es
Feedback
Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Ir al canal en Telegram

​💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል ​በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2

Mostrar más
1 878
Suscriptores
-124 horas
-157 días
-5630 días
Archivo de publicaciones
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ፣ የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል የሁለተኛ ሴሚስተር ከተማ አቀፍ ሞዴል ፈተና መስጫ ጊዜ ሰሌዳ
+3
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ፣ የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል የሁለተኛ ሴሚስተር ከተማ አቀፍ ሞዴል ፈተና መስጫ ጊዜ ሰሌዳ

📚 ርዕስ: ከፈተና በፊትና በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች ውድ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች፤ የፊታችን ግንቦት 10 እስከ 12/2018 ዓ.ል ለምትወስዱት የሞዴል ፈተና እንዲሁም ለቀጣዩ የሚኒስትሪ ፈተና ስንቅ ይሆን ዘንድ፣ ይህንን አጭር እና ጠቃሚ ምክር በጥንቃቄ አንብቡት። የፈተና ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ እና ተፈጥሯዊ ነገር ነው። ይህንን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት። 1. ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገቡን ወርቃማ ዘዴዎች ♦️አመለካከትን ማስተካከል፡ ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። መሳሳትን አትፍሩ፤ ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጁ መሆን የብልህ ተማሪ መገለጫ ነው። ♦️የጋራ ጥናት፡ ከጓደኞቻችን ወይም ከወላጆቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ ትልቅ ጥቅም አለው። ይህ ዘዴ የማስታወስ ብቃታችንን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያደርጋል። ♦️በቂ እረፍት እና እንቅልፍ፡ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ጭንቀትን ይቀንስልናል፤ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። 💡የሳይንቲስቶች እይታ፡ "እንቅልፍ የተማርነውን አዲስ እውቀት ወደ ዘላቂ ማህደረ-ትውስታ (Long-term memory) የምናሸጋግርበት ወርቃማ ድልድይ ነው።" ስለዚህ በቂ እንቅልፍ ማግኘት ያጠናነውን እንዳንረሳ ያደርገናል።    2. በፈተና ወቅት መከተል ያለብን ጥበቦች ♦️ቅድመ ዝግጅት፡ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት አለብን። ♦️ድንገተኛ ጭንቀትን ማሸነፍ፡ በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይኖርብናል። ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ወሳኝ ነው። 📖 ነቢዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ከባድ ሀላፊነት ሲገጥማቸው አላህን እንዲህ ብለው ተማጸኑ፦ ❝ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ፤ ነገሬንም ለእኔ አግራልኝ።❞ (ሱረቱ ጣሀ፡ 25-26)። እናንተም በፈተና ወንበር ላይ ስትቀመጡ ይህንን በማሰብ አላህ ነገራችሁን እንዲያገራላችሁ ጠይቁ።    ♦️ራስን ማረጋጋት፡ "እኔ የምችለውን አድርጌያለሁ (ሰበብ አድርሼያለሁ)፣ የቀረውን ለአላህ ሰጥቼዋለሁ!" በማለት የማረጋጊያ ቃላትን ለራሳችሁ ንገሩ። ♦️የጥያቄ አያያዝ ስልት፡ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግምት መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይገባናል። በተደጋጋሚ ሰአት በቃን አልበቃን እያልን መጨነቅ የለብንም። 🔴 መሰረዝና መደለዝን መቀነስ፡ ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ሌላ መልስ እንድንሰጥ ስለሚያረግ፣ በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ አለብን። 3. ከፈተና በኋላ... አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት መገመት አይገባንም። ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን፣ ከዚህ ይልቅ እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ይመከራል። አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን አለብን። ⭐💫 ማጠቃለያ ሁሌም ልናስታውሰው የሚገባን ትልቁ እውነት፡- ፈተና ማለት ለጀነት ማለፊያ ትኬት እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን ነው። ሁሉም ነገር አላህ ከወሰነው ውጭ እንደማይሆን ማመን አለብን። ከኛ የሚጠበቀው የአቅማችንን ያህል ማድረግ፣ ሌላውን ለአላህ መተው ነው። አላህ በናንተው ጥረት ብቻ ሳይሆን በሱ እዝነት መልካም የሆነ ውጤትን ይሰጣችኋል። 🤲 ዱዓ ያ አላህ! አንተ እውቀትን ሰጪ፣ ልብን ከፋች አምላክ ነህና ለእነዚህ ልጆች ልባቸውን አስፋላቸው። ያጠኑትን ወደ አእምሮአቸው መልስላቸው፤ ያልገባቸውን አብራራላቸው። በፈተና ወቅት የሚመጣን ጭንቀት እና መደናገር አንሳላቸው። በጥረታቸው ብቻ ሳይሆን በአንተ ሰፊ እዝነት፣ ልፋታቸውን አሳምረህ አስደሳች እና ያማረ ውጤት ወፍቃቸው። ያረብ... ቀጣዩን የህይወት ዘመናቸውንም በስኬት፣ በኢማን እና በጥበብ የተሞላ አድርግላቸው! አሚን! 🤲 ═══════════════ ◆ ጥረት ካለ ስኬት አይርቅም፤ ትጋት ካለ ድል አይታጣም!! ✅ ስኬት ለልጆቻችን፣ ለአበቦች፣ ለአንፀባራቂ ኮከቦች! ✨━━━━━━━━━━━━✨ 🌈 ꧂ ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈

