የፍቅር ግጥሞች(ፍ.መ) love poem/yefikir gitmoch le FM
Open in Telegram
🕊🌿🍃🌹🍃..............✍️ 🌱ሰዎችን በልቤ ማስቀመጥ ከተውኩ ቆየሁ በመዳፌ ነው የማስቀምጣቸው በእምነት የተደገፍኳቸው ሰዎች ጥለውኝ በሄዱ ቁጥር ስወድቅ የሚሰበረው ያመነው ልቤ ነው። ከዚህ ሁሉ ይልቅ በመዳፌ ይዤ መሄድ ሲፈልጉ መውደቅ አያስፈልግም መልቀቅ ብቻ ነው ። ያኔ መሄድ ለነሱ ቀላል እንደሆነ ሁሉ ለእኔም መልቀቅ ይቀለኛል
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
1 251
Subscribers
No data24 hours
+17 days
+2430 days
Data loading in progress...
Similar Channels
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
September '26
September '26
+22
in 0 channels
August '26
+60
in 0 channels
Get PRO
July '26
+65
in 0 channels
Get PRO
June '26
+54
in 0 channels
Get PRO
May '26
+46
in 0 channels
Get PRO
April '26
+43
in 0 channels
Get PRO
March '26
+31
in 0 channels
Get PRO
February '26
+41
in 0 channels
Get PRO
January '26
+39
in 0 channels
Get PRO
December '25
+34
in 0 channels
Get PRO
November '25
+26
in 0 channels
Get PRO
October '25
+195
in 1 channels
Get PRO
September '250
in 1 channels
Get PRO
August '250
in 1 channels
Get PRO
July '250
in 0 channels
Get PRO
June '250
in 0 channels
Get PRO
May '250
in 0 channels
Get PRO
April '250
in 2 channels
Get PRO
March '250
in 0 channels
Get PRO
February '250
in 0 channels
Get PRO
January '250
in 0 channels
Get PRO
December '24
+13
in 0 channels
Get PRO
November '24
+37
in 0 channels
Get PRO
October '24
+56
in 0 channels
Get PRO
September '24
+21
in 0 channels
Get PRO
August '24
+33
in 0 channels
Get PRO
July '24
+8
in 0 channels
Get PRO
June '24
+13
in 0 channels
Get PRO
May '24
+25
in 0 channels
Get PRO
April '24
+85
in 0 channels
Get PRO
March '240
in 0 channels
Get PRO
February '24
+180
in 1 channels
Get PRO
January '240
in 0 channels
Get PRO
December '230
in 0 channels
Get PRO
November '230
in 0 channels
Get PRO
October '230
in 0 channels
Get PRO
September '230
in 0 channels
Get PRO
August '230
in 0 channels
Get PRO
July '230
in 0 channels
Get PRO
June '230
in 0 channels
Get PRO
May '230
in 0 channels
Get PRO
April '230
in 0 channels
Get PRO
March '230
in 0 channels
Get PRO
February '230
in 0 channels
Get PRO
January '230
in 0 channels
Get PRO
December '22
+32
in 0 channels
Get PRO
November '22
+9
in 0 channels
Get PRO
October '220
in 0 channels
Get PRO
September '22
+16
in 0 channels
Get PRO
August '22
+12
in 0 channels
Get PRO
July '220
in 0 channels
Get PRO
June '22
+13
in 0 channels
Get PRO
May '22
+34
in 0 channels
Get PRO
April '22
+26
in 0 channels
Get PRO
March '22
+40
in 0 channels
Get PRO
February '22
+23
in 0 channels
Get PRO
January '22
+46
in 0 channels
Get PRO
December '21
+26
in 0 channels
Get PRO
November '21
+32
in 0 channels
Get PRO
October '21
+58
in 0 channels
Get PRO
September '21
+33
in 0 channels
Get PRO
August '21
+44
in 0 channels
Get PRO
July '21
+57
in 0 channels
Get PRO
June '21
+49
in 0 channels
Get PRO
May '21
+394
in 0 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 11 September | 0 | |||
| 10 September | +1 | |||
| 09 September | +1 | |||
| 08 September | +1 | |||
| 07 September | +2 | |||
| 06 September | 0 | |||
| 05 September | +2 | |||
| 04 September | +3 | |||
| 03 September | +2 | |||
| 02 September | +4 | |||
| 01 September | +6 |
Channel Posts
✍️ተባብለን_ባይ_ባይ💔
ደህና ሁን ደህና ሁኚ ተባብለን ነበር
ያለቀ ሲመስለን የጀመርነው ፍቅር
አሁን ምን አመጣው የትዝታን ፈረስ
ከአንቺ ከእኔ እያለ ናፍቆት ሊያመላልስ
ሰው አላለያየን በፍቅራችን ገብቶ
ሰበቡ የእኛው ነው የገመድነው ላልቶ
አሁን ከረፈደ ከሌላ ተላምደን
ትዝታችን መጥቶ ምን ፍጠሩ ሚለን?
