cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

የስነ-ልቦና ትምህርቶችን በነፃ ያግኙ

Show more
Advertising posts
89 557
Subscribers
+35024 hours
+3 9057 days
+13 83630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ትዳር!!!… ፍቅር!!!…(የተገጣጠሙ – ገጠመኞች) “…ባሌ ውስጥ ባሌን አጣሁትና ባሌን ፍለጋ ወክ አደርጋለሁ፡፡…” ክፍል 5 አንድ ወዳጄ ያጫወተኝን ደግሞ ላውጋችሁ፡፡  ወዳጄ አለቃ አለችው፡፡ – እርጉዝ አይደለችም ግን – አማረኝ ማለት ትወዳለች፡፡ አማረኝ ባለች ቁጥር ደስ ይለዋል፡፡ ገንዘብ ትሰጠውና ገዝቶ ያመጣል፡፡ አትበላም – ለተሳትፎ ያህል ለኮፍ ለኮፍ አድርጋ ትተዋለች፡፡ እሱ ጥርቅም አድርጎ ይበላል፡፡ እሷ ያምራታል – እሱ ይበላል፡፡ እርጉዝ ሆና ስላላወቃት ቁጭት ያንገበግበዋል፡፡ “ እንዴት ትመቸኛለች መሰለህ?…” ድንጋጤ ፊቱ ላይ እየተነበበበት ዞር – ዞር ብሎ አካባቢውን ቃኘ፡፡ “እኔ ሌላ ነገር አላልኩም፡፡ – የተመቸችኝ አማረኝ ብላ የምታስገዛውን ሆዴን እያሻሸሁ ጥብስቅ አድርጌ ስለምበላ ብቻ ነው፡፡…” ሳቅ አለ፡፡ ምነው ሳቅክ?… ወዳጄን ጠየቅኩት “አንድ ቀን ጠዋት የመስሪያ ቤታችን በር ላይ እኩል ደረስን፡፡ ግቢውን አልፈን ጎን- ለጎን እያወራን የቢሮዋ በር ላይ ደረስን፡፡ በሩን ከፍታ ወደ ወንበሯ ስትራመድ ትኩር ብዬ ከኋላዋ አስተዋልኳት፡፡ እንዴት ታምራለች?!!!…” ቀልቧ ነገራት መሰለኝ ሳትቀመጥ ዞር ብላ አየችኝ፡፡ – ሳቅ አለች እና  “… አይዞህ !!!… አይነ-ስጋ ይቻላል፡፡” አላገጠችብኝ፡፡ ከዚያ ወዲህ በሙሉ አይኔ አይቻት አላውቅም፡፡ ትላንት ታድያ በጠዋቱ የስራ ጠረጴዛዬ ድረስ መጥታ “አማረኝ” አለችኝ፡፡ ከቤት ስወጣ ቁርስ አልበላሁም ነበርና ወስፋቴ ተንጫጫ፡፡ ምን አማረሽ?… ገንዘብ እንድትሰጠኝ እጄን ዘረጋሁ፡፡ ሳቅ አለችና “ያማረኝ የድሮ ቦይ -ፍሬንዴ ነው!!!… እሱንም ትበላው?…” ኩምሽሽ አልኩ፡፡ “ኤድያ!!!…. ስንት የሚበላ ነገር እያለ በዚህ ሰአት የድሮ – ቦይፍሬንዷ ያምራታል?!!!…. የድሮ ቦይፍሬንዷን ባላውቀውም ሲያስጠላ!!!… ብየዋለሁ፡፡” ባወራልኝ ታሪክ ከልቤ ስቄ ሳልጨርስ – “ ታሪኩ ሳያልቅ ምን ያስገለፍጠሀል?…” ብሎ ክው አደረገኝ፡፡ ቀጠለ፡፡ “… ባሏን አውቃቸዋለሁ፡፡ በእድሜ አይመጣጠኑም፡፡ ከባሏ ጋር አልጋ ላይ ሆና እንኳ የድሮ – ቦይፍሬንዷን ታስታውሰዋለች፡፡ ባሏን የምትስማቸው የድሮ – ቦይፍሬንዷን እየሳመችው እንደሆነች ለራስዋ አሳምና ነው፡፡…” እንዴ !!!… የታሪኩን ዙር አከረርከው እኮ!!! ኮስተር አልኩበት፡፡ እንዳልሰማ ሆኖ ወሬውን ቀጠለ፡፡ የድሮ ቦይፍሬንዷ ደግሞ አገር ውስጥ የለም ፡፡ የራሱን ኑሮ ይመራል፡፡ ከነመፈጠሯም ረስቷታል፡፡ እሷ ግን ለደቂቃዎች ከህሊናዋ አውጥታው አታውቅም፡፡ አብረው እያሉ ትልቁ መዝናኛቸው ምግብ ነበረ፡፡ – ለዚህ ነው በየግዜው ላትበላው “አማረኝ” የምትለው፡፡ “ ባልሽ ያውቃሉ?…. ያ… ያወቃል?