+3
📚 Addis Ababa City Administration Education Bureau 🔶 2018 E.C. Grade 8 Ministry Exam Answer Sheet

✅ የMS-Word ሙሉ ክህሎት በተግባር የተደገፈ ቪድዮ ይሀውና!! 📧 MS-Word ሙሉ ትምህርት በቪድዮ 📧 የሰዓት ቆይታ: 1:46 ደቂቃ (አንድ ሰዓት ከ46 ደቂቃ) 📧 የMB መጠን: 265MB አዘጋጅ እና ድምፅ: ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ════════════════ 📧 ታላቁ ሰሀባ አቡ ደርዳእ እንዲህ ይላል፦ 📧 "እኔ አኺራ ላይ የሚያስፈራኝ ነገር ቢኖር ባወቅከው ምን ሰራህበት መባሌ ነው"!! ════════════════ ⭕️ ቪድዮውን አይታችሁ ስትጨርሱ አስተያየት: ..........................! 📧 📧 ════════════════ ለመምህራን የተሰጠ ስልጠና፤ እናንተም ተጠቀሙበት!! ✍️ Basic Computer Skills 🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻 Telegram: t.me/BasicComputer_Skills tiktok.com/@basiccomputerskills

ጥቆማ‼ ====== (ልጆቻችሁን ቶሎ አስመዝግቡ። በመሰል ነገሮች ከጠቆምኳችሁ ዓይናችሁን አትሹ!) || ✍️ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ! የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በተከታዮቹ መስኮች ራሳችሁን የምታንጹበት ታላቅ የክረምት ስልጠና አዘጋጅቶላችኋል። በፈንዳሜንታል ኦፍ ኤ.አይ፣ 💻 ፕሮግራሚንግ፣ 🧠 ማሽን ለርኒንግ፣ ⚙️ በሮቦቲክስ እና IOT፣ 📊 ዳታ ሳይንስ እና በሌሎችም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፎች ራሳችሁን የምታንጹበት ታላቅ የክረምት ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል። እስከ ግንቦት 30፤ 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በተከታዩ የጉግል ፎርም https://forms.gle/uDGPmQsiZcWWeNuRA በመጠቀም ይመዝገቡ።