አንቺም የሌላ ነሽ እኔም የሌላ ሰው
ትዝታሽ ከእኔ ቤት ምን አመላለሰው
አርፎ መኖር እንጂ ችሎ እንደነገሩ
በክራሩ ቅኝት እያንጎራጎሩ!!!
እህል ውሃ እንዲህ ነው አገናኝቶ ነጣይ
ሳንጀምር ቋጨነው ተባብለን ባይ💔😥
በእውነተኛ ገጠመኝ የተፃፈ ᶠ💔ᶠᵒʳ𝗙.𝗠💔ᶠʳᵒᵐ𝗘.𝗧✍️
| 2 | ውበት ቃል ቢኖረው 💚
ውበት ቃል ቢኖረው አውቃለው ልክሽ ነው
ማስተዋል ስም ኖሮት ቢጠራም ባንቺው ነው
ቁመትም ቢለካ ውበትስ ቢመዘን
እንድ አንቺ ጋር ሚደርስ አላቅም በዘመን❤️ | 664 |
| 3 | ሀሁ
ፊደል ላስቆጥርሽ እጅሽን ደግፌ በምቾት ታቅፌ
ፊደል ላስቆጥርሽ ባንቺነትሽ ፍቅር በመውደድ ፈዝዤ ደንዝዤ
አቡጊዳ ልበል መቁጠሪያውን ይዤ
አይንሽን እያየው በፍቅርሽ ፈዝዤ
ባንቺነትሽ ግርማ እኔነቴን ትቼ
ፊደል ላስቆጥርሽ መቁጠሪያውን ይዤ
ከሀ ይጀምራል የሁሉም መነሻ
ምነው አንቺን ለኔ ባረገሽ መሸሻ
የመጀመሪያዬ የእስትንፋሴ ዋሻ
ባደረገሽ አንቺን ለኔ መነሻም መድረሻ
ያኔ የኔታ የፊደሉ ጌታ
ፊደል ሲያስቆጥሩን ቁጭ አርገው በተርታ
እንሰማቸው ነበር በዝምታ ቃታ
የድምጣቸው ቃና የፊደሉ ሞገስ
ማህሌት ሚመስል ቅዳሴ ሚሰለስ
ጥዑም ነው ዜማቸው እጅግ የሚማርክ
ለቅዳሴ ቤቱ ይፈለጋል በሰርክ
ማህሌት ሲሰማ ሰአታቱ ሲቀርብ
ይሰማን ነበረ ድምጣቸው ከርቀት
የሚገርመኝ ነገር በሀ አስመስዬ ያንቺን ስም መጥራቴ
በሁ አስመስዬ ስልሽ ነው ህይወቴ
ምን ተሰማሽ ታድያ ንገሪኝ በሞቴ
ልቤም ከጅሎሻል አንድ በይኝ እቴ።
L o v e 😍 | 473 |
| 4 | በቃኝ
እሳት ሆኜ ስነድ ፣ አንቺ ቆፈን ወርሶች
ሎሚ ብወረውር ፣ እንቧይ ሆኖ ደርሶሽ
ዝምድና ሳያንሰን ፣ እየቆየሽ ባዳ
መላመድ ሳይጎድለን ፣እያደርሽ እንግዳ፤
እንግዲህ ደህና ሁኝ!
