en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል

Open in Telegram

​💻 Tech & AI Hub | የቴክ እና AI ማዕከል ​በቻናላችን የሚለቀቁ ዋና ዋና ይዘቶች፦ 🚀 Programming & Software 🖥️ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀቶች 🤖 የ-AI ክህሎቶች እና የ Prompt Tips 🎓 ነፃ ቴክኖሎጂ ነክ የትምህርት ዕድሎች 💡 ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችና ጠቃሚ ጥቆማዎች Tiktok: tiktok.com/@techaihub2

Show more
1 829
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-1630 days
Posts Archive
የንግድ ባንክ አፕሊኬሽን ለመክፈት ስትሞክሩ እንደዚህ "Suspicious Accessibility Service" እያለ አልከፍት ካላችሁ ለማስተካከል ⚫Settings ውስጥ ግቡና Accessibility የ
የንግድ ባንክ አፕሊኬሽን ለመክፈት ስትሞክሩ እንደዚህ "Suspicious Accessibility Service" እያለ አልከፍት ካላችሁ ለማስተካከል ⚫Settings ውስጥ ግቡና Accessibility የሚለውን ምረጡ። ⚫Installed Apps ውስጥ ስትገቡ ከተዘረዘሩት አፕሊኬሽኖች ውስጥ On የሆነ ካለ Off አድርጋችሁ ውጡ። የከፈታችሁትን CBE አፕሊኬሽን ዘግታችሁ እንደገና ስትከፍቱት ይሰራላችኋል። @bighabesha_softwares

OpenAI launches new GPT-5.6 models. ከአሜሪካ መንግስት ጋር ለ12 ቀናት በደህንነት ፍተሻ ዙሪያ በነበረው ውይይት ምክንያት ውስን ለሆኑ ተቋማት ብቻ ተለቆ የነበረው GPT-5.6 አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ተፈቅዶ ለአለም አቀፍ ተጠቃሚዎች ይፋ ሆኗል። ይህ አዲሱ ሞዴል በሶስት የተለያዩ ስሪቶች (Variants) የቀረበ ሲሆን እያንዳንዳቸው ለተለያዩ የስራ አይነቶችና የክፍያ መጠን አላቸው። 1️⃣ GPT-5.6 SOL - የOpenAI ዋናውና ትልቁ Flagship ሞደል ሲሆን በተለይ ራሳቸውን ችለው ለሚሰሩ የኮዲንግ ስራዎች (Agentic Coding)፣ በCybersecurityና በባዮሎጂ ምርምሮች ላይ ከፍተኛ አቅም አለው ተብሏል። ከዋና ተፎካካሪው Claude Fable 5 የላቀ ውጤት ያሳየ ቢሆንም በ3 እጥፍ ያነሰ ዋጋ የሚጠይቅና እጅግ ፈጣን ነው። 2️⃣GPT-5.6 Terra - ለዕለታዊ የቢሮና የፈጠራ ስራዎች የተሰራ ሲሆን የቀድሞው የGPT-5.5ን ያህል ጠንካራ አቅም አለው ነገር ግን ዋጋው በግማሽ የቀነሰ እና ወጪ ቆጣቢ ነው። 3️⃣GPT-5.6 Luna - Budget-friendly ሞዴል ሲሆን በጣም ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ እና በዋጋ ደረጃ እጅግ በጣም ርካሹ model ነው። ✨  Main Features በኮዲንግ ስራዎች ላይ የቶከን አጠቃቀም ቅልጥፍናን በ54% ያሻሻለ ሲሆን፣ ድርጅቶች ለሶፍትዌር ማበልጸጊያ የሚያወጡትን ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። ከተለያዩ ሰነዶች እንዲሁም እንደ Slack, Notion, Microsoft 365 እና Google Drive ካሉ አፕሊኬሽኖች ላይ መረጃዎችን በመውሰድ በራሱ ጊዜ ሙሉ የPowerPoint Presentation፣ ፋይናንሻል ሞዴሎችን እና የኤክሴል ስፕሬድሺቶችን ያዘጋጃል። ቀደም ሲል ከነበሩት ሞዴሎች በ10 እጥፍ በበለጠ ሁኔታ አደገኛ እና ጎጂ የሆኑ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅም አለው። ይህንን ሞዴል አሁን ላይ በChatGPT፣ በOpenAI APIና በCodex ላይ መጠቀም ይችላላል። ©️

