en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Open in Telegram
1 321
Subscribers
+124 hours
+77 days
+14530 days
Posts Archive
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሦስተኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ አምስተኛ ዙር የአቻ ለአቻ ውይይት ተካሄደ።
+4
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሦስተኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ አምስተኛ ዙር የአቻ ለአቻ ውይይት ተካሄደ።

#ዜና /"የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ለወጣቶች አዳዲስ እና በገበያው ላይ ተፈላጊ የሆኑ የሙያ ዘርፎችን በማሰልጠን ወጣቶችን የሙያ ባለቤት እያረጉ ይገኛሉ"- የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር #DGC ጥቅምት 1/2018 የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠኑአቸውን 1042 ሰልጣኞችን በድምቀት እያስመረቁ ይገኛል። በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለተመራቂ ሰልጣኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ለምታደርገው ጉዞ በሙያዊ ክህሎትና ሥነ-ምግባር የታነፀ፣ ለሥራ ፍቅርና ተነሳሽነት ያለው እንዲሁም ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሠራሮች ጋር ተዋህዶ መሥራት የሚችል የሰው ኃይል በብዛት እና በጥራት በማሰልጠን ረገድ ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ጉል ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል። በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ለወጣቶች አዳዲስ እና በገበያው ላይ ተፈላጊ የሆኑ የሙያ ዘርፎችን በማሰልጠን ወጣቶችን የሙያ ባለቤት እያረጉ እንደሚገኙም ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ገልፀዋል። ከንቲባ ከድር አያይዘውም ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ትኩረት ሰጥተው የሰሩ ሀገሮች ዛሬ ላይ የደረሱብት የኢኮኖሚያዊ እመርታ እና የቴክኖሎጂ የበላይነትን ላይ እንዲደርሱ እንዳስቻላቸው ጠቁመው፤ በሀገራችንም ዋነኛ ተግዳሮት የሆነውን ስራ አጥነትን ለማስወገድና ለሀገራችን ዘላቂ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የድሬዳዋ ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች በቴክኖሎጂ ታግዘው እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል። በመጨረሻም ከንቲባ ከድር ተመራቂ ሰልጣኞች በስልጠናው ወቅት ያሳዩትን የሙያ ፍቅር እና ዲሲፒሊን በስራው ዓለምም በማስቀጠል በተለይም በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና እና በሌሎችም በተፈጠሩት የኢንደስትሪ ማዕከላት በመሰማራት ድሬዳዋን ብሎም ሀገርን የሚጠቅም ስራ እንዲሰሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ©️ DGC

#አሁን #Happening_Now የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች ምረቃ ስነ-ስርዓት
#አሁን #Happening_Now የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች ምረቃ ስነ-ስርዓት

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት የGRM ኮሚቴ የ2018 የመጀመሪያ ሩብ አመት መደበኛ ስብሰባውን አከናወነ፡፡ በኮሌጁ እየተገነባ ያለው የልህቀት ማእከል ግንባታው ምንም ችግር ሳይፈ
+6
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት የGRM ኮሚቴ የ2018 የመጀመሪያ ሩብ አመት መደበኛ ስብሰባውን አከናወነ፡፡ በኮሌጁ እየተገነባ ያለው የልህቀት ማእከል ግንባታው ምንም ችግር ሳይፈጠር እና ማህበረሰቡ ላይ ተጽእኖ ሳይኖረው በአግባቡ ተገንብቶ ለሚፈለገው አላማ እንዲውል እንዲሁም ችግር ቢከሰት በተገቢው መንገድ እንዲፈታ እያደረገ ላለው አስተዋጽኦ የGRM ኮሚቴ ምስጋና ያቀረቡት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ አያይዘውም ባለፉት አመታት በኮሌጁ፣ በኮሚቴው እንዲሁም በፕሮጀክቱ በኩል የተሰሩ ስራዎች አመርቂ መሆናቸውን የተናገሩ ሲሆን ባለፉት አመታት የተገኘውን ልምድ በመጠቀም በቀጣይም የሚሰሩ ስራዎች በሙሉ የማህበረሰቡን፣ የኮሌጁ እንዲሁም የመንግስትን ፍላጎት በተከተለ መልኩ ሊሰራና ችግሮችም በተገቢው መንገድ እንዲፈቱ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን መስከረም 29/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ ለወቅታዊ ትኩስ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መረጃ You tube: Dire Dawa Polytechnic College(DDPTC) Facebook: https://web.facebook.com/Dire Dawa Polytechnic College Regional Flagship TVET Institute Telegram: t.me/Dire Dawa Polytechnic College TikTok: tiktok.com/@diredawapolytechnicollege