ምኞቴም በረደ ፣ ቁጣዬም አለፈ
ከእድሉ ጋር ታግሎ ፣ ማነው ያሸነፈ።
✍️✍️በዕውቀት ሥዩም | 453 |
| 5 | #ምንነት
አብረን በዋልንበት - በሄድንበት ሁሉ
ካንቺ ጋራ ያዩኝ - ያልገባቸው ውሉ
ምኗ ነው እያሉ - ሰው ይጠይቃሉ።
እናምልሽ ውዴ
ምኗ ነው እያሉ - ለሚጠራጠሩ
ስለኔ ምንነት - አውቀው እንዲኖሩ
ከቻልሽ አስረጃቸው - ገልፀሽ በአጭሩ።
እሱ ማለት ለኔ - ገና ከጅምሩ
በሰም የታጠረ - ቅኔ ነው ሚስጥሩ።
ቅኔ ማለት ደግሞ - የማይታይ ጌጡ
ተዘርፎ የማያልቅ - ወርቅ አለ በውስጡ
ለሱ ግን
ከሀብቱ የሚልቅ ሌላ በዚች አለም
ደስታ የሚፈጥር ምንም ይሁን ምንም
ከኔ ሳቅ የሚበልጥ አንዳች ነገር የለም።
መሳቅ ማለት ደስታ - ደስታ ማለት ደሞ
በልቡ ማሳ ላይ - የተዘራው ቀድሞ
የመንፈሱ ችግኝ - ስጋ ያበቀለው
የሚቀጥፈው መውደድ - ጊዜ ያበሰለው
ጣፍጦት የሚበላው የነፍሱ ፍሬ ነው።
ፍሬው ባስተሳሰብ - ዳግም የሚዘራ
የዘሩ ቅርንጫፍ - ከዕምነት የተጋራ
ፍቅር ያዳበረው - ወዳጅ የሚያፈራ
ጥሩ ጓደኛነት - በሚያጠላው ጥላ
እኔ ያስጠለለ - የሆነኝ ከለላ
አፍቅሮኝ የሚኖር - የማይመኝ ሌላ
ታማኝ ወዳጄ ነው - የዕምነቴ ኬላ።
ብለሽ አስረጃቸው
ስለኔ ምንነት - ማወቅ ተስኗቸው
ምኗ ነው ለሚሉ - ፍቅር ላልገባቸው። | 602 |
| 6 | ጡር አለው
ጠብቄው ነበረ ብዕርሽ'ን በጨረር
ባትልኪው ቀርቶብኝ አላውቅ ያንቺን ነገር
እኔ እንዳልከትብልሽ አንተ እንዳፅፍ ብለሽ
መገናኛችንን አጠፋሽ ቆራርጠሽ
ወይ አፅፊ ነገር አልፃፍኩልሽ ከቶ
ምን ሁኚ አላውቅም አንቺን አስመልክቶ
በዘመን አመጣሽ ያየር ቴክኖሎጂ
አልጠቀም ብትይ ሰው ላኩ አማላጂ
እሱንም ብትንቂ አሻፍረኝ ብለሽ
ብዙ ደጅ ፀናው ልቤንም አሳዘንሽ
ዳሩ ድሮውንም ፍቅር የለሽ ነበር
መፅናኛ አረግሽኝ ከድሬሽ ሲሰበር
ግና እኮ አለሜ የፍቅር ጡር ይድረስ
ያንቺም ልብ ተነክቶ ሞልቶ በዓይንሽ ይፍሰስ
ያኔ ይገባሻል ፍቅር ጡር ነገሩ
ያለ' ልብ ተሰርቀው ያለልብ ሲቀሩ
እናም አልፃፍሽልኝም። | 617 |
| 7 | ➲ፍቅር እና ጉንፋን
● ● ● ● ● ●
ከለታት አንድ ቀን ባንክ ቤት አየኋት
በጄ የያዝኩትን ብርቱካን🍊 ሰጠኋት
ሙሉ ማንነቴን ልቤን❤️ አስረከብኳት
••●••
ና ካለች ሔዳለሁ ካለችበት ቦታ
ሰዓት አይገድበኝ ቀንም ሆነ ማታ
••●••
ሰኞለት ፒያሳ እሮብ መካኒሳ
ሀሙስ ደግሞ ቦሌ አርብ ቀን ጉለሌ
እሁድና ቅዳሜ ከሷ ጋር ባብነት
አብረን እንውላለን በፍቅር ባንድነት
ሚስቴ ስላት ባሌ
ትለኛለች ሁሌ
አሁን ሁሉም ቀረ... ታሪክ ተቀየረ.....