OpenAI launches new GPT-5.6 models. ከአሜሪካ መንግስት ጋር ለ12 ቀናት በደህንነት ፍተሻ ዙሪያ በነበረው ውይይት ምክንያት ውስን ለሆኑ ተቋማት ብቻ ተለቆ የነበረው GPT-5.6
OpenAI launches new GPT-5.6 models. ከአሜሪካ መንግስት ጋር ለ12 ቀናት በደህንነት ፍተሻ ዙሪያ በነበረው ውይይት ምክንያት ውስን ለሆኑ ተቋማት ብቻ ተለቆ የነበረው GPT-5.6 አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ተፈቅዶ ለአለም አቀፍ ተጠቃሚዎች ይፋ ሆኗል። ይህ አዲሱ ሞዴል በሶስት የተለያዩ ስሪቶች (Variants) የቀረበ ሲሆን እያንዳንዳቸው ለተለያዩ የስራ አይነቶችና የክፍያ መጠን አላቸው። 1️⃣ GPT-5.6 SOL - የOpenAI ዋናውና ትልቁ Flagship ሞደል ሲሆን በተለይ ራሳቸውን ችለው ለሚሰሩ የኮዲንግ ስራዎች (Agentic Coding)፣ በCybersecurityና በባዮሎጂ ምርምሮች ላይ ከፍተኛ አቅም አለው ተብሏል። ከዋና ተፎካካሪው Claude Fable 5 የላቀ ውጤት ያሳየ ቢሆንም በ3 እጥፍ ያነሰ ዋጋ የሚጠይቅና እጅግ ፈጣን ነው። 2️⃣GPT-5.6 Terra - ለዕለታዊ የቢሮና የፈጠራ ስራዎች የተሰራ ሲሆን የቀድሞው የGPT-5.5ን ያህል ጠንካራ አቅም አለው ነገር ግን ዋጋው በግማሽ የቀነሰ እና ወጪ ቆጣቢ ነው። 3️⃣GPT-5.6 Luna - Budget-friendly ሞዴል ሲሆን በጣም ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ እና በዋጋ ደረጃ እጅግ በጣም ርካሹ model ነው። ✨ Main Features በኮዲንግ ስራዎች ላይ የቶከን አጠቃቀም ቅልጥፍናን በ54% ያሻሻለ ሲሆን፣ ድርጅቶች ለሶፍትዌር ማበልጸጊያ የሚያወጡትን ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። ከተለያዩ ሰነዶች እንዲሁም እንደ Slack, Notion, Microsoft 365 እና Google Drive ካሉ አፕሊኬሽኖች ላይ መረጃዎችን በመውሰድ በራሱ ጊዜ ሙሉ የPowerPoint Presentation፣ ፋይናንሻል ሞዴሎችን እና የኤክሴል ስፕሬድሺቶችን ያዘጋጃል። ቀደም ሲል ከነበሩት ሞዴሎች በ10 እጥፍ በበለጠ ሁኔታ አደገኛ እና ጎጂ የሆኑ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅም አለው። ይህንን ሞዴል አሁን ላይ በChatGPT፣ በOpenAI APIና በCodex ላይ መጠቀም ይችላላል። @bighabesha_softwares

OpenAI አዲስ advanced የሆነ Voice model አስተዋወቀ። GPT-Live የተሰኘው ይህ Voice model ከሮቦት ጋር ሳይሆን ልክ ከእውነተኛ ሰው ጋር እንደማውራት ያለ advanced ex
OpenAI አዲስ advanced የሆነ Voice model አስተዋወቀ። GPT-Live የተሰኘው ይህ Voice model ከሮቦት ጋር ሳይሆን ልክ ከእውነተኛ ሰው ጋር እንደማውራት ያለ advanced experience እንዳለው ተነግሯል። ⚫በአንድ ጊዜ መስማትና መናገር (Full-Duplex): ከዚህ በፊት እንደነበረው ንግግሩን ከሰማ በኋላ ጊዜ ወስዶ የሚመልስ ሳይሆን በተመሳሳይ ጊዜ እየሰማ እያሰበ መናገር ይችላል። ልክ እንደ እውነተኛ ሰው "እሺ"፣ "አሃ" እያለ ትኩረት እየሰጠ እንደሆነ ያሳያል። ሀሳባችሁን ለመሰብሰብ ዝምታ ሲያስፈልጋችሁም በትዕግስት ይጠብቃል። ⚫የበለጠ ብልህ እና ፈጣን ነው: ጥልቅ ምርምር፣ search ማድረግ ወይም ከበድ ያሉ ስሌቶችን የሚጠይቁ ጥያቄዎችን ሲጠየቅ GPT-5.5 ሞዴልን በመጠቀም ፈጣን ምላሽ ይሰጣል። ⚫አይቋረጥም: ከበስተጀርባ መልሶችን እስከሚያዘጋጅ ድረስ ንግግሩን ሳያቋርጥ ከእናንተ ጋር ማውራቱን ይቀጥላል። ይህ ቴክኖሎጂ በሂደት ይበልጥ ውስብስብ፣ ረጅምና ራሳቸውን ችለው ለሚሰሩ Agentic ስራዎች በድምፅ ትዕዛዝ ለመስጠት የሚያስችል አቅም ይፈጥራል። አሁን ላይ GPT-Live-1 እና GPT-Live-1 mini የተባሉ ሁለት ሞዴሎች በአለም አቀፍ ደረጃ ለChatGPT ተጠቃሚዎች መለቀቅ ጀምረዋል። @bighabesha_softwares

​🌟 የኩራትና የብስራት ዜና ከሙምታዝ አካዳሚ! 🌟 ​የሙምታዝ ድምፅ እንደገና በክብር አስተጋባ! በዕውቀት፣ በስነ-ምግባርና በትጋት ኮትኩተን ያሳደግናቸው ውድ አበቦቻችን በከተማ አቀፉ የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አዲስ የድል ምዕራፍ ከፍተዋል! ​የሙምታዝ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኝ አበቦች፣ አንፀባራቂ ኮከቦች ሁሉም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ወደ 7ኛ ክፍል አልፈዋል! አንድም ተማሪ ሳይቀረው ሙሉ በሙሉ (100%) የማለፋቸው ታላቅ የምሥራች የትምህርት ቤታችንን የላቀ የትጋት ደረጃ በግልጽ ያሳያል። ​ይህ አስደናቂ ውጤት የልጆቻችን የሌሊት እቅድና የቀን ጥረት፣ የወላጆች ያላሰለሰ ክትትልና ዱዓ፣ እንዲሁም የመምህራኖቻችን ያልተቆጠበ ፍቅርና ድካም ፍሬ ነው። ​💎 የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ለተፈተናችሁ አበቦች በሙሉ፦ ​በየትኛውም ትምህርት ቤት ሆናችሁ ዘንድሮ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናን ወስዳችሁ የጥረታችሁን ፍሬ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ውድ ተማሪዎች በሙሉ፤ አላህ ልፋታችሁን ባርኮላችሁ፣ ልባችሁን በሐሴት የሚሞላና ቤተሰቦቻችሁን የሚያኮራ እጅግ ማራኪ ውጤት እንደምታመጡ ትልቅ ተስፋ አለን። ​ለትጋታችሁና በቅርቡ ለምታስመዘግቡት ብሩህ ስኬት ከወዲሁ እንኳን ደስ አላችሁ! ወደ 7ኛ ክፍል የምታደርጉት አዲሱ ጉዞም የላቀ የዕውቀት ብርሃን የሚበራበት፣ የላቀ ራዕይ የምትሰንቁበት ይሁን!
​✨ ጥረት ካለ ስኬት አይርቅም፤ ትጋት ካለ ድል አይታጣም!! ​ስኬት ለልጆቻችን፣ ለአበቦቻችን፣ ለአንፀባራቂ ኮከቦቻችን! ለመላው የሙምታዝ አካዳሚ ማህበረሰብ፣ ለወላጆችና ለድርጅቱ አመራሮች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን!
​🤲 ዱዓ ​አላህ ሆይ! እነዚህን ብሩህ አእምሮዎች፣ የወደፊት ተስፋዎቻችንን ከመጥፎ ነገር ሁሉ ጠብቅልን። የወላጆቻቸው አይን ማረፊያ፣ የሀገርና የኡማው ኩራትና አለኝታ አድርጋቸው። ​አላህ ሆይ! ዕውቀታቸውንና ጥበባቸውን ጨምርላቸው፤ በቀጣዩ የ7ኛ ክፍል የትምህርት ጉዟቸውና በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ከዚህ የላቀ፣ ይበልጥ የገዘፈ ስኬትና ድልን አጎናጽፋቸው። በሄዱበት መስክ ሁሉ ሁልጊዜም ቀዳሚ፣ አንፀባራቂና መሪ ኮከቦች ያድርጋቸው! ​አሚን ያ ረበል ዓለሚን! 🤲✨ ​✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