…” ፈገግ ብላ “… አያውቅም፡፡ – ለምን እንዳገባሁት አላውቅም፡፡ ግን መገመት እችላለሁ፡፡ – ገንዘብ ፈልጌ አይደለም፡፡… የድሮ ቦይፍሬንዴ ጥሎኝ – ደህና ሁኝ እንኳ ሳይለኝ ከሀገር ሲወጣ አጠገቤ ሆኖ ያፅናናኝ አባቴ ነበረ፡፡ አባቴ ሲሞት የአባቴን ፍቅር የሰጠኝ ይህ ባሌ ነው፡፡ በቃ!!!…. አባቴን ይመስለኛል፡፡…” የሚገርም ትዳር ነው፡፡ – ጓደኛዬ ባወራልኝ ታሪክ አግራሞት ተለጉሜ ዝም አልኩኝ፡፡ አንድ የሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ገጠመኜን ደግሞ ልቦንሳችሁ፡፡ ሚኒባስ ነው፡፡- የተቀመጥነው ደግሞ የመጨረሻው ወንበር ላይ ለአራት፡፡ ሁለት ሴቶችና ሁለት ወንዶች፡፡ ቆይ…ቆይ!!!…. ሚኒባስ ውስጥ የመጨረሻው ወንበር ላይ ከሴቶች ጋር ስቀመጥ የሚጠበኝ ለምንድነው?… እኔ እየሰፋሁ ነው ወይስ?… እኔን ጠቦኝ ጨንቆኛል፡፡ በዛ ላይ ደግሞ ታክሲው በጣም ይሞቃል፡፡ – የሆነ ሰው ፀሀይን ይዞ የተሳፈረ ይመስላል፡፡ አንዱ ጎረምሳ ከእኔ በስተቀኝ የመስኮቱን ጥግ ተደግፎ ባለው ክፍት ቦታ እግሩን ዘርግቶ በግምት የአራት አመት ህፃን ልጅ አቅፎ ተቀምጧል፡፡ በስተግራዬ የተቀመጡት እና በአለባበስ ዘመናዊነት የሚንፀባረቅባቸው ወጣት ሴቶች “ሲያምር… ሲያምር….” ሲባባሉ ሰማሁና እኔን መስሎኝ በደስታ ልቤ በሰውነቴ ልክ ሆነች፡፡ ዞር ብዬ ሳያቸው “ሲያምር” የሚሉት ለካ ህፃኑን ነው፡፡ M እንደዚህ ግን ልብን ማንጠልጠል ይቻላል?… “ልጅህ ነው?…” በህብረት ጠየቁት “አዎ!!!…” ልጁ ቆንጆ ስለተባለ ጎረምሳው ደረቱን ነፋ አደረገ፡፡ “ በእናቱ ወጥቶ ነው፡፡ እናቱ ቆንጆ ነች ማለት ነው!!!…” መልእክታቸው ግልፅ ነበርና ቡፍ!!!… ብዬ ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ ጎረምሳው የበሸቀ ይመስላል፡፡ – በቅኔ እንደጎሸሙት ገብቶታል፡፡ “ይሆናል!!!… ግን እናቱን አላውቃትም!!…” ኮስተር ብሎ መለሰላቸው፡፡ “እንዴት?…” አይናቸውን በልጥጠው ተጠጉት “ከማንኛዋ እንዳረገዝኩት አላወቅኩም!!!….” ቂቂቂቂቂ… (አንተኛው ወዳጄ!!!… “ሞቷል ብላችሁ ለእድር ነግራችሁ አስለፍፉና አባዬ – የልጄ አባት – ባሌ ምንምን እያሉ የሚመጡትን ከድንኳኑ ጀርባ ሆኜ ልቁጠራቸው!!!…” ያልከኝ- እንዴት ነው?… በኋላ “አለሁ!!!” ስትል “ያለ መስሎት ነው እንጂ ሞቷል!!!… ስለዚህ ሞቷል ይባልልን!!!…” ብለው ፍርድ ቤት ቢገትሩህስ?…ቂቂቂቂቂ….) እኛ ሰፈር ውስጥ አንድ “ ሴት አትለፈኝ!!!…” የሚሉ የሽማግሌ ፍንዳታ ነበሩ፡፡ ባለትዳር ናቸው፡፡ ሚስታቸው የባላቸውን አመል ቢያውቁም “ለልጆቼ!!!” እያሉ አብረው ይኖራሉ፡፡ ታድያ የእኛ እናቶች አንዲት ሴት “ አረገዘች!!!…” የሚል ወሬ ሲሰሙ የመጀመሪያ ጥያቄአቸው “ከማን እንዳረገዘች ታውቋል?…” ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!              ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን #ይቀጥላል @BiniGirmachew     @BiniGirmachew
Show all...