••●••
የኔ ውድ ፍቅሬ ብላ እንዳልጠራችኝ
ዛሬ ሁሉም ቀርቶ ለአይኗ ጠላችኝ
ተመስገን ማለት ኑሮ አስተምሮኛል
ትናንት ፍቅር ይዞኝ ዛሬ ተሽሎኛል
የዘንድሮ ፍቅር ጉንፋን ሆኖብኛል
••●••
ፍቅር እንዲ ተራ በሆነባት አለም
አብሮ መዝለቅ እንጂ ማፍቀር ብርቅ አይደለም | 489 |
| 8 | ~እሽሩሩ ልቤ~
////////////////
ተው አታንገላታኝ ቀስ አድርገህ ያዘኝ
ጠና በል እባክህ ሞተህ አታሙተኝ
እዳህን ተሸከም እንደፈረደብህ
እኔን ለቀቅ አርገኝ እስኪ በፈጠረህ
ልቤ ተለመነኝ ደግሞ ልለምንህ
አልችልም እሮሮ የሲቃ ጋጋታ
ያኔ ተወኝ ስልህ የጋለብክ ለታ
ማንንም ሳትሰማ ጆሮህ ተጠምሮ
ዛሬ ለኔ ም ተርፏል ዳፋህ ተስፈናጥሮ
ግዙፍ እያዋረድክ በጠባብ ጉሮሮ
ደስታ እየተራጨ ሲነገር ሮ ሮ
ያለወግ ያለአባት እልቆ የለሽ መውደድ
ከአንጀቱ ስር ቋጥሮ
ያለ ልክ አፍቅሮ
ይነተርከኛል
ሰላም ይነሳኛል ያብሰከስከኛል
ያለ ልጓም ጋልቦ ትቶኝ ይሰደዳል
የሩቅ ህልም አልሞ
ተስፋ ተሸክሞ
ከአድማሱ ባሻገር ከተራራው ማዶ
ጠይም ዘለግ ያለ ልቤ ቆንጆ ወዶ
ዘመናት አለፉ በውል ሳይቀመጥ እንዳው
ተንጎራዶ------
አትረበሽ ሆደ
ብሶህ አታስብሰኝ
ተዳፍኖ የኖረ ረሀብ ጥማቴን ክፉኛ
አታስታውሰኝ
ረጋ በልልኝ የጠፈፈ ቁስሌን
አታስመርቅዝብኝ
እሽሩሩ ልቤ እባክህ ተለመን እስኪ ልለምንህ
ግደለም ጠና በል ባብተህ አታባባኝ
-------- ሞቸ እንዳልሞትብህ። | 628 |
| 9 | በማይካ ተወግቶ ታሞ ይድናል ሰው
እንዴት በውቅራት በጥርስ ይሞታል ሰው
ቀን በካቻማሌ እንግዳ ሰው መጥቶ
ዋጃ ላይ ቀረ አሉ ዘቦዋ አንቺን አይቶ
የፍቅር መዳኒት የለም ወይ ባገሩ
ዘብናየ እያለ ሲሸበር መንደሩ
ስንት እጅ ሰጠላት ከነ ምንሽሩ
❤️❤️❤️ወሎ ደሴ | 643 |
| 10 | ትዝታ❤️🔥
ማውራት አቆምን እንጂ
መናፈቁን መች ተውነው!!🤍
🥀🤐🤐🤐😓 | 558 |
| 11 | ከሸህ ሁሴን አገር ከሚያፈራው ሸጋ
የደግነት ውሀ እየጠጣች አድጋ
የፍቅር ጥምቆራጭ የውበት አውድማ
ልብን ታጠፋለች ስትሄድ አግድማ። | 687 |
| 12 | አበባና ውበት
የአበባ ውበቱ
ሳቢ ደም ግባቱ
የሚታይ ድምቀቱ
የማር መስሪያነቱ
እሰከሚከስም ነው
ሁሉም የሚከበው
ፍቅረኞች ለፍቅር
አልቃሾች ለቀብር
ንቦች ደግማ ለማር
ለአበባ የሚዘመር
የሚንከባከቡት
አለውህ የሚሉት
ውበቱ እስካለ ነው
ከዚያ ወዳቂ ነው። | 577 |
| 13 | ቅበጭ_እንደ_ልብሽ
በጫንቃዬ ለዋልሽ ሸክሙ ላልከበደኝ፣
ቅብጠትሽ የመጨ እኔን ከተመቸኝ፣
ምን አርጊ ይሉሻል? ቢሉሽም ተያቸው፣
በእራሴ ትክሻ ምን ቁርጥ አርጓቸው?