🌟 የኩራትና የብስራት ዜና ከሙምታዝ አካዳሚ! 🌟 ​የሙምታዝ ድምፅ እንደገና በክብር አስተጋባ! በዕውቀት፣ በስነ-ምግባርና በትጋት ኮትኩተን ያሳደግናቸው ውድ አበቦቻችን በከተማ አቀፉ የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አዲስ የድል ምዕራፍ ከፍተዋል! ​የሙምታዝ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኝ አበቦች፣ አንፀባራቂ ኮከቦች ሁሉም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ወደ 7ኛ ክፍል አልፈዋል! አንድም ተማሪ ሳይቀረው ሙሉ በሙሉ (100%) የማለፋቸው ታላቅ የምሥራች የትምህርት ቤታችንን የላቀ የትጋት ደረጃ በግልጽ ያሳያል። ​ይህ አስደናቂ ውጤት የልጆቻችን የሌሊት እቅድና የቀን ጥረት፣ የወላጆች ያላሰለሰ ክትትልና ዱዓ፣ እንዲሁም የመምህራኖቻችን ያልተቆጠበ ፍቅርና ድካም ፍሬ ነው።
​✨ ጥረት ካለ ስኬት አይርቅም፤ ትጋት ካለ ድል አይታጣም!! ​ስኬት ለልጆቻችን፣ ለአበቦቻችን፣ ለአንፀባራቂ ኮከቦቻችን! ለመላው የሙምታዝ አካዳሚ ማህበረሰብ፣ ለወላጆችና ለድርጅቱ አመራሮች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን!
​🤲 ዱዓ ​አላህ ሆይ! እነዚህን ብሩህ አእምሮዎች፣ የወደፊት ተስፋዎቻችንን ከመጥፎ ነገር ሁሉ ጠብቅልን። የወላጆቻቸው አይን ማረፊያ፣ የሀገርና የኡማው ኩራትና አለኝታ አድርጋቸው። ​አላህ ሆይ! ዕውቀታቸውንና ጥበባቸውን ጨምርላቸው፤ በቀጣዩ የ7ኛ ክፍል የትምህርት ጉዟቸውና በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ከዚህ የላቀ፣ ይበልጥ የገዘፈ ስኬትና ድልን አጎናጽፋቸው። በሄዱበት መስክ ሁሉ ሁልጊዜም ቀዳሚ፣ አንፀባራቂና መሪ ኮከቦች ያድርጋቸው! ​አሚን ያ ረበል ዓለሚን! 🤲✨ ​✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ውጤት ተለቋል.... የክፍለ  ከተማችን የ6ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከላይ የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ በጋዜጣዊ መግለጫው ተጠቁሟል።

🔹ውጤት ሲለቀቅ ...
የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ  ፈተና ውጤት ይፋ ሲሆን ለመመልከት ከታች የሚገኘውን ሊንክ መጠቀም ይችላሉ።
👉 https://aa6.ministry.et/#/result

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ጠዋት ይፋ ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ጠዋት ይፋ ይሆናል፡፡

