en
Feedback
Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Open in Telegram

​💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል ​በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2

Show more
1 879
Subscribers
+124 hours
-157 days
-6430 days
Posts Archive
+3
📚 Addis Ababa City Administration Education Bureau 🔶 2018 E.C. Grade 8 Ministry Exam Answer Sheet

✅ የMS-Word ሙሉ ክህሎት በተግባር የተደገፈ ቪድዮ ይሀውና!! 📧 MS-Word ሙሉ ትምህርት በቪድዮ 📧 የሰዓት ቆይታ: 1:46 ደቂቃ (አንድ ሰዓት ከ46 ደቂቃ) 📧 የMB መጠን: 265MB አዘጋጅ እና ድምፅ: ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ════════════════ 📧 ታላቁ ሰሀባ አቡ ደርዳእ እንዲህ ይላል፦ 📧 "እኔ አኺራ ላይ የሚያስፈራኝ ነገር ቢኖር ባወቅከው ምን ሰራህበት መባሌ ነው"!! ════════════════ ⭕️ ቪድዮውን አይታችሁ ስትጨርሱ አስተያየት: ..........................! 📧 📧 ════════════════ ለመምህራን የተሰጠ ስልጠና፤ እናንተም ተጠቀሙበት!! ✍️ Basic Computer Skills 🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻 Telegram: t.me/BasicComputer_Skills tiktok.com/@basiccomputerskills

ጥቆማ‼ ====== (ልጆቻችሁን ቶሎ አስመዝግቡ። በመሰል ነገሮች ከጠቆምኳችሁ ዓይናችሁን አትሹ!) || ✍️ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ! የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በተከታዮቹ መስኮች ራሳችሁን የምታንጹበት ታላቅ የክረምት ስልጠና አዘጋጅቶላችኋል። በፈንዳሜንታል ኦፍ ኤ.አይ፣ 💻 ፕሮግራሚንግ፣ 🧠 ማሽን ለርኒንግ፣ ⚙️ በሮቦቲክስ እና IOT፣ 📊 ዳታ ሳይንስ እና በሌሎችም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፎች ራሳችሁን የምታንጹበት ታላቅ የክረምት ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል። እስከ ግንቦት 30፤ 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በተከታዩ የጉግል ፎርም https://forms.gle/uDGPmQsiZcWWeNuRA በመጠቀም ይመዝገቡ።