​⏳ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ (Entrance) ፈተና፦ የድል፣ የተስፋ እና የቁርጠኝነት ዘመቻ! ​(ለተፈጥሮ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች) ​✨ "ትልቁ ሽልማት የጀመርከው ከመሆን ይልቅ ምን እንደምትሆን ነው!" ​ውድ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች እና ወላጆች፣ የአስራ ሁለት ዓመታት የትምህርት ጉዞ ፍሬ የሚያፈራበት፣ የህይወታችሁ ትልቁ ምዕራፍ ሊከፈት ከፊታችሁ ቆሟል። የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ል እንደሚሰጥ ታውቋል። ይህ ማለት የዩኒቨርሲቲን በር በክብር ከፍታችሁ ለመግባት የቀራችሁ ጊዜ አንድ ወር ከ20 ቀን ገደማ ብቻ ነው! ​ይህ ቀሪ ጊዜ ልክ እንደ ሰይፍ ስለት ነው፤ በቸልተኝነት ከያዝነው ይቆርጠናል፣ በብልሃትና በቁርጠኝነት ከተጠቀምንበት ግን የተደቀኑብንን የፈተና እሾሆች ይመነጥርልናል! ስኬት በድንገት አይከሰትም፤ ስኬት የዲሲፕሊን፣ የትጋት እና በአላህ (ሱ.ወ) ላይ የመመካት (ተወኩል የማድረግ) ጣፋጭ ውጤት ነው። ​🚀 የጥናት ስልቱ፦ ​ከላይ በምስሎቹ ላይ የምትመለከቱት የጥናት መርሃ ግብር፣ ከ11ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ የተፈጥሮ (Natural) እና የማኅበራዊ (Social) ሳይንስ ተማሪዎች በልዩ ጥንቃቄ የተዘጋጀ ነው። አጭሩን ጊዜ በከንቱ ከመባከን አድኖ፣ አዕምሮን በከፍተኛ ንቃት የሚያሰራው ሳይንሳዊ ስልት ይኸውላችሁ፦ ​🌙 የማታ ጥናት (Evening Study)፦ ጸጥታው ሲሰፍን ማታ ላይ የምታጠፉት ሰዓት፣ ጽንሰ ሀሳቦችን (Concepts) በጥልቀት የምትረዱበት እና የዕለቱን ትምህርት የምታደራጁበት ወርቃማ ጊዜ ነው። ​🌅 የጥዋት ጥናት (Morning Study)፦ አዕምሮ ሙሉ እረፍት አግኝቶ እንደ ንጋት ፀሀይ በሚያበራበት የጠዋት ሰዓት ማጥናት ትልቁ ስኬት ነው። በተለይ እንደ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ የመሳሰሉትን ትኩረት የሚጠይቁ ትምህርቶች በዚህ ጊዜ ማጥናት የማይበገር አቅም ይገነባል። ​🎯 የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ፦ እያንዳንዷ ደቂቃ ትቁጠር! ​ፈተናን ለማሸነፍ ሰዓታትን ዝም ብሎ ማሳለፍ ሳይሆን፣ ጊዜን በስልት መግራት ወሳኝ ነው። መርሃ ግብሩ ይህንን ሚስጥር ይዟል፦ ​1. ለጠቅላላ ትምህርቶች (45 + 10 + 25): ​📖 45 ደቂቃ (Study)፦ በሙሉ ትኩረት ማጥናት፤ ዓለማችሁን መጽሐፉ ላይ ብቻ ማድረግ። ​☕ 10 ደቂቃ (Tea Break)፦ አዕምሮን ለማደስ አጭር እረፍት ማድረግ። ​📝 25 ደቂቃ (Questions)፦ ያነበባችሁትን ወደ አዕምሮ ጠልቆ እንዲገባ፣ ያለፉት ዓመታት ጥያቄዎችን በተግባር መስራት! ​2. ለሂሳብ ትምህርት ልዩ ቀመር (35 + 10 + 35): 🔶​ሂሳብ የልምምድ ትምህርት ስለሆነ፣ 35 ደቂቃ ህጎችን ካጠናችሁ በኋላ፣ አጭር እረፍት ወስዳችሁ በቀጥታ ወደ 35 ደቂቃ የጥያቄ ልምምድ ግቡ። ጥያቄ መስራት በራስ መተማመናችሁን ከፍ ያደርገዋል! ​🔥 ተስፋ አትቁረጡ፣ የድል አጥቢያ ላይ ናችሁ! ​ውድ ተማሪዎች፣ በዚህ ወሳኝ ሰዓት እንቅልፍ ማጣት፣ መድከምና ጭንቀት ሊሰማችሁ ይችላል። ነገር ግን ዛሬ የምትከፍሉት እያንዳንዱ የመስዋዕትነት ላብ፣ ነገ ካምፓስ ገብታችሁ ለምታፈሱት የደስታ እንባ ዋጋ ነው። ፈተናው ፍርሃት ሳይሆን ብቃታችሁን የምታሳዩበት ትልቅ መድረክ ነው! ​"ስኬት የመጨረሻ አይደለም፤ ውድቀትም ገዳይ አይደለም፤ ዋናው ነገር ለመቀጠል ያለው ድፍረት ነው!" ዛሬ ያመለጠቻችሁን ደቂቃ ነገ በማካካስ ከትላንቱ የተሻላችሁ ሁኑ። ሰብቡን (ምክንያቱን) አድርሱ፤ ዱዓችሁን ከጥረታችሁ ጋር አስተባብሩ። አላህ (ሱ.ወ) በንጋት ተነስቶ ለሚለፋ፣ ተስፋ ሳይቆርጥ ለሚጥር ባሪያው በረካውን አይነፍገውም! ​═══════════════ ◆ ጥረት ካለ ስኬት አይርቅም፤ ትጋት ካለ ድል አይታጣም!! ✅ ስኬት ለልጆቻችን፣ ለአበቦች፣ ለአንፀባራቂ ኮከቦች! ✨━━━━━━━━━━━━✨ ​🌈 ꧂ ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈

Grade ⓬ 📌ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት እያደረጉ ነው? ✅በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ አጋዥ የትምህርት ይዘቶች እና የመለማመጃ ጥያቄዎችን የያዙ ቪዲዮዎች በድረ-ገፅ ያገኛሉ። ይለማ
Grade ⓬ 📌ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት እያደረጉ ነው? ✅በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ አጋዥ የትምህርት ይዘቶች እና የመለማመጃ ጥያቄዎችን የያዙ ቪዲዮዎች በድረ-ገፅ ያገኛሉ። ይለማመዱ ⬇️⬇️⬇️ https://examinfo.moe.gov.et/guides ➡️የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ል እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል። ✅#SHARE መልካም  ጥናት✅

Google messages ስትጠቀሙ RCS On ማድረጋችሁ ምን ይጠቅማችኋል? ⚫Message ስትልኩ ብር አይቆርጥባችሁም። ነገር ግን Data ማብራት ይጠበቅባችኋል። የምትልኩለት ሰው Google mess
Google messages ስትጠቀሙ RCS On ማድረጋችሁ ምን ይጠቅማችኋል? ⚫Message ስትልኩ ብር አይቆርጥባችሁም። ነገር ግን Data ማብራት ይጠበቅባችኋል። የምትልኩለት ሰው Google messages የሚጠቀምና Online መሆን አለበት። ⚫የGemini AI እዛው Google messages ላይ መጠቀም ትችላላችሁ። ⚫ የድምፅ መለዕክት፣ ፎቶ፣ location፣ GIFና Sticker መላላክ ትችላላችሁ። ⚫End-to-End encrypted ነው። ያ ማለት የምትልኩትን መልዕክት ማንኛውም service provider (ቴሌ ወይም ሳፋሪኮም) የማየት እድል የላቸውም። ግን ሁለታችሁም Google messages ከተጠቀማችሁና E2EE on ከሆነ ብቻ ነው። ⚫Message የላካችሁለት ሰው የላካችሁትን መልዕክት ማየቱና አለማየቱን ማዎቅ ትችላላችሁ። እንዲሁም type በሚያደርግበት ጊዜ Typing....ይላችኋል። እዚ ጋ ጥንቃቄ ማድረግ ያለባችሁ RCS on አድርጋችሁ Message ስትልኩ እናንተ data ካላበራችሁ message error ይላችኋል። የምትልኩለት ሰውም Online ካልሆነ የላካችሁት message አይገባለትም። ይህን ነገር ለማስተካከል የምትልኩለት ሰው profile ላይ ገብታችሁ "Only send SMS and MMS messages" የሚለውን On ማድረግ ይጠበቅባችኋል። RCS Chat እንዴት on እንደሚደረግ ማዎቅ ከፈለጋችሁ https://t.me/bighabesha_softwares/1779 @bighabesha_softwares