ሌላ ጥቆማ‼ ========= (የክረምት የቴክ ኮርስ ምዝገባ ላመለጠችሁ የመጨረሻ ዕድል!) || ✍️ ባለፈው ሚዛን MiT የክረምት ስልጠና አስመልክቶ ጥቆማ ሰጥቻችሁ ነበር። መደበኛ የምዝገባ ጊዜያቸው
+1
ሌላ ጥቆማ‼ ========= (የክረምት የቴክ ኮርስ ምዝገባ ላመለጠችሁ የመጨረሻ ዕድል!) || ✍️ ባለፈው ሚዛን MiT የክረምት ስልጠና አስመልክቶ ጥቆማ ሰጥቻችሁ ነበር። መደበኛ የምዝገባ ጊዜያቸውን ቢያጠናቅቁም፣ ባለው ከፍተኛ ፍላጎት ምክንያት የቅበላ አቅማቸውን አሳድገው ተጨማሪ ውስን ኮታዎችን ሰጥተዋል! ግን ... ይህ የተጨማሪ ዕድል ምዝገባ የሚያበቃው ነገ ቅዳሜ ነው! የቀሩት ቦታዎች እጅግ በጣም ውስን ስለሆኑ፣ ነገን ራሱ ሳትጠብቁ ይህን ጽሁፍ እንዳነበባችሁ አሁኑኑ እንድትመዘገቡ እመክራለሁ። 🎁 ልዩ የቅናሽ ዕድል (እንዳያመልጣችሁ)፦ ተቋሙ ለመምህራን (እስከ 22%) እና ለጤና ባለሙያዎች (እስከ 30%) ያደረገው ልዩ ቅናሽ አለ! የመምህራኑ የቅናሽ ዕድል ዛሬ ያበቃል እንዳነበብኩት ከሆነ፣ የጤና ባለሙያዎቹ ደግሞ ነገ ያልቃል። ኮታው ካላለቀ ፈጥናችሁ ተጠቀሙበት! ☑ በአካል ለምትማሩ የቀሩት ክፍት ቦታዎች ዝርዝር ውስን ነው። በኦንላይን መማር ለምትፈልጉ ግን በሁሉም ኮርሶች ያልተገደበ ክፍት ቦታ አላቸው። ⏰ አራት የመማሪያ አማራጭ አላቸው፦   - መደበኛ (Regular): ጠዋት (3፡00-5፡00) ወይም ከሰዓት (7፡30-9፡30)   - ማታ (Extension): ከቀኑ 11፡00 - 1፡00   - ቅዳሜና እሁድ (Weekend): ግማሽ ቀን (ጠዋት 3:00–6:00 ወይም ከሰአት 7:30–10:30) - Online አላቸው።   ስልጠናቸው የሚጀመረው: ሰኞ (ሰኔ 29) ነው። 📌 አንዳንድ ፈረቃዎች ቶሎ ስለሚሞሉ፣ ከመመዝገባችሁ በፊት በቴሌግራማቸው ክፍት ቦታ መኖሩን ማጣራት አትርሱ! 🔗 ለምትፈልጉ መመዝገቢያ ይህን ሊንክ ተጠቀሙ: www.mizantechinstitute.com/admissions 📞 ለማንኛውም ጥያቄ (MiTን ለማግኘት)፦   - ስልካቸው: 0987143030   - በቴሌግራም: @MizanInstituteOfTechnologyEthio   - አድራሻቸው: ቤቴል፣ አፕል ፕላዛ፣ 7ኛ ፎቅ … ጊዜው የቴክኖሎጂ ነው። ይህን ዕድል ተጠቀሙበት። ከገባችሁ በኋላ ግን ዝልፍልፍ አትሁኑ፤ ቆፍጠን ብላችሁ ተማሩ፣ ተለማመዱ፣ ያስመዘገባችኋቸውን ልጆች ተከታተሉ፣ ተቆጣጠሩ፣ በዚህ የኑሮ ውድነት ዝም ብሎ ገንዘብ ማባከን ብቻ አይጠቅምም! ይጠቅማቸዋል ለምትሏቸው ሼር አድርጉላቸው። || t.me/STEMwithMurad

📢 ልዩ ጥቆማ‼ ============ ✍️ ዛሬ አንድ ምርጥ የቴክኖሎጂ ተቋም ላካፍላችሁ/ልጠቁማችሁ። ሸገር የቴክኖሎጂ ተቋም (Shaggar Institute of Technology - SIT) ለ 2026
📢 ልዩ ጥቆማ‼ ============ ✍️ ዛሬ አንድ ምርጥ የቴክኖሎጂ ተቋም ላካፍላችሁ/ልጠቁማችሁ። ሸገር የቴክኖሎጂ ተቋም (Shaggar Institute of Technology - SIT) ለ 2026 የትምህርት ዘመን አዲስ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል። እውነት ለመናገር በጣም አሪፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ነው!ትምህርቱን የሚሰጡት ሙሉ በሙሉ በውጭ ሃገር ስታንዳርድ ሲሆን፣ አሪፍ አሪፍ ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮች ያሉበት ነው። ከዚህም አልፎ አንዳንዶቹ አስተማሪዎች በቀጥታ ከውጭ ሃገር ሆነው ነው የሚያስተምሩት። ይህን ዕድል አያምልጣችሁ፤ በቃ ተማሩ ብያለሁ ተማሩ! ስጠቁማችሁ ሳታንገራግሩ መስፈርቱን አሟልታችሁ መግባት ብቻ ነው አማራጫችሁ¡ 📅 • ምዝገባው የተጀመረው፦ June 25, 2026 • ምዝገባው የሚጠናቀቀው፦ August 1, 2026 • የመግቢያ ፈተና እና ኢንተርቪው የሚሰጥበት ቀን ወደፊት ይገለፃል። 📋 ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች: 🔹 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አማካይ ውጤት (Average) 90% እና ከዚያ በላይ 🔹 በኢትዮጵያ ብሄራዊ ፈተና (EHEEE) እጅግ ከፍተኛ ውጤት ያመጣ (95th percentile) 🔹 የ SIT ተቋምን የመግቢያ ፈተና ማለፍ 🔹 ከ500–750 ቃላት ርዝመት ያለው እና ለሳይንስ/ቴክኖሎጂ ያላችሁን ፍላጎት የሚያሳይ ማህበረሰባዊ አስተዋፅኦ የሚገልፅ አጭር ፅሁፍ (Essay) 🔹 ከአስተማሪ ወይም አማካሪ የተፃፈ 1 የድጋፍ ደብዳቤ (Recommendation letter) 🔹 ከዚህ በፊት የሰራችሁት ፕሮጀክት ካለ (Portfolio) ማቅረብ ይበረታታል (ግዴታ አይደለም) ማስታወሻ: ልዩ ተሰጥኦ (Gifted) ላላቸው ተማሪዎች የተለየ የመግቢያ ዕድል (Special track) ተመቻችቷል! 📝 እንዴት መመዝገብ ይቻላል? ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ፕሮፋይላችሁን አስተካክሉ፤ አስፈላጊ ዶክመንቶችን Upload አድርጉ። ፈተና እና ሌሎች መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ በምዝገባው ሂደት ላይ የቴሌግራም አካውንታችሁን ከፖርታሉ ጋር Link ማድረግ አትዘንጉ! 👉 አሁኑኑ ለመመዝገብ: https://sitedu.info/admission/application/register ይህን ወርቃማ ዕድል ተጠቀሙበት! መረጃውን ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ሼር በማድረግ አድርሷቸው! || t.me/STEMwithMurad

የአዲስአበባ የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ውጤት ተለቋል 💻ውጤት ለማየት https://aa.ministry.et/#/result ይጠቀሙ

Repost from Riseup Tech
💥💥አልተመዘገባችሁም❔💥💥 👑  አትዘግይ! የለውጡ አካል ሁን✅ 😀 ገደብ የለሽ ትምህርት ከ RiseUpTech Solution ✅ ➡️አለም በየሰከንዱ እየተለወጠ ነው! እርስዎ የዚህ ለውጥ አካል ነዎት ወይስ ተመልካች? ➡️ርቀት⁉️ ዕድሜ⁉️ ሳይገድብዎ✔️ ቤትዎ የትም ይሁን፣ የትም ሀገር ይኑሩ፣ ስራዎ ምን ይሁን! ከእኛ ጋር የአለምን የቴክኖሎጂ እውቀት የትም ቦታ ሆነው ያግኙና በዓለም ዙሪያ የሚፈለጉ ባለሙያ ይሁኑ። ➡️በOnline🌐፣ በአካል😮፣ በቀን😮 እና በማታ😮፣ እንዲሁም ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለእርስዎ በሚመች መርሐግብር ተዘጋጅቷል።😮 ➡️ለምቾትዎ ሁሌም ቅድሚያ የሚሰጠው ተቋማችን! ለሴቶች ሴት፣ ለወንዶች ወንድ አስተማሪዎች አዘጋጅተናል። ➡️💻 የምንሰጣቸው ድንቅ ስልጠናዎች (Coding & ቋንቋ) ✅ Fullstack (MERN) Development  ✅ Python Programming ✅ Mobile App Development ✅ Basic Computer Skill ✅ English Language ✅ Arabic Language ➡️ስለትምህርቱ ይበልጥ ለመረዳት ይህን😀 https://t.me/riseuptech/113 ይጎብኙ! 🚨ትላንት ታሪክ ነው🕹ነገ ደግሞ ህልም🎁 ያለን ዛሬ ነው እና ዛሬውኑ ይወስኑ😀 📞 አሁኑኑ ይመዝገቡ! ቦታዎች ከመሞላታቸው በፊት ፈጥነው ቦታ ይያዙ✅ በዌብሳይት🌐 https://riseuptechsolution.com/form.php ስልክ 😀 +251907667777      +251923565957 ቴሌግራም ✈️ @riseuptechsolution ቻናል✈️⬇️⬇️⬇️ https://t.me/riseuptech https://t.me/riseuptech 😀 በአካል: ቤቴል ከአደባባይ ወደ ዌራ ወረድ ብሎ፣ ዳሽን ባንክ አጠገብ ያለው ቴምር ሕንፃ 3ኛ ፎቅ።

✅ የMS-Word ሙሉ ክህሎት በተግባር የተደገፈ ቪድዮ ይሀውና!! 📧 MS-Word ሙሉ ትምህርት በቪድዮ 📧 የሰዓት ቆይታ: 1:46 ደቂቃ (አንድ ሰዓት ከ46 ደቂቃ) 📧 የMB መጠን: 265MB አዘጋጅ እና ድምፅ: ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ════════════════ 📧 ታላቁ ሰሀባ አቡ ደርዳእ እንዲህ ይላል፦ 📧 "እኔ አኺራ ላይ የሚያስፈራኝ ነገር ቢኖር ባወቅከው ምን ሰራህበት መባሌ ነው"!! ════════════════ ⭕️ ቪድዮውን አይታችሁ ስትጨርሱ አስተያየት: ..........................! 📧 📧 ════════════════ ለመምህራን የተሰጠ ስልጠና፤ እናንተም ተጠቀሙበት!! ✍️ Basic Computer Skills 🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻 Telegram: t.me/BasicComputer_Skills tiktok.com/@basiccomputerskills