#ዜና | በስራ እድል ፈጠራና በስራ ፈጠራ አገልግሎት ዙሪያ ስልጠና መስጠት ተጀመረ #DGC መስከረም 29/2018 የድሬዳዋ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጄክት ምዕራፍ ሁለት በገጠር ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የአመራር በቡድን ክህሎት፣በስራ እድል ፈጠራና በስራ ፈጠራ አገልግሎት ዙሪያ የተዘጋጀ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡ስልጠናው ከፌደራል ፕሮጀክት ዩኒት እና ከድሬዳዋ ስራና ክህሎት ቢሮ ለተውጣጡ ባለሞያዎች የሚሰጥ ነው። በስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ኢሳም ሁሴን የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻል ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጠጥ ውሃ፣የመንገድ ግንባታ ፣የገጠር ቁጠባ እና ብድር ማህበራት ማደራጀት ፣በስራ እድል ፈጠራ እና በግብርና ዘርፍ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ፕሮጀክቱ የመንግስት የልማት አቅጣጫ ከመደገፍ አንፃር በሌማት ቱሩፋት እና አረንጓዴ አሻራ ላይ ሰፊ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግዋል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ፈቺና ፋይዳቸው ላቅ ያሉ ስራዎን እየሰራ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ የዛሬው ስልጠና በመሰረታዊነት በዚህ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው በአዲስ የሚመሰረቱ 40 ያህል ማህበራት የወረዳ አመራሮች ባለድርሻ አካላት ወደ ስራ ከመግባታቸው አስቀድሞ ስለአፈፃፀም ሂደቱ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይህ ስልጠና መዘጋጀቱን አውስተዋል። ዛሬ ስለ ስራ ፈጠራ አገልግሎት፣ የንግድ ስራ ዕቅድ ዝግጅት እና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተዘጋጀ መመሪያን በተመለከተ ግንዛቤ ተሰጥቷል። በግብርና እንዲሁም በሌሎች ከግብርና ዘርፍ ውጪ ባሉ የስራ ዕድሎች ላይ ተሰማርተው የሚደረግላቸውን ድጋፍ ለተገቢ ዓላማው በማዋል ኑሯቸውን የሚያሻሽሉበት ሁኔታ ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡LLRP2 የአርብቶ እና አርሶ አደር ማህበረሰብ የኑሮ ሁኔታን ማሻሻልና የምርትና ምርታማነት ማሳደግ ሂደቱን መደገፍ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡ በገጠር ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የአመራር፣ በቡድን ክህሎት፣በስራ እድል ፈጠራና በስራ ፈጠራ አገልግሎት ዙሪያ በተዘጋጀው ስልጠና የስራ ክህሎት ቢሮ ባለሞያዎች ፣የወረዳ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰራተኞች የወረዳ አስተባባሪዎ እና ባለሞያዎች በስልጠናው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል ሲል ዘገባውን ያደረሰን የግብርና ውሀ መአድን እና ኢነርጂ ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ነው።

ለፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን የተዘጋጀ በተግባር የተደገፈ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሄደ፡፡ ይህ የአቅም ግንባታ መድረክ የኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ሙያዊ ብቃታቸውን ከማሳደግ ባሻገር በየሙያ መስኩ በየኢንዱስትሪው ተግባራዊ ዕውቀትና ክህሎት የሚያገኙበት ሆኖ መሰናዳቱና የተሻለ ልምድና ተሞክሮዎችን ከአቻዎቻቸው የሚቀስሙበትን ዕድል የሚፈጥር መድረክ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረዋል፡፡ የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በበኩላቸው ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃት እንዲሳተፉ እና ስልጠናውን አጠናቀው ሲጨርሱ በማሰልጠን የስልጠና ጥራትን ለማሻሻልና የሥራ ገበያውን ፍላጎት ለመመለስ በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ርብርብ ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ለማበርከት ከወዲሁ እንዲዘጋጁ አሳስበዋል፡፡ በዚህ የአቅም ግንባታ ስልጠና የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን ተሳታፊ ሲሆኑ ገበያው የሚፈልገውን ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ ለማፍራት የአሰልጣኞችን ብቃት ተከታታይነት ባለው መልኩ ማሳደግ ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይም ትኩረት እንደሚሰጠውም በቢሮው የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መስከረም 27/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች በዛሬው  እለት “ከጂኦስትራቴጂ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና እና ወደ ተሻለ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ የመንግስት ያለፉት ዓመታት ጉዞና የቀጣይ ዓመታት የትኩረት መስኮች ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ  አካሄደዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት ሰራተኞች በሀገራዊ ቀጣይ የእድገት ጉዞ ላይ የጠራ ግንዛቤን እንዲጨብጡና ለሀገራዊ ለውጡ በሁሉም መስክ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አቅም የሚፈጥርላቸው ይሆናል። መድረኩም የድሬዳዋን እድገትና ተምሳሌትነት እንዲሁም የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በቀጣይም የመንግስትን አሻጋሪ ዕሳቤዎች በቁርጠኝነት ለመፈፀምና ለማስፈፀም ተግባቦት የፈጠረ መሆኑን ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መስከረም 27/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

#ዜና |የቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና በገበያ ተፈላጊ በሆነ ሞያና ክህሎት የበቁ ዜጎችን በማፍራት ብዙዎች ተጠቃሚ እነሆኑ ነው ። #DireTvአማርኛ | መስከረም 27፥2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ የሞያና ክህሎት ስልጠና ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘብ በኩልም የህብረተሰቡ ንቃት መዳበሩ ይነገራል። በዚህ ዙሪያ የድሬዳዋ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ከቴክኒክና ሞያ ሰልጥነው ስራ ላይ ከተሰማሩ ነዋሪዎች ጋር ቆይታ አድርጓል። ነጃት ተገኔ እንደሚከተለው አዘጋጅታዋለች

Repost from E-LMIS - ብቁ
ክፍት የሥራ ማስታወቂያ ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ! ኦቪድ ሆልዲንግ (Ovid Holding) በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS በኩል በExecutive Assi
ክፍት የሥራ ማስታወቂያ ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ! ኦቪድ ሆልዲንግ (Ovid Holding) በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS በኩል በExecutive Assistant የሥራ መደብ ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ። ስለሆነም በዚህ የሥራ እድል ለመመዝገብና ለመወዳደር በቅድሚያ lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ ወረዳ/ቀበሌ የአንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር/ labor ID/ ይዛችሁ በዚህ https://forms.lmis.gov.et/ovid/ ማስፈንጠሪያ በመግባት ትክክለኛ የትምህርት፣ የስራ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎቻችሁን በማሰገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

“የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ለወጣቶች ሥራ ፈጠራ” የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ ሙያዎች የአካባቢውን ወጣቶች ሕይወትን እንዴት እየለወጠ እንዳለ ይወቁ። 🌍💻 በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተተገበረው ይህ ስልጠና በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የክህሎት ስልጠና እና የኢንተርፕረነርሺፕ ኮርሶችን በመስጠት ወጣቶችን በፋሽን ዲዛይን ዘርፍ የስራ ተጠቃሚነትን እያሳደገ ይገኛል። በኮሌጁ በተሰጠዉ ክህሎት እና የስልጠና እድሎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ስኬታማ ሆና ያገኘችውን የቴ/ሙ/ት/ምና ስልጠና እየሰለጠነች ያለቸውን ወጣት ውብርስት ጸጋዬን አድምጡ። ለወቅታዊ ትኩስ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መረጃ You tube: Dire Dawa Polytechnic College(DDPTC) Facebook: https://web.facebook.com/Dire Dawa Polytechnic College Regional Flagship TVET Institute Telegram: t.me/Dire Dawa Polytechnic College TikTok: tiktok.com/@diredawapolytechnicollege