Ethio telecom የGoogle RCS(Rich Communication Services) አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቃላችሁ? RCS ማለት በሞባይል ስልክ መልዕክትን በኢሞጂ፣ በፎቶ፣ በቪዲዮ እና በድምፅ
Ethio telecom የGoogle RCS(Rich Communication Services) አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቃላችሁ? RCS ማለት በሞባይል ስልክ መልዕክትን በኢሞጂ፣ በፎቶ፣ በቪዲዮ እና በድምፅ አንድ ለአንድ ወይም በቡድን ያለገደብ በመልዕክት ማጋራት የሚያስችል መንገድ ነው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው የGoogle Messaging መተግበሪያን አውርዶ መጠቀም ብቻ ነው፡፡ አገልግሎቱን ለማስጀመር ▪️“Google Messages’’ መተግበሪያን ከጉግል አፕ ማውረድ ▪️የጂሜል አካውንት በማስገባት default messaging ማድረግ ▪️በመተግበሪያው ከላይ በቀኝ በኩል ‘’Messages settings’’ የሚለውን መምረጥ ▪️‘’General’’ የሚለውን በመጫን በመቀጠል ‘’RCS Chats’’ የሚለውን ምረጡ ▪️ ‘’Verify Your Number’’ የሚለውን በመምረጥ የሞባይል ቁጥርዎን በማስገባት መጨረስ። Google Messages Playstore link 🌐 @bighabesha_softwares

😺 ChatGPT is now available as an add-on in Excel and Google Sheets. It can help analyze messy data, write formulas, update spreadsheets, and explain what it’s doing along the way without leaving your spreadsheet. Powered by GPT-5.5.

📚በአዲስ አበባ የ2018 E.C የ2ኛ ሴሚስተር የሞዴል ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 🔴 የ6ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 E.C ይሰጣል! 🔴 የ8ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እና 11 /2018 E.C
+3
📚በአዲስ አበባ የ2018  E.C የ2ኛ ሴሚስተር የሞዴል ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 🔴 የ6ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 E.C ይሰጣል! 🔴 የ8ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እና 11 /2018 E.C ይሰጣል! 🔴 የ12ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 E.C ይሰጣል! መልካም  ፈተና!! ✨━━━━━━━━━━━━✨ ከእያንዳንዱ ጥረት ጀርባ የስኬት አሻራ አለና ጥረታችሁን መቼም አታቁሙ። ​🤲 አላህ ይርዳችሁ፤ ብሩህ ስኬትን ይወፍቃችሁ! 🤲

📚በአዲስ አበባ የ2018 E.C የ2ኛ ሴሚስተር የሞዴል ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 🔴 የ6ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 E.C ይሰጣል! 🔴 የ8ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እና 11 /2018 E.C
+2
📚በአዲስ አበባ የ2018  E.C የ2ኛ ሴሚስተር የሞዴል ፈተና የጊዜ ሰሌዳ 🔴 የ6ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 E.C ይሰጣል! 🔴 የ8ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እና 11 /2018 E.C የሚሰጥ ይሆናል! መልካም  ፈተና!! ✨━━━━━━━━━━━━✨ ከእያንዳንዱ ጥረት ጀርባ የስኬት አሻራ አለና ጥረታችሁን መቼም አታቁሙ። ​🤲 አላህ ይርዳችሁ፤ ብሩህ ስኬትን ይወፍቃችሁ! 🤲

ስለClaude AI ሙሉ ኮርስ በነፃ መውሰድ ከፈለጋችሁ (በተለይ ዴቨሎፐሮች) በዚህ link ተመዝግባችሁ በነፃ መውሰድ ትችላላችሁ። https://anthropic.skilljar.com/claude-101
ስለClaude AI ሙሉ ኮርስ በነፃ መውሰድ ከፈለጋችሁ (በተለይ ዴቨሎፐሮች) በዚህ link ተመዝግባችሁ በነፃ መውሰድ ትችላላችሁ። https://anthropic.skilljar.com/claude-101 @bighabesha_softwares