ቴክኖሎጅ:- 📱 Xenderን ለፋይል ማስተላለፊያ ብቻ የሚጠቀሙ ከሆነ እነዚህን 4 ድብቅ ጥቅሞች አምልጠውዎታል! ብዙዎቻችን Xenderን የምናውቀው ፎቶ እና ቪዲዮ ከስልክ ስልክ ለመላላክ ብቻ ነው። ነገር ግን ይህ መተግበሪያ ህይወታችንን የሚያቀሉ ሌሎች አስገራሚ ጥቅሞችን በአንድ ላይ ይዟል። መተግበሪያው ውስጥ ተደብቀው የሚገኙትን 4 ዋና ዋና ጥቅሞች እነሆ👇 1️⃣ ቪዲዮን ወደ MP3 (ኦዲዮ) መቀየር ጥቅሙ፡ የቪዲዮ ሙዚቃዎችን ወይም ንግግሮችን ወደ ኦዲዮ (Audio) ለመቀየር ሌላ ተጨማሪ መተግበሪያ መጫን አያስፈልግዎትም። አጠቃቀም፡ Xender ውስጥ ገብተው ከታች "ToMP3" የሚለውን ይጫኑ ➡️ "Select Video" የሚለውን በመንካት ቪዲዮዎን ይምረጡ። በሰከንዶች ውስጥ ወደ MP3 ይቀየርልዎታል። 2️⃣ የማህበራዊ ሚዲያ ቪዲዮዎችን ማውረጃ (Downloader) ጥቅሙ፡ ከፌስቡክ፣ ከኢንስታግራም ወይም ከቲክቶክ ቪዲዮዎችን በቀላሉ ማውረድ ይችላሉ። አጠቃቀም፡ Xender ውስጥ ከታች "Social" የሚለውን ይጫኑ ➡️ ማውረድ የሚፈልጉትን የቪዲዮ ሊንክ (Link) ኮፒ አድርገው እዚህ ላይ ይለጥፉ (Paste ያድርጉ) ➡️ "Download" የሚለውን ይንኩ። 3️⃣ ያለ ኬብል ስልክን ከኮምፒውተር ጋር ማገናኘት ጥቅሙ፡ ምንም አይነት የዩኤስቢ (USB) ኬብል ሳይጠቀሙ ፋይሎችን ከስልክ ወደ ላፕቶፕ/ኮምፒውተር በፍጥነት መጫን ያስችላል። አጠቃቀም፡ Xender ላይ በቀኝ በኩል ያለውን ምልክት ነክተው "Connect to PC" ይምረጡ ➡️ የስልክዎን Hotspot አብርተው ኮምፒውተርዎን ያገናኙ ➡️ ኮምፒውተርዎ ብሮውዘር (Browser) ላይ ስልኩ ያሳየዎትን የድር አድራሻ (IP Address) ይተይቡ። 4️⃣ አዲስ ስልክ ሲገዙ ዳታ ማዛወሪያ (Phone Clone) ጥቅሙ፡ አዲስ ስልክ ሲቀይሩ በድሮ ስልክዎ ላይ ያሉትን ስሞች (Contacts)፣ ፎቶዎች እና መተግበሪያዎች በአንድ ጊዜ ወደ አዲሱ ስልክ ያዛውራል። አጠቃቀም፡ በሁለቱም ስልኮች Xender ላይ "Phone Clone" የሚለውን ይምረጡ ➡️ አንዱን "Old" ሌላኛውን "New" በማድረግ ያገናኙ እና ሁሉንም መረጃዎች በቀላሉ ያዛውሩ።

ወላጅ እናቱን የሚኒስትሪ ፈተናው ቀን በሞት ያጣው ተማሪ ኻሊድ የባንክ አካውንት ይፋ ሆኗል። ተማሪ ኻሊድን መርዳት የምትፈልጉ የሲንቄ ባንክ እና የአዋሽ ባንክ አካውንት ተከፍቷል። ተማሪ ኻሊድ እድሜ
ወላጅ እናቱን የሚኒስትሪ ፈተናው ቀን በሞት ያጣው ተማሪ ኻሊድ የባንክ አካውንት ይፋ ሆኗል። ተማሪ ኻሊድን መርዳት የምትፈልጉ የሲንቄ ባንክ እና የአዋሽ ባንክ አካውንት ተከፍቷል። ተማሪ ኻሊድ እድሜው 18 ስላልሞላውና ዘመድም ስለሌለው፤ ብቻውን ገንዘብ አውጥቶ መጠቀም ስለማይችል፣ አካውንቱ በአካባቢው መስጅድ ኡስታዝ፣ ከሀገር ሽማግሌ እና ከራሱ ጋር በጋራ በመሆን አካውንት ተከፍቶለታል። ①) ስንቄ ባንክ 11 14385901915 ②) አዋሽ ባንክ 013201115433100