👍 2🥰 1🙏 1
ትዳር!!!… ፍቅር!!!…(የተገጣጠሙ – ገጠመኞች) “…ባሌ ውስጥ ባሌን አጣሁትና ባሌን ፍለጋ ወክ አደርጋለሁ፡፡…” ክፍል 4 “ ምን አስቤ እንደነበረ ታውቃለህ?…” ምን?… ጥያቄውን በጥያቄ መለስኩለት፡፡ “ ፖሊስ ጠርቼ ላስይዘው ነበር!…. ላዋርደው!!!… ግን አሁን የደነገጠው ራሱ በቂ ነው ብዬ ተውኩት፡፡ ” በወንጀል ስነ-ስርአት ህጋችን መሰረት አንተኮ ይህን ወንጀል ጠቁመህ ሰውየው እንዲያዙ ማድረግ አትችልም፡፡ ጋብቻ የህግ ጥበቃ ይደረግለታል፡፡ ሰውየውን በፖሊስ እንዲያዙ ማድረግ የሚችሉት ሚስትየው ብቻ ናቸው፡፡ “ ፊቱን ቅጭም አድርጎ እኔ ስለ ህጋችሁ አያገባኝም፡፡ ሰውየው ያልጠበቁትን ጋብቻ ህጉ እንዴት ይጠብቀዋል?… ጉረኛ!!!…” አልገባኝም!!… ጉረኛ ያልከው እኔን ነው ህጉን?…. ዝም አለኝ፡፡ እኔም ልክ-ልኩን ነገርኩት፡፡ – ዝጋታም!!!!….. ግን ለትዳር ውስልትና የሚገፋፋው ምንድነው?… የግልፅነት አለመኖር ይሆን?… አለም አንድ መንደር ሆናለች፡፡- እኛ ግን በአንድ ጋብቻ አንድ ሆነን አንድ መሆን አልቻልንም፡፡ በትዳር ውስጥ በግልፅነት መወያየት ከሌለ የትዳር አሜኬላዎች ማቆጥቆጣቸው አይቀርም፡፡ አንዳንድ ባልና ሚስት ከአንድ ምንጭ ቀርቶኮ ከአንድ ውቅያኖስም መቀዳታቸው እያጠራጠረን ነው፡፡ አንዲት በሶቅራጥስ አማካኝነት የተዋወቀችን ቆንጅዬ ልጅ “ ላገባ ነውና በሰርጌ ተገኙልኝ!!!…” ብላ የጥሪ ካርድ ላከችልን፡፡ የጥሪ ካርዶቹን አሳየንና መልሶ ወደኪሱ ከተተው፡፡- ሶቅራጥስ ስጠን እንጂ!!!… እጄን ዘረጋሁ “ልጅቷን ታውቃታለህ፡፡ ቆንጆ ነች፡፡…” አቋረጥኩት፡፡ እንዳትፈላሰፍብኝ!!!… በቆንጆ ሁኔታ የተሰራች ጭቃ ናት… ምናምን… እያልክ ስትፈላሰፍ አንተ የራስህ ጉዳይ – እኛን ግን አስመለጥከን፡፡ … ንግግሬ ከረር ያለ ነበር፡፡ ሶቅራጥስ ትከሻዬን ይዞ እንደ ህፃን ያባብለኝ ጀመር፡፡ “ እንኳን ቀረችብኝ!… እንኳን ቀረችብህ!… እንኳን ቀረችባቸው!… አየህ!!!… የተሰራችው ከጭቃ ነው፡፡ ግን ጭቃው ያምራል፡፡ – ክፋቱ ማሰቢያዋ የማያምር ጭቃ ነው፡፡….”  ዛሬስ ጫን ያለው ፍልስፍና መጣ፡፡ ቀጠለ፡፡ “…. የምታገባው ህንፃ ያለው ሀብታም ነጋዴ እንደሆነ ነግራኛለች፡፡ በፍቅር ሳይሆን ለገንዘብ ብላ ነው የምታገባው፡፡ በአጭሩ – የምታገባው ሰውየውን ሳይሆን ህንፃውን ነው ማለት ነው፡፡ እኔም ሆንኩ እናንተ ሰውን ከንብረት ጋር ለማጋባት በሚደረግ የሰርግ ስነ-ስርአት ላይ ተገኝተን አድማቂ የመሆን ፍላጎት የለንም፡፡ ሰለዚህ የጥሪ ካርዱን እመልስላታለሁ፡፡ ….” በረጅሙ ተነፈሰና ቀጠለ፡፡ “… ምናልባት ወደፊት ይህን ትዳር ወይም አዳር ትታ ሰው አፍቅራ ካገባችና ለሰርጓ ከጠራችን እንገኛለን፡፡ ተወዛውዘን – ሌሎቹንም አወዛውዘን እንድራታለን፡፡ ለዛሬው ግን ይለፈን፡፡…” የሶቅራጥስ ውሳኔዎች ይግባኝ የማይባልባቸው ናቸውና ሊከራከረው የሞከረ አልነበረም፡፡ ፍልስፍናውን እና ውሳኔውን የጋተን አሪፍ ቁርጥ ጋብዞን በመሆኑ ብዙም አልከፋንም፡፡ ለመበተኛ አምቦ ውሀ ጠጥተን እኛም ወደየቤታችን ተበተንን፡፡ አንድ ነገር ግን ላማክራት አሰብኩ፡፡ አፍንጫዋን እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ እንወድላታለን፡፡ ባሏም አፍንጫዋን እንደሚወደው እርግጠኛ ነኝ፡፡ ስለዚህ ለአፍንጫዋ የግጭት መከላከያ ነገር ብታሰራለት መልካም ይመስለኛል፡፡ የሰይጣን ጆሮ ድፍን ይበልና – እንዳው በሆነ አደጋ አፍንጫዋ ውበቱን ቢያጣ እሷስ- ትዳሯስ ምን ዋስትና አላቸው?… እንዳውም ለጥንቃቄ ብሔራዊ ባንክ በአደራ ብታስቀምጠው አሰተማማኝ ነው፡፡ ቂቂቂቂቂ……. (እንዴት ነው አሪፍ የብሔራዊ ባንክ ማስታወቂያ ነው አይደል?… እነ እንትና… ደግሞ እቺንም ኮፒ አድርጓትና በቲቪ አቅርቧት!!!… ቂቂቂቂቂ….)     አንድ ወዳጄ ያጫወተኝን ደግሞ ላውጋችሁ፡፡  ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!              ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን #ይቀጥላል @BiniGirmachew     @BiniGirmachew
Show all...
