታውቀዋል። ©️Ethiopian Broadcasting Corporation

በድሬዳዋ አስተዳደር ስራ ፈጣሪና ስራ ፈላጊ የሆኑ ወጣቶችን ለማበረታታት በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ በተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፎር አፍሪካ ልዑካን ቡድን በዛሬው እለት በድሬዳ
+5
በድሬዳዋ አስተዳደር ስራ ፈጣሪና ስራ ፈላጊ የሆኑ ወጣቶችን ለማበረታታት በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ በተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፎር አፍሪካ ልዑካን ቡድን በዛሬው እለት በድሬዳዋ አስተዳደር ስላለው የኢኮኖሚ እና የወጣቶች የስራ አጥነት ሁኔታ እንዲሁም ከፍልሰት ጋር ተያይዞ የተለያዩ ጥናቶች በማካሄድ በቀጣይ ለችግሮቹ መፍትሄ የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ውይይት አካሂደዋል ። በእለቱም የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አዲሱ እሳቤ ምን እንደሚመስል ፣ የስራ እድል ፈጠራ ስራዎች ከዚህ ቀደም የነበረውና አሁን ላይ በአዲስ መልክ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ፣ የኢንደስትሪ ሰላም ግንኙነት አዳዲስ እይታዎች እንዲሁም ደግሞ የተሻሻለው የወጣቶች ፖሊሲ ይዟቸው የመጣው አዳዲስ ሀሳቦች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት መደረጉን የድሬዳዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል ። በድሬዳዋ አስተዳደር ስራ ፈጣሪ የሆኑ እና ስራ ፈላጊ ወጣቶችን እንዲሁም ደግሞ በከተማዋ ያሉትን ፋብሪካዎች መመልከታቸውን በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የሶሻል ዲቪዥን አማካሪ የሆኑት አቶ ጀላል አብዱለጢፍ ተናግረው በቀጣይም በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራዎች ላይ በርካታ ስራዎችን ለመስራት እቅድ እንዳላቸውም አስታውቀዋል። ©️ DGC የካቲት 4/2018

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ SIFA ፕሮጀክት እንዲሁም በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የScience, Technology and Innovation Week 2026 ኤግዝቪሽን ላይ እያስተዋወቀ ይገኛል
+3
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ SIFA ፕሮጀክት እንዲሁም በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የScience, Technology and Innovation Week 2026 ኤግዝቪሽን ላይ እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ከFeb 11-15/2026 በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን በዚህ የመሪዎቸ ስብሰባ ጎን ለጎን የScience, Technology and Innovation Week 2026, Exhibition ከFeb 10 - 11, 2026 በSkylight Hotel በይፋ የተከፈተ ሲሆን በዚህ ኤግዚቪሽን ላይም የኮሌጁ ልኡክ ቡድን ከተለያዩ አለማት ስብሰባውን ለመሳተፍ አዲስ አበባ ለሚገኙ እንግዶች በኮሌጁ እንዲሁም በ SIFA ፕሮጀክት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የማስተዋወቅ ስራዎች እየሰራ ይገኛል። በትናንትናው እለት የተጀመረው መርሃ ግብር "Shaping African's Future through AI, Science, Technology and Innovation" በሚል መሪ ቃል የተጀመረ ሲሆን በዚህም ረገድ ኮሌጁ ያለውን ልምድና ተሞክሮ ኤግዚቪሽኑን ለመታደም ለመጡ እንግዶች አቅርቧል። የኮሌጁ ኮምኒኬሽን የካቲት 4/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ለኢኮኖሚ ዕድገት ዋነኛው ሞተርና ለብቁ የሰው ኃይል ግንባታ መሠረት ነው። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ወጣቶች አስፈላጊ ክህሎቶችን እንዲታጠቁ በማድረግ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠ
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ለኢኮኖሚ ዕድገት ዋነኛው ሞተርና ለብቁ የሰው ኃይል ግንባታ መሠረት ነው። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ወጣቶች አስፈላጊ ክህሎቶችን እንዲታጠቁ በማድረግ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለኢንዱስትሪ ሽግግሩ ስኬት ጽኑ መሠረት በመጣል ላይ ትገኛለች። በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የሚሰጥባቸው ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው፦ 1. ማኑፋክቸሪንግና ኢንዱስትሪ 2. ኮንስትራክሽንና መሰረተ-ልማት 3. መረጃና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) 4. ንግድ፣ ፋይናንስና አገልግሎት 5. ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት 6. ጤናና ማኅበራዊ አገልግሎት #EthiopianBroadcastingCorporation #technical #vocationaltraining

"ቤተሰባዊነትን ያስቀደመ ተቋም ተልዕኮውን ከግብ ለማድረስ የሚያደርገው ጉዞ ቀልጣፋና ውጤታማ ይሆናል" አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የመረዳጃ ዕድር ይፋዊ ምስረታ አንደኛ አመት ምክንያት በማድረግ መርሃግብር ተካሄደ። በዚህ መርሃግብር ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው አመራሩ እና ሠራተኛው በደስታና በሃዘን የሚገጥማቸውን የህይወት ገጠመኞች በመረዳዳትና በመደጋገፍ የሚያደርጉት መተጋገዝ በቀጥታ በመንግስታዊ ተልዕኮ መፈጸም ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንዳለው ገልጸው ቢሮውም ይህን ቤተሰባዊነት የሚያጠናክር ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የመረዳጃ ዕድር ኮሚቴ ተወካዮች በበኩላቸው የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና ማኔጅመንታቸው ዕድሩን የሚያጠናክሩ የተለያዩ ድጋፎችን ስላደረጉ እና ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ስላበረከቱ አመሥግነዋል። በማጠቃለያውም ባለፈው አንድ አመት የተከናወኑ ተግባራትና የፋይናንስ ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በተለያየ ምክንያት በተጓደሉ የመረዳጃ ዕድሩ ኮሚቴ አባላት ምትክ አዲስ የኮሚቴ አባላትን በመምረጥ መርሃግብሩ ተጠናቋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 1/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