የድል ብስራት! የስኬት ማማ! 🏆 ​📖 «...ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨምርልኝ በል፡፡» (ሱረቱ ጣሃ: 114) ​አልሃምዱሊላህ! የቻናላችን ቤተሰቦች ሆይ፣ ዛሬ ሰኔ 12/2018 ዓ.ል የሀገራችን የዓይን ብርሃን የሆኑት የ8ኛ ክፍል አበቦቻችን፣ የሀገር ድምቀቶች እና አንፀባራቂ ኮከቦቻችን የከተማ አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተናቸውን በላቀ የዲሲፕሊን መንፈስ እና በታላቅ ስኬት አጠናቀዋል። ​ውድ ልጆቻችን! የለፉበት የጥናት ምሽቶች፣ የደከሙበት የመማሪያ ክፍሎች ውጤት ዛሬ በፈገግታችሁ መታተሙ ያስደስተናል። እናንተ የነገዋ ሀገር ተስፋ፣ የቤተሰባችሁ የኩራት ምንጭ ናችሁ። ይህ ጉዞ ለትልልቅ ስኬቶች መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም። ገና ብዙ የስኬት ማማዎችን ትረግጣላችሁ፤ የላቀ ታሪክም ትሰራላችሁ! 🚀 ​ለወላጆች፣ መምህራን፣ የትምህርት ቤት አስተዳደርና ለመላው ማህበረሰብ፦ ለዚህ ክብር ያበቃችሁ፣ ሌት ተቀን የደከማችሁ፣ በሀሳብ፣ በምክርና በዱዓ ከልጆቻችሁ ጎን የቆማችሁ ሁሉ፤ አላህ ውለታችሁን በጀነት ይክፈለው። የአንድ ልጅ ስኬት የመላው ማህበረሰብ ድልና ኩራት ነው። ✨ ​🤲 ዱዓችን፦ ሁሉም እጁን አንስቶ አሚን ይበል! ​🔷 ያ አላህ! ያጠናቀቁትን ፈተና ለልጆቻችን የላቀ ውጤት እና የደስታ ማብሰሪያ አድርግላቸው፤ ድካማቸውን ከንቱ አታድርግባቸው። ​🔷 ያ ረብ! ለእነዚህ የሀገር ድምቀቶች በምድራዊ ሕይወታቸው ጠቃሚ ዕውቀትን፣ በወዲያኛው ዓለም ደግሞ መዳንንና ስኬትን ለግሳቸው። ​🔷 ያ አላህ! ለልጆቻቸው ስኬት ደፋ ቀና ለሚሉ ወላጆች፣ ዕውቀታቸውን ለሚለግሱ መምህራንና ለአስተዳደር አካላት በሙሉ ኸይር ጀዛቸውን አብዝተህ ክፈላቸው፤ ማህበረሰባችንንም በዕውቀትና በሰላም ገንባው። ​🔷 ያ አላህ! አሁን ላይ የማጠቃለያ ፈተና (Final Exam) መፈተን ለጀመሩ፣ ለቀጣይ የትምህርት ምዕራፍ ሌት ተቀን ለሚተጉ አበቦቻችንና አንፀባራቂ ኮከቦቻችን ሁሉ አእምሯቸውን አብራልን፣ የረሱትን አሳስባቸው፣ የፈሩትን አስወግድላቸው። በዕውቀት አሳድጋቸው፣ በስኬት አስውባቸው፣ በውጤት አበሽብሻቸው! ​አሚን ያ ረበል ዓለሚን! 🤲 ​📚 የዕውቀት ጎዳና፤ ዘወትር የተባረከ ነው! ​✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ውድ ተማሪዎች እንዲሁም መላው የቻናላችን ቤተሰቦች ​ሰላም፣ ጤና እና የአላህ እዝነት በእናንተ ላይ ይሁን፤ ​አልሃምዱሊላህ! የሀገር ተስፋዎች፣ የ6ኛ ክፍል አበቦቻችን እና አንፀባራቂ ኮከቦቻችን ከተ
ውድ ተማሪዎች እንዲሁም መላው የቻናላችን ቤተሰቦች ​ሰላም፣ ጤና እና የአላህ እዝነት በእናንተ ላይ ይሁን፤ ​አልሃምዱሊላህ! የሀገር ተስፋዎች፣ የ6ኛ ክፍል አበቦቻችን እና አንፀባራቂ ኮከቦቻችን ከተማ አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተናቸውን ዛሬ በሰላም፣ በስኬት እና በታላቅ የዲሲፕሊን መንፈስ አጠናቀዋል። ​ልጆቻችን ይህንን ምዕራፍ በልበ ሙሉነት እንዲሻገሩ በሃሳብ፣ በምክርና በዱዓ ከጎናቸው ለነበራችሁ ውድ ወላጆች እና መላው ማህበረሰብ አላህ ኸይር ጀዛችሁን አብዝቶ ይክፈላችሁ። 🤲 ​ቀጣዩ የተስፋ ምዕራፍ፦ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ​ነገ ሐሙስ፣ ሰኔ 11/2018 ዓ.ል ደግሞ ሌላኞቹ የቤታችን ድምቀቶች፣ የ8ኛ ክፍል አበቦች እና አንፀባራቂ ኮከቦቻችን የከተማ አቀፍ ሚኒስትሪ ፈተናቸውን በይፋ ይጀምራሉ። እነዚህ ልጆቻችን የደከሙበትን የጥናት ፍሬ የሚያዩበት፣ የተመኙትን የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡበት እንዲሆን ሁላችንም በዱዓ እና በቅን ምኞት ከጎናቸው እንቁም! ​🤲 ለተማሪዎቻችን ዱዓ ​ያ አላህ! ነገ ፈተና ለሚጀምሩት የ8ኛ ክፍል ልጆቻችን አእምሯቸውን አብርቶላቸው፣ ያጠኑትን አሳስባቸው፤ የፈሩትን አስወግደህ ልባቸውን በሰኪና (በረጋ መንፈስ) ሙላው። ብዕሮቻቸውን ቀጥ አድርግላቸው፣ ፈተናውን አግራልላቸው፤ የድካማቸውን አምረውና ደምቀው እንዲያዩ፣ የወላጆቻቸውም የኩራት ምንጭ እንዲሆኑ መልካም ውጤትን ለግሳቸው። ​ያ ረብ! ዛሬ ፈተናቸውን በሰላም ያጠናቀቁትን የ6ኛ ክፍል አበቦቻችንንም ድካማቸውን ከንቱ አታድርግባቸው፤ የለፉበትን ውጤት አሳምረህ በመልካም የምስራች ልባቸውን አስደስት። ለቀጣዩ የትምህርት ህይወታቸውም በርካታ ስኬቶችንና ብሩህ ተስፋን ስጣቸው። ​አሚን ያ ረበል ዓለሚን! 🤲 📚 ​አላህ ልጆቻችንን ለታላቅ ስኬት ያብቃቸው! ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