​⏳ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ (Entrance) ፈተና፦ የድል፣ የተስፋ እና የቁርጠኝነት ዘመቻ! ​(ለተፈጥሮ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች) ​✨ "ትልቁ ሽልማት የጀመርከው ከመሆን ይልቅ ምን እንደምትሆን ነው!" ​ውድ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች እና ወላጆች፣ የአስራ ሁለት ዓመታት የትምህርት ጉዞ ፍሬ የሚያፈራበት፣ የህይወታችሁ ትልቁ ምዕራፍ ሊከፈት ከፊታችሁ ቆሟል። የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ል እንደሚሰጥ ታውቋል። ይህ ማለት የዩኒቨርሲቲን በር በክብር ከፍታችሁ ለመግባት የቀራችሁ ጊዜ አንድ ወር ከ20 ቀን ገደማ ብቻ ነው! ​ይህ ቀሪ ጊዜ ልክ እንደ ሰይፍ ስለት ነው፤ በቸልተኝነት ከያዝነው ይቆርጠናል፣ በብልሃትና በቁርጠኝነት ከተጠቀምንበት ግን የተደቀኑብንን የፈተና እሾሆች ይመነጥርልናል! ስኬት በድንገት አይከሰትም፤ ስኬት የዲሲፕሊን፣ የትጋት እና በአላህ (ሱ.ወ) ላይ የመመካት (ተወኩል የማድረግ) ጣፋጭ ውጤት ነው። ​🚀 የጥናት ስልቱ፦ ​ከላይ በምስሎቹ ላይ የምትመለከቱት የጥናት መርሃ ግብር፣ ከ11ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ የተፈጥሮ (Natural) እና የማኅበራዊ (Social) ሳይንስ ተማሪዎች በልዩ ጥንቃቄ የተዘጋጀ ነው። አጭሩን ጊዜ በከንቱ ከመባከን አድኖ፣ አዕምሮን በከፍተኛ ንቃት የሚያሰራው ሳይንሳዊ ስልት ይኸውላችሁ፦ ​🌙 የማታ ጥናት (Evening Study)፦ ጸጥታው ሲሰፍን ማታ ላይ የምታጠፉት ሰዓት፣ ጽንሰ ሀሳቦችን (Concepts) በጥልቀት የምትረዱበት እና የዕለቱን ትምህርት የምታደራጁበት ወርቃማ ጊዜ ነው። ​🌅 የጥዋት ጥናት (Morning Study)፦ አዕምሮ ሙሉ እረፍት አግኝቶ እንደ ንጋት ፀሀይ በሚያበራበት የጠዋት ሰዓት ማጥናት ትልቁ ስኬት ነው። በተለይ እንደ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ የመሳሰሉትን ትኩረት የሚጠይቁ ትምህርቶች በዚህ ጊዜ ማጥናት የማይበገር አቅም ይገነባል። ​🎯 የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ፦ እያንዳንዷ ደቂቃ ትቁጠር! ​ፈተናን ለማሸነፍ ሰዓታትን ዝም ብሎ ማሳለፍ ሳይሆን፣ ጊዜን በስልት መግራት ወሳኝ ነው። መርሃ ግብሩ ይህንን ሚስጥር ይዟል፦ ​1. ለጠቅላላ ትምህርቶች (45 + 10 + 25): ​📖 45 ደቂቃ (Study)፦ በሙሉ ትኩረት ማጥናት፤ ዓለማችሁን መጽሐፉ ላይ ብቻ ማድረግ። ​☕ 10 ደቂቃ (Tea Break)፦ አዕምሮን ለማደስ አጭር እረፍት ማድረግ። ​📝 25 ደቂቃ (Questions)፦ ያነበባችሁትን ወደ አዕምሮ ጠልቆ እንዲገባ፣ ያለፉት ዓመታት ጥያቄዎችን በተግባር መስራት! ​2. ለሂሳብ ትምህርት ልዩ ቀመር (35 + 10 + 35): 🔶​ሂሳብ የልምምድ ትምህርት ስለሆነ፣ 35 ደቂቃ ህጎችን ካጠናችሁ በኋላ፣ አጭር እረፍት ወስዳችሁ በቀጥታ ወደ 35 ደቂቃ የጥያቄ ልምምድ ግቡ። ጥያቄ መስራት በራስ መተማመናችሁን ከፍ ያደርገዋል! ​🔥 ተስፋ አትቁረጡ፣ የድል አጥቢያ ላይ ናችሁ! ​ውድ ተማሪዎች፣ በዚህ ወሳኝ ሰዓት እንቅልፍ ማጣት፣ መድከምና ጭንቀት ሊሰማችሁ ይችላል። ነገር ግን ዛሬ የምትከፍሉት እያንዳንዱ የመስዋዕትነት ላብ፣ ነገ ካምፓስ ገብታችሁ ለምታፈሱት የደስታ እንባ ዋጋ ነው። ፈተናው ፍርሃት ሳይሆን ብቃታችሁን የምታሳዩበት ትልቅ መድረክ ነው! ​"ስኬት የመጨረሻ አይደለም፤ ውድቀትም ገዳይ አይደለም፤ ዋናው ነገር ለመቀጠል ያለው ድፍረት ነው!" ዛሬ ያመለጠቻችሁን ደቂቃ ነገ በማካካስ ከትላንቱ የተሻላችሁ ሁኑ። ሰብቡን (ምክንያቱን) አድርሱ፤ ዱዓችሁን ከጥረታችሁ ጋር አስተባብሩ። አላህ (ሱ.ወ) በንጋት ተነስቶ ለሚለፋ፣ ተስፋ ሳይቆርጥ ለሚጥር ባሪያው በረካውን አይነፍገውም! ​═══════════════ ◆ ጥረት ካለ ስኬት አይርቅም፤ ትጋት ካለ ድል አይታጣም!! ✅ ስኬት ለልጆቻችን፣ ለአበቦች፣ ለአንፀባራቂ ኮከቦች! ✨━━━━━━━━━━━━✨ ​🌈 ꧂ ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈

Grade ⓬ 📌ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት እያደረጉ ነው? ✅በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ አጋዥ የትምህርት ይዘቶች እና የመለማመጃ ጥያቄዎችን የያዙ ቪዲዮዎች በድረ-ገፅ ያገኛሉ። ይለማ
Grade ⓬ 📌ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት እያደረጉ ነው? ✅በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ አጋዥ የትምህርት ይዘቶች እና የመለማመጃ ጥያቄዎችን የያዙ ቪዲዮዎች በድረ-ገፅ ያገኛሉ። ይለማመዱ ⬇️⬇️⬇️ https://examinfo.moe.gov.et/guides ➡️የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ል እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል። ✅#SHARE መልካም  ጥናት✅

Google messages ስትጠቀሙ RCS On ማድረጋችሁ ምን ይጠቅማችኋል? ⚫Message ስትልኩ ብር አይቆርጥባችሁም። ነገር ግን Data ማብራት ይጠበቅባችኋል። የምትልኩለት ሰው Google mess
Google messages ስትጠቀሙ RCS On ማድረጋችሁ ምን ይጠቅማችኋል? ⚫Message ስትልኩ ብር አይቆርጥባችሁም። ነገር ግን Data ማብራት ይጠበቅባችኋል። የምትልኩለት ሰው Google messages የሚጠቀምና Online መሆን አለበት። ⚫የGemini AI እዛው Google messages ላይ መጠቀም ትችላላችሁ። ⚫ የድምፅ መለዕክት፣ ፎቶ፣ location፣ GIFና Sticker መላላክ ትችላላችሁ። ⚫End-to-End encrypted ነው። ያ ማለት የምትልኩትን መልዕክት ማንኛውም service provider (ቴሌ ወይም ሳፋሪኮም) የማየት እድል የላቸውም። ግን ሁለታችሁም Google messages ከተጠቀማችሁና E2EE on ከሆነ ብቻ ነው። ⚫Message የላካችሁለት ሰው የላካችሁትን መልዕክት ማየቱና አለማየቱን ማዎቅ ትችላላችሁ። እንዲሁም type በሚያደርግበት ጊዜ Typing....ይላችኋል። እዚ ጋ ጥንቃቄ ማድረግ ያለባችሁ RCS on አድርጋችሁ Message ስትልኩ እናንተ data ካላበራችሁ message error ይላችኋል። የምትልኩለት ሰውም Online ካልሆነ የላካችሁት message አይገባለትም። ይህን ነገር ለማስተካከል የምትልኩለት ሰው profile ላይ ገብታችሁ "Only send SMS and MMS messages" የሚለውን On ማድረግ ይጠበቅባችኋል። RCS Chat እንዴት on እንደሚደረግ ማዎቅ ከፈለጋችሁ https://t.me/bighabesha_softwares/1779 @bighabesha_softwares