👍 9🙏 4 2🥰 2🏆 2
ትናንት ድቺ ውስጥ የሚያድረው ልጅ ዛሬ ላይ ከአጠቃላይ ተማሪዎች 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ይዞ መጨረስን በየዓመቱ የግሉ አድርጎታል ። ምሳ ሳያቋጠርልቸው አይዞህ የሚል ወላጅ ሳይኖራቸው ውጤታማ ከሆኑ ብዙ ብደረግላቸው ነገ ላይ ትልቅ ሰው መሆን ይችላሉ ።🙏😍 አንዳንድ የሥራህን ውጤት ሰው ውስጥ ስታይ እንዴት ደስ ይላል። ስለሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን
Show all...
🥰 14👍 6👌 5👏 4 2🏆 1
Surprise notcoin እንደገና ተጀመረ https://t.me/notcoin_bot?start=er_45621782 ባለፎ በደንብ አብዛኛው ሰው ተጠቅማል አሁን ሞከሩ ትንሽ ሰው በብዛት እየተጠቀመ ስለሆነ እንቢ ሊል ይችላል። በእርጋታ ሞኩሩ https://t.me/notcoin_bot?start=er_45621782 https://t.me/notcoin_bot?start=er_45621782
Show all...
🥰 2
የአእምሮ ህመም እና እርግዝና በእርግዝና ወቅት ከእርግዝናው ጋር በተያያዙ በርካታ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ለውጦች ምክንያት አዲስ የአእምሮ ህመም በአንዳንድ ነፍሰጡር ሴቶች ላይ ሊከሰት የሚችል ሲሆን ሲጀምርም የአእምሮ ህመም ከነበረ ደግሞ ህመሙ ሊባባስ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። ይህ ለአእምሮ ህመም የተጋላጭነት ሁኔታ ከእርግዝናው ጋር ተያይዘው በሚመጡ አካለዊ ለውጦች፣ ስጋቶች፣ ሀላፊነትን ለመቀበል በሚደረግ መደበኛ የአእምሮ ማስተካካያ ሂደቶች ወ.ዘ.ተ ጭንቀት እንዲሁም ድብርት በነፍሰጡር እናቶች ላይ ሊፈጠር ይችላል። ነገር ግን የአእምሮ ህመም በተለያየ ምክንያት በስፋት ሊከሰት ወይንም ሊባባስ የሚችለው በድህረ ወሊድ ጊዜ እንደሆነ ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል። የሆነው ሆኖ አብዛኛው የአእምሮ ህመም ያለባቸው እናቶች እንደማንኛውም እናት መደበኛ እርግዝና መደበኛ ወሊድ እንዲሁም ጤናማ ጨቅላ ህፃን ሊያገኙ እንደሚችሉ ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል። በሚከተሉት ምክንያቶች ነፍሰጡር እናቶች አእምሯዊ ጫና ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ⇒ ከመደበኛው ጊዜ የተለየ የስራ ድርሻ ለውጥ (የልጅ እናት የመሆን) ⇒ በጋብቻ እና በእርግዝናው ምክንያት የማህበራዊ ግንኙነት ለውጥ መከሰት ⇒ ጥሩ ወላጅ እሆናለሁ አልሆንም የሚል ሀሳብ መከሰት ⇒ በእርግዝናው ጊዜ በልጅ ላይ ችግር ይከሰት ይሆን የሚል ሀሳብ መከሰት ⇒ እርግዝናው አካል ክፍሌ ላይ ችግር ይፈጥር ይሆን ወይ የሚል ሀሳብ መከሰት ⇒ ወሊድን የመፍራት ስሜት መከሰት ⇒ የማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ አለመኖር ይሁንና ሁሉም ነፍሰ ጡር እናቶች ለእንደዚህ አይነቱ አእምሯዊ ጫና የተለያየ ምላሽ የሚኖራቸው ሲሆን ሁሉም ነፍሰጡር ሴቶች የእእምሯዊ ህመም ምልክቶችን በትክክል ተገንዝበው ተገቢውን የህክምና እርዳታ መሻት ይጠበቅባቸዋል። ሁሉም ነፍሰጡር እናቶች ላይ የተወሰነ መጠን ያለውና መደበኛ የሆነ የመጨናነቅና የመፍራት ሁኔታ የሚታይባቸው ቢሆንም የሚከተሉት ምልክቶች በነፍሰጡር እናቶች ላይ ከታዩ በአስቸኳይ የአእምሮ ሀኪምን እንዲሁም የፅንስ ማህፀን ስፔሻሊስትሀኪምን ማማከርና መታከም ይኖርባቸዋል፦ ☞ መደበኛን ስራ እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያውክ የጭንቀት ሁኔታ ☞ መደበኛ ስራን እንዲሁም ማህበራዊ ህይወትን የሚያውክ ድብርት ☞ያልተለመዱና ወጣ ያሉ ንግግሮች ከተከሰቱ ☞ ጤናማ የሆነ ሰው የማያያቸውንና የማይሰማቸውን ነገሮች የማየት የመስማት ሁኔታዎች ከተከሰተ ☞ ያልተለመዱና ወጣ ያሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎች አንድ ነፍሰጡር ሲጀምርም የአእምሮ ህመም ከነበራት በእርግዝናው ጊዜ የመባባስ እድሉ ሰፊ ስለሆነ ይህንን ለመከላከል ከመፀነሷ በፊት የአእምሮ ህክምና ባለሙያን ማማከር የግዴታ ያስፈልጋታል። ከዚሁም ጋር ተያይዞ በተለይም የአእምሮ ህመም መድሀኒት የምትወስድ ሴት መድሀኒቶቹን በምን መልኩ መውሰድ እንዳለባት እንዲሁም መድሀኒቶቹን የማስተካከል ሁኔታ እንዳለ ከሀኪም ጋር መነጋገር ያስፈልጋታል። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ለአእምሮ ህመም የሚሰጡ አንዳንድ መድሀኒቶች በፅንሱ ላይ ጉዳት እነዲሁም የአፈጣጠር ችግር ሊፈጥሩ ስለሚችሉ አፅንኦት ሰጥቶ ሀኪም ማማከር የግዴታ ያስፈልጋል። ⇒ በአጠቃላይ የአእምሮ ህመም በነፍሰጡር እናቶች ላይ የሚያደርሰው ጫና በሚከተሉት ምክንያቶች ይወሰናል፦ ⇒ የአእምሮ ህመሙ አይነት ⇒  የአእምሮ መድሀኒት የሚወስዱ ከሆነ የመድሀኒቱ አይነት ⇒  የአእምሮ ህመም መድሀኒት የሚወስዱ እናቶች የመድሀኒት አወሳሰድ ሁኔታ ⇒  በቅርብ የተከሰተ አስጨናቂ ጉዳይ መኖር አለመኖር ⇒ እርግዝናውን ራሱ የመቀበልና ያለመቀበል ሁኔታ ⇒ መጥፎና የሚያበሳጩ ትዝታዎች መኖር አለመኖር ⇒ የአእምሮ ህመም የሚያስከትለውን ችግር ለመቀነስ የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ ይመከራል ✓ እርግዝናን ባግባቡ መከታተል ✓ በቂ እረፍት መውሰድ ✓ የታዘዙ መድሀኒቶችን በትክክል መውሰድ ✓ አዲስ የአእምሮ ህመም ምልክት ሲከሰት በፍጥነት ሀኪም ማማከር ✓ አደገኛ እፅ ከመውሰድ መቆጠብ ✓ አልኮል ከመጠጣት መቆጠብ ✓ ለአእምሮ ህሙማን የቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል ወደ እኛ ይምጡ BGN የእናቶች እና የህፃናት ልዩ ህክምና ማዕከል የ24 አገልግሎት ይሰጣል ⚡ ሁሉም ህክምናዎች በእስፔሻሊስት እና ልዩ እስፔሻሊስት ይሰጣል 📍 አድራሻ-አዲስ አበባ  ፣ ሀያ ሁለት: ጎላጎል አካባቢ ከመክሊት ህንፃ ጀርባ 300ሜትር ገባ ብሎ ለህክምና ቀጠሮ ለመያዝ  +251927707000/  +251941282829
Show all...