#ጥቆማ #USA የ2027-2028 የ " ሁበርት ኤች. ሃምፍሬይ " ፕሮግራም ክፍት መደረጉን በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ አሳውቋል። ምዝገባም ተጀምሯል። የአሜሪካ መንግሥት ሙሉ ውጪውን የሚሸፍነው
+2
#ጥቆማ #USA የ2027-2028 የ " ሁበርት ኤች. ሃምፍሬይ " ፕሮግራም ክፍት መደረጉን በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ አሳውቋል። ምዝገባም ተጀምሯል። የአሜሪካ መንግሥት ሙሉ ውጪውን የሚሸፍነው ይኸው ፕሮግራም በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችን (እድሜያቸው ከ32 እስከ 45) የሚመለከት ሲሆን አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ለአንድ የአካዳሚክ አመት ብቃትን ለማሳደግ እና ለልምድ ልውውጥ እድል የሚሰጥ ነው። ይህ ፕሮግራም የዲግሪ ፕሮግራም ሳይሆን፣ ባለሙያዎች ብቃታቸውን የሚያሳድጉበትና ከአሜሪካውያን አቻዎቻቸው ጋር ጠንካራ የሥራ ትስስር የሚፈጥሩበት ልዩ መድረክ ነው። የ2027-2028 መስኮች ምን ምን ናቸው ? ➡️ ኮሙኒኬሽን እና ጋዜጠኝነት (Communications and Journalism) ➡️ ሕግ እና መልካም አስተዳደር (Law and Governance) ➡️ የተፈጥሮ ሀብት ፖሊሲ (Natural Resources Policy) ➡️ የሕዝብ እና ኢኮኖሚ ፖሊሲ (Public and Economic Policy) ➡️ የሕዝብ ጤና ፖሊሲና አስተዳደር (Public Health Policy and Management) ➡️ የቴክኖሎጂ ፖሊሲና አስተዳደር (Technology Policy and Management) መመዘኛዎቹ ምንድናቸው ? አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። 1. በመንግሥታዊም ሆነ በግል ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ፣ የአመራር ብቃት ያላቸውና ለሕዝብ አገልግሎት ቁርጠኝነታቸውን ያሳዩ ባለሙያዎች። 2. ዕድሜያቸው ከ32 እስከ 45 ዓመት የሆኑ። 3. የዩኒቨርሲቲ መጀመሪያ ዲግሪ (የ4 ዓመት የባችለር ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ) ያላቸው። 4. አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ ከተጠናቀቁ በኋላ በተሰማሩበት የሙያ መስክ ቢያንስ የ5 ዓመት የሙሉ ጊዜ ፕሮፌሽናል የሥራ ልምድ ያላቸው፤ እንዲሁም በሙያ ዘርፋቸው ውስጥ ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ፍላጎት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል። 5. ለፕሮግራሙ ቆይታ ጊዜ ከሚሰሩበት ተቋም የሥራ ፈቃድ ማግኘታቸውን የሚያሳይ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ መቻል አለባቸው። 6. በሥራ ገበታቸው ላይ የአመራር ወይም የፖሊሲ ኃላፊነት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤ ይህም የዩኒቨርሲቲ መምህራንን እና እንግሊዘኛን እንደ ውጭ ቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራንን (የኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉትን) ያጠቃልላል። 7. በጽሑፍም ሆነ በንግግር እንግሊዘኛ ቋንቋ አቀላጥፈው መፃፍም መናገርም የሚችሉ እና ከተመረጡ ለTOEFL ፈተና ለመቀመጥ ፈቃደኛ የሆኑ (ተመጣጣኝ ውጤት 72/100/60)። 8. የኢትዮጵያ ዜጋ የሆኑ ወይም በሀገሪቱ የተሰጠ ሕጋዊ ፓስፖርት ያላቸው ቋሚ ነዋሪዎች። 9. ትምህርቱን እንዳጠናቀቁ ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት ሀገርንና ማኅበረሰብን ለመጥቀም ቢያንስ ለሁለት ዓመታት ወደ ሀገር ተመልሶ ለማገልገል ቁርጠኝነት ያላቸው። 10. በአሜሪካ ሀገር ውስጥ በሚገኝ ድኅረ-ምረቃ ለአንድ የትምህርት ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የተማሩ ባለሙያዎች ለዚህ ፕሮግራም ብቁ አይደሉም (ማመልከት አይችሉም)። 11. ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ በአሜሪካ መንግሥት በሚደገፉ ማናቸውም ፕሮግራሞች ላይ የተሳተፉ አመልካቾች ማመልከት አይችሉም። ለማመልከት የሚያስፈልጉ ሰነዶች ምን ምንድናቸው ? ምዝገባው ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት (ኦንላይን) ብቻ የሚከናወን ሲሆን የሚከተሉት ሰነዶች ያስፈልጋሉ። 1. CV ፦ የአመልካቹን አጠቃላይ የሥራ ልምድ እና የሙያ ብቃትን በዝርዝር የሚያሳይ ማብራሪያ። 2. የፕሮግራም ዕቅድ ፦ አመልካቾች በዚህ ፕሮግራም ላይ በመሳተፍ ምን ለማሳካት እንደሚያስቡና ወደፊት ምን ለመሥራት እንዳቀዱ የሚያሳይ ዝርዝር መርሐ-ግብር። 3. የተሟሉ የጽሑፍ መልሶች ፦ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሙሉ የተሟላ ምላሽ መስጠት፤ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚዘጋጁት እነዚህ መልሶች (Essay) የቀረቡትን ዋና ዋና ነጥቦች በጥልቀትና በዝርዝር የዳሰሱ መሆን ይኖርባቸዋል። 4. የድጋፍ ደብዳቤ ፦ የሁለት ሰዎች የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልጋል። አንዱ አሁን ከሚሰሩበት ተቋም ኃላፊ/አሰሪ መሆን አለበት። 5. የትምህርት ማስረጃ ፦ ለመጀመሪያ ዲግሪ (Bachelor's) የተወሰዱ ኮርሶችን እና የተገኙ ውጤቶችን የሚያሳይ በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ የውጤት መግለጫ መያያዝ አለበት። 👉 የማመልከቻ ጊዜ፦  እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም (July 19, 2026) ድረስ ነው። 👉 የማመልከቻ ድረ-ገጽ፦ https://apply.iie.org/huberthhumphrey 👉 ለተጨማሪ መረጃ ፦ et.usembassy.gov/announcements/ ስታመለክቱ ግልጽ ያልሆነላችሁ ጥያቄ ካለ በ PASaddisexchanges@state.gov ላይ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲን ማነጋገር ይቻላል። ማሳስቢያ ፦ ማመልከት የሚቻለው በኦንላይን ብቻ ሲሆን ማመልከቻ ይዛችሁ ወደ አሜሪካ ኤምባሲ እንዳትሄዱ። ❌ በፕሮግራሙ ወቅት ማንኛውም የቤተሰብ አባል አብሮ መሄድ አይችልም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