Ethio telecom የGoogle RCS(Rich Communication Services) አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቃላችሁ? RCS ማለት በሞባይል ስልክ መልዕክትን በኢሞጂ፣ በፎቶ፣ በቪዲዮ እና በድምፅ
Ethio telecom የGoogle RCS(Rich Communication Services) አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቃላችሁ? RCS ማለት በሞባይል ስልክ መልዕክትን በኢሞጂ፣ በፎቶ፣ በቪዲዮ እና በድምፅ አንድ ለአንድ ወይም በቡድን ያለገደብ በመልዕክት ማጋራት የሚያስችል መንገድ ነው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው የGoogle Messaging መተግበሪያን አውርዶ መጠቀም ብቻ ነው፡፡ አገልግሎቱን ለማስጀመር ▪️“Google Messages’’ መተግበሪያን ከጉግል አፕ ማውረድ ▪️የጂሜል አካውንት በማስገባት default messaging ማድረግ ▪️በመተግበሪያው ከላይ በቀኝ በኩል ‘’Messages settings’’ የሚለውን መምረጥ ▪️‘’General’’ የሚለውን በመጫን በመቀጠል ‘’RCS Chats’’ የሚለውን ምረጡ ▪️ ‘’Verify Your Number’’ የሚለውን በመምረጥ የሞባይል ቁጥርዎን በማስገባት መጨረስ። Google Messages Playstore link 🌐 @bighabesha_softwares

😺 ChatGPT is now available as an add-on in Excel and Google Sheets. It can help analyze messy data, write formulas, update spreadsheets, and explain what it’s doing along the way without leaving your spreadsheet. Powered by GPT-5.5.

📚በአዲስ አበባ የ2018 E.C የ2ኛ ሴሚስተር የሞዴል ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 🔴 የ6ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 E.C ይሰጣል! 🔴 የ8ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እና 11 /2018 E.C
+3
📚በአዲስ አበባ የ2018  E.C የ2ኛ ሴሚስተር የሞዴል ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 🔴 የ6ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 E.C ይሰጣል! 🔴 የ8ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እና 11 /2018 E.C ይሰጣል! 🔴 የ12ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 E.C ይሰጣል! መልካም  ፈተና!! ✨━━━━━━━━━━━━✨ ከእያንዳንዱ ጥረት ጀርባ የስኬት አሻራ አለና ጥረታችሁን መቼም አታቁሙ። ​🤲 አላህ ይርዳችሁ፤ ብሩህ ስኬትን ይወፍቃችሁ! 🤲

📚በአዲስ አበባ የ2018 E.C የ2ኛ ሴሚስተር የሞዴል ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 🔴 የ6ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 E.C ይሰጣል! 🔴 የ8ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እና 11 /2018 E.C
+2
📚በአዲስ አበባ የ2018  E.C የ2ኛ ሴሚስተር የሞዴል ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 🔴 የ6ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 E.C ይሰጣል! 🔴 የ8ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እና 11 /2018 E.C የሚሰጥ ይሆናል! መልካም  ፈተና!! ✨━━━━━━━━━━━━✨ ከእያንዳንዱ ጥረት ጀርባ የስኬት አሻራ አለና ጥረታችሁን መቼም አታቁሙ። ​🤲 አላህ ይርዳችሁ፤ ብሩህ ስኬትን ይወፍቃችሁ! 🤲

ስለClaude AI ሙሉ ኮርስ በነፃ መውሰድ ከፈለጋችሁ (በተለይ ዴቨሎፐሮች) በዚህ link ተመዝግባችሁ በነፃ መውሰድ ትችላላችሁ። https://anthropic.skilljar.com/claude-101
ስለClaude AI ሙሉ ኮርስ በነፃ መውሰድ ከፈለጋችሁ (በተለይ ዴቨሎፐሮች) በዚህ link ተመዝግባችሁ በነፃ መውሰድ ትችላላችሁ። https://anthropic.skilljar.com/claude-101 @bighabesha_softwares