👍 7🫡 2 1🥰 1🙏 1🏆 1
የአእምሮ ህመም እና እርግዝና በእርግዝና ወቅት ከእርግዝናው ጋር በተያያዙ በርካታ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ለውጦች ምክንያት አዲስ የአእምሮ ህመም በአንዳንድ ነፍሰጡር ሴቶች ላይ ሊከሰት የሚችል ሲሆን ሲጀምርም የአእምሮ ህመም ከነበረ ደግሞ ህመሙ ሊባባስ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። ይህ ለአእምሮ ህመም የተጋላጭነት ሁኔታ ከእርግዝናው ጋር ተያይዘው በሚመጡ አካለዊ ለውጦች፣ ስጋቶች፣ ሀላፊነትን ለመቀበል በሚደረግ መደበኛ የአእምሮ ማስተካካያ ሂደቶች ወ.ዘ.ተ ጭንቀት እንዲሁም ድብርት በነፍሰጡር እናቶች ላይ ሊፈጠር ይችላል። ነገር ግን የአእምሮ ህመም በተለያየ ምክንያት በስፋት ሊከሰት ወይንም ሊባባስ የሚችለው በድህረ ወሊድ ጊዜ እንደሆነ ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል። የሆነው ሆኖ አብዛኛው የአእምሮ ህመም ያለባቸው እናቶች እንደማንኛውም እናት መደበኛ እርግዝና መደበኛ ወሊድ እንዲሁም ጤናማ ጨቅላ ህፃን ሊያገኙ እንደሚችሉ ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል። በሚከተሉት ምክንያቶች ነፍሰጡር እናቶች አእምሯዊ ጫና ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ⇒ ከመደበኛው ጊዜ የተለየ የስራ ድርሻ ለውጥ (የልጅ እናት የመሆን) ⇒ በጋብቻ እና በእርግዝናው ምክንያት የማህበራዊ ግንኙነት ለውጥ መከሰት ⇒ ጥሩ ወላጅ እሆናለሁ አልሆንም የሚል ሀሳብ መከሰት ⇒ በእርግዝናው ጊዜ በልጅ ላይ ችግር ይከሰት ይሆን የሚል ሀሳብ መከሰት ⇒ እርግዝናው አካል ክፍሌ ላይ ችግር ይፈጥር ይሆን ወይ የሚል ሀሳብ መከሰት ⇒ ወሊድን የመፍራት ስሜት መከሰት ⇒ የማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ አለመኖር ይሁንና ሁሉም ነፍሰ ጡር እናቶች ለእንደዚህ አይነቱ አእምሯዊ ጫና የተለያየ ምላሽ የሚኖራቸው ሲሆን ሁሉም ነፍሰጡር ሴቶች የእእምሯዊ ህመም ምልክቶችን በትክክል ተገንዝበው ተገቢውን የህክምና እርዳታ መሻት ይጠበቅባቸዋል። ሁሉም ነፍሰጡር እናቶች ላይ የተወሰነ መጠን ያለውና መደበኛ የሆነ የመጨናነቅና የመፍራት ሁኔታ የሚታይባቸው ቢሆንም የሚከተሉት ምልክቶች በነፍሰጡር እናቶች ላይ ከታዩ በአስቸኳይ የአእምሮ ሀኪምን እንዲሁም የፅንስ ማህፀን ስፔሻሊስትሀኪምን ማማከርና መታከም ይኖርባቸዋል፦ ☞ መደበኛን ስራ እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያውክ የጭንቀት ሁኔታ ☞ መደበኛ ስራን እንዲሁም ማህበራዊ ህይወትን የሚያውክ ድብርት ☞ያልተለመዱና ወጣ ያሉ ንግግሮች ከተከሰቱ ☞ ጤናማ የሆነ ሰው የማያያቸውንና የማይሰማቸውን ነገሮች የማየት የመስማት ሁኔታዎች ከተከሰተ ☞ ያልተለመዱና ወጣ ያሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎች አንድ ነፍሰጡር ሲጀምርም የአእምሮ ህመም ከነበራት በእርግዝናው ጊዜ የመባባስ እድሉ ሰፊ ስለሆነ ይህንን ለመከላከል ከመፀነሷ በፊት የአእምሮ ህክምና ባለሙያን ማማከር የግዴታ ያስፈልጋታል። ከዚሁም ጋር ተያይዞ በተለይም የአእምሮ ህመም መድሀኒት የምትወስድ ሴት መድሀኒቶቹን በምን መልኩ መውሰድ እንዳለባት እንዲሁም መድሀኒቶቹን የማስተካከል ሁኔታ እንዳለ ከሀኪም ጋር መነጋገር ያስፈልጋታል። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ለአእምሮ ህመም የሚሰጡ አንዳንድ መድሀኒቶች በፅንሱ ላይ ጉዳት እነዲሁም የአፈጣጠር ችግር ሊፈጥሩ ስለሚችሉ አፅንኦት ሰጥቶ ሀኪም ማማከር የግዴታ ያስፈልጋል። ⇒ በአጠቃላይ የአእምሮ ህመም በነፍሰጡር እናቶች ላይ የሚያደርሰው ጫና በሚከተሉት ምክንያቶች ይወሰናል፦ ⇒ የአእምሮ ህመሙ አይነት ⇒  የአእምሮ መድሀኒት የሚወስዱ ከሆነ የመድሀኒቱ አይነት ⇒  የአእምሮ ህመም መድሀኒት የሚወስዱ እናቶች የመድሀኒት አወሳሰድ ሁኔታ ⇒  በቅርብ የተከሰተ አስጨናቂ ጉዳይ መኖር አለመኖር ⇒ እርግዝናውን ራሱ የመቀበልና ያለመቀበል ሁኔታ ⇒ መጥፎና የሚያበሳጩ ትዝታዎች መኖር አለመኖር ⇒ የአእምሮ ህመም የሚያስከትለውን ችግር ለመቀነስ የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ ይመከራል ✓ እርግዝናን ባግባቡ መከታተል ✓ በቂ እረፍት መውሰድ ✓ የታዘዙ መድሀኒቶችን በትክክል መውሰድ ✓ አዲስ የአእምሮ ህመም ምልክት ሲከሰት በፍጥነት ሀኪም ማማከር ✓ አደገኛ እፅ ከመውሰድ መቆጠብ ✓ አልኮል ከመጠጣት መቆጠብ ✓ ለአእምሮ ህሙማን የቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል
Show all...
እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን በሰላም ተመልሰዋል
Show all...
🥰 39👍 12🙏 8👌 5🏆 4👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
BGN የእናቶች እና የህፃናት ልዩ ህክምና ማዕከል የ24 አገልግሎት ይሰጣል። ⚡ ሁሉም ህክምናዎች በእስፔሻሊስት እና ልዩ እስፔሻሊስት ይሰጣል 📍 አድራሻ-አ.አ ፣ ሀያ ሁለት: ጎላጎል አካባቢ ከመክሊት ህንፃ ጀርባ 300ሜትር ገባ ብሎ ለህክምና ቀጠሮ ለመያዝ  +251927707000/  +251941282829
Show all...
🙏 4🥰 2👍 1🏆 1
ትዳር!!!… ፍቅር!!!…(የተገጣጠሙ – ገጠመኞች) “…ባሌ ውስጥ ባሌን አጣሁትና ባሌን ፍለጋ ወክ አደርጋለሁ፡፡…” ክፍል 3 አንተ ስለርቀት ትዳር ታወራለህ እንዴ?…. አንድ ወዳጄ ጠየቀኝ፡፡ ባል እና ሚስት አብረው እየኖሩ ሚስታቸውን – ባላቸውን የቅርብ እሩቅ የሚያደርጉ አላጋጠሙህም?… ይህ ወዳጄ ትምባሆ ያቦናል፡፡ – ጠላታችሁ ቡን ይበልና!!!… አሜን!!!… ግን የአካባቢው ሰው እንዲያውቅበት አይፈልግም፡፡ ማጨስ ሲፈልግ ከአካባቢው ርቆ ነው፡፡ አንድ ምሽት ታድያ “ አማረኝ!!!…” አለ፡፡ – በቃ!!!…ሲጋራ ማጨስ አማረው፡፡ ( አንተኛው ወዳጄ!!!… በጠራራ ፀሀይ በጥቁር ካፖርት ተጀቡኖ ሲጋራ እያቦነነ የከሰል ባቡር የመሰለኝን ሰው የገለፅክበት አባባል ተመችቶኛል፡፡ – “ እሳት ለብሶ – እሳት ጎርሶ!!!…” ቂቂቂቂቂ…….) በቅንፍ ያስቀመጥኩዋትን ቦነስ ወስዳችሁ ሲጋራ ወደ አማረው ወዳጄ ራዳሬን ልመልስላችሁ፡፡ ከአንድ መሸታ ቤት ቤት ገብቶ የሚያዘውን አዞ ሲጋራውን ከኪሱ ከማውጣቱ በፊት አካባቢውን ገልመጥ ሲያደርግ አንድ የምናከብራቸው ትልቅ ሰው ከቤቱ ኮርነር አካባቢ ተቀምጠው ሀሳባቸውን እየሰለቀጡ በቀዝቃዛ ጊዮርጊስ ቢራ ያወራርዱታል፡፡ ወዳጄ ተበሳጨ!!… እንዲህ ሲጋራ አምሮት – አምሮቱን እንዳይወጣ ምቀኛ ስለሆኑበት አዘነባቸው፡፡ አጎንብሶ መሬቱን በእግሩ እየተመተመ “ ምን ላድርግ?…” በሚል አጀንዳ ዙሪያ ለመነጋገር እራሱን ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠራ፡፡ ከዚያም ወሰነ፡፡- ወደ ሌላ ቤት ለመሄድ፡፡ አሰተናጋጅዋን ለመጥራት እና ሂሳብ ለመክፈል ቀና ሲል ሰውየው የሉም፡፡ የት ሄዱ?… ግራ ገባው፡፡ ብቻ ደስ አለው፡፡- አምሮቱን የሚወጣበት ቀዳዳ አገኘ ማለት ነው፡፡ “ ለማንኛውም – ለጥንቃቄ ” ብሎ ሊያጨስ ወደ ጓሮ ወጣ፡፡ ጓሮው የመኝታ ክፍሎች የተገጠገጡበት ነው፡፡ ሲጋራውን በአፉ ይዞ፤አንድ የመኝታ ክፍል መስኮት ተደግፎ፤ ክብሪት ከኪሱ ሊያወጣ ሲል ድንገት ከውስጥ አንድ የሚያውቀውን ድምፅ ሰማና እጁ ኪሱ ውስጥ እንዳለ ግንባሩን ሸብሽቦ ጆሮውን ወደ መስኮቱ አስጠግቶ ለማጣራት ሞከረ፡፡ ድምፁ በትክክል የሰውየው ነው፡፡ ከአንዷ- የቤቱ አስተናጋጅ ጋር ሊተኙ እየተዘጋጁ ነው፡፡ የሚነጋገሩትን አዳመጠ፡፡ ፊቱን ቅጭም አድርጎ፤ ከክፍሉ በር አጠገብ ተቀምጦ ሲጋራውን ለኮሰ፡፡ ባለቤታቸውን ያውቃቸዋል፡፡ ሁለት ጎረምሳ ልጆችም አሏቸው፡፡ ታድያ “ ይህ ለምን?