🌟 የተስፋ ኃይል፡ የፍርሃትን ገበያ የሚያከስረው "አንዱ" ምክንያት! 🌟 ​🔶 የፍርሃት ገበያ ላይ ተስፋ ለመቁረጥ ሺህ ምክንያቶችን ልናገኝ እንችላለን... ነገር ግን ተስፋ ላለመቁረጥ አንድ ምክንያት በቂ ነው!! ​በዙሪያችን ያለው ዓለም አንዳንዴ "የፍርሃት ገበያ" ይመስላል። በዚህ ገበያ ውስጥ ውድቀት፣ ጥርጣሬ፣ ሰነፍ ጓደኞች እና "አትችሉም" የሚሉ ድምፆች በብዛት ይቸበቸባሉ። ተስፋ እንድንቆርጥ የሚያደርጉ ሺህ ምክንያቶች እንደ ሸቀጥ ተደርድረው "ግዙን" ይሉናል። ነገር ግን እኛ በዚህ ገበያ ውስጥ ገብተን ተስፋ መቁረጥን አንገዛም! ​ታላቁ ሊቅ ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) የልብንና የተስፋን ሚዛን እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል፦ ​"ልብ ወደ አላህ በሚያደርገው ጉዞ ልክ እንደ ወፍ ነው፤ አላህን መውደድ ጭንቅላቱ ሲሆን፣ ፍርሃትና ተስፋ ደግሞ ሁለት ክንፎቹ ናቸው።" ​ወፍ በአንድ ክንፍ መብረር አትችልም። ፍርሃት ብቻውን ሲነግስ ሽባ ያደርገናል። ተስፋ መቁረጥ ደግሞ ክንፋችንን ሰብሮ መሬት ላይ ይጥለናል፤ ጉዞአችንንም ያሰናክላል። ስለዚህ በሺህ የፍርሃት ምክንያቶች መካከል ያችን "አንዲት" የተስፋ ክንፋችንን አጥብቀን መያዝ አለብን። ​ያች ተስፋ እንዳንቆርጥ በቂ የሆነችው "አንዲት ምክንያት" ምንድን ናት? እርሷማ ከአላህ ዘንድ የሚመጣው ድልና እገዛ ናት! አላህ (ሱ.ወ) በቅዱስ ቁርኣኑ ውስጥ የፍርሃታችንንና የጭንቀታችንን ግንብ እንደ ሚሳኤል ግቡን በሚመታ ቃል እንዲህ ይፈታዋል፦ ​"ከችግርም ጋር በእርግጥ ምቾት አለ።" (አሽ-ሸርህ፡ 5) ​ይህ አንቀፅ የሚነግረን ችግርና ምቾት አይለያዩም፤ አብረው ናቸው። ፈተናው ሲመጣ መፍትሄውም አብሮ ተልኳል። ይህን ካወቅን ተስፋ ለመቁረጥ ሺህ ምክንያቶች ቢደረደሩልንም፣ "አላህ ከመከራው ጀርባ ድልን ደብቆልናል" በሚል አንዲት ምክንያት ሁሉንም እናሸንፋለን። ​ለስኬታችን ደግሞ እንደ ሰይፍ የሳለ እና ተግባራዊ ሰዎች የሚያደርገንን የአላህ መልክተኛ (ﷺ) መመሪያ እንያዝ፦ ​"የሚጠቅምህን ነገር ለማግኘት ጉጉት ይኑርህ፣ በአላህም ተመካ፣ አቅመ-ቢስም