🌟 የተስፋ ኃይል፡ የፍርሃትን ገበያ የሚያከስረው "አንዱ" ምክንያት! 🌟 ​🔶 የፍርሃት ገበያ ላይ ተስፋ ለመቁረጥ ሺህ ምክንያቶችን ልናገኝ እንችላለን... ነገር ግን ተስፋ ላለመቁረጥ አንድ ምክንያት በቂ ነው!! ​በዙሪያችን ያለው ዓለም አንዳንዴ "የፍርሃት ገበያ" ይመስላል። በዚህ ገበያ ውስጥ ውድቀት፣ ጥርጣሬ፣ ሰነፍ ጓደኞች እና "አትችሉም" የሚሉ ድምፆች በብዛት ይቸበቸባሉ። ተስፋ እንድንቆርጥ የሚያደርጉ ሺህ ምክንያቶች እንደ ሸቀጥ ተደርድረው "ግዙን" ይሉናል። ነገር ግን እኛ በዚህ ገበያ ውስጥ ገብተን ተስፋ መቁረጥን አንገዛም! ​ታላቁ ሊቅ ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) የልብንና የተስፋን ሚዛን እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል፦ ​"ልብ ወደ አላህ በሚያደርገው ጉዞ ልክ እንደ ወፍ ነው፤ አላህን መውደድ ጭንቅላቱ ሲሆን፣ ፍርሃትና ተስፋ ደግሞ ሁለት ክንፎቹ ናቸው።" ​ወፍ በአንድ ክንፍ መብረር አትችልም። ፍርሃት ብቻውን ሲነግስ ሽባ ያደርገናል። ተስፋ መቁረጥ ደግሞ ክንፋችንን ሰብሮ መሬት ላይ ይጥለናል፤ ጉዞአችንንም ያሰናክላል። ስለዚህ በሺህ የፍርሃት ምክንያቶች መካከል ያችን "አንዲት" የተስፋ ክንፋችንን አጥብቀን መያዝ አለብን። ​ያች ተስፋ እንዳንቆርጥ በቂ የሆነችው "አንዲት ምክንያት" ምንድን ናት? እርሷማ ከአላህ ዘንድ የሚመጣው ድልና እገዛ ናት! አላህ (ሱ.ወ) በቅዱስ ቁርኣኑ ውስጥ የፍርሃታችንንና የጭንቀታችንን ግንብ እንደ ሚሳኤል ግቡን በሚመታ ቃል እንዲህ ይፈታዋል፦ ​"ከችግርም ጋር በእርግጥ ምቾት አለ።" (አሽ-ሸርህ፡ 5) ​ይህ አንቀፅ የሚነግረን ችግርና ምቾት አይለያዩም፤ አብረው ናቸው። ፈተናው ሲመጣ መፍትሄውም አብሮ ተልኳል። ይህን ካወቅን ተስፋ ለመቁረጥ ሺህ ምክንያቶች ቢደረደሩልንም፣ "አላህ ከመከራው ጀርባ ድልን ደብቆልናል" በሚል አንዲት ምክንያት ሁሉንም እናሸንፋለን። ​ለስኬታችን ደግሞ እንደ ሰይፍ የሳለ እና ተግባራዊ ሰዎች የሚያደርገንን የአላህ መልክተኛ (ﷺ) መመሪያ እንያዝ፦ ​"የሚጠቅምህን ነገር ለማግኘት ጉጉት ይኑርህ፣ በአላህም ተመካ፣ አቅመ-ቢስም አትሁን (ተስፋ አትቁረጥ)።" (ሶሂህ ሙስሊም) ​ይህ ሀዲስ ዝም ብለን ለተቀመጥን ሰዎች አይደለም። የሚጠቅመንን (ትምህርታችንን፣ ስራችንን፣ ራዕያችንን) ለማሳካት እንደ ውሃ ጠጥተነው በውስጣችን ሊሰርፅ የሚገባ የጥንካሬ ቀመራችን ነው። "አቅመ-ቢስ አትሁን" የሚለው የአላህ መልክተኛን (ﷺ) ቃል ተስፋ መቁረጥንና መሸነፍን ሙልጭ አድርጎ የሚቆርጥ ሰይፍ ነው። ​ብዙዎቻችን ፈተና ሲበዛብን አላህ የረሳን ይመስለናል። ነገር ግን ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ ​"ፈተናዎች ወደ አላህ የሚያቃርቡህ ከሆነ ካንተ የተሰወሩ ፀጋዎች ናቸው።" ​🚀 ከፍርሃት ገበያ ወደ ተስፋ ሜዳ የምንሸጋገርባቸው 3 እርምጃዎች፦ ​አሁን ካለንበት የተስፋ መቁረጥ ስሜት ወጥተን ወደ ስኬት ጎዳና ለመመለስ እነዚህን ሦስት ተግባራዊ ነጥቦች በጋራ እንተግብራቸው፦ ❶ ​ልባችንን እንጠግን፦ በየቀኑ ፈጣሪያችንን በማውሳት (ዚክር) የፍርሃትን ድምፅ እናጥፋው። አላህ እንዲህ ይላልና፦ "ልቦች አላህን በማውሳት ይረካሉና።" (አር-ራዕድ፡ 28)። የልብ መርጋት የተስፋ መጀመሪያ ነው። ❷ ​አካባቢያችንን እንመርምር፦ ሁሌም "አይቻልም" የሚሉንንና ተስፋችንን የሚሰርቁንን "የፍርሃት ነጋዴዎች" እንራቃቸው። በተስፋ ከሚሞሉን፣ ራዕይ ካላቸውና አብረውን ከሚተጉ ሰዎች ጋር እንቀላቀል። ❸ ​በትንሿ እርምጃ እንጀምር፦ ትልቁን ተራራ አይተን አንደንግጥ፤ ዛሬ መራመድ የምንችላትን አንዲት እርምጃ ብቻ እንራመድ። ግቡ ላይ ለመድረስ ሺህ ኪሎ ሜትር መጓዝ ካለብን፣ በዛሬዋ አንዲት እርምጃ መጀመር ግድ ይለናል። የተቀረውን ለፈጣሪያችን እንተው! ♦️​የመጨረሻ መልዕክታችን፦ ትላንት የተሳሳትንባቸው ስህተቶች፣ ዛሬ የገጠሙን መሰናክሎች እና ነገ የሚመጡት ስጋቶች በሙሉ የፍርሃት ገበያ ሸቀጦች ናቸው። እኛ ግን ከእኛ ጋር ያለውን ጌታ፣ ውስጣችን ያለውን አቅም እና ከፊታችን ያለውን ብሩህ ቀን እናስብ። ያ "አንዱ ምክንያት" ሺህ የፍርሃት ሰራዊትን ለማሸነፍ በቂ ነው! ​ተስፋ አንቁረጥ! ጉዞአችንን እንቀጥል! ✨━━━━━━━━━━━━✨ 🌈 ꧂ ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈

Claude AI ያለVPN መስራት ጀምሯል መጠቀም ትችላላችሁ። አፕሊኬሽኑ play store ላይ የለም። Claude.ai ላይ አካውንት በመክፈት መጠቀም ትችላላችሁ።
Claude AI ያለVPN መስራት ጀምሯል መጠቀም ትችላላችሁ። አፕሊኬሽኑ play store ላይ የለም። Claude.ai ላይ አካውንት በመክፈት መጠቀም ትችላላችሁ።

ጥቆማ‼ ===== ✍️ ነቃ በሉ፣ አታንቀላፉ! ማለፍ የሌለባችሁ ወርቃማ የስታርታፕ ዕድል! የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት (EAII) በአይነቱ ልዩ የሆነውን የስታርታፕ (Startup) ድጋፍ 2ኛ ዙር ምዝገባ ይፋ አድርጓል። ባለፈው በመጀመሪያው ዙር የገቡት ከ200 በላይ ልጆች ምን ያህል ተጠቃሚ እንደሆኑና በወረቀት ላይ የነበረ ሃሳባቸውን ወደ ተጨባጭ ቢዝነስ እንደቀየሩ አይተናል። አሁን ደግሞ ይበልጥ ሰፍቶ እና አዳዲስ ድጋፎችን አካቶ መጥቷል። እንደ ወንድም ልምከራችሁ፡- ምናልባት "ገና እኮ ሞዴል ትሬይን (Train) አድርጌ አልጨረስኩም" ብላችሁ ወደኋላ እንዳትሉ። ማቅረብ ያለባችሁ ፕሮጀክት ከኤአይ (AI) ጋር የተያያዘ መሆን አለበት እንጂ፣ የግድ የተጠናቀቀ ሞዴል ይዛችሁ ቅረቡ አይባልም። ከሃሳብ እና ከፕሮቶታይፕ (Prototype) ጀምሮ ይዛችሁ መግባትና መወዳደር ትችላላችሁ። መድረኩን ካገኛችሁ በራስ መተማመን ሃሳባችሁን በሚገባ አስረዱት (Pitch it well)፤ በደስታ ነው የሚቀበሏችሁ። ይሄ ፕሮግራም ዝም ብሎ ማዳመጥ ብቻ አይደለም፤ ከሃሳብ ጀምሮ፣ እውን አድርጋችሁት፣ ከዛ ጋር የተያያዘ ፈንድ (Funding) አግኝታችሁ፣ ተግባር ላይ የሚውል ፕሮዳክት እስኪሆን ድረስ አብረዋችሁ ሆነው ያግዟችኋል። በተለይ ይሄ እድል ለነማን ነው አሪፍ? በኤአይ (AI) ዘርፍ ላይ ፈጠራ አስባችሁ ነገር ግን መስሪያ ቦታ (Workspace) ላጣችሁ ስታርታፖች፣ የኤአይ ሞዴሎችን ትሬይን የምታደርጉበት አቅም ያለው ኮምፒውተር/ጂፒዩ (GPU) ለሌላችሁ፣ እንዲሁም ለዲፕሎይመንት (Deployment) ለተቸገራችሁ ወጣቶች... ይሄ እድል ፈፅሞ ሊያመልጣችሁ አይገባም! 🎯 የትኞቹ ዘርፎች ላይ መሳተፍ ይቻላል? በግብርና፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በሮቦቲክስ፣ በኤ.አይ ኤጀንት (AI Agent)፣ እንዲሁም በቨርችዋል እና ኦግመንትድ ሪያሊቲ (VR/AR) ዘርፎች ላይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ ሁሉ መሳተፍ ትችላላችሁ። ⏰ የምዝገባ ጊዜ፡- ከሚያዚያ 15፣ 2018 እስከ ግንቦት 06፣ 2018 ብቻ! (ቀኑ እየሄደ ነው ቶሎ በሉ) 🔗 ለማመልከት፡- ይህን ድረ-ገፅ ይጠቀሙ ▶️ aistartup.aii.et የፈጠራ ሃሳብዎን ወደ ተጨባጭ ምርት፣ ህልምዎን ወደ እውነታ የሚቀይሩበት ጊዜ አሁን ነው። በድጋሚ እላለሁ ነቃ በሉ፣ አታንቀላፉ! ለሌሎች ጓደኞቻችሁም እንዲደርሳቸው ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ! || https://t.me/STEMwithMurad