…” መልስ ያላገኘለት ጥያቄ:: ልጅቷ ፀጉሯን እና ልብሷን እያስተካከለች ስትወጣ፤ በሩ አጠገብ በመቀመጡ ደንግጣ  “ ዋይ!!!….” ስትል ጮኸች፡፡ ወድያው ሰውየው በግልገል ሱሪ ብቻ እንደሆኑ “ ምንድነው?!!!… ምንድነው?!!!… “ እያሉ ሲወጡ ከወዳጄ ጋር አይን ለአይን ተገጣጠሙ፡፡ በጣም እንደደነገጡ ያስታውቃል፡፡ “አንተ!!!…. ሲ…. ሲጋራ ታጨሳለህ እንዴ?….”  “ በኮንዶም!!!….” ቂቂቂቂቂ…. ወዳጄ ሳቀ፡፡ እሳቸው ግን ይበልጥ ተደናበሩ፡፡ እንደምንም ተወራጭተው የክፍሉን በር ዘጉት፡፡ “ ምን አስቤ እንደነበረ ታውቃለህ?…” ይቀጥላል ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!    ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን @BiniGirmachew     @BiniGirmachew እግዚአብሔር ይመስገን 89ሺ ነገ ደሞ 100ሺ ይሆናል
Show all...
👍 14🙏 7 1🥰 1👏 1🏆 1🫡 1
በእድሜ ገፍቶ እርግዝና የእርግዝና ለመጀመሪያ ጊዜ ከ35 አመት በላይ በሆናቸው ሴቶች ላይ ሲከሰት የሚከተሉትን ቸግሮች ሊያስከትል ይችላል፦ ⇨  የእርግዝና የደም ግፊት የመከሰት እድሉ መጨመር ⇨  በሌላ ጊዜ የመፀነስ እድል መጥበብ ⇨  የእርግዝና የስኳር ህመም የመከሰት እድሉ መጨመር ⇨ እንግዴ ልጅ ያለጊዜው ከማህፀን ግድግዳ የመላቀቅ እድሉ መስፋት ⇨  የምጥ መርዘም ⇨  ኦፕሬሺን የመደረግ እድሉ መጨመር ⇨  በመጎተቻ የመውለድ እድሉ መጨመር ⇨  የማህፀን እጢ የመከሰት እድሉ መጨመር ⇨ ውርጃ የመከሰት እድሉ መጨመር ⇨  የአፈጣጠር ችግር የመከሰት እድሉ መጨመር ⇨  ያለጊዜው ልጅ መወለድ ⇒ የጨቅላ ህፃን ህመም እንዲሁም ሞት በተለያየ ምክንያት የመከሰት እድላቸው መጨመር በእድሜ ገፍቶ እርግዝናን ለመከላከል እንዲሁም እርግዝናው ከተከሰተ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ ያስፈልጋል፦ ⇨  በተቻለ መጠን በጊዜ መውለድ (20 እስከ 34) ✓ እርግዝናው ከተከሰተ ደግሞ ባግባቡ የእርግዝና ክትትል አገልግሎትን ማግኘት ✓ በወሊድ ጊዜ በጥሩ የወሊድ አገልግሎት በሚሰጡ የጤና ተቋማት ብቻ መውለድ ወደ እኛ ይምጡ BGN የእናቶች እና የህፃናት ልዩ ህክምና ማዕከል የ24 አገልግሎት ይሰጣል ⚡ ሁሉም ህክምናዎች በእስፔሻሊስት እና ልዩ እስፔሻሊስት ይሰጣል 📍 አድራሻ-አ.አ ፣ ሀያ ሁለት: ጎላጎል አካባቢ ከመክሊት ህንፃ ጀርባ 300ሜትር ገባ ብሎ ለህክምና ቀጠሮ ለመያዝ  +251927707000/  +251941282829
Show all...
👍 17🥰 2👏 1🙏 1🏆 1🫡 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.