ቅበጭ እንደ ልብሽ ደስ ይበልሽ በርቺ፣
ተከፍተሽ ሳይሽ ነው የሚጨንቀኝ ላንቺ፣
ምን ይሉኝ አትበይ ካሉሽም ተያቸው፣
እነርሱን ካልነካሽ ምን ጥልቅ አርጓቸው?
እንኳንስ ጫንቃዬን ልቤንም ወስደሻል፣
ገና እጨምራለሁ ላንቺ እኮ ያንስሻል፣
ብቻ አደራ ውዴ ከሌላ አትቅበጭ፣
በእኔ ሰውነት ላይ ሰክነሽ ተቀመጭ። | 805 |
| 14 | ፨፨፨፨፨ ወሎ ፨፨፨፨፨፧
ወሎ ወሎ እያልኩኝ ደጋጥሜ ልጥራሽ
ጠበው ባያጠቡሽ ወትሮማ ሰፊ ነሽ
ተነግሮ ያማያልቅ ብዙ ታሪክ አለሽ
ስላንች ስወራ የሚያንገበግበው
ጠበሀል ሰፍተሀል ብሎ እሚያላዝነው
ሲያሻው ጠበብክ ይበል ሲፈልግ ጠቢብ ነው
ያውራ እንደፈለገ ምቀኛሽ ብዙ ነው
እኔ ግን ስላንች ዘላለም ባወራው
ብፅፈው አያልቅም ታሪክሽ ብዙ ነው
ቅኝትሽ አያልቅም ብመዘው ብመዘው
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እናት አለም ወሎ እምየ ልበልሽ
የሓይቅ እስጢፋኖስ መገኛ ምድር ነሽ
የእዉቀትና ጥብብ መፍለቂያ ቦታ ናሺ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ብዙ ታሪክ አለ ወሎየ ሲጠራ
እምነትና እዉቀትን በጋራ የሰራ
የጥንቱ የጠዋቱ ሀገርን የሰራ
እዉቀት ያካፈለ ቀድሞ የታተረ
ዕውቀት ያፈለቀ ጥበብ ያዳበረ
ከሌሎች ህዝቦች ጋር በጋራ የኖረ
ቅኔ ሰምና ወርቅ ዜማን ያስተማረ
የአምባሰል ትዝታ አንችሆየ ባቲ
የ4ቱ ቅኝቶች የጥበብ ተራኪ
ዜማና ቅላፄ የጥበብ ባለቤት
የሚነገርበት እዉነተኛ ትንቢት
ሸህ ሁሴን ጅብሪልን ያበቀለ መሬት
ቢላልን ያፈራ የሐበሻ ኩራት
የመንዙማ ዜማ ሽህወች የሞሉበት
የኪታብ ማዕከል የተከማቸበት
የቅዱስ መፀሀፍ ዉዳሴ ባልተቤት
የዕምነትና አማኞች ነፍሳዊ ባለቤት
ለስጋው የማይኖር ለነብሱ የሚሞት
እምነትና አማኞች የተከማቹበት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ብሄድ ወደ ወሎ ወደ ከማራ ሳይንት
ቤተ እምነት ስላሴ ጊወርጊስ ያለበት
ብዙ ቤተ - እምነቶች የተከማቹበት
አሁን የት ይገኛል እንደ ከአማራ ሳይንት
የሚታወቅበት የመንፈስ ውዳሴ
በፍቅሯ ከተማ ይታደስ መንፈሴ
አይወድም አትንካው ጀግና ነው ሳይነቴ
ልሙትልህ ብሎ ምሎ በስላሴ
በእምነቱ ከማለ አይፈራም ሳይንቴ
ጀግና ነው ወሎየው አማራ ሳይንቴ
እኔም ወሎየ ነኝ ተቀብሯል እትብቴ
ጀግና ነህ አለሜ ኑርልኝ ኩራቴ
በመቅደላ ተንታ በሚካኤል አምባዉ
ሸህ ሁሴን ጅብሪልን ያፈራ መሬት ነው
ቦረና ወግዲ ከላላን ስጠራው
የቦረናው ጌታ ትውልድ ቦታ ነው
በአመት የሚዘየር የጸሎት ቦታ ነው
፨፨፨፨ እረ ስንቱን ልጥራው ፨፨፨
ተወርቶ የማያልቅ ሌላም ሚስጥር አለው