ለተማሪዎች ምርጥ PDF ማንበቢያ App FLEX PDF READER - Group PDF files together - Table of contents - Merge multiple PDFs - Split PDF - A
+2
ለተማሪዎች ምርጥ PDF ማንበቢያ App FLEX PDF READER - Group PDF files together - Table of contents - Merge multiple PDFs - Split PDF - Add watermark - Images to PDF - PDF to Image - Lock PDF - Unlock PDF - Create Bookmarks - Search PDFs - Dark and light mode Install 👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.smartpdf.reader

ክፍል 11፦ ማጠቃለያና የነፍስ ቃል ​ውድ ወላጆች፤ ልጆቻችን የአላህ አማናዎች ናቸው። በትምህርት ቤታችን የተሰጠው የጥናት መርሐ ግብር (Schedule) እናንተን ለማገዝ የተዘጋጀ "ካርታ" ነው። ይህን ካርታ በፍቅር፣ በትዕግስትና በእምነት ተጠቀሙበት። የልጆቻችሁን ልዩ ተሰጥኦ እዩላቸው፣ ጥረታቸውን አድንቁላቸው። ዛሬ የምታሳዩአቸው ርህራሄና የምትሰጧቸው ማበረታቻ፣ ነገ ለሚገነቡት ታላቅ ስብዕና ዋነኛው ግብዓት ነው። ​➤ የድርጊት ቃል ኪዳን፦ ይህን መልዕክት ካነበባችሁ በኋላ፣ ዛሬውኑ ማታ ከልጆቻችሁ ጋር አዲስ የፍቅርና የክትትል ምዕራፍ ጀምሩ። ​ ​🌸 አላህ ይርዳችሁ እና ትምህርታችሁንም ይባርክላችሁ። ዛሬ የምታደርጉት እያንዳንዱ ትንሽ ጥረት ነገ ብሩህ ስኬት ይሆናል! 🌸 🤲  🤲 ━━━━━━━━━━━━━━ ​📢 ለልጆቻችን ስኬትና ብሩህ ተስፋ! ​✅ ይህ መመሪያ በአላህ ፈቃድና እገዛ የልጆቻችንን ሁለገብ ስኬት ለማገዝ የቀረበ አነስተኛ ጥረት ነው። ሁሉም ስኬት የሚገኘው በአላህ ፈቃድ ነውና፣ ይህ መልዕክትም ለልጆቻችን እድገት ሰበብ እንዲሆንልን እንመኛለን። ​➡ መልዕክቱ 11 ወሳኝ ክፍሎችን የያዘ በመሆኑ ረዘም ሊል ይችላል፤ ሆኖም እያንዳንዱ ነጥብ ለልጆቻችን ስኬትና ሥነ-ምግባር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ የታሰበ ነው። ኢንሻአላህ!! ​💡 ትኩረት ለልጆቻችን ስኬት፦ እነዚህን ነጥቦች በአግባቡ ለማደራጀትና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማሰባሰብ ረጅም ሰዓታት ቢፈጁም፤ እናንተ ለልጆቻችሁ ስኬት ሲባል ጥቂት ደቂቃዎችን ሰጥታችሁ አስራ አንዱንም ክፍሎች ብታነቧቸው፣ በአላህ ፈቃድ ለትልቅ ለውጥ መነሻ ይሆናል። ​መልካም ንባብ! ✨━━━━━━━━━━━━✨ 🌈 ꧂ ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈

​🔶 የተግባር እርምጃ፦ ባለፉት ሦስት ወራት ልጃችሁ የትኛው ትምህርት ላይ የተሻለ ዝንባሌ እንዳለው መዝግቡ። ደካማ በሆነበት ላይ ድጋፍ አድርጉ እንጂ ወቀሳ አታውርዱበት። ​ክፍል 5፦ የተሰጥኦ ሚስጥር፦ "እያንዳንዱ ለተፈጠረለት ይገራል" ​እያንዳንዱ ልጅ ለተፈጠረለት አላማ የተመቻቸ ነው። ወላጅ የልጁን ደካማ ጎን ብቻ ከመመልከት ይልቅ፣ ጠንካራ ተሰጥኦውን መፈለግ አለበት። የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ሶሐባዎቻቸውን የገመገሙት በተለያየ መስክ ነበር። አቡበክር (ረ.ዐ) በለገስነታቸው፣ ዑመር (ረ.ዐ) በጥንካሬያቸው፣ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ በጦር መሪነታቸው እንደተመሰገኑት ሁሉ፤ የእናንተም ልጅ ነገ ለዓለም የሚተርፍበት የራሱ መስክ ይኖረዋል። ​ሳይንቲስቱ አልበርት አንስታይን እንዲህ ይላል፦ "ሁሉም ሰው ሊቅ ነው፤ ነገር ግን አንዲትን አሳ ዛፍ ላይ የመውጣት ችሎታዋን መለኪያ አድርገህ ብትመዝናት፣ እድሜዋን ሙሉ ጅል እንደሆነች አስባ ትኖራለች።" የልጃችሁን የ"ዋናተኛነት" ተፈጥሮ ሳታዩ ለምን እንደ ዝንጀሮ ዛፍ ላይ አልወጣህም ብላችሁ አትውቀሱት። ​▶ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ❝ስሩ፤ እያንዳንዱ ሰው ለተፈጠረለት ነገር የተገራ/የተመቻቸለት ነው።❞ [ቡኻሪና ሙስሊም] ​⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ የልጄ "የተገራለት" (ተፈጥሯዊ) ዝንባሌ ምንድነው? እኔስ እሱን ለማሳደግ ምን አድርጌያለሁ? ​ 🔶 የተግባር እርምጃ፦ ልጁ ከትምህርት ውጪ የሚያሳያቸውን የፈጠራ ስራዎች በጥሞና ተከታተሉና አድናቆት ስጡ። ​ክፍል 6፦ የኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) የትምህርት ፍልስፍና ​የልጆቻችንን አቅም እንዴት መገምገም እንዳለብን ሊቃውንት ትልቅ ጥቆማ ሰጥተውናል። ትምህርት ማለት የመረጃ ጭነት ሳይሆን የተሰጥኦ ጥበቃ ነው። የልጁን ተፈጥሯዊ ዝንባሌ ማስተዋልና እሱን ማሳደግ ከሁሉ በላይ ዋጋ አለው። ​ሳይንቲስቱ ሃዋርድ ጋርድነር "የብዝሃ-እውቀት" ቲዎሪውን ሲያቀርብ፣ ሰው በስምንት የተለያዩ መንገዶች ሊቅ ሊሆን እንደሚችል አረጋግጧል። ሒሳብ ላይ 100 ያላመጣ ልጅ በንግግር፣ ከሰው ጋር በመግባባት ወይም በቴክኖሎጂ አቻ የሌለው ሊቅ ሊሆን ይችላል። ​🎤 ​​ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "ወላጅ የልጁን የተፈጥሮ ዝንባሌ ማስተዋል አለበት። ልጁ ዝንባሌ በሌለው ትምህርት በግድ እንዲወጠር ማድረግ የለበትም። ዝንባሌውን ያገኘ ልጅ በዚያ መስክ የላቀ ይሆናል፤ የማይወደውን የተጫነ ግን ሁለቱንም ያጣል (አዲሱንም አያውቅም፣ የራሱንም ተሰጥኦ ይገድላል)።" ​ ⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ እኔ የምገነባው የልጄን ስብዕና ነው ወይስ የእኔን ያልተሳካ ህልም በእሱ ላይ ለመጫን እየሞከርኩ ነው? ​ 🔶 የተግባር እርምጃ፦ ልጃችሁ የማይወደውን ትምህርት ለምን እንደማይወደው በረጋ መንፈስ ጠይቁት። ችግሩ ከተፈጥሮ ዝንባሌ ከሆነ አማራጭ መንገዶችን ፈልጉ። ​ክፍል 7፦ "ጥረት" ከ "ውጤት" ይበልጣል ​እንደ ወላጅ ትኩረታችን መሆን ያለበት ልጆቻችን ባመጡት "ቁጥር" ላይ ሳይሆን፣ ባሳዩት "ጥረት" ላይ ነው። ውጤት በብዙ ነገሮች ሊለዋወጥ ይችላል፤ ጥረት ግን ቋሚ ስብዕና ነው። ቶማስ ኤዲሰን መብራትን ከመፍጠሩ በፊት 10,000 ጊዜ ወድቆ ነበር። እናቱ ግን "ውድቀት" ብላ አልጠራችውም፤ "ለመስራት የማይችሉ 10,000 መንገዶችን አገኘህ" ብላ አበረታታችው እንጂ። ዛሬ በጥረት ያገኘው 80፣ ነገ ወደ 100 ያደርሰዋል። ጥረትን ማድነቅ ተማሪው ተስፋ እንዳይቆርጥ ያደርገዋል። ​🎤 ​ኢማም አሽ-ሻፊዒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "እውቀት ማለት መረጃን በቃል መያዝ ሳይሆን፣ ለተግባር የሚጠቅመውና ሰውን የሚቀይረው ነው።" ​⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ልጄ ዛሬ ቢለፋም