አትሁን (ተስፋ አትቁረጥ)።" (ሶሂህ ሙስሊም) ​ይህ ሀዲስ ዝም ብለን ለተቀመጥን ሰዎች አይደለም። የሚጠቅመንን (ትምህርታችንን፣ ስራችንን፣ ራዕያችንን) ለማሳካት እንደ ውሃ ጠጥተነው በውስጣችን ሊሰርፅ የሚገባ የጥንካሬ ቀመራችን ነው። "አቅመ-ቢስ አትሁን" የሚለው የአላህ መልክተኛን (ﷺ) ቃል ተስፋ መቁረጥንና መሸነፍን ሙልጭ አድርጎ የሚቆርጥ ሰይፍ ነው። ​ብዙዎቻችን ፈተና ሲበዛብን አላህ የረሳን ይመስለናል። ነገር ግን ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ ​"ፈተናዎች ወደ አላህ የሚያቃርቡህ ከሆነ ካንተ የተሰወሩ ፀጋዎች ናቸው።" ​🚀 ከፍርሃት ገበያ ወደ ተስፋ ሜዳ የምንሸጋገርባቸው 3 እርምጃዎች፦ ​አሁን ካለንበት የተስፋ መቁረጥ ስሜት ወጥተን ወደ ስኬት ጎዳና ለመመለስ እነዚህን ሦስት ተግባራዊ ነጥቦች በጋራ እንተግብራቸው፦ ❶ ​ልባችንን እንጠግን፦ በየቀኑ ፈጣሪያችንን በማውሳት (ዚክር) የፍርሃትን ድምፅ እናጥፋው። አላህ እንዲህ ይላልና፦ "ልቦች አላህን በማውሳት ይረካሉና።" (አር-ራዕድ፡ 28)። የልብ መርጋት የተስፋ መጀመሪያ ነው። ❷ ​አካባቢያችንን እንመርምር፦ ሁሌም "አይቻልም" የሚሉንንና ተስፋችንን የሚሰርቁንን "የፍርሃት ነጋዴዎች" እንራቃቸው። በተስፋ ከሚሞሉን፣ ራዕይ ካላቸውና አብረውን ከሚተጉ ሰዎች ጋር እንቀላቀል። ❸ ​በትንሿ እርምጃ እንጀምር፦ ትልቁን ተራራ አይተን አንደንግጥ፤ ዛሬ መራመድ የምንችላትን አንዲት እርምጃ ብቻ እንራመድ። ግቡ ላይ ለመድረስ ሺህ ኪሎ ሜትር መጓዝ ካለብን፣ በዛሬዋ አንዲት እርምጃ መጀመር ግድ ይለናል። የተቀረውን ለፈጣሪያችን እንተው! ♦️​የመጨረሻ መልዕክታችን፦ ትላንት የተሳሳትንባቸው ስህተቶች፣ ዛሬ የገጠሙን መሰናክሎች እና ነገ የሚመጡት ስጋቶች በሙሉ የፍርሃት ገበያ ሸቀጦች ናቸው። እኛ ግን ከእኛ ጋር ያለውን ጌታ፣ ውስጣችን ያለውን አቅም እና ከፊታችን ያለውን ብሩህ ቀን እናስብ። ያ "አንዱ ምክንያት" ሺህ የፍርሃት ሰራዊትን ለማሸነፍ በቂ ነው! ​ተስፋ አንቁረጥ! ጉዞአችንን እንቀጥል! ✨━━━━━━━━━━━━✨ 🌈 ꧂ ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈

Claude AI ያለVPN መስራት ጀምሯል መጠቀም ትችላላችሁ። አፕሊኬሽኑ play store ላይ የለም። Claude.ai ላይ አካውንት በመክፈት መጠቀም ትችላላችሁ።
Claude AI ያለVPN መስራት ጀምሯል መጠቀም ትችላላችሁ። አፕሊኬሽኑ play store ላይ የለም። Claude.ai ላይ አካውንት በመክፈት መጠቀም ትችላላችሁ።

ጥቆማ‼ ===== ✍️ ነቃ በሉ፣ አታንቀላፉ! ማለፍ የሌለባችሁ ወርቃማ የስታርታፕ ዕድል! የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት (EAII) በአይነቱ ልዩ የሆነውን የስታርታፕ (Startup) ድጋፍ 2ኛ ዙር ምዝገባ ይፋ አድርጓል። ባለፈው በመጀመሪያው ዙር የገቡት ከ200 በላይ ልጆች ምን ያህል ተጠቃሚ እንደሆኑና በወረቀት ላይ የነበረ ሃሳባቸውን ወደ ተጨባጭ ቢዝነስ እንደቀየሩ አይተናል። አሁን ደግሞ ይበልጥ ሰፍቶ እና አዳዲስ ድጋፎችን አካቶ መጥቷል። እንደ ወንድም ልምከራችሁ፡- ምናልባት "ገና እኮ ሞዴል ትሬይን (Train) አድርጌ አልጨረስኩም" ብላችሁ ወደኋላ እንዳትሉ። ማቅረብ ያለባችሁ ፕሮጀክት ከኤአይ (AI) ጋር የተያያዘ መሆን አለበት እንጂ፣ የግድ የተጠናቀቀ ሞዴል ይዛችሁ ቅረቡ አይባልም። ከሃሳብ እና ከፕሮቶታይፕ (Prototype) ጀምሮ ይዛችሁ መግባትና መወዳደር ትችላላችሁ። መድረኩን ካገኛችሁ በራስ መተማመን ሃሳባችሁን በሚገባ አስረዱት (Pitch it well)፤ በደስታ ነው የሚቀበሏችሁ። ይሄ ፕሮግራም ዝም ብሎ ማዳመጥ ብቻ አይደለም፤ ከሃሳብ ጀምሮ፣ እውን አድርጋችሁት፣ ከዛ ጋር የተያያዘ ፈንድ (Funding) አግኝታችሁ፣ ተግባር ላይ የሚውል ፕሮዳክት እስኪሆን ድረስ አብረዋችሁ ሆነው ያግዟችኋል። በተለይ ይሄ እድል ለነማን ነው አሪፍ? በኤአይ (AI) ዘርፍ ላይ ፈጠራ አስባችሁ ነገር ግን መስሪያ ቦታ (Workspace) ላጣችሁ ስታርታፖች፣ የኤአይ ሞዴሎችን ትሬይን የምታደርጉበት አቅም ያለው ኮምፒውተር/ጂፒዩ (GPU) ለሌላችሁ፣ እንዲሁም ለዲፕሎይመንት (Deployment) ለተቸገራችሁ ወጣቶች... ይሄ እድል ፈፅሞ ሊያመልጣችሁ አይገባም! 🎯 የትኞቹ ዘርፎች ላይ መሳተፍ ይቻላል? በግብርና፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በሮቦቲክስ፣ በኤ.አይ ኤጀንት (AI Agent)፣ እንዲሁም በቨርችዋል እና ኦግመንትድ ሪያሊቲ (VR/AR) ዘርፎች ላይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ ሁሉ መሳተፍ ትችላላችሁ። ⏰ የምዝገባ ጊዜ፡- ከሚያዚያ 15፣ 2018 እስከ ግንቦት 06፣ 2018 ብቻ! (ቀኑ እየሄደ ነው ቶሎ በሉ) 🔗 ለማመልከት፡- ይህን ድረ-ገፅ ይጠቀሙ ▶️ aistartup.aii.et የፈጠራ ሃሳብዎን ወደ ተጨባጭ ምርት፣ ህልምዎን ወደ እውነታ የሚቀይሩበት ጊዜ አሁን ነው። በድጋሚ እላለሁ ነቃ በሉ፣ አታንቀላፉ! ለሌሎች ጓደኞቻችሁም እንዲደርሳቸው ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ! || https://t.me/STEMwithMurad

ለተማሪዎች ምርጥ PDF ማንበቢያ App FLEX PDF READER - Group PDF files together - Table of contents - Merge multiple PDFs - Split PDF - A
+2
ለተማሪዎች ምርጥ PDF ማንበቢያ App FLEX PDF READER - Group PDF files together - Table of contents - Merge multiple PDFs - Split PDF - Add watermark - Images to PDF - PDF to Image - Lock PDF - Unlock PDF - Create Bookmarks - Search PDFs - Dark and light mode Install 👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.smartpdf.reader