ከጥንት እስከ ዛሬ የታሪክ ምድር ነው
የአማረኛ ቋንቋ ፊደል ባለቤት ነው
የዛሬ ቅኝቴን እዚህ ላይ ላቁመው
ፊደልና ቋንቋን ጀምሬ እንዳልተወው
ቦረና ወግድ ሳይንት ላድር ነው | 1 035 |
| 15 | ሩቅ ያለውን ጠላትህን ሳይሆን መፍራት ያለብህ ፤ ድክምትህን የነገርከውን እና ወዳጄ የምትለውን ሰው በደንብ ፍራው ።
ምክንያቱም ድክመትህን የሚያውቅ ሰው አንተ እንዴት መጣል ያለበት ያውቃል ፤ ስለዚህ ድክመታችሁን ለማንም አትናገሩ ፤ ወዳጄም ነው ብለህ አምነው ስትናገር መቼ ጉድጓድ ቆፍሮ እንደሚጥልህ አታውቁም ። | 1 489 |
| 16 | ሁላችንም ያልተነበቡ ገፆች አሉን..ማንም ማያውቃቸው ከህይወት መፅሐፋችን ጥራዝ ስር የተሸሸጉ። በደብዛዛ ቀለም የተቀለሙ ፤ እንዳይገኙ አርገን አርቀን የሸሸግናለቸው ለማንም ለምንም
የማንገልጣቸው ስውር ገፆች አሉን።
…💌! | 1 502 |
| 17 | የፍቅራችን ቅኔ
በፍቅር ሰሌዳ በመዋደድ ቅኔ፣
የኔ ልብ ባንቺ ያንቺ ልብ በኔ።
የነፍስያችን ወግ ካሳባችን ሰርፆ፣
በልባችን ሀዉልት ፍቅራችን ተቀርፆ።
ደምሽና ደሜ ፍፁም ተዋህዶ፣
ባንደበት ሊገለፅ በቃላት ተጋምዶ።
ቀና ብለሽ እያት ዉቢቷን ጨረቃ፣
የብርሃን ዝናር በወገቧ ታጥቃ።
ተስፋ ልታድል ጽልመት ለጋረደዉ፣
በትዝታ ጋሪ ሞሽራ ልትሸኘዉ።
ያቺ ዉብ ጨረቃ ምስክር ትሁንሽ፣
በሷ ብርሃን የኔ መልክ ይታሽ።
ከዋክብትን ስታይ ከደጃፉ ቆመሽ፣
በአንቺ ብርሃን ድምቀቴ ይታወስሽ።
የኔና አንቺ ፍቅር በወርቅ ይመሰላል፣
ካፈር ተደባልቆ ከሳት ይፈተናል።
ከጭቃዉ ይጠራል ነበልባሉን አልፎ፣
ከነፍስ ተራቆ ከህሊና ገዝፎ።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️ | 1 714 |
| 18 | አብዶ_ከነፈልሽ_ተብሎ_ሊወራ_Hayliye_Tadese_Yabede_Manew_ሃይልዬ_ታደሰ_ያበደ_ማነው_.mp3 | 1 675 |
| 19 | አብዶ ከነፈልሽ☺️.mp3 | 1 725 |
| 20 | 💔የማያሽር...ጠባሳ💔
፨።።።💘💘💘።።።፨
ቀኑም አይመሽልኝ ለሊቱም አይነጋ
ልቤ እየተቀጣ በሀሳብ አለንጋ
ከልብ ውስጥ የማይጠፋ ከቶ ማይረሳ
ህመሙ የማይድን የማይሽር ጠባሳ
ቁስሉ የሚቆጠቁጥ የህሊናን ዕዳ
አሸክማኝ ሄደች በሰውፊት አዋርዳ
ሀዘን ድንኳ ጥሎ ጎጆውን ቀልሶ
ልቤውስጥ ይኖራል ጎኔን ተንተርሶ
ልቤ ፍቅርን ብሎ ለፍቅር ባደረ
ሀዘን ቤቴን ወርሶት ቅስሜ ተሰበረ
.
.
.
ያላረኩት የለም ልቤን ለማሳመን
በደልሽን ችዬ ካንቺ ጋር ለመሆን
ግን አንቺ አልገባሽም ባንቺ መጎዳቴ
በብርሀን ጭለማ መሆኗን ህይወቴ።።።።
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ | 2 079 |