ውጤቱ ባይመጣ፣ ጥረቱን አይቼ "አይዞህ" እለዋለሁ? ወይስ "ጊዜዬን አባከንክ" ብዬ እገስጻለሁ? ​ 🔶 የተግባር እርምጃ፦ "100 ስላመጣህ ጎበዝ ነህ" ከማለት ይልቅ "ዛሬ 40 ደቂቃ ሙሉ በጥሞና ስላጠናህ ኩራት ይሰማኛል" የሚለውን አገላለጽ ተጠቀሙ። ​ክፍል 8፦ የቤት ድባብ፦ የዕውቀት ቤተ-ሙከራ ​ቤት የዕውቀት ድባብ ከሌለው ትምህርት ቤት የሰጠው እውቀት ይከስማል። እናንተ ስልካችሁን እያያችሁ ልጁን "አጥና" ብትሉት ውጤት የለውም። የልጁ አርአያ እናንተ ናችሁ። ልጁ በሚያጠናበት 40 ደቂቃ ውስጥ እናንተም መጽሐፍ ወይም ቁርኣን በመያዝ የንባብ ድባብ ፍጠሩ። ቤቱ የቲቪና የስልክ ጫጫታ ከሆነ፣ የልጁ አእምሮ በትምህርቱ ላይ ሊያተኩር አይችልም። ​♦️ በተጨማሪም የጥናት ቦታው አካላዊ ዝግጅት ወሳኝ ነው። ልጆች አልጋ ላይ ተኝተው እንዳያጠኑ ማሳሰብ ይገባል፤ አእምሮ አልጋን ከእንቅልፍ ጋር ስለሚያያይዘው ትኩረት ይበተናል። ጸጥታ ያለበት፣ በቂ ብርሃንና ንጹህ አየር ያለው ማዕዘን ለጥናት ሊመደብላቸው ይገባል። ​🎤 ​ኢብኑ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "ወላጅ ለልጁ ምሳሌ የሚሆን ተግባር ካላሳየ ምክሩ ብቻውን ፍሬ አያፈራም።" ​⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ቤቴ የዕውቀት ማዕከል ነው ወይስ የመዝናኛ ስፍራ? ልጆቼ ሲያጠኑ እኔ ምን እያደረግኩ ነው? ​ 🔶 የተግባር እርምጃ፦ የጥናት ሰዓት ሲጀምር በቤቱ ውስጥ ያሉ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን (ቲቪ፣ ስልክ) በሙሉ ለተወሰነ ሰዓት የመዝጋት ልማድ አዳብሩ። ​ክፍል 9፦ ስሜታዊ ደኅንነት፦ የመማር ቁልፍ ​አእምሮ ስጋትና ጭንቀት ውስጥ ሲሆን የመማር አቅሙ ይዘጋል። ልጆች በትምህርታቸው ውጤት ካላመጡ ምናልባት ውስጣቸው ሰላም አጥቶ ሊሆን ይችላል። የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ለልጆች የነበራቸው ርህራሄና ፍቅር ልባቸውን እንዲከፍቱ ያደርጋቸው ነበር። ፍቅርና መረጋጋት ባለበት ቤት ውስጥ ተማሪው የትምህርት ቤት ፕሮግራሙን ለመተግበር አይቸገርም። ​♦️ ልጆች ውጤት ሲቀንስባቸው ቤት ውስጥ የሚኖረው መሸማቀቅ (ፍርሃት) ለቀጣይ ውድቀት ይዳርጋቸዋል። ከስህተት መማር እንደሚቻል ማሳየት ያስፈልጋል። በተለይም ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ባለው የዕድሜ እርከን (በተለይ ወደ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ሲጠጉ) የራሳቸው የሆነ ስሜታዊ ሽግግርና የጓደኛ ግፊት ውስጥ ስለሚገቡ፣ ወላጅ "አዛዥ" ከመሆን ይልቅ "አማካሪ እና ጓደኛ" መሆን አለበት። ልጆቻችሁን "ለምን አልመጣህም?" ብላችሁ ከመውቀሳችሁ በፊት፣ "ለማጥናት ምን ጎደለህ/ሽ? ምን የሚያስጨንቅሽ ነገር አለ?" ብላችሁ በጥበብ ጠይቁ። ​⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ልጄ እኔን የሚያየኝ እንደ "አስፈሪ ዳኛ" ነው ወይስ እንደ "አጋዥ ደጋፊ"? ​ 🔶 የተግባር እርምጃ፦ በሳምንት አንድ ቀን ከትምህርት ውጪ በሆነ ጉዳይ ላይ ከልጃችሁ ጋር ብቻችሁን ጊዜ አሳልፉ። ​ክፍል 10፦ የቴክኖሎጂ እና የስክሪን አስተዳደር ​በአሁኑ ዘመን የወላጆች ትልቁ ፈተና ቴክኖሎጂ ነው። ስልክ፣ ጌም እና ቴሌቪዥን የልጆችን ጊዜና ትኩረት በከፍተኛ ሁኔታ ይሰርቃሉ። ነገር ግን ቴክኖሎጂን ከማጥፊያነት ወደ ማሳደጊያ መሣሪያነት መቀየር ይቻላል። ለምሳሌ ለጥናት የሚረዱ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን እንዲያዩ በማድረግ በሥርዓት እንዲጠቀሙ መምራት ያስፈልጋል። ቴክኖሎጂን ያለ ገደብ መልቀቅ የልጆችን ተፈጥሯዊ የመማር ፍላጎት ያደነዝዛል። ​ ⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ የቤቴ ቴክኖሎጂ ልጆቼን እያሳደጋቸው ነው ወይስ ትኩረታቸውን እየሰረቀ? ​ 🔶 የተግባር እርምጃ፦ ልጆች ስክሪን የሚያዩበትን ሰዓት ገደብ በማውጣት፣ ከትምህርት ጋር የተገናኙ ጠቃሚ ይዘቶችን ብቻ እንዲከታተሉ መምራት።